Fairway School plc
Открыть в Telegram
A vision that works for all our kids. ሁሌም ስነምግባር እናስተምራለን። Fairway School PLC
Больше5 197
Подписчики
+324 часа
+127 дней
-1030 день
Архив постов
5 197
🌟 እንኳን ደስ አላችሁ! 🌟
ውድ የፌር ዌይ ስኩል (Fairway School) ቤተሰቦች፤
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን በዘንድሮው ብሔራዊ ፈተና ላስመዘገቡት የሚያኮራ ውጤት የተሰማንን ጥልቅ ደስታ እየገለጽን፤ ለውድ ተማሪዎቻችን፣ ሁሌም ከጎናቸው ለነበሩ ወላጆች እንዲሁም ሌት ተቀን ለደከሙ መምህራን በሙሉ ልባዊ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
ለተማሪዎቻችን በቀጣይ የዩኒቨርሲቲ ጉዟቸው የላቀ ስኬትን እንመኛለን!
ፌር ዌይ ስኩል
5 197
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤታቸውን ዛሬ ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምረው ማየት ይችላሉ - የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸውን ማስፈንጠሪያዎች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ አድርጓል፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡
በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ
https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ማቅረብና ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et፣ ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram፣ አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡
https://result.eaes.et/sms መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡
5 197
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን በሙሉ !
እንኳን ለነብዩ መሃመድ የልደት በዓል
(መውሊድ) በሠላምና በጤና አደረሳችሁ፤ በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆን ፌርዌይ ስኩል መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
መልካም በዓል !!
