ግጥም
Открыть в Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Больше5 651
Подписчики
+824 часа
+247 дней
+11730 дней
Архив постов
5 663
#ርዕሰ_ያጣ_ግጥም
እፉየ ገላ ነኝ ያንቺ መጫወቻ
በትንፋሽሽ ሙቀት በራሪ ለብቻ
እፍ! በይኝና ልብረር አንቺ ሳቂ
በደስታ ሰክረሽ ቀን በቀን ድመቂ
እፉየ ገላሽ ነኝ አባሪኝ በትንፋሽ
አየር ላይ ሰፍፌ አንቺን ቁልቁል ልይሽ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 663
እኔን ከፋኝ ብላ ዓለም ላትጨነቅ
መቆዘሜን ትቼ በመጠኑ ልሳቅ
እርሷ ምን ቸገራት በእኔ ሀዘን ትጨነቅ
ቢከፋም ቢለማም እኔው ለእኔ ልሳቅ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 663
#አልፈርድብሽም
ጥሩ ህሊና አለሽ መልካም ነሽ ብልሽም
ቆሜ ስንከላወስ ያለሁ ቢመስልሽም
የምነግርሽ አለኝ ካንቺ ማልደብቅሽ
አይገባሽም እንጅ እኔን ስላይደለሽ
ጀግናም ሰው ይሞታል ሲሉ ስለሰማሽ
እናም የኔ ጀግና ይኸው ሰው ገለሻል
ሰው የራበው አንጀት የማይሞት መስሎሻል🔪!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 663
ኖትኮይን በቅርቡ ሊስት እንደሚደረግ ይጠበቃል ሊስት ሲደረግ ግን የአገልግሎት ክፍያ/Gas Fee መጠየቁ አይቀርም ለዚህም TON ኮይን ያስፈልገናል ይህ ኮይን በቴሌግራም ዋሌት ላይ ባሁኑ ሰአት ከ650 - 700 ብር ድረስ ይሸጣል ነገር ግን ይሄን ኮይን ቀላል ታስኮችን በመስራት ብቻ በነፃ የሚሰጡን ቦቶች አሉ
👉ከነዚህ ቦቶች ውስጥ አንዱ ፕሪቶን ድሮፕ የሚባል ቦት አለ ለመጀመር ይሄን ሊንክ በመንካት ማስጀመር
https://t.me/preton_drop_bot?start=e134de39-7b23-40b2-8f75-c1c922a4ccba
👉በመቀጠል የሚመጣውን ቻናል(https⚔️:/./t.me/preton_eng/8)
ጆይን ማድረግ
ከዛም የሚሰጣችሁን ሊንክ ለሌሎች በማጋራት TON ኮይን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል
👉ልክ 1 TON እንደደረሳችሁ በቀጥታ ወደ ዋሌታችሁ ማስተላለፍ ትችላላችሁ 💬
5 663
ተደግፌ ነበር የሰው አጥር ትላንት
ተሰብሮ ጥሎኛል ሁሉም ሆኖ ወረት
አይ አለማወቄ ከንቱ ነበርኩ እኔ
ፈጣሪ እያለልኝ ፍጡርን ማመኔ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 663
#ብትኖሪ_ባትኖሪ!
ለእኔ ቦታ የለው መምጣትትሽ መቅረትሽ
ባለሽበት ሆነሽ ቀን በቀን ልውደድሽ
ማጣት አያርቀው ማግኘት አያቀርበው
የፍቅር መነሻው ሚዛኑ ልብ ነው❤️
እድሜ ቢገሰግስ በዓመታት ቢቆጠር
ዘላለማዊ ነው አያረጅም ፍቅር
ብትኖሪ ባትኖሪ ብትርቂ ብትቀርቢ
የእኔን ናፍቆ መኖር ቀን በቀን አስቢ
ጎዳናው እድሜያችን ትዝታን ጎትቶ
ያመጣው የለም ወይ ከትላንት አስማምቶ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 663
#ገጣሚ_ኤልያስ_ሽታሁን ከሁሉም በላይ በዚህ ቻናል ይነግሳል ! ሌሎችም ድንቅ እና እውቅ ገጣምያን ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ፣ ኤፍሬም ስዩም ፣ ገብረክርስቶስ ደስታ ፣
መስፍን ወንድወሰን አስታወሰኝ ረጋሳ እና ሌሎች ገጣሚያን ስራቸው በዚህ ቻናል ይለቀቃል ! እናንተ ቻናሉን ተቀላቀሉ #Share በማድረግ ቤተሰባዊ ሀላፊነታችሁን ተወጡ🙏 እኔ @Henilogy ነኝ 🥰🥰🥰🥰🥰 ኩሩ ኢትዮጵያዊ
t.me/eliyasshitahun
t.me/eliyasshitahun
t.me/eliyasshitahun
5 663
የዓለም ስልጣኔ ዘምኑ ሲስፋፋ
ለልብ ስብራት መድኃኒቱ ጠፋ!!!
ለተሰበረ ልብ ክህደት ላደቀቀው
ከፍቅር በስተቀር ከቶ ሀኪሙ ማነው?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 663
#ነይ_አብረን_እንጠጣ!!
ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል ጌሾ
ነይ እንጠጣ ውዴ ላለመባል ዋሾ
እውነቱን እውነቱን እንድንነጋገር
ደጋግመን እንጠጣ ነይ አብረን እንስከር
አንቺም የልብሽን እኔም የልቤን ምት
በጌሾ በብቅል በሰካራም ድፍረት
መደባበቅ ሳይኖር ከማስመሰል ወጥተን
ከጠጁ ከጠላው እንጠጣ ደጋግመን!!!
እውነት በመናገር ነፃነት እንውጣ
ማስመሰል ይገፈፍ ነይ አብረን እንጠጣ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 663
ሞትን ድል አድርጎ ቃሉን አከበረ
የሰይጣንን ቅጥር በድል ሰባበረ
አዳም ነጻ ወጣ ባርነት ተሻረ
የሲኦል ከተማ በቃል ተሸበረ።
➕ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን➕
🔤🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤🌷🔤🌹
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 663
•sᴛᴜᴄᴋ ɪɴ ᴀ ɢᴇɴᴇʀᴀᴛɪᴏɴ ᴡʜᴇʀᴇ ʟᴏᴠᴇ ɪs ᴊᴜsᴛ ᴀ ǫᴜᴏᴛᴇ ᴀɴᴅ ʟʏɪɴɢ ɪs ᴛʜᴇ ɴᴇᴡ ᴛʀᴜᴛʜ°•🚬
https://t.me/OFFICIAL_YANET
5 663
እባክሽ አንች እርግብ ነይ ተላኪኝማ
ሚስጥሬን ደብቀሽ ሌላ ሰው ሳይሰማ
ባደግኩበት ምድር በተወለድኩበት
አኩኩሉ አባሮሽ በተጫወትንበት
ለነበሩ ልጆች እኔ ለማውቃቸው
ለሁሉም ንገሪ እንደምወዳቸው
አደራ የኔ ውድ መልዕክቴን ስጫቸው
እነዳንረሳሳ ደግመሽ ንገሪያቸው
ዛሬ እንጀራ ሆኖ ምንም ብንራራቅ
ብዙ ትዝታ አለን እርቆ የማይርቅ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 663
#ትለያለሽ_እማ
ፍትህ በምድር ካለ ሰውም ካስተዋለ
መልካም እየሰራ መልካም ጋር ከዋለ
ንፁህ ፍቅር የት ነው እንዲያው ከተባለ
እውነተኛ አፍቃሪ እንዳንቺ ማን አለ
አያልቅ አይጎልብሽ የፍቅር አውድማ
የመልካም ሞዴል ነሽ የጥሩነት አርማ
ምንም ብትከፊ ውስጥሽ አያውቅም ቅር
አንች ነሽ ሚዛኗ የእውነተኛ ፍቅር
አያልፍ ወረት የለው ሁሌም የሚጠማ
የርህራሄ ምንጭ የመውደድ ቄጠማ
በፍትህ ፍርድ ላይ ብትቀመጭማ
ፍቅርሽ የትም የለም ትለያለሽ እማ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
