ch
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

前往频道在 Telegram

EEP Communication

显示更多

📈 Telegram 频道 EEP Communication 的分析概览

频道 EEP Communication (@eepcommuication) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 692 名订阅者,在 技术与应用 类别中位列第 8 014,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 155

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 692 名订阅者。

根据 30 八月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 145,过去 24 小时变化为 2,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 31.28%。内容发布后 24 小时内通常能获得 16.96% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 909 次浏览,首日通常累积 2 661 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
EEP Communication

凭借高频更新(最新数据采集于 31 八月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 技术与应用 类别中的关键影响点。

15 692
订阅者
+224 小时
+187
+14530
帖子存档
photo content
+3

መኾኒ ከተማ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ   ከ500 በላይ የታወር ብረቶች ተያዙ …///… በሰሜን ሪጅን ከአላማጣ – መኾኒ – መቐለ አቅጣጫ በተዘረጋው የ230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት መምሰሶዎች ላይ ተሰርቀው የተደበቁ ከ500 በላይ ብረቶች መያዙን የሰሜን ሪጅን ፊዚካል ሴኩሪቲ አስታወቀ፡፡  በሪጅኑ የመሰረተ ልማት ደህንነት ፊዚካል ሴኩሪቲ አባል ኮሎኔል ማዕረግ አሰፋ እንዳስታወቁት በሪጅኑ ከአላማጣ – መኾኒ – መቐለ አቅጣጫ በተዘረጋው የ230 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር በሚያጋጥመው ተደጋጋሚ ስርቆት ከፍተኛ ውድመት የሚደርስበት አካባቢ ነው፡፡ በተለይም በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን፣ ራያ ዓዘቦ ወረዳ፣ መኾኒ ከተማና አካባቢው ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ በመሆኑ ከመደበኛ የጥገና ሥራዎች ጎን ለጎን የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ደህንነትን ለማስጠበቅ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማወያየት የቅድመ መከላከል ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የጠቀሱት ኮሌኔሉ በሥጋት ቀጠናዎች ላይ ክትትል እና ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ  ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ሥር እያዋሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንደ ኮሌኔሉ ገለጻ በመኾኒ ከተማ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ለጊዜው ግምታዊ ዋጋቸው ያልታወቀ ከ500 በላይ የታወር ብረቶች የተያዙ ሲሆን በጉዳዩ ላይ አንድ ባጃጅ እና አምስት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ሥር ውለው ክስ ተመስርቶባቸዋል። በሪጅኑ የሚገኙ የተቋሙን መሰረተ ልማቶች ደህንነት የመጠበቅ ሥራ ከሪጅኑ አመራርና ሠራተኛ እንዲሁም ከአካባቢው የመስተዳደር አካላትና ከመላው ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 20  ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+3

🌍 Today is World Clean Energy Day! (January 26) Did you know that Ethiopia is one of the greenest countries in the world whe
🌍 Today is World Clean Energy Day! (January 26) Did you know that Ethiopia is one of the greenest countries in the world when it comes to energy? 🇪🇹 Here are 4 reasons why today matters: 1️⃣ Climate Protection: Renewable energy is helping us fight the 1.5°C global warming limit. 2️⃣ Affordability: Solar energy is now the cheapest source of electricity in history! 3️⃣ National Success: 98% of our electricity comes from clean sources like the sun, wind, and water. 4️⃣ Regional Leadership: With a capacity of over 9,700 MW, Ethiopia is becoming the clean energy hub for all of East Africa. Let’s celebrate a cleaner, brighter future for our children. Happy World Clean Energy Day! #CleanEnergy #Ethiopia #GreenEnergy #WorldCleanEnergyDay #Sustainability

🌍 የዓለም የንፁህ ኢነርጂ ቀን (ጥር 18) የንፁህ ኢነርጂ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ጥር 18 ወይም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጃንዋሪ 26 ቀን ይከበራል። ዋነኛ ዓላማው፦ ✅ አካባቢን የማይበክሉ የንፁህ ኢነርጂ ምንጮችን (ፀሃይ፣ ንፋስ፣ ሃይድሮ፣ ጂኦተርማል፣ ባዮማስ) ማስተዋወቅ እና ጥቅም ላይ ማዋል ✅ የነዳጅ ጥገኛነት መቀነስ ✅ ርካሽ ኢነርጂን ለተጠቃሚው ማቅረብ ✅ የማህበረሰብ ግንዛቤ ማሳደግ የኢነርጂ ዘርፍ በየጊዜው በርካታ ታሪካዊ ስኬቶችን አስመዝግቧል። 1. የአቅም እድገት 💡 30%፦ በዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ምርት ውስጥ የታዳሽ ኃይል ግምታዊ ድርሻ። o በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በበርካታ ታላላቅ ኢኮኖሚዎች ውስጥ የንፋስ እና የፀሐይ ኃይል ከድንጋይ ከሰል (Coal) የተሻለ ውጤት እያስመዘገቡ ነው። 💡 510 ጊጋ ዋት (GW)፦ ባለፈው ዓመት ብቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጨመረው የታዳሽ ኃይል መጠን ሲሆን፣ ይህም ካለፉት ዓመታት የ50% እድገት አሳይቷል። 💡 $1.8 ትሪሊዮን ዶላር፦ ባለፈው ዓመት ለንፁህ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎች (የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች፣ ለኃይል ማመንጫዎች እና ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ግንባታ) ኢንቨስት የተደረገው ግምታዊ ዓለም አቀፍ በጀት ነው። ይህም ለነዳጅ እና ጋዝ ከሚወጣው መዋዕለ ንዋይ በእጅጉ ይበልጣል። 2. የፀሐይ እና የንፋስ ኃይል የበላይነት 🎯 ከ$0.02 – $0.05 ዶላር በኪሎዋት ሰዓት (kWh)፦ በትላልቅ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች የሚመረት የኤሌክትሪክ አማካኝ ዋጋ ሲሆን ይህም በታሪክ ውስጥ በብዙ የዓለም ክፍሎች የፀሐይ ኃይልን ርካሹ የኤሌክትሪክ ምንጭ አድርጎታል። 🎯 1 ቴራዋት (TW)፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተተከለው የፀሐይ ኃይል አቅም ነው፤ ይህም ታሪካዊ ዕድገት ተብሎ ተመዝግቧል። 🎯 11%፦ በአሁኑ ወቅት ከንፋስ ኃይል የሚገኘው የዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ድርሻ ሲሆን በተለይም በባህር ላይ የሚገነቡ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ፈጣን እድገት እያሳዩ ነው። 3. የአፍሪካ ሁኔታ (በተለይ የኢትዮጵያ ሁኔታ) 🇪🇹 98%፦ በዜና ዘገባዎች እንደተጠቀሰው፣ ይህ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ከታዳሽ ምንጮች (በዋነኝነት ከውሃ፣ ከንፋስ እና ከጂኦተርማል) የሚመረትበት መቶኛ ነው። 📊 600 ሚሊዮን፦ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያገኙ ሰዎች ቁጥር ነው። ይህም እንደ IRENA እና COP32 ያሉ ጉባኤዎች ችግሩን ለመፍታት መስራት ያለባቸው ን ሰፊ የ"ንፁህ ኢነርጂ ክፍተት" እንዳለ ያሳያል። 📊 5,150 ሜጋዋት (MW)፦ የምስራቅ አፍሪካ የንፁህ ኢነርጂ የጀርባ አጥንት የሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) የኃይል ማመንጨት አቅም ነው። ኢትዮጵያ እንደሀገር ከ9 ሺህ 7 መቶ ሜጋ ዋት በላይ የማመንጨት አቅም ፈጥራለች፡፡ 4. የአካባቢ ተፅዕኖ 🌱 1.50C፦ ዓለም የሙቀት መጠኗ ከዚህ እንዳያልፍ እየታገለች ያለችበት ገደብ ነው። ይህንን ለማሳካት የታዳሽ ኃይል አቅም እስከ 2030 ድረስ በሶስት እጥፍ ማደግ ይኖርበታል። 🌱 12 ጊጋ ቶን፦ በአሁኑ የታዳሽ ኃይል አጠቃቀም እና የኢነርጂ ብክነትን በመቀነስ እርምጃዎች አማካኝነት በየዓመቱ ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ የተደረገ የCO2 መጠን ነው። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content

የክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ የሥራ መደብ መረጃ የሥራ መደብ መጠሪያ፦ ቧንቧ ጥገና ሰራተኛ (Plumber Technician) የሥራ ደረጃ፦ ጂኤስ4 ደመወዝ፦ በድርጅቱ ስኬል መሰረት ብዛት፦ እንደ አስ
የክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ የሥራ መደብ መረጃ የሥራ መደብ መጠሪያ፦ ቧንቧ ጥገና ሰራተኛ (Plumber Technician) የሥራ ደረጃ፦ ጂኤስ4 ደመወዝ፦ በድርጅቱ ስኬል መሰረት ብዛት፦ እንደ አስፈላጊነቱ የሥራ ቦታ፦ ዋናው መ/ቤት የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት የመመዝገቢያ ቀን፦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ ይሆናል ። የምዝገባ ቦታ፦ ኮተቤ ብረታብረት በሚገኘው በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የሰው ኃይል ቅጥርና ምደባ ቢሮ በአካል በመገኘት መመዝገብ ይቻላል ። ለተጨማሪ መረጃ ከላይ የተያያዘዉን ፎቶ ይመልከቱ! 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 16 ቀን 2018 ዓ.ም

መምሪያው የተቋሙን የአሠራር ስርዓት ለማዘመን እየሰራ መሆኑን ገለፀ …….///…….. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፕሮሰስ፣ ፖሊሲና የለውጥ ሥራ አመራር መምሪያ ቀልጣፍ እና ውጤትን መሠረት ያደረገ
+3
መምሪያው የተቋሙን የአሠራር ስርዓት ለማዘመን እየሰራ መሆኑን ገለፀ …….///…….. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፕሮሰስ፣ ፖሊሲና የለውጥ ሥራ አመራር መምሪያ ቀልጣፍ እና ውጤትን መሠረት ያደረገ የአሠራር ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ። የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ አንዷለም ኪዳኔ እንደተናገሩት የአሰራርና የዶክመንቴሽን ስርዓቶችን በማዕከል ለማደራጀት፣ ደህንነታችውን ለመጠበቅና ለተጠቃሚዎች ምቹ ለማድረግ የሚያስችል ሲስተም የማበልጸግ ስራ ተከናውኗል። የተቋሙን የመፈፀም አቅም የሚያጎለብቱ የፖሊሲ ዝግጅት፣ መመሪያ፥ ማጣቀሻ ሰነዶች እና ቴምፕሌቶች ተዘጋጅተው ወደ ስራ መገባቱን ዳይሬክተሩ አብራርተዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=መምሪያው-የተቋሙን-የአሠራር-ስርዓት-ለማ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም

ዘርፉ የተጀመሩ የቅንጅት ሥራዎች ይበልጥ መጠናከር አለባቸው ……///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መልካም አስተዳደርን በዘላቂነት ለማስፈን በኮርፖሬት ገቨርናንሰ እና ኮምፕሊያንስ ዘርፍ ሥር የሚ
+9
ዘርፉ የተጀመሩ የቅንጅት ሥራዎች ይበልጥ መጠናከር አለባቸው ……///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መልካም አስተዳደርን በዘላቂነት ለማስፈን በኮርፖሬት ገቨርናንሰ እና ኮምፕሊያንስ ዘርፍ ሥር የሚገኙ መምሪያዎች በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የዘርፉ ሥራ አስፈፃሚ አሳሰቡ፡፡ በዘርፉ ሥር የሚገኙት የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን፤ የህግ አገልግሎት፤ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ እንዲሁም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያዎች በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወኗቸውን ሥራዎች አቅርበው ተገምግሟል፡፡ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ በተቋሙ የሚገኙ ሴት ሠራተኞች መብትና ጥቅም ለማስከበር እና ማህበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት መንቀሳቀሱን ሲገልጽ የህግ አገልግሎት መምሪያ በበኩሉ የተቋሙን ጥቅም የሚያስጠብቁ የፍትሐብሔር፣ የሥራ ክርክር እና  የካሳ ጉዳዮችን በመከታተል የመርታት አቅሙን ማሳደጉን ገልጿል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ዘርፉ-የተጀመሩ-የቅንጅት-ሥራዎች-ይበልጥ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም

‎ዘርፉ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ነው             ‎.....///..... ‎በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ገቨርናንስ እና ኮምፕሊያንስ ሥራ አስፈፃሚ ዘርፍ  የ2018 በጀት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን መገምገም ጀምሯል። ‎ የዘርፉ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዱጉማ ነዳ ‎በግምገማው መክፈቻ ላይ እንደገለጹት እንደ ተቋም የተያዙ ስትራቴጂያዊ ዕቅዶችን ለማሳካት የዘርፉን አበርክቶ መገምገም አስፈላጊ ነው። ስለሆነም በዘርፉ ስር ያሉ ሁሉም መምሪያዎች በስድስት ወራት ውስጥ ያከናወኗቸውን ዋና ዋና ሥራዎችን በዝርዝር በማቅረብ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን ለማረም ግምገማው ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በዘርፉ የተከናወኑ የዕቅድ አፈጻጸሞች በግምገማው የሚቀርቡ ሲሆን የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችና የታዩ ክፍተቶችን በመገምገም እንዲሁም የቀጣይ ሥራዎችን አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ግምገማው ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+5

ተቋሙ የመሰረተ ልማት ሥርቆትን ለመከላከል የዘረጋው ስትራቴጂ ውጤት እያመጣ ነው ..….///….… በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ የሚፈ
+2
ተቋሙ የመሰረተ ልማት ሥርቆትን ለመከላከል የዘረጋው ስትራቴጂ ውጤት እያመጣ ነው ..….///….… በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን ለመከላከል የተዘረጋው ስትራቴጂ ውጤት እያመጣ መሆኑን በተቋሙ የኃይል መሰረተ ልማት ደህንነት፣ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ገለፀ፡፡ የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ከሊል ሽፋ እንደገለፁት ባለፉት ስድስት ወራት በመሰረተ ልማቶቹ ላይ ይፈፀም የነበረው ስርቆት ካለፉት ዓመታት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የመቀነስ አዝማሚያ ታይቷል፡፡ በ12 ሪጅኖች የቀድሞ የመከላከያ መኮንኖችን በመመደብ የኃይል መሰረተ ልማት ደህንነትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ተቋሙ-የመሰረተ-ልማት-ሥርቆትን-ለመከላከ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም

ባለፉት ስድስት ወራት ለ139 ጉዳዮች ምላሽ ተሰጥቷል ……///….. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2018 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ከውጭ ተገልጋዮች እና ከተቋሙ አመራርና ሠራተኞች ለቀረቡ 139 አ
+4
ባለፉት ስድስት ወራት ለ139 ጉዳዮች ምላሽ ተሰጥቷል ……///….. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2018 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ከውጭ ተገልጋዮች እና ከተቋሙ አመራርና ሠራተኞች ለቀረቡ 139 አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠቱን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ሙላት ገዛኸኝ እንደገለፁት ባለፉት ስድስት ወራት ለ 152 አስተዳደራዊ ጉዳዮች ምላሽ ይሰጣል በሚል የታቀደ ቢሆንም ለቀረቡት 139 አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ ከዋና ስራ አስፈጻሚ በተሰጠ ውክልና መሠረት የተቋሙ ባለሙያዎች ለሚያከናውኗቸው ሙያዊ ተልዕኮዎች ድጋፍ ከመስጠት አንፃር ለ107 ሠራተኞችና የሥራ መሪዎች የፓስፖርት እድሳትና አዲስ ፓስፖርት እንዲያገኙ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ባለፉት-ስድስት-ወራት-ለ139-ጉዳዮች-ምላሽ-ተሰ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል አቅርቦት ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ ረገድ ሚናው የጎላ ነው ……///……. የኃይል አቅርቦት በኮምቦልቻ ከተማ በተኪና ወደውጭ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት ላይ ለተሰማሩ እንዲሁም ለፌደራል ለመንግ
+6
የኃይል አቅርቦት ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ ረገድ ሚናው የጎላ ነው ……///……. የኃይል አቅርቦት በኮምቦልቻ ከተማ በተኪና ወደውጭ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት ላይ ለተሰማሩ እንዲሁም ለፌደራል ለመንግስት ታክስ በመክፈል በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ያሉ ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ በኩል ሚናው የጎላ እንደሆነ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ወንድወሰን ልሳነወርቅ እንዳስታወቁት በኮምቦልቻ ከተማ 127 ከፍተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ይገኛሉ፡፡ ከማህበረሰቡና ከመንግስታዊ ተቋማት በተጨማሪ በከተማዋ የሚገኙት የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ የአምራችና የማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከፍተኛ የሆነ የኃይል ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-አቅርቦት-ኢንዱስትሪዎችን-በመደ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል አቅርቦት አስተማማኝነት የሚያሳድጉ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው …….///…… በኮምቦልቻ ቁጥር 2 ማከፋፈያ ጣቢያ በየጊዜው እያደገ የሚመጠውን የኃይል ፍላጎት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ሥራዎች
+7
የኃይል አቅርቦት አስተማማኝነት የሚያሳድጉ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው …….///…… በኮምቦልቻ ቁጥር 2 ማከፋፈያ ጣቢያ በየጊዜው እያደገ የሚመጠውን የኃይል ፍላጎት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን የጣቢያው ኃላፊ አስታውቀዋል፡፡ ኃላፊው አቶ ዝናቡ ገብሩ እንዳስታወቁት የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የኢንዱስትሪ እና ከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ በማከፋፈያ ጣቢያው ላይ ያለው የኃይል አቅርቦት ፍላጎት በፍጥነት እያደገ ይገኛል፡፡ ማከፋፈያ ጣቢያው በ2002 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት ሲጀምር 63 ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያለው አንድ ትራንስፎርመር እና አራት ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች ብቻ እንደነበሩት ያስታወሱት አቶ ዝናቡ በየጊዜው እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት መሰረት በማድረግ በተለያዩ ጊዜያት የአቅም ማሳደግ፣ ማስፋፊያና ማዘመን ሥራዎች እንደተከናወኑለት ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-አቅርቦት-አስተማማኝነት-የሚያሳ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም

ሪጅኑ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች ማከናወኑን ገለፀ ……..///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ባለፉት ስድስት ወራት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦ
+7
ሪጅኑ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች ማከናወኑን ገለፀ ……..///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ባለፉት ስድስት ወራት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች ማከናወኑን አስታወቀ። የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ተሻገር እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ በዕቅድ ላይ የተመሰረቱ የአስቸኳይ ጥገና እና የፍተሻ ሥራዎች ተሰርተዋል። በግማሽ በጀት ዓመቱ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ለማረጋጋት እና ተደራሽነትን ለማስፋፋት የሚያስችሉ የጥገና እና የማሻሻያ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልፀው ይህም የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ እና የኢንዱስትሪዎችን ፍላጎት ለማሟላት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ https://www.eep.com.et/?amh-news=ሪጅኑ-አስተማማኝ-የኃይል-አቅርቦትን-ለማ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ .....///...... የሥራ መደብ፡ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ አድራጊ ቴክኒሻን I (Technician I EV Battery Charger) የትምህርት ደረጃ፡ ኮሌጅ ዲፕሎማ
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ .....///...... የሥራ መደብ፡ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ አድራጊ ቴክኒሻን I (Technician I EV Battery Charger) የትምህርት ደረጃ፡ ኮሌጅ ዲፕሎማ/TVET 10+3 ወይም በደረጃ 4 በአውቶሞቲቭ ኤሌክትሪካል/ኤሌክትሮኒክስ ወይም አውቶሞቲቭ ኤሌክትሮ ሜካኒካል የተመረቀ። ልዩ መስፈርት፡ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) ማቅረብ የሚችል። የሥራ ልምድ፡ አይጠይቅም (0 ዓመት)። የምዝገባ ቦታ፡ ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት፣ የሰው ኃይል ቅጥርና ምደባ ቢሮ (በአካል በመገኘት) ለበለጠ መረጃ በድረ ገጻችን https://www.eep.com.et/?amh-announcement=ክፍት-የሥራ-ቦታ-ማስታወቂያ መመልከት ትችላላችሁ። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም

የአይሻ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን የፋይናንስ ሥምምነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው …..///….. በመንግሥት እና የግል አጋርነት ማዕቀፍ ለሚገነባውና 300 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ላለው
+6
የአይሻ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን የፋይናንስ ሥምምነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው …..///….. በመንግሥት እና የግል አጋርነት ማዕቀፍ ለሚገነባውና 300 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ላለው የአይሻ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የፋይናንስ ሥምምነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከዋና ዋና የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር የከፍተኛ ደረጃ የአበዳሪዎች የቅድመ ኢንቨስትመንት ምርመራ ስብሰባ በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል፡፡ በስብሰባው ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የማክሮ ኢኮኖሚ እና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያዎችን በማድረግ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የአይሻ-1-የንፋስ-ኃይል-ማመንጫ-ፕሮጀክትን&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም

@9:00

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አገኘ .....///…... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቀደም ሲል የነበረበትን ከፍተኛ የዕዳ ጫና በመቋቋም እና አሠራሩን በማዘመን ለመጀመሪ
+1
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አገኘ .....///…... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቀደም ሲል የነበረበትን ከፍተኛ የዕዳ ጫና በመቋቋም እና አሠራሩን በማዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትርፋማነት መሸጋገሩን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አስታወቀ። የኢንቨስትመንት ሆልዲንጉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ ( ዶ/ር) እንደገለፁት ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዝግቧል፡፡ አሁን ላይ የተመዘገበው ትርፍ ተቋሙ ካለበት የብድር ጫና ወጥቶ ራሱን እንዲችል መንገድ የሚከፍት መሆኑ ጠቁመዋል። ተቋሙ የነበረበት ከፍተኛ የብድር ጫና ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መተላለፉ፣ በመንግሥት የተተገበረው የኢኮኖሚ ሪፎርም እና የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ለትርፉ መመዝገብ ድርሻው የጎላ መሆኑን ዶ/ር ብሩክ አብራርተዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም