የቀጠናው ተመልካች
Відкрити в Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
4 346
Підписники
+624 години
+487 днів
-3030 днів
Архів дописів
4 346
🇮🇷⚡️🇺🇸🇯🇴 🇮🇱 ዮርዳኖስ እስራኤልን የምትከላከል ቁልፍ፣ የመጨረሻዋ እና በጣም አስፈላጊው ንብርብር ጋሻ ናት። በዮርዳኖስ ላይ እየጨመረ የመጣው የኢራን የቀጥታ ምቶች መጠን፣ ከዚህ በፊት ኢራን በኩዌት፣ በባህሬን፣ በኤሜሬት እና በኳታር የደመሰሰቻቸው ራዳሮች እና ሌሎች የአሜሪካ መሣሪያዎች ቀጥተኛ ውጤት ነው። ኢራን እነዚህን ሀገራት፣ በዓመታት በቀላሉ የማይተኩትን የአየር መቃወሚያ ሚሳዬሎቻቸውን አሟጠው እንዲጠቀሙ አስገድዳቸዋለችም። በመሆኑም፣ ሰማዩ ለኢራን ሚሳዬሎች ክፍት ሆኗል።
በ20 ዓመታት ውስጥ CENTCOM የአረብ ሀገራትን እስራኤልን የሚከላከሉ የብረት ጉልላት አድርጓቸዋል፣ እና ኢራን አሁን በዘዴ እያፈረሰችው ያለችው ይሄንን ነው። 📎
4 346
—❗️🇮🇷/🇴🇲 "ማለፍ ክልክል ነው" የሚለውን የIRGC ትዕዛዝ በመጣስ ሊያልፉ የሞከሩ ሁለት መርከቦች፣ በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ ተመትተዋል - ኢራን ጦር።
4 346
🇺🇸🇮🇷⚡️ - ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረገውን ጦርነት ለማስፋት በማሰብ፣ አሜሪካ ተጨማሪ F-16 እና F-35 ተዋጊ ጄቶችን ከአውሮፓ ወደ መካከለኛው ምስራቅ፣ እንዲሁም ተጨማሪ የአየር ላይ ነዳጅ ሞይ ታንከሮችን ለመላክ አቅዳለች ሲል CNN ዘግቧል።
4 346
🇺🇸🇮🇷⚡️ - ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረገውን ጦርነት ለማስፋት በማሰብ፣ አሜሪካ ተጨማሪ F-16 እና F-35 ተዋጊ ጄቶችን ከአውሮፓ ወደ መካከለኛው ምስራቅ፣ እንዲሁም ተጨማሪ የአየር ላይ ነዳጅ ሞይ ታንከሮችን ለመላክ አቅዳለች ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል።
4 346
🇮🇷🇺🇸⚡️IRGC ትናንት ሌሊት በጎረቤት አረብ ሀገራት የአሜሪካ ዒላማዎች ላይ፣ የሰነዘራቸውን ጥቃቶች የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቋል።
ጥቃቱ በአሜሪካ ጦር ላይ፣ የሳተላይት ምስሎችን በመመልከት እና የአሜሪካ መረጃ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ፣ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
ተዋጊ ጀቶች፣ ሄሊኮፕተሮች፣ ሎጀስቲክ ሴንተሮች፣ ሚሳዬል ማስወንጨፊያዎች እና ራዳሮች የወደሙ ሲሆን፣ የበርካታ ወታደሮችንም ሕይወት የቀጠፈ ጥቃት ሆኗል።
በዚህ ቪዲዮ የሚገርመው፣ IRGC ለቪዲዮው ማጀቢያ በተለምዶ ሂዝቦላ ለራሱ የጥቃት ቪዲዮዎች የሚጠቀምበትን ሙዚቃን መጠቀሙ ነው። ሙዚቃዋ በጣም ፌመስ ሆናለች።
ይሄ የኢራን ሥራ ከኢትዮጵያ የደራሲዎች ማሕበር የኮፒ ራይት ጥያቄን አስነስቷል።
አሁን ስጋቱ ዩትዩብ የኢራንን መንግሥት ከፕላትፎርሙ ላይ እንዳያወርደው ነው። ይሄ ከሆነ፣ በዩትዩቡ የሚሠሩ፣ ወደ 31 የሚጠጉ ሠራተኞቹን የኢራን መንግሥት ከሥራ እንዳያባርራቸው ተሰግቷል።
ላይቭ ካላዘጋጁ፣ ምናልባት ጎ ፈንድ ሚ ካልከፈቱ፣ ቻናሉና ቤተሰቡ አደጋ ላይ ይወድቃል።
*-*-*
የመጀመሪያው የ IRGC ነው፣ ሁለተኛው የሂዝቦላ ነው።
4 346
🇮🇷🇺🇸⚡️ያልተቋረጡ የኢራን ጥቃቶች፣ የአሜሪካን ንብረቶችን፣ በኩዌት እና በባሕሬን፣ እየመቱ ናቸው።
ከዚህም በተጨማሪ፣ ከተወቻት ወራት በኋላ፣ ኢራን ኤሜሬትን እንደገና መታታለች።
አሜሪካ በበኩሏ፣ እንደ ኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር እኩለ-ሌሊት ገደማ በኢራን የጀመረችው ጥቃት፣ እስከ አሁን ሰዓት ድረስ አላባራም።
4 346
🇺🇸 በአሜሪካ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የዓለም ዋንጫ ማለቁ ይታወቃል። ስፔንም አሸንፋለች።
በስፔን (የቀድሞ ገዢ) ማሸነፍ መላው ላቲን አሜሪካ ደስተኛ ነው። ላቲኖች ለአርጀንቲና በታሪክ ብዙም ፍቅር የላቸውም። ዘረኛ፣ ከሀገሩ ሕዝብ ይልቅ ለፈረንጅ ባዕዳን የሚሰግዱ፣ እያሉ ያሟቸዋል።
አርጀንቲናዎች በበኩላቸው፣ ላቲኑ የሚጠላን እና የሚቀናብን፣ ሀብታም ስለሆንን፣ እኛን ፈልጎ ለሥራ ስለሚሰደድ፣ ሁልቀን ሥጋ ስለምንበላ፣ ሀገራችን በመሰልጠኑ ነው ይላሉ። ያም ሆኖ፣ መላው ላቲን በአርጀንቲና ሽንፈት ደስተኛ ነው።
በተቃራኒው፣ በአርጀንቲና መሸነፍ አይሁድ እስራኤል አዝኗል። አርጀንቲና የብዙ አይሁዶች መኖሪያ በመሆኗ፣ የአሁኑ መንግሥትዋ ግንባር ቀደም የእስራኤል ደጋፊ በመሆኑ፣ ፕሬዝዳንትዋ ዣቪየር ሜሊ አይሁድ በመሆኑ - ካቶሊክ ነኝ እያለ ቢፎግርም - እና ኔታንያሁን ጨምሮ የእስራኤል ባለሥልጣናት፣ አርጀንቲና እንድታሸንፍ ፍላጎታቸውን ሲያንፀባርቁ በመክረማቸው፣ የአርጀንቲና ሽንፈት ለአይሁድ እስራኤል ሐዘን ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ፣ በስፔን ማሸነፍ መላው አረብ ተደስቷል። ስፔን በምዕራቡ ዓለም አንደኛ ፀረ- እስራኤል መንግሥት ሀገር ሆናለች።
አውሮፓ በታሪክ ጠንካራ የፍልስጤም ደጋፊ እና የእስራኤል ነቃፊ ቢሆንም፣ ስፔን ያንን ታሪካዊ የአውሮፓ አቋም ሺ ጊዜ አብልጣ ከፍ አድርገዋለች። በሁሉም መንግሥታዊ እና ሕዝባዊ ፖሊሲዎቿ፣ ባሁኑ ጊዜ፣ ስፔን ከእስራኤል በተፃራሪ የቆመች ሆናለች። ስፔን የእስልምና ታሪኳም ሰፊ ነው። በዚህና በሌሎችም ተመሳሳይ ምክኒያቶች፣ የአረቡ ዓለም በስፔን ማሸነፍ ጮቤ ረግጧል።
ስፔን ለአሜሪካ የኢራን ጦርነት፣ አየሬንም፣ ውሃዬንም፣ አላስጠቅምም ማለቷ እና የአሜሪካን ጦር ከሀገሯ ማስወጣቷ፣ በብዙ ዓለም ዘንድም አስከብሯታል።
አውሮፓዊያን ደግሞ፣ ጎረቤታቸው ስፔን በማሸነፏ ደስተኛ ሆነዋል። ጥያቄ የለውም።
የሚገርመው፣ አውሮፓዊያን አንድ ወር በነበራቸው የአሜሪካ ቆይታ፣ በሁሉም ነገር፣ በሚበላውም፣ በሚጠጣውም፣ በቤቱም፣ በመንገዱም፣ በሳሩም በባሕሉም፣ በስርዓቱም፣ በሀብቱም … ብቻ በአጠቃላይ አሜሪካ፣ እንዲህም ያለ ሀገር አለ እንዴ? ብለው እጃቸውን አፋቸው ላይ ጭነው ሲገረሙ ነው የከረሙት። ዩቲዩብ እና ኢንስትግራም በእንዲህ ያሉ ቪዲዮዎች ተጨናንቀው ይገኛሉ። አዎ፣ እንደ አሜሪካ ዓይነት በረከቱ የተትረፈረፈለት ሀገር፣ እውነት ነው፣ በምድር ላይ የለም።
አሜሪካኖች በበኩላቸው፣ የዓለም ዋንጫ በመጠናቀቁ ደስተኛ ናቸው። አሁን "እፎይ፣ የማንወደውን ስፖርት እንደምንወደው መስለን መንቀሳቀሱ አበቃልን" እያሉ እየቀለዱ ናቸው። ብዙ ሚምስ፣ ብዙ ጽሑፍ እንዲህ በማለት እያወጡ ናቸው።
ከብዙ አንግል፣ የዘንድሮ የዓለም ዋንጫ የተዋጣለት ነበር።
4 346
🇮🇱🇺🇸⚡️🇮🇷 እስራኤል ወደ ጦርነቱ መልሳ ለመግባት በከፍተኛ ሁኔታ ቋምጣለች። አሜሪካ ብቻዋን ጦርነቱን ስላልቻለችውም፣ እስራኤል በሰበባ ሰበብ እንድትገባ እና ድብደባዋን እንድትጀምር እየወተወተቻት ይገኛል።
መግቢያ ሰበብ ቢያጡ፣ አሜሪካ እስራኤልን
ገና ለገና "አያቶላህ ሙጅተባ ጥቃት ሊሰነዝርብኝ እያሰበ ነው" በሚል ምክኒያት፣ ወደ ጦርነቱ እንድትገባ ለማስቻል ዳር ዳር እያሉ ናቸው።
ኢራን በገልፍ ሀገራት ላይ ጥቃቶቿን እንደቀጠለች ነው። በኩዌት፣ በባሕሬን እና በዮርዳኖስ ላይ፣ በአሁኑ ሰዓት ጥቃት ከፍታለች።
የኃይል ማመንጫዎች፣ የኤሌክትሪክ ሰብ ስቴሽኖች እና የውሃ ማጣሪያዎች በኩዌትና በባሕሬን፣ እንዲሁም የአየር ማረፊያዎች እና ጦር ሰፈሮች በዮርዳኖስ እየተጠቁ ናቸው።
አሜሪካም በበኩሏ፣ ከጠዋት ጀምሮ እስከ አሁን በዘለቀ ጥቃት፣ ኢራንን እየመታች ትገኛለች።
4 346
🇮🇷🇺🇸⚡️የኩዌት አየር ኃይል ሁለት የዩሮተዋጊ ታይፎን ጀቶች፣ በዓሊ አል ሠሊም አየር ማረፊያ የጠነከረ የአውሮፕላን መጠለያዎች ላይ ባነጣጠረ የኢራን ባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃት፣ ወድመዋል - Al Mannar
4 346
🇮🇷❌🇯🇴🇺🇸 - The New York Times እንደዘገበው፣ ኢራን በዮርዳኖስ ላይ ያደረገችው ጥቃት "ከፍተኛ ቁጥር" ያላቸው የዩኤች-60 ብላክ ሃውክ ሄሊኮፕተሮችን አበላሽቷል።
እንደ WSJ ዘገባ ከሆነ ደግሞ፣ ኢራን በዮርዳኖስ ላይ ባደረገችው ጥቃት፣ ሰው ሰራሽ እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ኢላማ ተደርጓል።
አንድ ምንጭ እንደገለጸው፣ ኢራን በሙዋፋክ ሳልቲ አየር ማረፊያ ላይ ባደረገችው ጥቃት፣ የዩኤስ አየር ኃይል (USAF) F-15E አድማ ንስር ወድሟል፣ ሌሎች በርካታ አውሮፕላኖች ተጎድተዋል።
4 346
🇺🇦⚡️🇷🇺 አዳዲስ ሚሳኤሎች ወደ ኪየቭ እያመሩ ነው፣ ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ባለስቲክ ሚሳኤሎች ወደ ኪየቭ ተተኩሰዋል። የሩስያ ጦር በአንድ ሰአት ውስጥ ወደ 50 የሚጠጉ ሚሳኤሎችን በዩክሬን ዋና ከተማ ጥሏል።
4 346
📢 🇸🇾 🇮🇷 የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቅርብ ቀናት ወዲህ ኢራን በባሕረ ሰላጤው ጎረቤቶቻቸው ላይ የምታደርገውን የታደሰ እና የተስፋፋ ጥቃት አውግዟል፣ ጥቃቱን "የሀገራትን ሉዓላዊነት በግልፅ መጣስ እና ለደህንነታቸው እና መረጋጋታቸው ቀጥተኛ ስጋት ነው" በማለትም ተናግሯል 📎
*-*-**
አሃ፣ ታዲያ ኢራን ዝም ብላ ብቻ ትመታ እንዴ? አትመልስ ምንም?
በነገራችን ላይ ከጥቂት ቀናት በፊት ማንም ብዙም ሲዘግበው ያልታየ ክስተት በሶሪያ ሆኗል። ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ በሶሪያ የአሜሪካ ጦርን ድብቅ ሰፈር ደብድባለች።
ብዙዎች ያልዘገቡት አሜሪካ በሶሪያ ውስጥ ጦር ሰፈር የላትም፣ ከየት የመጣ ነው በሚል ነው። ኢራን ግን፣ የደረሰችበት ነገር አለ፣ አሜሪካ በድብቅ፣ ይፋ ያላደረገችው፣ በሶሪያ ውስጥ የምትዘውራቸው፣ የድሮን ቤዞች፣ የደህንነት መ/ቤቶች እና command and control ጣቢያዎች እንዳሏት ደርሳበት አጥቅታታለች።
ምናልባት ሶሪያ ደንግጣ ነው ይሄን መግለጫ ያወጣችው።
4 346
የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድጋሚ "የኢስላማባድ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) መከበር እና ተጨማሪ መባባስ መወገድ እንዳለበት ተናገረ።"
በመካሄድ ላይ ባለው የአሜሪካ እና የኢራን ግጭት፣ ሁሉም ወገኖች ከማባባስ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና እቀባ እንዲያደርጉም አሳስቧል።
ከአንድ ቀን በፊት፣ ሐምሌ 17 ቀን፣ ፓኪስታን በሳውዲ አረቢያ ላይ የሚደርስ ማንኛውም ጥቃት በፓኪስታን ላይ እንደደረሰ አድርጋ እንደምትቆጠር ማስጠንቀቋ የሚታወስ ነው፣ እናም ለሪያድ ያላትን የፀጥታ ቃል በድጋሚ አረጋግጣለች።
4 346
🇺🇸🇮🇷 ኢራን ከአሜሪካ ጋር ከተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ለጊዜው በይፋ መውጣቷን አስታወቀች። ለውሳኔዋ፣ አሜሪካን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ አድርጋለች።
"በእያንዳንዱ የስምምነት ነጥብ ላይ ጥሰት ፈጽማለች" ብላታለች፣ አሜሪካንን ኢራን።
