ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше3 954
Подписчики
+22224 часа
+3937 дней
+1 35930 дней
Архив постов
ሰበር..በፋኖ የተመታው ወታደራዊ አዛዥ በሄሊኮፍተር ተጭኖ ወደ አዲስ አበባ ተወሰደ!
በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና ምዕራብ ወረዳዎች ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ተጋድሎ ማዕረጉ በውል ያልታወቀ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ በፋኖ ስናይፐር ተመትቶ በሞትና በሕይወት መካከል ይገኛል።
ወታደራዊ አዛዡ ወደ ደሴ ተወስዶ እንዳይታከም የቀጠናው ዙሪያ ገባ በፋኖ ክርችም ተደርጎ በመዘጋቱ፡ የአዛዡን ሕይወት ለማትረፍ ዛሬ ጥር 28/2018 ዓ/ም ረፋድ 5:00 ሰዓት ገደማ በወግዲ ወረዳ ጫቀታ ላይ አንድ የጦር ሄሊኮፍተር ማረፉን የአይን እማኞች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።
የጦር ሄሊኮፍተሯ ቁስለኛውን ወታደራዊ አዛዥ ከጫነች በኋላ ካረፈችበት ጫቃታ በመነሳት፡ በጋስጫና በደገር አቆራርጣ ወደ ሸዋ አዲስ አበባ አቅጠጫ መብረሯንም መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የአይን እማኞች አክለው ገልፀዋል።
አዛዡ ውጊያውን ሲመሩ ከነበሩ ዋና ዋና ወታደራዊ አዛዦች መካከል አንዱ እንደነበር የገለፁት ምንጮቻችን፡ የደረሰበት ጉዳት ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ሕይወቱ ላይተርፍ ይችላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ዘውዱ ሰጣርጌ እና ብርጋዲየር ጄነራል ሞሲሳ እንዲሁም አንድ በአየር ወለድ ኮማንዶ ዕዝ የአንድ ኮር አዛዥ የሆነ የሌፍትናንት ጄነራል ማዕረግ ያለው ወታደራዊ አዛዥ፡ በሁለት ድሮን፣ በሦስት አየር መቃዎሚያና በሁለት ጄነራል መድፍ፣ በ10 ሞርተርና ቢኤም 107 እንዲሁም በ23 ዶሽቃ መሣሪያ ታግዘው ውጊያውን በዋናነት ሲመሩ እንደነበር መረብ ሚዲያ በትናንቱ ዜና እወጃው መዘገቡ ይታወቃል።
ከአየር ኃይሉ ጀምሮ በከባባድ መሣሪያዎች ታግዞ በሦስት ጄነራሎች እየተመራ ወደ ውጊያ የገባው ከ60 በላይ ተሽከርካሪ ሙሉ የአገዛዙ ኃይል፡ ከወደ ፋኖ የገጠመውን ጠንካራ የሆነ የፀረ መከላከልና የመልሶ ማጥቃት እርምጃን መቋቋም አቅቶት፡ ለሰዓታት ቆሞ መዋጋት በማይችልበት ሁኔታ ተሽመድምዶ እየፈረጠጠ ይገኛል።
(ምስል ከማህደር)
+1
1000 ወታደር አሰልፈው በለው ሲሉ የነበሩት ጀነራል በቀለ ዱጋሳ እና ሌሎች አራት የጦር መኮንኖች መገናኛ ሬዲዮናቸው በጀግኖቹ የአፋብን የጦር ጠበብቶች ተጠልፎ በአልሞ ተኳሾቹ እርምጃ ሲወሰድባቸው መሪዎቻቸው መገደላቸውን የሰሙት የጠላት ሀይሎች ሲደናበሩ ዙሪያውን የከበበው ድል ቁርሳቸው የሆነው የምንሊክ እዝ ሰራዊቶች 619 አንድ ሁለት ተብሎ የተቆጠረ የብልጽግናን ሰራዊት ላይመለስ ሲደመስሱት 24 ተማርኳል ሌሎቹም ተከበዋል በማይክራፎን እጅ ስጡ እየተባለ ነው። የተከበቡትን ለመታደግ ተጨማሪ ጦር ቢልክም ነገሩ ያልተዋጠላቸው የስርአቱ የጦር አመራሮች ወደኋላ ተመልሰዋል።
ብልፅግና የተራ ወታደሩን ክሬሳ ላሞራ በትኖ የአመራሮቹን እሬሳ ሰብስቦ ፈርጥጧል።
ድል ለአፋብን ሰራዊት ድል ለአማራ ህዝብት]
1000 ወታደር አሰልፈው በለው ሲሉ የነበሩት ጀነራል በቀለ ዱጋሳ እና ሌሎች አራት የጦር መኮንኖች መገናኛ ሬዲዮናቸው በጀግኖቹ የአፋብን የጦር ጠበብቶች ተጠልፎ በአልሞ ተኳሾቹ እርምጃ ሲወሰድባቸው መሪዎቻቸው መገደላቸውን የሰሙት የጠላት ሀይሎች ሲደናበሩ ዙሪያውን የከበበው ድል ቁርሳቸው የሆነው የምንሊክ እዝ ሰራዊቶች 619 አንድ ሁለት ተብሎ የተቆጠረ የብልጽግናን ሰራዊት ላይመለስ ሲደመስሱት 24 ተማርኳል ሌሎቹም ተከበዋል በማይክራፎን እጅ ስጡ እየተባለ ነው። የተከበቡትን ለመታደግ ተጨማሪ ጦር ቢልክም ነገሩ ያልተዋጠላቸው የስርአቱ የጦር አመራሮች ወደኋላ ተመልሰዋል።
ብልፅግና የተራ ወታደሩን ክሬሳ ላሞራ በትኖ የአመራሮቹን እሬሳ ሰብስቦ ፈርጥጧል።
ድል ለአፋብን ሰራዊት ድል ለአማራ ህዝብት
+1
ኤርትራ ነው ሲሉት ከጎንደር ብቅ ይላል፤ ሱዳን ነው ሲሉት ከቤኒሻንጉል ብቅ ይላል፤ ትግራይ ነው ሲሉት ከወሎ ብቅ ይላል። ይህ ሰው መንፈስ ሆነባቸው እኮ አቦ ይቻላል!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በተሳተፉበት ውይይት ለዓመታት በታጣቂወች ታግተው የነበሩ ሴቶችን ማስለቀቅ ተችሏል።
በመተከል ቀጠና በለተያዬ ጊዜ በነበሩ አገዛዙ በፈጠራቸው ግጭቶች ምክንያት በርካታ አማራወች ሲፈናቀሉ፣ ሲጨፈጨፉ እና ሲታገቱ የቆዩ መሆኑ ይታወቃል። ሊቀመንበሩ በቀጠናው ካሉ ታጣቂወች ጋር ባደረጉት ውይይት በባለፉት ዓመታት በተከታታይ በተከሰቱ በእነዚህ ግጭቶች አጋጣሚ እስከ አራት ዓመታት ድረስ ታግተው የቆዩ አስር ያህክል ሴት ወጣቶችን ለማስለቀቅ ተችሏል።
በቀጠናው ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ኃይሎች ጋር ቀናትን የወሰደ ውይይት ያደረጉት አርበኛ ዘመነ ካሴ እህቶቻችንን ከታገቱበት ቦታ ተረክበው ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ሸኝተዋቸዋል።
በእለቱም አርበኛ ዘመነ ካሴ ተከታዩን መልዕክት አስተላፈዋል።
"እኛ አማራዎች ሰው ከሚፈጥረው የፖለቲካ ክፋትና ፀረ አማራ ርእዮት ጋር እንጅ ከሰው ልጆች ጋር ፀብ የለንም።ሰው ክቡር ነው። ርእዮታችን የሚቀዳውም ከዚህ የአስተሳሰብ ባህር ነው።እና ማንም ህዝብ ወገናችን ነው። (በዚህ ጉዳይ የጉምዝ ህዝብም)። ስለዚህ በመተከል በጉምዝና የአማራ ህዝብ መካከል፥ በሽናሻና የአማራ ህዝብ መካከል፥ በቤኒሻንጉልና የአማራ ህዝብ መካከል መገዳደልን ሊዘራ የሚሞክረውን የረጅም ጊዜ የጠላት አስተሳሰብ እየነቀልነው በቦታው ፍቅርንና አብሮነትን እየተከልን ነው።በዚህም የተነሳ ከድርጅቶች ጋር ጥሩ መቀራረብ ፈጥረናል።
በመሆኑም በተለያዬ ጊዜ በተነሱ ግጭቶች ምክንያት በጉምዝ ሃይሎች ከስራ ቦታቸው እየተያዙ እስከ አራት አመታት ታግተው የቆዩ አስር የአማራ ልጆችን ማስመለስ ችለናል። በዚህ ወቅት እህቶቻችን ተረክበን ወደ ቤተሰቦቻቸው እየላክን እንገኛለን።ይቀጥላል።"
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተለያዬ ማንነት ካላቸው ኃይሎች ጋር የሚያደርገውን የአጋርነት እና የትብብር ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በዚህ ረገድ ድርጅታችን በኢትዮጵያ ህልውና፣ በህዝቦች አብሮነት፣ እና በአገዛዙ የጋራ ጠላትነት ላይ የተመሰረቱ ተጨባጭ ስራወችን አጠናክሮ የሚሰራ ይሆናል።
የአማራ ህዝብ የሰላም፣ የአንድነት፣ የአብሮነት እሴቶችን በሚያጎለብት መንገድ በሁሉም ማዕዘናት ለሚኖረው ህዝባችን ደህንነት አስፈላጊዉን ሁሉ ማድረጋችን ይቀጥላል።
አንድነቱን ለማምጣት ረዥም ጊዜ የወሰድነው የአመራር ምደባ ለማድረግ ሳይሆን የድርጅቱን አላማና ግብ በግልፅ ለማስቀመጥ ነው።
ባቡሩ በትክክለኛው ሃዲድ ላይ እንዲጓዝ ብዙ ክርክሮችንና ውይይቶችን አድርገናል። በትግሉ ውስጥ የነበሩ የርዕዮትዓለም፣ የመዳረሻና የግብ ልዩነት የመሳሰሉትን ጉዳዮች በመቋጨት የጋራ አቋም ይዘናል። ትግሉ የሚመራው በሰለጠነ ድርጅታዊ አሰራር ነው። ይህ የድርጅቱ ዘላቂነት ማረጋገጫ ነው።
ከዚህ በኋላ ሁለት ትግል አለ። አንድም የነጻነት ትግሉን መቀላቀል፣መደገፍ። አንድም ከጠላት ጋር መሰለፍ።
የአማራ የወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ለድርድር የማይቀርቡ በድርጅታችን በግልጽ የተቀመጡ ቀይ መስመሮች ናቸው ። በዚህ ጉዳይ አማራን አሳልፎ ለሸጠ አክቲቪስቶች ግን ምላሽ አንሰጥም።
ለብአዴን አክቲቪስቶች ምላሽ አንሰጥም። የአማራ ወሰን እና ማንነትን ዛሬ አርበኛ ዘመነ ካሴ፣ አርበኛ ምሬ ወዳጆ፣አርበኛ መከታው ማሞ፣አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ሚዲያ ቀርበው የእኛ ነው እንዲሏችሁ አትጠብቁ። የእነዚህ መሪዎች፣የእኛ ዓላማ ከዚህ በላይ ነው። ይህ አጀንዳ በብአዴን መልክት የተላከው ነው። እኛ ይህን ሁሉ በመረዳት በረሃ የወጣን ታጋዮች ነን።
በትግሉ የኖሩ እንጂ ለትግሉ ያልኖሩ አሉ። ከዚህ በኋላ አርበኛ ምሬን፣ዘመነን፣መከታውን፣ደረጄን ማንም እየተነሳ ስማቸውን ሲያጠፋ ማየት አንፈልግም።
መንግስት ይመጣሉ የሚላቸው፣የሄዱት ዋጋ ይከፍላሉ፣የሚሄዱ ካሉም እነሱ ያስቀመጧቸው የነበሩ ናቸው ማለት ነው።"
አርበኛ ፕሮፊሰር ጌታ አስራደ- በአፋብን ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ!
የአረመኔው አብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ከትናንት ጀመሮ በመላው አማራ ፋኖን ከአማራ መሬት አጠፋለሁ በማለት በሁሉም ግንባሮች እንቅስቃሴዎች ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል። ሆኖም በፋኖ ድሎችን ያገኘናቸውን መርጃ ከግንባር ሁነን ለመላው ህዝባችንን ለማድረስ እኛም አለን ከእናንተም የሚጠበቀው ሸርና ጆይን በማድርግ መወዳጀት ብቻ ነው።
❤Dawit fano አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
"የአማራ ሕዝብ ለብዙ ዘመናት ደሙን እያፈሰሰ አጥንቱን እየከሰከሰ ባቆያት ሃገር፤ ሃገር አልባ እንዲሆን በጥላቶቹ ተፈርዶበት ለአምስት አስርት አመታት በብዙ ስቃይና ግፍ ውስጥ አልፏል::
ይህን የሃገር ባውለታ የሆነውን ሕዝብ እንደ ጥላት እንዲፈረጅ ሁሉም እንዲጠላው እና በሃገሩ ተቅበዝባዥ እንዲሆን ብዙ የሐሰት ትርክትን ከመተረክ አልፎም የጥላቻ ሐውልትን በመገንባት በወገኖቹ እንደ ጥላት እንዲታይና እንዲበተን በማድረግ በግፍ እንዲጨፈጨፍ ሆኗል::
ይህንን የሕልውና አደጋ እንደ ሕዝብ ለመመከት የሚያስፈልገው አንድ ድርጅት ወይም ተቋም በመሆኑ ከብዙ ልፋት ጥረት ቡኋላ ድርጅታችን አፋብን ተመስርቷል:: ይህ ድርጅት እንዲመሰረት ትልቅ ሚና ለተወጣችሁ ወገኖቻችን እንዲሁም ታዛቢ ሽማግሌዎች በታላቁ የአማራ ሕዝብ ስም እንኳን ደስ አላችሁ::
ይህ ድርጅት አማራን ብሎም ኢትዮጵያን የሚያሻግር ድርጅት ነውና ሁሉም ፍትሕን የሚናፍቅ ወጥቶ መግባትን የሚናፍቅ ሕዝብ ድርጅታችንን እንደ ዐይን ብሌናችን እንድትጠብቁ መልዕከቴን አስተላልፋለሁ ::"
የአፋብን ተ/ምክትል ሊቀ መንበር አርበኛ መከታው ማሞ
ድርጅት የፈጠርነው ሁለት ድርጅቶችን አክስመን ነው። እጅ ለመስጠት ድርጅት አልመሰረትንም።
በኢትዮጵያ አንድነትና በአማራ ህዝብ ህልውና ላይ በጥልቀት በመወያየት አንድ አይነት መስመር ፈጥረናል።
ከቅድመ ውይይቱ በፊት ከ90 ፐርሰንት በላይ ተመሳሳይ አቋም በመያዛችን ወደ አንድ እንድንመጣ አድርጎናል።
የመሰረትነው ድርጅት የጋራ አመራር የሚከተል ነው። በየ 3 ወራት ግምገማ ያደርጋል። በየዘርፉ ያሉት አመራሮችም አፈፃፀማቸው ታይቶ የስራ ሽግሽግ ያደርጋሉ። በህገ ደንቡ ላይ ያስቀመጥናቸው ደንቦችም የድርጅቱን ዘላቂነትና አስተማማኝነት የሚያረጋግጡ ናቸው። የስነ-ስርዓትና ቁጥጥር ኮሚቴዎችም ተጠያቂነትን ለማስፈን በአግባቡ ተደራጅተዋል።
በኢትዮጵያ ህልውናና አንድነት ላይ የተዛባ አቋም የለንም። የሁሉም ኢትዮጵያውያን አብሮነት ይገደናል።
አብይ አህመድ ለኢትዮጵያውን የሚጠቅም አገዛዝ ባለመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ ተረባርቦ ሊጥለው ይገባል ብለን እናምናለን።
ትብብርን በተመለከተ ግን ኢትዮጵያውን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ጭምር ፋኖን መተባበር አለባቸው። ( ያው አብይ አህመድ ከአረብ ኤመረትስና ሌሎች ሀገራት በብድርና በተውሶ ድሮን እየጨፈጨፈን እኛ የህዝብ ጥቅምን ጠብቀን የምንፈጥረው አጋርነት ስህተት ሊሆን አይገባም እንደማለት ነው።)
የአመራር አንድነትን በተመለከተም ዕዞች በተሰጣቸው ኮታ እኩል ምደባ ተሰጥቷል።
እጅ ለመስጠት ድርጅት አልመሰረትንም።
ድርድርን በተመለከተ አገዛዙ የአማራን ህዝብ ጥያቄ ያለ ጠብመንጃ ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን ስናረጋግጥና አስፈላጊ ሆኖ ስናገኘው ያኔ የምናስብበት ይሆናል።
አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ !
የዝኑዬን ዱቄት ተሸካሚ መንጋ ያንጫጫ ፎቶ!
ከቀጠናው ሀይል ጋር የሚያደርገው ብስለት የተሞላበት ግንኙነት ጠላትን እያስራደ ነው። በተለይ ደግሞ ስኳድንና የዝኑዬን ዱቄት ተሸካሚ መንጋ ይለያል።
ውሸት፥ ቅጥፈት፥ ድንፋታ፥ ጉራና ቀረርቶ የሞላው የአብይ አህመድ ከሶስት ቀን በፊት የነበረው የምክር ቤት ውሎ እንደተለመደው አዲስ ነገር ሳይኖረው እጅ እጅ እንዳለ ያበቃ ነው። ውስጡን የሰላም እጦትና ፍርሃት እየናጠው እንዳለ ከሁኔታው በሚገባ መረዳት ይቻላል። የዛሬው ውሸት ደግሞ ክብረወሰን የሰበረ ነው። ስለኢኮኖሚ እድገት የሚያወራውን ማንሳት የሱን ውሸትና ባዶ ዲስኩር መልሶ ማስተጋባት ስለሚሆን እንተወው። አንድም እውነት ስለሌለው። ይልቅስ በተገላቢጦሽ ሀገሪቱን መቀመቅ እየወሰዳት መሆኑን መሬት ላይ ያሉ ሁነቶች ቁልጭ አድርጎ ስለሚመሰክሩ ሌላ ነገር መጨመር አያስፈልግም። የኢትዮጵያ ህዝብ ''እየሞከርኩኝ ነው'' የሚለው መልዕክት ብቻ የአብይ አህመድን ቁልል ውሸት የሚንደው ነው።
ስለኤርትራ ያነሳውም ቢሆን ሰውዬው በክህደት ወደር የሌለው መሆኑን ለሚያውቅ ብዙም የሚገርመው አይሆንም። በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ትዕግስትን ከኢዮብ ጋር ማያያዝ እንደሚቻል ሁሉ በምድር ላይ ክህደትን ከአብይ አህመድ ልቆ የሚገልጻት ሰው ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ። ክህደት መገለጫው ነው። ባለፉት ስምንት ዓመታት ስንቱ ካደ፥ ስንቱን ቀርጥፎ በላ፥ የስንቱን ውለታ ውሃ ቸለሰበት፥ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። በኤርትራና በአይኔ ቀልድ የለም ያለን እሱ ራሱ ነው። ኢሱን የነካ አይኔን የነካ ነው እያለ ሲነግረን የነበረው እሱ ነው። በመሃላችን ንፋስ እንኳን አይገባም በሚል ቀለበት ያሰረለት አብይ መሆኑን አልረሳነውም። የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆኜ ለኤርትራ እሟገትላታለሁ በሚል የቀላመደው አብይ አህመድ ነው። ኤርትራ ባትኖር ምን ይውጠን ነበር ብሎም በምክር ቤት ያስጨበጨበው እሱ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።
ታዲያ ዛሬ ይህ ሁሉ ውርጅብኝ ማንን ለማሳመን ነው? የማንን አንጀት ለመብላት ነው? እንደው የኢትዮጵያ ህዝብ መጫወቺያ ሆኖ ይቅር?!
ለማንኛውም እየሞከርን ነው! #mesay
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ምስረታን አስመልክቶ ማብራሪያ እየተሰጠ በሚገኝበት መድረክ ላይ ተገኝቶ አስተያየቱን የሰጠው የድርጅቱ የፖለቲካ ዘርፍ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ረ/ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ👇👇👇
“የአማራ የወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ለድርድር የማይቀርቡ በድርጅታችን በግልጽ የተቀመጡ ቀይ መስመሮች ናቸው። በዚህ ጉዳይ አማራን አሳልፎ ለሸጠ አክቲቪስቶች ግን ምላሽ አንሰጥም።
አርበኛ ዘመነ ካሴ ተነስቶ መተከል የኔ ነው፣ አርበኛ ሔኖክ አዲሴ ተነስቶ ራያ የኔ ነው፣ አርበኛ መከታው ማሞ ተነስቶ ደራ የኔ ነው ማለት አይችሉም። የቀደሙ እነ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የተገደ'ሉባቸው የአማራ ሕዝብ ቀይ መስመር ጥያቄዎች ናቸው” ሲል በማብራሪያው ላይ አርበኛ ረ/ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ ተደምጧል።
#ጥብቅ_መልዕክት‼️
ወደ አማራ ምድር ከሰሞኑን በርካታ ሜካናይዝድ መሳሪያና ሰራዊት መግባቱ ይታወሳል። ይህ ሀይል የለሊት ማጥቃት ለማድረግ ወደ ፋኖ ቀጠናዎች በለሊት እንዲንቀሳቀስ ትዛዝ የተሰጠ ሲሆን የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በበርካታ የፋኖ ግዛቶች እየተቆራረጡ መሆናቸውንም ንስር አማራ ባሰባሰበችው መረጃ ማረጋገጥ ተችሏል።
ስለሆነም አገዛዙ ያለ የለለ የሰው ኃይልና መሳሪያ በመታገዝ የግንኙነት መንገዶችን ሙሉ በሙሉ አቋርጦ የለሊት ጥቃት የመክፈት እቅድን በአንዳንድ ቦታዎች ተግባራዊ ያደረገው ስለሆነ የወገን ሀይል ከወትሮው በተለዬ ዝግጁ እንዲሆን እናሳስባለን።
27/ዐ5/2018 ዓ.ም
#ሰበር_የድል_ዜና‼️
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና
አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር ድል ተቀናጀ ።
ጥር 27/05/2018 ዓ.ም፡ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር ጠላት ላይ ባደረሰው የደፈጣ ምት ድል መቀዳጀቱን ተገለፀ ። የጦርነት አዙሪት የተጠናወተው የብልፅግው መንግስት ከፋኖ ጋር የገባውን ጦርነት ከመንበረ-መንግስቱ ሊያወረደው ከጫፍ ደርሶ በመንገዳገድ ላይ እያለ የሚደግፈውና ከጎኑ ያሰለፋቸው ተዋጊ ሰራዊቶች ከመሠረታዊው ወታደር እስከ ኮሎኔን እና ጀነራልነት ማዕረግ ያላቸው እየከዱት ፋኖን መቀላቀላቸው ያሰግው ብልፅግና አዲስ የማደናገሪያ ዜና ሲሰራ እንደከረመ ሰሞኑን መዘገባችን የሚታወስ ነው ።
ይህም "ቀይ ባህርን ላስመልስላችሁ ነው በግድ ደግፉኝ" በማለት የተመናመነበትን ሰራዊት በወደብ ሰበብ ለመሙላት ከቅስቀሳ ወደ አፈሳ መሻገሩን ሁሉም ያወቀው ፥ ፀሐይ የሞቀው ሀቅነው ። ታዲያ ይህንን ተግባሩን ይመሩልኛል ያላቸውን በሰመ አማራ በጥቅም የተገዙ ሆድ አደር ባንዳ ሚሊሻና ፖሊስ በማስቀደም የለመደውን አፈሳ ለማፈስ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኢራንቡቲ ቀበሌ ቆቦ አካባቢ የተንቀሳቀሰው ሰራዊት ላይ፤ በነበልባል ክፍለ ጦር አራተኛ (፬ኛ) መብረቁ ሻለቃ በተወሰደበት የደፈጣ ምት ከፍተኛ የሰራዊት አባላቶቹ እስከ ወዲያኛው የተሸኙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ መንገድ ሲመሩ ከነበሩት የእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎች ውስጥ
1ኛ. ፲ አለቃ ዘላለም አስናቀ ---- ከዚህ በፊት በፋኖ ስም ሲነግድና ሲያጭበረብር የነበረ፤ ከዚያም የአማራን ህዝብ ከድቶ ሚሊሻ በመሆን ማህበረሰቡን ሲያስጨንቅ የቆየ ግለሰብ ነው ።
በተጨማሪም፤ ስማቸው በውል ያልታወቀ 2 ሚሊሻዎችና አንድ የፖሊስ አባል እንዲሁም ከ23 በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባል በመብረቁ ሻለቃ እስከ ወዲያኛው የተሸኙ ሲሆን ለአፈሳ የመጣው የብልፅግና ጥምር ጦር በክንደ ጠንካራው ነበልባል ክፍለ ጦር መብረቁ ሻለቃ በምትኩ የሬሳ ክምር ሰራታለት አምሽታለች ። ይህ ደፈጣ የታሰበለትን አላማ ያሳካ ነበር ያሉን የመብረቁ ሻለቃ አዛዥ ናቸው ።
የዚህ ደፈጣ ዋና አላማችን የናት ጡት ነካሽ የሆነውን የአስር አለቃ ዘላለምን ታርጌት ያረገ ነበር ያሉት ደግሞ የመብረቁ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ነበሩ ።
ከዚህ ቀደም የኛ አባል በመሆንና በዘመቻነት ተመድቦ መረጃችንን ለጠላት አሳልፎ በመስጠትና ጦሩን የተለያየ ያልተጣሩ የሀሰት ወሬዎችን በሰራዊቱ መካከል በማስወራት ጦሩን ለመበተን ያደረገው ሙከራ በመጋለጡና ከፍተኛ ክትትል እየተደረገበት እያለ በክዳት ወደ ቀጣሪው ብልፅግና ከፍተኛ ገንዘብ በመዝረፍ መግባቱ ይታወቃል። እናም ይህ ስግብግብና ወገኑን የካደ ባንዳ ዘላለም የለመደውን የዝርፊያና የበደል ስራውን በከተማው ህዝብ ላይም በማድረስ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በርከት ያሉ የችግሩ ሰለባ የሆኑ ንፁሃን ዜጎች በተደጋጋሚ የሰራውን ግፍና በደል ነግረውናል ።
'መስረቅ የለመደ እናቱን ያስማማል' እንደተባለው ሁሉ ባንዳ ዘላለም የብልፅግና ታማኝነቱን ለመግለፅ የገዛ ህዝቡን እያፈሰ ሲያስረክብ ከፍተኛ የሆነ የውሎ አበል በንፁሀን አርሶ አደሮች ደም በመከፈሉ አፈሳውን ለሱና ለግበረ አበሮቹ እንደ የገቢ ምንጭ ቆጥሮ ከግብራበሮቹ ጋር የለመደውን የድሃ ልጅ ለማፈስ ሲንቀሳቀስ በመረጃ በመከታተል እና ታርጌቱን ሙሉ ባንዳ ዘላለም ላይ በማረግ የማያዳግም እርምጃ መብረቁ ሻለቃ መውሰዱን አስታውቋል ።
ይህ የመጀማሪያም የመጨረሻም አይደለም ከእኛ የከዱና መረጃችንን ለጠላት አሳልፈው የሰጡ ላይ ልዩ ክትትል በማረግ እርምጃችንን የምንቀጥል ይሆናል ሲሉ የመበረቁ ሻለቃ አዛዥ በድጋሜ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
ከዚሁጋ በተያያዘ ዜና፤ በእዚያው በኢራንቡቲ ቀበሌ ዙሪያ ቀጠናውን በማስፋት ወደ ተለያየ አቅጣጫ ለመንቀሳቀስ የሞከረው የብልፅግና ጥምር ጦር በራስ በኃይሉ በሶስተኛ(፫ኛ) ሻለቃ በተወሰደበት እርምጃ ወደ ኋላ ለመመለስ እንደተገደደ የራስ በኃይሉ ሻለቃ አዛዥ አሳውቀውናል ሲል አፋብን ደቡብ አማራ በቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ሪፖርተራችን አርበኛ እንግዳ መረጃውን አድርሶናል ።
ዘገባው፦ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር አርበኛ ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ ነው ።
©የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
አሳምነው ክፍለ ጦር ለከበባ የመጣን ጠላት ስበው በማስገባትና በርካታ ሃይሉን በመደምሰስ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::
የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ዛሬ ጥር 27/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ ከወልድያ ከተማ በመነሳት በርካታ እግረኛ ሰራዊት ወደ ጃርሳ ታዳጊ ከተማ ቢያዘምትም አሳምነው ክፍለ ጦር 4ኛ እና 5ኛ ሻለቃ ባግባቡ በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ በርካታ ሃይል ሙትና ቁስለኛ አድርገው ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦር ጠላትን ተደጋጋሚ ጊዜ የመቱበት ወልድያ ከተማ ዙሪያ ዛሬም የፋሽስቱ ሰራዊት መቀበሪያ ሆኗል:: ጀግኖቹን ለመክበብና ለማፈን የተንቀሳቀሰው የጠላት ሰራዊት የጀግኖቹን ክንድ ቀምሶ ወደመጣበት ተመልሷል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም
የጥንቃቄ መልዕክት
በሰሜን ሸዋ ዞን የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል ተብሏል። በቀጠናው የምትገኙ ፋኖዎች የመረጃ መረባችሁን እንድታስተካክሉ ይሁን‼️
ለወልድያ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ የጥንቃቄ መልክት!
የሰሜን ወሎ ዞን እና የወልድያ ከተማ አመራሮች ፋኖን ከህዝብ እንነጥላለን በሚል ስሌት ባለፉት ሁለት አመትና ከዛ በላይ ጊዜያት ህዝቡ ላይ በርካታ ግፎች መፈፀማቸውን በማስረጃ ማጋለጣችን ይታወቃል::
ይህ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ተግባር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎ ከዚህ በታች በተዘረዘሩትና በተጠቀሱት ስምና ስልክ ቁጥሮች እየተደወለ በፋኖ ስም ከማህበረሰቡ ገንዘብ አምጡ እያሉ እንደሆነ በማስረጃ ለማረጋገጥ ችለናል:: ይህንን ድርጊትም የሚፈፅሙት በስውር በሚሊሻ እና አድማ ብተና አባላቶች እንደሆነ አረጋግጠናል!
ስለሆነም ጀምበር የጠለቀችበት ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ጣረ ሞት ላይ በመሆኑ ስልጣኔን ያቆይልኛል ያለውን ሁሉ ከማድረግ አይቆጠብምና ህዝባችን ይህንን በመገንዘብ መወሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች ሁሉ እንዲወስድ ስንል መልክታችንን እናስተላልፋለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 27/2018 ዓ.ም
