uk
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Відкрити в Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
4 290
Підписники
+124 години
-157 днів
-8430 днів
Архів дописів
🇷🇺🇺🇦⚡️— ሩሲያ የዋና ከተማዋን የአየር መከላከያ መረብ ለማጠናከር እያደረገች ባለችው ጥረት፣ የPantsir-SMD የአየር መቃወሚያ መሳሪያዎችን በMi-26 ሄሊኮፕተሮች በመጠቀም በሞስኮ ባሉ ከፍተኛ ሕንፃዎች ጣሪያዎች ላይ እየሰቀለች ነው። ዛሬ ላይ፣ የዩክሬን ድሮኖች እና ሚሳዬሎች፣ ሞስኮ ድረስ ዘልቀው በመግባት ጥቃት እየፈጸሙ ናቸው። በዚህም ዋና ከተማዋን በመከላከል ዙሪያ፣ ሩሲያ ሰፊ ሥራ እንድትሰራ ትገድዳለች።

🇪🇹⚡️አንድ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣን፣ በባሕር ዳር ስቴዲየም ምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረገው ንግግር፣ ስቴዲየሙ እንደ ፓሪስ ሴይንት ጀርሜን፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ሊቨርፑል እና የመሳሰሉት የአውሮፓ ክለቦች ሀገራቸው ሙቀት ሲሆን መጥተው ሊጫወቱበት እንደሚችሉ ተናገረ። ይሄን ያለው፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ አብይ አሕመድ ዓሊ ከፍተኛ አማካሪና የሀገሩ የደህንነት ኃላፊ ነው። ብዙዎች፣ ዛሬ ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉት አብዛኛዎቹ ባለስልጣናት፣ በአእምሮ ቅንጭርና እና ውስንነት የተጎዱ ናቸው ብለው በመክሰስ፣ በሁሉም ዘርፍ ሀገሩ ለገባበት ድቀት ተጠያቂ ሲያደርጓቸው ይሰማሉ። በሌላ በኩል፣ ሌሎች፣ ለዚህ ሁሉ መቀመቅ ሕዝቡን በግንባር ቀደምትነት ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ይሞግታሉ። እነዚሁ አካላት፣ "ግን ምን ሆነን ነው?" ሲሉ ራሳቸውን ይጠይቃሉ።

+2
🇺🇦❌🇷🇺— የዩክሬን ድሮኖች ዛሬ ጠዋት ላይ በሩሲያ የሚገኘውን የቲዩመን የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ላይ ጥቃት በመሰንዘር በተቋሙ ላይ ከፍተኛ እሳት እንዲነሳ አድርገዋል።

🇺🇸🇮🇱🇸🇦 ለግል ኩባንያዎ ከሳዑዲ አረቢያ 2 ቢሊዮን ዶላር ለምን ወሰዱ? 🗣 ጃሬድ ኩሽነር (የትራምፕ ሴት ልጅ ባል): የተቀበልኩትን ገንዘብ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ግንኙነት ለመፍጠር እና ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከእስራኤል የመጡ ነጋዴዎችን እርስ በእርስ ለማገናኘት በእስራኤል ውስጥ ኢንቨስት አድርጌዋለሁ።"

🇺🇸🇮🇱🇸🇦 ለግል ኩባንያዎ ከሳዑዲ አረቢያ 2 ቢሊዮን ዶላር ለምን ወሰዱ? 🗣 ጃሬድ ኩሽነር (የትራምፕ ሴት ልጅ ባል): የተቀበልኩትን ገንዘብ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ግንኙነት ለመፍጠር እና ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከእስራኤል የመጡ ነጋዴዎችን እርስ በእርስ ለማገናኘት በእስራኤል ውስጥ ኢንቨስት አድርጌያለሁ።"

🇺🇸🇮🇱 የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ጦርነት ላይ የሚያደርገውን ውስጣዊ ውይይት ለመስረቅ እስራኤል በአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በኃይል ስለላ እያደረገች ነው ሲል፣ NBC ዘግቧል። የአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል በአሜሪካ ላይ የምታደርገው ስለላ አዲስ እንዳልሆነ እና እስራኤላዊያን የአሜሪካን ወታደራዊ ሚስጥሮችን፣ የመሳሪያ ቀመሮችን እና ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ድሮም ጀምሮ በግልፁ እንደሚሰልሉ ይናገራሉ። በአሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲ የፔንታጎንን ግምገማ "ሙሉ በሙሉ የውሸት" ብሎ የጠራው ሲሆን፣ ቴል አቪቭ ጠላቶቿን ብቻ እንጂ አጋሮቿን እንደማትሰልል ገልጿል።

🇺🇸🇮🇱 የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ጦርነት ላይ የሚያደርገውን ውስጣዊ ውይይት ለመስረቅ እስራኤል በአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በኃይል ሰላይ እያደረገች ነው ሲል NBC ዘግቧል። የአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል በአሜሪካ ላይ የምታደርገው ስለላ አዲስ እንዳልሆነ እና እስራኤላዊያን የአሜሪካን ወታደራዊ ሚስጥሮችን፣ የመሳሪያ ቀመሮችን እና ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ድሮም ጀምሮ በግልፁ እንደሚሰልሉ ይናገራሉ። በአሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲ የፔንታጎንን ግምገማ "ሙሉ በሙሉ የውሸት" ብሎ የጠራው ሲሆን፣ ቴል አቪቭ ጠላቶቿን ብቻ እንጂ አጋሮቿን እንደማትሰልል ገልጿል።

🇺🇸🇮🇱 የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ጦርነት ላይ የሚያደርገውን ውስጣዊ ውይይት ለመስረቅ እስራኤል በአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በኃይል ሰላይ እያደረገች ነው ሲል NBC ዘግቧል። የአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል በአሜሪካ ላይ የምታደርገው ስለላ አዲስ እንዳልሆነ እና እስራኤላዊያን የአሜሪካን ወታደራዊ ሚስጥሮችን፣ የመሳሪያ ቀመሮችን እና ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ድሮም ጀምሮ በግልፁ እንደሚሰልሉ ይናገራሉ። በአሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲ የፔንታጎንን ግምገማ "ሙሉ በሙሉ የውሸት" ብሎ የጠራው ሲሆን፣ ቴል አቪቭ ጠላቶቿን ብቻ እንጂ አጋሮቿን እንደማትሰልል ገልጿል።

🇮🇱🇺🇸 ሰበር፡ ፔንታጎን እስራኤል በከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ በኃይል እየሰለለች እንደሆነ ባለው ስጋት ምክንያት፣ የእስራኤልን የጸረ-ስለላ የስጋት ደረጃ ወደ "ወሳኝ" ወደሚባለው ከፍ
+1
🇮🇱🇺🇸 ሰበር፡ ፔንታጎን እስራኤል በከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ በኃይል እየሰለለች እንደሆነ ባለው ስጋት ምክንያት፣ የእስራኤልን የጸረ-ስለላ የስጋት ደረጃ ወደ "ወሳኝ" ወደሚባለው ከፍተኛው ደረጃ ከፍ አድርጓል፣ በ NBC News መሠረት።

🇮🇷❌🇺🇸🇰🇼— የአካባቢው ነዋሪዎች በኩዌት ውስጥ ቢያንስ አስር ፍንዳታዎችን እንደሰሙ ሪፖርት አድርገዋል። የአየር መቃወሚያዎች ይሁኑ የወደቁ ሚሳዬሎች፣ ግልጽ አይደለም።

🇮🇷❌🇰🇼- የኩዌት ጦር ሰራዊት በአሁኑ ጊዜ በጠላት ሚሳይሎች እና ድሮኖች ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን አስታውቋል።
🇮🇷❌🇰🇼- የኩዌት ጦር ሰራዊት በአሁኑ ጊዜ በጠላት ሚሳይሎች እና ድሮኖች ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን አስታውቋል።

🇮🇷⚡️🇧🇭 ሰበር ዜና፡ በባሕሬን በርካታ ፍንዳታዎች እየተሰሙ ነው።

🇺🇸❌🇮🇷- ሰበር ዜና፡ ከ30 ደቂቃዎች በፊት አምስት የአሜሪካ የአየር ጥቃቶች በባንዳር ሲሪክ የባሕር ኃይል ጣቢያ ላይ ተከስቷል፣ የበርካታ የIRGC አባላትን ሞት አስከትሏል።

🇪🇹⚡️የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስተር፣ አቶ መለስ ዜናዊ፣ ከ15 ዓመታት በፊት፣ ዛሬ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ስላለው ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋ፣ ቁልጭ ያለ ምስላዊ ምልከታና ግንዛቤ ነበረው። ሁኔታውን በትክክል አንብቦት ነበር! በጊዜው፣ በፖርላማ ፊት ቃል በቃል የተናገረው ንግግሩ፣ ከፍተኛ እውነትን የያዘ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የቀጠናችንን፣ የአህጉራችንን ብሎም የዓለም አቀፉን ነባራዊ ሁኔታ በሚገባ የተረዳ እንደነበረ የሚያሳይ ነው። በእርግርጥ፣ ዛሬ ሀገሩ ለገባበት መቀመቅና ቀውስ እርሱ ያራምድ የነበረው የዘር ፖለቲካ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተ ቢሆንም፣ እዚህ ቦታ ላይ እና በዚህ ንግግሩ ግን፣ የማያወላውለውን የእውነታውን ዒላማ፣ አናቱ ላይ መትቶታል።

— 🇱🇧/🇮🇷 የሊባኖስ ፕሬዝዳንት፣ ጆሴፍ አውን፦ 'ኢራን በደቡብ ሊባኖስ ላይ ርህራሄ እንድታሳይ እና ሀገራችንን ማውደም እንድታቆም ጥሪ አቀርባለሁ'

⚡🇵🇸🇹🇷🇮🇷🇺🇸 Jerusalem Post እንደዘገበው፡ የእስራኤል የስለላ ምንጮች፣ ምክትል ፕሬዝዳንት JD Vance የኩርድ ኃይሎችን በኢራን ላይ ለመጠቀም የሞሳድ እቅድን በቀጥታ ለኤርዶጋን አሳውቋል፣ በማለት ከስሰውታል፣ ከዚያም ኤርዶጋን ትራምፕ እንዲሰርዘው ጫና አድርጓል። ትራምፕም፣ ዘመቻውን ከዚያ በኋላ ነበር የሰረዘው። *-*-*- ጦርነቱ በተጀመረ በጥቂት ቀናት ውስጥ፣ እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ የመሬት ወረራ ለመክፈት ኩርዶችን አደራጅተው መሳሪያ ልከውላቸው ነበር። በኋላ፣ ይሄን እቅድ ኤርዶጋን ሲሰማ፣ ትራምፕን ደውሎ እንዲያቆም ተማጽኖት ነበር። ኢራኖችም ይህን እቅድ ቀድመው ስላወቁ ኢራቅ በሚገኙ ሚሊሻ ወኪሎቻቸው፣ ኩርዲስታንን ደጋግመው በድሮንና በሚሳዬል ሲያስደበድቡ ከርመዋል። IRGCም በተደጋጋሚ ሰሜን ኢራቅ ያሉ ኩርዶችን፣ እንዲሁ፣ ሲመቱ ቆይተዋል።

🇺🇦❌🇷🇺— ዩክሬን ድሮኖችን ወደ ምዕራባዊ ሩሲያ እና ክራይሚያ ልካለች።
🇺🇦❌🇷🇺— ዩክሬን ድሮኖችን ወደ ምዕራባዊ ሩሲያ እና ክራይሚያ ልካለች።

🇺🇸⚔️🇮🇷የዩናይትድ ስቴትስ ኮማንድ (INDOPACOM) ከኢራን የነዳጅ ዘይት በማጓጓዝ ላይ ነበር ያለውን፣ የዘይት ታንከሩን ዳቪናን፣ በሕንድ ውቅያኖስ በስሪ ላንካ አቅራቢያ መያዙን አስታውቋል።

🇮🇷⚔️🇺🇸🏴‍☠️🇶🇦 እንደ Air Force Magazine ዘገባ መሠረት፣ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካን የአየር ውጊያዎች ከ2 አስርት ዓመታት በላይ የመራው የአሜሪካ የትዕዛዝ ማዕከል በአ
🇮🇷⚔️🇺🇸🏴‍☠️🇶🇦 እንደ Air Force Magazine ዘገባ መሠረት፣ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካን የአየር ውጊያዎች ከ2 አስርት ዓመታት በላይ የመራው የአሜሪካ የትዕዛዝ ማዕከል በአሜሪካ ከኢራን ጋር በተደረገው ጦርነት ወቅት ከባድ ጉዳት ደርሶበታል። በጦርነቱ የመጀመሪያ ሳምንታት ላይ፣ በርካታ የኢራን ሚሳኤሎች፣ በኳታር የሚገኘውን የአል-አዲድ አየር ኃይል ቤዝ የተቀናጀ የአየር ኦፕሬሽን ማዕከልን፣ በመምታት እንዳይሰራ አድርገውታል። *-*-*- ይሄ ጦርነት ለኢራን ትልቅ ዕድል አምጥቷል። ከምዕራቡ ዓለም ጋር ተጣብቀው አንሶላ ሲጋፈፉ ለኖሩት አረብ ጎረቤቶቿ፣ ያላትን አቅም ለማሳየት ዕድል ፈጥሮላታል። አረቦቹ ምናልባት፣ ኢራንን ለዘመናት ያሰቡት፣ ጥርስ እንደሌለው አንበሳ አድርገው ነበር፣ መጮህ እንጂ መናከስ እንደማይችል አንበሳ። ይሄ እሳቤአቸው ዛሬ ላይ ለዘላለሙ ተለውጧል። የገልፍ አረቦች ጉልበትና አቅም እንደሌላቸውና አለን የሚሉት ኃይልም (አሜሪካ፣ እንግሊዝ…) እነሱን እንደማይታደጋቸው ያዩበት ነው። በቀጣይ ምን ይሆናል? የምናየው ነው።

⚡️🇮🇷🌐 ኢራን የጦርነቱን ሽፋን ታሰፋዋለች! 📣 ጄኔራል ሙህሲን ረዛይ ለCNN በሰጡት ቃለ መጠይቅ ፦ 🔘 ጦርነቱ ከቀጠለ እና የባሕር ኃይሉ እገታ ካልተነሳ፣ ጦርነቱን ወደ ሕንድ ውቅያኖስ፣ ወደ ባብ-ኤል-ማንደብ በር፣ ወደ ቀይ ባሕር እና ወደ ሜዲትራኒያን እናዛውራለን ። ሌሎች የአሜሪካ ካምፖችን በመምታት፣ ለጦርነቱ አዳዲስ ልኬቶችን እና ግንባሮችን እንፈጥራለን። አሜሪካ እጅግ የላቀ ኪሳራ እንደሚደርስባት ምንም ጥርጥር የለውም ። በአሜሪካ ላይ የሚደርሰው ጉዳት በጣም ከባድ ይሆናል።"