ru
Feedback
Purity Matters

Purity Matters

Открыть в Telegram

"ትቀደሱ ዘንድ ፈልጉ ...(ዕብ12፥14) ቅድስና እግዚአብሔርን የምናይበት መንፈሳዊ ዐይናችን ነው! 📖 የጸሐፊው የታተሙ መጻሕፍት፦ 1️⃣ ፖርኖርሽኝ (የፖርኖግራፊ መርዝ፣ መዘዝ እና መድኃኒት) 2️⃣ የኅሩያን ሕይወት (የወሲባዊ ቅድስና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሖዎች እና አተገባበራቸው) 📩 መጻሕፍቱን ለማዘዝና ለመግዛት፦ • በቴሌግራም፦ @minassieyirgu • በስልክ ቁጥር፦ 0986552076

Больше
1 323
Подписчики
+524 часа
+247 дней
+5130 дней
Архив постов
«ወንዶች ሁሉ ውሻ ናቸው?!» — የታክሲዋ ትዝብት 😅 አንድ በዕለቱ ውካባና ድካም የመረረው ወጣት በታክሲ የኋለኛ ወንበር ላይ ተሠይሟል። ታክሲዋ በከተማዋ የትራፊክ ሰልፍ ውስጥ እየተጋፋች ትጓዛለች። አጠገቡ የተቀመጡ ሦስት ቆነጃጅት ደግሞ የጦፈ ወሬ ይዘዋል። ርእሰ ጉዳያቸው፦ "ወንዶች ልክስክስ ፍጥረቶች ናቸው!" የሚል ነው። ሦስቱም እኩል ያወራሉ፣ እኩል ይጮኻሉ፣ እኩል ይሣሣቃሉ። የታክሲዋን የኋለኛ ክፍል የሰንበት ጠጅ ቤት አስመስለውታል። ወጣቱ ዝም ብሎ በታዛቢነት ያዳምጣቸዋል። የሴቶቹ የስድብ ውሽንፍር ግን እያደገ እንጂ እየቀነሰ አልሄደም። ከሦስቱ አንዷ ድምጿን ከፍ አድርጋ፣ በልበ ሙሉነት፦ "ኧረ እንደውም ወንዶች ሁሉ ውሻ ናቸው!" አለች። በታክሲው ውስጥ ጥቂት ረጭ ያለ ዝምታ ሰፈነ። በዚህ ጊዜ፣ ያ የመረረው ወጣት ወሬያቸውን አቋርጦ በተረጋጋና ረጋ ባለ ድምፅ፦ "ሚያው!" አለ። 😅 («እንዲያው ከሆነማ... እኔ ድመት ነኝ!» ማለቱ ነው እንጂ!) መልእክቱ፦ ቀልዷ በታክሲ ውስጥ ፈገግታን ብታመጣም፣ ከበስተጀርባዋ ግን ሁላችንም ልናስብበት የሚገባ አንድ እውነት አለ። አልፎ አልፎ በሕይወታችን በሚገጥሙን አንዳንድ ሰዎች ምክንያት "ወንዶች ሁሉ እንዲህ ናቸው" ወይም "ሴቶች ሁሉ እንዲህ ናቸው" የሚሉ አጠቃላይ ድምዳሜዎችን እንደ ዋዛ እንሰነዝራለን። ነገር ግን ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በውሻ ወይም በሌላ ፍጡር ምሳሌ የሚገለጹ አይደሉም፤ በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተፈጠሩ፣ ክብርና ውበት ያላቸው የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረቶች ናቸው። አንዳንዴ የበፊቱን ቁስላችንን ወይም የከፋንበትን አጋጣሚ በአጠቃላይ ጾታ ላይ ከመወርወር ይልቅ፣ ሰዎችን በሰባዊነታቸውና በእግዚአብሔር አምሳልነታቸው ማየት ብንችል ፍቅራችንና አብሮነታችን ይበልጥ ያምር ነበር። (ለማንኛውም... እሱ «ሚያው» ማለቱን ከተወ፣ እኛም ሰዎችን «ውሻ» ማለታችንን ብንተው ይበልጥ ያምርብናል! 😉)

አንድ የመረረው ወጣት ታክሲ ውስጥ ከኋላ ወንበር ላይ ተሠይሟል። አጠገቡ ያሉት ሦስት ቆነጃጅት የጦፈ ወሬ ይዘዋል። የሚያወሩበት ርእሰ ጉዳይ "ወንዶች ልክስክስ ፍጥረቶች ናቸው" የሚል ሲሆን፣ ሦስቱም እኩል እያወሩ፣ እየጮኹ፣ እየተሣሣቁ ታክሲውን ጠጅ ቤት አስመስለውታል። ከሦስቱ ቆነጃጅት መካከል አንዷ "ወንዶች ሁሉ ውሻ ናቸው" ስትል፣ ወጣቱ "ሚያው" አለ። እኔ ግን ድመት ነኝ ማለቱ ነው😅😅😅
ሴቶች ወንዶች በእግዚአብሔር መልክ እና አምሳል የተፈጠሩ ሰዎች እንጂ ውሾች አይደሉም።

ብሩህ ዓለምነህ "ፍልስፍና-1" በሚለው መጽሐፉ የወንዶችን የሴሰኝነት ባሕርይ ከፍትወት ጋር ፣ የሴቶቹን የሴሰኝነት ባሕርይ ደግሞ ከውበት ጋር እያነጻጸረ ያቀርባል፤ እንዲህ ሲል..."......
ለወንዶችና ለሴቶች የሴሰኝነት ትርጒምን መስጠት ያለብን እንደ ተፈጥሯዊ ዝንባሌያቸው እንጂ እስከዛሬ እንደነበረው የሴሰኝነት ትርጒም፣ የወንዱን ተፈጥሯዊ ስሜት ብቻ መሠረት ያደረገ መኾን የለበትም። የወንዶች ተፈጥሮ ከወሲብ ጋር የተያያዘ ስለኾነ ሴሰኝነት ለወንዶች ልቅ የወሲብ ፍላጐት ሲኾን፤ የሴቶች ተፈጥሮ ደግሞ ከውበት ጋር የተያያዘ ስለኾነ ሴሰኝነት ለሴቶች ከልቅ የውበት ፍላጐት (ስሜት) ጋር የተያያዘ ነው ። ልቅ የውበት ስሜት ለሴቶች የሴሰኝነት መገለጫ ነው።"
አንድ ወንድ ሴሰነ የምንለው፣ ፍትወታዊ አምሮቱ ሲቀሰቀስ እና ያንንም አምሮት በአእምሮው ውስጥ ሲያብሰለስለው እና በሴሰኝነት በተቃኘ የሕይወት ምልልስ በተግባር ሲገልጠው ሲኾን፣ አንዲት ሴት ሴሰነች የምንለው ደግሞ፣ የውበት እና የአትኲሮት ረኀብ ሲያክለፈልፋት እና በኀልዮ (በዐሳብ) የነበረው የመዋብ ፍላጐቷን በገቢር (በድርጊት) አፈንጋጭ እና ልቅ በኾኑ ንግግሮች፣ አኳኀኖች እና አለባበሶች ስትገልጠው ነው።

photo content

ወንዶች የሴቶችን ምስለ ርቃን በፖርን ትዕይንቶች ላይ ሲመለከቱ፣ በምናባቸው የሚሥሉት በምስሉ ከምትታየው እንስት ጋር ወሲብ ሲፈጽሙ ነው። ወንዶች ይበልጥ የሚዝናኑት በምናባቸው በሚፈጥሩት ወሲባዊ ቅዥቶች (Sexual fantasies) እንጂ በፍቅር ቃላቶች ወይም ቅርርብ ተኰር በኾኑ ግንኙነቶች አይደለም። የወንዶች አንጐል ግብ ተኰር አካሔድን ስለሚከተል፣ ወንዱ የወሲብ ስሜቱን ማርካት ተቀዳሚ ዓላማው ነው።
ወንዶች በፍቅር ተረማምደው ወደ ወሲብ ጋር መድረስ ፍላጐታቸው ነው። ሴቶች ደግሞ በወሲብ ተረማምደው ፍቅር ጋር ለመድረስ ይሞክራሉ።
የሴቶች አንጐል በቀዳሚነት የሚያስበው የጥልቅ ግንኙነት መመሥረትን በመኾኑ፣ ግንኙነት ተኰር አካሔድን ይከተላሉ። አን ሞይር እና ዴቪድ ዐሳባቸውን ሲያጠቃልሉም "ወንዶች ፍትወታዊ ስሜታቸው ከተነሣሣ ለሌሎች ነገሮች ዕውር ይኾናሉ። ከፍተኛ የኾነ የቴስቶስቴሮን እድገንጥር (ሆርሞን) በአንጐላቸው ውስጥ መለቀቊም የትኲረት አቅጣጫቸውን ይበልጥ እንዲጠብብ ያደርገዋል" ብለዋል። 📚ፖርኖርሽኝ (ገጽ 100)

በምድራዊው ሥርዓትና በተፈጥሮ ሕግ እሳት በውኃ እንደሚጠፋ ቢታወቅም፣ በመንፈሳዊው ዓለም ስሌት ግን ነገሩ ፈጽሞ የተለየ ነው። በሰውኛ ድካምና በግልብልብ የፍትወት እሳት የሚናወጠውን የሰውን ማንነት በሰውኛ ጥረት፣ በሕግጋት መደርደር ወይም ስሜትን ዝም ብሎ በመጨቆን (በውኃ) ለማጥፋት መሞከር ዘላቂ መፍትሔ ሊሆን አይችልም። ይህንን ፈታኝና የሚለበልብ የሥጋ ምኞት ማሸነፍ የሚቻለው፣ ከዚያ በሚበልጥና በሚበላ ሌላ መለኮታዊ እሳት ሲዋጥና ሲተካ ብቻ ነው። ስለዚህ ወሲባዊ ቅድስናን በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ በተግባር ማረጋገጥ የሚቻለው ከፈተናዎች በመሸሽ ወይም ራስን በማታለል ሳይሆን፣ ያንን የፍትወት እሳት በመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ እሳት በመርታትና በመዋጥ ነው። 📚የኅሩያን ሕይወት (ገጽ 147)

መሸሽ ዐደጋ ሊያደርስ ከሚችል ከማንኛውም ነገር ለማምለጥ የምንወስደው የጥንቃቄ ርምጃ ነው። መሸሽ ልንጋፈጠው የማንችለው ነገር ሲመጣብን የምንሰጠው ደመ ነፍሳዊ ምላሽ ነው። መሸሽ በእጅ አልሰጥም ባይነት ከመዋጋት ይልቅ ከመሞት መሰንበት በሚል ድምፀት ራስን ለማዳን መፈትለክ ነው። መሸሽ በብዙኀኑ ዘንድ የፈሪዎች ድርጊት እንደኾነ ተደርጐ ይታሰባል። ታግለው የማያሸንፉትን ጠላት ሸሽተው የማያመልጡ አላዋቂዎች መጠሪያቸው ጀግኖች የሚል የመዓርግ ስም ሳይኾን ሞኞች የሚል የወል ስም ነው። መሸሽ አንዳንዴ ጥበብ ነው! መዳረሻ ያለው ፍርጠጣ፣ ዓላማ ያለው የእግሬ አውጪኝ ሩጫ ከኾነ ሽሽት መልካም ነው። ሽሽት ወይም ማፈግፈግ አንዱ የጦርነት ስልት ነው። ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ በጐ ወታደር መልካሙን ገድል እንዲጋደል እንደተጠራ ኹሉ፣ እንደ ሕያው ቤተ መቅደስ ከሚያረክሰው ከማንኛውም ነገር እንዲሸሽም ጭምር ታዝዟል። ክርስቲያን እንዲሸሽ ከታዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱና ዋነኛው ክፉ የጐልማሳነት ምኞት ነው። ይኽ ክፉ የጐልማሳነት ምኞት የዝሙት ወላጅ አባት ነው። ስለዚህ በተዘዋዋሪ ሽሹ እያለን ያለው ከዝሙትም ጭምር ነው። በርግጥ፣ ጳውሎስ በቀጥታ ለቈሮንቶስ አማኞች "ከዝሙት ሽሹ" በማለት ሐዋርያዊ የማስጠንቀቂያ ቃልን እንዳስተላለፈ ዕውቅ ነው። ዝሙት ኃይለኛውን መስፅን ሶምሶንን፣ ልበ እግዚአብሔር የተባለውን ንጒሥ ዳዊትን እና ስመ ገናናውን ጠቢብ ንጒሥ ሰሎሞንን የጣለ ዐደገኛ ጠላት ነው። ሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ ሲል ይኼንንም የብሉይ ታሪክ እያሰበ ሳይኾን አይቀርም። ዝሙት መንፈስን የሚያረክስ፣ ነፍስን የሚያሳድፍ፣ ሥጋንም የሚያጐድፍ የአጋንንት መሥዋዕት ነው። ዝሙት እጅ በእጅ የማይፋለሙት ባላንጣ፣ በወንድነት ወኔ ተጋጥመው የማያሸንፉት አሳድዶ ገዳይ ጠላት ነው። 📚ፖርኖርሽኝ (ገጽ 226)

በዓመታት የተገነባን መንፈሳዊ ግርማ እና እግዚአብሔር የሰጠንን ታላቅ ዓላማ በጥቂት ቅጽበታት ስሜት መለወጥ ብኲርናንን ማቃለል በመሆኑ ዐደጋው የከፋ ነው። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰዉ የሰጠው ታላቅ እምቅ አቅም እና ሊደርስበት የሚገባ የሕይወት ግብ አለ። ወሲባዊ ርኲሰት ግን ይህንን ግብ የሚያጨናግፍ እና ከታየልን ክብር የሚያጐድል ሥውር ወጥመድ ነው። 📚የኅሩያን ሕይወት (ገጽ 146)

የሰው ልጅ ለማዳ ፍጡር ነው። በስሜት ሕዋሳቱ አማካኝነት በሚቃርመው መረጃ በዙሪያው ካሉ ሰዎችና ከአካባቢው ጋር በመላመድ፣ በፍጥነት ከሚለዋወጠው የኑሮ ሥርዐት ጋርም ዐብሮ በመለወጥ እና ራስን በማሠልጠን ሒደት ውስጥ ያለማቋረጥ የሚያልፍ የምንጊዜም የሕይወት ተማሪ ነው። የሰው ልጅ ከሕይወት ትምህርት ቤት የሚያገኛቸው ትምህርቶች ጭማቂ ደግሞ ልማደ ሕይወት (EXPERIENCE) በመባል ይጠራል። ልማድ በአንድ ጀንበር የማይገነባ፣ በአንድ ጀንበርም የማይፈርስ ነገር ነው፤ ልማድ የልምምድ ውጤት ነውና። ልማድ የየዕለት ድርጊቶች እና ክንውኖች ድምር ውጤት ነው። የሰው ልጅ የልማዱ እሥረኛ ነው ሲባል እንሰማለን፤ በርግጥም ነን። (ድመት መንኲሳ አመሏን አትረሳ እንዲሉ!)። አንድን ነገር ልማድ ካደረግን በኋላ እንዲኹ ለመላቀቅ የማይቻል ነው። ከምንወደው ጐጂ ልማድ ራሱ የምንላቀቀው በሌላ በማንወደው ገንቢ ልማድ ነው። የሰው ልጆች ስንባል ሊሰበር በማይችል የልማድ ቀለበት ቅርቃር ውስጥ የገባን ልማደኛ ፍጡሮች ነን። ልማድ መንታ ገጽታን የተላበሰ በመኾኑ እንደሚያደርሰው ተጽዕኖ ሠናይ (በጐ) ወይም እኲይ (ክፉ) ሊኾን ይችላል። የልማድ እስረኛነታችን አርነት የሚመስል ባርነት ያለበት ከኾነ (ልክ እንደ አደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት) ልማዱን ጐጂ (እኲይ) ልማድ ብለን ስንጠራው፥ በተቃራኒው ደግሞ ባርነት የሚመስል ግን አርነትን የሚያጐናጽፍ ከኾነ (ለምሳሌ በጠዋት ተነሥቶ ስፖርት መሥራት፣ ስኳር የበዛበትን ምግብ መቀነስ ወዘተ...) ልማዱን ጠቃሚ (ሠናይ) ልማድ ብለን እንጠራዋለን። በዚኹ የትርጒም ማሕቀፍ ውስጥ ኾነን የኀጢአት ልምምድን ከክፉ ልማድ ውስጥ መመደብ እንችላለን። የኀጢአት ልምምድ ግን ከክፉ ልማዶች ተርታ ብቻ የሚሰለፍ አይደለም፤ የክፉ ልማዶች ኹሉ መፍለቂያ ምንጭም ጭምር እንጂ! ኀጢአት ከምኞት ማኅፀን ተወልዶ እና አድጐ ሞትን እስከሚወልድበት ጊዜ ድረስ በመኻከል ያለውን ጒዞ ነው የኀጢአት ልምምድ እያልን የምንጠራው። ይኽ የኀጢአት ልምምድ መነሻው እዚህ ግባ የማይባል እና ቀላል የሚመስል ምኞት ዐዘል ዐሳብ ነው። ረቂቅ የነበረችው ምኞት ግዘፍ ነሥታ ደጋግማ በግብር የመገለጥ ዕድል ስታገኝ የኀጢአት ልምምድ ትኾናለች።
የኀጢአት ልምምድ "ግማሽ መርዝ አይገድልም" (HALF POISON WON'T KILL) በሚል ዕብደት የተቀላቀለበት ጀብደኝነት በምኞት እሳት መጫወት ወይንም ለምለም ሳሩን ብቻ የማየት ዝንጒነት በተጠናወተው አኳኋን ወደ ጥፋት ገደል መንደርደር ማለት ነው።
📚ፖርኖርሽኝ (ገጽ 167-168)

በፖርኖግራፊ ሱስ ምክንያት የሚከሠት የበታችነት ስሜት ከሰው ኹሉ የተለየኹ ርኲስ ነኝ ያስብላል፤ ከራስ ጋር ያፋልማል። ልብን ለዐመፅ ያጀግናል፤ ለንስሓ ደግሞ ያደነድናል። ከማኅበራዊ ሕይወት ራስን ማግለልን ያስከትላል። ከደስታ አፋትቶ ከኀዘን ያጋባል። ርካታ የለሽነትን ያመጣል፤ ተስፋ መቊረጥ እና ጨለምተኝነት እንዲያንሰራራ ያደርጋል፤ ውሻ ወደ ትፋቱ እንዲመለስ እንዲኹ ወደ ፖርኖግራፊእና ወደሌሎች ጊዜያዊ ወደኾኑ የስሜት ማደዘንዣዎች እና የመደበቂያ ዋሻዎች ገብቶ መመሸግን ምርጫ አልባ አማራጭ አድርጐ ያቀርባል። አለፍ ሲልም ራስን በማጥፋት እስከ ወዲያኛው ይኽችን አታክቴ ዓለም መሰናበትን ያስመኛል። በማስመኘት ብቻ አያበቃም፣ ራስን ለማጥፋት ድፍረት ሰጥቶ ያስሞክራል፤ ከተሳካለትም ለአንዴና ለመጨረሻ ከአፈር ይቀላቅላል። 📚ፖርኖርሽኝ ገጽ 144

እግዚአብሔር በመዓቱ ከመጣ የሚተርፍ የለም። ዝም ካለንም የሚመለስ የለም። ለካ እግዚአብሔር የሚቀጣን ስለሚያዝንልን ነው። ዲ. አ. መ.

ገንዘቡ ተሟልቷል🎉🎉🎉🎉🎉

ይቺን መጽሐፍ ከማተሚያ ለማውጣት የቀረን ብር 27,000 ብር ብቻ ነው። ማን ይሆን ይኼንን ገንዘብ በመሙላት የቅድስናን ወንጌል የማስፋትን ራዕይ የሚደግፍ? ማን ትሆን የእግዚአብሔርን የልብ ጩኸት ለ
ይቺን መጽሐፍ ከማተሚያ ለማውጣት የቀረን ብር 27,000 ብር ብቻ ነው። ማን ይሆን ይኼንን ገንዘብ በመሙላት የቅድስናን ወንጌል የማስፋትን ራዕይ የሚደግፍ? ማን ትሆን የእግዚአብሔርን የልብ ጩኸት ለማስተጋባት ቀኝ እጁን የሚዘረጋ?

በምድር ላይ ትልቁ ውድቀት ለክብር ተጠርቶ በውርደት መኖር ነው። ወሲባዊ ርኲሰት የሚያደርገው ይኽንን ነው። የሕይወት ዓላማንና ዐቅምን ነጥቆ፣ በትርጒም የለሽ ሕይወት እና በጥፋተኝነት ስሜት ውስጥ በመዝፈቅ፣ በማይቆም የውርደት አዙሪት ውስጥ እንድንዳክር ያደርጋል። 📚የኅሩያን ሕይወት (ምዕራፍ 8)

Psalm 119:101-104 AMPC [101] I have restrained my feet from every evil way, that I might keep Your word [hearing, receiving, loving, and obeying it]. [Prov. 1:15.] [102] I have not turned aside from Your ordinances, for You Yourself have taught me. [103] How sweet are Your words to my taste, sweeter than honey to my mouth! [Ps. 19:10; Prov. 8:11.] [104] Through Your precepts I get understanding; therefore I hate every false way.

ክርስቶስ በምድር እስክንባል ድረስ ቃሉ ከእኛ ጋር መዋሓድ አለበት። ምክንያቱም፣ እኛ የክርስቶስ መዳረሻ እግሮች፣ መዳሰሻ እጆች፣ ማጽናኛ አንደበቶች፣ መመልከቻ ዐይኖች ነንና። ዲ. አ. መ.

Purity Matters - Статистика и аналитика Telegram-канала @puritymatters7