ru
Feedback
الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ

الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ

Открыть в Telegram

​الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ ​እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
2 157
Подписчики
-224 часа
+367 дней
+41730 дней
Архив постов
​عن أبي هريرة رضي الله عنه قال قال رسول الله صلى الله عليه وسلم أكمل المؤمنين إيمانا أحسنهم خلقا وخياركم خياركم للنساء

ባል ሁን ባል ሁን? ምርጥ ባል ማለት ሲሞት ብቻ እንጂ ሚስቱ ልቧ የማይሰበር ጀግና ወንድ ነው የሴቶችን ልብ አደራ አደራ አደራ ወሏሂ ሴት ልጅ ልቧ ብርጪቆ ነው?! ሴት ልጅ በፍቅር ልቧ ይለመልማል
ባል ሁን  ባል ሁን? ምርጥ  ባል ማለት  ሲሞት ብቻ እንጂ ሚስቱ ልቧ የማይሰበር  ጀግና ወንድ ነው  የሴቶችን ልብ አደራ አደራ አደራ ወሏሂ ሴት ልጅ ልቧ ብርጪቆ ነው?! ሴት ልጅ በፍቅር ልቧ ይለመልማል በግዴለሽነት ደግሞ ይሰበራል።

📚ኪታብ በነፃ መማር የሚፈልግ ብቻ 🎊 በዚሁ ቴሌግራም በኦንላይን ያለ ክፍያ ማስተማር ተጀመረ 🌛 ቦታ ሳይሞላ ፍጠኑ
📚ኪታብ በነፃ መማር የሚፈልግ ብቻ 🎊 በዚሁ ቴሌግራም በኦንላይን ያለ ክፍያ ማስተማር ተጀመረ 🌛 ቦታ ሳይሞላ ፍጠኑ

🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺   #የታሪኩ_ርዕስ #በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"       #ክፍል_☞ #ስምት_⓼ ፣ ✍ #ፀሀፊ_☞ #አቡ_ኹዘይማ .................. #እራቢያ ................ #ባለቤቱ_የሌለው_ስደት" የጫካው ሌሊትና የጸጸት እንባ ......... ከደላላው ግርፋት በኋላ፣ በሌላ ሰልፍ ተተክተን ክፍት መኪና ላይ ወጣን። የሌሊቱ ብርድ እንደ ሰይፍ ገላን ይቆርጣል፤ ነፋሱም አጥንት ውስጥ ዘልቆ ይገባል። እራቢያ ግን እኔ ላይ ተለጥፋ፣ የገረፈኝን ጀርባዬንና ፊቴን እየዳበሰች "አስመታሁህ አይደል?" እያለች በስስት ትመለከተኝ ነበር። ከረዥም ጉዞ በኋላ አንድ ጫካ ውስጥ አወረዱንና "ተኙ" ተባልን። እራቢያን በጃኬቴ አልብሼ፣ እቅፍ አድርጌ አስተኝቻት እኔ ግን ከእንቅልፍ ጋር ተጣላሁ። ፎቅቅ ብዬ ቁጭ አልኩና ያሳለፍኩትን ሁሉ መቃኘት ጀመርኩ። በዚያች ቅጽበት የጸጸት ጎርፍ መጣና ዓይኖቼን አጥለቀለቃቸው። እኔ ገና ከልጅነቴ ጀምሮ በመከራ የታሸሁ ልጅ ነኝ፤ ድህነትና ስደት አያስደነግጡኝም። ነገር ግን... አሁን እራቢያ ጋር የማደርገው ነገር እንደ እሳት ይፈጀኝ ጀመር። "አላህ አሁን በዚህ ሁኔታዬ ቢገለኝ መጨረሻዬ ምን ይሆን? ባህር ውስጥ ሰምጬ የአሳ እራት ብሆንስ?" የሚለው ጥያቄ የሕሊና እረፍት ነሳኝ። "ጀርባዬ ቢቆስል - በደላላው ብትር፣ ልቤ ግን የቆሰለው - በጌታዬ ፍርሀትና ክብር፤ አላህ እያየኝ - ወንጀል ስደራርብ፣ ነፍሴ ተሸበረች - በጸጸት ማዕበል።" እራቢያ ከእንቅልፏ ነቅታ ስታየኝ፣ በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ብቻዬን እያለቀስኩ ነበር። "ምን ሆነህ ነው? አትተኛም እንዴ?" እያለች በነዚያ በሚያምሩ እጆቿ እንባዬን ጠረገችልኝ። እኔ የሚያስለቅሰኝ የእምነቴ መላላትና የወንጀሌ ብዛት እንደሆነ አልገባትም። እሷ ግን አሁንም "አንለያይም" እያለች፣ የከንፈሯን ጣፋጭነት ልታቀምሰኝ ትሞክራለች። ብርዱና ረሃቡ ባይቆልፈን ኖሮ፣ ወደ ትልቁ ጥፋት (ዝሙት) ልንደርስ ምንም አልቀረንም ነበር። በዚህ መሃል ግን... የሌሊቱን ጸጥታ የሚሰብሩ፣ መልካቸው ከሰይጣን ያልተናነሰ ሰዎች መጡ። ጉንጮቻቸው በጫት ያበጡ፣ ሰውነታቸው በሲጋራና በሺሻ የከረፋ፣ ሽታቸው ድባቡን የሚቀይር አዲስ ደላላዎች ብቅ አሉ። "የሲጋራው ጢስ - ጫካውን አፈነው፣ የጫት ቃሚዎች - መዓት መጣብን አሁን ደግሞ ምንድነው? መልካቸው አስፈሪ - ሽታቸው ክርፋት፣ በስደት ማኅደር - መጣ አዲስ ሰቆቃና ስቃይት።" የአዲሶቹ ደላላዎች መልክ ያስፈራል፤ ፀጉራቸው የቆመ፣ ገጻቸው የጨለመ፣ ንፅህና የሚባል ነገር የማያውቁ የጭካኔ ተምሳሌቶች ናቸው። የኢትዮጵያ ደላላዎችን ስም እየጠሩ "የገሌ ልጆች በዚህ፣ የገሌ በዚህ ተሰለፉ" ሲሉ፣ የልባችን ትርታ ቆመ። እኔና እራቢያ ልንለያይ መሆኑ ታወቀ። ያኔ እራቢያ ዓለሙን በለቅሶ አቀለጠችው። በረሃብና በውኃ ጥም በደረቁ ከንፈሮቿ ደጋግማ እየሳመችኝ፣ "አብሽር፣ እንገናኛለን" እያለች ትማጸነኝ ነበር። የገረፈኝን ጀርባዬን እየዳበሰች፣ በራሷ ስቃይ ላይ የእኔን ሕመም እያከመች፣ ያለ ከልካይ ስንብቷን በከንፈሮቼ ላይ አተመችው። እኔም ከእርሷ በላይ ተንበርክኬ፣ በዝምታ ማዕበል ውስጥ ሰጥሜ ነበር። "በረሃብ የደረቀ - ያ ጣፋጭ ከንፈርሽ፣ በስንብት መዓዛ - ነፍሴን አነቀሽ፤ ደላላው ሲለየን - በግድ እየጎተተ፣ የፍቅራችን ጅማሮ - በእንባ ተረታ።" ውድ አንባቢያን ሆይ! አሁንም አደራችሁን። ይህንን የምነግራችሁ ስሜታችሁን ለመቀስቀስ አይደለም፤ ነገር ግን በዚያ መከራ ውስጥ የሰው ልጅ ነፍስ ምን ያህል ደካማና ለፈተና ቅርብ እንደሆነች እንድታዩት ነው። የታሪኩ ዋና ቁምነገርና ትምህርቱ ያለው መጨረሻው ላይ ነውና፣ በትዕግሥት ተከተሉኝ። ሳንወድ በግድ ተለያየን። እኔን ወደ "ዴኬል" በሚወስደው መኪና ላይ ጫኑኝ። ያለ እሷ፣ ያለ ያቺ ጣፋጭ ወሬኛ ልጅ፣ ጉዞው ባዶ ሆነብኝ። "እሷ ምን ሆና ይሆን?" የሚለው ስጋት አንጀቴን ይበላው ጀመር። ንጋት አካባቢ የጅቡቲ ባሕር ዳርቻ ደረስን። ወይ ያሳቲር!አሏህ  ያ አስፈሪ ባሕር ከፊት ለፊቴ ተዘርግቷል። ማዕበሉ ድምፅ እያሰማ "በእኔ ላይ ትሻገራለህ" የሚለኝ ይመስላል። እኔ... ያ ከየብስ ፈተና ያልወጣሁት ምስኪን፣ አሁን ደግሞ በባሕር ላይ ልቆም ነው? የስደቱ ትልቁ ገጽ ይኸው ተገለጠ። "የባሕሩ ግርማ - ልብን ሲያስደነግጥ፣ ተስፋዬ ተንጠለጠለ - በማዕበል ላይ ሊቀጥል፤ ያለ እራቢያ ትንፋሽ - ያለ እሷ ሙቀት፣ ባሕሩን ልጋፈጠው - ቆሜ በብቸኝነት።" ቀጣይ... የዴኬል ሞገድና የጸጸት ማዕበል በሚል               ክፍል⓽..!! ይ... ቀ-----ጥ -ላ ---------ል

አንድ ውድ የሆነን ነገር ከእጃችን ሲወጣ ወይም ስንጎዳው ነው ዋጋው የሚገባን ዘግይቶ ..! ....የሴት ልብ እና የሺቶ ጠርሙስ ሲሰበር ነው የሁለቱም ጠረን እና ጥቅም ጎልቶ የሚገባህ ግን ለመጨረሻ
አንድ ውድ የሆነን  ነገር ከእጃችን ሲወጣ ወይም ስንጎዳው ነው ዋጋው የሚገባን ዘግይቶ ..!   ....የሴት ልብ እና የሺቶ ጠርሙስ ሲሰበር ነው  የሁለቱም ጠረን እና ጥቅም ጎልቶ  የሚገባህ ግን ለመጨረሻ ጊዜ ነው መልሰህ አታገኛቸውም  ✅✍️        ሁለቱም በህይወት ሳሉ እና ሳይሰበሩ ዋጋቸው ሊገባን ይገባል?

ፈጥኖ የመለስ ምርጥ ቻናል ይሸለማል ሙስሊሞች ነን ?

مَتْنُ ثَلَاثَةِ الْأُصُولِ وَأَدِلَّتُهَا ]ኪታብ ደርስ ተ ጀ መ ረ በኡስታዝ ኸድር ቢን አህመድ ሐፊዘሁላሁ ተዓላ ገባ ገባ በሉ ሸር ሸር አድርጉ https://t.me/+eBmwYuwue7xiZTY0 https://t.me/+eBmwYuwue7xiZTY0

አሏህ ሆይ ጌታችን ያረብ የድሮውን ጊዜ መልስልን ሴቷ በቤቷ ጉድጉድ ወንዱ ወጣብሎ ሰርቶ ማታሲገባ ነበር የምናቀው 🥺 አሁን አሁን እኮ ነገሩ ተበላሸ ተገላቢጦሽ ሆነ ሴቷ ውጭ ለውጭ ወንዱ ቤት ለቤት
አሏህ ሆይ  ጌታችን ያረብ የድሮውን ጊዜ መልስልን  ሴቷ በቤቷ ጉድጉድ    ወንዱ ወጣብሎ ሰርቶ ማታሲገባ ነበር  የምናቀው  🥺 አሁን አሁን  እኮ ነገሩ ተበላሸ ተገላቢጦሽ ሆነ   ሴቷ ውጭ ለውጭ  ወንዱ  ቤት ለቤት🤔 የሆነበት  ጊዜ  ፈሳድም ተስፋፋ  ኢላሂ   እኛ ......... እገዘን ያረብ  ለዚች ለጠፊ ዱኒያ 💦💦  ስት እህቶች ናቸው  ስራ ስራ ፈልጉ በማለት በችግር ላይ ያሉት  ኢጃዛቤት ለምግብ እኳን የሌላቸው ያረብ አተ የሲሳዬን በር ክፈትላቸው

📚ኪታብ በነፃ ልናስተምራችሁ ነው🎊 በዚሁ ቴሌግራም በኦንላይን ያለ ክፍያ ማስተማር ተጀመረ 🌛 ቦታ ሳይሞላ ፍጠኑ
📚ኪታብ በነፃ ልናስተምራችሁ ነው🎊 በዚሁ ቴሌግራም በኦንላይን ያለ ክፍያ ማስተማር ተጀመረ 🌛 ቦታ ሳይሞላ ፍጠኑ

_መልካም ቃል ዘላቂ ተክል ነው ዋጋውም የሚታወቀው ከኛ አልፎ በሌሎች ሕይወት ውስጥ ሲያብብ ነው።"_

_መልካም ቃል ዘላቂ ተክል ነው ዋጋውም የሚታወቀው ከኛ አልፎ በሌሎች ሕይወት ውስጥ ሲያብብ ነው።"_ 🖇️⬇️⬇️ https://t.me/umu_afifah_ami_chanal

ቆይ በሰው ቻናል ስም እና ፕሮ ፋይል ሌላ ቻናል የምከፍቱት ለምነው ?! ለምን በሌላ ስሞች አከፍቱም ?! በእናተንተ ቻና ሌላ ነገር ቢለቀቅበት ማነው ይባላል?! የማነው ቻናል ይባላል?! ለምን ነው እደዚህ የምታደርጉት !✍️ አንዳድ ጊዜ እራስን መሆን ጥበብ ነው ?!

🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺   #የታሪኩ_ርዕስ #በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"       #ክፍል_☞ #ሰባት_⓻ ፣ ✍ #ፀሀፊ_☞ #አቡ_ኹዘይማ .................. #እራቢያ ................ #ባለቤቱ_የሌለው_ስደት" ...........? የተራራው ግርማና የእራቢያ ቃል ኪዳን ከሦስት ቀን የናፍቆት እስር በኋላ፣ እራቢያ ዳግም ልክ እንደ ጠዋት ፀሐይ በፊቴ ብቅ አለች። መከራዋን ሁሉ ረስታ፣ በስስት ዓይኖቿ እያየችኝ የናፍቆት ዜማዋን ታንጎራጉርልኝ ጀመር። "አሁንስ አንለያይም አይደል?" ስትለኝ፣ እኔም በውስጤ የጸጸት እሳት እየነደደብኝ "ኢንሻ አራህማን" እላለሁ። የአላህን ስም በጠራሁ ቁጥር፣ በሠራሁት ወንጀልና በቆምኩበት የጥፋት መድረክ ምክንያት ውስጤ "እርር" ይላል። እንዲህ አልኩ፦ "በአንደበቴ አላህን - በልቤ ስሜትን፣ ተሸክሜ ዞርኩኝ - ይዤ ማንነቴን፤ አራህማን ስል ውስጤ - በእሳት ይቃጠላል፣ የእምነት ዋልታዬ - በስደት ይላላል።" የሌሊቱ ግማሽ ሲጋመስ፣ ጉዞው በጭነት መኪናዎች ተጀመረ። እስከ ፈጅር (ንጋት) ድረስ በአቧራ ተለውሰን ከተጓዝን በኋላ፣ ዳገታማው ተራራ ስር ደረስን። ጨለማው ለብርሃን ቦታውን ሲለቅ፣ ስድስት መቶ የሚጠጋው ስደተኛ እንደ በግ መንጋ በተራራው ላይ ይነዳ ጀመር። ድንበር ልንሻገር ነው! የኢትዮጵያን ምድር ተሰናብተን ወደማናውቀው ዓለም ልንረግጥ ነው! ደላላው "ፍትሕ" በሚመስል ጭካኔ ሴቶችን ከፊት፣ ወንዶችን ከኋላ አሰለፈ። እኛ ስድስት መቶ ነፍሶች፣ በተራራው ላይ ስንጓዝ አፈሩን የምንመስል፣ ተስፋችንን በዳገቱ ላይ የምንለጥፍ ምስኪኖች ነበርን። እራቢያ ግን ከሴቶቹ መሪ ጋር መሄድ ሲገባት፣ የልቧ መሪ እኔ ጋር ነበርና ከአይኔ ልትራቅ አልፈለገችም። የሴቶቹ ሰልፍ መጨረሻ ላይ ሆና እኔን ስትጠባበቅ፣ ደላላው "ሂጂ! ወንዶች ከኋላ ናቸው!" እያለ በቁጣ ይገፋታል። እሷ ግን በዚያች የረቀቀችና ማራኪ አንደበቷ "ባሌ ነው! እሱን ጥዬ መሄድ አልችልም!" ብላ አምባገነኑን ደላላ ተጋፈጠችው። አቤት ያኔ ያየኋት እራቢያ! ቁመናዋ ልክ እንደ ተራራው ግርማ ሞገስ ያለው፣ ንግግሯ ደግሞ እንደ ምንጭ ውኃ የሚፈስ፣ ማንኛውም ወንድ ቢያያት ሊወድቅላት የሚችል አበባ ነበረች። እኔን "ባሌ" ብላ ስትጠራኝ፣ በሐሰትና በእውነት መሃል የቆምኩት "የሙሐመድ ልጅ" በድንጋጤና በሐፍረት ተዋጥኩ። "ድንበሩ ሊሻገር - ተራራው ሲናወጥ፣ እራቢያ ቆመች - ጥላዋን ሳትለውጥ፤ 'ባሌ ነው' ስትል - በአደባባይ ጮኻ፣ እኔን አኖረችኝ - በሐፍረት ተዘፍቃ። ውበቷ እንደ ሰማይ - ቃሏ እንደ መብረቅ፣ በረሃውን ሞላው - በፍቅር ሲያብለጨልጭ።" የበረሃው ጅራፍና የነፍስ መስዋዕትነት የተራራው ጉዞ ቀጠለ። እራቢያ ለቅሶዋና ሐዘኗ የደላላውን ልብ እንኳን ሊያሸንፍ በቃ። "ማነው ንገሪኝ? ላምጣላሽ!" ብሎ ደላላው ሲጠይቃት፣ እኔን ለይቶ ወደ እርሷ አመጣኝ። በዚያ በስድስት መቶ ሰው ፊት፣ እጇን ሳትለቅቀኝ፣ እንደ ጥላዬ ተለጥፋ ቀኑን ሙሉ ተጓዝን። የሰው ሁሉ ዓይን በእኛ ላይ ነበር፤ አንዳንዱ በቅናት፣ አንዳንዱ በግርምት ያየናል። እኔ ግን በሷ ምክንያት ከወንዶቹ ግፊ ተገላግዬ፣ የእርሷን እጅ እንደ መሪ ጨብጬ ተራራውን አቋረጥኩ። ፀሐይ ለጨለማው ቦታዋን ስታስረክብ፣ አስፈሪና ድንጋያማ ተራራ ስር አረፍን። በዚያ በረሃ ውስጥ ሱማሌዎቹ ምግብ ይሸጣሉ። ረሃቡ አንጀታችንን ሲበላው፣ ገዝተን መብላት ጀመርን። እራቢያ... ያቺ በቅመም ምላሷ ልብን የምታቀልጥ አበባ፣ "ላጉርስህ" እያለች በጣፋጭ ወሬዋ ታጎርሰኝ ጀመር። ያ የጉርሻ ጣዕም በአንደበቴ ሲያልፍ፣ በውስጤ ግን "የአላህ ትእዛዝ የት ገባ?" የሚል የጸጸት ጩኸት ይሰማኝ ነበር። እንዲህ አልኩ፦ "አንጀቴ ሲራብ - ጉርሻው ጣፈጠኝ፣ ነፍሴ ግን በኃጢአት - ሰጥማ ታነቀኝ፤ የበረሃው እራት - ቢሆንም መዳኛ፣ የሰለፎች ቂርዓት - ሆነብኝ ዳኛ።" ብርዱ መጣ። እራቢያን አቅፌ ተኛሁ። የስደቱ መከራ፣ የውኃው ጥምና የረሃቡ ስቃይ ስሜትን ቢያደነዝዘውም፣ ከትልቁ ስህተት (ዝሙት) በቀር ሁሉንም ደፍረን ነበር። "ሱብሐነላህ!" አልኩ በውስጤ፤ ሰው እንዴት እንዲህ አቅመ ቢስ ይሆናል? እኩለ ሌሊት ላይ መኪና መጣ። በቁጥር መጫን ተጀመረ። እኔ ተቆጥሬ ስገባ፣ የእራቢያ ተራ ሲደርስ ግን "ቁጥር ሞላ!" ተባለ። እራቢያ ቀረች! ያኔ በረሃው በጩኸቷ ተናወጠ። ደላላው በጫት የጀዘበና በሲጋራ የከረፋ ማንነቱን ይዞ፣ በቁጣ ሊመታት ብጥሩን (ዱላውን) ሰነዘረ። እኔ... እንዴት ከመኪናው እንደወረድኩ አላውቀውም፤ ብቻ የእራቢያን ስቃይ ማየት አልቻልኩም። ደላላው ሊመታት ሲሰነዝር፣ ጀርባዬን ሰጠሁት። የመጀመሪያው ዱላ እኔ ላይ አረፈ! ሁለተኛውም ደገመኝ! ጀርባዬ በእሳታማ ዱላ ሲገረፍ፣ እራቢያ "አትምቱት!" እያለች በጩኸት ዓለሙን አቀለጠችው። ያ የደላላው ጭካኔና የእራቢያ ስቅስቅታ በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የታሪክ ጠባሳ ሆኖ ተቀረጸ። "በራቢያ ፋንታ - ገላዬ ሲገረፍ፣ የደላላው ብትር - በጀርባዬ ሲያርፍ፤ ፍቅርና መከራ - በአንድነት ታሹ፣ የስደቱ ቀናት - በእንባ ታጠቡ።" ከዚያ ዱላ በኋላ ደላላው ምን አደረጋችሁ? አብራችሁ መሆን ቻላቹሁ ወይስ የጫካው ሌሊትና የጸጸት እንባ ⤵️                           ክፍል.⓼ ይ-- -ቀ ---ጥ -------ላ ------------ል --------------▫

ቀጣይ ክፍል 7 ለይል ይለቀቃል ኢንሻአሏህ እዚህ የምታውቁትና የምትረዱት ነገር የተፃፈውን በሌላ እናተ በፈቀዳቺሁት ሀሳብ መልኩ ልትገነዘቡት አይደለም ይልቁንም እኛ አሁን በሀራም ግንኙነት ፍቅር ላይ ነን ወይስ በሀላሉ ብላቺሁ ራሳቺሁን ልትመለከቱ ነው ልትማሩበትም ጪምር ነው ጠይብ ያሳልፍኩትስ ግንኙነት እደት ነው ብላቺሁ ትክክለኛ ተውበትን ትክክለኛ መመለስን ልትመለሱ ዘንድ እጂ የተፃፈው ባለታሪኩ የሳለፈውን የሀራም ግንኙነቶችን እድትይዙና ስሜት እድትገቡ አይደለም አይ ያለ ሰው ከባለታሪኩ ጋራ ትረዳዱ ዘዳ በውስጥ ፃፉልኝ✅👍

ፈጥኖ የመለስ ምርጥ ቻናል ይሸለማል ቁርአን ዉስጥ 124 ሱራ አለ ?

ፈጥኖ የመለስ ምርጥ ቻናል ይሸለማል ቁርአን ዉስጥ 124 ሱራ አለ ?

🟠 አሁን ቀጥታ ስርጭት ቂራአት ~~ 📖 የቁርአን ተፍሲር   🎙 በኡስታዝ አቡ ሐኒፋ ሑሰይን ኢድሪስ ሰዒድ ሐፊዘሁሏህ ተ    ጀ       መ           ረ 👉 ሸር አድርጉት. ተቀላቀሉ አድም አድርጉ https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris?videochat=59dc0e0734fd48907f

+1
🎀አይዞሽ እራሴ  አንድቀን የቤት እመቤት ሆነሽ  ከቤትሽ ሁነሽ  እፎይ ትያለሽ ኢንሸአሏህ ትንሽ ብቻ صبر
🤍 ኢንሻ አሏህ! ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል! የትዕግሥት ፍሬዋ ጣፋጭ ነውና ትንሽ ትዕግሥት ብቻ አሁንም ታጠቂ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ሁሉ ድካም አልፎ በቤተሰብሽ መሀል በሰላም በድል እና በእፎይታ የምትቀመጪበት ቀን ይመጣል።
إن شاءلله