ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

Открыть в Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
320
Подписчики
+124 часа
-47 дней
+5530 дней
Архив постов
✅እህህህህህ ሲደክምኮ ....‼️ 👉የኔ ጌታ እገዘኝ...⁉️ ------------------- ለበደሉህ ሁሉ ይቅር በል ለሚለው ለቃልህ ስገዛ፡ በተደጋጋሚ የሚፈታተነኝ ማጅራት መች በዛ፡ ህሌናችን ዛለ፤ ጂስማችን በለዘ የሚቀጠቀጠው፡ አንተ ታገሱ አልከን፤ ክፉ ተከታይን #ወደት እናምልጠው⁉️ እስኪ ይሁን ብለን ስንጓዝ ታግሰን፡ እንደ #ጂል ቆጥረውን አለፉብን ወሰን፡ መታገስ ሞኝነት ሆኖ ተቆጠረ፡ አወ አንተ እምታውቀው ብዙ ተፈጠረ!! ...አሁንም ልታገስ..!? በህይወት ጉዞ ላይ ባሰመርነው መንገድ፡ በተቻለን መጠን ስንወለጋገድ፡ በየመታጠፊያው መቱኝ ማጅራቴን፡ እኔም ታገስኳቸው እየሰጠሁ ፊቴን፡ ፈገግ የሚሉትን ጥርሶቼን እያዩ፡ ሞኝ ነው በማለት እየተወያዩ፡ ማን እንበል ይሉኛል ማንነቴን ያዩኝ፡ ወዳጆቼ ሁሉ አልቻሉም ሊለዩኝ...!! ...አሁንም ልታገስ...!? እውነት ነው አምናለሁ ጥሩ ነው መታገስ፡ ከፍታን ለማየት ፈጥኖ ለመገስገስ፡ ግን ደግሞ ያስንቃል ለተባይ ለፈንገስ፡ ትዕግስትን ከፍርሀት ለሚቆጥር ጀዝባ፡ የእዝነት ቤሳቢስቲ ለሌለው ገለባ፡ የክፋትን ሴራ ለሚፈፅም በገፍ፡ ጭንቅላቱን ይዞ ጥርሱን ነበር ማርገፍ፡ እንደዚህ እያለች ስትቀስተኝ ነፍሴ፡ ተው ታገስ ይለኛል ህሌና መንፈሴ፡ እንደመሸ ማወቅ ከንጋት ይበልጣል፡ መነሳት ስላለ ህልምህን አትጣል፡ ለሰው ክፉ አታስብ አሏህ ዘንድ ያስቀጣል፡ እያለ አዕምሮዬ ሰርክ ሲመጉተኝ፡ በጭንቀት ወጥሮ ይዞ ሲቀስተኝ፡ ምንም ነገር የትም መፈፀም አቃተኝ!! ሁሉን ላንተ ሰጠሁ አንተ ተመልከተኝ። እየሞከርኩኝ ነው ታግሸ ለማለፍ፡ እየሞከርኩ ነው ከዘላፊወች ጋር ላለመዘላለፍ፡ ሳይጥሉ ሳይወድቁ አልፎ ግብ ለመምታት፡ እየሞከርኩ ነው፤ ድክመቴን ለመቅረፍ ችግሬን ለመርታት፡ ካንተ እማፀናለሁ፤ የመቻልን ጥበብ የትዕግስትን ብርታት፡ እየሞከርኩ ነው፤ በቀልን ለመተው ፍቅርን ለመተካት፡ እየሞከርኩ ነው፤ መልካምን እያሰብኩ ህልሜን ለማሳካት፡ እየሞከርኩ ነው፤ ህይወትን ለመኖር እምነቴ እንዳዘዘኝ፡ ወንጀሌ ከብዶኛል፤ መሸከም አልቻልኩም የኔ ጌታ እገዘኝ..⁉️ «አምናለሁ አሏህ ክፉ አይሰራም» «ሁሉንም በስኬት አጠናቅቀዋለሁ ኢንሻ አሏህ» .....ኑረዲን አል-አረብ...✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►► 🌟 ቢሻራህ ኦንላይን የሴቶች መድረሳ በሴት ኡስታዛ 🌟 ያለ ምንም ፍርሀት እና ጭንቀት በጥሩ ተጅዊድ ቁርአንን መማር ለሚፈልጉ እህቶች በሙሉ ጥሩ እድል ተዘጋጅ
►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►► 🌟  ቢሻራህ ኦንላይን የሴቶች መድረሳ በሴት ኡስታዛ 🌟 ያለ ምንም ፍርሀት እና ጭንቀት በጥሩ  ተጅዊድ ቁርአንን መማር ለሚፈልጉ እህቶች በሙሉ ጥሩ እድል  ተዘጋጅቶሎታል  !! ● የምንሰጣቸው ትምህርቶች ፦ ➪ ቃኢዳ በተጅዊድ ➪ ቁርአን ነዘር ➪ ሂፍዝ ከሙራጀአ ጋር ➪ መሰረታዊ የዲን ትምህርቶች 📍ለሴቶች በሙሉ ምቾት፣ ነፃነትና ግላዊነት ያለው የትምህርት እድል !! ⏰ ሰአታችን ለእርስዎ ከሚመች  ፕሮግራም ጋር የሚጣጣም ! ⚠️ ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ ! ለመመዝገብ ፦🔻 @bisharat_al_quran  ያናግሩን ! «اقْرَؤُوا الْقُرْآنَ فَإِنَّهُ يَأْتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ شَفِيعًا لِأَصْحَابِهِ» “ቁርአንን አንብቡ፤ እርሱ በቂያማ እለት ለባለቤቶቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣል።”  (ሶሂህ ሙስሊም)

ፎቶሽን እንዳትልኪ! ~ ምንም ያህል ብታፈቅሪው፣ ምንም ያህል «እንደ ራሴ አምነዋለሁ» ብትይ እንኳ በሀራም ግንኙነት ውስጥ እያለሽ ፎቶሽን በፍጹም እንዳትልኪለት! ● አንደኛ፦ ያለ ኒካህ የሚደረግ ግ
ፎቶሽን እንዳትልኪ! ~ ምንም ያህል ብታፈቅሪው፣ ምንም ያህል «እንደ ራሴ አምነዋለሁ» ብትይ እንኳ በሀራም ግንኙነት ውስጥ እያለሽ ፎቶሽን በፍጹም እንዳትልኪለት! ● አንደኛ፦ ያለ ኒካህ የሚደረግ ግንኙነት ራሱ ሀራም ሆኖ ሳለ፣ ፎቶ በመላክ አውራሽን መግለጥ ድርብ ወንጀል ነው። ● ሁለተኛ፦ የሰው ልጅ ልብ ተለዋዋጭ ነው። ዛሬ ያመንሽው ሰው ነገ ሲቀያየር ነውርሽን በሚዲያ ላለማውጣቱና ህይወትሽን ላለማበላሸቱ ዋስትና የለሽም። ● ሦስተኛ፦ ነገ በአላህ ፈቃድ ሌላ ንጹህ ትዳር በምትመሰርቺበት ጊዜ፣ ያ ትናንት በስሜት የላክሽው ፎቶ የትዳርሽን ጣሪያ እንዳያፈርሰውና እንዳያዋርድሽ ተጠንቀቂ። የሚያፈቅርሽ ወንድ በአላህ መንገድ በኒካህ ወደ ቤትሽ ይመጣል እንጂ በስልክ ፎቶሽን እየለመነ ለፈተና አይዳርግሽም። የኔ እህት ዕንቁ ነሽ፤ ክብርሽን በአላህ ፍራቻ ጠብቂ!✅👈 ከነጭራሹም ወደትዳር በፍጥነት ለማይገባ ወንድ ገና አገባሻለሁ እያለ ለሚያታልል በጭራሽ ቤትሽን አትክፈች ትዳርኳን ከመጣልሽ ከሳምንት በላይ አታውሪው በሳምንት ውስጥ ማንነቱንና ድኑን አጥኚ ከሆነ ቶሎ ወደሀላል ካልተዋጠልሽ በብሎክ አሰናብች በስልክሽ ውስጥ block የሚል የተቀመጠው ለእንደዚህ አይነት ቀማኞች ማሰናበቻ ነው ቆራጥ ሁኚ ውዷ👑 https://t.me/qdemiy_letwuhide

• ራስህሽን ለሰዎች ማስረዳት ስታቆሚ የሚጠቅምሽን ነገር ብቻ ስታደርጊ ሕይወት በጣም ቀላል ትሆናለች። *የኔ ሴት በአላማሽ ላይ ብቻ ፅኒ🫶🌹💥

የአእምሮህ ሰላም ይቅደም አላስፈላጊውን ነገር እርሳው! እረፍትህን የሚነሱና ስሜትህን የሚረብሹ ገጠመኞችንም ሆነ የበደሉህን ሰዎች ለመርሳት ወይም እንዳልነበሩ አድርገህ አልፈህ ለመተው ጣር፤ መርሳት ትልቅ ፀጋ ነውና። ጤናህና የልብህ ሰላም ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚና ትልቅ ዋጋ ያላቸው ናቸው። አላህ  በቂህና ያጣኸውን ነገር እንደሚሰጥህ፣ እንደሚበቃህና በተሻለ ነገር እንደሚተካህ ሁልጊዜም በሙሉ እምነት ላይ ሁን። t.me/ibrahim_furii

«ታላላቅ ታቢዕዮች» ----------------- ❶♦️ሰዒድ ኢብኑ ሙሰዬብ ❷♦️ሐሰኑል በስሪ ❸♦️ዑወይስ አል-ቀረኒ ❹♦️ሙሀመድ ኢብኑ ሲሪን ❺♦️ዑመር ኢብኑ አብደል አዚዝ ⛔️ማስታወሻ‼️ ታቢዕይ
«ታላላቅ ታቢዕዮች» ----------------- ❶♦️ሰዒድ ኢብኑ ሙሰዬብ ❷♦️ሐሰኑል በስሪ ❸♦️ዑወይስ አል-ቀረኒ ❹♦️ሙሀመድ ኢብኑ ሲሪን ❺♦️ዑመር ኢብኑ አብደል አዚዝ ⛔️ማስታወሻ‼️ ታቢዕይ ማለት፦ «በነብዩ አምኖ ሶሀቦችን የተገናኘ ብሎም በእስልምና ላይ እንደፀና የሞተ ሲሆን....እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ደግሞ...እውቀትን ለቀጣዩ ትውልዳቸው ያሰራጩ ባለ ውለታዎች ናቸው። .....ኑር...✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

አስደሳች ዜና ለዕውቀት ፈላጊዎች በሙሉ ዳዕወቱል አንቢያ ኢሥላማዊ ድርጅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አዲስ አበባን ጨምሮ መድረሳዎችን እና የሂፍዝ ማዕከሎችን በመገንባት ለህዝበ ሙስሊሙ የሸሪዓህ እውቀቶችን በማስተማር፣ የሚድያና የጎዳና ዳዕዋ በማካሄድ፣ የሃይማኖት ንጽጽር ኮርሶች እና የተለያዩ ሳይንሳዊ ስልጠናዎችን በመስጠት ሙስሊሙን ማህበረሰብ በማገልገል ላይ ያለ ተቋም ነው። በቀጣይ በ2019 ዓ.ል አድማሱን በማስፋት በአዲስ አበባ ባዘጋጀው ምቹ ቦታ #ከክፍያ_ነጻ በሆነ መልኩ ለወንዶች በአዳሪነት ብቁ በሆኑና ልምድ ባላቸው መሻይኾች #በዲፕሎማ_መርኃ_ግብር በአቂዳ፣ በሐዲስ፣ በፊቅህ፣ በነሕው፣ በሶርፍ፣ በሃይማኖት ንጽጽር ትምህርት እና ሌሎችም የትምህርት ዘርፎችን በመቅረጽ በሁለት ዓመት የሚጠናቀቅ የዲፕሎማ መርኃ ግብር በማሰናዳት ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቆ ይገኛል። ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛዉም እውቀት ፈላጊ በተቀመጠው አድራሻ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ በመደወል መመዝገብ የምትችሉ መሆናችሁን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው !              የመመዝገቢያ መስፈርቶች ❶) ሙሉ 30 ጁዝ ቁርአን የሀፈዘና ሽሀዳ ማቅረብ የሚችል ➋) በአካባቢው ከሚታወቁ መሻይኾች መሰረታዊ ሙኽተስር /አጫጫር/ ኪታቦችን የቀራ ➌) እድሜው ከ 15 እስከ 20 የሆነ ➍) አረበኛ ቋንቋ መጻፍ፣ ማዳመጥና መናገር የሚችል ➎) መልካም ስነምግባር እንዳለው የሚያረጋግጥ፣ ከአካባቢው መሻይኾች ወይም ከኢስላማዊ ተቋም የድጋፍ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል    ➏) ከወላጅ ወይም ከአሳዳጊ ፍቃደኝነታቸዉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ➐) ከተላላፊ በሽታ ነጻ የሆነና ከሚታወቅ የህክምና ተቋም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል   ➑) የመዕሐዱን ህግና ደንብ የሚያከብር ➒) የመቅራት  አላማና ቁርጠኛነት ያለው ➓) ስምንተኛ ክፍል እና ከዛ በላይ ያጠናቀቀ       ማሳሰቢያ ❶) ከምዝገባ ቡሗላ አዲስ አበባ በሚገኘው በድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት ተቋሙ ያዘጋጀዉን የመግቢያ ፈተና በአካል መቶ መፈተን ግዴታ ነው ➋) ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ያለን ቦታ ዉስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ      ለበለጠ መረጃ    አድራሻ ሸገር ከተማ ፉሪ ክ/ከተማ ጃዕፈር ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ስ.ቁ 0921637766        0907416666 @DAIO_registration

እኛም እንድናለን እነሱም ይድናሉ! ~ እኛ አጅር አግኝተን እነሱ ወንጀል ከሚሰሩ እኛም ድነን እነሱም መዳነቸው ይሻላል!     ምርጥ ታሪክ ከሰለፎች፦ ታላቁ ሊቅ ኢብራሂም አን-ነኸዒ (ረሒመሁላህ) አንድ ዓይናቸው የማይሰራ ነበሩ ተማሪያቸው ሱለይማን ኢብኑ ሚህራን (አል-ዕመሽ) ደግሞ ዓይናቸው (ደካማ) ነበሩ። በዕለቱ ሁለቱ ሊቃውንት #በኩፋ ጎዳናዎች በኩል ወደ መስጊድ ሊሄዱ አብረው እየተጓዙ ነበር። በመንገድ ላይ እያሉም ኢማም አን-ነኸዒ ተማሪየቸውን እንዲህ አሏቸው፦ "ሱለይማን ሆይ! አንተ አንዱን መንገድ ይዘህ እኔ ሌላኛውን መንገድ ብይዝ ምን ይመስለሃል? ምክንያቱም አብረን ሆነን ስንሄድ የሰፈሩ ሞኞች (ሰዎች)፦ 'አንድ ዓይን ያለው ሰው ዕውር ሰው እየመራ ነው!' እያሉ እንዳያሾፉብን እፈራለሁ። በዚህም ምክንያት ሐሜት ውስጥ ወድቀው ኃጢአት ይሸከማሉና።" ሱለይማን እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦ "አይ አባ ዐምራን! እኛ (በትዕግስታችን) ምንዳ አግኝተን እነሱ ኃጢአት ቢሰሩ ምን ችግር አለው?" ኢብራሂም አን-ነኸዒም (ረሒመሁላህ) ልብ የሚያረካ ይህንን ታላቅ ወርቃማ መልስ ሰጡ፦ "ሱብሐናልላህ! ይልቅ እኛም (ከኃጢአት) እንድናለን እነሱም (ከኃጢአት) ይድናሉ እኛ አጅር አግኝተን እነሱ ወንጀል ከሚሰሩ እኛም ድነን እነሱም መዳነቸው ይሻላል !" 📚 [አል-ሙንተዘም ፊ አት-ታሪክ - 7/15] ሰለፎች እንዲህ ነበሩ እውቀት የማይቋረጥ ታሪክ መልካም ባህሪ ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም መኖር! የተወሰደ

የሱፊያ ጭፈራ በዑለማእ እይታ ~ 1. ኢማሙ ማሊክ፡- “እኛ ዘንድ ሱፊያ የሚባሉ ሰዎች አሉ። በብዛት ይበሉና ከዚያ ያንጎራጉራሉ። ከዚያም ተነስተው ይጨፍራሉ” ሲሏቸው * “ህፃናት ናቸው ወይ?” ብለው ጠየቁ። - “አይደሉም” አሏቸው። * “እብ ^ዶች ናቸው?” ሲሉ - “አይደሉም። ሸይኾች ናቸው” አሏቸው። * “እኔ ከኢስላም ሰዎች ይህን የሚሰራ አንድም አልሰማሁም” አሉ። [ተርቲቡል መዳሪክ፡ 2/53] 2. አቡል ወፋእ ኢብኑ ዐቂል፡- "በዜማና የመሳሪያ ድምፅ እየተከተለ የሚደንስና የሚጨፍር ባለ ፂም ማየት ምንኛ አስቀያሚ ነው? ባለ ሽበት ሲሆን ደግሞ የባሰ ነው! በተለይ ደግሞ በወጣቶችና በሴቶች ድምፅ ሲታጀብ። ከፊቱ ሞት፣ ጥያቄ፣ መቀስቀስና ሲራጥ ያለበት፣ ከዚያም ከሁለቱ አገሮች ወደ አንዱ የሚሆን ሰው እንደ እንስሳት ዝላይ ሊዘል፣ እንደ ሴቶች ማጨብጨብ ሊያጨበጭብ እንዴት ይዋጥለታል?" “ሱፊዮች ስራን ያበላሻሉ። የእምነት መሰረቶችን ያናጋሉ። ቦዘኔነትንና ዜማ ማዳመጥን ይወዳሉ።” [ተፍሲሩል ቁርጡቢይ፡ 10/263] 3. ኢብኑል ጀውዚይ፡- የሱፊያ ክፍሎችን ተግባር አንስተው ባወገዙበት እንዲህ ብለዋል:– “በየምግቡ ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ሲጠግቡ ጊዜ ይደንሳሉ፡፡ … ከመዐቶቻቸው ሁሉ የከፋው መዐት ግን ይህንን (ጭፈራ) መቃረቢያ (ዒባዳ) አድርገው መሞገታቸው ነው፡፡ ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው እንደሚከ -ፍ*ር በርግጥም የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጥሯል፡፡” [ሶይዱል ኻጢር፡ 168] 4. አል-ቁርጡቢይ፡- “ሱፊዮች የፈጠሩትን (ዜማ) በተመለከተ በክልክልነቱ ላይ ውዝግብ ከማይነሳበት ነገሮች ነው። ነገር ግን ብዙ በመልካም የሚታሰቡ ሰዎችን ስሜት አሸንፏቸዋል። ብዙዎቹ ላይ የእ-ብ-ዶችና የህፃናት ስራዎች እስከሚታዩባቸውና በተጠና መልኩ እስከሚደንሱ ደርሰዋል። ከዚያም ከፊል ሰዎች መቃረቢያና መልካም ስራ እስከማድረግ ደረሱ።…” [ተፍሲሩል ቁርጡቢ፡ 14/54] 5. አስ-ሲዩጢይ፡- "ከነዚህም (ከቢድዐዎች) ውስጥ የሆነው በመስጂድ ውስጥ የሚፈፀም ጭፈራ፣ ዘፈን፣ ድቤ መምታት፣ ማሲንቆና ሌሎችም የሙዚቃ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ ይህንን ከመስጂድ ውስጥ የፈፀመ ሊባረርና ሊደበደብ የሚገባው ጠ -ማ -ማ ሙብ -ተ-ዲዕ ነው፡፡ ምክንያቱም አላህ እንዲላ፞ቅ ያዘዘውን ነገር እያቃለለ ነውና፡፡ … (ከመስጂድ ውስጥ) የዘፈነ ወይም የጨፈረ ቅጣት የሚገባው የሆነ ጠሞ አጥ -ማሚ ሙብ -ተ-ዲዕ ነው፡፡” [ሐቂቀቱ ሱና፞ ወልቢድዐ፡ 191] በነገራችን ላይ ይሄ መስጂድ ውስጥ መጨፈር የመካ ሙሽሪkoች ተግባር ነው። አላህ እንዲህ ብሏል:- ‏﴿وما كان صلاتهم عند البيت إلا مكاء وتصدية فذوقوا العذاب بما كنتم تكفرون﴾ "በቤቱ ዘንድም (በካዕባ) ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም። ትክዱት በነበራችሁትም ነገር ቅጣትን ቅመሱ (ይባላሉ)።" [አንፋል፡ 35] = ( Ibnu Munewor ፣ ጥቅምት፡ 27/2012) https://t.me/IbnuMunewor

በደዕዋ እና ተድሪስ ላይ የተሰማራ ሰው አጥብቆ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ቢኖር የኢኽላስ ጉዳይ ነው። ይዩልኝ፣ ይስሙልኝ፣ ዝና ፍለጋ፣ እና መሰል ልክፍቶች ልፋትን ሁሉ በዜሮ የሚያባዙ መጥፎ በሽ
በደዕዋ እና ተድሪስ ላይ የተሰማራ ሰው አጥብቆ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ቢኖር የኢኽላስ ጉዳይ ነው። ይዩልኝ፣ ይስሙልኝ፣ ዝና ፍለጋ፣ እና መሰል ልክፍቶች ልፋትን ሁሉ በዜሮ የሚያባዙ መጥፎ በሽታዎች ናቸው። ከነዚህ በሽታዎች መራቅ በጣም ከባድ ነው። ቢሆንም የሐቅ ከለፉ አላህ የልፋትን አያሳጣም። ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም። ጥረታችን ግን ሰሞንኛ ሳይሆን በየጊዜው መታገል ይገባል። * የሪያእን አደጋ ማሰብ፣ * ስለ ኢኽላስ ደጋግሞ መማር፣ * የሰለፎችን ከኢኽላስ ጋር የተያያዙ አስደማሚ ታሪኮች ማየት፣ * በዚህ ጉዳይ ላይ ሌሎችን ማስተማር፣ እራሳችንን ለመለወጥ የሚያግዙ ወሳኝ ነጥቦች ናቸው። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

Repost from N/a
መዉሊድ ቢድአ ነው‼️

መልእክት~ በሀገራችን በሀበሻ ረቢኡል አወል /12/ ቀን የነብዩ መውሊድ እያሉ ቤተሰቦቻችን በየቦታው ወደ ሽርክያት መንደር እንደሚጓዙ የሚታወቅ የሆነ ነገር ነው። በተለይ ገጠር አከባቢ ያለው ማህበሠሳባችን፣እናቶቻችን፣አባቶቻችን፤ ወደተለያየ ከአላህ ውጭ ወደሚመለክበት ቦታ ይጓዛሉ። ለምሳሌ ያክል 👇👇👇👇 ❌ወደ ጀማንጉስ ❌ወደ ማይባር ❌ወደ አርባ ጫማ ❌ ወደ ገታ ❌ወደ አና ❌ወደ ዳና ❌ወደ አብሬት ❌ወደ ቃጥባሬ ❌ወደ አብሬት ❌ወደ ቦረና ጌታው ሸህየ ❌ወደ መጂት ❌ወደ ሰይድ መሳል ❌ወደ አማን አንብይ ❌ወደ ጫሌ ❌ወደ ኑር ሁሴን ስንቱ ተቆጥሮ ይዘለቃል ዛሬ ጀምረው ይጓዛሉ ❌ጫት ይያዛል ❌ ቡና ይያዛል ❌ስለትም በየ አይነቱ ይጎተታል ሙክት በግ ዶሮ ❌የመሳሰሉት ይጎርፋል ማህበረሰባችን አጋፋሪወች አሉ ሆን ተብሎ ኮሚቴ ተዋቅሮ ማህበረሰባችንን በእስቲጋሳ ፣በተበሩክ ስም ሽርክ ያሰሩታል ሶላትማ አይታወቅም❌ ኩፍር ብቻ ይታወጃል ፤አላህ የሚጠላቸው ስንት ስራ ይሰራል❌ ከአላህ ውጭ ይጠራል ለጅን ይገበራል ሴትና ወንድ ይቀላቀላል ይጨፈራል እርጉም የሆነው ጫት ይቃማል ስንቱ ጉድ በሚሰራበት በዚህ እርጉም የፈጠራ በአል(መውሊድ) ቁጥር አንድ ተጠቃሚም ተዳናባሪም ቃልቻ ተብየ እውቀት ቀመስ መሆኑ ፍንትው ያለ እውነታ ነው። በዋናነት የሚያሳዝነውና የሚሸወደው ደግሞ ተራው ማህበረሰባችን ነው። እናም ወገኖቸ ሆይ ቤተሰቦቻችሁን ሀገርም ሁናችሁ ውጭም ሁናችሁ በአካልጨሁናችሁ ማስተማርና ማስጠንቀቅ ባትችሉ በስልክ እየደወላችሁ እንዲታስተምሩና ከዚህ አይነት ቦታ እንዳይሄዱ እንድታስጠነቅቁ ስል ትንሹ ወንድማችሁ በሀያሉ ጌታ ስም ጥሪየን አስተላልፍላችኋለሁ። በድምፅ ለመቀዳት አልተመቸኝ ሆኖ ነው መልእክቱን ሸር አድርገን እናዳርሰው ቤተሰቦቻችን ወደ ጓዝ ሳይሸክፋ ✍ወንድማችሁ አቡ ሹራ አህመድ ከወሎ https://t.me/Sobabilalmesjid/4247 https://t.me/Sobabilalmesjid/4247

⚠️ "ድብቅ ከሆነ ስሜት" ተጠንቀቁ! ⚠️ (ከአሕመድ ቢን ሚስኪን አስገራሚ ታሪኮች) ስለ "የተሰወረ ስሜት" አደገኝነት ሰምተው ያውቃሉ?
ታላቁ ሊቅ አሕመድ ቢን ሚስኪን እንዲህ ይላሉ፦
"በ219ኛው የሂጅራ ዘመን እጅግ በከፋ ድህነት ተፈተንኩ። እኔ፣ ሚስቴና ልጄ ሆዳችን እስኪጣበቅ ድረስ በርሃብ ተቆራመድን። በመጨረሻም ቤቴን ሸጬ ለመኖር ወሰንኩና ገዥ ፍለጋ ወጣሁ። በመንገድ ላይ አቡ ናስር የተባለ ጓደኛዬን አገኘሁት፤ ሁኔታዬን ስነግረው ሁለት በጣፋጭ የተሞሉ ዳቦዎችን ሰጠኝና 'ለቤተሰቦችህ ውሰድላቸው' አለኝ። ደስ ብሎኝ ወደ ቤቴ እየተመለስኩ ሳለ፣ አንዲት እናት የታቀፈችውን ሕፃን እያሳየችኝ፦ 'ጌታዬ ሆይ! ይህ ሕፃን የቲም ነው፣ በርሃብ እያለቀ ነው፤ ለአላህ ብለህ አንዳች ነገር አብላው' አለችኝ። ሕፃኑ አይን አይኔን ሲያየኝ ያየሁት እይታ ፈጽሞ ከውስጤ አይወጣም። በእጄ የነበሩትን ዳቦዎች በሙሉ ሰጠኋትና፦ 'ውሰጂውና ልጅሽን አብዪው፤ በአላህ እምላለሁ ከዚህ ውጭ ያለኝ አንዳች ነገር የለም፣ በቤቴም ከእናንተ በላይ የራቡ ቤተሰቦች አሉኝ' አልኳት። እናቲቱ በደስታ አለቀሰች፤ የሕፃኑም ፊት በብርሃን በራ። እኔ ግን በሐዘን ተውጬ 'አሁን ቤተሰቦቼን ምን እላቸዋለሁ?' እያልኩ ግንብ ተደግፌ ሳስብ፣ አቡ ናስር እንደ ወፍ እየበረረ መጣ! 'አቡ ሙሐመድ ሆይ! እዚህ ምን ታደርጋለህ? በቤትህ እኮ ታላቅ ሀብትና በረካ ፈሷል!' አለኝ። በድንጋጤ 'ከየት መጣ?' አልኩት። እሱም፦ 'ከ30 ዓመታት በፊት ከአባትህ ጋር ይነግድ የነበረ አንድ ነጋዴ፣ የአባትህ ንብረትና ለ30 ዓመታት ያተረፈው ትርፍ በአሁኑ ሰዓት እጅግ በዝቶ መጥቷል፤ አባትህ ስለሞቱ ለወራሾቹ ሊመልስ መጥቶ ቤተሰቦችህን አገኘ' አለኝ። አላህን አመሰገንኩ፤ ከዚያች እናትና ልጅ ጀምሮ ለድሆች በረካ መሆን ጀመርኩ። በሀብቴ እጅግ ብዙ መልካም ስራዎችን ሰራሁ።
ነገር ግን እዚህ ጋር ፈተናው ጀመረ! በምሰ
ራው መልካም ስራ ሁሉ በራሴ መደመም መደነቅ ጀመርኩ። የመላእክት መዝገብ በመልካም ስራዎቼ እንደተሞላ ሳስብ ደስ ይለኝ ነበር። 'አላህ ዘንድ እኔ እጅግ ደግ ሰው ነኝ' ብዬ ራሴን ማድነቅ ጀመርኩ።
በአንድ ሌሊት ግን እንዲህ ያለ ሕልም አየሁ፦
የቂያማ ቀን ቆሟል፤ ሰዎች እንደ ማዕበል ይናወጣሉ። እያንዳንዱ ሰው የሰራውን ወንጀል ተሸክሞ ያያል። ከዚያም ሚዛን ተቀመጠ፤ የእኔም ስራዎች ሊመዘኑ ቀረቡ። ወንጀሎቼ በአንድ በኩል፣ በመዝገብ የተሞሉ መልካም ስራዎቼ ደግሞ በሌላ በኩል ተቀመጡ። ነገር ግን የሚያስደነግጥ ነገር ሆነ! እነዚያ በመዝገብ የሞሉ መልካም ስራዎቼ ሁሉ ሚዛን አልደፉም፤ ወንጀሎቼ ከበዱ።
ከእያንዳንዱ መልካም ስራዬ ስር 'የተሰወረ ስሜት' ተገኘ! * አንዱ ላይ ሪያእ (ይዩልኝ) ተገኘበት፣ * አንዱ ላይ ኩራት ተገኘበት፣ * ሌላው ላይ ደግሞ የሰዎችን ምስጋና መፈለግ ተገኘበት... አንዳችም ንጹህ ስራ አጣሁ። 'ከእንግዲህ ለዚህ ሰው የሚተርፈው ስራ የለምን?' የሚል ድምፅ ሰማሁ። በድንገት፦ 'ይህች ትቀረ
ዋለች' ተባለ። ስመለከት እነዚያ ለሕፃኑ የሰጠኋቸው ሁለት ዳቦዎች ናቸው። 'እኔ እኮ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ዲናር ሶደቃ ሰጥቻለሁ፤ እነሱ ያልጠቀሙኝ እነዚህ ሁለት ዳቦዎች ምን ሊያደርጉልኝ ነው?' ብዬ ተስፋ ቆረጥኩ። ዳቦዎቹ በሚዛኑ ላይ ተቀመጡ፤ ሚዛኑ ጥቂት ዝቅ አለ። በመቀጠልም ያቺ ምስኪን እናት በደስታ ያፈሰሰቻቸው ዕንባዎች መጥተው በሚዛኑ ላይ ተቀመጡ፤ ሚዛኑ ይበልጥ ከበደ። ከዚያም የሕፃኑ ፈገግታ ተጨመረ... በሚዛኑ ላይ እየጨመሩ ሲሄዱ በመጨረሻም፦ 'ዳነ! ዳነ!' (ነጃ ወጣ!) የሚል ድምፅ ተሰማ።ሲሉ ታሪካቸውን ይተርኩልናል 💡 ከዚህ ታሪክ የምንማረው ቁምነገር 1. የኢኽላስ (የንጹህ ኒያ)አስፈላጊነት በሚሊዮን የሚቆጠር ስራ ሰርተህ በውስጡ "የሰዎችን ምስጋና" ወይም "ኩራት" ካለበት አላህ ዘንድ ዋጋ የለውም። አላህ የሚቀበለው ለእሱ ብቻ ተብሎ የተሰራን ስራ ነው። 2. መልካም ስራን መናቅ እንዴሌለብን፦ ለአላህ ተብሎ የተደረገች አንዲት ትንሽ ስራ (ልክ እንደ ግማሽ ተምር)፣ በኩራት ከተሰራ ተራራ የሚያክል ስራ ትበልጣለች። 3. የተሰወረ ስሜትን መጠንቀቅ፦ ራስን ማድነቅ (ዑጅብ) እና ይዩልኝ መልካም ስራን እንደ እሳት የሚበሉ አጥፊዎች ናቸው። መልካም ስራን አታናንቁ፤ ወንድምህን በፈገግታ መገናኘት እንኳ ቢሆን! ከእሳት እራሳችሁን ጠብቁ፤ በግማሽ ተምር ሶደቃ ቢሆን እንኳ!ተብለናልና የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

የታላቁ ሀበሻዊ ዐሊም ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ አል ወለዊ አልቦረንይ ረሂመሁላህ ትምህርቶች በApp ተዘጋጅተው ቀርቦለዎታል።ለሌሎችም share እናድርግ።ባረከላሁ ፊኩም።

የሸይኽ መሀመድ ወሌ ትምህርቶች.apk312.66 MB

📢 አዲስ አፕ ተለቀቀ! 📖 የውርስ ህግን የተመለከቱ ትምህርቶች ✍️ 3ት ኪታቦችን በአንድ የያዘ App 🎙 የደርሱ አቅራቢ:- 🎧 ኡስታዝ አቡ ሒዛም አብዱረህማን ሰዒድ ━━━━━━━━━━━━ 1️⃣ منظومة القلائد البرهانية 👤 ሸይኽ መሀመድ አልቡርሃኒ 27 ክፍል 2️⃣ تقريب الفرائض 👤 ዶ/ር ዐብዱረህማን ቢን ሱለይማን አሽ-ሸምሳን 25 ክፍል 3️⃣ تلخيص فقه الفرائض 👤 ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን 10 ክፍል ━━━━━━━━━━━━ (PDF ከድምፅ ጋር     (ማስታወሻ መፃፍ ይቻላል (ያለ ኢንተርኔት ይሰራል (ጥራቱን በጠበቀ ድምፅ አሁኑን ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ! ለሌሎችም ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቀዳሽ ይሁኑ! 📡 ለተመሳሳይ ስራዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ 🔗 https://t.me/kasimApp      የኡስታዝን ቻናል ለማግኘት      https://t.me/durusuabihizam

ዐቅላችን ትንሽ ነው፤ ከኛ ዐቅል ያነሰ ዐቅል ካለው ሰው ጋር ከተቀማመጥን ያ ትንሹ ዐቅላችን ይሄዳል"። -ሹዕባህ {[ روضة العقلاء ]}
ዐቅላችን ትንሽ ነው፤ ከኛ ዐቅል ያነሰ ዐቅል ካለው ሰው ጋር ከተቀማመጥን ያ ትንሹ ዐቅላችን ይሄዳል"። -ሹዕባህ     {[ روضة العقلاء ]}