የቀጠናው ተመልካች
前往频道在 Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
显示更多未指定国家未指定类别
4 330
订阅者
+2824 小时
+307 天
-4230 天
帖子存档
4 330
🇮🇱 🇮🇷 "የጠላት" የተባሉ ድሮኖች፣ በቴህራን ሰማይ ምሽቱን በኢራን አየር ኃይል ተመትተው ተወግደዋል -- Mehr የኢራን መገናኛ ብዙሃን
የሞሳድ ድኖራዊ እንቅስቃሴ ሊሆን ይችላል።
4 330
🇮🇷 | የኢራን መገናኛ ብዙሃን TASNIM,
አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብ ለመያዝ ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም፣ የ IRGC የባሕር ኃይል መርከቦች በሰላም ወደ ኢራን አጅበዋታል። ሩዝ የተሸከመችው መርከቧ፣ የኦማን ባሕርን አቋርጣ የመጥለፍ ሙከራ ቢደረግባት የኢራን ውሃ ደርሳለች።
4 330
🇮🇷 የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጠባቂ ሠራዊት IRGC ባሕር ኃይል፣ የኢራን መርከቦችን በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ ማጀብ መጀመሩ ተሰምቷል። ሁለት መርከቦችም በእጀባ ወሽመጡን አልፈው፣ ወደ መዳረሻቸው እንዳመሩ ታውቋል።
4 330
+1
🇮🇱 የእስራኤል ፖሊስ፣ የእስራኤልና የፍልስጤም ባንዲራ የተሰፋበትን ኮፍያ ያያደረገን አይሁድ፣ 'ለምን አደረግህ' በሚል ውንጀላ በቁጥጥር ሥር ካዋሉት በኋላ፣ ከኮፍያው ላይ የፍልስጤምን ባንዲራ ቆርጠው በመጣል፣ ግለሰቡን ግለሰቡን እንደለቀቁት ተሰምቷል።
4 330
+3
🇱🇧❌🇮🇱 - ሂዝቦላህ በሃይፋ እስራኤል የሚገኘው የራምባም ሆስፒታል ምክትል ዳይሬክተር አቪ ዌይስማንን በመጥቀስ፣ የሚከተሉትን ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያ አጋርቷል።
"በሊባኖስ በተካሄደው ከባድ ጦርነት ምክንያት እጅና እግራቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ብዙ ናቸው። ይህ በእውነት፣ የአንደኛውና የሁለተኛውን የሊባኖስ ጦርነቶች ዘመን ያስታውሰኛል።"
4 330
🇮🇱❌🇮🇷 - የእስራኤል የጦር ሚኒስቴር
- የአሜሪካን አረንጓዴ መብራት ብቻ እየጠበቅን ነው። በመጀመሪያ እና ከሁሉም በላይ፣ የኻሜኒይን ሥርወ መንግሥት መወገድን እናጠቃልላለን።በ 12 ቀኑ ጦርነትም ይሁን በዚህኛው እንደታየው፣ የእስራኤል ጦር ብቻውን እንደ ኢራን ያለ አገርን መዋጋት አቅም የለውም። በዚህ ጦርነት ከአሜሪካ እና ከገልፍ አገሮች ጋር በአንድ ተጣምረውም፣ ኢራንን ሊያንበረክኩ ተስኗቸዋል። ምናልባት እስራኤል ልትዋጋና የበላይ መሆን የምትችለው በፍልስጤም እና በሊባኖስ ባሉ ሽምቅ ተዋጊዎች ላይ ሊሆን ይችላል። እሱም ቢሆን እስካሁን ልታጠናቅቅ ያልቻለችው ነው።
4 330
🇨🇺 — Havana አብርታለች።
በወራቶች ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ኩባ መብራቷ ተመልሷል።
የቬንዝዌላ መሪን ውድቀት ተከትሎ፣ የኩባ መንግሥት ይወድቃል በሚል ተስፋ፣ አሜሪካ ወደ ኩባ ምንም ነዳጅ እንዳይገባ እገዳ ጥላ ነበር። በዚህም የተነሳ ፋብሪካዎች እና እርሻዎች ሥራ ለማቆም ተገደዋል። ትምህርት ቤቶች አልነበሩም፣ ሆስፒታሎች ሥራ አቁመው ነበር፣ በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ ህመምተኞች፣ አብዛኞቹ ሕፃናት፣ ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ሲዘገብ ቆይቷል። በመጨረሻ ግን፣ በሩሲያው መሪ ፑቲን ትዕዛዝ፣ ነዳጅ የጫኑ መርከቦች የአሜሪካን እገዳ ጥሰው የዛሬ ሳምንት ኩባ ዳርቻዎች ደርሰው ነበር። በጊዜው፣ ከሩሲያ ጋር ሰጣ ገባ ላለመግባት የአሜሪካ ባሕር ኃይል ጣልቃ ከመግባት ተቆጥቧል።
"የሩሲያ ነዳጅ በኩባ ሆስፒታሎች ሕይወትን ታድጓል።"
4 330
- 🇺🇸 / 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ Truth Social -
‹‹ኢራን መሪዋ ማን እንደሆነ ለማወቅ በጣም ተቸግራለች! በቃ መሪያቸው ማን እንሆነ አላወቁትም! በጦር ሜዳ ላይ ክፉኛ በተሸነፉት "አጥባቂዎች" እና "ለዘብተኞች" (በእውነቱ ግን ለዘብተኛ ያልሆኑት) መካከል ያለው የርስ በእርስ ፍትጊያ መረን ለቋል። በሆርሙዝ ባሕር ላይ ሙሉ ቁጥጥር አለን። ከዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል ፈቃድ ውጭ የትኛውም መርከብ መግባትም ሆነ መውጣት አይችልም። ኢራን ስምምነት ማድረግ እስክትችል ድረስ፣ "በጥብቅ የታሸገ" ነው!! ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ስላደረጉ አመሰግናለሁ። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕ።"
4 330
🇮🇹🇩🇪 የአውሮፓ ሕብረት ከእስራኤል ጋር ያለውን የንግድ ስምምነቶቹን ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ ያቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ በጣልያን እና በጀርመን እምቢታዊ ምርጫ ውድቅ ሆኗል። ከሁለቱ አገሮች በስተቀር፣ ሁሉም የሕብረቱ አባላት እሺታቸውን የለገሱ ሰነድ ነበር።
4 330
🇱🇧 | Al - Manar፡ በ IDF ቁጥጥር ሥር ባለው/በተያዘው ደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ ካሉት መኖሪያ ቤቶች፣ የሞተር ሳይክሎች፣ የቴሌቪዥኖች፣ የሥዕሎች፣ የሶፋዎች እና የምንጣፎች መሰረቅን ጨምሮ መጠነ ሰፊ ዝርፊያ በጦሩ ተካሂዷል።
4 330
🇺🇸🇮🇹🇮🇷 የትራምፕ አስተዳደር፣ በመጪው የዓለም ዋንጫ FIFA ኢራንን በጣሊያን እንዲተካ ጠይቋል። ዕቅዱ፣ በትራምፕ እና በጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል የሚደረግ ጥረት ነው የተባለ ሲሆን፣ ይህ የሆነው ኢራን ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኗን በገለጸችበት ነው ሲል Financial Times ዘግቧል
4 330
🇺🇸⚡️የአሜሪካ የጦር ሚኒስቴር፣ Pete Hegseth, ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ ባለው አንድ ዓመት ውስጥ፣ የወታደሩን አመራር ሰንሰለታዊ እዝ በኃይል እያቀዣበረው ይገኛል። ታላላቅ ወታደራዊ አመራሮችን፣ የዛሬውን የባሕር ኃይል ሚንስቴርን ጨምሮ፣ ከአመራርነታቸው አስወግዷል። በአብዛኛው በ"ፖለቲካዊ ውገናቸው" ከሥራቸው ተባረዋል፣ ምንም እንኳ ሠራዊቱ ከማንኛም ፓርቲ ፖለቲካ የጸዳ አገራዊ ተቋም ቢሆንም።
4 330
- 🇮🇱 /🇱🇧/ 🇺🇳 በደቡባዊ ሊባኖስ በእስራኤል ወታደር የወደመው የኢየሱስ ክርስቶስ ሐውልት፣ በጣሊያን UNIFIL ወታደሮች በአዲስ መልክ ተጠግኖ ተተክሏል።
4 330
⚡️🇮🇷 ኢራን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ለፀጥታው ምክር ቤት በጻፈችው ደብዳቤ፡
- ዋሽንግተን የተባበሩት አረብ ኤሚሬትን ግዛቶች እና የአየር ክልልን ተጠቅማ በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ላይ ጥቃት እየፈፀመች ሲሆን፣ ዩናይትድ ስቴትስ አሁንም የተባበሩት አረብ ኤሚሬትን ግዛቶች ተጠቅማ መሳሪያ እየሰበሰበች እና እየተደራጀች ትገኛለች። በኢራን ላይ ለሚሰነዘር ሌላ ጥቃትም ግዛቷን ለአሜሪካ መጠቀሚያ አሳልፋ ሰጥታለች።
4 330
🇮🇶 የጦር ጀቶች በአሁኑ ሰዓት በኢራቅ ሰማይ ላይ እየታዩ ነው። ኢራን ላይ ጥቃት ደርሷል የሚሉ ሪፖርቶች እየወጡ ነው። አልተረጋገጠም!
4 330
🇺🇸❗️የአሜሪካ የጦር ሚንስቴር፣ Pete Hegisth, የባሕር ኃይሉን ሚኒስቴር፣ John C Phelan, ከሥልጣን አባሯል።
"ወደፊት ለሚገጥምህ መልካሙን እመኛለሁ።"
4 330
🇮🇱❗️እስራኤል Channel 14: "ሁለት የእስራኤል አየር ኃይል ወታደሮች፣ ለኢራን በመሰለል እና ስለ F-15ን ተዋጊ ጀቶች ሚስጥራዊነት ያለው መረጃ በማስተላለፍ፣ ተከሰዋል። ሁለቱ ወታደሮች፣ በቀድሞው የሠራዊቱ ዋና አዛዥ ሄርዚ ሃሌቪ እና ሚኒስትር ቤን-ግቪር ላይም መረጃ በመሰብሰብ ወንጀልም ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ናቸው።
