uk
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Відкрити в Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
4 307
Підписники
-124 години
-217 днів
-8630 днів
Архів дописів
🇺🇸 🇮🇱 ሰበር ዜና - የእስራኤል አየር ኃይል በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል። ምናልባትም፣ በኢራን ላይ ጥቃት ሊደርስ ከሆነ፣ በ 48 ደቂቃዎች ውስጥ የአሜሪካ ገበያዎች ሲዘጉ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። አሜሪካ እና እስራኤል በጥምረት ሊያጠቁ ይችላሉ።

🇺🇸 🇮🇱 ሰበር ዜና - የእስራኤል አየር ኃይል በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል። ምናልባትም፣ በኢራን ላይ ጥቃት ሊደርስ ከሆነ፣ በ 48 ደቂቃዎች ውስጥ የአሜሪካ ገበያዎች ሲዘጉ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። አሜሪካ እና እስራኤል በጥምረት ሊያጠቁ ይችላሉ።።

⚡️🇮🇷 የኢራን ምንጭ፡ በርካታ የጦር ጀቶች ከበስተ ምዕራብ አቅጣጫ ወደ ኢራን እየተጠጉ ነው።

🇮🇷⚡️IRGC፣ በኢርቢል ኢራቅ፣ የኩርዶችን ማዘዣ ጣቢያ በመደብደብ ላይ ነው፣ በርካታ ፍንዳታዎች ይሰማሉ።

🇮🇷🇺🇸⚡️የኢራን የፓርላማ ሚንስትር ጋሊባፍ፡ እኛ በዲፕሎማሲ ንግግር እናምናለን፣ ነገር ግን ሌሎች ቋንቋዎችንም አቀላጥፈን እንናገራለን። ቃል-ኪዳንህን የሰበርክ ቀን፣ ቋንቋችንን አቀላጥፈን ወ
🇮🇷🇺🇸⚡️የኢራን የፓርላማ ሚንስትር ጋሊባፍ፡ እኛ በዲፕሎማሲ ንግግር እናምናለን፣ ነገር ግን ሌሎች ቋንቋዎችንም አቀላጥፈን እንናገራለን። ቃል-ኪዳንህን የሰበርክ ቀን፣ ቋንቋችንን አቀላጥፈን ወደ ምናወራው እንቀይራለን።

🇮🇷⚡️🇮🇱🇺🇸 የዕብራይስጥ ሚዲያ፡ የእስራኤል ዳሰሳ፣ ትራምፕ በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ኢራንን እንደሚያጠቃ ያሳያል።

🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካ ሄሊኮፕተር ከሚሳዬል ይልቅ፣ በአጥፍቶ ጠፊ ሸሂድ ድሮን ነው ተመትቶ የወደቀው፣ እንደ መረጃዎች፣ አውቀው ይሁን በስህተት የመቱት አልታወቀም። በሌላ ዘገባ፣ ትራምፕ፣ ከበላዩ የኢራን መሪ ሙጅተባ ኻመኒይ ጋር እስከ አሁን መነጋገር ባለመቻሉ፣ ከፍተኛ ብስጭት ተሰምቶታል። Axios and NYT

🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ ትራምፕ ምላሽ ለመስጠት ዛተ፡- ትናንት ምሽት፣ ኢራናውያን በሆርሙዝ ባሕር ላይ ሲዘዋወር የነበረውን፣ እጅግ በጣም ዘመናዊ ከሆኑት Apache ሄሊኮፕተሮቻችን መካከል አን
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ ትራምፕ ምላሽ ለመስጠት ዛተ፡- ትናንት ምሽት፣ ኢራናውያን በሆርሙዝ ባሕር ላይ ሲዘዋወር የነበረውን፣ እጅግ በጣም ዘመናዊ ከሆኑት Apache ሄሊኮፕተሮቻችን መካከል አንዱን፣ በጥይት መትተው መጣላቸውን በታላቅ ወጦራችን ተገልፆልኛል። ሁለት አብራሪዎች ነበሩ፣ ሁለቱም ደህና እና ያልተጎዱ ናቸው። ቢሆንም፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለዚህ ጥቃት የግድ ምላሽ መስጠት አለባት። ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ስለሰጡን እናመሰግናለን!

🇮🇷🇺🇸 የአሜሪካ ባለስልጣናት፣ 'ፔንታገን፣ የኢራን ከመሬት ወደ አየር ሚሳኤል የአሜሪካውን AH-64 Apache ሄሊኮፕተር ትናንት በሆርሙዝ ወሽመጥ አቅራቢያ እንዲወድቅ ምክኒያት ሆኗል ወይ የሚለውን 'እየመረመሩ ነው' ብለዋል። 

🇮🇱 እስራኤል ሓዮም፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ "ምላሽ አለመስጠት የኢራንን አቋም ያጠናክራል" በሚል ሰበብ፣ ትራምፕ የእስራኤልን ጥቃት በኢራን ላይ እንዲፈቅድ አሳምኖታል።
🇮🇱 እስራኤል ሓዮም፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ "ምላሽ አለመስጠት የኢራንን አቋም ያጠናክራል" በሚል ሰበብ፣ ትራምፕ የእስራኤልን ጥቃት በኢራን ላይ እንዲፈቅድ አሳምኖታል።

🇺🇦 ዘለንስኪ፡ በአውሮፓ ዩክሬንን የሚስተካከል ጦር ሰራዊት ያለው ሀገር አለ ብዬ አላምንም። ዩክሬን አውሮፓን ከምትፈልገው በላይ፣ አውሮፓ ዩክሬን ያስፈልገዋል። አውሮፓን ከሩሲያ ቅዥብና የመጠበቅ አቅም ያላት ዩክሬን ብቻ ናት። በተቻለ ፍጥነት ኔቶን እንድንቀላቀል ይሁን!

🇮🇱❌🇮🇷 - የIDF ዋና አዛዥ ኢያል ዛሚር - IDF ወደ ኢራን እና ወደ ጦርነት ለመመለስ ንቃተ ህሊናውን እና አፋጣኝ ዝግጁነቱን ጠብቆ ቀጥሏል። ሁሉም የመከላከያ እና የጥቃት ሥርዓቶቻችን ን
🇮🇱❌🇮🇷 - የIDF ዋና አዛዥ ኢያል ዛሚር -
IDF ወደ ኢራን እና ወደ ጦርነት ለመመለስ ንቃተ ህሊናውን እና አፋጣኝ ዝግጁነቱን ጠብቆ ቀጥሏል።
ሁሉም የመከላከያ እና የጥቃት ሥርዓቶቻችን ንቁ እና ዝግጁ ነበሩ። ለዚያም ነበር፣ በእኛ ላይ የተተኮሱትን ጥቃቶች አክሽፈን ኢራንን በፍጥነት እና በኃይል ያጠቃነው። በኢራን ያደረግነው ጥቃት፣ ለበለጠ ጉልህ እና ከባድ ድብደባ ዝግጅት ነበር። ተመልሰን በኢራን ላይ ሌላ ከባድ እና ጥልቅ ጉዳት ለማድረስ ዝግጁ ነን።

🇺🇦 'የቀድሞ የቸልሲ ክለብ ባለቤት፣ የሮማን አብራሞቪች ብር፣ ለዩክሬን ሊሰጥ ይገባል' ዘለንስኪ ዘለንስኪ የብሪታንያ መንግስት በቅርቡ በባንክ የተያዘውን የአብራሞቪችን ገንዘብ ወስዶ ወደ ዩክሬን እንዲያስተላልፍ ሀሳብ አቅርቧል፣ ሲል ዘ ጋርዲያን ዘግቧል። ዘለንስኪ፣ የሩሲያው ባለ ሀብት፣ አብራሞቪች፣ ከቼልሲ እግር ኳስ ክለብ ሽያጭ የተቀበለውን $2.4 ቢሊዮን ፓውንድ ለዩክሬን እንዲሰጥ እና የአየር መከላከያ መቃወሚያዎች ለመግዛት እንዲውል ጠይቋል። ባሳለፍነው ሳምንት፣ ፑቲን፣ አብራሞቪችን ወደ ዩክሬን ከዘለንስኪን ጋር ጦርነቱን በማብቃት ዙሪያ እንዲያነጋግረው ልኮት እንደነበር እና እሱም ከዘለንስኪ ጋር ተገናኝቶ እንደተወያየ ይታወቃል። 

🇦🇱 የአልባኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢዲ ራማ፣ ለትራምፕ ቤተሰብ የተሸጠውን ጥብቅ ደሴት በተመለከተ የተነሳበትን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ የተሸጠው መሬት "ለሀብታሞች ብቻ ነው፣ ባለቤቶቹ እነሱ ናቸው፣ የአልባኒያ ሕዝብ አይደለም" ሲል በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ተናግሯል። በአልባኒያ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞው ያየለ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ በአስቸኳይ ሥልጣኑን እንዲለቅ በመጠየቅ ላይ ነው።

🇬🇧🇺🇸 - የዩናይትድ ኪንግደም የሀገር ውስጥ መሥሪያ ቤት፣ ጎግል እና አፕል ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ተጠቃሚዎችን ተደራሽነት፣ እንዲገድብ ጠይቋል። የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ወላጆች የልጆቻቸውን የመስመር ላይ ተደራሽነት እንዲገድቡ የሚያስችላቸውን ተግባራት (Age Restrictions) አስቀድመው እንዳቀረቡ መልሰዋል። ዩናይትድ ኪንግደም ይሄ በቂ አይደለም፣ ለአቅመ-አዳም ያልደረሱ ልጆች ከማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ በካምፓኒዎቹ እኝዲታገዱ እፈልጋለሁ፣ ካልሆነ በኩባንያዎቹ ላይ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች። *-*-*- በነገራችን ላይ፣ በአሜሪካም፣ በተለይ በካሊፎርኒያ ግዛት የሚገኙ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች (1280) እንደ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ፣ ሶሻል ሚዲያዎችን ከትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ስለማገድ እና ከ21 ዓመት በታች ያሉ በምንም ሁኔታ ለሶሻል ሚዲያ access እንደይኖራቸው በመገደብ ላይ ውሳኔ ሊያሳልፉ ጫፍ ደርሰዋል።

ኢራን ሐማስን ገሸሽ ያደረገችው የሚመስለኝ፣ ለእስራኤል እጅ በመስጠቱ ነው። በይፋ፣ መሸነፉን አምኖ ነጭ ባንዲራ በማውለብለቡ ነው። ኢራን ይሄን አልወደደችውም። እንደምናየው ኢራን ጋር 'እጅ መስጠት' የሚባል ነገር የለም። 'ድል ወይም ሞት' የሚለውን አባባል ትርጉም የወሰዱት፣ ከነ ጥሬ ትርጉሙ ነው። ለዚያም ነው የ12 ቀኑንም፣ ይኼኛውንም ጦርነት፣ እንደ በርካታ ምዕራባዊያን ተንታኞች ድምዳሜ፣ ያሸነፉት። እጅ ባለመስጠት። አስታውሱ፡ ለኢራን ማሸነፍ ማለት አለመንበርከክ ማለት ነው። ካልተንበረከኩ አሸንፈዋል። ለእስራኤል እና ለአሜሪካ ደግሞ መሸነፍ ማለት ኢራንን አለማንበርከክ መቻል ነው። ካላንበረከኳት፣ ተሸንፈዋል።

🇮🇷⚡️በአልሃዳዝ ቻናል የቀረበ ዘገባ ብዙዎችን አስገርሟል፡- የጋዛ ነዋሪዎች ኢራንን ክፉኛ እየወቀሱ ናቸው ያሉት። ኢራን በቤይሩት በዳሂህ ላይ ለደረሰው የቦምብ ጥቃት በሰጠችው ምላሽ እና እስራኤል በጋዛ ላይ ላደረሰችው የቦምብ ጥቃት ምላሽ ባለመስጠቷ ጋዛውያን ኢራን ላይ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ኢራን በድርድሯ ላይ ሊባኖስን አካትታ ሳለ፣ እኛን እንዴት አላካተተችንም? ሊባኖስን ቀይ መስመሬ ናት ስትል፣ እኛንስ ለምን ተወች? የሚል ነው የጋዛውያን ቅሬታ። ለኢራን በ12ቱ ቀን ጦርነት ወቅት ብዙ ድጋፍ አድርገንላታል የሚሉት ጋዛውያን፣ ኢራን በዚህ መልኩ የረሳቻቸው ስለመሰላቸው ተበሳጭተዋል። ለምንድነው ፍልስጤማውያን በነዚህ ድርድሮች ውስጥ ያልተካተቱት? ሲሉም ይጠይቃሉ። ኢራን ለዓመታት ሐማስን እና ፍልስጤማዊያንን ከማንኛውም አረብ ሀገር በላይ ስትደግፍ እና ድምጽ ስትሆንላቸው መቆየቷ ሊታወስ ይገባል።

🇮🇱🇺🇸🇱🇧⚡️— ሮይተርስ፡ ኔታንያሁ ለትራምፕ፡ 'ከኢራን ጋር ምንም ፍጠር ምንም፣ ሂዝቦላህ ዒላማችን ሆኖ ይቆያል።

🇮🇷🇺🇸 የእስራኤል አቋም ምንም ይሁን ምን፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ጋር ስምምነት መፈለጓን ትቀጥላለች -- ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ።