የቀጠናው ተመልካች
Відкрити в Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
4 334
Підписники
+124 години
+307 днів
-3930 днів
Архів дописів
4 334
+1
🇪🇹⚡️ዛሬ ምሽት 1:45 ገደማ፣ በሰመራ አፋር በሚገኘው የክልሉ ፕሬዝዳንት መቀመጫ ቤተ መንግሥት ውስጥ፣ ከባድ የድሮን ጥቃት ተሰንዝሯል - መሠረት ሚዲያ
4 334
🇷🇺🇩🇪🇰🇿 ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር በጣም ጥሩ ግንኙነት አለኝ። እና ዛሬ፣ ፕሬዝዳንት ፑቲን፣ እንደ ሩሲያ መሪ በአውሮፓ እና በዓለም ላይ በጣም ተቀባይነት ያለው የፖለቲካ ሰው እንደሆነ በታላቅ እምነት እናገራለሁ።"- የካዛኪስታን ፕሬዝዳንት፣ በበርሊን ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ከጀርመኑ መርዝ ጎን በአንድ መድረክ ቆመው።
4 334
🇸🇦 አሜሪካ፣ ከሁቲዎች ጋር የተገናኙ ምንጮች ግጭቱን ለማባባስ እና የሳዑዲ ዓረቢያን ወሳኝ መሠረተ ልማት ለማጥቃት ማስፈራራታቸውን ተከትሎ፣ የፔትሪዮት ሚሳይል ሲስተሞችን በድልድዮች፣ በኤሌክትሪክ ማመንጫ ጣቢያዎች፣ በወታደራዊ ሰፈሮች እና በውሃ ማጣሪያ ፋብሪካዎች ዙሪያ፣ በአዲስ መልክ እንደገና በማስቀመጥ ላይ ናት። ሒሳቡን፣ ሳዑዲ በሂደት የምትከፍል ይሆናል- CNN
4 334
🇺🇦⚡️🇷🇺 የዩክሬን ድሮን፣ በምዕራብ ሩሲያ ከሚገኝ አየር ማረፊያ ሊነሳ በማኮብኮብ ላይ የነበረን የሩሲያ Su-30SM ተዋጊ ጀትን፣ ለትንሽ ስቶታል።
*-*-*-
ድሩወን፣ አይ ድርወን። ላጥ አርጋው ነበር።
4 334
🇮🇱❌🇵🇸 — የእስራኤል ብሔራዊ ደህንነት ሚንስትር፣ ቤን-ገቪር፡
በተያዘው ዌስት ባንክ፡ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ብሆን፣ አካባቢዎች ሀ እና ለ፣ ልክ እንደ ሐ (ጋዛ) ይሆናሉ፣ መጥዳት አለበት። ሁሉም የኛ ነው፣ የፍልስጤም የሚባል ሀገር የለም። እዚህ መኖር አለብን - ሰፈሮችን እዚህ መገንባት አለብን። በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ስደትን ማበረታታት አለብን። እንደዚህ ያለ ፍላጎት አለ - በጁዳያ እና ሰማርያ (ዌስት ባንክ) የሚኖሩ ፍልስጤሞች፣ ብዙ ሀገር አላቸው፣ አረብ ሀገሮች። እዛ መሄድ ይችላሉ፣ ለመሄድ የሚፈልጉ ብዙ ሰዎችም አሉ። እኛ ግን እቺው ናት ሀገራችን፣ እዚህ ቤታችን ነው፣ እኛ ለዘላለም እዚህ ነበርን ፣ እናም እዚህ ለዘላለም እንኖራለን።
4 334
🇪🇹⚡️ሰበር ዜና!
ዛሬ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ የሰመራ የድሮን እና የሚግ አየር ማረፊያ የአየር ጥቃት እንደደረሰበት ምንጮች ከስፍራው አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ የባህርዳር አየር ሀይል እና መኮድ ዛሬ ዘጠኝ ግዜ የአየር ጥቃት እንደረሰበትና ከዚሁ መካከል ሁለቱ የሮኬት ድምጽ እንደሆነ የአይን እማኞች ገልፀውልናል።
ትላንትና እሁድ እለት የቢሾፍቱ ሀረር ሜዳ፣ የኮምቦልቻና የባህርዳር አየር ሀይል ግቢዎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ጥቃት መፈፀሙና ሰብአዊና የንብረት ውድመት ማስከተሉ ይታወቃል - Zara Media
*-*-*-
በዓለም ላይ ያሉ የጦር አውደ ውጊያቸው፣ ዘመን አፈራሽ የጦር ቴክኖሎጂዎችን በቀላሉ በሚያገኙና በሚጠቀሙ አካላት ምክኒያት፣ አንድ አካል በብቸኝነት፣ ብቻውን፣ ሲቀማጠልበት የቆየውን 'የውጊያ የበላይነት' በማጥበብ ከፍተኛ ትራንስፎርሜሽንን አምጥተዋል።
በኢትዮጵያ፣ በአሁኑ ሰዓት እያየን ያለነው ይህን ነው። መደበቅ የማይቻል ገሃዳዊ ሃቅ የሆነው፣ ይኸው፣ የኢትዮጵያ አገዛዝ የአየር የበላይነቱ compromised እንደሆነበት ነው።
ጥምረት ፈጠርን ያሉ ኃይሎች፣ በቀናቶች፣ በአየር እየተገዳደሩት ነው። አገዛዙ የጦር አይሮፕላኖቹን፣ ጀቶቹን እና ድሮኖቹን ከአየር ቤዙ ለማሸሽም ተገዷል።
ይሄ፣ አገዛዙ በአስደንጋጭ ፍጥነት የተቀማው እና የጠበበው የበላይነት ነው።
የኛ ሰው፣ በፈለገ ጊዜ፣ ቴክኖሎጂን ከሌሎች በፈጠነ ሁኔታ የመረዳት እና የመጠቀም ፍጥነት አለው። ይህን አውቃለሁ! በሌሎች ክፍላተ ዓለማት እየተደረጉ ያሉ ጦርነቶችንም በትኩረት እከታተላለሁ። በኢትዮጵያ በጥምረት ኃይሎች ዘንድ እያየሁት ያለሁት የድሮን አጠቃቀም ብቃት እና የደረጃ ከፍታ፣ ከዚህ አንፃር፣ አስደማሚ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች በርካታ ዓለም አቀፋዊ የውጊያ አንጃዎች በልጦብኛል።
በበርማም፣ በሩዋንዳ ኮንጎም፣ በባላቹስታን ፓኪስታንም፣ ጦርነቶች አሉ፣ ለቴክኖሎጂዉም ከእኛ በተሻለ አክሰሱ ይኖራቸዋል፣ ቅርብም ናቸው፣ ግን እንዲህ በኢትዮጵያ እያየነው እንዳለነው፣ በቀናቶች፣ ቴክኖሎጂውን አዳፕት አድርገው በዚህ ልክ ሲጠቀሙበት አላየሁም። የአገዛዞቻቸውን በርካታ ዓለም አቀፋዊ አየር ማረፊያዎችን እና ጦር ቤዞችን በመምታት፣ ቴክኖሎጂውን ተጠቅመው የሰማዩን የባለቤትነት የበላይነት፣ እንደዚያው፣ ሲገዳደሩም አላየሁም።
4 334
🇪🇹⚡️ሰበር ዜና!
ዛሬ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ የሰመራ የድሮን እና የሚግ አየር ማረፊያ የአየር ጥቃት እንደደረሰበት ምንጮች ከስፍራው አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ የባህርዳር አየር ሀይል እና መኮድ ዛሬ ዘጠኝ ግዜ የአየር ጥቃት እንደረሰበትና ከዚሁ መካከል ሁለቱ የሮኬት ድምጽ እንደሆነ የአይን እማኞች ገልፀውልናል።
ትላንትና እሁድ እለት የቢሾፍቱ ሀረር ሜዳ፣ የኮምቦልቻና የባህርዳር አየር ሀይል ግቢዎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ጥቃት መፈፀሙና ሰብአዊና የንብረት ውድመት ማስከተሉ ይታወቃል - Zara Media
*-*-*-
በዓለም ላይ ያሉ የጦር አውደ ውጊያቸው፣ ዘመን አፈራሽ የጦር ቴክኖሎጂዎችን በቀላሉ በሚያገኙና በሚጠቀሙ አካላት ምክኒያት፣ አንድ አካል በብቸኝነት፣ ብቻውን፣ ሲቀማጠልበት የቆየውን 'የውጊያ የበላይነት' በማጥበብ ከፍተኛ ትራንስፎርሜሽንን አምጥተዋል።
በኢትዮጵያ፣ በአሁኑ ሰዓት እያየን ያለነው ይህን ነው። መደበቅ የማይቻል ገሃዳዊ ሃቅ የሆነው፣ ይኸው፣ የኢትዮጵያ አገዛዝ የአየር የበላይነቱ compromised እንደሆነበት ነው።
ጥምረት ፈጠርን ያሉ ኃይሎች፣ በቀናቶች፣ በአየር እየተገዳደሩት ነው። አገዛዙ የጦር አይሮፕላኖቹን፣ ጀቶቹን እና ድሮኖቹን ከአየር ቤዙ ለማሸሽም ተገዷል።
ይሄ፣ አገዛዙ በአስደንጋጭ ፍጥነት የተቀማው እና የጠበበው የበላይነት ነው።
የኛ ሰው፣ በፈለገ ጊዜ፣ ቴክኖሎጂን ከሌሎች በፈጠነ ሁኔታ የመረዳት እና የመጠቀም ፍጥነት አለው። ይህን አውቃለሁ! በሌሎች ክፍላተ ዓለማት እየተደረጉ ያሉ ጦርነቶችንም በትኩረት እከታተላለሁ። በኢትዮጵያ በጥምረት ኃይሎች ዘንድ እያየሁት ያለሁት የድሮን አጠቃቀም ብቃት እና የደረጃ ከፍታ፣ ከዚህ አንፃር፣ አስደማሚ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች በርካታ ዓለም አቀፋዊ የውጊያ አንጃዎች በልጦብኛል።
በበርማም፣ በሩዋንዳ ኮንጎም፣ በባላቹስታን ፓኪስታንም፣ ጦርነቶች አሉ፣ ለቴክኖሎጂዉም ከእኛ በተሻለ አክሰሱ ይኖራቸዋል፣ ቅርብም ናቸው፣ ግን እንዲህ በኢትዮጵያ እያየነው እንዳለነው፣ በቀናቶች፣ ቴክኖሎጂውን አዳፕት አድርገው በዚህ ልክ ሲጠቀሙበት አላየሁም። የአገዛዞቻቸውን በርካታ ዓለም አቀፋዊ አየር ማረፊያዎችን እና ጦር ቤዞችን በመምታት፣ ቴክኖሎጂውን ተጠቅመው የሰማዩን የባለቤትነት የበላይነት፣ እንደዚያው፣ ሲገዳደሩም አላየሁም።
4 334
🇪🇹⚡️የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ዋና ወታደራዊ ቃል አቀባይ፣ አርበኛ አበበ ሙላቱ፣ አሁናዊ ሁኔታዎች በተመለከተ አጠር ያለ ማብራሪያ ሰጥቶ አይተናል።
4 334
🇪🇹⚡️አሁን እንደሰማነው፣ በጥምር ጦሩ በባሕር ዳር አየር ኃይል ዲቪዥን ላይ ጥቃት ካደረሱት አምስት ካማካዚ ድሮኖች ውስጥ፣ ሦስቱ ዒላማቸውን መምታት የቻሉ ሲሆን ሁለቱ በአየር መቃወሚያ ተመትተው ወገልሳ ጫካ ላይ ወድቀዋል።
በዚያ ያለ ምንጫችን፣ በባሕር ዳር በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ፣ "ፍንዳታዎች እንደ ፈንዲሻ እየተንጣጡ ነው" ብሎናል።
4 334
🇪🇹⚡️ባህርዳር፣ ዛሬ ቀን 6:55 በኢትዮጵያ አቆጣጠር፣ ተጨማሪ የድሮን ጥቃቶች መደረጋቸው ታውቋል። ጥቃቶቹ መኮድና የባሕር ዳር አየር ኃይል ዲቪዥን ላይ ያተኮሩ ናቸው ተብሏል።
እንደ ምንጮች ዘገባ፣ በተቋሙ ዙሪያ አምስት ከባባድ ፍንዳታዎችን መስማታቸውን ነግረውናል።
ባህርዳር ያሉት ባለስልጣናት መካከል ከባድ ጭንቀት ተፈጥሯል።
በተመሳሳይ በማይጨው ከተማም የድሮን ጥቃት መፈፀሙ ተሰምቷል።
4 334
🇸🇦⚡️🇾🇪 በየመን፣ ሳዑዲ በአጋፋሪነት የምትመራው PLC አንጃ፣ በአንሷረላህ (ሁቲ) ላይ ክተት አወጀ።
አቅሙ ለውትድርና የደረሰ የየመን ሰው ለሳዑዲ PLC ይቁም! ተብሏል።
በተመሳሳይ፣ ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ ዋና ሙፍቲ የሆኑት፣ አባ ሳልህ ቢን ፈውዛን አል ፈውዛን፣ ለሳዑዲ መዋጋት 'ከታላላቅ ሃይማኖታዊ ግዴታዎች ተርታ የሚሰለፍ ነው' በማለት፣ የሳዑዲ ወታደሮች ህይወታቸውን እስከ መሰዋት እንዲዘጋጁ አሳስበው፣ በየመን ላይ እሳቸውም 'ክተት' አውጀው እንደነበር ይታወሳል።
4 334
🇷🇺⚡️🇺🇦 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ ሩሲያ ጥቃቶቿን በዩክሬን ዳታ ሴንተሮች እና የቴሌኮም መሠረተ-ልማቶች ላይ አድርጋለች።
ባለፉት ጥቂት ቀናቶችም በከፍተኛ ሁኔታ ዳታ ሴንተሮችን በጀራን ድሮኖች አጥቅታለች። ይህም፣ በቴክኖሎጂ ላይ በስፋት በተመሠረተው የዩክሬን ጦር እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ማዛባትን ፈጥሯል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ ለሚሊዮን ዩክሬንያዊያኖች የስልክም ሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት ቆርጦባቸዋል።
4 334
🇮🇱🇦🇪 ዛሬ ቀን ላይ፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ፣ ከሙሐመድ ቢን ዘይድ ጋር ለመገናኘት ወደ አረብ ኤምሬትስ ገብተዋል።
እንደ እስራኤሉ ቻናል 13 ዘገባ ከሆነ፣ ስብሰባው ከ6 ሰዓታት በላይ የዘለቀ ሲሆን በዋናነት ኢራን ላይ ያተኮረ ነበር።
4 334
🇺🇦🇷🇺🇰🇵⚡️ — የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ፡
የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ወደ ሩሲያ ስለ መሰማራታቸውም አዲስ መረጃ አለን። በአሁኑ ጊዜ ከ8,000 በላይ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በሩሲያ ግዛት ውስጥ ይገኛሉ። በተጨማሪም ሌሎች 10,000 ወታደሮችን ለማሰማራት ዝግጅት እየተደረገ ነው - ለስልጠና እና በቀጣይ ወደ ሩሲያ ለመሰማራት- በሰሜን ኮሪያ እየተመረጡ ያሉ ተጨማሪ ተዋጊዎች አሉ። በምላሹ ሩሲያ ለሰሜን ኮሪያ እየከፈለቻቸው ያለው፣ በቴክኖሎጂ ክህሎት ስልጠና ነው። በአሁኑ ጊዜ በሰሜን ኮሪያ በሩሲያ ቴክኒካል ድጋፍ የሸሂድ ዓይነት የጥቃት ድሮኖች ማምረት ተችሏል።
4 334
🇾🇪🇸🇦🇵🇸⚡- የአንሷሩላህ (ሁቲ) ከፍተኛ ባለስልጣን እና የዳማር ግዛት አስተዳዳሪ፣ መሐመድ አል ቡኻይቲ፣ ጦራቸው በአንሷሩላህ-ሳውዲ ዓረቢያ ጦርነት፣ የሐማስን ሽምግልና ጥረት መቀበላቸውን ተናገሩ።
-*-*-
ሐማስ ሽማግሌ ሆኖ ሲከሰት።
ሳዑዲ የጠበቀችው እርግጠኛ ነኝ፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ዓለም አቀፉ ኃያላኖች ያስታርቁኛል፣ ያባብሉኛል ነበር፣ ያው ያላት ደረጃም፣ ገንዘብም ከፍ ያለ ስለሆነ …
4 334
🇪🇹⚡️የኢትዮጵያ አገዛዝ በኤርትራ ተወርሬአለሁ፣ ማለቱ ተሰማ። የአፋሩ ርዕሰ መስተዳደር፣ አቶ አወል አርባም፣ "ነገሮች ከአቅማችን በላይ ሆነዋል፣ የሚመለከተው አካል ይድረስልን" ሲሉ ተማፅነዋል - አል ጀዚራ።
የኢትዮጵያ አገዛዝ ምሽቱን 'ኤርትራ ወረረችኝ' ማለቱ ተሰምቷል። ይህን ያለው በአፋር በኩል የኤርትራ ጦር ድንበር ጥሶ በመግባት ከአማፂያኑ ጋር እየተባበረብኝ ነው ብሎ ባቀረበው አቤቱታ ነው። የጥምረት ኃይሉ ብሎም ኤርትራ፣ ይህን የአገዛዙን ክስ ውድቅ አድርገው፣ "የውስጥ ችግሮቹን በተለመደው መልኩ በውጭ አካላት ላይ ለማላከክ የሚጥር" ብለውታል።
በሌላ ዜና፣ በሀገሪቱ ባሉ የተለያዩ አየር ማረፊያዎች ላይ ከትናንት ጀምሮ በተወሰዱ ወታደራዊ እርምጃዎች የተነሳ፣ ገሚሱ በረራ ያቋረጡ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ፣ እንደ ባሕር ዳር አይነቶች፣ ሙሉ ድሮኖቻቸውን እና ኦፕሬተሮቻቸውን ለመደበቅ ወደ ሌላ ቦታ ሲያዘዋውሩ ውለዋል ተብሏል። በዚህም፣ ዛሬ ምንም የድሮን ጥቃት በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ በአገዛዙ ሳይሰነዘር ውሏል።
*-*-*-
አገዛዙ ኤርትራን እየከሰሰ ያለው፣ ኤርትራን ሊደበድብ ፍላጎት ስላለው ነው። አርፎ ቢቀመጥ ይሻለዋል፣ እንደ "ቀጠናው ተመልካች" ምልከታ።
አሜሪካ ከኤርትራ ላይ ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ ማዕቀቧን አንስታለች። በቀይ ባሕር ላይ ባላት ፍላጎት፣ ከኤርትራ ጋር ግንኙነቷን በከፍተኛ ሁኔታ እያደሰች ነው፣ ስለዚህ፣ እንዲህ ያለው የአብይ አሕመድን እርባና ቢስ ወሬና ክስ፣ እንደሌላው ጊዜ ቁጭ ብላ የምታይ አይመስለኝም።
አገዛዙ በዚህ ክስ ምናልባት ተስፋ ያደረገው ሌላ ነገር፣ እነ ኤሜሬትና ኳታር እገዛቸውን ከፍ ያደርጉልኛል፣ አስፈላጊ ከሆነም የመን እንዳደረጉት፣ ሰራዊታቸውን በተወሰነ ያስገቡልኛል፣ ብሎ ነው። ይሄ ሩቅ ቢመስልም፣ ኤሜሬትና አረቦች እሱን ለማዳን አሁን ላይ በወታደራዊ አይሮፕላኖች እያጋዙለት ያለው ቀለሃና ቦንብ ሲታይ፣ ነሀሩ ሩቅ አይሆንም።
የሆነው ሆኖ፣ የአብይ አገዛዝ ጉዳዩን አጡዞ ቀጠና አቀፋዊ ጦርነት ለማድረግ እየጣረ ይመስላል።
4 334
Repost from Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
• የርግቤ የዕለቱ ሪፖርት…
• የራያ አሁናዊ ሁኔታ
"…ስለዘገየሁ ይቅርታ እጠይቃችኋለሁ። የዘገየሁት ሸለብ አድርጎኝ ነው። ትናንት ምሽት በዘመድ ቴቪ በነበረኝ መርሀ ግብር ላይ ቆይቼ እንደጨርስኩ ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ ጋር ቀጠሮ ነበረን እና እዚያ ላይ ተሳትፌ አርፍጄ ነው ሊነጋ ሲል ለመተኛት የሞከርኩርከት። ጥቂት ተኝቼ ጉዳይ ስለነበረኝ ተነስቼ እየተጨናበስኩ ሄድኩ፣ ጉዳዬን ጨርሼ የተመለስኩት ከምሳ ሰዓት በኋላ ነበር። ምሳ በልቼ ግን ዓይኔን መግለጥ ቢያቅተኝ ጊዜና ጥቂት ሸለብ ልበል ብዬ ጋደም አልኩ። ተኛሁ፣ ተኛሁ በቃ አሁን ገና መንቃቴ ነው። ራሴን ስታዘበው ግን ከእርጅናው ይሁን ከጭንቀት መጥፋቱ ብቻ አላውቅም እንቅልፋም ሆኜአለሁ። ስተኛ ደግሞ የሞት ያህል ነው የምተኛው። እግዚአብሔር ይመስገን።
• ወደ ሪፖርቱ ስንመለስ…
"…እስከአሁን በደብረ ዘይትም፣ በኮምቦልቻ እና በባህርዳር አየር ማረፊያዎች ላይ ተደረገ ስለተባለው የድሮን ጥቃት ከወፎቼ የሰማሁት መረጃ፣ የደረሰኝም ሪፖርት የለም። ከሱዳን የመገናኛ ብዙሃን እና ከእንግሊዛዊው ማርቲን ፕላውት በቀርም ዘገባ የሠራ አላየሁም። የአየር በረራዎች ግን ላሊበላን ጨምሮ ባህርዳር፣ ሰመራ እና ኮምቦልቻ መቆማቸውን ሰምቻለሁ። የኮምቦልቻው ቆይቶም ቢሆን ዛሬ መጀመሩን የላሊበላው ግን የአሜሪካው አምባሳደር ማሲንጋ ባለፈው ላሊበላ ሄዶ ከጥቃት ካመለጠ ወዲህ በረራ ማቆሙን፣ መቀሌ በሕወሓት ቁጥጥር ስር በመግባቱ ምክንያት በረራ ሲቆም አክሱም እና ሽሬ ደግሞ አገዛዙ ራሱ በረራ ማቆሙን ሰምቻለሁ።
" …ጦርነት አይደል? የእርስ በእርስ ጦርነት። አዎ በጦርነት ወቅት ተፋላሚዎቹ እጠቃበታለሁ የሚሉትን ስፍራ ማጥቃት የተለመደ እና ተገቢ፣ ተፈጥሮአዊ ቢሆንም የሕዝብ ማመላለሻ አውሮጵላን ጣቢያዎችን እና የስቢል ሮጱላዎችን መምታትን እኔ ዓልደግፍም፣ በዓለምአቀፍም ሕግ ወንጀል ነው። መምጣት ካስፈለገ የድሮን መነሻ፣ የአየር ኃይልን፣ ወታደራዊ ቤዞችን መምጣት አያስኮንንም። እንጂ ሌላው ትክክል አይሆንም። አገዛዙ የሲቢል አውሮጵላን ተጠቅሞ በረራ የሚፈጽም ከሆነ፣ አይደለም አይሮጵላን በቀይ መስቀል እና በቀይ ጨረቃ መኪኖች የጦር መሳሪያ ለታጠቁ አማጽያንም ሆነ አገዛዙ ራሱ አራዳ አራዳ ተጫውቶ ሲጠቀም ቢገኝ እና ተመተው ቢወድቁ መቺው ተጠያቂ አይሆንም።
"…ለምሳሌ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አውሮጵላን የጦር መሣሪያ ማመላለሱ ተደርሶበት አውሮጵላኑ ቦሌም ይሁን ድሬደዋ፣ ባህርዳርም ይሁን ደብረ ዘይት ጎንደር ተፈጥሮ ቢታይ እና አማጽያኑ ቢያደባዩት ቢጸድቁ እንጂ አይኮነኑም። እናም አገዛዙ በሲቢል አውሮጵላን ጣቢያ ውስጥ የድሮንም፣ የወታደርም፣ የጦር መሳሪያም፣ የጦር ሂሊኮፕተርም ሆነ ጀቶች ማንቀሳቀስ የለበትም። ሲያንቀሳቅስ በመረጃ ተገኝቶበት ቢመታ ግን ተጠያቂው ራሱ አገዛዙ ይሆናል ማለት ነው። ምንም ዓይነት ከጦር ጋር የተያያዘ ነገር ሳይኖር የሲቢል አየር ማረፊያዎችን መምጣት ግን አደገኛ የጦር ወንጀል ነው።
"…ይሄን ካልን ዘንዳ በቀጥታ ወደ ራያ ሰሜን ወሎ ቤተ ዐምሓራ ሪፖርት እናምራ።
👉 አገዛዙ ወደ ቆቦ እና ወደ ዋጃ ወስዶት የነበረውን ተተኳሽ እና አንዳንድ ቁሳቁሶች ወደ ወልዲያ እና ወደ ሃራ እየመለሰ መሆኑ ታይቷል። ይሄን የሚያደርገው እና የጦር መሣሪያዎቹን ወደ ኋላ የሚመልሰው ምን ቢገጥመው ነው ? ምንስ አስፈርቶት ነው ?ለሚለው ግን እርግጠኛ የሆነ መልስ እስከአሁን የለም።
👉 አገዛዙ እኔ ከእንቅልፌ እስከነቃሁበት ሰዓት ድረስ አላማጣ እንዳልገባ ሲሆን የነበረኝ መረጃ ነገር ግን ቤተሰቦቻቸው ዓላማጣ ከሆኑ ሰዎች በደረሰኝ መልእክት መሠረት አገዛዙ ወደ አላማጣ መግባቱን ካደረሱኝ፣ መረጃዎች ለመረዳት ችያለሁ። "በዘፈቀደ በተተኮሱ ከባድ መሳሪያዎች ብዙ ንፁሐን ሰዎች በአላማጣ መጎዳታቸውን የነገሩኝ ሲሆን፣ የኢንተርኔት አገልግሎት በአላማጣ በመቋረጡ ምክንያት መረጃዎች እንደልብ ሊወጡ አለመቻላቸውም ነው የሰማሁት። ይሄንን በነገው ዕለት ወፎቼ የሚያጠሩት ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
👉 የትብብሩ ኃይሎች ገዤ መሬቶችን እንደያዙ የኦሮሙማውን ኃይል ከነ ስንቁና ትጥቁ ወደ ውስጥ እየሳቡት መሆኑ እየገባው የመጣው አገዛዙ እንደለመደው ተንደርድሮ ወጥመድ ውስጥ መግባቱን አለመመርጡንም የወፎቼ ግምገማ ያመለክታል። ይሄ የኮምቦልቻው፣ የባህር ደሩ፣ የደብረ ዘይቱና የኮምቦልቻው በወልቃይትም በኩል ያለውን የአገዛዙ የአየር መቃወሚያ በድሮን ተመትቷል የሚለው ያልተረጋገጠ ወሬም ከተሰማ በኋላ እስከ አሁን በአየር ላይ ብልጫ የነበረው፣ በድሮንም ይቀጠውጥ የነበረው ኦሮሙማው ውሎውን አንድም ቦታ ድሮን ያለማንቀሳቀሱ ብቻ ሳይሆን ተኩስ ያለመግጠሙም ነው የተነገረው። ይሄ ደግሞ የድሮኑ ዜና እውነት ነው ወደሚለው ያመራናል ማለት ነው።
👉 ትናንት በወልዲያ ዙሪያ እዜት ላይ የሆነው ነገር እና የቆንጆዎቹ የድል እንቅስቃሴ፣ የምሽግ ሰበራው ያላማረው አገዛዙ ወደፊት ከመግፋት ይልቅ ወደ ኋላ ወልድያን ማየቱን መመርጡን የወፎቼ መረጃ ያመለክታል። ተተኳሽ ወደ አላማጣ ወደፊት መሄድ እንጂ ወደ ኋላ ወደ ወልድያ መመለሱ የሚያመላክተው አንዳች ነገር እንዳለ ነው የሚያሳየው።
👉 ወፌን የባህርዳሩን ጉዳይ እንዳታጣራ ልኬያት ነበር። እሷ በቦታው የነበረች ባይሆንም ጓደኞቿን ጠይቃ እንዲህ የሚል መረጃ ልካለች። መረጃውም እንዲህ ይነበባል። "ትላንት ማታ 5:30 አካባቢ ከባድ ዝናብ መጥቶ ነበር። ሆኖም ዝናቡ ከመዝነቡ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት ቢበዛ 3 ደቂቃ በፊት አንድ የፍንዳታ ድምጽ ተሰምቶ ነበር። ከዚህ የፍንዳታ ድምጽ በኋላ ወዲያውኑ ከፍተኛ ነጎድጓድ እና መብረቅ አዘል ከባድ ዝናብ መዝነብ ጀመረ። በዚህም ተደጋጋሚ መብረቅ ነበር። ነገር ግን የመጀመሪያው መብረቅ ይሁን ሌላ ፍንዳታ ለማወቅ አልቻልኩም። እዉነት ለመናገር በወቅቱ ከባድ መሳሪያ የተተኮሰ ነበር የመሰለኝ ግን ወዲያውኑ ከባድ እና መብረቅ የበዛበት ዝናብ መጣል ጀመረ። ከፍንዳታ ድምፅ በኋላ ወዲያው ነጎድጓድ እና መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ መዝነቡ የፍንዳታ ድምፁን ምንነት ለማረጋገጥ አልተቻለንም ብለዋል።
• አጠቃላይ የራያ አሁናዊ ሁኔታን በተመለከተ…
1ኛ፦ ከጎብየ በቅርብ ርቀት በሚገኘው "ካራይንሳ" በሚባል ቦታ አገዛዙ ባከማቸው ከባድ መሳሪያ ላይ በትናንትናው ዕለት በአጥፍቶ ጠፊ ድሮን መመታቱ እና ከባድ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።
2ኛ፦ ቆንጆዎቹ ጥሙጋ አካባቢ ያለውን ከፍ ያለ ገዥ ቦታ እና አላማጣ ወጣ ብሎ የሚገኘውን "ግራካሶ" የሚባል ሰንሰለታማ የሆነ ቦታ እንደያዙ እና አገዛዙ በአላማጣ አቅራቢያ ላይ ሆኖ ልግባ ወይስ ልመለስ በሚል ሁለት መንታ መንገድ ላይ እንደሆነ (አንዳንዶችም አላማጣ ገብቷል እንደሚሉ) ሁለት መረጃ ነው ያለው። ከላይ እንደተገለፀው የአላማጣን ኔትዎርክ አገዛዙ ስላጠፋው በዚህ ዙሪያ የተሟላ ሪፖርት ከቦታው ሲገኝ መረጃው ይደርሳችኋል።
3ኛ፦ በመኾኒ እና በባላ፣ በጨርጨር እና ባንድራ በሚባሉ አካባቢዎችም ከቆንጆዎቹ በኩል ከፍተኛ ዝግጅት ስለተደረገ በዚህ መስመርም አገዛዙ ሊሞክረው እንዳልፈለገ የወፎቼ ሪፖርት ያመለክታል።
4ኛ፦ አሁን ከመሸ መነሻቸውን ከወልዲያ ያደረጉ ለቁጥር የሚያታክቱ ባዶ አውቶቡሶች እና የተለያዩ ምንም አይነት ዕቃ ያልጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ዋጃ በኩል እየተጓዙ ነው። ይሄ እንግዲህ አገዛዙ ወደ ፊት ወደ መቀሌ ሊንቀሳቀስ ይሆን ወይስ አመሻሹን ሰው ሳያየው ወታደሮቹን ጭኖ ወደ ኋላ ሊያፈገፍግ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። መልሱን ነበነገው ዕለት አብረን የምናየው ይሆናል።
"…ትብብሩ በአፋር በኩል እየገሰገሰ ወደፊት እየሄደ ሲሆን በዚሁ ግስጋሴው ከቀጠለ እና ዋነኛውን የኢትዮጵያ ደም ስር የኢትዮ ጅቡቲን መስመር ከቆረጠ፣ በሸዋ ያለው ኃይልም በደብረ ብርሃን መስመር 68 ኪ ሜትር፣ በኦሮሚያ ድንበር 10 እና 15 ኪሎ ሜትሮች ላይ መቀመጡ፣ በፍቼ ሰላሌ ብቅብቅ ማለቱ በቅርቡ ለታቀደው ድንገቴ ማዕበል ዘመቻ ምልክት እንደሚሆንም ተነግሯል። ትብብሩ የሚለው ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ሸዋ ያለው፣ እየገባ ያለው የአገዛዙ ጦር መውጣት የለበትም ባዮች ናቸው።
• ለዛሬ በዚህ አበቃሁ። በነገው ዕለት "የቤተ መንግሥቱን ሌባ ሪፖርት እና የሊቃውንተ ኢትዮጵያን አስደማሚ ትንተና በርእሰ አንቀጽ መልክ አዘጋጅቼ ከምስጋና በኋላ አደርሳችኋለሁ። እስከዚያው ድረስ ባለፈው ዓመት ጥር 27/2018 ዓም ሊቃውንተ ኢትዮጵያ በርእሰ አንቀጽ መልክ የጻፉላችሁን ""…ተንሥእ ሰሜን ወነዓ ደቡበ፤ ሰሜን ሆይ ተነሥ ደቡብም ና። መኃ 4፥ 16" በሚል ርእስ የቀረቡላችሁን እያነበባችሁ ጠብቁኝ። https://t.me/ZemedkunBekeleZ/34011
"…በተረፈ በአጠቃላይ ከትናንቱ የድሮኖች ጥቃት በኋላ ዛሬ ራያ አካባቢ በሰማዩም በምድሩም የነበረው ድብልቅልቅ ፀጥ ረጭ ብሎ ውሏል። ዛሬ ጭራሽ ውጊያም የለም። አገዛዙ ተጨንቋል። ሽመልስ አብዲሳ በግድ የተሾመ ይመስል አኩርፏል። ለጊዜው ያለው ሁኔታ ይሄንን ይመስላል። አዲስ ነገር ካለ በሰበር ወደ እናንተ ይደርሳል።
• ድል ለዐማራ ፋኖ
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ
• አዛኜን ዐማራ ድብን አድርጎ በዝረራ ያሸንፋል።
4 334
🇪🇹⚡️BBC:
ሰባት የኢትዮጵያ ታጣቂ ቡድኖች፣ ለምን ተዋሃዱ? ዓላማቸውስ፣ ምንድን ነው? BBC ጠይቋል። በአንድ ወቅት በጠላትነት ይፈላለጉ የነበሩ ኃይሎች፣ ዛሬ 'ለሕልውናችን መቀጠል' በሚል ጥላ ሥር አንድ ሆነዋል። እነዚህን ኃይሎች ወደ አንድ ማምጣቱ በራሱ፣ እጅግ ከባድ ሥራ ቢሆንም፣ ትልቁና ዋናው ፈተና፣ አንድነታቸውን በዘላቂነት ያስቀጥላሉ ወይ? የሚለው ነው። ይህን ወደ ፊት እናያለን። ዓላማቸውን ጠይቀናል፡ በሚሊዮኖች በሚቆጠር የንፁሐን ደም የጨቀየውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን አገዛዝ ማስወገድ፣ የሽግግር መንግሥት ማቋቋም እና አዲስ ሕገ-መንግሥት መቅረጽ እንደሆነ ነግረውናል።
4 334
🇪🇹⚡️የሱዳን ጦር፣ ሱዳን በኢትዮጵያ የጸረ-አገዛዝ ትግሉን እየደገፈች ነው የሚለውን የኢትዮጵያን ክስ ውድቅ አደረገች - Sudan Tribune
የሱዳን መንግሥት ጦር ኢታማዦር ሹም ቃል አቀባይ፣ አሲም ወሃድ አብዱልወሃብ፣ የኢትዮጵያን ክስ "መሰረተ-ቢስ እና አገዛዙ የገባበትን የውስጥ ቅርቃር በውጭ ኃይል ላይ ለማላከክ ያቀረበው ሰበብ" በማለት ክሱን አጣጥሏል።
አንዴ ሱዳንን፣ ሲያሻው ኤርትራን፣ በሌላ ጊዜ ግብፅን፣ እያለ ጎረቤቶቹን የሚነክሰው ኃይል፣ ለችግሮቹ ወደ ውስጡ ይመልከት ብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ የኢትዮጵያ አገዛዝ እኩይ እጅ፣ የሱዳን አፈንጋጮችን (RSF) በተጨባጭ በመደገፍ፣ በሱዳን ሕዝብ ላይ ሰቆቃን ያራዘመ መሆኑ መረሳት የለበትም ብሏል።
4 334
🇪🇹⚡️የጥምረቱ አባል፣ የትግራይ አማፂያን፣ በአፋር ኢሬብቲን ከያዙ በኋላ ወደ አፍዳራ እየገሰገሱ ናቸው።
ግስጋሴው፣ ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ ጋር የሚያገናኛትን የጂቡቲ ኮሪደርን መቁረጥ ሲሆን፣ ይህም አማፂያኑ በአዲስ አበባ አገዛዝ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ለማሳደር ያስችላቸዋል - Euro News.
