uk
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Відкрити в Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
4 327
Підписники
+2824 години
+307 днів
-4230 днів
Архів дописів
🇺🇸⚔️🇮🇷 US Central Command (ማዕከላዊ እዝ)፡ ከብዙ አሥርተ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት አውሮፕላኖች አጓጓዦች ደምሳሽ መርከቦች በመካከለኛው ምስራቅ በአንድ ጊዜ እየሠሩ
🇺🇸⚔️🇮🇷 US Central Command (ማዕከላዊ እዝ)፡ ከብዙ አሥርተ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት አውሮፕላኖች አጓጓዦች ደምሳሽ መርከቦች በመካከለኛው ምስራቅ በአንድ ጊዜ እየሠሩ ነው። የ US አውሮፕላን አጓጓዥ መርከቦች፣ አብርሃም ሊንከን (ሲቪኤን 72)፣ ጄራልድ ፎርድ (ሲቪኤን 78) እና ጆርጅ ኤችደብሊው ቡሽ (ሲቪኤን 77)፣ ከ200 በላይ አውሮፕላኖችን እና 15,000 መርከበኞችን እና የባሕር ኃይል ወታደሮችን አቅፈው በቀጠናው እየተንቀሳቀሱ ናቸው።

🇺🇸❌🇮🇷🛢 - ኢራን የድፍድፍ ዘይት የማከማቻ አቅሟ እያለቀ በመምጣቱ፣ የድሮውን የነዳጅ መርከብ Nasha ን ከጡረታ አውጥታ ወደ ሥራ መልሳለች። የ30 ዓመቱ ታንከር ለብዙ ዓመታት ባዶ ሆኖ
🇺🇸❌🇮🇷🛢 - ኢራን የድፍድፍ ዘይት የማከማቻ አቅሟ እያለቀ በመምጣቱ፣ የድሮውን የነዳጅ መርከብ Nasha ን ከጡረታ አውጥታ ወደ ሥራ መልሳለች። የ30 ዓመቱ ታንከር ለብዙ ዓመታት ባዶ ሆኖ በመልህቁ ታስሮ ቆይቶ የነበረ ሲሆን፣ አሁን እንደ የባሕር ዳርቻ ማከማቻነት እንዲያገለግል ሆኖ ወደ ሥራ ገብቷል። የአሜሪካ እገዳ እየጠነከረ ነው፣ ኢራንም በአብዛኛው ዘይት ወደ ውጭ መላክ አልቻለችም። በመሆኑም ኢራን የማከማቻ አቅሟን አሟጣ ከተጠቀመች በኋላ፣ የነዳጅ ጉድጓዶቿን መዝጋት ሊኖርባት ይችላል። ይህ ደግሞ በጣም ከባድ እና ውስብስብ ሥራ ሲሆን፣ መልሶ ለመክፈት ወራቶችን ይወስዳል።

🇺🇸🇮🇷 "አሜሪካ ከኢራን ጋር የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ለመቅደድ በዝግጅት ላይ ትገኛለች፣ የጥቃት ዒላማዎችንም እያዘጋጀች ነው CNN ከዒላማዎቹ መካከል በሆርሙዝ ወሽመጥ የኢራን የባሕር ኃይል ይገኝበታል።"

🇸🇦 🤝 🇺🇸 ዛሬ በሳዑዲ ዓረቢያ የአሜሪካ ግዙፍ ወታደራዊ ነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖች፣ እጅግ በብዛት ሲንቀሳቀሱ ታይተዋል። በአሁኑ ጊዜ፣ በአየር ላይ ቢያንስ ስድስት "የሚበሩ ታንከሮች" እንዳሉ
🇸🇦 🤝 🇺🇸 ዛሬ በሳዑዲ ዓረቢያ የአሜሪካ ግዙፍ ወታደራዊ ነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖች፣ እጅግ በብዛት ሲንቀሳቀሱ ታይተዋል። በአሁኑ ጊዜ፣ በአየር ላይ ቢያንስ ስድስት "የሚበሩ ታንከሮች" እንዳሉ ይታያል። ይህም በተዘዋዋሪ፣ በኢራን ላይ ሌላ ዙር ድብደባ ሊጀመር ቋፍ ላይ እንደተደረሰ እና ዛሬም እነ ሳዑዲ ለአሜሪካ ጦር ሽፋን እየሰጡ እንደሆነ አመላካች ነው።

🇵🇸 🇱🇧
ከእስራኤል በፊት ያልነበረችው እና በኋላ የተፈበረከችው ዮርዳኖስ እና ሁሉም ከፍልስጤም የመጡ እና ቃል በቃል ወንድሞቻችን ብለን የምንጠራቸው ዮርዳኖሳውያን፣ እንደ ሊባኖስ ሕዝብ ከእኛ (ፍልስጤማዊያን) ጋር አልቆሙም።
አዎ! ሊባኖሶች ጎረቤታችን ናቸው፣ ግን ዮርዳኖሳዊያን ለእኛ በጣም ይቀርቡን ነበር። ወደ 70% የሚሆኑት ከፍልስጤም የመጡ ናቸው። ድርጊታቸውን ላየ ግን፣ በጭራሽ እንደዚያ አይመስሉም። ሊባኖስን ሁሌም እናመሰግናለን።" Palestinian Observer 

🇵🇦 የፓናማ የባሕር መተላለፊያ ክፍያ በሦስት እጥፍ ጨምሯል፣ Financial Times የሆርሙዝ ባሕር መዘጋት የአማራጭ መንገዶችን ፍላጎት ጨምሯል፣ የዓለም አቀፍ የኃይል ማጓጓዣ ወጪዎችንም እንዲ
🇵🇦 የፓናማ የባሕር መተላለፊያ ክፍያ በሦስት እጥፍ ጨምሯል፣ Financial Times የሆርሙዝ ባሕር መዘጋት የአማራጭ መንገዶችን ፍላጎት ጨምሯል፣ የዓለም አቀፍ የኃይል ማጓጓዣ ወጪዎችንም እንዲሁ። የፓናማ የባሕር ወሽመጥ ክፍያ፣ ከ130,000 ዶላር ወደ 385,000 ዶላር (3 እጥፍ) እና በአንዳንድ ሁኔታዎች እስከ 4 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል።

🇺🇸🇮🇱❌🇮🇷❗️ - እንደ እስራኤሉ ቻናል 13 ዘገባ ከሆነ፣ የእስራኤል ባለስልጣናት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚያደርገውን ጥቃት ዳግም እንዲጀምር በማሳመን ላይ ለመዘጋጀት፣ ከኔታንያሁ ጋር ተገ
🇺🇸🇮🇱❌🇮🇷❗️ - እንደ እስራኤሉ ቻናል 13 ዘገባ ከሆነ፣ የእስራኤል ባለስልጣናት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚያደርገውን ጥቃት ዳግም እንዲጀምር በማሳመን ላይ ለመዘጋጀት፣ ከኔታንያሁ ጋር ተገናኝተዋል። 📺 ቻናል13

🇸🇦 🇶🇦 🇧🇭 🇰🇼 🇦🇪 የገልፍ አገራት እና የሳዑዲ ዓረቢያ የጀት ነዳጅ አቅርቦት፣ በ 80 በመቶ አሽቆልቁሏል ተብሏል። ከእነዚህ አገራት ወደ ውጭ የሚላከው የጀት ነዳጅ፣ በመጋቢት ወ
🇸🇦 🇶🇦 🇧🇭 🇰🇼 🇦🇪 የገልፍ አገራት እና የሳዑዲ ዓረቢያ የጀት ነዳጅ አቅርቦት፣ በ 80 በመቶ አሽቆልቁሏል ተብሏል። ከእነዚህ አገራት ወደ ውጭ የሚላከው የጀት ነዳጅ፣ በመጋቢት ወር በ80 በመቶ ቀንሷል። በቀን ይላክ ከነበረው ከ605,000 በርሜል ፍጆታ፣ አሁን ላይ ወደ 127,000 በርሜል ወርዷል። በዓለም ሁለተኛዋ ትልቋ የጀት ነዳጅ አቅራቢ የሆነችው ኩዌት፣ አቅርቦቷ በ97 በመቶ የቀነሰ ሲሆን፣ የአገራቱ የዓለም አቀፍ የጀት ነዳጅ አቅርቦት ድርሻ፣ ከጦርነቱ በፊት ከነበረበት 32 በመቶ በሚያዝያ ወር ወደ 3.7 በመቶ ወርዷል።

🇱🇧🇮🇱🇺🇸 "የሊባኖስ ህዝብ፣ የእስራኤል ሕዝብ፣ ጎረቤታማቾች ናቸው፣ እና መግባባት ይፈልጋሉ" - Mike Huckabee በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር። ነገር ግን በመሃላቸው፣ በሰፈር ውስጥ የሚኖር ረባሽ ትንሽ ልጅ አለ፣ በጎረቤቶቹ መስኮት ላይ ድንጋይ የሚወረውር (ያስቸገራቸው እሱ ነው)። ሂዝቦላህ ማለቱ ነው።

🇮🇱 የእስራኤሉ ጋዜጣ፣ Haaretz እንደዘገበው፣ የእስራኤል ወታደሮች በደቡባዊ ሊባኖስ በሰፊው ዘረፋ እየፈጸሙ ሲሆን ሞተር ሳይክሎችን፣ ቴሌቪዥኖችን እና ሌሎች መሳሪያዎችን እንዲሁም የቤት እቃዎ
🇮🇱 የእስራኤሉ ጋዜጣ፣ Haaretz እንደዘገበው፣ የእስራኤል ወታደሮች በደቡባዊ ሊባኖስ በሰፊው ዘረፋ እየፈጸሙ ሲሆን ሞተር ሳይክሎችን፣ ቴሌቪዥኖችን እና ሌሎች መሳሪያዎችን እንዲሁም የቤት እቃዎችን እየወሰዱ ነው። ⚠️ ይህ የሆነበት ምክንያት፣ አንዳንድ ወታደራዊ የጥበቃ ኬላዎች ስለተወገዱ እና አንዳንዶቹም ፈጽሞ ስላልነበሩ፣ ለዝርፊያውም ምንም ዓይነት ቅጣት ስለሌለባቸው ነው፣ ብሏል።

🇮🇱 🇮🇷 "የጠላት" የተባሉ ድሮኖች፣ በቴህራን ሰማይ ምሽቱን በኢራን አየር ኃይል ተመትተው ተወግደዋል -- Mehr የኢራን መገናኛ ብዙሃን የሞሳድ ድኖራዊ እንቅስቃሴ ሊሆን ይችላል።

🇮🇷 | የኢራን መገናኛ ብዙሃን TASNIM,
አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብ ለመያዝ ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም፣ የ IRGC የባሕር ኃይል መርከቦች በሰላም ወደ ኢራን አጅበዋታል። ሩዝ የተሸከመችው መርከቧ፣ የኦማን ባሕርን አቋርጣ የመጥለፍ ሙከራ ቢደረግባት የኢራን ውሃ ደርሳለች።

🇮🇷 የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጠባቂ ሠራዊት IRGC ባሕር ኃይል፣ የኢራን መርከቦችን በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ ማጀብ መጀመሩ ተሰምቷል። ሁለት መርከቦችም በእጀባ ወሽመጡን አልፈው፣ ወደ መዳረሻቸው እንዳመሩ ታውቋል።

🇮🇱 የእስራኤል ፖሊስ፣ የእስራኤልና የፍልስጤም ባንዲራ የተሰፋበትን ኮፍያ ያያደረገን አይሁድ፣ 'ለምን አደረግህ' በሚል ውንጀላ በቁጥጥር ሥር ካዋሉት በኋላ፣ ከኮፍያው ላይ የፍልስጤምን ባንዲራ ቆ
+1
🇮🇱 የእስራኤል ፖሊስ፣ የእስራኤልና የፍልስጤም ባንዲራ የተሰፋበትን ኮፍያ ያያደረገን አይሁድ፣ 'ለምን አደረግህ' በሚል ውንጀላ በቁጥጥር ሥር ካዋሉት በኋላ፣ ከኮፍያው ላይ የፍልስጤምን ባንዲራ ቆርጠው በመጣል፣ ግለሰቡን ግለሰቡን እንደለቀቁት ተሰምቷል።

🇱🇧❌🇮🇱 - ሂዝቦላህ በሃይፋ እስራኤል የሚገኘው የራምባም ሆስፒታል ምክትል ዳይሬክተር አቪ ዌይስማንን በመጥቀስ፣ የሚከተሉትን ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያ አጋርቷል። "በሊባኖስ በተካሄደው ከባድ
+3
🇱🇧❌🇮🇱 - ሂዝቦላህ በሃይፋ እስራኤል የሚገኘው የራምባም ሆስፒታል ምክትል ዳይሬክተር አቪ ዌይስማንን በመጥቀስ፣ የሚከተሉትን ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያ አጋርቷል።
"በሊባኖስ በተካሄደው ከባድ ጦርነት ምክንያት እጅና እግራቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ብዙ ናቸው። ይህ በእውነት፣ የአንደኛውና የሁለተኛውን የሊባኖስ ጦርነቶች ዘመን ያስታውሰኛል።"

🇮🇱❌🇮🇷 - የእስራኤል የጦር ሚኒስቴር
- የአሜሪካን አረንጓዴ መብራት ብቻ እየጠበቅን ነው። በመጀመሪያ እና ከሁሉም በላይ፣ የኻሜኒይን ሥርወ መንግሥት መወገድን እናጠቃልላለን።
በ 12 ቀኑ ጦርነትም ይሁን በዚህኛው እንደታየው፣ የእስራኤል ጦር ብቻውን እንደ ኢራን ያለ አገርን መዋጋት አቅም የለውም። በዚህ ጦርነት ከአሜሪካ እና ከገልፍ አገሮች ጋር በአንድ ተጣምረውም፣ ኢራንን ሊያንበረክኩ ተስኗቸዋል። ምናልባት እስራኤል ልትዋጋና የበላይ መሆን የምትችለው በፍልስጤም እና በሊባኖስ ባሉ ሽምቅ ተዋጊዎች ላይ ሊሆን ይችላል። እሱም ቢሆን እስካሁን ልታጠናቅቅ ያልቻለችው ነው።

🇨🇺 — Havana አብርታለች። በወራቶች ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ኩባ መብራቷ ተመልሷል። የቬንዝዌላ መሪን ውድቀት ተከትሎ፣ የኩባ መንግሥት ይወድቃል በሚል ተስፋ፣ አሜሪካ ወደ ኩባ ምንም ነዳጅ እንዳይገባ እገዳ ጥላ ነበር። በዚህም የተነሳ ፋብሪካዎች እና እርሻዎች ሥራ ለማቆም ተገደዋል። ትምህርት ቤቶች አልነበሩም፣ ሆስፒታሎች ሥራ አቁመው ነበር፣ በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ ህመምተኞች፣ አብዛኞቹ ሕፃናት፣ ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ሲዘገብ ቆይቷል። በመጨረሻ ግን፣ በሩሲያው መሪ ፑቲን ትዕዛዝ፣ ነዳጅ የጫኑ መርከቦች የአሜሪካን እገዳ ጥሰው የዛሬ ሳምንት ኩባ ዳርቻዎች ደርሰው ነበር። በጊዜው፣ ከሩሲያ ጋር ሰጣ ገባ ላለመግባት የአሜሪካ ባሕር ኃይል ጣልቃ ከመግባት ተቆጥቧል። "የሩሲያ ነዳጅ በኩባ ሆስፒታሎች ሕይወትን ታድጓል።"

- 🇺🇸 / 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ Truth Social - ‹‹ኢራን መሪዋ ማን እንደሆነ ለማወቅ በጣም ተቸግራለች! በቃ መሪያቸው ማን እንሆነ አላወቁትም! በጦር ሜዳ ላይ ክፉኛ በተሸነፉት
- 🇺🇸 / 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ  በ Truth Social -
‹‹ኢራን መሪዋ ማን እንደሆነ ለማወቅ በጣም ተቸግራለች! በቃ መሪያቸው ማን እንሆነ አላወቁትም! በጦር ሜዳ ላይ ክፉኛ በተሸነፉት "አጥባቂዎች" እና "ለዘብተኞች" (በእውነቱ ግን ለዘብተኛ ያልሆኑት) መካከል ያለው የርስ በእርስ ፍትጊያ መረን ለቋል። በሆርሙዝ ባሕር ላይ ሙሉ ቁጥጥር አለን። ከዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል ፈቃድ ውጭ የትኛውም መርከብ መግባትም ሆነ መውጣት አይችልም። ኢራን ስምምነት ማድረግ እስክትችል ድረስ፣ "በጥብቅ የታሸገ" ነው!! ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ስላደረጉ አመሰግናለሁ። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕ።"

🇮🇹🇩🇪 የአውሮፓ ሕብረት ከእስራኤል ጋር ያለውን የንግድ ስምምነቶቹን ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ ያቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ በጣልያን እና በጀርመን እምቢታዊ ምርጫ ውድቅ ሆኗል። ከሁለቱ አገሮች በስተቀር፣ ሁሉም የሕብረቱ አባላት እሺታቸውን የለገሱ ሰነድ ነበር።

🇱🇧 | Al - Manar፡ በ IDF ቁጥጥር ሥር ባለው/በተያዘው ደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ ካሉት መኖሪያ ቤቶች፣ የሞተር ሳይክሎች፣ የቴሌቪዥኖች፣ የሥዕሎች፣ የሶፋዎች እና የምንጣፎች መሰረቅን ጨምሮ መጠነ ሰፊ ዝርፊያ በጦሩ ተካሂዷል።