የቀጠናው ተመልካች
Ir al canal en Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
4 303
Suscriptores
-624 horas
-247 días
-9030 días
Archivo de publicaciones
4 303
🇺🇸🇮🇱 የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ጦርነት ላይ የሚያደርገውን ውስጣዊ ውይይት ለመስረቅ እስራኤል በአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በኃይል ስለላ እያደረገች ነው ሲል፣ NBC ዘግቧል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል በአሜሪካ ላይ የምታደርገው ስለላ አዲስ እንዳልሆነ እና እስራኤላዊያን የአሜሪካን ወታደራዊ ሚስጥሮችን፣ የመሳሪያ ቀመሮችን እና ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ድሮም ጀምሮ በግልፁ እንደሚሰልሉ ይናገራሉ።
በአሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲ የፔንታጎንን ግምገማ "ሙሉ በሙሉ የውሸት" ብሎ የጠራው ሲሆን፣ ቴል አቪቭ ጠላቶቿን ብቻ እንጂ አጋሮቿን እንደማትሰልል ገልጿል።
4 303
🇺🇸🇮🇱 የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ጦርነት ላይ የሚያደርገውን ውስጣዊ ውይይት ለመስረቅ እስራኤል በአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በኃይል ሰላይ እያደረገች ነው ሲል NBC ዘግቧል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል በአሜሪካ ላይ የምታደርገው ስለላ አዲስ እንዳልሆነ እና እስራኤላዊያን የአሜሪካን ወታደራዊ ሚስጥሮችን፣ የመሳሪያ ቀመሮችን እና ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ድሮም ጀምሮ በግልፁ እንደሚሰልሉ ይናገራሉ።
በአሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲ የፔንታጎንን ግምገማ "ሙሉ በሙሉ የውሸት" ብሎ የጠራው ሲሆን፣ ቴል አቪቭ ጠላቶቿን ብቻ እንጂ አጋሮቿን እንደማትሰልል ገልጿል።
4 303
🇺🇸🇮🇱 የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ጦርነት ላይ የሚያደርገውን ውስጣዊ ውይይት ለመስረቅ እስራኤል በአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በኃይል ሰላይ እያደረገች ነው ሲል NBC ዘግቧል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል በአሜሪካ ላይ የምታደርገው ስለላ አዲስ እንዳልሆነ እና እስራኤላዊያን የአሜሪካን ወታደራዊ ሚስጥሮችን፣ የመሳሪያ ቀመሮችን እና ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ድሮም ጀምሮ በግልፁ እንደሚሰልሉ ይናገራሉ።
በአሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲ የፔንታጎንን ግምገማ "ሙሉ በሙሉ የውሸት" ብሎ የጠራው ሲሆን፣ ቴል አቪቭ ጠላቶቿን ብቻ እንጂ አጋሮቿን እንደማትሰልል ገልጿል።
4 303
+1
🇮🇱🇺🇸 ሰበር፡ ፔንታጎን እስራኤል በከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ በኃይል እየሰለለች እንደሆነ ባለው ስጋት ምክንያት፣ የእስራኤልን የጸረ-ስለላ የስጋት ደረጃ ወደ "ወሳኝ" ወደሚባለው ከፍተኛው ደረጃ ከፍ አድርጓል፣ በ NBC News መሠረት።
4 303
🇮🇷❌🇺🇸🇰🇼— የአካባቢው ነዋሪዎች በኩዌት ውስጥ ቢያንስ አስር ፍንዳታዎችን እንደሰሙ ሪፖርት አድርገዋል። የአየር መቃወሚያዎች ይሁኑ የወደቁ ሚሳዬሎች፣ ግልጽ አይደለም።
4 303
🇺🇸❌🇮🇷- ሰበር ዜና፡ ከ30 ደቂቃዎች በፊት አምስት የአሜሪካ የአየር ጥቃቶች በባንዳር ሲሪክ የባሕር ኃይል ጣቢያ ላይ ተከስቷል፣ የበርካታ የIRGC አባላትን ሞት አስከትሏል።
4 303
🇪🇹⚡️የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስተር፣ አቶ መለስ ዜናዊ፣ ከ15 ዓመታት በፊት፣ ዛሬ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ስላለው ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋ፣ ቁልጭ ያለ ምስላዊ ምልከታና ግንዛቤ ነበረው።
ሁኔታውን በትክክል አንብቦት ነበር!
በጊዜው፣ በፖርላማ ፊት ቃል በቃል የተናገረው ንግግሩ፣ ከፍተኛ እውነትን የያዘ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የቀጠናችንን፣ የአህጉራችንን ብሎም የዓለም አቀፉን ነባራዊ ሁኔታ በሚገባ የተረዳ እንደነበረ የሚያሳይ ነው።
በእርግርጥ፣ ዛሬ ሀገሩ ለገባበት መቀመቅና ቀውስ እርሱ ያራምድ የነበረው የዘር ፖለቲካ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተ ቢሆንም፣ እዚህ ቦታ ላይ እና በዚህ ንግግሩ ግን፣ የማያወላውለውን የእውነታውን ዒላማ፣ አናቱ ላይ መትቶታል።
4 303
— 🇱🇧/🇮🇷 የሊባኖስ ፕሬዝዳንት፣ ጆሴፍ አውን፦ 'ኢራን በደቡብ ሊባኖስ ላይ ርህራሄ እንድታሳይ እና ሀገራችንን ማውደም እንድታቆም ጥሪ አቀርባለሁ'
4 303
⚡🇵🇸🇹🇷🇮🇷🇺🇸 Jerusalem Post እንደዘገበው፡ የእስራኤል የስለላ ምንጮች፣ ምክትል ፕሬዝዳንት JD Vance የኩርድ ኃይሎችን በኢራን ላይ ለመጠቀም የሞሳድ እቅድን በቀጥታ ለኤርዶጋን አሳውቋል፣ በማለት ከስሰውታል፣ ከዚያም ኤርዶጋን ትራምፕ እንዲሰርዘው ጫና አድርጓል።
ትራምፕም፣ ዘመቻውን ከዚያ በኋላ ነበር የሰረዘው።
*-*-*-
ጦርነቱ በተጀመረ በጥቂት ቀናት ውስጥ፣ እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ የመሬት ወረራ ለመክፈት ኩርዶችን አደራጅተው መሳሪያ ልከውላቸው ነበር። በኋላ፣ ይሄን እቅድ ኤርዶጋን ሲሰማ፣ ትራምፕን ደውሎ እንዲያቆም ተማጽኖት ነበር። ኢራኖችም ይህን እቅድ ቀድመው ስላወቁ ኢራቅ በሚገኙ ሚሊሻ ወኪሎቻቸው፣ ኩርዲስታንን ደጋግመው በድሮንና በሚሳዬል ሲያስደበድቡ ከርመዋል። IRGCም በተደጋጋሚ ሰሜን ኢራቅ ያሉ ኩርዶችን፣ እንዲሁ፣ ሲመቱ ቆይተዋል።
4 303
🇺🇸⚔️🇮🇷የዩናይትድ ስቴትስ ኮማንድ (INDOPACOM) ከኢራን የነዳጅ ዘይት በማጓጓዝ ላይ ነበር ያለውን፣ የዘይት ታንከሩን ዳቪናን፣ በሕንድ ውቅያኖስ በስሪ ላንካ አቅራቢያ መያዙን አስታውቋል።
4 303
🇮🇷⚔️🇺🇸🏴☠️🇶🇦 እንደ Air Force Magazine ዘገባ መሠረት፣ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካን የአየር ውጊያዎች ከ2 አስርት ዓመታት በላይ የመራው የአሜሪካ የትዕዛዝ ማዕከል በአሜሪካ ከኢራን ጋር በተደረገው ጦርነት ወቅት ከባድ ጉዳት ደርሶበታል።
በጦርነቱ የመጀመሪያ ሳምንታት ላይ፣ በርካታ የኢራን ሚሳኤሎች፣ በኳታር የሚገኘውን የአል-አዲድ አየር ኃይል ቤዝ የተቀናጀ የአየር ኦፕሬሽን ማዕከልን፣ በመምታት እንዳይሰራ አድርገውታል።
*-*-*-
ይሄ ጦርነት ለኢራን ትልቅ ዕድል አምጥቷል። ከምዕራቡ ዓለም ጋር ተጣብቀው አንሶላ ሲጋፈፉ ለኖሩት አረብ ጎረቤቶቿ፣ ያላትን አቅም ለማሳየት ዕድል ፈጥሮላታል። አረቦቹ ምናልባት፣ ኢራንን ለዘመናት ያሰቡት፣ ጥርስ እንደሌለው አንበሳ አድርገው ነበር፣ መጮህ እንጂ መናከስ እንደማይችል አንበሳ። ይሄ እሳቤአቸው ዛሬ ላይ ለዘላለሙ ተለውጧል።
የገልፍ አረቦች ጉልበትና አቅም እንደሌላቸውና አለን የሚሉት ኃይልም (አሜሪካ፣ እንግሊዝ…) እነሱን እንደማይታደጋቸው ያዩበት ነው። በቀጣይ ምን ይሆናል? የምናየው ነው።
4 303
⚡️🇮🇷🌐 ኢራን የጦርነቱን ሽፋን ታሰፋዋለች!
📣 ጄኔራል ሙህሲን ረዛይ ለCNN በሰጡት ቃለ መጠይቅ ፦
🔘 ጦርነቱ ከቀጠለ እና የባሕር ኃይሉ እገታ ካልተነሳ፣ ጦርነቱን ወደ ሕንድ ውቅያኖስ፣ ወደ ባብ-ኤል-ማንደብ በር፣ ወደ ቀይ ባሕር እና ወደ ሜዲትራኒያን እናዛውራለን ።
ሌሎች የአሜሪካ ካምፖችን በመምታት፣ ለጦርነቱ አዳዲስ ልኬቶችን እና ግንባሮችን እንፈጥራለን።
አሜሪካ እጅግ የላቀ ኪሳራ እንደሚደርስባት ምንም ጥርጥር የለውም ። በአሜሪካ ላይ የሚደርሰው ጉዳት በጣም ከባድ ይሆናል።"
4 303
🇮🇷🇺🇸⚡️— የኢራን የዓለም ዋንጫ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ወደ አሜሪካ ለመግባት ቪዛ እንደተሰጣቸው የኋይት ሃውስ ባለሥልጣንን በመጥቀስ ሮይተርስ ዘግቧል።
*-*-*-
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን፣ ከ DC ከተማ የእግር ኳስ ክለብ ጋር የወዳጅነት እንዳይጫወትና በዚያውም የዓለም ዋንጫን አንድ ሁለት ጌም አይተው መጥፋት እንዳይችሉ፣ 'ኢቦላ ይዛችሁብን ልትመጡ ስለምትችሉ' ተብለው፣ ቪዛ የተከለከሉት በዚሁ ባሳለፍነው ሳምንት ነበር።
4 303
+2
🇪🇹⚡️የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር፣ አቶ አብይ አሕመድ አሊ፣ በአርሲ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ፣ አወገዘ።
በመግለጫው፣ ለአርሲው የሰላማዊ ዜጎች ጭፍጨፋ በዋናነት ኃላፊነት የሚወስደው "ኦነግ ሸኔ" ነው ያለ ሲሆን፣ በዐማራ ግዛቶች የሚንቀሳቀሰው "የፋኖ ኃይል"ም ብጥብጥ ለመፍጠር ሲተጋ ነበር ብሎ ከሷል።
በመግለጫው፣ ስለ አርሲ ጭፍጨፋ ሦስት መስመር ጽሑፍ ብቻ ነው የሰፈረው። የተቀረው፣ ስለ ምርጫ ታዛቢዮች፣ ስለ ምርጫ ሂደቱ፣ ስለ ኢኮኖሚ፣ ስለ ህዳሴ ግድብ፣ ስለ ንግድ፣ ስለ ኢንዱስትሪ እና በሱማሌ ክልል ስላለው ስለ ጎዴ የማዳበሪያ ፋብሪካ የሚያትት ነው።
4 303
🇮🇱❌🇱🇧 — የእስራኤል የሰፈራዎች እና የብሔራዊ ተልእኮዎች ሚኒስትር ኦሪት ስትሩክ፣ ትናንት በሊባኖስ ላይ በተደረገው የካቢኔ ስብሰባ ላይ፣ በ Ynet መረጃ መሰረት፦
'ድንበሩ ይቀየርልን። የሊባኖስ ደቡብ ክልል ይጠቅለል፣ በዚህ አቅጣጫ መሄድ አለብን።'
4 303
🇮🇱🇦🇿⚡🇮🇷 CNN፦ እስራኤል ከኢራን ጋር በተካሄደው ጦርነት ወቅት ልዩ ወታደራዊ እና የስለላ ኃይሎቿን በሚስጥር ወደ አዘርባጃን ሪፐብሊክ ልካ፣ የጦር ሰፈር አቋቁማ ነበር።
ይህ እርምጃ፣ እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ፣ ምዕራብ እስያ እና አካባቢው፣ በኢራን ላይ የሚደረጉ ተግባራትን ለማመቻቸት እና ሚስጥራዊ የማዕከላት እና የተግባራዊ መረቦችን ለመዘርጋት የምታደርገው ጥረት አካል ነው።
*-*-*-
ያሳቀኝ፣ እስራኤል ኢራቅ በረሃ ውስጥ የጦር ሰፈር መሥርታ፣ አይሮፕላን እያሳረፈች እና እያስነሳች፣ ሎጀስቲክ እየጫነች እና እያራገፈች፣ ለሁለት ዓመት፣ ሳይታወቅ፣ ስትገለገልበት፣ ስትዘጋጅበት እና ስትታጠቅበት ከርማ፣ ለኢራን ጦርነት ከተገለገለችበት በኋላ ለቃ መውጣቷ ነው።
እሱንም፣ የፍየል እረኛ በዚያ ሲያልፍ አይቶ ነው፣ ኧረ ይሄ ነገር ብሎ በኋላ መንግሥቱ የባነነው።
እና ሀገሮች እስራኤል ገብታ እልም ያለ የጦር ሰፈር ስትሰራባቸው ላያውቁ ይችላሉ። አፍዝዝ አደንግዝ ስለሚጠቀሙ።
