ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት
Открыть в Telegram
በብ/ዓ/ቅ/ጴጥሮስ ወጳውሎስ እና ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ገጽ ነው
Больше3 278
Подписчики
+224 часа
+47 дней
+3730 дней
Архив постов
3 278
+4
Church NewsTo celebrate the annual feast of Our Lady Saint Mary, His Grace Abune Ermias, Archbishop of North Wollo, South Wollo, and Kemissie Dioceses; His Grace Abune Makarios, Archbishop of the Western Canada Diocese of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church; Teacher Qomos Abba Leyikun Wendifraw, Chief Executive Officer of the South Wollo Diocese; and the diocese's delegation were present at Gishen Debre Kerbe Saint Mary Church to celebrate the occasion. #Fre_Haymanot_Media https://t.me/FrehaymanotSS
3 278
+4
📣 ዜና ቤተክርስቲያንዓመታዊውን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓል ለማክበር ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣የደቡብ ወሎ እና የከሚሴ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ መምህር ቆሞስ አባ ለይኩን ወንድይፍራው የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የሀገረ ስብከቱ ልዑካን በግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ተገኝተው አክብረዋል። #ፍሬ_ሃይማኖት_ሚዲያ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ። https://t.me/FrehaymanotSS
3 278
ብዙኃን ማርያምበቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤ በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡ በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡ ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን ‹‹ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ›› ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ መካከል ፫፻፲፰ (ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው ‹‹ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው›› ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም ‹‹ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን›› ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት ‹‹ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን›› የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት ‹‹ብዙኃን ማርያም›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡ በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤ ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው ‹‹የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል›› አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር ‹‹የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ›› የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ ‹‹ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት›› ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡ ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡ መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ›› የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ›› ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡ ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡ ምንጭ፡- መጽሐፈ ታሪክ ወግስ፣ መ/ር አፈወርቅ ተክሌ፤ ፳፻፭ ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ ገጽ ፫፶፬-፫፶፮፡፡ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእመቤታችን አማላጅነት፣ የክርስቶስ የመስቀሉ ኃይል፣ የአባቶቻችን ሊቃውንትና ነገሥታት በረከት አይለየን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ። https://t.me/FrehaymanotSS #ፍሬ_ሃይማኖት_ሚዲያ
3 278
+2
📣 ዜና ፍሬ ሃይማኖት
የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እድሳት ተጠናቆ ታቦቱ ተመለሰ።
ለሦስት ወራት በእድሳት የቆየው የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሥራው ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከተባረከ በኋላ ታቦተ ምሥዋዕ ወደ መንበረ ክብሩ ተመልሷል።
የገዳሙ ዋና አስተዳዳሪ አባ ኪዳነማርያም ዮሴፍ ዕድሳቱ በፓትርያሪኩ ጸሎትና በካህናትና ምእመናን ትብብር በአጭር ጊዜ መጠናቀቁን ገልጸዋል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ሥራው በእግዚአብሔር ጥበብ የተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እድሳቱን ድንቅ በማለት ተሳታፊዎችን ባርከው መርሐ ግብሩን በጸሎተ ቡራኬ ዘግተዋል።
መስከረም 21/2019
#ፍሬ_ሃይማኖት_ሚዲያ
3 278
መስከረም ፳፩ ለምን ይከበራል?👉 ብዙኃን ማርያም በመስከረም 21 ቀን የሚከበረው የእመቤታችን በዓል 318ቱ ሊቃውንት አንድ ልብ ሆነው «ወልድ ከአብ ጋር በመለኮት አንድ ነው» ብለው ጽፈው አርዮስን አውግዘው የሃይማኖት ጸሎቱን አረጋገጡ። በአንድነት የተሰባሰቡበት ቀን መስከረም 21 ስለሆነ «ብዙኃን ማርያም» ተባለ። 👉 ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የጌታችን መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መሆኑ ነው። ዐፄ ዳዊት በረሃብና በቸነፈር ጊዜ መስቀሉን ከኢየሩሳሌም አስመጡ። እሳቸው ግን መስቀሉን ለመቀበል እስከ ስናር (በአሁኑ ሱዳን) ድረስ ሄደው በዚያ ሞቱ። ልጃቸው ዘርዐ ያዕቆብ መስቀሉን ወደ ኢትዮጵያ አምጥተው በተለያዩ ቦታዎች አስቀምጠውት ከቆዩ በኋላ በእግዚአብሔር ራእይ በወሎ ግሸን ደብረ ከርቤ ላይ በ1446 ዓ.ም በክብር አስቀመጡት። ከዚያ ጀምሮ መስከረም 21 በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል። ንስሐ ገብተው በዚያ ቀን የሚጸልዩ እስከ ሰባት ትውልድ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙ ተጠቅሷል። የጌታችን ጸጋ፣ የእመቤታችን አማላጅነት፣ የመስቀሉ ኃይልና የአባቶቻችን በረከት አይለየን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር። #ፍሬ_ሃይማኖት_ሚዲያ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ። https://t.me/FrehaymanotSS
3 278
+4
ዜና ቤተ-ክርስቲያንየሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ ለሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው በሰላም ተመልሰዋል። ለቅዱስነታቸው እና ለልዑካን ቡድናቸው ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የጉራጌ ሃድያና ሰልጤ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቦሌ አለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል። #ፍሬ_ሃይማኖት_ሚዲያ
3 278
+9
ዜና ፍሬ ሃይማኖትየፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ልማት ተቋም በተለያዩ የመንፈሳዊ የዜማ መሣሪያ ሥልጠናዎች ለአንድ ዓመት፣ ለስድስት ወራት እና በክረምት ሲያሠለጥናቸው የቆዩትን ከ150 በላይ ሠልጣኞች በመስከረም ወር 2019 ዓ.ም. አስመረቋል። በምርቃት መርሐ ግብሩ መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የተመራቂ ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት በበኩረ ሐዋርያት አዳራሽ ተካሂዷል። ከተመራቂዎቹ መካከል: 🔹 የበገና አድቫንስ የአንድ ዓመት ሰልጣኞች፣ 🔸 የበገና የስድስት ወር ሰልጣኞች፣ የበገና የክረምት ሰልጣኞች፣ 🔹 የክራር የስድስት ወር ሰልጣኞች፣ እና 🔸 የከበሮ የአራት ወር ሰልጣኞች ይገኙበታል። #ፍሬ_ሃይማኖት_ሚዲያ
3 278
📽 የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ትውስታዎች 🎞
https://youtu.be/avBk9uAHnb4?si=Sdp1UOyaGB1b1gx_
➕ ቻናሉን Subscribe በማድረግ የፍሬ ሃይማኖት Youtube ቤተሰብ ይሁኑ።
3 278
✨ አስደሳች ዜና ✨
ታዳጊ ማዕዶት ስለሺ ከካንሰር ህመሟ አገግማ ወደ ሀገሯ ተመለሰች።የሰንበት ት/ቤታችን የህፃናት እና አዳጊ ትምህርት ክፍል ተማሪ የሆነችው ታዳጊ ማዕዶት ስለሺ ለህክምና እርዳታ ወደ ህንድ ሀገር አቅንታ የካንሰር ህመሟ በሙሉ ሁኔታ ማገገሙን የሚያሳይ የምርመራ ውጤት በማግኘቷ ወደ ሀገሯ መመለሷ ተነገረ። ታዳጊዋ በደም ካንሰር ህመም ተይዛ በሀገር ውስጥ የኬሞቴራፒ ህክምና ስትከታተል የቆየች ሲሆን፣ ተጨማሪ የመቅኔ ንቅለ ተከላ ህክምና እንድታገኝ በህዝብ በተሰበሰበ ገንዘብ ወደ ህንድ ተልካ ነበር። በህንድ ሀገር በተደረገላት ጥልቅ ላብራቶሪ እና የፍሎሳይቶሜትሪ የምርመራ ውጤቶች መሠረት፣ በሰውነቷ ውስጥ ይገኝ የነበረው የካንሰር ህዋስ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱ በመረጋገጡ ተጨማሪ የንቅለ ተከላ ህክምና ሳያስፈልጋት ወደ ሀገሯ ተመልሳለች። በሀገር ውስጥ የወሰደችው ህክምና ከፍተኛ ውጤት በማምጣቱ አሁን ላይ ከበሽታው ነጻ መሆኗ የተረጋገጠ ሲሆን፣ በቀጣይም ለአምስት ዓመታት ያህል መደበኛ ክትትል ብቻ የሚደረግላት ይሆናል። ታዳጊዋ በደስታ ወደ ሀገሯ ስትመለስ ወዳጆቿ በተገኙበት ልዩ የደስታና የምስጋና ስነ-ስርዓት የተደረገላት ሲሆን፣ ቤተሰቦቿም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላደረገላት ድጋፍና ጸሎት ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። #ፍሬ_ሃይማኖት_ሚዲያ
3 278
+1
ከእኔ በኅላ ሊመጣ የሚወድ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ማቴ. 16፥24🌼 እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ 🌼
3 278
🕯 የሐዘን መግለጫ 🕯
"ሕያው ሆኖ የሚኖር ሞትንስ የማያይ ማን ነው" (መዝሙረ ዳዊት መዝ 89፤48 )የሰንበት ት/ቤታችን አገልጋይ የሆነው የ ዲ/ን ዮሐንስ አበበ እናት ስላረፉ የቀብር ሥርዓታቸውም ዛሬ መስከረም 17ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ በ6:00 በደብራችን ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ስለሚፈጸም በዕለቱ ከቀኑ 05:00 ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን በመገኘት ልብሰ ስብሐት እንድትለብሱ በትህትና እንጠይቃለን። በዕለተ ሰኞ (መስከረም 18 ቀን 2019) ከምሽቱ 12:00 በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝተን ስለምናጽናና ሁላችሁም እንድትገኙ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለወንድማችን እግዚአብሔር መፅናናትን ይስጥልን! 📍 አድራሻ: ዊንጌት ኢንዱስትሪ መንደር
"ኢየሱስም ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳን ሕያው ይሆናል" ዮሐ 11፥25
