ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
Открыть в Telegram
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
320
Подписчики
+124 часа
-47 дней
+5530 дней
Архив постов
ሀዳድዮች ሆይ! ለተምዮች ሆይ! ወደ ትክክለኛው መንገድ(መንሐጀ ሰለፍ) መመለሻችሁ አልደረሰም ወይ?! የእውነት አላህን #የምትፈሩ ከሆናችሁ ለምን የተለያየንባቸውን *ነጥቦች እናንተም እኛም ለምናምንባቸው ዑለማዎች አናቀርባቸውም?!?
ሀዳድዮች፦ እንደው ለመሆኑ የጀምዕያ፣የመስዓለቱ ዑዝር ቢልጀህል ጉዳይ #ኢጅቲሀድ አይገባበትም ስትሉ የአላህን ፊት ፈልጋችሁ ነው ወይስ ምንድን ነው?
ለተምዮችስ <<የጀርህ ወተዕድል>> ጉዳይ ኢጅቲሐድ አይገባበትም ብላችሁ ስትሞግቱ የእውነት የአላህን ፊት ፈልጋችሁ ነው? በጀርህ ወተዕድል ጉዳይ ለውይይት ቀረባችሁ። ከዚያም በጉዳዩ ላይ ተስማማችሁ። ከዚያ በኋላ ምን አግኝቷችሁ ከአቋማችሁ አፈገፈጋችሁ? ጉዳዩ ማለትም የጀርህ ወተዕድል መስዓላህ ኢጅቲሐድ እንደሚገባበት ጠፍቷችሁ አይመስለንም።ጉዳዩ ካፈርኩ አይመልሰኝ ነው።
አላህ ሁላችንንም በትክክለኛው መንገድ ላይ እንዳፀናን እንለምነዋለን።
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444
Repost from Abu Hayder Aliy
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ዛሬ ጁሙዓ ነዉ የጁሙዓ ሱናዎች
➖➖➖➖➖➖➖
↩️💎 سنن يوم الجمعة🌿🌿🌿
➊ 💎الغسل
➋💎 الطيب
➌ 💎السواك
➍💎 لبس الجميل
➎💎 قراءة سورة الكهف
➏💎 التبكير لصلاة الجمعة
➐💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
➊ 🌺መታጠብ
➋ 🌺ሽቶ መቀባት
➌🌺 ሲዋክ መጠቀም
➍ 🌺ጥሩ ልብስ መልበስ
➎ 🌺ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን
➏ 🌺ለጁመዓ ሶላት መጣድ
➐ 🌺በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿〰
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ
🌺በሰለዋት በዚክር ያውለን ያረብ
ﷺ 🌹 .................🌹
ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ🌹🔹🔹🌹
ﷺ ﷺ ﷺ 🌹🔹🔹🌹
በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ !!
https://t.me/abu_haider_aliye
https://t.me/abu_haider_aliye
Repost from የዐረበኛ ቋንቋ ትምህርቶች
الصَّحَابَةُ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ
(ሶሐቦች - አሏህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና)
هُمْ أَعْلَمُ النَّاسِ بِدِينِ اللَّهِ
وَهُمْ أَحْرَصُ الْخَلْقِ عَلَى الْخَيْرِ
وَأَشَدُّ النَّاسِ حُبًّا لِلنَّبِيِّ ﷺ
وَأَكْثَرُهُمْ تَمَسُّكًا بِسُنَّةِ النَّبِيِّ ﷺ
👉 وَمَعَ ذَلِكَ لَمْ يَحْتَفِلُوا بِالْمَوْلِدِ النَّبَوِيِّ
لَوْ كَانَ خَيْرًا لَسَبَقُونَا إِلَيْهِ
እነርሱ ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ ስለ አሏህ ሃይማኖት አዋቂዎች ናቸው፤
እነርሱ ከፍጥረታት ሁሉ ይበልጥ ለመልካም ነገር እጅግ በጣም የሚጓጉ ናቸው፤
እነርሱ ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ ነቢዩን ﷺ እጅግ በጣም የሚወዱ ናቸው፤
እነርሱ ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የነቢዩን ﷺ ሱና አጥብቀው የሚይዙ ናቸው።
👉 ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ ግን የነቢዩን መውሊድ አላከበሩም!
«መልካም ነገር ቢሆን ኖሮ ቀድመውን ባደረጉት ነበር።»
«إِذَنْ، لَنْ أَحْتَفِلَ بِالْمَوْلِدِ»
==>"ስለዚህ መውሊድ አላክብርምምምምምም"
نسأل الله أن يثبتنا على السنّة، وأن يجعلنا من المتبعين الحقيقيين للنبي ﷺ.
" اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ "
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
በ-ኢሞም (IMO) መጥተናል!
● ዓላማችን በወጣቱ ቋንቋ ስለ ወጣቱ እያወራን ቀልባችንን በጋራ ማስተካከል ነው።
አድሱን የ ኢሞ ገፃችንን ፎሎው በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! 👇❝ስለ ቀልባችን❞
https://s.channelcom.tech/vvBknq?from=TG
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሰው መሳይ በሸንጎ
~
ከውጭ ትጥቅ አሳማሪ ብንሆንም፣ ውስጣችን ክፋት፣ ቅናት፣ ምቀኝነት ያረገዘ ከሆነ ራሳችንን እየሸወድን ነው። ለአላህ እንደሆነ የሚሰወረው ነገር የለም። የውስጣችንም እንደ ውጫችን ግልፅ ነው። ለሰዎች ጥሩ መስሎ ለመታየት ከመልፋት ይልቅ የእውነት ጥሩ ሆኖ መገኘት ነው ትርጉም ያለው። መቼስ መሆንና መምሰል የተለያዩ ነገሮች እንደሆኑ ግልፅ ነው።
ከሰው ፊት ጤነኛ፣ ኸይረኛ፣ አላህን ፈሪ የምንመስል ከሰው እይታ ገለል ስንል ሰቅጣጭ ወንጀሎችን የምናጨማልቅ ብዙ ሰዎች አለን። አውዛዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "በአደባባይ የአላህ ወሊይ፣ በድብቅ ግን ጠላቱ አትሁን።" [አዝ-ዙህድ፣ ኢማም አሕመድ]
በዚህ ዘመን እንደ ልብ ትኩረት ያጣ ነገር የለም። ለውጫዊ ገፅታችን የምንጨነቀውን ሩብ ታክል እንኳ ለልባችን እያሰብን አይደለም። ልብ ካልተገራ እና አላህን ከመፍራት ከተራቆተ ደግሞ ሌላው ሰውነት ቀፎ ነው፣ ቢከፍቱት ተልባ! ብዙዎቻችን ሰው ሰው እንሸታለን እንጂ ሰውነት አጥተናል። እንደ ሰው እንተውናለን እንጂ ባህሪያችን ከአው^ሬ የከፋ ሆኗል። በልብስና በምላስ የተሸፈነው አው^ሬነታችን በተለያዩ ክስተቶች ጥፍሩን ቀስሮ፣ ጥርሱን አግጥጦ ሲወጣ እየታየ ነው። ሁላችንም ሰባኪ ሆነናል። በምናውቃት መስራት ላይ ግን የለንም። እንዲሁ ወሬ ብቻ! ኢላ መታ?!
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 03/2015)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማለዳ መልእክት (47)
~
ልጅ ትልቅ ሃብት ነው። እንዲያውም ከልጅ በላይ ሀብት የለም። ህንፃ ቢደረደር፣ ሃብት ቢትረፈረፍ ያለ ልጅ ጣእም የለውም። የልጅን ኒዕማ የሚያቃልለው ወይ ህይወት ያለ ልጅ ምን ያክል ባዶ እንደሆነች የሚረዳበት የእድሜ ክልል ላይ ያልደረሰ ነው። ወይ ደግሞ አእምሮው በሌሎች መጥፎ አስተሳሰብ የተበከለ አካል ነው። እንጂ በተትረፈረፈ ሃብት ውስጥ ብትሆን እንኳ ያለ ልጅ ህይወት ጣእም አልባ ናት። የአላህ ነብይ ዘከሪያ የነበራቸውን ስሜት እና የሰጣቸውን ፈረጃ አላህ እንዲህ ሲል ይገልፀዋል:-
{ وَزَكَرِیَّاۤ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥ رَبِّ لَا تَذَرۡنِی فَرۡدࣰا وَأَنتَ خَیۡرُ ٱلۡوَ ٰرِثِینَ (89)
"ዘከሪያንም፡ 'ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፡፡ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ' ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡''
فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ وَوَهَبۡنَا لَهُۥ یَحۡیَىٰ وَأَصۡلَحۡنَا لَهُۥ زَوۡجَهُۥۤۚ إِنَّهُمۡ كَانُوا۟ یُسَـٰرِعُونَ فِی ٱلۡخَیۡرَ ٰتِ وَیَدۡعُونَنَا رَغَبࣰا وَرَهَبࣰاۖ وَكَانُوا۟ لَنَا خَـٰشِعِینَ (90) }
"ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ የሕያንም ሰጠነው፡፡ ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት፡፡ እነርሱ በበጎ ሥራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ሆነው የሚለምኑንም ነበሩ፡፡ ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ፡፡" [አልአንቢያእ፡ 89-90]
በርግጥ ትልቁ ነገር እንዲሁ ልጅ መኖሩ ብቻ አይደለም፣ አስተዳደጉ ሲያምር ነው ልጅ የዓይን ማረፊያ፣ የዱንያ ምርኩዝ፣ የኣኺራ ስንቅ የሚሆነው። ስለዚህ ልጆቻችን ከየትኛውም ሃብት በላይ ናቸውና አጥብቀን እንድከምላቸው።
ውለዱ፣ ክበዱ። አስተዳደጋቸው ላይ ትኩረት ስጡ። የሌላችሁ አላህ ልጅ ይስጣችሁ። ያልተሰካላችሁ አላህ ስብራታችሁን ጠግኖ በኣኺራ ይካሳችሁ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 05/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from N/a
⭕️ይህ መልዕክት ለሱና ቻናል ባለቤቶች ⭕️
➲ ቻናላችሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ የሚያስችል ዌቭ በአዲስ መልክ ጀምረናል
🛑በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ 📥
➦ ከ #300 በላይ ተከታዮች
ከ #500 እና #1000 በላይ ተከታዮች
ላላቸው
⚡️ የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ
👉 @Quran_mylife1
Repost from ስለ ቀልባችን
📢 አስደሳች ዜና ለጠቅላላው የሙስሊም ማህበረሰብ!
ኢኽላስ የቁርኣን እና የተርቢያ ማዕከል የ10 ወር የቆይታ ጊዜ ያለው የበጋ ልዩ ኮርስ ማዘጋጀቱን በታላቅ ደስታ ይገልፃል!
💡 የፕሮግራሙ ልዩነት፦
በዚህ 10 ወር ውስጥ ማንኛውም የእውቀት ፈላጊ ጧሊበል ዒልም ሊቀራቸው የሚገቡ መሠረታዊ የሸሪዐ የትምህርት ፈኖችን በጥልቀት የሚያስጨብጥ እና ጠንካራ መሠረት የሚጥል ልዩ የእውቀት ማዕድ ተዘጋጅቶልዎታል!
ልጆቻችሁን እና እራሳችሁን በቁርኣን፣ በስነ-ምግባር እና በእስልምና እውቀቶች ለማነፅ እና ለማበልፀግ የቀረበ ወርቃማ አጋጣሚ!
የትምህርቱ
በወንድም አብዱረዛቅ አል-ባጂ አስተምህሮ የሚሰጥ ይሆናል።
📚 የሚቀሩት ፈኖች
● ዓቂዳህ
● ፊቅህ አሻፊኢይ
● ኡሱሉል ፊቅህ
● ቀዋዒዱል ፊቅሂ
● አዳብ እና ሱሉክ
📖 በተጨማሪ፦ በቆይታው ውስጥ የተለያዩ ጠቃሚ የሸሪዐ መትኖች ይተሐፈዛሉ እያንዳንዱ ቂርዐት እራሱን የቻለ ፈተና ይኖረዋል።
⚠️ ማሳሰቢያ፦ ለፕሮግራሙ የተቀመጠው የቦታ መጠን የተገደበ በመሆኑ ቦታ ሳይሞላቦት ፈጥነው በመመዝገብ ቦታዎን ያስይዙ!
📍 አድራሻ
አድራሻ፦ ቦሌ ሚካኤል — ከእግረኛ ድልድዩ ወደ ውስጥ 50 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥሮች፦
📞 0911119260
📞 0919829850
Repost from درر العلامة المحدث-ربيع بن هادي المدخلي
المجموع الواضح في رد منهج وأصول فالحتأليف فضيلة الشيخ العلامة ربيع بن هادي عمير المدخلي-حفظه الله- https://t.me/DrRabeeM/4268 الدال على الخير كفاعله
ልቤ ሆይ ተመከር! ነገ ነገ ብለን፣ ስንቱን አቅደናል፤ ለጠፊዋ አለም፣ ስንቱን አስበናል። ሞቱን ዘንግተነው፣ በፍፁም ረስተነው፤ ልባችን ሸፍቷል፣ አላህ ይመልሰው። ልቤ ሆይ!! ተመከር ይቅርብህ መዋለል፤ በጠፊዋ አለም፣ ዘወትር መታለል። ልቤ ሆይ!! ተመከር ተው ግን ይቆጭሀል፤ አስተውል፣አሰተንትን ነገ ይፀፅትሀል። ዛሬም እድል አለህ፣ ልቤ ልብ ይኑርህ። አደራ አደራ ይህንን ነው ምልህ!! t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from 🛍 𝑹𝑬𝑾𝑫𝑨 𝑪𝑶𝑳𝑳𝑬𝑪𝑻𝑰𝑶𝑵🇦🇪🇪🇹🛍
እኛ ሠለፍዮች ነን አልሀምዱሊላህ
ማንም ሙብተዲዕ ቢለን አንሆንም
ማንም ካፊር ቢለን አንሆንም በስራችን ቢሆን እንጅ
ሸርር አድርጓትማ
ወደቻናሉ ለመቀላቀል
https://t.me/Ahlul_hadis_wel_asser
https://t.me/Ahlul_hadis_wel_asser
❌አሉ አትበል እወቅ ምክንያቱም ባንተ ላይ ማወቁ ግደታነዉና⁉️
✅ የተከበርከው ወንድሜ ሆይ የገደል ማሚቶ አትሁን።
🌿 የገደል ማሚቶ የራስህን ድምፅ ነው የሚያስተጋባው።
👉 አንተም የሸሪዓ ዕውቀት ካልተማርክ የሌሎችን ድምፅ ነው የምታስተጋባው።
- ኤከሌ ሙብተዲዕ ነው ሲሉህ አንተም ተከትለህ ሙብተዲዕ ነው ትላለህ።
- ኤከሌ ካፊር ነው ሲሉህ አንተም ተከትለህ ካፊር ነው ትላለህ።
✅ በል አኺ እንደውም ሶላት በቀን አምስት ጊዜ እንሰግዳለን።
አስኪ ለአይምሮህን ይሄን ጥያቄ ጠይቀው።
1⃣ የሶላት ሸርጥ ባጎድል በምድነው የምጠግነው?
2⃣ የሶላቴን ሩክን(መሰረት) ባጎድል በምድነው የምጠግነው?
3⃣ ዋጅቡን ባጎድል በምድነው የምጠግነው? ብለህ ጠይቀው።
👉 መልሱን ከመለስክ ጎበዝ ነህ እየተማርክ ነው ማለት ነው። ካልመለስክ ግን ከባድ የጥያቄ ምልክት ውስጥ ነህ ምክንያቱም የዲንህ መሰረት የሆነው ስለ ሶላትህን አታውቅም።
✅ በ24 በሰዓት አምስት ጊዜ የምንሰግደው ሶላት አፈፃፀሙ ካላወቅን ሌሎች የእስልምና መሰረቶችን በተመለከተ የበለጠ አጅሀል ነን። ስለዚህ ወንድሜ ሁለት ነገር አስወግደህ እውቀትህን ተማር፦
1⃣ ኩራት፦ ኩራት እውቀት ከመፈለግ ያግዳል።
2⃣ የተወቀሰ ሀያ፦ የተወቀሰ ሀያ እውቀትን ከመፈለግ ያግደሃል። ሰዎች ለመጠየቅ ታፍራለህ። አሏህን አናፍረውም ሰው ግን እናፍራን።
✅ ብርቅዬ ሴት ሰሐባዎች ስለጀናባ አስተጣጠብ፣ስለሐይድ ስለመንይ ሌሎችም ሴት ሰሐቦች ከነብዩﷺ አንሰተው ወደኛ አስተላልፈዋል። ዲናቸው የሚያበላሽባቸው ነገር ለማወቅ ሳያፍሩ ሳይሸማቀቁ ይጠይቁ ነበር።
🚫 እኛ ግን አናውቅም ለመጠየቅ እናፍራለን።
✅ አብዘኛው ሰው ባቅሙ ልክ ይሸጣል ይገዛል። ግን ስለግብይት ምንም የምናውቀው ነገር የለም።
✅ ወንድሞቼ እንማር ዲናችን በእውቀት የተመሰረተ ነው እኛ ግን ከእውቀት ነፃ ነን።
🚫 ደግሞ እውቀት መፈለግ ለተወሰኑ ሰዎች እናደርገዋለን።ልክ አይደለንም እውቀት መፈለግ በሁሉም ሰው ላይ ግዴታ ነው።
عن أنس بن مالك قال : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم :
" طلب العلم فريضة على كل مسلم "
የሸሪዓ እውቀት መፈለግ በሁሉም ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የሰዎች ህይወት እና ንብረት በሌላው ላይ ሐራም ነው!
~
ከአቡ በክረህ (አላህ ይውደድላቸው) ተይዞ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" إِنَّ دِمَاءَكُمْ وَأَمْوَالَكُمْ وَأَعْرَاضَكُمْ بَيْنَكُمْ حَرَامٌ كَحُرْمَةِ يَوْمِكُمْ هَذَا، فِي شَهْرِكُمْ هَذَا، فِي بَلَدِكُمْ هَذَا "
“ደማችሁ (ሕይወታችሁ)፣ ንብረታችሁ እና ክብራችሁ በእናንተ ላይ እርም (የተከለከለ) ነው፤ ልክ በዚህ ወራችሁ እና በዚህ አገራችሁ ውስጥ ይሄ ቀናችሁ እንዳለው ክብር።”
[ቡኻሪይ (39) ከዘገቡት ሐዲሥ የተወሰደ ነው። ሙስሊምም (2816) ዘግበውታል።]
* ቡኻሪይ (7078) ውስጥ በሚገኝ ሌላ ዘገባ ደግሞ እንዲህ የሚል አለ፦
" وَأَبْشَارَكُمْ، عَلَيْكُمْ حَرَامٌ كَحُرْمَةِ يَوْمِكُمْ هَذَا "
“አካሎቻችሁም እንዲሁ እንደዚህ ቀናችሁ ክብር የተከበሩ ናቸው።”
* በተጨማሪም ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" لَا تَرْجِعُوا بَعْدِي كُفَّارًا، يَضْرِبُ بَعْضُكُمْ رِقَابَ بَعْضٍ "
“ከኔ በኋላ ከፊላችሁ የከፊሉ አንገት የሚሰይፍ ከሃዲዎች ሆናችሁ አትመለሱ።” [ቡኻሪይ (67 እና 7078] እና ሙስሊም (1679) ዘግበውታል።]
የቃላት መፍቻ፦
=
1. “ይሄ ቀናችሁ” የተባለው ዙልሒጃ አስር ሲሆን የዒደል አድሓ የመጀመሪያው ቀን ነው።
2. “በዚህ ወራችሁ” የተባለው የተከበረው የዙልሒጃ ወር ነው።
3. “በዚህ ሃገራችሁ” የተባለው የተከበረው የአላህ ቤት፣ የተከበረችዋ መካ ለማለት ነው።
ከሐዲሡ የሚወሰዱ ትምህርቶች፦
=
1. የሙስሊሞች ደም ፈፅሞ ሊደፈር የማይገባው እርም እንዲሁም በጣም የተከበረ እንደሆነ፣
2. የሰዎችን ንብረትና ክብር መዳፈር ክልክል እንደሆነ እና
3. የሙስሊም ደሙ፣ ንብረቱ እና ክብሩ ከተከበረው ሃገር፣ ከተከበረው ወር እና ከተከበረው ቀን ክብር በላይ እንደሆነ እንወስዳለን።
ዐብዱላህ ብኑ ዐምር ብኒል ዓስ (አላህ ይውደድላቸው) ባስተላለፉት ሐዲሥ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ لَقَتْلُ مُؤْمِنٍ أَعْظَمُ عِنْدَ اللهِ مِنْ زَوَالِ الدُّنْيَا "
“ነፍሴ በእጁ በሆነችው (ጌታዬ) እምላለሁ! አንድን አማኝ መግደል አላህ ዘንድ ከድፍን ዓለም መጥፋት የከፋ ነው።” [ነሳኢይ (3986) ዘግበውታል።]
* ሙስሊም ያልሆኑ አካላትም እንዲሁ ሊበደሉ አይገባም። ይህንን የሚመለከት ማስረጃ ሌላ ጊዜ አቀርባለሁ፣ ኢንሻአላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ወዳጄ_ሆይ!
👉 ሰው ሁሉ ምንም ያህል #ቢክደው የውስጥ ሕመም አለው።እያንዳንዱ ልብ ምንም ያህል #ቢደብቀው የውስጥ ስብራት አለው። ገጽታዎች አያታሉህ። ነገሮች እንደሚመስሉት አይደሉም። በረጋ መንፈሱ የምትቀናበት ያ ሰው፣ በልቡ ውስጥ አላህ እንጂ ማንም የማያውቀው እሳት #እየነደደ ሊሆን ይችላል። ጭስ አለመውጣቱ ሰውየው እየነደደ አይደለም ማለት አይደለም።
ወንጀለኛው በወንጀሉ ሰላም የለውም። አላህን የሚፈራውም ያንን ጽናቱን በቀላሉ አላገኘውም። እንዳያጣው ጥርሱን ነክሶ የያዘው አፍቃሪም ሰላም የለውም።በልቡ ውስጥ ያለውን ክፍተት ገና ያልሞላውም ሰላም የለውም።
እንደሚባለው"መጽሐፉን በሽፋኑ አትመዝነው!"
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
«የሀገራችን ኢኽዋኖች ተከታታይ ፅሁፍ»
√ #ክፍል 02
|• «የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን ምን አሉ?»
በክፍል አንድ ባሰማሁት የድምፅ ፋይል ሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን «"ኢኽዋን ከአህለሱና ውጭ ነው የሚለው" ትክክል አይደለም። ያው አህለሱና የሆኑት ሊቃውንቶች ከአህለሱና ውጭ እንዳልሆነ አረጋግጠውለታል።» ማለታቸው ይታወሳል። እናም ዛሬ በአላህ ፍቃድ የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን ምን እንዳሉ እንመልከታለን። ከዚያም ሸይኹ የተናገሩት እውነት ነው ወይስ በሱና ዑለማኦች ላይ፣ ወይ እየዋሹባቸው ወይ ያለ ዕውቀት አየመሰከሩባቸው የሚለውን እናረጋግጣለን።
√| ከዚህ በታች በአላህ ፍቃድና እገዛ ታላላቅ የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን የተናገሩትን ለማቅረብ እሞክራለሁ።
1. ታላቁ ኢማም የዘመናችን ሙሐዲሥ ሸይኽ አል-አልባኒ (ረሒመሁላሁ) እንዲህ ይላሉ፦
|√ «ليس صوابا أن يقال إن الإخوان المسلمين هم من أهل السُنة لأنهم يحاربون السُنة» (من شريط فتوى حول جماعة التبليغ والإخوان من تسجيلات منهاج السنة في الرياض)
√| «አልኢኽዋን አል-ሙስሊሙን ከአህሉስ-ሱና ወል-ጀማዓ ናቸው ብሎ መናገር ትክክል አይደለም፤ ምክንያቱም እነርሱ ሱናን ይዋጋሉና።»
• ይህንን ሊንክ በመጫን ንግግራቸውን ማድመጥ ይቻላል። 14 years ago የተለጠፈ https://youtu.be/d20Zb6JpAAA?si=KcLPeC_Zn2AQ-Sf0
√|| «لا يجوز أن نقول "الخلاف بيننا وبين الإخوان المسلمين فرعي والإخوان المسلمون من أهل السنة" لا!. هم يحاربون أهل السنة ويقولون دعوتكم الآن تفرق. نحن عاشرناهم في سوريا وهنا.» (من أشرطة سلسلة الهدى والنور، الشريط رقم 356.)
√|| «"በእኛና በኢኽዋን አልሙስሊሚን መካከል ያለው ልዩነት በፈርዕ (በቅርንጫፍ ጉዳዮች) ላይ ብቻ ነው፣ ኢኽዋን ሙስሊሚንም ከአህሉስ-ሱና ናቸው።" ብሎ መናገር አይፈቀድም። በጭራሽ! (እንዴውም) እነሱ አህለሰሱናን ይቃወማሉ፤ (እኛንም) "ጥሪያችሁ አሁን ሰዎችን ትከፋፍላለችሁ"ም እያሉ ነው። እኛ በሶሪያም እዚህም ከእነርሱ ጋር አብረን ኖረናል።»
• ይህንን ሊንክ በመጫን ንግግራቸውን ማድመጥ ይቻላል። 7 years ago የተለጠፈ
https://youtu.be/JDLVfowcQBk?si=-fxNGSlEv0IYvvu6
√ ማሳሰቢያ፦
እንደሚታወቀው ኢኽዋን መልከ ብዙና በሸይኹ የህይወት ዘመን የተስፋፋ አንጃ በመሆኑ ሸይኹል አልባኒ ከህይወታቸው መጀመሪያ እስከ ህይወታቸው ፍጻሜ በኢኽዋኖች ላይ ተመሳሳይና አንድ አቋም አልነበራቸውም። ከእርሳቸው የፈትዋ የድምፅ ቅጅዎች እንደምንረዳውና ታሪካቸውን በቅርበት የሚያቁት ዑለማኦች እንደገለፁት ሸይኹ በአንጃው ሦስት መርሐላዎች (ደረጃዎች) ነበራቸው።
1• በመጀመሪያ ደረጃ ሸይኽ አል-አልባኒ ለኢኽዋን አልሙስሊሚን መልካም ግምት ነበራቸው። ምክንያቱም እነዚህ ኢኽዋኖች ቁርአንና ሱናን መከተልን መፈክራቸው ያደርጉ ነበርና። በዚህም የተነሳ እነርሱን ከሱና ውስጥ እንዳሉ ይቆጥሯቸው ነበር። ነገር ግን የዛኔም ቢሆን ከሱና ባያስወጧቸውም ከእነርሱ ይመለከቱ የነበረውን የዓቂዳ ድክመትና ወደተውሒድ ከመጣራት በላይ ለፖለቲካ የሚሰጡትን ትኩረት ይተቹ ነበር።
2• በሁለተኛው ደረጃ ሸይኽ አል-አልባኒ የኢኽዋን መንጋ ፈር መልቀቅ ግልጽ ይሆንላቸው ጀመር። ከዚያም አንዱ ኢኸዋኒይ የሰለፊያን ደዕዋ መተቸት ሲጀምርና “ሰለፊዮች የሚጨነቁት በውጫዊ ጉዳዮች ብቻ ነው” ብሎ የፃፈው ሲደርሳቸው የሸይኹ ትችት የበለጠ ጠነከረ። እንዲህም አሉ፦
«ما أعتقد أن سلفيًا عقيدةً وسلوكًا بإمكانه أن يتبنى منهج الإخوان المسلمين وأمثالهم»
ትርጉሙም፦ “በዓቂዳውም ሆነ በአካሄዱ ሰለፊይ የሆነ ሰው የኢኽዋን ሙስሊሚንንና እንደነሱ ያሉትን መንገድ ሊይዝ ይችላል ብዬ አላምንም።”
እናም ሸይኹ የኢኽዋን መንገድ ሰዎች የተለያዩ ዓቂዳዎች ቢኖራቸውም ሁሉንም በአንድ የፖለቲካ ቡድን ውስጥ ለመሰብሰብና ለማደራጀት የሚሞክር መንገድ መሆኑ ግልጽ እየሆነላቸው መጣ። ሆኖም ግን ሸይኹ ኢኽዋንን ከሌሎች ቡድኖች ይልቅ ወደ ሐቅ የቀረቡ እንደሆኑ ይናገሩ ነበር፦
«الإخوان المسلمون هم أقرب الجماعات إلى الحق، لكنهم ليسوا على الحق.»
ትርጉሙም፦ “ኢኽዋን አልሙስሊሚን ከቡድኖች ሁሉ ወደ እውነት የቀረቡ ናቸው፤ ነገር ግን እነርሱ በእውነት ላይ አይደሉም።”
3• በመጨረሻው ደረጃ ሸይኽ አል-አልባኒ የኢኽዋን ሙስሊሚንን አቋም በግልጽ መቃወም ጀመሩ። እነርሱ ከሚያስተካክሉት ይልቅ የሚያበላሹት እንደሚበዛ እና ብዙ መሰረታዊ ስህተቶችን ሲመለከቱ እንዲህ ሲሉ የመጨረሻ አቋማቸውን አወጁ፦
«خلافنا مع الإخوان المسلمين خلافٌ في الأصول لا في الفروع فقط.»
“ከኢኽዋን አልሙስሊሚን ጋር ያለን ልዩነት በመሠረታዊ ጉዳዮች ነው፤ በቅርንጫፍ ጉዳዮች ብቻ አይደለም።”
እንዲሁም ከላይ እንዳሰፈርኩት፦
«ليس صوابًا أن يقال الإخوان المسلمون من أهل السنة، لأنهم يحاربون السنة.»
“ኢኽዋን አልሙስሊሚን ከአህሉስ-ሱና ናቸው ማለት ትክክል አይደለም፤ ምክንያቱም ሱናን ይዋጋሉና።” ሲሉ ኢኽዋን ከአህለሱና አመሆናቸውን አረጋግጠዋል።
እናም ሸይኹ መጀመሪያ ላይ እነርሱ ቁርአንና ሱናን እንከተላለን ብለው በሚያሳዩት መፈክር ላይ የተመሠረተ መልካም ግምት ነበራቸው። በኋላ ግን የቡድኑ እውነተኛ መንገድና ተግባራዊ ጥመታቸው ሲገለጥላቸው አቋማቸውን እንደቀየሩ ነው ታሪክ የሚነግረን።
ስለዚህ የዑለማዎችን ንግግር በታሪካዊና በጊዜያዊ አውዱ መሠረት መረዳት የፍትሕ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የዕውቀታዊ ታማኝነትም ጉዳይ ነው። አንድን የዓሊም ንግግር ከተናገረበት ደረጃና አውድ ነጥሎ ለሌላ ዓላማ መጠቀም ትክክል አይደለም።
በዚህ ረገድ ሸይኽ አሕመድ ሙሐመድ አስሷዲቁ አንነጃር በ blogpot ገፃቸው
«موقف الشيخ الألباني من جماعة الإخوان المسلمين»
በሚል ርዕስ የለጠፉትን ያንብቡ፦ http://abuasmaa12.blogspot.com/2025/10/blog-post_20.html
የሌሎች ዑለማኦችን ንግግር በቀጣይ ክፍል አቀርባለሁ ኢንሻአላህ።
√ #ክፍል 01
t.me/Abu_lmran_Alaseriy/3682
=
(አቡ ዒምራን፣ ነሃሴ 11/2018)
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from N/a
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው ብዙ
የሱና ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን
ያገኛል ።
ጥያቄ 1
💎ተዉሂድ በስንት ይከፈላል?
