ru
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Открыть в Telegram

📈 Аналитический обзор Telegram-канала EEP Communication

Канал EEP Communication (@eepcommuication) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 554 подписчиков, занимая 8 397 место в категории Технологии и приложения и 2 165 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 554 подписчиков.

Согласно последним данным от 21 июня, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 10, а за последние 24 часа — 1, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 25.74%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 14.94% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 003 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 2 323 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 9.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
EEP Communication

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 22 июня, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Технологии и приложения.

15 554
Подписчики
+124 часа
+87 дней
+1030 день
Архив постов
photo content
+4

ሪጅኑ የ2018 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ነው   ........///........ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ አንድ ሪጅን የ2018 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል። የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ገዛኸኝ እንደገለፁት የግምገማ መድረኩ በሩብ ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው። በሩብ ዓመቱ አስተማማኝ ኃይል ለደንበኞች ለማቅረብ እንዲቻል በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ መጠነ ሰፊ የኦፕሬሽንና ጥገና ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡  ለሦስት ቀናት በሚቆየው ግምገማ ላይ ሪጅኑ በሩብ ዓመቱ የዕቅድ ክንውን ላይ የታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች፣ መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ይካሔድባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሪጅኑ የሚገኙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሥራ አስኪያጆች እንደገለፁት ከደንበኞችና ኢንዱስትሪዎች ጋር የነበረው ግንኙነት መሻሻሉን፣ የኃይል መቆራረጥ ችግር ላይ አፋጣኝ መፍትሄ እየሰጡ መሆኑን እንዲሁም የሚወገዱ ንብረቶችን በአግባቡ የመለየት ሥራ በአግባቡ መስራታቸዉን አብራርተዋል፡፡ እንደ ሥራ አስኪያጆቹ ገለፃ በሩብ ዓመቱ የጥገና ሥራዎችን በራስ አቅም በማከናወን ችግሮችን ለመፍታት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+4

የማህበሩ አጠቃላይ ካፒታል  ከ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ደረሰ ‎…..…///……. የኢትዮ ኤሌክትሪክ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የሕ/ሥራ ማህበር በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ ካፒታሉ ከ 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን የማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ገለጹ፡፡ ሰብሳቢው አቶ አንበሴ ግዛቸው ይህን የገለጹት ‎የሕብረት ሥራ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የሥራ አመራር ቦርዱን 2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡ የማህበሩ ካፒታል በመጋቢት 2014 በጀት ዓመት ከነበረበት 995  ሚሊዮን 754 ሺህ 689 ብር በ2017 በጀት ዓመት ወደ 1 ቢሊዮን 925 ሚሊዮን 137 ቪህ 79 ብር  ማሳደግ  መቻሉን አመልክተዋል፡፡ በበጀት አመቱ ከተሰበሰበው ብር 815 ሚሊዮን 77 ሺህ 102 ብር ከ17 ሳንቲም ውስጥ  ለ1 ሺህ 70 አዲስ ብድር ጠያቂ አባላት 372 ሚሊዮን 388 ሺህ 204 ብር ከ19 ሳንቲም ብድር መስጠቱን ተናግረዋል። በተመሳሳይ በብድር ላይ ብድር ለጠየቁ 1 ሺህ 6 አባላት 423 ሚሊዮን 341 ሺህ 242 ብር ብድር መሰጠቱን ገልጸዋል ፡፡ በዚህም ማህበሩ በበጀት ዓመቱ በድምሩ 795 ሚሊዮን 729 ሺህ 446 ብር ከ21 ሳንቲም ለአባላት ብድር ሰጥቷል ብለዋል፡፡ በጀት ዓመቱ 1 ሺህ 763 አዲስ አባላትን ማፍራት የተቻለ ሲሆን በልዩ ልዩ ምክንያት ከማህበሩ 922 አባላት መልቀቃቸውን አብራርተዋል፡፡ ጠቅላለ ጉባኤው በቆይታው የብድር ምጣኔ ጣሪያውን ከነበረበት 800 ሺህ ወደ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የማሳደግ እና የብደር መክፈያ ጊዜውን ከ15 ዓመት ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዲል ወስኗል። በተጨማሪም የሥራ አመራር ቦርዱ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትን እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ማሻሻያን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+1

በተቋሙ የሚከናወኑ ሥራዎች ግልጽነትና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አለባቸው ‎.....///..... ‎በተቋሙ የሚከናወኑ ሥራዎች ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ያረጋገጡና የተቋሙን ጥቅም ያስጠበቁ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት፣ የኮርፖሬት ገቨርናንስና ኮምፕሊያንስ፣ የውስጥ ኦዲት እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፎች የ2018 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ በሪፖርቱ ‎የተቋሙን አሰራሮች በማዘመን ሀብቱን ከመጠበቅና ገጽታውን ከመገንባት ግልጸኝነትንና ተጠያቂነትን ከማስፈን እንዲሁም የሴቶችን ተሳትፎ ከማሳደግ አንጻር የተከናወኑ ሥራዎች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ቀርበዋል፡፡ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው በሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ማብራሪያዎችና ምላሾች ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ‎በግምገማው ማጠቃለያ እና የሥራ አቅጣጫ የሰጡት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በሩብ ዓመቱ በዘርፎቹ የተከናወኑ ሥራዎች ክፍተቶች የታየባቸውና ትኩረት የሚፈልጉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በተለይም ተቋሙ የሚሰራቸውን ሥራዎች ከማስተዋወቅና ከገጽታ ግንባታ አንጻር ከመረጃ አያያዝ ጀምሮ የሚስተዋሉ ችግሮች በአስቸኳይ መታረም እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ የውስጥ ኦዲት ሪፖርቶች በኦፕሬሽንና በፕሮጀክቶች ላይ አላግባብ የሚወጡ ወጪዎችን መቆጠብ የሚያስችል ምክረ ሀሳብ ለተቋሙ አመራር በሚያቀርብ መልኩ መዘጋጀት እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል። ‎ ‎ጊዜው የመፍጠንና የመፍጠር በመሆኑ የተቋሙን አሰራሮች ወደ ዲጂታል እንዲቀየሩ እና የሪፎርም ሥራዎች ወደ መሬት እንዲወርዱ ሁሉም አመራር በትብብርና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባው ጠቁመዋል፡፡ ‌‎ከመረጃ አያያዝ፣ ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ፣ ከፕሮጀክት አፈጻጸም፣ ከክትትልና ቁጥጥር ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች መኖራቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው እነዚህንና ሌሎች ችግሮች በጥናት ተለይተው መፍትሔ አምጪ ምክረ ሀሳቦች እንዲቀርቡ የፓወር አካዳሚ ሚና ከፍተኛ ሊሆን እንደሚገባም ነው የገለፁት። በሩብ ዓመቱ ‎ያልተሰሩት ሥራዎች በአጭር ጊዜ የድርጊት መርሀ ግብር ተዘጋጅቶ መከናወን እንዳለባቸውና ይሄን በማያደርጉ የሥራ ክፍሎችና አመራሮች ላይ ተጠያቂነት እንደሚኖር አብራርተዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content

photo content
+9

‎በዕቅድ እና ሪፖርት አቀራረብ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማረም ይገባል ~አሸብር ባልቻ ‎.....///...... ‎በተቋሙ ከዕቅድ እና ሪፖርት አቀራረብ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማረም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ አሳሰቡ። ‎ ‎የኮርፖሬት ፕላኒንግ ዘርፍ የ2018 በጀት የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በሥራ አስፈፃሚው አቶ ሕይወት እሸቱ ቀርቧል። ‎ ‎ዘርፉ ለተቋሙ አዋጭ የሆኑ ሣይንሳዊ መንገዶችን በመጠቀም የአጭር፣ መካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅዶችን ማዘጋጀት፣ መከታተልና መገምገም እንዲሁም ምክረ ሀሳብ እንደሚያቀርብ ገልፀዋል። ‎ ‎እንደ ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ ክፍሉ የአዋጭነት፣ የአካባቢ ደህንነትና የመልክዓ ምድር ጥናቶች እየሰራ ይገኛል። ‎ ‎በሩብ ዓመቱ በራስ አቅም የሲስተም ማሻሻያ እና የግሪድ አቅምን ለማሳደግ የሚያስችሉ ጥናቶች መከናወናቸውን ተናግረዋል። ‎ ‎በተጨማሪም የሁለት ፕሮጀክቶችን የዋጋ ጥናት እና የሦስት ከተሞችን የኃይል ፍላጎት ትንበያ ሥራዎች ማከናወናቸውን አብራርተዋል። ‎ ‎ታዳሽ፣ የተቀናጀ፣ ዘላቂ ኃይልና ዲጂታላይዜሽን ፕሮግራም ዕቅድ መጽደቁንም ነው አቶ ሕይወት የጠቆሙት። ‎ ‎በፕሮጀክት አስተዳደር ላይ የሚታዩ መዘግየቶች መንስዔዎቻቸውን ለመለየትና የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሚያስችል ጥናት ለመዘጋጀት መረጃ የማሰባሰብ ሥራዎች መጠናቀቃቸውንም ተናግረዋል። ‎ ‎የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በበኩላቸው የክትትልና የድጋፍ ሥርዓቱን በማጠናከር የተቋሙን ዋና ዋና ጉዳዮች የያዘ የተደራጀ፣ የተቀናጀና የተናበበ ዕቅድና ሪፖርት መዘጋጀት እንዳለበት ገልጸዋል። ‎ ‎የፕላኒንግ ዘርፍ የተቋሙን መነሻና መዳረሻ የምንወስንበት በመሆኑ አደረጃጀቱን በማስተካከልና በሠለጠነ የሠው ኃይል በማሟላት መልሶ ማደራጀት እንደሚገባ ተናግረዋል። ‎ ‎እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገለፃ አንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት የሚለውን የመንግሥት አቅጣጫ ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም የተቋሙ አመራር በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅበታል። ‎ ‎የተቋሙን ሥጋቶችና በባለድርሻ አካላት የሚሰጡ ግበረ መልሶችን በዕቅድ አካቶ ከመስራት አንጻር ክፍተቶች እንደሚስተዋሉም ጠቁመዋል። ‎ ‎ዘርፎች ወደ ኮርፖሬት ፕላኒግ የሥራ ክፍል የተጠናቀቀና መግባባት ላይ የተደረሰበት ጥራት ያለው ዕቅድና ሪፖርት በተቀመጠው ጊዜ በመላክ በዕቅድ እና በሪፖርት አቀራረብ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማረም እንደሚገባ አሳስበዋል። ‎ ‎ዕቅድና ሪፖርት አዘጋጅቶ ማቅረብ የሁሉም ሥራ ኃላፊዎች ግዴታ መሆኑን የጠቆሙት ኢንጂነር አሸብር በወቅቱ ምላሽ በማይሰጡ የሥራ ዘርፎች ላይ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ተናግረዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+8

ዘርፉ በሩብ ዓመቱ የገቢ አሰባሰብ እና ወጪ ቅነሳ ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ ቆይቷል ‎.......///........ ‎የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ፋይናንስና ሀብት አስተዳደር ዘርፍ በ2018 በጀት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በገቢ አሰባሰብ እና ወጪ ቅነሳ ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ መቆየቱን ገለፀ። ‎ ‎የዘርፉ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደመረ አሰፋ እንደተናገሩት በሩብ ዓመቱ የነዳጅ አጠቃቀምን በጂፒኤስ የአሰራር ሥርዓት በመታገዝ፣ የብቃት ምዘናና ሥልጠናን በራስ አቅም በማከናወን፣ የሠራተኞችን የሰረቪስ ኪራይ በማስቀረት እና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን ቅድመ ጥገና በማከናወን ወጪ መቀነስ ተችሏል። ‎ ‎ተቋሙ የዕውቅና ሽልማት እንዲያገኙ ዘጠኝ ሠራተኞችን በፈጠራ ሥራ እና 19 በቡድን ሥራ እንዲሁም በሥራ አፈፃፀማቸው ዕውቅና የሚሰጣቸው ሠራተኞችን ለይቶ ለውሳኔ ማቅረቡን ገልፀዋል። ‎ ‎በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ዘርፍ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዕድገት እያሳየ መምጣት በግሪድ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ የገመገመ የመጀመሪያ የጥናት ረቂቅ ማውጣት መቻሉንም ነው የተናገሩት። ‎ ‎በሩብ ዓመቱ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥልጠና ከወሰዱ 37 የሥራ መሪዎች መካከል 16ቱ ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት ሲያገኙ 15ቱ በሒደት ላይ እንዲሁም 6ቱ ውጤት ሳይመጣላቸው መቅረቱን አስረድተዋል። ‎ ‎በራስ አቅም የሚከናወኑ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ ስትራቴጂካዊ አመራር መስጠት፣ የተቋሙን የአደረጃጀትና የአሰራር ሥርዓት ማሻሻያ ትግበራ ማጠናቀቅ እና የሰው ኃይል ስብጥር ምጣኔን ማሻሻል እንዲሁም የተቋሙን ስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት ያደረገ የሰው ኃይል ልማት ዕቅድ ማዘጋጀትና መተግበር ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን አብራርተዋል። ‎ ‎የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በበኩላቸው በአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማዕከል ለመሆንና ትርፋማ ተቋም ለመፍጠር እንዲቻል አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ መስራት አለበት። ‎ ‎ከተቋሙ ገቢ፣ ከሠራተኞች እርካታና ለሥራ መሰጠት፣ ከአመራር ቁርጠኝነት እና ከመረጃ ጥራት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማረም እንደሚገባ አሳስበዋል። ‎ ‎እንደ ኢንጂነር አሸብር ገለፃ የተቋሙን ገቢ ከማሳደግ አንፃር የኃይል ሽያጭ የሜትር ንባብን ከሰው ንክኪ የፀዳና በዘመናዊ የአውቶሜሽን ሥርዓት የታገዘ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎችን በየጊዜው መፈተሽ ይገባል። ‎ ‎ከአበል እና ነዳጅ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችን ለማረም ዘርፉ አፋጣኝ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለበት ተናግረዋል። ‎ ‎የተቋሙ ሠራተኞች በቁርጠኝነትና በጊዜ የለኝም ስሜት እንዲሰሩ ለማስቻል አመራሩ የክትትልና ድጋፍ ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል አለበት ብለዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+8

‎ዘርፉ በሩብ ዓመቱ የታዩ ክፍተቶችን በማረም የፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ለማሻሻል ይሰራል ‎......///..... ‎በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የታዩ ክፍተቶችን በማረም የፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ለማሻሻል እንደሚሰራ ገለፀ። ‎ ‎የዘርፉ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ውድነህ የማነ የዘርፉን አፈጻጸም ሲያቀርቡ እንደተናገሩት የኃይል ማመንጫ፣ ማከፋፈያና ማስተላለፊያ መስመሮች እንዲሁም የሲቪል ሥራዎች ዲዛይን ላይ የተሻለ አፈጻጸም ተመዝግቧል። ‎ ‎በሩብ ዓመቱ የበቆጂ፣ የደብረ ታቦር፣ የደጀን-ደብረ ማርቆስ የማከፋፈያና ማስተላለፊያ መስመሮች ግንባታ እንዲሁም የአሸጎዳ ማከፋፈያ ጣቢያ የትራንስፎርመር ቤይ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ውጤታማ እንደነበርም ገልጸዋል። ‎ ‎ለተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች የመዝጊያ ሪፖርት መስራት መቻሉንም ነው ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው የጠቆሙት። ‎ ይሁንና ‎በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት አንድ ሥር የሚገኙ ሰባት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመሮች ፕሮጄክቶች ግንባታ ላይ ዝቅተኛ አፈጻጸም መመዝገቡን ኢንጂነር ውድነህ ገልጸዋል። ‎ ‎እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍም ዘርፉ የፕሮጀክቶችን መሰረታዊ ችግሮች በመለየት የፋይናንስ እና የፊዚካል አፈጻጸሞችን መገምገሙን ተናግረዋል። ‎ ‎ዘርፉ በሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ላይ የፋይናንስ ወጪን ያገናዘበ የሥራ ጥራት እና ቅልጥፍና መለያዎቹ እንዲሆኑ ግንዛቤ መፍጠርና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ መቻሉንም አብራርተዋል። ‎ ‎በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ሥር የሚገኙ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ትርፋማ እና ውጤታማ ሆነው እንዲቀጥሉ እንዲሁም ከነባር ፕሮጀክቶች ተንከባለው የመጡ የፋይናንስ ችግሮችን መፍታት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውንም አንስተዋል። ‎ ‎በቀጣይም ዘርፉ በሩብ ዓመቱ የታዩ መልካም ጅምሮችን በማጠናከር እና ክፍተቶቹን በማረም ዓመታዊ ዕቅዱን እንዲያሳካና ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ፣ ጥራት እና ወጪ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ኢንጂነር ውድነህ አረጋግጠዋል። ‌‎ ‎የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በበኩላቸው ተቋሙ ከዲዛይን ጀምሮ እስከ ፕሮጀክት ትግበራ የሚታዩ ችግሮችን በቅርበት በመፍታት እንዲሁም የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎችን በማጠናከር የፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ለማሻሻል እንዲችል ዘርፉን በአዲስ መልክ አዋቅሮ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ ‎ ‎በዘርፉ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት እና በውጭ የሥራ ተቋራጮች የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው በጀት፣ ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቁ የሚያስችሉ የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች በመስራት የኦፕሬሽን ሥራዎች እንዲቀላጠፉ ለማድረግ ዘርፉ በትኩረት መስራት አለበት ብለዋል። ‎ ‎ዘርፉ ወደ ፊት የተሟላ ሥራ ተቋራጭ ለመሆን ከያዘው ዕቅድ አንፃር ትርፋማ መሆን እንዳለበትና ለዚህም የተቋሙ ከፍተኛ አመራር ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። ‎ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+3

‎የተቋሙን የሕግ የአሰራር ሥርዓት ለማጠናከር የሚያስችል ሥምምነት ተፈረመ ‎.....///..... ‎የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሕግ የአሰራር ሥርዓት ለማጠናከር የሚያስችል የማዕቀፍ ሥምምነት ከዓለም አቀፉ አዲስ የሕግ ግሩፕ ሊሚትድ ሊያቢሊቲ ፓርትነርሽፕ (ALG LLP) ጋር በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራርሟል። ‎ ‎ሥምምነቱን የተፈራረሙት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እና የጥብቅና ቢሮው ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ዘውድነህ በየነ ናቸው። ‎ ‎የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት እንደተናገሩት የጥብቅና ቢሮው ከአሁን ቀደም ተቋሙ በሕዳሴ እና ኮይሻ እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ የኃይል ቋት ሥራዎች ላይ የተለያዩ የሕግ ጉዳዮችን ሲያማክር ቆይቷል። ‎ ‎ሥምምነቱ ተቋሙ በሕግና የፕሮጀክት አስተዳደር ሥራዎች ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበትና ክፍተቶችን ለማረም የሚያስችል ነው ብለዋል። ‎ ‎የጥብቅና ቢሮው እስከ አሁን ለተቋሙ ለሰጠው የሕግ አገልግሎት ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተቋሙ በቀጣይም በሥምምነቱና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ተባብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል። ‎ ‎አዲስ የሕግ ግሩፕ ሊሚትድ ሊያቢሊቲ ፓርትነርሽፕ ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ዘውድነህ በየነ በበኩላቸው ቢሮው ዋና መቀመጫውን በአሜሪካን ሀገር አድርጎ በአውሮፓ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ የህግ ጉዳዮች ላይ እየተንቀሳቀሰ እንደሚሰራ ገልፀዋል። ‎ ‎የጥብቅና ቢሮው በዕውቀት ክፍተት ምክንያት በሚፈረሙ ውሎች  የሚባክነውን ሀብት ለመጠበቅ በዋናነት የአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል። ‎ ‎ሥምምነቱ በተቋሙ የሕግና ተየያዥ ጉዳዮች ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማስወገድ በበይነ መረብ እና በአካል እስከ ሁለተኛ ድግሪ ድረስ ሥልጠናዎችን ለመስጠት እንደሚያስችል ገልጸዋል። ‎ ‎ይህም የሚፈረሙ ውሎች የተቋሙን ጥቅም የሚያስጠብቁ እንዲሆኑ በዕወቀት ላይ የተመሰረተ የሕግ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ እንደሚያስችል አብራርተዋል። ‎ ‎የማዕቀፍ ሥምምነቱ ለሁለት ዓመት የሚቆይ መሆኑ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ተገልጿል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+3

አመራሩ ለውጥ ለማምጣት መረባረብ አለበት ~ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ‎.....///..... ‎የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራር በኃይል ልማት ዘርፉ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት መረባረብ እንዳለበት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሳሰቡ። ‎ ‎ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ይሄን የተናገሩት ተቋሙ የ2018 በጀት የመጀመሪያውን ሩብ  ዓመት የጀነሬሽን እና የትራንስሚሽን ቢዝነስ ዘርፎችን ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት መድረክ ላይ ነው። ‎ ‎ተቋሙ የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን በማሻሻል እና የኦፕሬሽን ሥራዎችን በማቀላጠፍ በዘርፉ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የመዋቅር ማሻሻያ አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውሰዋል። ‎ ‎ተቋሙ አዳዲስ የኃይል መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ከመገንባት ባሻገር ያለውን ሲስተም አስጠብቆ ለተጠቃሚው አስተማማኝ ኃይል ተደራሽ ማድረግ ዋነኛ ተልዕኮው መሆኑን ጠቁመዋል። ‎ ‎ሆኖም አመራሩ የተናበበ ዕቅድ አቅዶ በትብብር ባለመስራቱና ሀብትን በአግባቡ ባለማስተዳደሩ በተቋሙ ለሚስተዋለው የፕሮጀክቶች መዘግየት ምክንያት እየሆነ ነው ብለዋል። ‎ ‎በዚህም በሩብ ዓመቱ በኦፕሬሽንና በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ በታዩ ጉድለቶች ሳቢያ ለኃይል መቆራረጥና ተቋሙን ለተጨማሪ ወጪ መዳረጉን አብራርተዋል። ‎ ‎እንደ ኢንጂነር አሸብር ገለፃ የባለሙያዎችን አቅም ከመገንባትና ተጠያቂነትን ከማስፈን አንጻር ክፍተት በመኖሩ በኦፕሬሽን ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል። ‎ ‎በመሆኑም የተቋሙ አመራር የገቢ አማራጮችን በማስፋት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንዲጀመሩ እንዲሁም በግንባታ ሒደት ላይ የሚገኙትም በጊዜ ተጠናቀው የተቀላጠፈ የኦፕሬሽን ሥራ ለማከናወን እንዲቻል በትብብርና በጊዜ የለኝም መንፈስ መስራት እንደሚጠቅበት አሳስበዋል። ‎ ‎በተቋሙ የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራት አንፃር የሚስተዋለውን ክፍተት ለመሙላትም መጠነ ሰፊ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ማከናወን እንደሚገባ በአፅዕኖት ገልፀዋል። ‎ ‎በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ውስጥ በሥራ ላይ የሚገኙ ትራንስፎርመሮችን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግም ነው ያብራሩት። ‎ ‎የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን በዕቅድ ላይ ተመስርቶ የዕድሳትና መልሶ ግንባታ ሥራዎች ማከናወን እንደሚገባ የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አመራሩ አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨትና በመተግበር ጭምር በኃላፊነትና ቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል። ‎ ‎ሪጅኖች የተቋሙ አምባሳደሮች በመሆናቸው ከየአካባቢው የመንግሥት መስተዳድር አካላት ጋር በቅርበት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ነው የጠቆሙት። ‎ ‎በፕሮጀክቶች እና ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ጥቅም ላይ የማይውሉ ቁርጥራጭ ብረቶችና ዕቃዎች ለስርቆት መንስዔ እየሆኑ መምጣታቸውን የጠቆሙት ኢንጂነር አሸብር ዕቃዎቹን በአግባቡ መዝግቦ የማደራጀት እና የማስወገድ ሥራ በአፋጣኝ መከናወን እንዳለበት ተናግረዋል። ‎ ‎ከመረጃ አያያዝ፣ ከሪፖርት አቀራረብ እና ከቅንጅታዊ አሰራር እንዲሁም ከሀብት አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ሰፊ ክፍተቶች እንዳሉ የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚው እነዚህና በሩብ ዓመቱ የተስተዋሉ ሌሎች ችግሮች የሚስተካከሉበት የድርጊት መርሀ ግብር ዘርፎቹ አቅደው ማምጣትና መፈጸም እንዳለባቸው አቅጣጫ ሰጥተዋል። ‎ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content

ተቋሙ በሩብ ዓመቱ ወደ 27 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ አግኝቷል ‎........///....... ‎የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ሦስት ወራት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ከቀረበ የኃይል ሽያጭ እና ተጓዳኝ አገልግሎቶች ከ26 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ገለጸ። ‎ ‎በተቋሙ የትራንስሚሽን ቢዝነስ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አንዷለም ሲዓ እንደተናገሩት በሩብ ዓመቱ ከኃይል ሽያጭ 24 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 26 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ  ተገኝቷል። ‎ ‎በሩብ ዓመቱ 7 ነጥብ 88 ቴራ ዋት ሰዓት ኃይል በመሸጥ በብር 10 ነጥብ 1 ቢሊዮን እንዲሁም በውጭ ምንዛሬ 117 ነጥብ 1 የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል። ‎ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ96 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑንም ተናግረዋል። ‎ ‎እንደ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ በሩብ ዓመቱ የተሸጠው የኃይል ምርት ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ47 በመቶ ወርሃዊ ዕድገት አለው። ‎ ‎በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለሽያጭ ከቀረበው ኃይል 93 በመቶ ለሀገር ውስጥ እንዲሁም 7 በመቶ ደግሞ ለውጭ ሀገራት የቀረበ መሆኑን ተናግረዋል። ‎ ‎ለሀገር ውስጥ ከቀረበው የኃይል ሽያጭ ውስጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 53 ነጥብ 6 በመቶ፣ የከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች 4 ነጥብ 6 በመቶ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች 34 ነጥብ 6 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ጠቁመዋል። ‎ ‎በተመሳሳይ ለጎረቤት ሀገራት ከቀረበው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ውስጥ ኬንያ እና ታንዛኒያ 4 ነጥብ 6 በመቶ እንዲሁም ጅቡቲ 2 ነጥብ 2 በመቶ ድርሻ አላቸው ብለዋል። ‎ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+3