ch
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

前往频道在 Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

显示更多
未指定国家未指定类别
4 316
订阅者
-824 小时
-117 天
-8230 天
帖子存档
🇪🇬 ግብጥ፣ የዓለማችን ትልቁን የመከላከያ ዋና መሥሪያ ቤት ይፋ አደረገች። 'ኦክታገን' በመባል የሚጠራ ሲሆን፣ ከአሜሪካ ፔንታገን ይበልጣል። ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ፣ በወታደራዊ ዩኒፎርም አሸብርቆ፣ በግብጥ እየተገነባ ባለው አዲሱ ዋና ከተማ የተሠራውን የጦሩን ስትራቴጂክ ዋና ማዘዣ ማእከልን፣ አስመርቋል።

🇺🇸⚡️ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ አያቶላውን የሚጠሉት መስሎኝ ነበር፣ የሚያለቅሱ ኢራናዊያንን በማየቴ ደንግጫለሁ Axios *-*-*- በዚህ ዓይነት፣ ፕሬዝዳንቱ ከደህንነት አባላቱ እና ከውጭ ፖሊሲ ቀራጮ
+9
🇺🇸⚡️ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ አያቶላውን የሚጠሉት መስሎኝ ነበር፣ የሚያለቅሱ ኢራናዊያንን በማየቴ ደንግጫለሁ Axios *-*-*- በዚህ ዓይነት፣ ፕሬዝዳንቱ ከደህንነት አባላቱ እና ከውጭ ፖሊሲ ቀራጮቹ፣ ምን ያህል የተንሻፈፈ እና የተሳሳተ ሪፖርት ሲጠቀጠቅ እንደነበር መገመት ይቻላል። በተለይ በእስራኤል በኩል ኢራንን በተመለከተ የሚሳልለት ስዕል ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው። አሜሪካዊያን የዋህ ናቸው፣ ውሸት አይወዱም። አይዋሹምም!!! ሰውም የሚዋሽ አይመስላቸውም። እያወራሁ ያለሁት በግለሰብ ደረጃ ነው። ወዳጅ መስለህ ከተጠጋሃቸው በኋላ የምትነግራቸውን ሁሉ ያምናሉ። ውሸትህን እንደነበር ያወቁ ቀን ግን፣ ከዚያ በኋላ ሰው አያደርጉህም። በመንግሥታቸው ደረጃም ቢሆን፣ ይሄ ሥነ- ምግባራቸው የተለመደ ነው።

🇸🇾🇺🇸⚡️ — የሶሪያው ፕሬዝዳንት እና የቀድሞው የአልቃኢዳ መሪ አሕመድ አል- ሻራ፡ አሜሪካ ሆይ፣ እንወድሻለን። እንደ ተምሳሌት የምናይሽ ውብ ሀገር ነሽ። እንኳን ደስ ያለሽ፣ ለልደት በዓልሽ
🇸🇾🇺🇸⚡️ — የሶሪያው ፕሬዝዳንት እና የቀድሞው የአልቃኢዳ መሪ አሕመድ አል- ሻራ፡ አሜሪካ ሆይ፣ እንወድሻለን። እንደ ተምሳሌት የምናይሽ ውብ ሀገር ነሽ። እንኳን ደስ ያለሽ፣ ለልደት በዓልሽ እንኳን በሰላም ያደረሰሽ። ከዚህም በላይ እድሜ ሰጥቶ ያቆይልን፣ ምንም ሳይጎልብሽ፣ ሙሉ እንደሆነ ቤትሽ፣ ለከርሞ ያድርስሽ እላለሁ፣ ሀገሬን እና ሕዝቤን ወክዬ።

🇷🇺⚡️በክራይሚያ የኃይል ማመንጫ ኢንዱስትሪ ላይ፣ በዩክሬን በተደረገ ያላባራ ተከታታይ ጥቃት ምክኒያት፣ ግዛቷ ሙሉ በሙሉ በጨለማ ተውጣለች።

🇷🇺⚡️🇺🇦 ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በባለፈው ምሽት በሩሲያ ጦር ድብደባ የወደመውን ሥፍራ በጎበኘበት ወቅት፣ እያለቀሰ፡ ሩሲያ እየተሸነፈች ነው ብሏል።
🇷🇺⚡️🇺🇦 ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በባለፈው ምሽት በሩሲያ ጦር ድብደባ የወደመውን ሥፍራ በጎበኘበት ወቅት፣ እያለቀሰ፡
ሩሲያ እየተሸነፈች ነው
ብሏል።

🇮🇱🇺🇸 ኔታንያሁ ለአሜሪካ፡
እንኳን ለ250ኛ የልደት በዓልሽ አደረሰሽ፣ እንወድሻለን … በተለያየ የዓለም ጫፍ ብንገኝም ሕልውናችን በአንድ የተጋመደ ነው።

🇺🇸🇮🇱 "ኔታንያሁ አለቃው ማን እንደሆነ አሳምሮ ያውቃል" ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ። ይህን ያለው በሚቀጥለው ሳምንት ኔታንያሁ ዋይት ሃውስን ለመጎብኘት አቅዷል የሚለው ዜና ከተሰማ በኋላ ነው
🇺🇸🇮🇱 "ኔታንያሁ አለቃው ማን እንደሆነ አሳምሮ ያውቃል" ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ። ይህን ያለው በሚቀጥለው ሳምንት ኔታንያሁ ዋይት ሃውስን ለመጎብኘት አቅዷል የሚለው ዜና ከተሰማ በኋላ ነው። ትራምፕ፣ "የጉብኝቱ ጥያቄ የመጣው ከኔታንያሁ ነው፣ ምናልባት ከአንካራው የሚቀጥለው ሳምንት የኔቶ ስብሰባ በኋላ እገናኘዋለሁ" ሲል ተናግሯል።

🇮🇷🇾🇪 የየመን ጦር ቃል አቀባይ፡ ዛሬ ጠዋት የሳዑዲ አውሮፕላኖች፣ ከ200 በላይ ዜጎችን የጫነውን የኢራን ሲቪል አውሮፕላን በሰነዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንዳያርፍ ለመከልከል፣ የየ
🇮🇷🇾🇪 የየመን ጦር ቃል አቀባይ፡
ዛሬ ጠዋት የሳዑዲ አውሮፕላኖች፣ ከ200 በላይ ዜጎችን የጫነውን የኢራን ሲቪል አውሮፕላን በሰነዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንዳያርፍ ለመከልከል፣ የየመንን የአየር ክልል ጥሰው ገብተው ነበር። ነገር ግን ሙከራው፣ በፈጣሪ ጸጋ እና በየመን ጦር ኃይሎች ይህን ትንኮሳ በመጋፈጥ የአየር መከላከያ ሚሳኤሎችን በመተኮሳቸው፣ የሳዑዲ ወራሪ ጀቶች ወደ መጡበት ለቅቀው ለመውጣት ተገድደዋል። ክብር ለኢራን ይሁንና፣ ከ11 ዓመታት የጽዮናዊያን ሳዑዲዎች የአየር ክልከላ በኋላ፣ ዛሬ ሰማያችን ለበረራዎች ክፍት ሊሆን ችሏል።

🇮🇷⚡️በኢራን በቀጠለው የታላቁ አያቶላህ የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ፣ "ትራምፕ ይገደል" መፈክሮች ከፍ ብለው ታይተዋል።
🇮🇷⚡️በኢራን በቀጠለው የታላቁ አያቶላህ የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ፣ "ትራምፕ ይገደል" መፈክሮች ከፍ ብለው ታይተዋል።

🇮🇷🇾🇪 ኢራን፣ በየመን አየር ክልል ላይ፣ ላለፉት 10 ዓመታት፣ በሳዑዲ እና በአሜሪካ ተጥሎ የነበረውን የበረራ ማዕቀብ በመጣስ፣ በምን ታመጣላችሁ ወኔ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲቪሊያን አይሮፕላን
🇮🇷🇾🇪 ኢራን፣ በየመን አየር ክልል ላይ፣ ላለፉት 10 ዓመታት፣ በሳዑዲ እና በአሜሪካ ተጥሎ የነበረውን የበረራ ማዕቀብ በመጣስ፣ በምን ታመጣላችሁ ወኔ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲቪሊያን አይሮፕላን በየመን አየር ማረፊያ አሳርፋለች። ሳዑዲ አረቢያ አይሮፕላኑ በየመን አየር ክልል እንደገባ ለማስቆም ሞክራ ነበር ተብሏል፣ ነገር ግን ከኢራን በተላለፈ ማስጠንቀቂያ፣ ምንም ከማድረግ ተቆጥባለች። ኢራን፣ በዛሬው ዕለት ማዕቀቡን በጥሳ አይሮፕላን ማሳረፏን ተከትሎ፣ ከእንግዲህ በመደበኛነት ወደ የመን በረራ እንደምትጀምር አስታውቃለች።

🇷🇺⚡️የሩሲያ ታዋቂ ወታደራዊ ተንታኝ፣ ዘርጉሊዮ፣ ፑቲን በኮንስታንቲኖቭካ ሙሉ በሙሉ መያዝ ስላበሰረው ታላቅ ድል፡ ዛሬ ኮንስታንቲኖቭካ የኛ ነው! የዩክሬን ጦር ኃይሎች የስላቪያንስክ-ክራማቶርስክ
🇷🇺⚡️የሩሲያ ታዋቂ ወታደራዊ ተንታኝ፣ ዘርጉሊዮ፣ ፑቲን በኮንስታንቲኖቭካ ሙሉ በሙሉ መያዝ ስላበሰረው ታላቅ ድል፡
ዛሬ ኮንስታንቲኖቭካ የኛ ነው! የዩክሬን ጦር ኃይሎች የስላቪያንስክ-ክራማቶርስክ መከላከያ ማዕከላቸው ትልቁ ምሽግ ተሰብሯል። ዩክሮናዚዎች ይህንን መስመር እንዴት እንዳጠናከሩ፣ ከተማውን በሲሚንቶ እና በብረት እንዴት እንዳጠሩት፣ በእሳት እና በኮንክሪት እንዴት እንደጠመጠሙት ማሰብ እንኳን አልፈልግም። አሁን ኮንስታንቲኖቭካ ነፃ ወጥቷል። አሁን ኮንስታንቲኖቭካ በወንድ ልጆቻችን ተሰብሯል። ጥሰቱ ተጥሷል። በሺዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ቢኖሩም፣ ምንም እንኳን ስታርሊንክ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቢኖሩም፣ ምንም እንኳን አውሮፓ ለዩክሮናዚዎች በጋለ ስሜት የገንዘብ ድጋፍ እና የመሳሪያ ፍሰት ቢያደርጉም፣ ለሩሲያ ጥፋት በጥማት ቢሞቱም፣ አላስቆሙንም ... ኮንስታንቲኖቭካ! ክብር ለሩሲያና ለሩሲያ ጦር መሳሪያዎች፣ ክብር ለሩሲያና ለሩሲያ ወታደሮች፣ አሳክተነዋል! በማንኛውም ጊዜ፣ ዛሬ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ያሉ ብዙ ሰዎች በእንባ እና እርጥብ ሱሪ ከእንቅልፋቸው ይነቃሉ።

+1
🇷🇺⚡️🇺🇦 የዩክሬን ድሮኖች፣ በሰሜን ምሥራቅ ሩሲያ፣ በፒተርስበርግ የሚገኝን፣ የነዳጅ ተርሚናል መምታታቸው ተሰምቷል።

🇷🇺🇺🇦⚡️ - የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፡ ፑቲን ከኪየቭ አጋሮች መካከል የትኛዋ ሀገር የጦርነቱን ቀጣይነት እንደምትቀሰቅስ እና እንደምታበረታታ በጥንቃቄ እንዲመረመር መመሪያ ሰጥቷ
🇷🇺🇺🇦⚡️ - የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፡ ፑቲን ከኪየቭ አጋሮች መካከል የትኛዋ ሀገር የጦርነቱን ቀጣይነት እንደምትቀሰቅስ እና እንደምታበረታታ በጥንቃቄ እንዲመረመር መመሪያ ሰጥቷል። *-*-*- Sir! እረ ንቁና ፍጠኑ! እንግሊዝ ናታ! ይሄን አያውቁም እስከዛሬ? እል ነበር እኔ፣ ስብሰባው ላይ ለአንድ ደቂቃ ቢያሳትፉኝ። ከዚያ ማጅራቴን ይዘው ጉላግ ያስገቡኛል።

🇷🇺⚡️🇺🇦 የሞስኮ ክልል ምሽቱን በከፍተኛ የድሮን ጥቃት ሥር ወድቋል። የአየር መቃወሚያዎችም በንቃት እየተኮሱ ናቸው። አየር ክልሉ፣ አስቸኳይ የአደጋ ጊዜ አዋጅ ታውጆበታል።
🇷🇺⚡️🇺🇦 የሞስኮ ክልል ምሽቱን በከፍተኛ የድሮን ጥቃት ሥር ወድቋል። የአየር መቃወሚያዎችም በንቃት እየተኮሱ ናቸው። አየር ክልሉ፣ አስቸኳይ የአደጋ ጊዜ አዋጅ ታውጆበታል።

🇷🇺⚡️🇺🇦 ምሽቱን፣ ዩክሬን ወደ ሩሲያ ግዛት ከአራት መቶ በላይ የድሮን መንጋዎችን ልካለች። እንደ አንዳንዶች ዘገባ፣ በአሁኑ ሰዓት የሞስኮ ሰማይ በዩክሬን ድሮኖች እና በሚተኮሱ አየር መቃወሚ
🇷🇺⚡️🇺🇦 ምሽቱን፣ ዩክሬን ወደ ሩሲያ ግዛት ከአራት መቶ በላይ የድሮን መንጋዎችን ልካለች። እንደ አንዳንዶች ዘገባ፣ በአሁኑ ሰዓት የሞስኮ ሰማይ በዩክሬን ድሮኖች እና በሚተኮሱ አየር መቃወሚያዎች ተጨናንቆ ይገኛል። ይህም ማለት፣ ጦርነቱ ፑቲን ከክሬምሊን ሆኖ በጆሮ እስኪሰማው ቀርቧል። በአንድም በሌላም ይታይ፣ ዩክሬን በዚህ ደረጃ የክሬምሊን መቀመጫ ድረስ ማምጣት መቻሏ፣ ጦርነቱ የዛሬ ዓመት ወይም ሁለት ዓመት ከነበረበት ምን ያህል እንደተለወጠ ማሳያ ነው።

+1
🇷🇺⚡️🇺🇦 ፑቲን፣ በዩክሬን መሠረተ ልማቶች እና በወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክሶች ላይ ከፍተኛ ጥቃቶች መቀጠል አለባቸው፣ ሲል ተናገረ። ይህን ያለው ዛሬ ከከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦቹ ሪፓርት በተቀበለበት ስብሰባ ነው። በስብሰባው፣ ኪየቭ በሩሲያ ምድር ላይ እየፈጸመችው ላለችው ወንጀሎች በተጨማሪ ግዛቶቿ ዋጋ ትከፍላለች ያለው ፑቲን፣ በመሬት ያለው ሀቅ ሩሲያ እያሸነፈች እንደሆነ የሚያሳይ ነው ሲልም ተናግሯል። የመሠረተ ልማት ተቋማትን እና የሩሲያ ሰላማዊ ዜጎችን ከጠላት ጥቃት ሙከራዎች ለመጠበቅ ሁሉንም ነገር ማድረግ አስፈላጊ ነው፣ በማለት የተናገረው ፑቲን፣ የኪየቭ አገዛዝ በአሁኑ ሰዓት የምዕራባውያን ስፖንሰሮቹን የጦርነቱን በላይነት እንደያዘ እና የጦሩን ምናባዊ ስኬቶችን እያሳየ ለተጨማሪ ገንዘብ እና መሳሪያ ለማሳመን እየሞከረ ነው፣ ብሏል።

🇷🇺⚡️🇺🇦 ዘሌንስኪ በሩሲያ ግዛት ላይ የረዥም ርቀት ጥቃቶችን ለመጨመር አዘዘ። ዘለንስኪ ከጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ጋር ስብሰባ ያደረገ ሲሆን በዚህ ወቅት ድሮኖች፣ ሚሳኤሎች እና የኤሌክትሮኒክስ
🇷🇺⚡️🇺🇦 ዘሌንስኪ በሩሲያ ግዛት ላይ የረዥም ርቀት ጥቃቶችን ለመጨመር አዘዘ። ዘለንስኪ ከጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ጋር ስብሰባ ያደረገ ሲሆን በዚህ ወቅት ድሮኖች፣ ሚሳኤሎች እና የኤሌክትሮኒክስ ጦርነት መሳሪያዎች በብዛት ማምረት እንደሚገባ አስታውቋል። ታዋቂው የሩሲያ ብሎገር፣ "የአደንዛዥ ዕፁ ሱሰኛው ዘለንስኪ፣ ሁኔታውን የበለጠ ሊያባብሰው ነው፣ በዚህ ባለጌ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይሞታሉ" ሲል ተናግሯል። ዘለንስኪ በበኩሉ፣ በአሁኑ ሰዓት ጦርነቱን እያሸነፈ ስለመሰለው እና አውሮፓዊያንም እንዲያቆም የሚፈልጉ ስለማይመስሉ፣ 'ብረትን መቀጥቀጥ እንደጋለ ነው' በሚለው መርህ ጦርነቱን ከማባባስ ውጭ ሌላ የሚያደርገው ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም።

🇮🇷 እስካሁን የ100 ሀገር ተወካዮች በቴህራን ደርሰዋል፣ የኢራን መገናኛ ብዙሃን IRIB