Dr. Estifanos(MD, Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ
Открыть в Telegram
ለ አዕምሮ ህክምና እና ምርመራ በ 0949476776 ይደውሉ በ Rama psychiatry & Rehabilitation center ያገኙኛል 📌ራማ የአዕምሮ ህክምና ማዕከል 📞+2519-85-52-88-88 📞+2519-99-67-68-69 📍:- Ayat Square,200m On the Main Road to Arabsa.(use google map).https://maps.app.goo.gl/yuEA1YiY76BCE6Q
Больше2 882
Подписчики
Нет данных24 часа
-47 дней
-2430 дней
Архив постов
Repost from Brook Thoughts
Article for Capital Newspaper on this year’s Mental health day theme “Lived experiences heard: real voices, real change” and the situation in Ethiopia.
https://capitalethiopia.com/2026/10/25/real-voices-real-change-%e1%8d%a1-ethiopias-mental-health-care-is-learning-to-listen/
'ለሰው ልጅ ትልቁ የመነሳሳት ምንጩ የበላይ መሆን/በልጦ መገኘት ነው' ይለናል አልፍሬድ አድለር::
የሰው ልጅ መታየትን ይፈልጋል፤ ታዋቂ እና ዝነኛ መሆንንም አንጠላም:: ሁሉም በመጠኑ ሲሆን ክፋት የለውም::
ይህን የበላይነት: አንዳንዱ ሌሎችን ባልጎዳ መልኩ ራሱ ላይ እየሰራ ፤ ሌላው ደግሞ ይበልጡኛል ብሎ ያሰባቸውን ጥሎ እና አጣጥሎ እየተረማመደባቸው ሊያሳካው ይችላል::
ለመሆኑ እኛ የቱ ጋር ነን?
እንደ ማህበረሰብ: ብሎም እንደ ሃገር ያሳለፍነው፤ እያሳለፍነውም ያለው ነገር ያሳዝናል:: የበፊት 'ጨቋኝ መደቦች' አሁን ተጨቋኝ ሁነዋል.. የጊዜ ጉዳይ እንጂ የአሁን 'ተጨቋኞች' እድሉን ሲያገኙ ጨቋኝ ሁነው መከሰታቸው የማይቀር ነው:: ባልታከመ Collective trauma ውስጥ ማለፍ መዘዙ ብዙ ነው::
ታዲያ ይህ የጨቋኝ ተጨቋኝን አዙሪት ለመረዳት አልተቻለንም..ወይ ልንረዳው አልፈለግምም::
ይህ አዙሪት እንዲቀጥል የሚፈልጉ የሰው ቁስልን በመቆስቆስ እና ሆድ በማስባስ የሚተዳደሩ ሙሾ አውራጆች የማህበረሰቡን ልብ ሰልበውታል:: ለነዚህ ሰዎችም: ለማህበረሰቡም ልቡና ይስጥልን!
ይህንን አዙሪት እንዴት ይቋጭ? ጉዳዩ ውስብስብ ቢሆንም: የሚከተሉት የመፍትሄ ሃሳቦች ይመስሉኛል:-
- ከልብ የመነጨ እና ሁሉን አካታች ውይይት፤
- የተፈጠሩ ክስተቶች ላይ መተማመን: ይቅር መባባል፤
- ከፖለቲከኞች እና ነጻ ያልወጡ ነጻ አውጪዎች Manipulation ራስን መጠበቅ፤
- ቁስልን ከሚቀሰቅሱ አሉታዊ ትርክቶች ራስን መጠበቅ፤
- ሰውን በሰውነቱ ማክበርን መለማመድ፤
- የሌሎችን ባህል እና ትውፊት ማክበርን መለማመድ..
- ከማህበረሰባዊ grandiosity (የተመረጥን ነን..የተዘከርን ዘሮች ነን..) ከሚል ትርክት በመውጣት ዘመኑን መዋጀት:
ሰላም ለሃገራችን!
+2
ዜና መዋዕል
***
ዛሬ መስከረም 30/2019 ዓ.ም የአለም የአዕምሮ ጤና ቀን በሃገር ደረጃ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል፤ 'የህይወት ተሞክሮዎች ተደማጭነት ይረጋገጥ: እውነተኛ ድምጾች ለእውነተኛ ለውጥ' በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል::
ይህ ቀን መታሰብ የጀመረው እ.ኤ.አ በ 1992 ነበር፤ በሃገራችን ኢትዮጲያ ሲከበርም ለ 14 ኛ ጊዜ ነው::
በዛሬው ፕሮግራማችን: የፓናል ውይይት እና የጥናታዊ ጽሁፎችን ጨምሮ ሌሎች ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ቀርበዋል::
ይህ በዓል ለአዕምሮ ጤና ሊሰጥ የሚገባውን ትኩረት ከማጉላት አንጻር ያለው ሚና ትልቅ ነው::
የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የተቀናጀ አዕምሮ ወ አካላዊ ህክምናን በመስጠት ላይ ያለ: Neuroscience ማዕከል ለመሆን አልሞ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ትልቅ ተቋም ነው:: ይህንን ትልቅ ሃገራዊ ዝግጅት በማዘጋጀታችን ትልቅ ክብር ይሰማናል::
ቅድሚያ ለአዕምሮ ጤናችን!
Join us for World mental Health Day 2026! Now on Air
Eka Kotebe Hospital warmly
invites all interested participants
for a day of learning, sharing, and meaningful discussion featuring:
🎤 Keynote Speech
🎬 Documentary Screening
💬 Panel Discussion – Lived Experience
🔬 Research Presentations
📅 Date: 30/01/2019 E.C.
📍 Venue: Eka Kotebe Hospital 4th Floor
Participate • Learn • Earn CEUs!
join with https://meet.google.com/rus-owoo-fem
World mental Health Day 2026! 🧠
Eka Kotebe Hospital warmly
invites all interested participants
to join us for a day of learning, sharing, and meaningful discussion featuring:
🎤 Keynote Speech
🎬 Documentary Screening
💬 Panel Discussion – Lived Experience
🔬 Research Presentations
📅 Date: 30/02/2019 E.C.
🕝 Time: 2:30 PM
📍 Venue: 4th Floor
Participate • Learn • Share • Earn CEUs!
join with https://meet.google.com/rus-owoo-fem
World mental Health Day 2026! 🧠
Eka Kotebe Hospital warmly
invites all interested participants
to join us for a day of learning, sharing, and meaningful discussion featuring:
🎤 Keynote Speech
🎬 Documentary Screening
💬 Panel Discussion – Lived Experience
🔬 Research Presentations
📅 Date: 30/02/2019 E.C.
🕝 Time: 2:30 PM
📍 Venue: 4th Floor
Participate • Learn • Share • Earn CEUs!
join with https://meet.google.com/rus-owoo-fem
🌍💚 NOTHING ABOUT US WITHOUT US
🧠 World Mental Health Day 2026
“Lived Experiences Heard: Real Voices, Real Change.”
Join us for a powerful live panel discussion bringing together:
✨ People with lived experience
⚖️ A legal professional and mental health advocate
🧠 A psychologist
🏛 A representative from the Ministry of Health/Government institution
🎤 An experienced moderator
Let’s talk about mental health rights, stigma, access to care, and why people with lived experience must have a voice in the decisions that affect their lives.
📅 Monday, 12 October 2026
⏰ 8:00 PM onwards
💻 Live Online | Amharic
🤝 Alenelachehu Charitable Organization in collaboration with MOH and EngenderHealth
🔗 Register here:
👉 https://forms.gle/ZQrJ4aYPqvU8QE5z6
💚 Your voice matters. Your experience matters. Your participation can help create change.
#WorldMentalHealthDay #NothingAboutUsWithoutUs #MentalHealthEthiopia #LivedExperience #MentalHealthMatters #RealVoicesRealChange
Honored to attend the EPA-AAP Conference at the Adwa Victory Memorial Museum in Addis Ababa, Ethiopia.
This year’s theme, "Digital Psychiatry in Africa: Leveraging AI for Accessible and Quality Mental Health Care," brought together stakeholders from across Africa and experts from Canada for impactful workshop and presentations.
It’s inspiring to see the association’s progress in hosting such impactful conference.
Honored to attend the EPA-AAP Conference at the Adwa Victory Memorial Museum in Addis Ababa, Ethiopia.
This year’s theme, "Digital Psychiatry in Africa: Leveraging AI for Accessible and Quality Mental Health Care," brought together stakeholders from across Africa and experts from Canada for impactful workshop and presentations.
It’s inspiring to see the association’s progress in hosting such impactful conference.
ጥቁር እና ነጭ አረዳድ(Black and White Thinking)
***
የድሮ TV ነገሮችን ጥቁር እና ነጭ አድርጎ ነበር የሚያሳየን:: የዚህ ዘመን ትውልዶች ቆየት ያሉ ክሊፖችን ስናይ: የድሮ ዘመን እንደ ክሊፑ ጥቁር እና ነጭ እንደሆነ አስበን ይሆናል😉 ምድር ግን ብዙ መልክ ያላት ባለ ብዙ ህብረ ቀለም ናት!
አንዳንድ ሰዎች ልክ እንደ ድሮ TV አዕምሯቸው ነገሮችን ጥቁር እና ነጭ አድሮጎ ይስልባቸዋል:: አንዳንድ ሰዎችን በቅጽበታዊ ሁነቶች ተነስተው በጣም ጥሩ ያደርጓቸውና መልዓክ ናችሁ ይሏቸዋል ፤ ትንሽ ህጸጽ ሲያገኙባቸው ደግሞ በጣም አክፍተው ይስሏቸውና ከሰይጣን ያዛምዷቸዋል:: አንድ የረሱት ነገር የሰው ልጅ መልዓክም ሰይጣንም ያይደለ : ጥሩ መጥፎም ጎኖች ያሉት 'ሰዋዊ' ፍጥረት መሆኑን ነው::
ይህ አስተሳሰባቸው ማህበራዊ ህይወታቸውን ይፈትነዋል:: በዚህ ጽንፍ መሃል እየዋለሉ ግንኙነታቸው መርጋት ይሳነዋል::
ይህ ጽንፍ የመያዝ አባዜ(black and white dichotomous thinking) በዘር ፓለቲካው፣ በአክራሪ ሃይማኖተኝነት ውስጥ በደምብ ይንጸባረቃል::
አንዱ ብሄርተኛ ሌላውን ከክፉት ውጭ መሳል እያቃተው፤ አክራሪ ሃይማኖተኛውም የሌላውን ሃይማኖት የማንቋሸሽ አባዜ ተጠናውቶት ተመልክተናል:: በአንጻሩ የሱ/የሷ መንጋ አንዳች ህጸጽ እንደሌለበት ሲመጻደቁ ማየት ትርፉ ትዝብት ነው::
ይህ Black or white thinking መጥፎ ያልነውን አካል መልካምነት፤ መልካም ነው ብለን የደመደምነውን አካል ህጸጽ በሰውኛ እሳቤ እንዳንረዳ መሰናክል ይሆንብናል:: ለቁንጽል ድምዳሜ ይዳርገናል::
ይህ አስተሳሰብ እንደ ሰውም እንደ ሃገርም ፈተና እያመጣብን እንደሆነ መናገር ይቻላል::
አሻም!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው: የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
+1
📢 የስፖንሰርሺፕ ጥያቄ
የእኔ ድርሻ በጎ አድራጎት ማህበር በመስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም. የአዲስ ዓመትን በዓል ከኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የአእምሮ ጤና ክፍል ከሚገኙ ታካሚዎች ጋር በጋራ ለማክበር የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር አዘጋጅቷል።
ይህ መርሃ ግብር ታካሚዎች በአዲሱ ዓመት የፍቅር፣ የተስፋ፣ የክብርና የማህበራዊ ድጋፍ ስሜት እንዲያገኙ የሚያግዝ ልዩ የበጎ ፈቃድ ተግባር ነው።
🙏 ለዚህ መልካም ተግባር የሚቻለውን ድጋፍ እንዲያደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ለበለጠ መረጃ
09127781 71
የእኔ ድርሻ በጎ አድራጎት
https://t.me/TizuPsychology
Hello there, dear.
I hope you are having a blessed weekend.
Since you are the panelist on our online event titled "Changing the Narrative on Suicide" this is a kind reminder that the program will be starting at 7:00pm. You can use the following link to join http://meet.google.com/sbn-koae-nxs
Join us to a panel discussion
💛ስለ ራስ ማጥፋት ያለንን አመለካከትና አረዳድ እንለውጥ!
እሁድ፣ ጳጉሜን 1 ሁላችሁም ተጋብዛቹዋል
መስከረም 10 (ሴፕቴምበር 10) ዓለም አቀፍ የራስ ማጥፋት መከላከያና ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው። ይህ ቀን ስለ ጉዳዩ በግልጽ በመነጋገር ግንዛቤን የምናሳድግበት፣ ዝምታን የምንሰብርበት፣ የተሳሳቱ አመለካከቶችን እና በእዚህ ዙሪያ የሚታየውን ማግለልሎችን (Stigma) የምናስወግድበት እንዲሁም ተስፋን የምናሰርጽበት ልዩ ወቅት ነው። 🫂
አለንላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅት እና AURA ይህንን እጅግ አስፈላጊ ቀን በማሰብ፣ ልዩ በሆነ የበይነ-መረብ (የቨርቹዋል) ውይይት ላይ እንድትሳተፉ በታላቅ አክብሮት ጋብዘንዎታል፦
🎙 ርዕስ፦ ስለ ራስ ማጥፋት ያለንን አመለካከትና አረዳድ እንለውጥ!
📅 ቀን፦ እሁድ፣ ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም (ሴፕቴምበር 6፣ 2026)
⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት (7:00 PM)
💻 የቀጥታ ስርጭት፦ በጉግል ሚት (Google Meet)
አብረን ለመነጋገር፣ ለመደማመጥ፣ እርስ በርስ ለመደጋገፍና የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ ሁላችንም አብረን እንቁም! ❤️
🎟 አሁኑኑ ይመዝገቡና የለውጡ አካል ይሁኑ!
https://forms.gle/1PABH9xgoG775Tpk8
ብቻዎን አይደሉም፤ እርዳታ ማግኘት ተስፋን ያለመልማል!💛
Repost from Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)
#HelloTomorrow
የአእምሮ ህመምን እንዴት ነው የምንረዳው?
https://youtu.be/UxRrF0LF3IE?si=pE-8ST4t55fCk_E8
