ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Открыть в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
912
Подписчики
-224 часа
-127 дней
+5130 дней
Архив постов
🌿 የነብዩሏህ ዩሱፍን ባህሪ የተሸከመ ወጣት 🌿 ሑሰይን ቢን ዐብዱረህማን እንዲህ ይላል፦ ከመዲና ሰዎች መካከል አንድ ወጣት ነበር። ከዑመር ቢን አል-ኸጣብ رضي الله عنه ጋር ሁሉንም ሶላቶች በጀመዓ ይሰግድ ነበር። ዑመርም በጀመዓ ካልታየ ይፈልገውና ሁኔታውን ይጠይቅ ነበር። ይህ ወጣት በአንዲት የመዲና ሴት ዘንድ የፍቅር ፍላጎት ተፈጠረባት። ለአንዲት የምታውቃት ሴትም ጉዳዩን ነገረቻት። እሷም፦ “እኔ እንዴት ወደ ቤቴ እንደምታስገባው እረዳሻለሁ” አለቻት።ከዚያም ወጣቱ በሚያልፍበት መንገድ ተቀመጠችና፦ “እኔ እድሜዬ የገፋ ሴት ነኝ፤ አንዲት በግ አለችኝ፣ እኔ ግን ማለብ አልችልም። እባክህ ወደ ቤቴ ገብተህ ታልብልኝ?” አለችው። ወጣቱም በመልካም ልብ ገባ። ነገር ግን ቤት ውስጥ ሲገባ ምንም በግ አላገኘም። ሴቲቱም፦“እዚህ ተቀመጥ፤ ልጠራት ሄጄ እመጣለሁ” አለችው። ከዚያም የታሰበውን አደረገች። ወጣቱን ለማሳሳት ሞከረች። ወጣቱ ግን ወዲያውኑ ወደ ቤቱ ውስጥ ያለ የሶላት ቦታ ሄዶ ተቀመጠ። እሷም ወደ እርሷ እንዲቀርብ ጠየቀችው። እሱ ግን፦ “አንቺ ሴት ሆይ! አላህን ፍሪ!” አላት። እሷ ግን አልተመለሰችም። ወጣቱ እምቢ ሲላት ጩኸት አሰማች። ሰዎችም መጡ። እሷ ግን እውነቱን ከመናገር ይልቅ ወጣቱን በመክሰስ፦ “ይህ ሰው ወደ እኔ መጥቶ ነበር!” አለች።ሰዎቹም ወጣቱን ያዙት፣ ደበደቡትና አሰሩት። ♦️ በማግስቱ ጠዋት ዑመር رضي الله عنه ሶላት ከጨረሱ በኋላ ይህ ወጣት ታስሮ ወደ እርሳቸው ቀረበ። ዑመርም ሲያዩት ወደ አላህ ዱዓ አደረጉና፦ «اللَّهُمَّ لَا تُخَلِّفْ ظَنِّي فِيهِ» “አላህ ሆይ! በእሱ ላይ ያለኝን መልካም ግምት አታሳስተኝ!” አሉ። ከዚያም ምን እንደተፈጠረ ጠየቁ። ሰዎቹም የተከሰተውን በራሳቸው መንገድ ነገሯቸው። ዑመር رضي الله عنه ግን ወጣቱን በመመልከት፦ “እውነቱን ንገረኝ” አሉት። ወጣቱም የተፈጠረውን ሁሉ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው በእውነት ነገራቸው። ዑመርም፦ “ያቺን አሮጊት ታውቃታለህ?” አሉት። “አዎን፣ እንደገና ባያት አውቃታለሁ” አለ። ዑመር رضي الله عنه የሴቲቱን ጎረቤቶችና አሮጊቶች አስጠሩ። እያንዳንዳቸው እያለፉ ሳለ፣ ያቺ ሴት በመጣች ጊዜ ወጣቱ፦ “እሷ ናት፣ የአማኞች መሪ ሆይ!” አለ። ዑመር رضي الله عنهም ወደ እሷ ተመልሰው፦ “እውነቱን ንገሪኝ!” አሏት። በመጨረሻም ሴቲቱ የወጣቱን ንግግር ሁሉ አረጋገጠች። ያን ጊዜ ዑመር رضي الله عنه እንዲህ አሉ፦ 🌿 «الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي جَعَلَ فِينَا شَبِيهَ يُوسُفَ عَلَيْهِ السَّلَامُ» “አላህ ምስጋና ይገባው! በመካከላችን ከዩሱፍ አለይሂሰላም ጋር የሚመሳሰል ሰው ያደረገልን አላህ ምስጋና ይገባው!” 🌿 ትልቁ ትምህርት የዚህ ታሪክ ውበት በመጨረሻው ቃል ብቻ አይደለም። ትልቁ ትምህርት በሰው ማያውቀው ቦታ አላህን መፍራት ነው። ማንም ሰው አያይህም ብለህ አታስብ፤ አላህ ያያል። ማንም አይደርስብህም ብለህ አትደፍር፤ አላህ ያውቃል። የሰው ምስክር ባይኖርም፣ የአላህ እውቀት አለ። ይህ ወጣት በምስጢር የቀረበለትን የኃጢአት እድል ትቶ የአላህን ፍርሃት መረጠ። በመጨረሻም አላህ እውነቱን አገለጠ፣ ክብሩንም ጠበቀለት። ዛሬም እውነተኛ ጽድቅ ይህ ነው፤ ሰዎች ሲያዩህ ብቻ ጥሩ መሆን ሳይሆን፣ ሰዎች በማያዩበት ጊዜም አላህን መፍራት። 📚 روضة المحبين — ኢብኑል ቀይም، ገጽ 459። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asself

📚ወደ ውስጥ ዘልቀው በሚገቡ ንግግሮች የተሞላ ለበርካታ ነገሮች ብርታት የሚሆኑ እና የሚያነቁ ምክሮችን ያዘለ አጠር ያለ ከልብ የሆነ ወደልብ ዘልቆ የሚገባ የትልቅ ሰው ምክር………        ክፍል 3⃣ 📝የኪታቡ ስም :— "ለፍተቱ-ል ከቢድ                             ኢላ ነሲሀቲል ወለድ" ✍ፀሀፊ:—ኢብኑ-ል ጀውዚይ رحمه الله      ለልጃቸው የመከሩት ምክር 🔊 አቅራቢ:- ወንድም ጀላሉ ሁሰይን ▪️ትምህርቱ የተሰጠው:—ለመርከዝ ኢብኑ      ዐባስ 2018 ተመራቂ ተማሪዎች https://t.me/bin_Husseynfurii

🎗ተቀርቶ የተጠናቀቀ ተከታታይ የኢንተቢህ አንተ ሙራቀብ ደርስ🎗 የኪታቡ Pdf ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1963 ክፍል 1 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1982 ክፍል 2 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/2014 ክፍል 3 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/2042 ክፍል 4 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/2078 ክፍል 5 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/2114 ክፍል 6⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/2173 ክፍል 7 ⤵️ የመጨረሻው https://t.me/Sle_qelbachn1/2174

ሁሉም ነገር ወደ ገንዘብ ተቀይሯል አንዳንድ የመስጂድ ወጣቶችን በትዳር ዙሪያ እንቅጩን ልንገራችሁ ፤ እንኳን ደሀ ሆናችሁ ደሃ ከመሰላችኋቸው ማንም ልጁን አይሰጣችሁም ፤ስለዚህ ፆም ተለማመዱ፤ የአሁን ሰው ስለ ትዳር መስጂድ ላይ ደእዋ ቢያደርግ እንዳታምኑ፤ሁሉም የራሱን እያበሰለ ነው፤አደራ አደራ  ደሃ ከሆናችሁ አትጠይቁ፤ከጠየቃችሁም ከናንተ በጣም የባሰች ደሃ ጠይቁ ፤ አሏህ ያዘነለት ጋር ካልሆነ ባሁኑ ወቅት ሁሉም ነገር ሽፋን ነው። ይህን የምንልህ ብዙ አይተን ነው፤የልጆቿን አባት አቦ ፍችውና ስራ ስሪ ብሎ የሚመክር ወላጅ እየበዛ ነው፤የገንዘብ ጉዳይ ብዙዎች ጋር ለድርድር አይቀርብም ፤ ሸርሁ ብዙ ነው ፤በአጭሩ ድሃ ከሆንክ ቀልብህን ሰብረው እንዳያስቀምጡህ አጠገባቸው አትድረስ።

አይገርማችሁም? ዛሬ የሱና ከዋክብት እያልን የምንጠራቸው ሊቃውንት፣ ትላንትና በኑሮ ፈተና ውስጥ ያለፉ ጀግኖች ናቸው። ​ሸይኽ ሙቅቢል አልዋድዒይ ረሂመሁላህ ለዒልም ፍለጋ በተሰደዱበት ዘመን፣ ረዳት በማጣታቸው ኑሮን በዘበኝነት ሲገፉት የኖሩ ናቸው። በተመሳሳይ ሁኔታ ተማሪያቸው ሸይኽ ሙሐመድ አል-ኢማምም በወጣትነታቸው በየመን ገበያ ሸክም በመሸከም (ወዛደር በመሆን) ይተዳደሩ ነበር። ​ሸይኽ ባሙሳ ስለ እርሳቸው ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦ ሙሐመድ አል-ኢማም በየመን ሸክም አውራጅ (ወዛደር) ነበር፤ ሆኖም በዒልም ላይ ባሳየው የላቀ ትጋትና ጥረት፣ ከሸክም አውራጁ ሙሐመድ (ሙሐመድ አል-ሐማል) ወደ ኢማሙ ሙሐመድ (ሙሐመድ አል-ኢማም) ተሸጋገረ። ​ይህንን የሕይወት ለውጥም በዐረብኛ እንዲህ ይገልጹታል፦ 'وأصبح من محمد الحمال إلى محمد الإمام' (ከሸክም አውራጁ ሙሐመድ ወደ ኢማሙ ሙሐመድ ተሸጋገረ።) ወዳጄ ሆይ! ማንነትህ የሚለካው በኪስህ ባለው ገንዘብ ወይም በምትሰራው ስራ አይደለም፤ ይልቁንም በችግር ማጥ ውስጥ ሆነህ ለዲንህ በምትከፍለው መስዋዕትነት ነው። እነዚህ ሊቃውንት፣ ትላንት ሸክም የተሸከመ ትከሻ ዛሬ የዒልም ሸክም መሸከም እንደሚችል የሚያሳይ ሕያው ምስክር ናቸው። ስለዚህ ተስፋ አትቁረጥ፤ ተማር!። = የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/Abulabas1444 t.me/Abulabas1444.

የዚህ ዓለም ትልቅ እድልና ጸጋ… አንድ ወንድ ታዛዥነቷና ፍቅሯ በፍርሃት ሳይሆን ከልቧ የሚመነጭላትን ሚስት ማግኘቱ ነው። 🤍 ​ለእሱ ርህሩህና ደግ የሆነች፣ በጥሩ እንክብካቤዋና እሱን በማክበሯ ምክ
የዚህ ዓለም ትልቅ እድልና ጸጋ… አንድ ወንድ ታዛዥነቷና ፍቅሯ በፍርሃት ሳይሆን ከልቧ የሚመነጭላትን ሚስት ማግኘቱ ነው። 🤍 ​ለእሱ ርህሩህና ደግ የሆነች፣ በጥሩ እንክብካቤዋና እሱን በማክበሯ ምክንያት «ግዴታዬ ምንድን ነው?» ብሎ ከመጨነቅ ይልቅ… እሷን ከማፍቀሩና ካለውለታነቷ የተነሳ ከ መብቷ በላይ ሊሰጣት የሚያልም። ​በወንዶች የበላይነት ተዋጊዎች (Masculinists) እና በሴቶች መብት ተከራካሪዎች (Feminists) መካከል በሚደረገው ጭቅጭቅና ጦርነት ውስጥ መግባት የማያስፈልገው ባል… ምክንያቱም እሱ ክብሩንና መብቱን ለማስከበር አይታገልም፤ እሷ ራሷ አክብራው መብቱን አሟልታ ከላዩም ትጨምርለታለች። ​የሴትነትንና የትዳር አጋርነትን ትክክለኛ ትርጉም የተረዳች ሚስት… ሴትነት ማለት እልህ፣ አመጽ ወይም ደግሞ መጽደቅ እንዳልሆነ፣ ድምፅን ከፍ ማድረግና ግትርነት ደግሞ የጥንካሬ ምልክት እንዳልሆኑ የተረዳች። ​እውነተኛ ሴት ባሏን ለማስደሰትና ለመንከባከብ ድካም አይሰማትም… የዓይኗ እይታና ፈገግታዋ ብቻ በቂ ነው፤ እሱም በግዴታ ሳይሆን በፍቅርና በደግነቷ በመማረክ ይረዳታል፣ ያደምጣታልም። 🤍 ​አላህ ለ እያንዳንዱ ወንድ ልጅ ደግና ርህሩህ፣ አላህን የምትፈራ መልካም ሚስት ይለግሰው። https://t.me/Mf11q https://t.me/Mf11q

فليست هذه الدنيا بشيء ... تسوئك حقبة وتسر وقتا وغايتها إذا فكرت فيها ... كفيئك أو كحلمك إذ حلمتا سجنت بها وأنت لها محب... فكي
فليست هذه الدنيا بشيء ... تسوئك حقبة وتسر وقتا وغايتها إذا فكرت فيها ... كفيئك أو كحلمك إذ حلمتا سجنت بها وأنت لها محب... فكيف تحب ما فيه سجنتا ምንም አየደለችም የዱንያዋ ህይወት ዘመን አስደስታህ ታዝናለህ ሌላ ወቅት ድካዋ'ኮ የሧ ስታስተነትናት ወይ እንዳንተ  ጥላ ወይ እንደ ህልምህ ናት ታሥረሃል በውስጧ የሷ ወዳጅ ሆነህ የታሰርክበትን እንዴት ትወዳለህ?! ከታኢየቱል ኢልቢሪ የተወሰደ ግርድፍ ትርጉም ሙሐመድሲራጅ

✅አንዳንዴ… 👌ይቅርታ የምታደርግላቸው ግን ደግሞ ስብራቱን የማትረሳላቸው ሰዎች አሉ። እነሱን ማየት የሚፈጥርብህ መጥፎ ስሜት ስላለ ይቅር ብያችኋላሁ ባይሆን ግን እንዳላያችሁ እሻለሁ የምትላቸውም አሉ። https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1

📮የሰለፎችን መዝሀብ ካላወቅክ አንተ ሰለፍያ አይደለህም ስም ብቻ አይደለም በሰለፎች መዝሀብ ላይ መሆን ከፈለክ መዝሀባቸውን ተማር ⁉️ ✅👉አልሸይኽ ሳልህ አልፈውዛን ❬ሀፊዘሁላህ❭ እንዲህ ይላሉ قال تعالى:- السابقون الأولون من المهاجرين والأنصار والذين اتبعوهم بإحسان ✅አላህ ሱበሀነሁ ወተአላ እንዲህ ይላል ⭕️👉የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች የሆኑት ሙሀጅሮች እና አንሷሮቹ እንዲሁም እነሱን በመልካሙ የተከተሉት በማለት ነው ያወደሳቸው🍀 💢👉በመልካሙ ሲባል በጥሩ በጥራት የተከተሏቸው ለማለት ነው ስለዚህ ሰለፍያ መሆን እኔ ሰለፍያ ነኝ እኔ በሰለፎች መዝሀብ ላይ ነኝ በማለት በንግግር ብቻ አይደለም‼️ 👉❌በስም ብቻ ሰለፍያ አይሆንም እንዴት መዝሀባቸውን ሳታቅ ሳትማር እኔ ሰለፍያ ትላለህ 👉❌አንዳድ ሰዎች የሰለፍያ መዝሀብ ምንድነው ብለህ ብትጠይቀው ወላሂ አላቅም ነገር ግን እኔ ሰለፍያ ነኝ ይልሀል እንዲህ ከሆነ አንተ ሰለፍያ አይደለህም እንለዋለን⁉️ 💢👉የሰለፎችን መዝሀብ አታውቅም እና ሰለፍያ አይደለህም እንዴት ነው መዝሀባቸውን የማታውቅ ሁነህ ከሰለፎች ጋር እንደሆንክ የምትቆጥረው 👉✅እነዚያ በመልካሙ የተከተሏቸው ነውኮ ያለው አላህ ሱበሀነሁ ወተአላ ስለዚህ በሰለፎች መዝሀብ ላይ መሆን ከፈለክ የሰለፎችን መዝሀብ ተማር አንብብ እወቅ እነሱ በሄዱበት ሂድ መዝሀባቸውን አጥብቀህ ያዝ⁉️ እና አሁን ምን ማድረግ አለብኝ ካላችሁ ኑኑኑ ተማሩ
📚የሚቀራውስ ኪታብ ካላችሁ
ሚን ወሷያ ሰለፊ ሊሸባብ የሸይኽ ዐብዱረዛቅ አል በድር
⏰ደርሱ የሚሰጥበት ሰአት ከምሽቱ
3:30 ይጠብቁን ኑ ተማሩ ወጣቶች ሁሉ አይለፋችሁ ኑ ከሁሉም በፊት ጎበስ ብላችሁ ተማሩ ኑ ሰለፍያን ኑ ተማሩ በየት ልከታታል ካላችሁ https://t.me/YekelelaWetatoce_gemah

የሰላም ዋጋ ~ የመንና ኦማን ጎረቤት ሀገራት ናቸው። ብዙ የሚያመሳስሏቸው የጋራ ነገሮች አሏቸው። ሁለቱም በዓረብ ባህረ ገብ ምድር ላይ ይገኛሉ። ሁለቱም ዐረቦች ናቸው። ሁለቱም ሙስሊሞች ናቸው። ሁለቱም ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ አላቸው። ሁለቱም ጥሩ የሚባል የተፈጥሮ የማዕድን ሃብት አላቸው። ሁለቱም ደረቃማ የአየር ንብረት ያደላባቸዋል። ሁለቱም ስትራቴጂክ አቀማመጥ አላቸው። ሁለቱም ረጅም የባህር ዳርቻ አላቸው። ሁለቱም የዓረብ ባህርን ይጋራሉ። በተጨማሪም ኦማን በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ፣ የመን በቀይ ባህር እና ባበል መንደብ ላይ ወሳኝ አቀማመጥ አላቸው። የመን ከኦማን የተሻለና የበለጠ የአየር ንብረት፣ የእርሻ መሬት፣ የቆዳ ስፋት፣ የአሳ ሃብት፣ አምራች የሰው ኃይል፣ አመታዊ የዝናብ መጠን፣ ከፍተኛ የብዝሀ ህይወት ስብጥር አላት። በሌሎች ነጥቦች ላይ ተመሳሰለው በነዚህ ነገሮች የመን ከኦማን ከበለጠች በአጠቃላይ ኢኮኖሚ በልጣ መገኘት ነበረባት። እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም። የመን ሰላም እና እድገት የራቃት፣ ኢኮኖሚዋ የደቀቀ፣ ለዘመናት ጦርነት የተፈራረቀባት ሃገር በመሆኗ የተፈጥሮ ሃብቷን በቅጡ መጠቀም አልቻለችም። መሰረተ ልማት የላትም። የኤሌክትሪክ፣ ውሃ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች፣ ኤርፖርቶች፣ ወደቦች፣ መንገዶች የደከሙ ናቸው። የጤናና የትምህርት ስርአቷ የወደቀ ነው። የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ በጣም ዝቅተኛ ነው። ህዝቧ በከፍተኛ ሁኔታ በጫት ሱስ የተለከፈ ነው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ። ኦማን ደግሞ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነባት በመሆኗ የተፈጥሮ ሃብቷን በመጠቀም በከፍተኛ ሁኔታ እያደገች ያለች ሃገር ነች። ከፍ ያለ የኢኮኖሚ እድገት፣ ያደገ መሰረተ ልማት፣ ጥሩ ደረጃ ላይ ያለ የጤናና የትምህርት ስርአት፣ የሀገሪቱን እድገት በከፍተኛ ሁኔታ እያቀላጠፈ ያለ የነዳጅና የተፈጥሮ ሃብት፣ ጥሩ የመብራት፣ የውሃ፣ የቴሌኮሙኒኬሽን አቅርቦት አላት። ወደቦቿ፣ ኤርፖርቶቿ፣ መንገዶቿ፣ የከተማ ልማቷ ከየመን ጋር የሚቀራረቡ አይደሉም። የመን ከአካባቢው የዓረብ ሃገራት ብቸኛዋ ድሃ ሀገር ናት። የተፈጥሮ ሀብት ሳያንሳት ሃገሪቱ በእድገት የዓለም ጭራ ስትሆን ህዝቦቿም በአስከፊ ድህነት ውስጥ ይማቅቃሉ። በብዙ ነገር እርዳታ ላይ ጥገኛ ናቸው። የሁለቱ ሃገራት የኢኮኖሚ እድገት በጣም የተራራቀ ነው። በ 2025 የኦማን GDP 109.6 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ሲሆን የየመን GDP ደግሞ 21.6 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ነው። የሚነፃፀሩ አይደሉም።  ዛሬ አንድ የኦማን ሪያል በ 2.6 የአሜሪካን ዶላር ይመነዘራል። አንድ የየመን ሪያል ደግሞ በ0.0042 የአሜሪካን ዶላር ይመነዘራል። ገልብጠን ብናየው አንድ የአሜሪካን ዶላር በ 38 የኦማን ሳንቲም የሚመነዘር ሲሆን በ236.65 የየመን ሪያል ይመነዘራል። ለምን በዚህ መጠን ተራራቁ? ምክንያቱ ወዲህ ነው። ኦማን ረጅም ዘመን ያስቆጠረ የተረጋጋ መንግስታዊ ስርአት አላት። ማዕከላዊ መንግስቷ ውጥረትና ክፍፍል የለበትም፣ አንድ ነው። የመን በተቃራኒው ለብዙ አመታት ሰላም የራቃት፣ በቀውስ የምትታመስ ሃገር ናት። ሰሜንና ደቡብ ከተዋሀዱ ገና 36 ዓመታቸው ነው። ከዚያም በኋላ በተደጋጋሚ የእርስ በርስ ጦርነት ተመታለች። የዓረቡን ዓለም ተከታታይ አብዮት ተከትሎ ዐሊ ዐብደላህ ሳላሕ ከተወገደ ወዲህ ችግሩ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኗል። ማእከላዊ መንግስቷ በከፍተኛ ደረጃ ተዳክሟል። ከሰሜን ሰዓዳ ግዛት የተነሳው በኢራን የሚደገፈው የሑሢ ቡድን ስፋቱ ቀለል ቢልም ዋና ከተማዋን ሶን0ን ጨምሮ የሀገሪቱ ከ70% በላይ ህዝብ የሚኖርበትን ግዛት በቁጥጥሩ አድርጓል። የቀደመው የሰሜን ደቡብ ክፍፍል አገርሽቷል። አቅሙ ደካማ ቢሆንም አልቃዒዳም በህቡእ ይሹለከለካል። ሀገሪቱ ዛሬ ላለችበት ክፍፍልና ውጥንቅጥ ከኦቶማን ቱርክ እና ከብሪታኒያ ቀኝ ግዛት የተወረሱ ችግሮች ቢኖሩም ከነፃነት በኋላ ስራቸውን ባለመስራታቸው ይሄው ዛሬ ላሉበት አስከፊ ደረጃ ደርሰዋል። ማሳረጊያ፦ የሰላም እጦት አገርን ይገ 'ድላል። ህዝብ ተረጋግቶ አገሩን ማሳደግ አይችልም። መሰረተ ልማቶችን ያሳጣል። ወጣቱን ተስፋውን ይነጥቃል። ጦርነት አምራች ሃይልን ያሳጣል። ይሄ ነው ተብሎ የማይገለፅ ማህበራዊ ምስቅልቅል ያስከትላል። ከአጎራባች ህዝቦች ጋር ደም በማቃባት ተንቀሳቅሶ የመስራት እድልን ይጎዳል። ለአንድ ህዝብ ለሰላምና መረጋጋት አጥብቀው የሚተጉ መሪዎችን ማግኘት እጅግ ትልቅ እድል ነው። በአንፃሩ የአንድ ህዝብ መሪዎች ጦረኛ መሆን የህዝቡን ስነ ልቦና በመበከል ወጣቱ በብዛት ጦርነትን እንዲያቀነቅን በማድረግ፣ ግጭትን በማብዛት ህዝቡ እንደ ደማ፣ እንዳለቀሰ፣ በመከራ እንደማቀቀ እንዲኖር ያደርገዋል። ከየመንና ኦማን ንፅፅር ባልተናነሰ የሀገራችን ተጨባጭ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

🌹🌹🌹የዝውውር ማስታወቂያ🌹🌹🌹                 ቀን: 14/01/2019 ዓ.ል السلام عليكم ورحمة الله وبركاته. 💐💐💐ለወሎ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ክፍል በመምረጥ ላይ ላላችሁ ተማሪዎች  በሙሉ :- 💐💐💐💐 በወሎ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ትምህርታችሁን ጨርሳችሁ ከተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ቀጥታ ወደ ዐረብኛ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል ለመዘዋወር ፍላጎቱ ያላችሁ ተማሪዎች  ወደ ዐረብኛ ትምህርት ክፍል መዘዋወር ስለተፈቀደ ከተፈጥሮ ሳይንስ/natural science/ ወደ ዐረብኛ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ት/ክፍል በአካል በመምጣት የጽሑፍ ማመልከቻ  በማስገባት ወደ ዐረብኛ ት/ክፍል  መዛወር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ 🌹ማሳሰቢያ ፡- 1/ ከተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ ትምህርት ክፍል ከመረጣችሁ በኋላ ዝውውር መጠየቅ አይቻልም። ለበለጠ መረጃ ፡0910228789

ያ ሁሉ ወጣት እንደ ቅጠል ረግፎ፣ ካለፈው ከደረሰው እንደ መማር ዛሬም ጠበንጃ መወልወል አሳዛኝ ነገር ነው። ክፉ ልክፍት! ደም የማይጠግብ አእምሮ!! የወጣቶች በአጭር መቀጨት፣ የእናቶች በሀዘን መሰ
ያ ሁሉ ወጣት እንደ ቅጠል ረግፎ፣ ካለፈው ከደረሰው እንደ መማር ዛሬም ጠበንጃ መወልወል አሳዛኝ ነገር ነው። ክፉ ልክፍት! ደም የማይጠግብ አእምሮ!! የወጣቶች በአጭር መቀጨት፣ የእናቶች በሀዘን መሰበር፣ የአዛውንቶች ያለ ጧሪ ቀባሪ መቅረት፣ የሃገር መቆርቆዝ የማያስደነግጠው ልብ ከጠላት በላይ ጨካኝ ነው። ሰው ሌሎች ላይ ከደረሰው፣ ከጎረቤቱ ይማራል። እሱ ቢቀር እንዴት በራስ ላይ ከደረሰው መማር ያቅታል?! ለማንኛውም ወጣት ሆይ! ለራስህ እወቅበት። በስምህ የሚምለው ሁሉ ተቆርቁሮልህ እንዳይመስልህ። ጀግና ጀግና የሚልህ ጀግና ስለሆንክ አይደለም። እየሸነገለህ ነው። ራሱንም ቤተሰቡንም ከእሳቱ አርቆ ነው አንተን የሚማግደው። ካንተ ሞት በኋላ ልጅህን፣ እናትህን ዞሮ አያይም። ግፋ ቢል ነገ ካንተ ሞት በኋላ የሰማእታት ሀውልት ብሎ የድንጋይ ክምር ቢያቆምልህ ነው። ይሄ ላንተም ለቤተሰብህም የሚጠቅመው ነገር የለም። ህዝብ ማደንዘዣ፣ ሌላ እልቂት ማቀጣጠያ እንጂ የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም። ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

Repost from ፈዋኢድ
العلاقة بين المعنى اللغوي والاصطلاحي: ⭐ اللغوي أوسع من الاصطلاحي، وهو الغالب: كالربا. ⭐ اللغوي يساوي الاصطلاحي: كالذهب. ⭐ الاصطلاحي أوسع من اللغوي: كالسهو؛ فالسهو في اللغة: النسيان، وفي باب سجود السهو: مطلق الخلل الواقع في الصلاة.

የኢትዮጵያ ታሪክ ከጥንት ጀምሮ የጦርነት ታሪክ ነው። ዘፈኑም፣ ቀረርቶውም፣ ተረትና ምሳሌውም እንዳለ ከመG ደል ጋር በተያያዙ መልእክቶች የታጨቀ ነው። ህዝቡም ሰርቶ ከመለወጥ፣ ኑሮን ከማሸነፍ በላይ ጦረኝነትን እና ገዳ ^ ይነትን እንደ ጀግንነት የሚቆጥር ነው። አባትሽ አይገ^ ድል ወንድምሽ አይገ^ ድል አርሶ ያብላሽ እንጂ ሆድሽ እንዳይጎድል። አገራቸው ወዲያ ዳርቻ ቀበሌ ተበድሮ ገ^ ዳይ ጥይት እንደ ጥሬ ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንዳባቱ፣ ስጡት አመልማሎ ይፍተል እንደናቱ በሀገራችን ከህግና ስርዓት፣ ከመልካም መኗኗር በላይ ጉልበተኝነት ነው የሚያስከብረው። ጉልበተኛ ወገን የሌለው ሰው አንገቱን ደፍቶ ነው የሚኖረው። ሁሉም ለጦርኝነቱ ምክንያት ቢደረድርም እውነታው ግን የህዝቡ ባህልና ስሪት ከጦረኝነት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው። ይሄ በአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች ያለ የነበረ ያልተቀየረ እውነታ ነው። ከየትኛው ጉዳይ በላይ በጦርነት ላይ ይረባረባል። ከየትኛውም ጉዳይ በላይ የጦርነት ዜና ይመስጠዋል፣ ያነፈንፋል። በርግጥ ጦረኝነት የዓለም ታሪክ ነው። ግን ዛሬ ላይ ሃገራት የህዝባቸውን አመለካከት እየቀየሩ ውስጣዊ ሰላም በማስፈን ተረጋግተው እየኖሩ ነው። እኛ ግን እዚያው ነን። የጦርነት አዙሪት ውስጥ ስንማቅቅ እንኖራለን። አንዱ መዓት ጠባሳ ጥሎ ሲያልፍ ደግሞ ሌላው ይጀምራል። አሳማሚ እውነት። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

በትግራይ፣ በአፋር፣ በአማራና በሌሎችም አካባቢዎች የምትኖሩ እህትና ወንድሞቻችን፤ አላህ ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቆ በመልካም ጥበቃው ስር ያውላችሁ።

📖📖📖 የቁርዐን ጉዞህን አታቋርጥ! 📍ቁርዐንን መሐፈዝ ጀምራችሁ በመካከል ያቋረጣችሁ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ አደራችሁን! የጀመራችሁትን የአላህን ቃል አትተዉ! አዎን፣ ሕይወት ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። 📍 የሚያደክሙን ሁኔታዎች፣ የሚያስቆሙን ችግሮች፣ የሚያዘናጉን ነገሮች ሊያጋጥሙን ይችላሉ። ከቁርዐን ልንርቅ፣ ልንደክም፣ እንኳን ልንቆም እንችላለን። ግን ለዘላለም አንቁም! 🌿 ትናንት ብትቆሙ፣ ዛሬ ተመለሱ። 🌿 ትናንት ብትደክሙ፣ ዛሬ እንደገና ጀምሩ። 🌿 ትናንት ብትረሱ፣ ዛሬ እንደገና አስታውሱ። 🌿 ብዙ ጊዜ ቢያልፍም፣ የተዘጋውን ሙስሐፍ እንደገና ክፈቱ። 📍የቀራችሁ ብዙ ከሆነ አትፍሩ። አንድ ገጽ በአንድ ገጽ፣ አንድ አንቀጽ በአንድ አንቀጽ፣ አንድ እርምጃ በአንድ እርምጃ ቀጥሉ። ትልቁን ርቀት ስለማትችሉ አትቁሙ፤ የምትችሉትን ትንሽ እርምጃ ዛሬ ውሰዱ። 📍ወንድሜ፣ እህቴ… የትናንት ድካምህ የዛሬ ተስፋህን እንዳይገድልብህ። ያለፈውን ተወው፤ ወደ ቁርዐን ተመለስ። 📖 ሙስሐፍህን ክፈት። ከቆምክበት ቦታ ጀምር። የረሳኸውን እንደገና ድገም። በትንሹም ቢሆን ቀጥል። አንድ ቀን ወደ ኋላ ተመልሰህ ስታይ፣ ዛሬ የወሰድከው ትንሽ እርምጃ ትልቅ ጉዞ እንደነበር ትገነዘባለህ። 🌹 አትተዉ… ተመለሱ! አትቁሙ… ቀጥሉ! ተስፋ አትቁረጡ… አላህን ተስፋ አድርጉ! 🤲 አላህ የቁርዐንን ፍቅር በልባችን ያስርጽ፣ ለመማርና ለመሐፈዝ ያበረታን፣ የተቋረጠውን ጉዞ እንድንቀጥል ያግዘን፣ ቁርዐንንም የሕይወታችን ጓደኛ እና የልባችን ብርሃን ያድርግልን። አሚን። 🤲 ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

ኢማሙ አህመድን መሆን ባትችል አቡሀይሰምን ሁን!!! አብዱላህ የኢማሙ አህመድ ልጅ እንድህ ይላል: አባቴን ሁል ጊዜ ""ጌታየ ሆይ አቡ ሀይሰምን ማረው እዘንለት" ሲል እሰማዋለሁ፣አቡሀይሰም ማነው ስል ጠየኩት ኢማሙ አህመድ: አንድ ፊቱን ያላየሁት የገጠር ሰው ነው አለ ከግርፋቴ በፊት በነበረችው ሌሊት ጨለማ እስር ቤት አረጉኝ፣ በጨለማው አንድ ሰው ነካ አረገኝና አንተ ኢማሙ አህመድ ነህ?አለኝ አወ አልኩ ታውቀኛለህ? አለኝ አላውቅህም አልኩት አቡ ሀይሰም እባላለሁ ሌባ ጠጪ ሽፍታ ነኝ በንጉሱ መዝገብ ላይ የሰፈረ በተለያየ ጊዜ አስራ ስምንት ሺህ ግርፋት ተገርፌያለሁ ያን በሸይጣን መንገድ ላይ ሁኘካ ችየዋለሁ አንተ በአላህ መንገድ ላይ ነው ታገስ ያ አህመድ አለኝ!!!!! ከዚያም ታስሬ ግርፋቱ ሲጀምር እያንዳንዱ አለንጋ ጀርባየ ላይ ሲያርፍ የአቡ ሀይሰምን ንግግር አስታውስና ለራሴ አህመድ ሆይ በአላህ መንገድ ላይ ነህ ፅና እላለሁ።!!!! መናቂቡ ኢማሙ አህመድ ገፅ 450_451 https://t.me/rebizidniielma