ru
Feedback
Exit Exam Preparation

Exit Exam Preparation

Открыть в Telegram

Exit Exam በከፍተኛ ውጤት ለማለፍ የሚረዳ ፣ ከዚ በፊት የነበሩ የExit Exam ጥያቄዎችን ከነ መልስና ማብራሪያቸው የያዘ Quiz Bot @Exit_Exam_preparationbot

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Exit Exam Preparation

Канал Exit Exam Preparation (@exit_exam_prep) является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 50 663 подписчиков, занимая 3 397 место в категории Образование и 661 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 50 663 подписчиков.

Согласно последним данным от 20 сентября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило -490, а за последние 24 часа — -34, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 39.79%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 12.52% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 20 160 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 6 341 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 43.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
Exit Exam በከፍተኛ ውጤት ለማለፍ የሚረዳ ፣ ከዚ በፊት የነበሩ የExit Exam ጥያቄዎችን ከነ መልስና ማብራሪያቸው የያዘ Quiz Bot @Exit_Exam_preparationbot

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 21 сентября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Образование.

50 663
Подписчики
-3424 часа
-1047 дней
-49030 дней

Загрузка данных...

Похожие каналы
Нет данных
Возникли проблемы? Пожалуйста, обновите страницу или обратитесь к нашему support-менеджеру .
Облако тегов
Нет данных
Возникли проблемы? Пожалуйста, обновите страницу или обратитесь к нашему support-менеджеру .
Входящие и исходящие упоминания
---
---
---
---
---
---
Привлечение подписчиков
сентябрь '26
сентябрь '26
+30
в 2 каналах
август '26
+409
в 8 каналах
Get PRO
июль '26
+352
в 2 каналах
Get PRO
июнь '26
+8 581
в 15 каналах
Get PRO
май '26
+4 461
в 18 каналах
Get PRO
апрель '26
+656
в 5 каналах
Get PRO
март '26
+3 313
в 14 каналах
Get PRO
февраль '26
+22 779
в 2 каналах
Get PRO
январь '26
+12 680
в 1 каналах
Дата
Привлечение подписчиков
Упоминания
Каналы
21 сентября0
20 сентября0
19 сентября0
18 сентября+2
17 сентября0
16 сентября0
15 сентября0
14 сентября0
13 сентября+1
12 сентября+2
11 сентября0
10 сентября+7
09 сентября+6
08 сентября+2
07 сентября0
06 сентября0
05 сентября0
04 сентября+1
03 сентября0
02 сентября+9
01 сентября0
Посты канала
Exit Exam ካሁኑ መዘጋጀት ምትፈልጉ department ከታች የተጠቀሰላቹ ተፈታኞች ቦቱ ላይ በተዘጋጁ ጥያቄና ማብራሪያዎች እራሳቹን ብቁ ማድረግ ትችላላቹ። °Pharmacy °BSC Nursing °
Exit Exam ካሁኑ መዘጋጀት ምትፈልጉ department ከታች የተጠቀሰላቹ ተፈታኞች ቦቱ ላይ በተዘጋጁ ጥያቄና ማብራሪያዎች እራሳቹን ብቁ ማድረግ ትችላላቹ። °Pharmacy °BSC Nursing °Computer science °Marketing °Accounting °Economic °Management  °Law °Public Health HO °Medical Laboratory °Information Technology  (IT) ለጊዜው 11 department ብቻ ያለው ቢሆንም በቅርቡ ሌሎች እንዲካተት የምትፈልጉትን department comment ላይ አስቀምጡልን። ቦቱን ለማግኘት 👇 @Exit_Exam_preparationbot

2
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አድርጓል። የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ይመልከቱ 👇 https://stude
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አድርጓል። የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ይመልከቱ 👇 https://student.ethernet.edu.et/view-placement በምደባው ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ቅሬታችሁን ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ጀምሮ በአምስት ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማያያዝ እንድታቀርቡ ተብሏል። ቅሬታ ለማቅረብ 👇 https://student.ethernet.edu.et/complaints በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በመሔድ የሚቀርብ የምደባ ቅሬታን የማያስተናገድ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ቅሬታ በምታስገቡበት ወቅት የሐሰት መረጃ፣ የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል። የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
12 804
3
#MoH ጳጉሜን 03/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የተግባር ሙያ ፈቃድ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ከዛሬ መስከረም 06/2019 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታችሁን ማየት እንደምትችሉ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋ
#MoH ጳጉሜን 03/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የተግባር ሙያ ፈቃድ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ከዛሬ መስከረም 06/2019 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታችሁን ማየት እንደምትችሉ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። https://hple.moh.gov.et ላይ በመግባት የብሔራዊ መለያ ቁጥር (FAN) እና Password በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል። በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁ. 952 በመደወል ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ 🔔 ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ከነገ መስከረም 07/2019 ዓ.ም ጀምሮ ስም ዝርዝራችሁ ወደ ክልል የሚላክ ስለሆነ የሙያ ፈቃዳችሁን 12ኛ ክፍል በጨረሳችሁበት ክልል ማውጣት ትችላላችሁ። የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
11 013
4
#MoE በ2018 ዓ.ም በወልቂጤ፣ ቦንጋ፣ ጋምቤላ እና ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን መግቢያ ቀን መስከረ
#MoE በ2018 ዓ.ም በወልቂጤ፣ ቦንጋ፣ ጋምቤላ እና ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን መግቢያ ቀን መስከረም 05/2019 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በ2019 ትምህርት ዘመን አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን በቅርቡ ይፋ የሚደረግ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል። የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
17 896
5
#NGATResult ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ተለቋል። ውጤትዎን ለማየት 👇 https://result.eth+1
#NGATResult ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ተለቋል። ውጤትዎን ለማየት 👇 https://result.ethernet.edu.et ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'NGAT Results' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ። የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
24 794
6
የ Anesthesia ሙያ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የተግባር ፈተና ጳጉሜን 03/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Anesthesia ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ በነሐሴ 2
የ Anesthesia ሙያ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የተግባር ፈተና ጳጉሜን 03/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Anesthesia ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ በነሐሴ 2018 ዓ.ም የፅሑፍ ፈተና ያለፋችሁና የተግባር ፈተና (OSCE) ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ፤ ፈተናው ጳጉሜን 03/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡ ተፈታኝ ጳጉሜን 02/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ መከታተል ይኖርባቸዋል ተብሏል። ተፈታኞች በፈተናው ዕለት ማንነታቸውን የሚገልፅ ብሔራዊ መታወቂያ መያዝ ይኖርባቸዋል የተባለ ሲሆን፣ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡ ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲሔድ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ ስሊፕ መያዝ ይጠበቅበታል፡፡ (ተመዛኞች የመረጣችሁትን የፈተና ጣቢያ እዚህ ይመልከቱ፡፡) የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
20 740
7
የመውጫ ፈተና አፈጻጸም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መንግሥት በመውጫ ፈተና ምክንያት ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወጪ መጋራት በሁለት ዓመት ብቻ 8 ቢሊዮን ብር ማጣቱን አንድ ጥናት አሳየ፡፡ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቀውና የመውጫ ፈተና ወስደው ያላለፉና ሰርተፍኬት ባለማግኘታቸው ምክንያት በኮንትራትም ሆነ በቋሚ መቀጠር ካልቻሉ ተማሪዎች፣ መንግሥት በሁለት ዓመት ብቻ ያገኝ የነበረውን ስምንት ቢሊዮን ብር እንዳጣ አንድ ጥናት አረጋገጠ፡፡ መንግሥት የተጠቀሰውን ያህል ገንዘብ እንዳጣ የተገለፀው፤ ትምህርት ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን፣ ከአሪዞና ዩኒቨርሲቲ እና ከሽያሾኔ ተቋም ጋር በመተባበር ባዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ ነው፡፡ የመውጫ ፈተና በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ ያለው አፈጻጸም፣ የታዩ ችግሮች እና የወደፊት መፍትሔ ምን ሊሆን እንደሚገባ ትኩረት ያደረገ ጥናት በመድረኩ ላይ ቀርቧል፡፡ ጥናቱን ያደረገው ቡድን ከአዲስ አበባ፣ ከሐዋሳ እና ከጅማ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጡ አባላት ያሉት መሆኑን፣ ጥናቱን ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ምርምር ማዕከል አባል አብርሃም ቱሉ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ በ2016 እና 2017 ዓ.ም. የመውጫ ፈተና ከሰጡ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከ128,000 በላይ ተማሪዎች መውደቃቸውንና ከተፈተኑት ውስጥ ከ52.7 ከመቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ማለፋቸው በጥናቱ ተመላክቷል፡፡ የግል የትምህርት ተቋማት ደግሞ 14.8 በመቶ ብቻ ተማሪዎች ማለፋቸውን፣ በዚህም ትልቁ የመውደቅ ምጣኔ የተመዘገበው በግል የትምህርት ተቋማት መሆኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡ ሦስት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በምንም ዓይነት የትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎችን አለማሳለፋቸው በመረጃ መረጋገጡን የጥናቱ አቅራቢ ተናግረዋል፡፡ በአጠቃላይ በሁለት ዓመታት ውስጥ የተመዘገበው የማለፍ ምጣኔ 33.1 በመቶ ሲሆን፣ 66.9 በመቶ የሚሆነው ደግሞ የመውደቅ ምጣኔ መሆኑን በጥናቱ ግኝት መካተቱ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም የመውጫ ፈተና አልፈው ተቀጥረው ቢሆን በሁለት ዓመት ውስጥ በትንሹ መንግሥት ከወጪ መጋራት ያገኝ የነበረው ከስምንት ቢሊዮን ብር በላይ መመለስ እንዳልቻሉ ተገልጿል፡፡ ተማሪዎቹ የሚማሩት ትምህርት በመጀመሪያ ምርጫቸው ከሆነ የማለፍ ምጣኔያቸው ከፍተኛ መሆኑን ለአብነትም የጤና፣ የኢንጅነሪንግና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ ከፍተኛ እንደሆነ፣ በተቃራኒው የማኅበራዊ ሳይንስ፣ የቢዝነስና የትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ ዝቅተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 64 በመቶ የሚሆኑት የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች ሰርተፍኬት ስለሌላቸው በጊዜያዊነትም ሆነ በቋሚነት መቀጠር እንዳልቻሉ፣ በዚህ ምክንያት ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መግባት በቤተሰብ፣ በአካባቢና በጓደኛ የማሸማቀቅ ሁኔታ በልጆቹ ላይ እንደሚደርስ፣ ከ94 በመቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በቤተሰብ ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ጥናቱ በተመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች በአብዛኛው ምንም ዓይነት የመውጫ ፈተና በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች የመስጠት ሁኔታ እንደማይታይና ከዚያ ይልቅ በተመረጡ ፕሮግራሞች ላይ ብቻ ተግባራዊ አንደሚደረግ አቅራቢው አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ብቻ በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ የመውጫ ፈተና ተግባራዊ ማድረግ የጀመረች አገር መሆኗንና፣ ትምህርት ሚኒስቴርም ወደ እዚህ ሁኔታ የገባው ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች ለሥራ ቅጥር ብቁ ባለመሆናቸው፣ ይህን ያስከተለውን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል ኃላፊነቱን በመውሰዱን ነው ብለዋል፡፡ 6,ዐ3ዐ ተማሪዎች በጥናቱ መሳተፋቸውንና ከእነዚህ ውስጥ 1,38ዐ የሚሆኑት ከአንድ እስከ አምስት ጊዜ የወደቁ መሆናቸውን እንዲሁም 78 የመንግሥት እና የግል ተቋማት፣ 13 የመንግሥት እና ሰባት የግል፣ በአጠቃላይ 20 ዩኒቨርሲቲዎች በጥናቱ መካተታቸው ተገልጿል፡፡ #ሪፖርተር የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
15 937
8
የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ያድርጉ! በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሐግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባ
የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ያድርጉ!   በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሐግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡   የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ማድረጊያ ጊዜ 👇 ከነሐሴ 28/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 05/2018 ዓ.ም   የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ የሚያደርጉበት ሊንክ 👇 https://student.ethernet.edu.et/   የሕክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከስድስት ወር በታች ህጻን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል።   የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
12 948
9
የ coc ውጤት ተለቋል ወደ ዌብሳይቱ በመግባት ውጤታቹን መመልከት ትችላላችሁ pharmacy cut point 42.4 ሆኗል Nursing 39 med 51.9 ho 40.9 https://hple.moh.gov
የ coc ውጤት ተለቋል ወደ ዌብሳይቱ በመግባት ውጤታቹን መመልከት ትችላላችሁ pharmacy cut point 42.4 ሆኗል Nursing 39 med 51.9 ho 40.9 https://hple.moh.gov.et/ የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
23 206
10
#RemedialResult በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል። https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Remedial Ex
#RemedialResult በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል። https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Remedial Examination ከሚለው ስር View Results የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ። ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የሪሚዲያል ፕሮግራም ፈተና 53,620 ተፈታኞች መውሰዳቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል። የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
24 944
11
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች ምዝገባ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ-ምረቃ በቀን መደበኛ መርሐግብር (በመንግሥት ስኮላርሺፕ እና በግል
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች ምዝገባ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ-ምረቃ በቀን መደበኛ መርሐግብር (በመንግሥት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሐግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። መስፈርቶች ➻ በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ወይም ደረጃ 4 አጠናቀው (COC) ያለፉ ➻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (UAT) ይወስዳሉ የምዝገባ ጊዜ 👇 እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ድረስ ኦንላይን ይመዝገቡ 👇 https://admission.aau.edu.et የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና (UAT) ከጳጉሜን 02-04/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
21 099
12
#MoH ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የሙያ ፈቃድ የፅሑፍ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ሙያ ተመዛኞች፣ ውጤታችሁን ከዛሬ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴ
#MoH ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የሙያ ፈቃድ የፅሑፍ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ሙያ ተመዛኞች፣ ውጤታችሁን ከዛሬ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። የፅሑፍ ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች የተግባር ፈተና ለመውሰድ ነሐሴ 23 እና 24/2018 ዓ.ም ብቻ ምዝገባ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል። በመሆኑም በተገለፁት ቀናት https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መለያ ቁጥር (FAN) እና Password በማስገባት መፈተኛ ጣቢያ በመምረጥ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ ተብሏል። ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ ሲስተሙ የሚሰጣችሁን QR Code የያዘ ስሊፕ ይዛችሁ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡ የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
26 475
13
#NGAT_Schedule የ2018 ዓ.ም መጨረሻ ዓመት ብሔራዊ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የፈተና መስጫ መርሐግብር፦ ፈተናው በጠዋት እና በከሰዓት ፈረቃ ነሐሴ 20 እና 21/
#NGAT_Schedule የ2018 ዓ.ም መጨረሻ ዓመት ብሔራዊ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የፈተና መስጫ መርሐግብር፦ ፈተናው በጠዋት እና በከሰዓት ፈረቃ ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም ይሰጣል። የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
28 757
14
#NGAT የሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket አሁን ላይ ማግኘት እንደምትችሉ ተገልጿል። በመሆኑ+1
#NGAT የሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket አሁን ላይ ማግኘት እንደምትችሉ ተገልጿል። በመሆኑም ፕሮፋይላችሁ ላይ በመግባት 'Exam Credentials' በሚለው ስር 'Download Entry Ticket' የሚለውን በመጫን ወደ ፈተና ማዕከል መግቢያ ትኬትዎን አውርደው ፕሪንት ያድርጉ። ፈተናው ከሚጀመርበት ሰዓት 30 ደቂቃ ቀድማችሁ መድረስ ይጠበቅባችኋል። ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡ የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
30 587
15
ለ2019 የትምህርት ዘመን የሪሚዲያል ተማሪዎች ቅበላ እንደሚኖር የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ በ2019 ዓ.ም ወደ ሪሚዲያል ፕሮግራም የሚገቡ ተማሪዎች እንደቀ
ለ2019 የትምህርት ዘመን የሪሚዲያል ተማሪዎች ቅበላ እንደሚኖር የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ በ2019 ዓ.ም ወደ ሪሚዲያል ፕሮግራም የሚገቡ ተማሪዎች እንደቀደሙት ዓመታት ብዙ እንደማይሆን ገልፀዋል። "ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ወደ ዩኒቨርሲቲ ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሪሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ምን ያህል ተማሪ ወደ ፕሮግራሙ ይገባል የሚለው ግን አጠቃላይ የውጤቱ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ የመቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለፅ ይሆናል ብለዋል። የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
26 256
16
|| የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወደ ፈተና ማዕከል ከመግባት ጋር በተያያዘ የዲሲፕሊን ችግር የተገኘባቸው 265 ተማሪዎች ከፈተናው
|| የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወደ ፈተና ማዕከል ከመግባት ጋር በተያያዘ የዲሲፕሊን ችግር የተገኘባቸው 265 ተማሪዎች ከፈተናው እንዲባረሩ ተደርጓል። ከኮምፒውተር ፈተና አሰጣጡ ጋር በተያያዘ Irregularities ጉዳያቸው እየታየ የሚገኙ ተማሪዎችም አሉ። ዘንድሮ በኦንላይን ፈተናው ከወሰዱ 18.37% ተማሪዎች አልፈዋል፤ በወረቀት ከተፈተኑት ውስጥ 4.2% አልፈዋል። ዘንድሮ በኦንላይን ፈተናው የወሰዱ ተማሪዎች በአጠቃላይ 60 በመቶ አካባቢ ነበር። በሚቀጥለው ዓመት ፈተናውን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ዕቅድ ይዘናል። የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
22 959
17
#National_Exam_Result የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት፦ ተፈጥር ሳይንስ ወንድ - 591.6 ኦዳ ልዩ አዳሪ ት/ቤት (አዳማ) ሴት - 583 አገው ምድር
#National_Exam_Result የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት፦ ተፈጥር ሳይንስ ወንድ - 591.6 ኦዳ ልዩ አዳሪ ት/ቤት (አዳማ) ሴት - 583 አገው ምድር ት/ቤት (እንጅባራ) ማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ - 576.2 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ት/ቤት ሴት - 569.1 ቦሌ ሱፐር ሆሊሴቪየር ት/ቤት የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
20 966
18
#National_Exam_Result | የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ወይም ማክሰኞ ለተማሪዎች ይላካል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ እ
#National_Exam_Result | የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ወይም ማክሰኞ ለተማሪዎች ይላካል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ እና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምልመላ እና ቅበላ ካደረጉ በኋላ ሌሎቹም ዩኒቨርሲቲዎች ቶሎ ጥሪ እንዲያደርጉ እየሠራን ነው። መስከረም 05/2019 ዓ.ም ትምህርት ይጀመር የሚለውን ለመጠበቅ እንፈልጋለን። የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
20 353
19
#National_Exam_Result በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 12.8% ተማሪዎች ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ። ለፈተና ከተቀመጡ 560,210 ተማሪዎች 70
#National_Exam_Result በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 12.8% ተማሪዎች ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ። ለፈተና ከተቀመጡ 560,210 ተማሪዎች 70,544 ወይም 12.8% የሚሆኑት ማለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለጋዜጠኞች ገልፀዋል። በመላ አገሪቱ የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ውስጥ 88 ትምህርት ቤቶች 100% ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ማሳለፋቸውን የገለፁ ሲሆን፣ 585 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ገልፀዋል። የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
16 742
20
#NGAT የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ለአገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) በፈተና ጣቢያነት ባለመካተታቸው ቅሬታ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማቅረባቸው ተሰምቷል፡
#NGAT   የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ለአገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) በፈተና ጣቢያነት ባለመካተታቸው ቅሬታ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማቅረባቸው ተሰምቷል፡፡   አገልግሎቱ ቅሬታ ላቀረቡ ዩኒቨርሲቲዎች በሰጠው ምላሽ፤ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች በፈተና ጣቢያነት ያልተመረጡት ከፌዴራል ተቋሙ የማስፈፀም አቅም ውስንነት ጋር በተያያዘ መሆኑን ገልጿል፡፡   "ፈተናውን ለማስፈፀም ከማዕከል የሚጠቀሟቸው አስተባባሪዎች እና የፌዴራል ፖሊስ ፀጥታ ኃይሎች ማሰማራት የማይችልባቸው ሁኔታዎች ስላሉ ብቻ" የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች በፈተና ጣቢያነት አለመካተታቸውን አገልግሎቱ አስረድቷል፡፡   የ NGAT ምዝገባ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሲከናወነ መቆየቱ ይታወሳል። አሁን ላይ የተወሰኑ ተፈታኞቹ ወደ ሌሎች ዩነቨርሲቲዎች እንዲዘዋወሩ መደረጉ ታውቋል፡፡   በመሆኑም ተፈታኞች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉና በተመደቡበት አቅራቢያ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ አገልግሎቱ ጥሪ አድርጓል፡፡   አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡   የ University  መረጃ የምታገኙበት  👉 @Exit_Exam_prep
19 421