ru
Feedback
Abu Hayder Aliy

Abu Hayder Aliy

Открыть в Telegram

نشرالكتاب والسنة وقول العلمآء بائذن الله الباري بأبي حيدر علي إبن سليمان إبن أحمد الولغاوي

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
571
Подписчики
Нет данных24 часа
+287 дней
+6030 дней
Архив постов
ዓልይ አብኑ አቢ ጧሊብ እንድህ ይላሉ :- ኢዕመል ሊዱንያከ ከአነከ ተዒሹ አበደን ወዕመል ሊኧኺረቲከ ከአነከ ተሙቱ غደን ለዱንያህ ዘላለም እንደምትኖር ሁነህ ስራ ለኧኼራህ ነገ እንደምትሞት ሁነህ ስራ https://t.me/abu_haider_aliye

~ አስደሳች ዜና ዛሬ ከዓስር በኋላ የ"መንዙመቱ ሪያዲል ጀነህ" ደርስ ይጀመራል። አቅራቢ፦ ሸይኽ ኢብራሂም አል'ሙሐይሚድ አድራሻ፦ ሀይቅ- [መዲና መስጂድ] ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል የሚተላለፍ ይሆናል። = T.ME/MULTEQA_SELEFIYIN T.ME/MULTEQA_SELEFIYIN

▫️የዉዷ እህታችን ኡሙ ፈዉዛን ሶፊያ ቢንት አብደላህ የሽኝት ፕሮግራም አስመልክቶ የተዘጋጀ የዳዕዋ ፕሮግራም▫️ 〰〰🌷〰〰🌷〰〰🌷〰〰 ዉዷ እህቴ አላህ በሰላም ለበተሰቦችሽ ለሀገርሽ ያብቃሽ ተጋባዥ
▫️የዉዷ እህታችን ኡሙ ፈዉዛን ሶፊያ  ቢንት አብደላህ  የሽኝት ፕሮግራም አስመልክቶ የተዘጋጀ የዳዕዋ ፕሮግራም▫️  〰〰🌷〰〰🌷〰〰🌷〰〰                   ዉዷ እህቴ አላህ በሰላም ለበተሰቦችሽ ለሀገርሽ ያብቃሽ ተጋባዥ ኡስታዞቻችን ❶🎙 ሼይኽ አወል አህመድ ሀፊዘሁሏህ ❷🎙 ሼይኽ ሙሀመድ መኪን ሀፊዘሁሏህ ➌🎙ኡስታዝ አቡ ሙሀመድ ሰዒድ ሀፊዘሁሏህ ❹🎙ኡስታዝ አቡ ነሚር ሀፊዘሁሏህ ➎🎙ኡስታዝ አቡ አማር ሀፊዘሁሏህ ➏🎙ወንድም አቡ ሂበቲላህ ሀፊዘሁሏህ ➐🎙ወንድም አቡ አመቲረህማን ሀፊዘሁሏህ ➑🎙ወንድም አቡ ሹራ አህመድ ሀፊዘሁሏህ ➒🎙 ወንድም ሙሐመድ ሲራጅ ሀፊዘሁሏህ ➓🎙ወንድም ኑረዲን አል አረቢ ሀፊዘሁሏህ ❶❶🎙ወንድም አቡ አይመን ሀፊዘሁሏህ ❶❷🎙ኡስታዝ አቡ ኡበይዳ ሀፊዘሁሏህ ❶➌🎙ኡስታዝ ሙሐመድ አያሌዉ ሀፊዘሁሏህ ❶❹🎙ኡስታዝ አብዱል መሊክ ሀፊዘሁሏህ  ❶➎🎙ኡስታዝ አቡ ሀሳን ሀፊዘሁሏህ 🔈ፕሮግራም መሪዎች 🎙ወንድም አቡ ማሂ 🎙ወንድም አቡ ሁዘይፋ  ቀን፦ ማክሰኞ ምሽት ⏰በኢትዮጵያ  2፡15 ⏰በሳኡድ 8፡15 ⏰በዱባይ 9፡15 👥እርሶም ለዚህ ልዩ ፕሮግራም ተጋብዘዋል! በሰዓቱ ይጠብቁን! ቀጥታ ስርጭት አድራሻ፦ ➛https://t.me/Asselefya3 ➛https://t.me/Asselefya3

متن_منظومة_رياض_الجنة_في_عقيدة_أهل_السنة.pdf1.08 MB

ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «ከበደሎች ሁሉ ትልቁ በደልና ከድንቁርና ሁሉ ትልቁ ድንቁርና ማለት ሰዎች እንዲያልቁህና እንዲያተልቁህ እየፈለክ፤ የአንተ ልብ ግን አላህን ከማተለቅና ከማላቅ ባዶ ከሆነ ነው።» 📚 ۞ الفـوائــد【272】۞ እስኪ እራሳችንን እንፈትሽ ! https://t.me/abu_haider_aliye https://t.me/abu_haider_aliye

➨የዚህች ምድር ድምቀት ወንድ «ስለ ወንድ ልጅ ወንድነት እናውራ» ---------------------------------- .....በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ሆነው ህይወትን በፀጥታ ተደብቀው እየገፉ ላሉ ወንድሞቼ ይድረስልኝ..... ወንድነት በራሱ በዝምታ ገዋን የተሸበበ ስውር-ስፍ ነው ብዬ አስባለሁ ደስታውም ሆነ ሀዘኑ በትዕግስተት የተቃኘ እጂግ ልዩ ፍጡር ወንድ ልጅ ነው። ...ሀላፊነት የሚሰማው ረቂቅ ሰው ወንድ ይባላል ለእናት ለአባቱ ፣ለእህት ለወንድሙ፣ለሚስትና ለልጆቹ ሲል መከራውን ችሉ የህይወትን አቀበት የሚቃትት የፀና ተራራ ወንድ ልጅ ይባላል። رجولتك تظهر في كلّ موقف تمرّ فيه، شجاعتك وحكمتك دائمًا مصدر فخر لي ወንድነትህ በሚያጋጥሙህ ሁኔታዎች ሁሉ ይንጸባረቃል... ድፍረትህና ጥበብህ ሁልጊዜ ለእኔ የኩራት ምንጭ ነው አወ አንተ ጀግና ነህ። ...አወ ወንድ ልጅ ለራሱ ለአንድ ነፍሱ ብዙ አይጨነቅላትም ራሱን መቻል እንደማያቅተው በተሰጠው ህሌናው ጠንቅቆ ያውቃል ግን ወንድነት ራስን መቻል ብቻ አንዳልሆነ ይረዳልና ...ዝቅ ሲል ለቤተሰቡ፣ ከፍ ሲል ለሀገሩና ለህዝቡ ሲል ብዙ ዋጋ እየከፈለ መራር ፅዋን የሚጎነጭ ምታዓታዊ የአሏህ ረቂቅ ፍጥረት #ወንድነት ነው። الأوقات الصعبة تصنع رجالاً أقوياء، والرجال الأقوياء يصنعون أوقاتاً سعيدة، والأوقات السعيدة تصنع رجالاً ضعفاء، والرجال الضعفاء يصنعون أوقاتاً صعبة. " አስቸጋሪ ጊዜያት ጠንካራ ሰዎችን፣ ጠንካራ ሰዎች መልካም ጊዜን ይፈጥራሉ፣ ጥሩ ጊዜዎች ደካማ ሰዎችን እና ደካማ ሰዎች አስቸጋሪ ጊዜን ይፈጥራሉ ይባላል አይደል ⁉️ ➨ታዲያ ወንድነት እንደዚህ ከሆነ ለምንድነው መኖር የደከመህ⁉️ ጀግናዬ ንገረኝ እስኪ ለምን መኖር ደከመህ⁉️ ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ⁉️ ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ⁉️ በስደት ስላለህ⁉️ በህመም ስለሆንክ⁉️ ያሰብከው ስላልተሳካልህ ነው⁉️ ያመንከው ስለከዳህ ነው⁉️ አሞታለሁ ብለህ ለምን ታስባለህ? ሞት ለማን ሲቀር አይተሀል⁉️ «.....ስማ ጀግናዬ #አበቦችኮ_ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው #ሳይፈኩ አይቀሩም...፡፡ » ስለዚህ ሰውም ሟች ነው ይህ ለአንተም ለኔም የሚዘነጋ አይደለም ግን ሟች ነኝ ብሎ ያለተስፋ መኖር የለበትም፡፡ .....ጀግናዬ ቅዠት ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም ይባላልኮ... ......ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ...ጀግናዬ እኔ አስረግጨ እነግርሀለሁ አንተ አላስፈልግም ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገርሮች አሉ። ...እመነኝ የኔ ጀግና...ወላሒ‼️ ➨ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡ ➨ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡ ➨ ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡ ➨ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡ ➨ያላንተ የማይነበብ ፅሁፍ አለ ይኸው ስላለህ ይህንን የኔን ፅሁፍ አነበብክ አይደል ይህ ማለት #ታስፈልገናለህ ማለት ነውኮ ወንድሜዋ ፡፡ ✅ይህቺ የዱንያ አለም ትልቅ የሻማ መብራቶች ክምችት ነች ..አንተ ደግሞ በስብሰባው ውስጥ ያለህ አንድ #የሻማ_ችቦ_ነህ አንተ ስትጠፋ የየሻማው የብርሀን ድምቀት ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል አብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ #በነገሮች_አትረበሽ፡፡ እደግመዋለሁ ህይወት ልክ እንደ ጨዋታ ነው፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ብልህ ጥሩ ጊዜ አሳልፎ የማይረሳ ትዝታ ይቀርፃል.... ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው ግን መቼም ቢህን ተስፋ እንዳትቆርጥ አደራ እልሀለሁ። ⭕️ በህይወትህ ውስጥ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ክስተት መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ ...ወንድማለም የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ነው፡፡ "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ወይም መሸነፍ ማለት ሳይሆን አቅማችን የሚችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው። በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው፡፡ ሳትኖር ለመሞት አትቸኩል ይሄ ማለት ሳትፅፍ ለማጥፋት ሞክር ማለት ነው፡፡ እስኪ አንተም ታሪክህን ፃፍና እናንብብልህ...እ ..አብሽር ትችላለህኮ የኔ ጀግና...። ......አንተ ፃፈው እኔ አነብልሀለሁ እሽ ትችላለህ በቃ አይዞህ በርታ ታገል ለስኬት ትንሽ ነው የቀረህኮ ...‼️ ......በኑረዲን አል-አረብ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

«ይህ ፀባይ መቼ ነው የሚለቀኝ!?» አንዳንዴ ሁሉንም ሰው እንደራሴ አድርጎ የሚያሳየኝ መነፀሬ ቢሰበርና ሌላ ቢገጠምልኝ እመኛለሁ። .....ይህ «ለሁሉም አንድ አይነት መሆን» ግልፅነት ወይስ ራስን ማስገመት⁉️"ግልፅነት መስሎን ብዙ ነገር አውርተን፣ ራሳችንን ያስገመትነው ስንቶቻችን ነን⁉️" ብዙዎቻችን ግልፅ መሆንን እንደ መልካም ስብዕና ቆጥረን፣ የልባችንን መዝገብ ለሰዎች በዝርዝር ስንተርክ እንገኛለን። .......ሰው ሁሉ እንደ እኛ ቅን መስሎን ልባችንን ብንከፍትም፣ የሰማን ሁሉ ግን እንደ ወዳጅ አልተረጎመውም። .......አንዳንዴ መሸሸግ የነበረብንን ድክመት ለሰዎች በማካፈላችን፣ ትላንት ባወራነው ወሬ ዛሬ ዋጋ እንከፍላለን። ያልተገባን ሰው የልባችንን ክፍል ስናሳየው፣ ሚስጥራችንን ለመጫወቻ እንዲሆን ስንሰጠውና ክብራችንን በገዛ ንግግራችን ስናቃልለው... ያኔ ነው "ግልፅነት" እና "ያለቦታው መናገር" ያላቸው ልዩነት የሚታየን። #የኔማ_ለየት_ያለ_ነው‼️ አንዳንዴ ዝምታ ከሺህ ቃላት በላይ ክብር አለው። ራሳችሁን ለሁሉ ክፍት አታድርጉ፤ ሁሉም ሰው የእናንተን ማንነት ጥልቀት ለመረዳት የሚያስችል "ሚዛን" የለውም። .....ነገር ግን ያለፈው አልፏል‼️ ግልፅ በመሆናችሁና በማውራታችሁ ራሳችሁን አስገምታችሁ ከሆነ፣ ያ የእናንተ የልብ ንፅህና እንጂ የነሱ ብልጥነት አይደለም። ➨ከዛሬ ጀምሮ ግን እነዚህን ሦስት ነገሮች እናስተውል፦ ❶➨. ልባችሁን ጠብቁ፡ ሁሉም ሰው ታሪክህን የመስማት እድል ሊኖረው አይገባም። ❷➨. ክብራችሁን አስቀድሙ ዝምታ የድክመት ሳይሆን የጥንካሬ ምልክት ነው። ➌➨.በጥልቀት መርምሩ ቃላት አንዴ ከአፍ ከወጡ አይመለሱም፤ ስለዚህ ከመናገራችሁ በፊት "ይህ ሰው ለዚህ ወሬ ይገባዋል⁉️ ብላችሁ ጠይቁ። ትላንት በንግግራችን ተገምተን ከሆነ፣ ዛሬ በዝምታችንና በበሰለ ማንነታችን ክብራችንን እንመልስ! «ኑረዲን አል-አረብ» t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

አሚን ያረብ جزاك الله خيرا

መግቢያ!-00- 📚 የኪታቡ ስም፦ ❞ذَمُّ قَسْوَةِ الْقَلْب❝ (የቀልብ መድረቅ አደገኝነት፣ መንስኤውና መፍትሔው) 🎙 በኡስታዝ፦ ዐብዱ ረዛቅ አል-ባጂ (ሐፊዘሁላህ)

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ዛሬ ጁሙዓ ነዉ የጁሙዓ ሱናዎች ➖➖➖➖➖➖➖ ↩️💎 ‏سنن يوم الجمعة🌿🌿🌿 ➊ 💎الغسل ➋💎 الطيب ➌ 💎السواك ➍💎 لبس الجميل ➎💎 قراءة سورة الكهف ➏💎 التبكير لصلاة الجمعة ➐💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➊ 🌺መታጠብ ➋ 🌺ሽቶ መቀባት ➌🌺 ሲዋክ መጠቀም ➍ 🌺ጥሩ ልብስ መልበስ ➎ 🌺ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን ➏ 🌺ለጁመዓ ሶላት መጣድ ➐ 🌺በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿〰 «اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ   🌺በሰለዋት በዚክር ያውለን ያረብ ﷺ 🌹 .................🌹 ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹🔹🔹🌹  ﷺ ﷺ ﷺ 🌹🔹🔹🌹 በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ !!                 https://t.me/abu_haider_aliye https://t.me/abu_haider_aliye

ኢብኑ_ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ  : - «ከፍ ያሉ ደረጃዎች በፈተናና በመከራ እንጅ አይገኙም።» 📚 ۞ مجموع الفتاوى【25/302】۞ ─────────── ሁላችንም መሆን የምንፈልገውን ለመሆን ማገኘት የምንፈልገዉን ነገር ለማገኘት ሙሉ አላማችንን ለማሳካት ብዙ የምናሳልፋቸዉ መሰናክልቶች /እንቅፋቶች እንደሚኖሩ ማወቅ አለብን ፈተናዎችንና መከራዎችን ቀስ ብለን ማለፍ ካልቻልን አደለም አላማችን ልንደርስ ቀርቶ ሂዎታችን ራሱ ጥያቄ ምልክት ዉስጥ መግባቱ አይቀርም  ። አላህ ከመከራና ከፈተና ይጠብቀን 🤲 ፈተናንና መከራን እምናልፍበትን ሶብር ና ኢማንን አላህ ይስጠን 🤲 https://t.me/abu_haider_aliye https://t.me/abu_haider_aliye

ቁርአንን ማወቅና መረዳት ለሰው ልጅ በዱንያም (በዚህ ዓለም) ሆነ በአኺራ (በመጪው ዓለም) ትልቅ ስኬትንና ክብርን ያጎናጽፋል። የቁርአን እውቀት ዋና ዋና ፋይዳዎችና ቱርፋቶች በሚከተሉት ነጥቦች በአጭሩ ማየት ይቻላል፦ 1. የአእምሮና የልብ እርካታ (ሰላም) ቁርአን ለሰው ልጅ ልብ ፈውስና እረፍት ነው። አላህ በቃሉ እንዲህ ይላል፡- "አላህን በማውሳት ልቦች ይረጋጋሉ።" ቁርአንን ማወቅ ጭንቀትን ያስወግዳል፣ ውስጣዊ ሰላምን ይሰጣል። 2. የአላህ ወዳጅ መሆን ቁርአንን የሚቀሩና በውስጡ ያለውን እውቀት የሚተገብሩ ሰዎች "የአላህ ቤተሰቦችና የላቁ ወዳጆቹ" ተብለው ይጠራሉ። ይህ በፈጣሪ ዘንድ ካሉ የክብር እርከኖች ሁሉ የላቀው ነው። 3. ለላቀ ስነ-ምግባር መታነፅ ቁርአን የተሟላ የሕይወት መመሪያ ነው። እውቀቱ ያለው ሰው እውነተኝነትን፣ ታማኝነትን፣ ትዕግስትንና ለወላጆች እንዲሁም ለሰዎች መልካም መዋልን ይማራል። ይህም በህብረተሰቡ ዘንድ ተወዳጅና የተከበረ ያደርገዋል። 4. የዕውቀት ብርሃን (ትክክለኛውን መንገድ መለየት) በሕይወት ውስጥ መልካሙን ከክፉው፣ እውነቱን ከሀሰቱ ለመለየት ቁርአን እንደ ብርሃን (ፉርቃን) ያገለግላል። አንድን ነገር ስንከውን በዕውቀት ላይ ተመስርተን እንድንወስን ይረዳናል። 5. ከፍተኛ ምንዳና ደረጃ በዱንያ፡ ቁርአንን ያወቀ ሰው በሰዎች ዘንድ መሪና አርአያ ይሆናል። በአኺራ፡ ቁርአንን ያነበበና ያወቀ ሰው በጀነት ውስጥ "እየቀራህ ውጣ" ይባላል፤ የመጨረሻው ደረጃውም በሚያቆምበት አንቀጽ ዘንድ ይሆናል። 6. አማላጅነት ቁርአን በቂያማ ቀን ለሚያውቁትና ለሚቀሩት ሰዎች አማላጅ ሆኖ ይቀርባል። ከቀብር ጨለማና ከፍርድ ቀን ስጋት ለመጠበቅ ትልቅ ዋስትና ነው። https://t.me/abu_haider_aliye https://t.me/abu_haider_aliye

ማስጠንቀቂያ ሀዋላ ላኩልን እህቴ ታማ አባቴ ታሞ እያሉ በዋትስ አፕ እና በቴሌ ግራም የሚደረግ ሌብነት አብዛኛዎቹ ካፊሮች ናቸው በሙስሊም ስም እየመጡ በደካማ ጎናችን ለመግባት ይሞክራሉ ሙስሊም ወላሂ ካለ እንደሚታመን እና እዛኚ መሆናችንን ያውቃሉ ብዙ እህቶች እና ወንድሞችም ተበልተዋል ተጭበርበብርዋል ሌቦቹ አሁንም ሌብነታችውን ቀጥለዋል ገንዘባችሁን ያዙ የት እና እንዴት ለማን መስጠት እንዳለባችሁ እውቁ በተለይ ደሞ እህቶች እንኳን ቤተሰቦቹ እሱ ለምን አይሞት ከፈለገ የትም ምንም የማቀን ሰው ሲያናግረን መንቃት እና ማጣራት አለብን ለመሆኑ ግን ብር ቅጠል ነው እንዴ ከዛፍ ላይ ነው የሚቀነጠሰው!!!! https://t.me/abu_haider_aliye https://t.me/abu_haider_aliye

አሰላሙ ዐለይኮም ወራህመቱላሂ ወበረከትሁ በአላም ላይ ያችሁ ውድ እና የተከበራችሁ እህት ወንድሞች እንዴት አላችሁ አላህ በእየላችሁበት አላህ ከመጥፎ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ ይህ ከላይ የምታዩት ህፃን
+1
አሰላሙ ዐለይኮም ወራህመቱላሂ ወበረከትሁ በአላም ላይ ያችሁ ውድ እና የተከበራችሁ እህት ወንድሞች እንዴት አላችሁ አላህ በእየላችሁበት አላህ ከመጥፎ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ ይህ ከላይ የምታዩት ህፃን ዘከሪያ ፡ሽምሰዲን ይባላ ፡የ8አመት ህፃን ልጅ ሲሆን በሆድ ውስጥ ህመም አጋጥሞት በአዋሳ ከተማ ሲታከም ቆይቶ ስላልተሻለው ወደ ጥቁር እንበሳ ሆስፒታል ሪፈር ተብሎ ሲታከም የቆየ ሲሆን ፡ ሊሻለው ባመቻሉ ኬዙ በጣም ከባድ በመሆኑ ወደ ህንድ አገር ሂዶ እንዲታከም ፡6,000,000 (ስድስት ሚሊያን ብር የተጠየቀ ስለሆነ ወላጆቹ ምንም አይነት የገቢ ምንጭም ሆነ ቋሚ ንብረት የሌላቸው በመሆኑ ታክሞ እንዲድንልን ከአላህ ቀጥሎ ሰበብ ሁኑን ይላሉ ስለሆነም ህፃን ዘከሪያ ሽምሰዲን ህክምናውን ለማድረግ ወላጆቹ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላቸው ፡በመሆኑ ህክምናውን እንዲታከም የሁላችንም ትብብር የሚጠይቅ ነው! የልጀ ስም :- ዘከሪያ ሸምሰዲን አብዱ የአባት ስም :- ሸምሰዲን አብዱ አያንሶ ስ.ቁ :- 0927270001 0926328897 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000380970582 https://chat.whatsapp.com/CcoyKrfJaDH5qOvPbZx9PN?mode=gi_t

ኢብኑ_ረጀብ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ  : - «ድህነት ማለት ገንዘብ ማጣት እንዳይመስልህ፣ ነገር ግን ዲንን ማጣት ከድህነቶች ሁሉ የከፋውና ትልቁ ነው።» 📚 ۞ مجمـوع الرسائـل【1/65】 https://t.me/abu_haider_aliye https://t.me/abu_haider_aliye

✨➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ▫️ ልዩ የሰረግ እና የዳዕዋ ፕሮግራም▫️ 〰〰🌷〰〰🌷〰〰🌷〰〰 بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في الخير የወንድማችን ሙሐመድ ሁሴን እና የእ
+1
✨➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ▫️ ልዩ የሰረግ እና የዳዕዋ ፕሮግራም▫️  〰〰🌷〰〰🌷〰〰🌷〰〰 بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في الخير የወንድማችን  ሙሐመድ ሁሴን እና የእህታችን ዘይንያ አሊ የኒካህ ፕሮግራም አስመልክቶ የተዘጋጃ                   የሙሓደራ ፕሮግራም ተጋባዥ ወንድሞቻችን ☹️🙁🙁☹️🙁🙁🙁😭 🎙ኡስታዝ አቡ አብደል'ሐይ ዩሱፍ 💡ኡስታዝ አቡ ነሚር ሙኽታር 🎙ወንድም አቡ ዑበይዳ ሙሀመድ 💡ወንድም አቡ ጁወሪያ ነስረዲን 🎙ወንድም አቡ ያሲር ሙሀመድ 💡ወንድም አቡ ማሒር አብደረህማን 🔈ፕሮግራም መሪ 🙁☹️😭🙁😭🙁☹️🙁 🎙️ወንድም አቡ ዩስራ አብደሏህ 🎙️ወንድም አቡ ሀፍሷ አብደሏህ 📅 ቀን፦ ሀሙስ ምሽት ⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ 👥እርሶም ለዚህ ልዩ ፕሮግራም ተጋብዘዋል! በሰዓቱ ይጠብቁን! ቀጥታ ስርጭት አድራሻ፦ 🔵https://t.me/Abu_Amar_Mohammed

ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች በሙሉ፤ ጥብቅ ማሳሰቢያ‼ ============================== (አካውንታችሁ ሀክ ተደርጎ አጸያፊ ነገሮች ከመላካቸው በፊት አሁኑኑ አንብቡት) || ✍️ ሰሞኑን የብዙ ወንድምና እህቶች የቴሌግራም አካውንት እየተጠለፈ (Hack እየተደረገ) በተለያዩ ግሩፖች፣ ቻናሎች እና በውስጥ መስመር Inbox ላይ አጸያፊ እና ሐራም የሆኑ ሊንኮች በስማቸው እየተላኩ ነው። ይህ ድርጊት የሰዎችን ክብር ከማጉደፍም ባለፈ፣ ወዳጅ ዘመድን ለማያስፈልግ ፈተና እና ለሐራም እይታ እያጋለጠ ይገኛል። ☑ ይህ ሁሉ ችግር ከየት መጣ⁉️ ዋናው የችግሩ ምንጭ ብዙዎቻችን ኦፊሴላዊውን የቴሌግራም መተግበሪያ ትተን ሌሎች ቴሌግራም መሰል የዘ ሦስተኛ ወገን (Unofficial) አፖችን መጠቀም መጀመራችን ነው። እነዚህ አፖች (ለምሳሌ፦ Nicegram, Mobogram, Vidogram, Plus, Huligram, Telega ወዘተ) የእናንተን የግል መረጃ አሳልፈው ለሌቦች የሚሰጡ አደገኛ መተግበሪያዎች ናቸው። ▫️ ቴሌግራም ኩባንያም ይህን በመረዳት እነዚህን አፖች በሚጠቀሙ ሰዎች ፕሮፋይል ላይ "Warning Label" (የማስጠንቀቂያ ምልክት) ማሳየት ጀምሯል። እርምጃ ካልወሰዳችሁ አካውንታችሁ በዘላቂነት ሊዘጋ ይችላል! እነዚህን አፖች መጠቀም ምን አደጋ አለው? ➡️ የመረጃ ስርቆት፦ የግል ሚስጥራችሁ፣ ፎቶዎቻችሁ እና መልዕክቶቻችሁ በሌሎች እጅ ይወድቃሉ። ➡️ አካውንት መነጠቅ፦ የይለፍ ቃል (OTP Code) በመስረቅ አካውንታችሁን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረው፣ በናንተ ስም ወንጀልና ማጭበርበር ይሰራሉ። ➡️ ያለፍቃድ ግሩፕ መግባት፦ ሳታውቁት የተለያዩ የክሪፕቶ፣ የፕሮፖጋንዳ እና የብልግና ግሩፖች ውስጥ ያስገቧችኋል። ⬅️ መፍትሄው ምንድን ነው? አሁኑኑ ማድረግ ያለባችሁ 3 ወሳኝ እርምጃዎች፦ 1️⃣ ትክክለኛውን ቴሌግራም ብቻ ተጠቀሙ: አሁኑኑ ስልካችሁ ላይ ያሉትን ኦፊሴላዊ ያልሆኑ አፖች (Nicegram, Mobogram...) አጥፉና (Uninstall አድርጉና)፣ ትክክለኛውን በሰማያዊ ምልክት የሚታወቀውን "Telegram" ከፕሌይስቶር ወይም ከአፕስቶር ላይ ብቻ አውርዳችሁ ተጠቀሙ። 2️⃣ አሁኑኑ ሌቦችን ከአካውንታችሁ አስወጡ (Terminate Sessions) አካውንታችሁ ሀክ መደረጉን ለማወቅ እና ለማስወጣት ይህንን ተከተሉ፦ ወደ ቴሌግራም Settings ግቡ። Devices (ወይም Privacy and Security ገብታችሁ Active Sessions) የሚለውን ተጫኑ። እዛ ላይ ከእናንተ ስልክ ውጪ የገቡ ሌሎች መሳሪያዎች (ኮምፒዩተርም ሆነ ሌላ ስልክ) ካያችሁ ወዲያውኑ "Terminate All Other Sessions" የሚለውን ቀይ ጽሑፍ ተጭናችሁ ሁሉንም አስወጡ! 3️⃣ Two-Step Verification አብሩ: አካውንታችሁን ማንም ሰው እንዳይገባበት በፓስዎርድ ቆልፉት። (Settings > Privacy and Security > Two-Step Verification ገብታችሁ ፓስዎርድ አስገቡ)። ▫️ ያላወቀው እንዲያውቅ፣ የተዘናጋውም እንዲነቃ ይህንን ወሳኝ መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ Share በማድረግ ከስርቆት እና ከሐራም ድርጊቶች እንታደጋቸው! || t.me/MuradTadesse

ኹጥባ ለአኸይራ መዘጋጀት https://t.me/SadatKemalAbuMeryem