en
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Open in Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
4 337
Subscribers
+124 hours
+307 days
-3930 days
Posts Archive
ለነገ ዜና ምን ብለን እንስራ? እስኪ አእምሮአችሁን ጭመቁ፣ EBC ለሠራተኞቹ። 🔴 በሬክታል ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መርካቶ አካባቢ ሱቆችን አፈንድቶ ነው … 🔴 መንግሥት፣ ሕዝቡ እንዳይረብሽ በማሰብ፣ አገልግሎታቸውን የጨረሱ መሳሪያዎችን በሌሊት አፈንድቶ ነው … 🔴 በማህበር የተደራጁ እንጀራ ጋጋሪዎች በተኙበት ኤሌክትሪክ ተቀጣጥሎ ፈንድቶ ነው … 🔴 መሬት ለመሬት ይሄድ የነበረ የነዳጅ ባንቧ (ነዳጅ እኮ የለንም)፣ ባጋጠመው የቴክኒክ ብልሽት ምክኒያት ፈንድቶ ነው …

ሶዬው ተመልሶ ይሆን በድንጋጤ? የኬንያ ገንፎ ተበልቶ ሳይብላላ፣ እንደወጠረው…

🇪🇹⚡️ጦር ሃይሎች አካባቢ ከባድ ተኩስ እና ፍንዳታ አለ፣ በዚህ ሰዓት - ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት።

🇪🇹⚡️⚡️ተደገመ! ሁለተኛ ከባድ ፍንዳታ፣ አሁን 7:12 ላይ: በአዲስ አበባ መሰማቱ ተነገረ። የፍንዳታዎቹ ድምጽ፣ እንደማንኛውም ጊዜ አይነት ፍንዳታ አይደለም፣ እጅግ ከባድና አስፈራሪ ነው፣ ብለዋል።

🇪🇹⚡️⚡️በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ በአሁኑ ሰዓት የድሮኖች ድምፅ እንደሚሰማ ነዋሪዎች እየነገሩን ነው።

🇪🇹 ሰበር ዜና⚡️⚡️ሰበር ዜና፡ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ከሌሊቱ 6፥25 ላይ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱ ተነገረ። የፈጠረው ነውጥ እጅግ ከባድ እንደነበርና ነዋሪውን ከእንቅልፉ እንዳስነሳው ምንጮች ተናግረዋል። ፍንዳታው አሁን ገና የተሰማ እንደመሆኑ፣ ቦታውን በትክክል ማወቅ እንዳልቻሉ ነገር ግን ወደ ጦር ኃይሎች አካባቢ ሳይሆን አይቀርም ብለውኛል።

🇮🇷🇦🇪⚡️ — የኢራን ከፍተኛ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፀሀፊ ሙህሲን ረዛኢ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ስለተደረገው ስብሰባ፡ የአሜሪካን ጦር ሰፈር ማስተናገድ ደህንነትን እንዳላመጣላችሁ ሁሉ
🇮🇷🇦🇪⚡️ — የኢራን ከፍተኛ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፀሀፊ ሙህሲን ረዛኢ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ስለተደረገው ስብሰባ፡
የአሜሪካን ጦር ሰፈር ማስተናገድ ደህንነትን እንዳላመጣላችሁ ሁሉ የጋዛ ሉኳንዳውን [ኔታንያሁ]ን ማስተናገድም ጥሩ ውጤት አይኖረውም። አሜሪካ ያልጠበቀቻችሁ፣ እስራኤል ልትጠብቃችሁ አትጠብቁ። ካለፈው ጦርነት ተማሩ፣ ጦርነቶችን ማቀጣጠል አቁሙ እና የኢራን ደሴቶችን፣ እና ሉዓላዊነቶችን በተመለከተ መሠረተ ቢስ የይገባኛል ጥያቄዎችን ማቅረብ አቁም!

🇮🇷🇦🇪⚡️ — የኢራን ከፍተኛ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፀሀፊ ሙህሰን ረዛኢ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ስለተደረገው ስብሰባ፡ የአሜሪካን ጦር ሰፈር ማስተናገድ ደህንነትን እንዳላመጣላችሁ ሁሉ
🇮🇷🇦🇪⚡️ — የኢራን ከፍተኛ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፀሀፊ ሙህሰን ረዛኢ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ስለተደረገው ስብሰባ፡
የአሜሪካን ጦር ሰፈር ማስተናገድ ደህንነትን እንዳላመጣላችሁ ሁሉ የጋዛ ሉኳንዳውን [ኔታንያሁ]ን ማስተናገድም ጥሩ ውጤት አይኖረውም። አሜሪካ ያልጠበቀቻችሁ፣ እስራኤል ልትጠብቃችሁ አትጠብቁ። ካለፈው ጦርነት ተማሩ፣ ጦርነቶችን ማቀጣጠል አቁሙ እና የኢራን ደሴቶችን፣ እና ሉዓላዊነቶችን በተመለከተ መሠረተ ቢስ የይገባኛል ጥያቄዎችን ማቅረብ አቁም!

🇮🇱/🇦🇪/🇸🇦/🇧🇭/🇲🇦/🇪🇬/🇴🇲/🇱🇾ከሳውዲ አረቢያ፣ ከሞሮኮ፣ ከኩዌት፣ ከባህሬን፣ ከሊቢያ (ሀፍታር)፣ ከኦማን እና ከግብፅ የተውጣጡ ባለስልጣናት፣ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረ
🇮🇱/🇦🇪/🇸🇦/🇧🇭/🇲🇦/🇪🇬/🇴🇲/🇱🇾ከሳውዲ አረቢያ፣ ከሞሮኮ፣ ከኩዌት፣ ከባህሬን፣ ከሊቢያ (ሀፍታር)፣ ከኦማን እና ከግብፅ የተውጣጡ ባለስልጣናት፣ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በኤሜሬት ተዘጋጅቶ በነበረው ስብሰባ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እና ከእስራኤል ተወካዮች ጋር እንደተገኙ የእስራኤል ቻናል 14 ዘግቧል። ኔታንያሁ እና ቢን ዘይድ መጀመሪያ ላይ ከሌሎች ሀገራት አመራሮች ጋር ከመቀላቀላቸው በፊት ለብቻቸው ሻይ ቡና ብለው ነበር። ውይይቶቹ፣ በኢራን፣ በእስራኤል እና በባህረ ሰላጤው ሀገራት መካከል መኖር ስላለበት ትብብር፣ ስለ ኢኮኖሚ እና ወታደራዊ ጉዳዮች፣ የእስራኤል የመከላከያ ስርዓቶችን በሀገራቱ ስለ መትከል እና በጋራ በመሥራት ላይ ያተኮሩ ናቸው። *-*-*- በስተመጨረሻ፣ አረብ ሀገራት በእስራኤል እቅፍ ውስጥ እየገቡ ናቸው። እንደ ሳዑዲ ዓረቢያ ያሉ፣ ከእስራኤል ጋር ኦፊሴላዊ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት የሌላቸው ጭምር፣ ተግደርድረው ቆይተውም ቢሆን፣ ' አጥብቀሽ እቀፊን' እያሏት ነው፣ እስራኤልን። ወደ አብራሃም ጎጆም (Abraham Accord)፣ እየተሽኮረመሙም ቢሆን፣ አንድ እግራቸውን አስገብተዋል።

እያወሩት እንዳሉት ከሆነ፣ የብልጥግና ጦር ሰራዊት በዓለም ላይ የሌለ፣ ከዩክሬንም በላይ የሆነ፣ ጠረ ድሮን መሳሪያ የታጠቀ ሰራዊት እንደሆነ ነው። ይሄ ደግሞ ለዓለም ስጋት ነው። በይ ሳዑዲ፣ ነይ ከብልጥግና ጠረ ድሮን ግዢ። ታይቶ የማይታወቅ አንጉሎ ጣይ ቴክኖሎጂ ታጥቄለሁ እያለ ነው።

🇪🇹⚡️በአዲስ አበባ እና አከባቢው ማንኛውንም ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ -EBC *** የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ በ
🇪🇹⚡️በአዲስ አበባ እና አከባቢው ማንኛውንም ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ -EBC *** የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ እና አከባቢው ማንኛውንም አይነት ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ አስታውቋል፡፡ ተቋሙ፣ ባሁኑ ሰዓት ድሮኖችን የሚቆጣጠር የተቀናጀ የጸረ-ድሮን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል፣ ብሏል፡፡ የተሰጠውን ማሰሰቢያ በመጣስ በየትኛውም አካባቢ በከፍታ የሚበሩ ድሮኖችን በመለየት፣ በመጥለፍ እና ወደ አስፈላጊው ቦታ በማሳረፍ እንዲሁም የአብራሪዎቹን ትክክለኛ መገኛ ቦታ በመለየትና በቁጥጥር ስር በማዋል፣ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል፣ ሲል ተናግሯል የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ የመጡ ድሮኖች እና መሰል ቴክኖሎጂ ወለድ መሣሪያዎች የሚፈጥሯቸውን የብሔራዊ ደኅንነት ስጋቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ የረቀቁ ቴክኖሎጂዎችን መታጠቁንና ብቁ የሰው ኃይል ማፍራቱን የጠቆመው መረጃው፤ ማሳሰቢውያውን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለማስፈጸም በቂ ዝግጅት እንዳለው አመልክቷል፡፡ -*-*-* ድሮኖች አዲስ አበባ ገብተው ተቀምጠዋል። ባሻቸው ሰዓት ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤተ መንግሥት ማደር እንደተወና ቤት እንደቀየረም የሰማነው ከቀናት በፊት ነው። ሌሎቹ ባለ ስልጣናትም እንደዚያው። ቤታቸውን ጥለው ወጥተዋል።

🇸🇦🇾🇪⚡️የየመን ሁቲ ጦር፣ ከጥቂት ሰዓታት በፊት የሳዑዲ ዓረቢያን ምዕራብ-ምሥራቅ የነዳጅ ማስተላለፊያ ትቦዎችን በድጋሜ እንደመቱት ታወቀ። የመቱት በሚሳዬሎች እንደሆነ ታውቋል። ከጥቂት ሳምን
🇸🇦🇾🇪⚡️የየመን ሁቲ ጦር፣ ከጥቂት ሰዓታት በፊት የሳዑዲ ዓረቢያን ምዕራብ-ምሥራቅ የነዳጅ ማስተላለፊያ ትቦዎችን በድጋሜ እንደመቱት ታወቀ። የመቱት በሚሳዬሎች እንደሆነ ታውቋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ ይህ የነዳጅ መስመር (ከመዲና ቀይ ባሕር) በተመሳሳይ ጥቃት ደርሶበት ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ እንደነበርና በሳዑዲ ዓረቢያ ላይ በታሪኳ ከፍተኛውን ኪሳራ እንድታስተናግድ ያደረገ እንደነበር የሚታወስ ነው። አሁንም በድጋሜ መመታቱ፣ ተቋሙ ተጠግኖ ወደ ሥራ ሊገባ ይችላል የሚለውን ተስፋ፣ አጨልሞታል። ዛሬ የተወሰደ የሳተላይት ምስል፣ መሠረተ ልማቱ በአሁኑ ሰዓት በርካታ እሳቶች ሲነዱበ ያሳያል።

🇪🇹⚡️የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ አቶ አብይ አሕመድ አሊ፣ በአሁኑ ሰዓት በኬንያ "ለጉብኝት" የገባ ሲሆን፣ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በናይሮቢ ተገናኝቷል። እንደ ምንጮች ዘገባ፣ አ
+1
🇪🇹⚡️የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ አቶ አብይ አሕመድ አሊ፣ በአሁኑ ሰዓት በኬንያ "ለጉብኝት" የገባ ሲሆን፣ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በናይሮቢ ተገናኝቷል። እንደ ምንጮች ዘገባ፣ አቶ አብይ አሕመድ አሊ፣ በኬኒያ ፕሬዝዳንቱን ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ጋር እንዲያስታርቀውና ሽማግሌ ሆኖ ጣልቃ እንዲገባለት መሆኑ ታውቋል። የሚገርመው ይላሉ የቀጠናው ምንጮች፡ አብይ አሕመድ አሊ አብሮት ወደ ኬኒያ የወሰደው ሰው ነው፣ ይኸውም፣ ኦባሳንጆን መሆኑ ነው። ጥምር ጦሩ ውጊያ በገባ በሦስተኛው ቀን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሱዳን ልኮት የነበረው የደህንነት ሹሙ፣ አቶ ረድዋን ሑሴን፣ ካርቱም እንዳይገባ በሱዳን መንግሥት ቪዛ ተከልክሎ መባረሩ ይታወቃል። *-*-* የነ ኳታርን፣ ኤሜሬትን፣ ጃፓንን እና የሌሎችንም ሩቅ ሀገራት፣ በጥምር ጦሩ ላይ ያወጡትን የውግዘት ደብዳቤ እየተመለከተ፣ ጥምር ጦሩ በዲፕሎማሲው በኩል እየተሸነፈ ያለ የሚመስለው ሰው ይኖራል። ይሄ ስህተት ያለው እይታ ነው። በእርግጥ በተወሰነ ትክክል ይሆናል፣ ግን እንደ አጠቃላይ የተሳሳተ አመለካከት ነው፣ በተለይ የጎረቤቶቻችን አሰላለፍ ላየ። ጥምር ጦሩ የዲፕሎማሲውን ጦርነት፣ በአሁኑ ሰዓት፣ በከፍተኛ ሁኔታ አሸንፎ ይታያል። ጎረቤት ኤርትራን በዲፕሎማሲው ከጎኑ አድርጓል፣ ጎረቤት ሱዳንን በዲፕሎማሲው ከጉኑ አድርጓል፣ ሱማሊያንም፣ ግብጽንም … ሌሎችንም ለኢትዮጵያ ቅርብ የሆኑ ወሳኝ ሀገሮችን ከጎኑ አድርጓል። ይሄ ትልቅ ድል ነው። የጃፓን፣ ኳታር፣ ማሌዥያ አሜሪካ… ሩቅ ያሉ ሀገሮችን ከጎንህ ከማድረግ፣ ጎረቤቶችህን ከጎንህ ማድረግ ይበልጣል! የሆነው ሆኖ በዚህ የዲፕሎማሲ ጦርነት የተበለጠው አብይ አሕመድ፣ በአሁኑ ሰዓት እንቅልፍ አጥቶ ጎረቤቶቹን እየለመነ ነው።

🇪🇹⚡️ዛሬ ምሽት 1:45 ገደማ፣ በሰመራ አፋር በሚገኘው የክልሉ ፕሬዝዳንት መቀመጫ ቤተ መንግሥት ውስጥ፣ ከባድ የድሮን ጥቃት ተሰንዝሯል - መሠረት ሚዲያ
+1
🇪🇹⚡️ዛሬ ምሽት 1:45 ገደማ፣ በሰመራ አፋር በሚገኘው የክልሉ ፕሬዝዳንት መቀመጫ ቤተ መንግሥት ውስጥ፣ ከባድ የድሮን ጥቃት ተሰንዝሯል - መሠረት ሚዲያ

🇷🇺🇩🇪🇰🇿 ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር በጣም ጥሩ ግንኙነት አለኝ። እና ዛሬ፣ ፕሬዝዳንት ፑቲን፣ እንደ ሩሲያ መሪ በአውሮፓ እና በዓለም ላይ በጣም ተቀባይነት ያለው የፖለቲካ ሰው እንደሆነ በታላቅ እምነት እናገራለሁ።"- የካዛኪስታን ፕሬዝዳንት፣ በበርሊን ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ከጀርመኑ መርዝ ጎን በአንድ መድረክ ቆመው።

🇸🇦 አሜሪካ፣ ከሁቲዎች ጋር የተገናኙ ምንጮች ግጭቱን ለማባባስ እና የሳዑዲ ዓረቢያን ወሳኝ መሠረተ ልማት ለማጥቃት ማስፈራራታቸውን ተከትሎ፣ የፔትሪዮት ሚሳይል ሲስተሞችን በድልድዮች፣ በኤሌክትሪክ ማመንጫ ጣቢያዎች፣ በወታደራዊ ሰፈሮች እና በውሃ ማጣሪያ ፋብሪካዎች ዙሪያ፣ በአዲስ መልክ እንደገና በማስቀመጥ ላይ ናት። ሒሳቡን፣ ሳዑዲ በሂደት የምትከፍል ይሆናል- CNN

🇺🇦⚡️🇷🇺 የዩክሬን ድሮን፣ በምዕራብ ሩሲያ ከሚገኝ አየር ማረፊያ ሊነሳ በማኮብኮብ ላይ የነበረን የሩሲያ Su-30SM ተዋጊ ጀትን፣ ለትንሽ ስቶታል። *-*-*- ድሩወን፣ አይ ድርወን። ላጥ አርጋው ነበር።

🇮🇱❌🇵🇸 — የእስራኤል ብሔራዊ ደህንነት ሚንስትር፣ ቤን-ገቪር፡
በተያዘው ዌስት ባንክ፡ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ብሆን፣ አካባቢዎች ሀ እና ለ፣ ልክ እንደ ሐ (ጋዛ) ይሆናሉ፣ መጥዳት አለበት። ሁሉም የኛ ነው፣ የፍልስጤም የሚባል ሀገር የለም። እዚህ መኖር አለብን - ሰፈሮችን እዚህ መገንባት አለብን። በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ስደትን ማበረታታት አለብን። እንደዚህ ያለ ፍላጎት አለ - በጁዳያ እና ሰማርያ (ዌስት ባንክ) የሚኖሩ ፍልስጤሞች፣ ብዙ ሀገር አላቸው፣ አረብ ሀገሮች። እዛ መሄድ ይችላሉ፣ ለመሄድ የሚፈልጉ ብዙ ሰዎችም አሉ። እኛ ግን እቺው ናት ሀገራችን፣ እዚህ ቤታችን ነው፣ እኛ ለዘላለም እዚህ ነበርን ፣ እናም እዚህ ለዘላለም እንኖራለን።

🇪🇹⚡️ሰበር ዜና! ዛሬ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ የሰመራ የድሮን እና የሚግ አየር ማረፊያ የአየር ጥቃት እንደደረሰበት ምንጮች ከስፍራው አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ የባህርዳር አየር ሀይል እና መኮድ ዛሬ ዘጠኝ ግዜ የአየር ጥቃት እንደረሰበትና ከዚሁ መካከል ሁለቱ የሮኬት ድምጽ እንደሆነ የአይን እማኞች ገልፀውልናል። ትላንትና እሁድ እለት የቢሾፍቱ ሀረር ሜዳ፣ የኮምቦልቻና የባህርዳር አየር ሀይል ግቢዎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ጥቃት መፈፀሙና ሰብአዊና የንብረት ውድመት ማስከተሉ ይታወቃል - Zara Media *-*-*- በዓለም ላይ ያሉ የጦር አውደ ውጊያቸው፣ ዘመን አፈራሽ የጦር ቴክኖሎጂዎችን በቀላሉ በሚያገኙና በሚጠቀሙ አካላት ምክኒያት፣ አንድ አካል በብቸኝነት፣ ብቻውን፣ ሲቀማጠልበት የቆየውን 'የውጊያ የበላይነት' በማጥበብ ከፍተኛ ትራንስፎርሜሽንን አምጥተዋል። በኢትዮጵያ፣ በአሁኑ ሰዓት እያየን ያለነው ይህን ነው። መደበቅ የማይቻል ገሃዳዊ ሃቅ የሆነው፣ ይኸው፣ የኢትዮጵያ አገዛዝ የአየር የበላይነቱ compromised እንደሆነበት ነው። ጥምረት ፈጠርን ያሉ ኃይሎች፣ በቀናቶች፣ በአየር እየተገዳደሩት ነው። አገዛዙ የጦር አይሮፕላኖቹን፣ ጀቶቹን እና ድሮኖቹን ከአየር ቤዙ ለማሸሽም ተገዷል። ይሄ፣ አገዛዙ በአስደንጋጭ ፍጥነት የተቀማው እና የጠበበው የበላይነት ነው። የኛ ሰው፣ በፈለገ ጊዜ፣ ቴክኖሎጂን ከሌሎች በፈጠነ ሁኔታ የመረዳት እና የመጠቀም ፍጥነት አለው። ይህን አውቃለሁ! በሌሎች ክፍላተ ዓለማት እየተደረጉ ያሉ ጦርነቶችንም በትኩረት እከታተላለሁ። በኢትዮጵያ በጥምረት ኃይሎች ዘንድ እያየሁት ያለሁት የድሮን አጠቃቀም ብቃት እና የደረጃ ከፍታ፣ ከዚህ አንፃር፣ አስደማሚ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች በርካታ ዓለም አቀፋዊ የውጊያ አንጃዎች በልጦብኛል። በበርማም፣ በሩዋንዳ ኮንጎም፣ በባላቹስታን ፓኪስታንም፣ ጦርነቶች አሉ፣ ለቴክኖሎጂዉም ከእኛ በተሻለ አክሰሱ ይኖራቸዋል፣ ቅርብም ናቸው፣ ግን እንዲህ በኢትዮጵያ እያየነው እንዳለነው፣ በቀናቶች፣ ቴክኖሎጂውን አዳፕት አድርገው በዚህ ልክ ሲጠቀሙበት አላየሁም። የአገዛዞቻቸውን በርካታ ዓለም አቀፋዊ አየር ማረፊያዎችን እና ጦር ቤዞችን በመምታት፣ ቴክኖሎጂውን ተጠቅመው የሰማዩን የባለቤትነት የበላይነት፣ እንደዚያው፣ ሲገዳደሩም አላየሁም።