ru
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Открыть в Telegram

📈 Аналитический обзор Telegram-канала EEP Communication

Канал EEP Communication (@eepcommuication) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 554 подписчиков, занимая 8 397 место в категории Технологии и приложения и 2 165 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 554 подписчиков.

Согласно последним данным от 21 июня, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 10, а за последние 24 часа — 1, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 25.74%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 14.94% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 003 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 2 323 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 9.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
EEP Communication

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 22 июня, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Технологии и приложения.

15 554
Подписчики
+124 часа
+87 дней
+1030 день
Архив постов
የፈተና አሰጣጥ ተአማኒነትን ለማሳደግ የሚያስችል ዲጂታላይዝ የፈተና ስርዓት መተግበሪያ ተዘጋጅቷል …….///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የበለፀገው የዲጂታል ፈተና ስርዓት መተግበሪያ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ማስተባበሪያ መምሪያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ አብዱ ይማም ከተቋሙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች እና ከሠራተኛ ማህበር አመራሮች ለተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በዲጂታል የፈተና ስርዓት አተገባበር ዙሪያ በተዘጋጀው ሥልጠና ላይ እንደተናገሩት የበለፀገው የፈተና ስርዓት  ወጪ እና ጊዜን በመቆጠብ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል፡፡ የዲጂታል የፈተና ስርዓቱ የፈተና አሰጣጡን ምቹ ከማድረጉም ባሻገር የፈተና ውጤት ተአማኒነትን እንደሚያሳድግም ነው የገለፁት። በፈተና ስርዓቱ ላይ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ የሳይበር ሴኪዩሪቲ፣ የኢትዮ ፓወር አካዳሚ የሥራ ክፍሎች እና ተፈታኞች ከፍተኛ ሚና ያላቸው መሆኑን የገለፁት ደግሞ በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ማስተባበሪያ መምሪያ የኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ኢንጂነር ቃለአብ አየለ ናቸው። ከእያንዳንዱ የሥራ ክፍል ሁሉንም የሙያ መደቦች ለመለካት የሚያስችል የመመዘኛ ጥያቄዎች በፈተና ቋት ውስጥ እንዲቀመጡ ይደረጋልም ብለዋል። ይህ ዲጂታላይዝ የፈተና ስርዓት የደረጃ ዕድገት፣ዝውውር፣ የቅጥር እና ሌሎች የምዘና ፈተናዎችን ለመስጠት የሚያስችል መተግበሪያ መሆኑ ተገልጿል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+7

መምሪያው የትውውቅ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማካሄድ ጀመረ ….///…. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተቋም ደህንነት መምሪያን ለተቀላቀሉ አዳዲስ ባለሙያዎች እና በመከላከያ ሚኒስቴር ተመልምለው የተላኩ የቀድሞ መከላከያ ሚኒስቴር አባላት የትውውቅ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የትውውቅ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ዋና ዓላማ የተቋሙን ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ተቋማዊ ስትራቴጂ፣ የተቋሙ አደረጃጀቶች እና አሰራር ተቋሙን ለተቀላቀሉ አዳዲስ ሠራተኞች ለማሳወቅ ነው፡፡ በትውውቅ መርሐ ግብሩ ላይ የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ከሊል ሽፋ እንደተናገሩት አዳዲሶቹ ባለሙያዎች እና በጡረታ ተሰናብተው የተቋሙን የንብረት እና የሰው ሀብት ደህንነት ሥራን ለማገዝ የተቀላቀሉ የቀድሞ መከላከያ አባላት በሀገሪቱ በሚገኙ የተቋሙ ሪጅኖች ምድብ ተሰጥቷቸው ይሰማራሉ፡፡  ዳይሬክተሩ በሰጡት ቃል ባለፉት ሶስት ዓመታት እንደ ተቋም እና ሀገር በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ውድመት መድረሱን ይፋ አድርገው በተቋም ደህንነት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ የበላይ አመራሩ እና ቦርዱ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ በመሆኑም መድረኩ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መምሪያውን ለተቀላቀሉ ባለሙያዎች ስምሪት ከመዉሰዳቸው በፊት የሥራ ደርሻቸውን በማሳወቅ በተቋመ ላይ የሚከሰቱ የአደጋ ስጋቶች ለመከላከል ያለመ መሆኑን በመድረኩ ተመላክቷል፡፡ ባለፈው ሩብ ዓመት መምሪያው በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የተቋሙን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ ሥራዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መሰራቱን የገለፁት አቶ ከሊል መምሪያውን የተቀላቀሉ ባለሙያዎች ለሥራዉ መቀላጠፍ የጎላ ድርሻ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ ከፓዎር አካዳሚ ጋር በመተባብር የተዘጋጀዉ ይህ የትውውቅ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+9

ጣቢያው የሲስተም ማዘመን ስራ እየሰራ ነው ……..///…………   የግልገል ጊቤ 1 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የመቆጣጣሪያ የስካዳ ሲስተሙን የማዘመን ስራ እየሠራ መሆኑን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ንጉሳ ገለፁ። ሲስተሙን ማዘመን  ያስፈለገው ጣያቢው ከሃያ ዓመት በላይ የቆየ በመሆኑ ቀደም ሲል ይጠቀምበት የነበረውን ሲስተም  አሁን ካለው ቴክኖሎጂ ጋር  አጣጥሞ ለመስራት እና ኃይል  የማመንጨት ሂደቱን አስተማኝ ለማድረግ በማስፈለጉ እንደሆነ አቶ ደሳለኝ  ተናግረዋል። አዲሱ ስካዳ 250  የተባለው ሶፍትዌር የስካዳ ሲስተሙ ከዋናው ኃይል መቆጣጠሪያ ግሪድ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በፍጥነት መቀበል፣  ማስተላለፍ እና ኃይል  በማመንጨት ሂደት  ወቅት በዩኒቶች ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ከነምክያታቸው መዝግቦ ማቆየት የሚችል እንደሆነ ሥራ አስኪያጁ  አብራርተዋል። ለሲስተም ማሻሻያው የሚያስፈልጉ የቅድመዝግጅት እና የኢንስታሌሽን ሥራዎች በጣቢያው የጥገና ሰራተኞች መሰራቱን ገልፀዋል። በጀነሬሽን ቢዝነስ የኮንትሮል እና ኢንስትሩመንቴሽን ሥራአስኪያጅ አቶ ዳንኤል አበባው  የስካዳ ሲስተም ማሻሻያ የሲስተሙ አምራች ከሆነው የኦስትሪያው አንድሪዝ ሃይድሮ ጋር በተደረገው ስምምነት ሥራው መጀመሩን ገልፀዋል ። በስምምነቱ መሰረት  የግልገል ጊቤ 1  እና በጣና በለስ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ሲስተም የማዘመን ስራ የሚሚሰራ በመሆኑ ጊቤ 1 ማመንጫ ጣቢያ  የማዘመን ሥራው መጠናቀቁን አስረድተዋል፡፡ በጣና በለስም የማሻሻያ ሥራውን ለማከናወን አስፈላጊ ዕቃዎቸወ በመጓጓዝ ላይ መሆናቸውን አቶ ዳንኤል ገልፀዋል። እንደ አቶ ዳንኤል ገለፃ አንድሪዝ ሃይድሮ ዕቃዎችን ማቅረብ፣ የኦፕሬቲነግ ሲሰተም ማስተካከል  እና የፍተሻ ሥራዎችን የሚያከናውን ሲሆን  በተጨማሪም ከሁለቱ ጣቢያዎች ለተውጣጡ የኦፕሬሽን የጥገና ባለሙያዎች በሁለት ዙር ሥልጠና የሚሰጥ ይሆናል። ከሁለቱ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ለተውጣጡ የጥገና ባለሙያወች በመጀመሪያው ዙር ሥልጠና መስጠት የተጀመረ ሲሆን ሥልጠናው ለወደፊት የሚያስፈልጉ የጥገና ሥራዎችን በራስ አቅም ለመስራት መደላድል ይፈጥራል ተብሎ ይታመናል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+6

የውጤት ማስታወቂያ .....///..... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነሀሴ 01 ቀን 2017 ዓ.ም በኢንቫይሮመንታሊስት 1ኛ ፣ በሶሾሎጂስት 1ኛ እና በኦኩፔሽናል ሄልዝና ሴፍቲ የስራ መደብ ማስታወቂ
+4
የውጤት ማስታወቂያ .....///..... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነሀሴ 01 ቀን 2017 ዓ.ም በኢንቫይሮመንታሊስት 1ኛ ፣ በሶሾሎጂስት 1ኛ እና በኦኩፔሽናል ሄልዝና ሴፍቲ የስራ መደብ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን አሟልታችሁ ከተመዘገባችሁት ተወዳዳሪዎች መካከል በኢንቫይሮመንታሊስት 1ኛ ፣ በሶሾሎጂስት 1ኛ እና በኦኩፔሽናል ሄልዝና ሴፍቲ የስራ መደቦች ከተ.ቁ 1 እስከ 4 ያላችሁ በተሰጠው የጽሁፍ ፈተና አብላጫ ውጤት ያመጣችሁ በመሆኑ ከህዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በዋናው መ/ቤት ኮተቤ ብረታብረት በሚገኘው የትራንስሚሽን ቢዝነስ ቅጥርና ምደባ ቢሮ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ እየቀረባችሁ የቅጥር ፎርም እንድትሞሉ እናሳውቃለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም

የውጤት ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለኮይሻ የውሃ ኃ/ማ/ፕሮጀክት ሲቪል መሐንዲስ 1ኛ (ፒአር1) ጂኦሎጂስት 1ኘሰ (ፒአር1) እና ጂኦቴክኒካል ላብ ቴክኒሻያን 1ኛ (ኤስፒ 1) የስራ መደ
+1
የውጤት ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለኮይሻ የውሃ ኃ/ማ/ፕሮጀክት ሲቪል መሐንዲስ 1ኛ (ፒአር1) ጂኦሎጂስት 1ኘሰ (ፒአር1) እና ጂኦቴክኒካል ላብ ቴክኒሻያን 1ኛ (ኤስፒ 1) የስራ መደቦች ላይ የውጭ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት መስፈርቱን አሟልታችሁ የፅሁፍ እና የቃል ፈተናውን ወስዳችሁ ያለፋችሁ አመልካቶች ከጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሲቪል ኢንጂነር እና በጂኦሎጂስት የሥራ መደቦች ላይ ያለፋችሁ ተወዳዳሪዎች የፋይዳ መታውቂያ ትምህርት ማስረጃችሁን እና ኮስት ሼሪንግ በመያዝ እንዲሁም ለጂኦቴክኒካል ላብ ቴክኒሺያን 1ኛ ያለፋችሁ ተወዳዳሪዎች የፋይዳ መታወቂያ፣ የትምህርት ማስረጃ እና ሲ.ኦ.ሲ በመያዝ እየቀረባችሁ የቅጥር ፎርም እንድትሞሉ እናሳውቃለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

‎በደሴና እና ኮምቦልቻ ከተሞች በከፊል የኃይል መቋረጥ ተከስቷል ‎.....///..... ‎በደሴና እና ኮምቦልቻ ከተሞች በከፊል የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምስራቅ 1 ሪጅን አስታወቀ። ‎ ‎በሪጅኑ የኦፕሬሽንና ጥገና መምርያ ዳይሬክተር አቶ በድሩ አህመድ እንደገለጹት የኃይል መቋረጡ ያጋጠመው በኮምቦልቻ አንድ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ካሉት ሁለት ትራንስፎርመሮች መካከል በአንደኛው ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ  ምክንያት ነው። በአደጋው የትራንስፎርመሩ ታፕ ቸንጀር ላይ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል። ‎ ሪጅኑ ‎የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ርብርብ እያደረገ በመሆኑ የኃይል መቋረጥ ባጋጠመባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+7

የፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ለማሻሻል የባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ወሳኝ ነው ………///…….. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በራስ አቅም የሚገነባቸውን ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ለማሻሻል የባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ወሳኝ መሆኑን የኢንጅነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ አስታወቀ። ተቋሙ በራስ ኃይል በሚሰራቸው ፕሮጀክቶች ላይ ለሚሳተፉ ባለሙያዎች በተዘጋጀው ሥልጠና ላይ የዘርፉ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ውድነህ የማነ እንደገለጹት ተቋሙ ባለሙያዎች በተግባር የሚያውቁትን ሥራ ሣይንሳዊ በሆነ መንገድ በመደገፍ አቅማቸውን ለማጎልበት አቅዶ እየሰራ ነው። በፕሮጀክቶች ላይ በረጅም ጊዜ ልምድ የሚሰሩና የትምህርት ማስረጃ የሌላቸውን ባለሙያዎች በሙያቸው የዕውቅና ሰርተፊኬት ለመስጠት ለማስቻል ሥልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል። ተቋሙ በራስ አቅም ካሪኩለም ቀርፆ መሰል ሥልጠናዎችን መስጠት መቻሉ ትልቅ ለውጥ መሆኑን ጠቁመዋል። ባለሙያዎቹ የተሰጣቸውን ሥልጠና ወደ ተግባር በመለወጥ በፕሮጀክት አፈጻጸሞች ላይ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻው አሳስበዋል። የተቋሙ የሰው ሀብት ሥራ አስፈጻሚ አቶ አታላይ አበበ በበኩላቸው የሠራተኞችን የተግባር ዕውቀት የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ሣይንሳዊ ሥልጠናው ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ባለሙያዎቹ የአቅም ግንባታ ሥልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ ጥሪ አቅርበዋል። ለአምስት ቀናት የሚቆየውን ሥልጠና 42 የሲቪልና የኮንስትራክሽን ቴክኒሺያኖችን እና 12 የማከፋፊያ ጣቢያ የኤሌክትሮ መካኒካል ባለሙያዎች እየወሰዱ ይገኛሉ። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+8

‎የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ ለምረቃ ዝግጁ ሆኗል ‎.....///..... ‎በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአይሻ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ የግንባታ ሥራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለምርቃት ዝግጁ መሆኑን የጀነሬሽን ቢዝነስ ዩኒት ገለጸ። ‎ ‎በቢዝነስ ዩኒቱ የዕቅድና ክትትል ባለሙያ አቶ ሰለሞን ተረፈ እንደገለጹት የአይሻ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ የተጀመረው በየካቲት 2016 ዓ.ም ነበር። ‎ 32 ተርባይኖች የተተከሉበት የግንባታው የመጀመሪያው ምዕራፍ፣  30 የሠራተኛ መኖሪያ ቤቶች ግንባታና የስዊች ያርድ የግንባታ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለምርቃት ዝግጁ ሆነዋል። ‎ በመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ ጣቢያው ሲጠናቀቅ ማመንጨት ከሚችለው 120 ሜጋ ዋት ውስጥ 80 ሜጋ ዋት እያመነጨ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ‎ ‎የቀሪው 16 ተርባይኖች ሥራ በ69 ሚሊዮን ዶላር ወጭ በምዕራፍ ሁለት ሥር ተካቶ ግንባታው እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል። ‎ ‎አሁን ላይ የስምንቱ ተርባይኖች ምርት ተጠናቆ ከቻይና የማጓጓዝ ሥራ መጀመሩንና በ45 ቀናት ውስጥ ሳይት ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አብራርተዋል። ‎ ‎የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 257 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር መሆኑንና ከዚህ ውስጥ ተቋሙ 15 በመቶውን ማለትም 38 ሚሊዮን ዶላሩ በኢትዮጵያ ብር ከፍሎ ማጠናቀቁን አስረድተዋል። ‎ ‎ሆኖም 85 በመቶውን የሚሸፍነው አበዳሪው የቻይና ኤግዚም ባንክ 114 ሚሊዮን ዶላር ከከፈለ በኋላ ቀሪውን በውሉ መሠረት ክፍያዎቹን ለሥራ ተቋራጩ መክፈል በማቋረጡ ምክንያት የፕሮጀክቱ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ አለመጠናቀቁን አቶ ሰለሞን ጠቁመዋል። አሁን ላይ የሁለተኛውን ምዕራፍ የግንባታ ፋይናንስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በመሸፈን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ‎ ‎ፕሮጀክቱ በንፋስ ኃይል የተሻለ የማምረት አቅም ያለው በመሆኑን ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ለምስራቁ ግሪድ የሲስተም መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ገልጸዋል። ‎ ‎የፕሮጀክቱ አማካሪ የተቋሙ የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዩኒት ሬዝዴንት ኢንጂነር አቶ እንድሪስ ገዙ በበኩላቸው አበዳሪው ባንክ የተወሰነውን ገንዘብ መልቀቅ ባይቻልም የሥራ ተቋራጩ የምዕራፍ አንድን የግንባታ ሥራዎች ማጠናቀቁን ገልጸዋል። ‎ ‎የምዕራፍ ሁለት የፕሮጀክቱን ሥራዎች ተቋሙ በራሱ ፋይናንስ ለማድረግ ከስምምነት ተደርሶ የቀሪ 16 ተርባይኖች የሲቪል ሥራ መጠናቀቁን አብራርተዋል። ‎ እንደ አቶ እንድሪስ ገለጻ ‎ተርባይኖቹ ሳይት እንደደረሱም የተከላ ሥራው እንደሚጀመርና ፕሮጀክቱን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል። ‎ ‎በኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ታሪክ የተቋሙ የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዩኒት በአማካሪነት ሲሳተፍ የአይሻ ቁጥር 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ የመጀመሪያ መሆኑን ያወሱት አቶ እንድሪስ ይህም የተቋሙ ከፍተኛ ወጭ ከማዳኑም ባሻገር የባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት በኩል ከፍተኛ ሚና መጫወቱን አስገንዝበዋል። ‎ ፕሮጀክቱ ‎ከአዲስ አበባ 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሶማሌ ክልል አይሻ ከተና አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን ዶንግ ፋንግ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን የተባለ የቻይና ሥራ ተቋራጭ ግንባታውን በማከናወን ላይ ይገኛል። የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 48 ተርባይኖች የሚኖሩት ሲሆን እያንዳንዳቸው 2 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት በድምሩ 120 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም አላቸው። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+8

‎ጣቢያው በሩብ ዓመቱ ከ34 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል አምርቷል ‎......//...... ‎በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአይሻ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በ2018 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ34 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል ማምረቱን የጣቢያው የጥገና ክፍል ኃላፊ ገለጹ። ‎ ‎ኃላፊው  አቶ ዮሐንስ አስማረ እንደገለጹት ጣቢያው በሩብ ዓመቱ በ32 ተርባይኖች 39 ነጥብ 72 ጊጋ ዋት ሰዓት ለማመንጨት አቅዶ 34 ነጥብ 67 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ያመረተ ሲሆን ይህም የዕቅዱን 87 ነጥብ 2 በመቶ ነው። ‎ ‎በተወሰኑ ተርባይኖች ላይ ከጀነሬተሩ የመነጨውን ኃይል ወደ ዩኒት ትራንስፎርመር በሚልከው ኮንዳክተር ላይ ባጋጠመ ቴክኒካል ችግር እና በዓመታዊ ጥገና ምክንያት ተርባይኖች ይቆሙ ስለነበር አፈፃፀሙ ዝቅ ማለቱን ተናግረዋል። ‎ ‎አሁን ላይ ያጋጠመው ቴክኒካዊ ችግር በመፈታቱና ዓመታዊ የጥገና ሥራዎች እየተጠናቀቁ በመሆኑ እንዲሁም ዓመታዊ የንፋስ አቅጣጫውና ፍጥነቱ እየጨመረ በመሆኑ በቀጣይ ጊዜያት የተሻለ ኃይል በማምረት ዓመታዊ ዕቅዱን ማሳካት እንደሚቻል ገልጸዋል። ‎ ‎በሩብ ዓመቱ ጣቢያውን ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ ከተዘረጋው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ጋር በማገናኘት ከጣቢያው የመነጨውን ኃይል ለጅቡቲ በቀጥታ ለመስጠት የሚያስችለውን የተሳካ የሙከራ ሥራ ማካሄዱንም ተናግረዋል። ‎ ‎በጣቢያው ከፍተኛ ንፋስና አቧራ በመኖሩ ተርባይኖቹን በየጊዜው ለማጽዳትና አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ የፍተሻና የጥገና ሥራዎችን ለማከናወን የሠው ኃይል እጥረት መኖሩን ጠቁመዋል። ‎ ‎በተጨማሪም በኮንትራት ሥምምነቱ መሠረት ለሦስት ዓመት ጥገና ሥራው የሚከናወነው በሥራ ተቋራጮቹ ድጋፍ መሆኑን አብራርተዋል። ‎ ‎ከአዳማ 1 እና 2 እንዲሁም ከአሸጎዳ በመቀጠል በአራተኛነት የተገነባው የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በዓመት 436 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+8

የጽሁፍ ፈተና ውጤትንና ለቃል ፈተና የተጠሩ አመልካቾችን ስለማሳወቅ ……..///………. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለኮይሻ የውሃ ኃ/ማ/ፕሮጀክት (Civil engineer I) ሲቪል መሐንዲስ I (ፔ
+4
የጽሁፍ ፈተና ውጤትንና ለቃል ፈተና የተጠሩ አመልካቾችን ስለማሳወቅ ……..///………. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለኮይሻ የውሃ ኃ/ማ/ፕሮጀክት (Civil engineer I) ሲቪል መሐንዲስ I (ፔአር1) ፣ (Geologist I) ጂኦሎጂስት I (ፒአር1) እና (Geothechnical Lab Technician I) ጂኦተክኒካል ላብ ቴክኒሻን I (ኤስፒ 1) የስራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መስፈርቱን አሟልታችሁ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም የተሰጠው ፈተና ውጤት ከዚህ በላይ የተገለፀው መሆኑን እያሳወቅን በቀጣይም ለቃል ፈተና የተጠራችሁ ሐሙስ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ጀነሬሽን ኮንስትራክሽን ቢሮ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም

ጣቢያው ለምርታማነት ማደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገለፀ ……..///………. የደብረብርሃን ቁጥር 2 ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በደብረብርሃን ከተማ እና ዙሪያው ለሚገኙ በርካታ ፋብሪካዎች አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ለምርታማነት ማደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስታወቀ። የጣቢያው ኃላፊ አቶ ዳኜ ይታገሱ እንደገለፁት ጣቢያው 33  እና 15 ኪሎ ቮልት አቅም ባላቸው 15 ወጪ መስመሮች አማካኝነት ለደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ዞንና ለሌሎች ግዙፍ ፋብሪካዎች ኃይል በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ በጣቢያው ባሉት 15 ወጪ መስመሮች በቀን በአማካኝ ከ110 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል እያቀረበ እንደሚገኝም ነው ኃላፊው የተናገሩት። እንደ አቶ ዳኜ ገለፃ ጣቢያው በተጨማሪም በ230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ለለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በቀን በአማካኝ 50 ሜጋ ዋት ኃይል በማቅረብ ላይ ነው። ለፋብሪካዎች ከሚያቀርበው ኃይል ባሻገር ጣቢያው ለደብረብርሃን ከተማ እና በአቅራቢያው ለሚገኙ እነዋሪ፣ ሸኖ፣ ሀገረማርያም፣ ይናገር፣ ጫጫ፣ ደነባ፣ መንዲዳ እና ፅጌረዳ ከተሞች ኃይል በማቅረብ ላይ ይገኛል። የካቲት 2011 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት የጀመረው ይህ ጣቢያ የኃይል አቅርቦቱን የሚያሳልጡ ሁለት አውቶ ትራንስፎርመሮች እና ሁለት ፓወር ትራንስፎርመሮች አሉት። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+4

ሪጅኑ የ2018 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ነው   ........///........ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ አንድ ሪጅን የ2018 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል። የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ገዛኸኝ እንደገለፁት የግምገማ መድረኩ በሩብ ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው። በሩብ ዓመቱ አስተማማኝ ኃይል ለደንበኞች ለማቅረብ እንዲቻል በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ መጠነ ሰፊ የኦፕሬሽንና ጥገና ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡  ለሦስት ቀናት በሚቆየው ግምገማ ላይ ሪጅኑ በሩብ ዓመቱ የዕቅድ ክንውን ላይ የታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች፣ መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ይካሔድባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሪጅኑ የሚገኙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሥራ አስኪያጆች እንደገለፁት ከደንበኞችና ኢንዱስትሪዎች ጋር የነበረው ግንኙነት መሻሻሉን፣ የኃይል መቆራረጥ ችግር ላይ አፋጣኝ መፍትሄ እየሰጡ መሆኑን እንዲሁም የሚወገዱ ንብረቶችን በአግባቡ የመለየት ሥራ በአግባቡ መስራታቸዉን አብራርተዋል፡፡ እንደ ሥራ አስኪያጆቹ ገለፃ በሩብ ዓመቱ የጥገና ሥራዎችን በራስ አቅም በማከናወን ችግሮችን ለመፍታት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም