cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

ይህ ይፋዊ የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ገጽ ነው፡፡ በዚህ ገጽ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት የጠበቁ ትምህርቶችን እናሰራጫለን፡፡ - የቅድስት ቤተክስቲያናችን እና የሰንበት ት/ቤቱን እንቅስቃሴ ወቅታዊ መረጃ እናደርስበታለን፡፡ ገጹን ለሌሎችም እያጋራችሁ የቤተክርስቲያናችንን አገልግሎት እናፋጥን፡፡ @EMeslene

Больше
Рекламные посты
5 910
Подписчики
+624 часа
+17 дней
+13630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ ....ከዚያም ለዐሥራ ሁለቱ ታየ ብሎ የጌታን ድኅረ ትንሣኤ አስተርእዮ ዘረዘረ:: እኔ ማለትን የማይወደው ትሑት ቅዱስ ጳውሎስ “ከሁሉ በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ አለ:: ጭንጋፍ ምንድር ነው? ጭንጋፍ (ጸዕጻዕ/ ተውራድ) ለፅንስ የሚነገር ቃል ነው:: መወለድ ያለበትን ጊዜ ያልጠበቀ ያለ ጊዜው የተወለደ ፅንስ ነው:: በመጠኑ ከሌላው ጊዜውን ከጠበቀ ፅንስ የሚያንስ ሲሆን ዕድገቱን በተገቢው ጊዜ ከሚወለድ ልጅ ጋር ለማስተካከል ሲባል በሙቀት ማቆያ ክፍል እንዲቆይ ይደረጋል:: ይህ ፅንስ ሲወለድ በሕመም ውስጥ ሆኖ ተሰቃይቶ ተጨንቆ ነው:: ቅዱስ ጳውሎስ ራሱን ለመግለጽ የተጠቀመበት ይህ አንድ ቃል የሕይወት ታሪኩን ጠቅልሎ የያዘ ድንቅ ቃል ነበር.... ሙሉውን ለማንበብ👇👇👇 from source
Показать все...
ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ

ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምእመናን ስለ ጌታ ትንሣኤ ማስረጃ እያቀረበ ነው:: በዚያን ዘመን ለጌታ ትንሣኤ ማስረጃ ስትጠቅስ በማቴዎስ ወንጌል እንዲህ ይላል ብለህ እንዳትጠቅስ ገና ወንጌላት አልተጻፉም:: ቢጻፉም ማቴዎስ በሕይወት እያለ በቃሉ መመስከር ሲችል ጽሑፉን ማስረጃ ማድረግ አያስፈልግህም:: ስለዚህ ለመነሣቱ ማስረጃዎች ከተነሣ በኋላ ያዩት ሰዎች ነበሩ:: በሕይወት ያሉትን የዓይን ምስክሮችን መጥቀስ ይቻላል:: የዓይን እማኞች ምስክርነት ከጽሑፍ በላይ የታሪክ ማስረጃ ነው:: ስለዚህ ጳውሎስ ስለ ጌታ ትንሣኤ “እነ እገሌ አይተውታል” እያለ መዘርዘርን መረጠ::

14👍 1🙏 1
39🥰 4
ግንቦት 04 2016 ዓ.ም ... 248 የሚሆኑ የሰንበት ትምህርት ቤታችን የሕጻናትና ማእከላውያን ክፍል አባላት ወደ መደበኛ የወጣት ክፍል መርሐግብር ተዘዋውረዋል። ከቀዳማይ ክፍል ጀምሮ በትምህርት ያሳለፉ ታዳጊ ወጣቶች ለዓመታት ሲሰጣቸው የነበረውን ትምህርትና ስልጠናዎች አጠናቀው በልዩ ጉባኤ እንዲዘዋወሩ ተደርጓል። 🏡ቤተሰብ ይሁኑ! የዩቲዩብ ቻናል፡ http://youtube.com/@EMislene የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/EMislene የፌስቡክ ገጽ፡ https://www.facebook.com/EMislene/ የኢንስታግራም ገጽ፡ https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/ የቲክቶክ ገጽ፡ https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28 ድሕረ ገጽ፡ www.debregelila.org
Показать все...
12👍 4
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ*     ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ /፪/ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ /፬/እኽ ምድር ጸዳች ሐሴት አረገች/፪/ በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች/፬/እኽ
Показать все...
Показать все...

10🙏 1
እንኳን ለዳግማዊ ትንሳኤ በዓል አደረሰን 45 ኛ ዙር የደም ልገሳ ግንቦት 11 ጠዋት ተገናኝተን ነፍስ የማዳን ስራ ተባብረን እንፈፅም 🏡ቤተሰብ ይሁኑ! የዩቲዩብ ቻናል፡ http://youtube.com/@EMislene የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/EMislene የፌስቡክ ገጽ፡ https://www.facebook.com/EMislene/ የኢንስታግራም ገጽ፡ https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/ የቲክቶክ ገጽ፡ https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28 ድሕረ ገጽ፡ www.debregelila.org
Показать все...
10👍 3🙏 2
ፍርሃትን የሚጥል ፍፁም ፍቅር ...እነኚህ ሴቶች የክርስቶስን ሞት ሰምተው መቃብሩን ሊያዩ ከሩቅ የመጡ እንግዶች አልነበሩም ይልቁንም በዕለተ አርብ እየተላጋ ሲወሰድ፣ በየመንገዱ ሲጎተትና መስቀል ተሸክሞ ሲሄድ እያለቀሱ በደም የተዋበ የመስቀሉን መንገድ በእንባ ያጠቡ ሴቶች ናቸው። ሐዋርያቱ ሸሽተው በሄዱበት አሁን አድን ያሉት የኢየሩሳሌም ሰዎች አሁን አጥፋው ብለው ጲላጦስን በሚማፀኑበት ወቅት ከእግረ መስቀሉ ሥር የነበሩ ሴቶች ናቸው። ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በአዲስ መቃብር ሲቀብሩት ከሩቅ ሆነው ያዩት ሴቶች ናቸው። ጌታቸውን በመቃብር ትተው እንቅልፍ አልወስድ ቢላቸው በሌሊት ተነስተው ወደ መቃብሩ ሄዱ.... from source
Показать все...
ፍርሃትን የሚጥል ፍፁም ፍቅር

በሌሊት ማለፍና በፀሐይ መውጣት መካከል ገና ጨለማ ሳለ ሁለቱ ማርያሞች ማርያም መግደላዊትና የያዕቆብ እናት ማርያም ከሰሎሜ ጋር ሽቱ ሊቀቡት ወደ መቃብሩ ሄዱ። በዚህ ግርማ ሌሊቱ ባልተለየው ድምፀ አራዊቱ በሚሰማበት ሌሊት የአይሁዳውያን ዛቻና የኃያላኑን የሮማ ወታደሮች ቁጣ ተጋፍጠው የክርስቶስን ክቡር ሥጋ ሽቶ ይቀቡ ዘንድ ወደ መቃብሩ ገሰገሱ። እነኚህ ሴቶች የክርስቶስን ሞት ሰምተው መቃብሩን ሊያዩ ከሩቅ የመጡ እንግዶች አልነበሩም ይልቁንም በዕለተ አርብ እየተላጋ ሲወሰድ፣ በየመንገዱ ሲጎተትና መስቀል ተሸክሞ ሲሄድ እያለቀሱ በደም የተዋበ የመስቀሉን መንገድ በእንባ ያጠቡ ሴቶች ናቸው።

17👍 3
አበው ስለ ጌታችን ትንሣኤ        በዚኽ በዓል ላይ በደስታ የተሞሉ የሴቶችና የወንዶች ወጣቶች ድምጾች እንደ መለከት፥ የሕፃናት መዝሙሮችም እንደ በገና ድርድር ነው። ድምፃቸውም የጌታቸውን ምስጋና ይዞ ወደ ሰማይ ይወጣል። ዝምታውም ከመባርቅት በላይ ለሚሰማ ለእርሱ ምስጋና ይገባል። እነሆ መሬት ከታች ድምፅዋን አሰማች፥ ሰማያትም ከላይ ከመባርቅት ድምፅ ጋር ጉርምርምታን አሰሙ። ሚያዝያ ሁለቱን ድምፆች አንድ ላይ አፈለቀች።እነዚህ ድምፆችም ከላይ የተሰሙ እና ከታች የተደመጡ ናቸው። ከቤተ መቅደስ የሚሰማው ምስጋናም ከመለኮታዊው ድምፅ እና ከመልካም መቅረዞች በሚንቦገቦጉት መብራቶች፣ እንደ ዝናብ ከሚፈስ ዕንባ ጋር የፋሲካውን በዓል እናከብራለን፡፡ ሙታን ዳግመኛ እንደሚነሡ ተስፋ ለሰጠን መሲህ ምስጋና ይገባል፡፡ እርሱ ሞትን አጥፍቶ ተነሥቷልና በሞት የበሰበሰው ዳግመኛ እንደሚታደስ ለሰው ልጅ ማረጋገጫ ሰጠ፡፡ እንግዲህ እናንተ ሙታን ሆይ የትንሣኤን ምሥጢር ስሙ! ተሰውሮ የነበረው እነሆ አሁን በግልፅ ታውጇልና። በኋለኛው ዘመን በቤተ ክርስቲያን በግልፅ ተነግሯል፡፡ እነሆ ክርስቶስ ለሦስት መዓልትና ለሦስት ሌሊት በሞት ከተያዘ በኋላ በሞት ተይዘው የነበሩትን ምርኮኞች ነፃ አወጣቸው። የሞትን ወታደሮች ድል ነሥቶ የበሰበሰውን የእኛን ሰውነት አደሰ፡፡ ከዚያን ጊዜ በፊት ሞት ዕብሪተኛ በመሆን ራሱን ከፍ ከፍ ያደርግ ነበርና፡፡ “እነሆ ካህናትና ነገሥታት በእኔ ግዛት ስር ናቸው፥ ግዞተኞች ሆነው በእኔ ወኅኒ ውስጥ ናቸው” ይል ነበር፡፡ በዕብሪተኛው ሞት ላይ ሳይጠብቅ ሰማያዊ ውጊያ መጣበት፥ እንደ ሽፍታም የተዋጊው ቀስት መታው፥ ከክብሩም ጣለው። ሞተው የነበሩትም አዳኝ የሆነውን ሕይወት አጣጣሙ፥ በጥልቁ የሞት ባሕር ውስጥም አዳኛቸውን አወቁት። ስለዚህ እርስ በርሳቸው በደስታ እየተጠቃቀሱ ተስፋቸው ፍጻሜ ማግኘቱን ተነጋገሩ፡፡ አዳም ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ ሕያው የሆነው እርሱ ከሞት ተነሥቶ የሞትን ዕብሪት እስኪደመስሰው ድረስ ሞት በሞቱ ሰዎች ላይ ሠልጥኖ ነበር። ነገር ግን ሕያው የሆነው እርሱ እንደ ታላቅ መብረቅ በሚያስደነግጠው ድምፁ ሞተው ለነበሩት ከሞት እስራት ነፃ መውጣታቸውን አበሠረላቸው። ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
Показать все...
8🙏 4👍 3😢 1
⛪️ ዘበእንቲአሃ ለቤተክርስቲያን ⛪️ ...ብዙዎቻችን ስለቤተክርስቲያን ስናስብ አእምሯችን ላይ የሚመጣው ህንፃው ወይም ተቋም ነው። በእርግጥ ህንፃ ቤተክርስቲያን ከቤተክርስቲያን ሦስቱ ትርጉሞች አንዱ ቢሆንምና ለአስተዳደር እንዲመች ሲባል ቤተክርስቲያን በተቋማዊ መልክ ብትገለጽም ቤተክርስቲያንን እንደ አንድ ድርጅት መረዳት ከሌሎች የእምነት ድርጅቶችና ፈራሽ ተቋማት ጋር የምትነፃፀር....  ሙሉውን ለማንበብ👇👇👇👇 from source
Показать все...
⛪️ ዘበእንቲአሃ ለቤተክርስቲያን ⛪️

የክርስቶስን መከራና ሕመም ኬርኤላይሶን ብለን ያሰብንበት ዕለተ ስቀለት ካለፈ አንድ ሳምንት ሞላው። በስግደትና በሐዘን ያሰብነው ሕማሙ መዳረሻው ለእኛ ካጠላብን የሐዘን ቀንበር ነፃ መሆን ነውና የከፈለልንን ፍፁም ፍቅር ለማሰብ ቅድስት ቤተክርስቲያን የሰሙነ ትንሳዔውን የመጀመሪያ አርብ ቅድስት ቤተክርስቲያን ብላ ትሰይመዋለች።

12👍 4🙏 4