ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
Открыть в Telegram
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
323
Подписчики
+124 часа
-77 дней
+5830 дней
Архив постов
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ደርስ፦
~
* በይቁኒያህ
* ክፍል፦ 01 (መግቢያ)
* የኪታቡን pdf በዚህ ሊንክ ታገኛላችሁ:- https://t.me/IbnuMunewor/10283
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
🕌 የደሴ መስጂደ አስ-ሱና የእርዳታ ጥሪ!
ዛሬ የምናበረክተው የነገውን የዕውቀት ብርሃን ለማስፋት ነው!
በአላህ ፈቃድ የሚተላለፍ የዒልም ብርሃን፤ ከዱንያ ሕይወታችን በኋላም የሚቀጥል ሰደቀተል ጃሪያ ነው!
📢 ለዓለም ዙሪያ ለምትገኙ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የተላለፈ የኸይር ጥሪ!
በደሴ ከተማ የሰለፊዮች ዐይን ፣ የሱና ብርሃን መፍለቂያ እና የቁርአንና የሸሪዓ ዕውቀት መማሪያ የሆነችው መስጂደ አስ-ሱና ዛሬ በእናንተ እገዛ የሚታሰብ ታሪክ ለመሥራት በር ከፍታለች!
በቅርብ ጊዜ ይህ መስጂድ በትንሽ ቦታ፣ ቆርቆሮ በቆርቆሮ በትንሽ ቦታ ላይ ፣ በትንሽ አቅምና በታላቅ ተስፋ ተጀመረች። በሸይኽ መሐመድ መኪን መሪነት የተለያዩ ቂርኣቶች፣ የዳዕዋ ፕሮግራሞች፣ የዒልም ደርሶችና የኮርስ ትምህርቶች ሲሰጡባት ቆይተዋል።
በዚያ ትንሽ ቦታ ውስጥ የአላህ ቃል ተነብቧል፤ የነቢዩ ﷺ ሱና ተምሯል፤ የዒልም ተማሪዎች ተቀምጠዋል፤ የብዙ ሕፃናትም ልብ በቁርአን ብርሃን እንዲበራ ጥረት ተደርጓል።
ነገር ግን፣ አልሐምዱ ሊላህ! ዛሬ በዚህች መስጂድ የሚቀሩ ሕፃናት ቁጥር እጅግ ጨምሯል። ይህ የሚያስደስት የኸይር ዜና ቢሆንም፣ የሚማሩበት ቦታ መድረሳ ጠባብ በመሆኑ ትልቅ ፈተና ሆኗብናል።
ዛሬ በዚያ ጠባብ መድረሳ ውስጥ የሚቀመጡት ሕፃናት የነገው የኡማችን ተስፋዎች ናቸው። ከእነርሱ መካከል የቁርአን ሐፊዞች፣ የሐዲስ ዕውቀት ተሸካሚዎች፣ የሱና ጥሪ አስተላላፊዎችና ለእስልምና የሚጠቅሙ የዒልም ሰዎች ሊወጡ ይችላሉ።
እነዚህ ሕፃናት የአላህን መጽሐፍ በሰፊ ቦታ፣ በተመቻቸ አካባቢና በተሻለ የመማሪያ ሁኔታ እንዲማሩ ማድረግ የእኛ የዛሬ ኃላፊነት ነው።
⚠️ ወዳጆቻችን ሆይ! የዚህ ታላቅ ኸይር ተባባሪዎች እንሁን!
የመስጂደ አስ-ሱናን የመማሪያ ቦታ ለማስፋፋት፣ ሕፃናቱ የሚቀሩበትን መድረሳ ለማሻሻልና የቁርአንና የሱና ትምህርት የበለጠ እንዲስፋፋ ለማድረግ የእናንተን ድጋፍ እንሻለን።
አንዳንዶቻችን ብዙ ልናዋጣ እንችላለን፤ ሌሎቻችን ደግሞ ትንሽ ልናዋጣ እንችላለን። ነገር ግን በአላህ ዘንድ የሚቀበለው በቁጥር ብቻ የሚለካ ሳይሆን በኢኽላስና በመልካም ዓላማ የሚመዘን ነው።
በትንሽ አቅማችሁ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ!
አንድ ሕፃን በእናንተ ድጋፍ ቁርአንን በትክክል ቢያነብ፣ አንድ ተማሪ ትክክለኛ የዲኑን ዕውቀት ቢያገኝ፣ አንድ ልጅ የተማረውን ዕውቀት ለሌሎች ቢያስተላልፍ፣ የእናንተ እገዛ በዚህ መልካም ሥራ ውስጥ ድርሻ እንዲኖረው አላህ ሊያደርግ ይችላል።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«إِذَا مَاتَ الْإِنْسَانُ انْقَطَعَ عَنْهُ عَمَلُهُ إِلَّا مِنْ ثَلَاثَةٍ: إِلَّا مِنْ صَدَقَةٍ جَارِيَةٍ، أَوْ عِلْمٍ يُنْتَفَعُ بِهِ، أَوْ وَلَدٍ صَالِحٍ يَدْعُو لَهُ».
“የሰው ልጅ በሞተ ጊዜ ሥራው ይቋረጣል፤ ከሦስት ነገሮች በስተቀር፦ የሚቀጥል ሰደቃ፣ ከእርሱ የሚጠቀምበት ዕውቀት፣ ለእርሱ ዱዓ የሚያደርግ መልካም ልጅ።”
📚 ሰሒሕ ሙስሊም፣ 1631
ወንድሞችና እህቶች ሆይ! ዛሬ በመስጂድ ማስፋፊያ ላይ የምናዋጣው ገንዘብ የዛሬ ድጋፍ ብቻ አይደለም። በዚያ ቦታ ቁርአን ሲነበብ፣ የአላህ ዲን ሲማር፣ ልጆች ሲያድጉና የሚጠቅም ዕውቀት ሲተላለፍ፣ አላህ ከምሕረቱ ድርሻ እንዲያደርግልን የምንሻበት ታላቅ እድል ነው።
እኛ እዚህ ምድር ላይ ለዘላለም አንኖርም። ነገር ግን በኢኽላስ የተሠራ መልካም ሥራ አላህ ከተቀበለው፣ ከሞታችን በኋላም የምንጠብቀው የኸይር ምክንያት ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ ዛሬ የምንችለውን እናድርግ፤ የምንችለውን እናዋጣ፤ ሌሎችም እንዲሳተፉ እንጋብዝ። ምናልባት በእኛ የተነሳ የአላህ ዲን የሚማሩ ልጆች ቁጥር ይጨምር ይሆናል።
⚠️ዛሬ የእናንተ ድጋፍ የእነዚህ ሕፃናት ተስፋ ነው!
🌍 በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለምትኖሩ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፦ በዚህ የኸይር ሥራ ላይ የቻላችሁትን ያህል ድጋፍ እንድታደርጉልን በአላህ ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የምትሰጡት ትንሽ ቢመስልም አትናቁት። የምታደርጉት ድጋፍ በአላህ ፈቃድ ለብዙ ሕፃናት የዒልም መንገድ ሊያመቻች ይችላል። ካልቻላችሁ ደግሞ ይህን ጥሪ ለሌሎች በማድረስ ተባበሩን። የኸይርን መንገድ የሚያመለክትም ከሠሪው ምንዳ ያገኛል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🏦 የመስጂደ አስ-ሱና የባንክ ሂሳቦች
💳 1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
1000469830277
💳 2. ዘምዘም ባንክ
0005649620101
💳 3. ሂጅራ ባንክ
1000030300001
📌 ከላይ የተጠቀሱት የባንክ ሂሳቦች በመስጂደ አስ-ሱና ስም የተመዘገቡ ናቸው።
ስለ መስጅዱ ሙሉ መረጃ ለማገኘትና ለመጠየቅ
ስልክ፦+251914718693
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
📣 ይህን መልእክት ሼር በማድረግ ለመስጂደ አስ-ሱና ማስፋፊያ የሚያግዙ ወንድሞችና እህቶች እንዲደርሱ እንርዳ!
🕌 በመስጂደ አስ-ሱና — ላይ የማናደርገው የዛሬው ድጋፋችን፣ የነገው የዒልም ብርሃን ያሰፋል!
አስር ምክሮች ለሙስሊም መምህራን
~~
① ሃላፊነት ይሰማህ። የምትገነባው ትውልድ ነው። የምታስተላልፈው ነገር እጅግ ውድ ነው።
"ሃላፊነት የሚሰማው ሰው እራሱን እንደ ህዝብ ንብረት አድርጎ ይቆጥራል።"
② የሚያዩህ፣ ምሳሌ የሚያደርጉህ አሉና ተጠንቀቅ። ክፉ ምሳሌ እንዳትሆን። ከባህሪህ፣ ከገፅታህ፣ ከአቀራረብህ ሰዎች ይማሩ ዘንድ መልካም ሁን።
③ ፍትሃዊ ሁን። አንዱ ባጠፋው በጅምላ አትቅጣ። በጥቂቶች ጥፋት ተማሪዎችን በትምህርት፣ በፈተና አትቅጣ። በበደለኛ አስተማሪዎች ሳቢያ ስንቶች ትምህርት አቋርጠዋል?! ስንቶች የተወሰኑ የትምህርት አይነቶችን ጠልተዋል። የስንቶች ውጤት ተበላሽቶ ሞራላቸው ተነክቷል።
"የትምህርት ተቋማት በሰፊው ስለ መብት የሚቀነቀንባቸው፣ ብዙ ጭቆና የሚፈፀምባቸው የግፍ አፀዶች ናቸው።"
④ ልዝብ ሁን አታስበርግግ። ቁጥብ ሁን አትባልግ። ትሁት ሁን አትጨፍግግ። የቸገረው ሊያዋይህ የማይፈራህ፣ የከበደው ሊጠይቅህ የማይሰጋህ፣ ያበጠበት የማይደፍርህ ሁን። ሚዛንህን ጠብቅ። ለሁሉም የሚገባው ቋንቋ ይኑርህ።
⑤ ክፋትን፣ ዘረኝነትን አትመግብ። ትውልድ አትመርዝ። በአሁኑ ሰዓት ዘረኝነት ከገበሬው ይልቅ ምሁሩ ጋር ጎልቶ የሚታይበት ምክንያቱ አርቀው ማየት የማይችሉ የተማሩ መሀይማን በመብዛታቸው ነው።
⑥ ብቁ ሁን። እራስህን በእውቀት ገንባ። ተዘጋጅተህ ወደ ክፍል ግባ። ካልሆነ ትናቃለህ። ካልሆነ ሃላፊነትህን በአግባቡ አትወጣም። ካልሆነ ልበ ሙሉነት /confidence/ ታጣለህ። የምትስሰለች ሳይሆን ልብ የምታንጠለጥል፣ የምትናቅ ሳይሆን የምትወደድ፣ የምትፍፈራ ሳይሆን የምትከበር ሁን።
⑦ ለችግር ደራሽ ሁን። የተማሪ ችግር ይግባህ። የጤና፣ የኢኮኖሚ ችግር ያለበት፣ ቤተሰባዊ ቀውስ ያጋጠመው፣ ስነ ልቦናው የተጎዳ፣ ልቡ በሀዘን፣ በጉዳት የተሰበረ ይገጥማልና በምትችለው አግዝ። "አይዞን"፣ "አብሺር" ማለት ለተጎዳ ሰው ዋጋው ትልቅ ነው።
⑧ ቂመኛ አትሁን። ያለፍክበትን ያላለፉ፣ ነገን አሻግረው የማያዩ ጨቅላዎች ጋር ቂም አትጋባ። ከተማሪ ጋር እልህ ውስጥ አትግባ። ተማሪህ የሚናገረውን፣ የሚጠይቀውን ሁሉ በክፉ አትተርጉም።
⑨ ጥንቃቄ ይኑርህ። በአነጋገርህ፣ በአቀራረብህ፣ በሁለ ነገርህ ጥንቃቄ አይለይህ። በምታስተምራቸው ተማሪዎች ቁጥር ልክ በየቤቱ አጀንዳ እንደሆንክ ልብ በል። በክፉ ወይም በበጎ በየቤቱ ትነሳለህ። ከረጅም አመታት በኋላ ዛሬም ድረስ በክፉ ወይም በበጎ የማንረሳቸው አስተማሪዎች አሉ። ለሰዎች ከልብ የማይጠፋ ክፉ ትዝታ አትሁን።
(10) ለዲንህ ዋጋ ስጥ። ዲንህን ስታውቅ ለተማሪዎችህ መልካም ምሳሌ ትሆናለህ። ዲንህን ስታውቅ የተሳሳተ አስተምህሮ ለተማሪዎችህ አትመግብም። መጠናቸው ቢለያይም ሁሉም የትምህርት አይነቶች ውስጥ ከዲን ጋር የማይሄዱ ነገሮች ይገጥሙሀል። ንቁና ብቁ ከሆንክ እርምት እየሰጠህ ማለፍ ትችላለህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
🗣🗣🗣በኡስታዝ አብዱሰላም ሸይኽ ሀሰን
👂👂የግቢ ቆይታ ለተማሪዎች የጁመዓ ኹጥባ
*የዱንያ ነገር!!*
~~~
ዐልይ ኢብኑል ሀይሠም እንዲህ ይላሉ:–
"አምሳያ ያላየሁለት የዘመን መገለባበጥ፣ የጊዜ መለዋወጥ አይቻለሁ።
★ የአልፈድል ኢብኑ ረቢዕ ንብረት በአንድ ሺህ ግመል ተጭኖ አይቻለሁ። ሌላ ጊዜ ግን ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተደብቄ አይቻለሁ። በውስጧ መድሃኒቶቹ ተጨምረው።
★ አልሐሰን ኢብኑ ሰህልን ደግሞ ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተመልክቻለሁ። ከዚያ ግን ንብረቱ በአንድ ሺ ግመል ላይ ተጭኖ አይቼዋለሁ።"
||
ዱንያ እንዲህ ነች። መርጋት የማታውቅ ወላዋይ!!
♣ ሃያላን ይዋረዳሉ። ደካሞች ይነግሳሉ።
♣ ሀብታሞች ጎዳና ላይ ይወድቃሉ። ምንዱባን በሰማይ ጠቀስ ህንፃ ይንፈላሰሳሉ።
♣ ሳር ቅጠሉን የተፀየፈው ጨፍጫፊ አረመኔ አለም ጠባው ከአይጥ ጎሬ ሲያደፍጥ ታየዋለህ። የትላንቱ ተሳዳጅ ተራውን ሲያሳድድ ትመለከታለህ።
® ይሄው ነች ዱንያ!! ብልጭ ብላ ድርግም፣ ቦግ ብላ እልም የምትል። ሁሌ ሳቅ የለም! ሁሌ ድል የለም።
|
♣ በድር ላይ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገሩ፣ ጥጋብ ያስከራቸው ቁረይሾች፣ 70 መኳንንቶቻቸው ትላንት ሲያሳድዷቸው በነበሩ ሶሐቦች ሰይፍ ተበልተው፣ ሌላ 70 ደግሞ በምርኮ አስረክበው የሐዘን ማቅ ለብሰዋል። መካ በዋይታ ተንጣለች።
|
♣ ኡሑድ ሌላ ቀን ነው። ሌላ ተራ!! አጋሪዎች የፈነደቁበት፣ እነ ሐምዛን፣ እነ ሙስዐብን ጨምሮ ከ70 በላይ ታላላቅ ጀግኖች ወድቀው ሌላ 70 የቆሰሉበት፣ አሳዝኝ ክስተት እውን የሆነበት ቀን። ሶሐቦች አካላቸው በስለት፣ ልባቸው በሐዘን ቢቆስል ጊዜ አላህ እንዲህ ሲል አሳሰባቸው: –
(إِنْ يَمْسَسْكُمْ قَرْحٌ فَقَدْ مَسَّ الْقَوْمَ قَرْحٌ مِثْلُهُ ۚ وَتِلْكَ الْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ النَّاسَ)
"ቁስል ቢያገኛችሁ ሰዎቹንም መሰሉ ቁስል አግኝቷቸዋል፡፡ እናም እነዚህን ቀናት በሰዎች መካከል (በመልካምና በሌላ) እናቀያይራቸዋለን፡፡" [ኣሉ ዒምራን: 140]
|||
ዱንያ አመሏ ነው። ዛሬም እንዲሁ ናት።
ግን ማነው የሚማረው? ግን ማነው የሚመረምረው? ግን ማነው የዱንያን ከንቱነት ተገንዝቦ ለዘላለም ቤቱ ከልብ የሚጨነቀው?
እስከ መቼ ነው የምናንቀላፋው?
እስከ መቼ ነው የምንዘናጋው?
እስከ መቼ ነው በከንቱ የምንባዝነው?
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!
ኢላሂ ልብ ስጠን!!
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from N/a
ስለ ለተሞ { አ/ልሀሚድ አልለተሚይ ቡድን }
የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት ማዳመጥ ይችላሉ❶የለተሞ ቡድን እና ኢብኑ መስኡዶች ጉዳይ ❷የለተሞ ውሸት ➌ኡ/ዝ ሳዳትና ኢብኑ ሙነወር ሱናን የኻለፍባቸው የቱ ➍ረድ በሻኪር ሱልጣን ➎የመሻይኮችጀለሳ ይሂን ያዳመጥብዥታአይገባውም ➏የሱና መፅሀፎችን ማቃጠል ➐በኡ/ዝ ኸድር እና አቡ ዘር መካከል የተደረገ ውይይት ➑እየው ሲላተምበት ➒ለተሞ አባጋራ ➓ ቡድንተኝነት ቅጥ ከማሳጣቱም በላይ ሐቅ ያሳጣል ❶❶ለተሞ ኡ/ዝ ሳደት እና ኢብኑ ሙነወር ሲሳደብ ❶❷በእውር ድብር የሚጓዘው የለተሞ ቡድን በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ክፍል 🥇ለቅጥፈት አራጋቢዎች ክፍል 🥈ስለ ኢልዛም ረድ በወሰን ተላላፊዎች ላይ
በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል ኬሚሴ ሀፊዘሁሏህክፍል ❶ የአ/ልሀሚድ አልለተሚይ ስህተቶች ክፍል ❷ የአቡዘር ስህተቶች እና ግጭጭቶች ክፍል ➌ለከት የሌለው የተገጫጨ ንግግራቸውን ክፍል ➍ እውነት የአቋም ለውጥ የተከሰተው ከማን? ክፍል ➎ አ/ልሀሚድ መረጃዎች ያለቦታቸው እየደረደረ ክፍል ➏ አ/ልሀሚድ የዑሰይሚን የአልባኒይ ተማሪ❓ ክፍል ➐ አ/ልሀሚድ ከወደቀባቸው ስህተቶች ውስጥ ክፍል ➑አ/ልሀሚድሙጅተሂድ እናኢጅቲሀድከበደው ክፍል ➒ የአ/ልሀሚድ ነጫጭ ውሸቶችን ማጋለጥ ክፍል ➓ አ/ልሀሚድ የሱፍያን ተግባር የፈፀመ ነው ረድ በ ሁሰይን ሙሀመድ አስልጢይ ላይ
ሚያመጣቸው ማምታቻዎች እና ማደናገሪያዎችን ግልፅ ማድረግ !!!
በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል ኬሚሴ ሀፊዘሁሏህክፍል ❶ ክፍል ❷ ክፍል ➌ ክፍል ➍ ክፍል ➎ ክፍል ➏ ክፍል ➐ ክፍል ➑ ክፍል ➒ ክፍል ➓ ረድ በሸይኽ በአቡዘር ላይ
ሸይኽ ሙሓመድ አሚን ላይ ላደረገው ንግግር የተሰጠመልስ
በኡስታዝኸድር አህመድ አል ኬሚሴ ሀፊዘሁሏህክፍል 🥇 ሸይኽ አቡዘር ከ ኢኽዋኖች የወረሰው አቋሙ ክፍል 🥈 የሱና ሰው ማስወጣት እና ኢብኑ መስዑዶችን ክፍል 🥉ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥ አስመልክቶ
ሰሞኑን የኦርቶዶክስ አባቶች አምላክ በስጋ ፍጡር ይባላል ወይስ አይባልም በሚለው እርስ በእርሳቸው እየተፋለሙ ነው። አምላክህን በጉባዔና በስብሰባ ስትወስን እንደዚህ መለያየትህ አይቀርም። አምላክ በስጋው ፍጡር ይባላል ወይስ አይባልም የሚለውን እንደበፊቱ አደባብሰውት ይተውታል ወይስ አንድ ሀሳብ ላይ ይስማማሉ የሚለውን እናያለን። ግን የሚስማሙ አይመስልም። ምክንያቱም አምላክ በስጋው ፍጡር ነው ማለት አምላክን ፍጡርነት አለበት የምናመልከው ፍጡርም ጭምር ነው ወደማለት ስለሚወስድ ይሄን ለመቀበል ይከብዳቸዋል። በተቃራኒው አምላክ በስጋው ፍጡር አይባልም ከተባለ የሰውነቱን ባህሪ መካድ ይሆንባቸዋል። ስለዚህ የሚኖራቸው አማራጭ አደባብሶ ማለፍ ነው። በመጨረሻ ለሁለቱ አንድ መልእክት አለኝ
قُلۡ يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ تَعَالَوۡاْ إِلَىٰ كَلِمَةٖ سَوَآءِۭ بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكُمۡ أَلَّا نَعۡبُدَ إِلَّا ٱللَّهَ وَلَا نُشۡرِكَ بِهِۦ شَيۡـٔٗا وَلَا يَتَّخِذَ بَعۡضُنَا بَعۡضًا أَرۡبَابٗا مِّن دُونِ ٱللَّهِۚ فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَقُولُواْ ٱشۡهَدُواْ بِأَنَّا مُسۡلِمُونَ ﴿64﴾
የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡ (አል-ዒምራን 3:64)
「📲 አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」
╭┄┈┈⟢
┆📚ሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም
╰─────────────╯
↗️🔊የደርሱ አቅራቢ:-
───⟢
┆🎧 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
╰─────────────
┌⧿⧿⛉
├🤩45 ኦድዮዎችን የያዘ
├🤩423MB ብቻ
├╶╶╶
├⏬አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ
│ይጠቀሙ!
│
┝ለሌሎችም ሼር በማድረግ የአጅሩ
│ተቋዳሽ ይሁኑ!
└───────────
┆➡️ ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን
┆✉️http://t.me/Yusuf_App1
╰╼────────────╯
ሚድያ ከተጠቀምን አይቀር የእነዚህን ምርጥ የሱና መሻይኾች እና ኡስታዞች ቻናል ስጦታ ልስጣችሁ? የእኛ ድምቀቶች እስኪ እንቀላቀላቸዉ። እንጠቀማለን እነሱንም አላህ ደረጃቸውን ከፍ ያድርገው ፅናትን ይለግሳቸዉ ይለግሰን አሚን ያረብ!
ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን ብን አደም
t.me/SheikhMuhammedZainAdam
ሸይኽ አወል አቡ ዐማር ከሚሴ
t.me/SheihkAbuAmarAwolIbnuAhmed
ሸይኽ አብዱሶመድ ከላላ
t.me/kelelaqiratcenter
ኡስታዝ ሳዳት ከማል
t.me/SadatKemalAbuMeryem
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
t.me/IbnuMunewor
ኡስታዝ ሙሐመድ ሱልጣን
t.me/ibnusultan38
ኡስታዝ አቡ ሙስሊም አል_አሩሲይ
t.me/AbumuslimAlarsi
ኡስታዝ ኸድር አህመድ ከሚሴ
t.me/UstazKedirAhmed
ኡስታዝ ሙሀመድ ሲራጅ
t.me/Muhammedsirage
ኡስታዝ ዐብዱ'ሶመድ ሙ/ኑር
t.me/AbdusomedMuhammedNur
ኡስታዝ አብዱል_ጀባር ሙ/ኑር
t.me/AbdulJebarMNur
ኡስታዝ አንዋር ሙ/ኑር
t.me/AnwarMNur
ኡስታዝ ሑሰይን ዐልይ
t.me/husseinali210
ኡስታዝ አቡ ሒዛም አብዱረህማን
t.me/durusuabihizam
ኡስታዝ ፉአድ ሙሐመድ
t.me/fuadorodurus
ኡስታዝ አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
ኡስታዝ ሰዒድ ሙሳ አቡል ቡኻሪ
t.me/AbulBukhariSeid
ኡስታዝ አቡ ፈዉዛን አብዱ'ሽኩር
t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
ኡስታዝ አህመድ ኑር
t.me/abuhureyrahmedresa
ኡስታዝ አቡ ረይስ
t.me/abu_reyyis_arreyyis
ኡስታዝ አብዱሰላም
t.me/durusuabdiselam
ኡስታዝ አብዱረዛቅ ባጂ
t.me/fewaidabdurazaq
ኡስታዝ አቡ አዩብ ሙሐመድ
t.me/abutoiba
ኡስታዝ በህረዲን ከማል
t.me/UstazBehredinKemal
ኡስታዝ አቡ ዑሰይሚን
t.me/abuUseyminabdurehman
ኡስታዝ አቡል_ዐባስ ናስር
t.me/Abulabas
ኡስታዝ ሙሐመድ ዐብዲላህ ባቲ
t.me/Muhammedbatii
ኡስታዝ ኢብራሂም ኸይረዲን
t.me/ibrahim_furii
ኡስታዝ ዐብዱል_ዐዚዝ
t.me/mumeti_a
ወንድም ሙሐመድ አልጃዊ
t.me/MOhamedAljawi
ወንድም አልዋን አቡ ዑበይዳ
t.me/ABUUBEYDAH_ALWAN
ወንድም አቡ ሁዘይፋ ሰዒድ
t.me/tubaliligurebae
ወንድም አቡ ሀፍሷ ሙሀመድ አልይ
t.me/tewhidfirst29
ወንድም ፉአድ ነብዋ ዩቱብ
t.me/NABAWITUBE
ወንድም አቡ ኑህ ኢብኑ ፈድሉ
t.me/Darutewhide
ወንድም ኑረዲን አል አረቢ
t.me/nuredinal_arebi
ወንድም አቡ ሀሳን ዐልይ
t.me/abu_hassan_aliy_yusuf
ወንድም ሙርሰል ሰዒድ
t.me/murselseid
ወንድም አቡ ማሒር አል_አስሪይ
t.me/ibnuidris_teppi
ወንድም አቡ ሀፍሷ ይማም
t.me/AbuHafsaYimam
ወንድም ሙሐመድ ሲራጅ ከሚሴ
t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie
ወንድም አቡ ሱፍያን ሑሰይን
t.me/AbuSufiyan_Albenan
ወንድም አቡ ሒበቲላህ ሑሰይን
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
ወንድም ዐብዱረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman
ወንድም አቡ አነስ ጦሃ ጀማል
t.me/Abuanus
ወንድም አቡ ሱለይማን
t.me/Abu_suleyman_dera
ወንድም አቡ ዐብዱረሒም
t.me/abuabdirehim
ወንድም አቡ ዑበይዳ ሰላሁዲን
t.me/selahudin_Islamic_knowlages
ወንድም አቡ አይመን
t.me/tgewid
ወንድም አቡል_ዐባስ
t.me/Abulabashsen
ወንድም አቡ ዒምራን
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
ወንድም አቡ ዐቲካህ
t.me/ikhlastube2
ወንድም አቡ ዐኢሻ አወል ካሳዉ
t.me/Abuebrahim22322
ወንድም አንሷር ሙሐመድ
t.me/sunnahlight8800
ወንድም አቡ ረስላን ከላላ
t.me/AbuReslanAsselefy
العلماء هم كواكب الأرض، ዑለማኦች የምድር ኮከቦች ናቸው።= https://t.me/Deewaselefyya1448.
Repost from Abu Useymin (أبو عثيمين ابن شافي )Channel
የጁሙዐ ኹጥባ ርዕስ፦ የሰላም ፀጋ!
🕌ቦታ ደሴ ጅብሪል ጎራ መስጅድ
🎙በ ዒዙዲን ኢብኑ ሻፊ
የቴሌግራም ቻናል፦
¤t.me/Ezedin_Ibnu_Shafi
⛓️ «የወንጀል እስራት እና የዕንባ መፍቻ!»
بسم الله الرحمن الرحيم
ውድ ወንድሜ… የተከበርሽ እህቴ!
ቆም ብለህአሰብክ ታውቃለህ ?
ቆም ብለሽ አስበሽስ ታውቂያለሽ ?
ወንጀል እጅና እግርን የማይታይ ሰንሰለት አግዶ የሚያስር፣ መንፈስን የሚያጠበብ፣ የልብን ብርሃን አጥፍቶ በጨለማ ክፍል ውስጥ የሚቆልፍ ከባድ እስራት ነው።
ስንቶቻችን ነን በየቀኑ የሚደጋገሙ ጥፋቶቻችን ታስረን፡
▾ ሶላት ለመስገድ ስንነሳ እግራችን የሚከብደን?
▾ ቁርኣን ለማንበብ እጃችንን ስንዘረጋ የሚዝልብን?
▾ ከአላህ ጋር ለመቀራረብ ስንል ልባችን ድርቅ ብሎ የሚፈታተነን?
ይህ ሁሉ የሌላ ነገር ውጤት አይደለም—የወንጀል እስራት ነው!
🔥 ወዳጆቼ ሆይ! አላህ ይዘንልንና… ለአንድ አፍታ እንኳ በሕይወታችን የሰራናቸውን ወንጀሎችና ጥፋቶች በቁጭት እሳትነት አቃጣይ ስሜት አስበናቸው እናውቃለን?
አላህ እያየን፣ የሰጠንን ጸጋ በእጁ እየተቀበልን፣ በእሱ ላይ ደፍረን ስናመፅ የነበረበትን ጊዜ ስናስበው ልባችን አይነድም? እስከ መቼ ነው በዚህ የወንጀልና የእስራት እንቅልፍ ውስጥ የምንቆየው?»
እስከ መቼ ነው በገዛ እጅህ የወንጀል ሰንሰለት እየተበተበህ የሸይጧን እና የነፍስህ ባሪያ ሆነህ የምትኖረው? እስኪ ንቃ! እስከ መቼ ነው በዚህ ውርደት ውስጥ የምትቆየው?
ስንት ሌሊት ነው አላህ እየተመለከተህ በምስጢር ወንጀል ስትጨማለቅ ያደርከው?
ሰዎች እንዳያዩህ በሩን ዘግተህ፣ መጋረጃውን ጣል አድርገህ፣ ስልክህን ደብቀህ ተደበቅክ… ነገር ግን የሰማይና የምድር ጌታ እያየህ እንደነበር አረሳኸውም?
የሰዎችን እይታ ፈራህ፤ የአላህን እይታ ግን አቀለልከው! ከዚህ በላይ ምን የሚያስቆጭና የሚያሳፍር ውርደት አለ?
እስኪ አስበው… ያንተን ጥፋትና ነውር አላህ ለሰዎች ቢገልጥብህ ኖሮ ዛሬ ማን ያከብርህ ነበር?
ማን አብሮህ ይቆም ነበር?
እሱ ግን ስትበድለው እንኳ ነውርህን ደብቆልህ፣ የአየር እስትንፋሱን ሳይከለክልህ፣ ጤናህን ሳይነጥቅህ እስከ ዛሬ ታገሰህ!
አንተ ግን በምታገኘው እያንዳንዱ ጸጋ እሱን ስታመፅበት አልፈራህምን?
በዓይንህ አላህ የከለከለውን ስታይ፣ በጆሮህ የተጠላውን ስትሰማ፣ በእግርህ ወደ ወንጀል ስትራመድ…
«የሞት መልአክ አሁን በዚች ቅጽበት ነፍሴን ቢነጥቃት አላህ ፊት በምን ፊት እቆማለሁ?💦
» ብለህ አልደነገጥክም? ቁጭቱና ፀፀቱ አያቃጥልህም?💦
"ነገ እመለሳለሁ፤ ነገ ተውበት አደርጋለሁ፤ ገና ወጣት ነኝ..." እያልክ እራስህን አታልለህ አትተኛ!
"ነገ አለህ… አንተ ግን በነገ ውስጥ ላይኖርህ ትችላለህ!" የሞት መልአክ በርህን ለማንኳኳት ያንተን ዕድሜ ማጠናቀቅ እንጂ ያንተን "ነገ እመለሳለሁ" የውሸት ምኞት አይጠብቅም።
ነገር ግን ተስፋ አትቁረጥ!
አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እኮ እንዲህ ይላል፦
«በላቸው፡- እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ አላህ ኃጢአቶችን ሙሉ በሙሉ ይምራልና። እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና።» (ዙመር፡ 53)
ዛሬ የዚያን የጠነከረ ልብህን ዕንባ መፍቻ ቀን አድርገው!
የአላህ ፍርሃት ከልብህ መንጭቶ በጉንጭህ ላይ የምታፈሳት አንዲት የቆጨች ዕንባ… አላህ ዘንድ እጅግ የተወደደች ናት።
ያች ዕንባ የእስራትህን ሰንሰለት ስብርብር አድርጋ የምትጥል፣ የነፍስህን የቆሸሸ ገጽታ አጥባ የምታጠራ ልዩ አሲብ ናት።
ዛሬውኑ ወስንወስኒ💦!
▾ እስኪ ወደ ኋላ ተመልከት፦ ያበላሸኸውን ታሪክ በቅን ተውበት እጠበው።
ያለፉትን የጨለማ ቀናትህን፣ ከአላህ መንገድ የራቅክባቸውን ዓመታት፣ የወደቅክባቸውን አሳፋሪ ወንጀሎች አስባቸው። ነገር ግን ተስፋ ልትቆርጥ ሳይሆን፣ በቁጭትና በዕንባ ልታጥባቸው ወደ ኋላ ተመልከት! አላህ ያለፈውን ጥፋትህን ሙሉ በሙሉ ደምስሶ በበጎ ሥራዎች የመለወጥ ቃል ገብቶልሃል።
ታሪክህ ምንም ያህል ቢበላሽ፣ በአላህ እዝነትና በእውነተኛ ተውበት የማይታደስበት ምንም ምክንያት የለም፤ ዛሬ አዲስ ገጽ ክፈት!»
▾ አሁኑኑ ቁም፦ "ነገ" የሚባለውን የሸይጧን ማታለያ ቀለበት በጥስ።
"ነገ እመለሳለሁ፣ ነገ እቀየራለሁ፣ ነገ ተውበት አደርጋለሁ..." እያልክ እራስህን አታታል! ሸይጧን ስንቱን በ"ነገ" ማታለያ ተስፋ እያሰጠ ቀስ እያለ ከቀጥተኛው መንገድ አወጣው? ስንቱ ሰው "ነገ እቀየራለሁ" እያለ ሳይቀየር በመጣበት ቅጽበታዊ ሞት ተነጥቆ ወደ ቀብር ወረደ?
"ነገ" ያንተ አይደለችም፤ ዛሬ ግን በእጅህ ላይ ናት! አሁኑኑ ተነሥ፣ የወንጀልን ሰንሰለት በጥስና ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነት አድስ። አሁኑኑ ካልቆምክ፣ ነገ በሚባለው ሀሰተኛ ተስፋ ውስጥ ተሸውደህ እስከወደቅክበት ልትቀር ትችላለህ!»
▾ እጆችህን ዘርጋ፦ በብቸኝነት አላህ ፊት ተንበርከክና እውነተኛ ዕንባህን አፍስስ፤
ሰዎች በሙሉ በተኙበት፣ በዚያ በጨለመው የሌሊት ክፍለ ጊዜ፣ ማንም የማያይህና የማይሰማህ ቦታ ላይ በብቸኝነት ተንበርከክ።
የሠራኸውን ነውር ሁሉ ለአላህ እያመንንክ፣ በሠራኸው ጥፋት ልብህ በቁጭት እየነደደ፣ እጆችህን ወደ ሰማይ ዘርጋ።
ከዓይንህ የምታፈሳት አንዲት የቆጨችና ከአላህ ፍርሃት የተነሳች ዕንባ… የጀሀነምን እሳት ለማጥፋት ብቁ ናት! ጌታህ እኮ ከሰው ይልቅ ለአንተ አዛኝ ነው፤ እጆችህን ባዶአቸውን ወደ እሱ ዘርግተህ ባዶህን ሊመልስህ ያፍራል።
ዛሬ በብቸኝነት አላህ ፊት አልቅሰህ ልብህን አርሳት፣ የወንጀልን ሰንሰለት በዚያች እውነተኛ ዕንባህ በጥስ!»
"ጌታዬ ሆይ! ተመለስኩብህ፣ ተቀበለኝ" በለው!
“ጌታዬ ሆይ! በወንጀል የቆሸሸችውን ነፍሴን፣ በምስጢር ያጠፋሁትን ጥፋቴን፣ የታከትኩበትን እድሜዬን ይዤ በደጅህ ወድቄአለሁና አትመልሰኝ! እስከ ዛሬ በባከነ መንገድ ላይ የተጓዝኩበት ይበቃኛል፤ እባክህ ማረኝ፣ ተቀበለኝ!” በለው!»
«ወንድሞቼና እህቶቼ ሆይ! ይህንን ማስታወሻ ወደ እናንተ ስልክ፣ እኔ ከእናንተ የተሻልኩ፣ ከወንጀል የጠራሁ ወይም ከማንም በላይ አላህን የምፈራ ሆኜ አይደለም።
እኔ ራሴ የወንጀልና የጥፋት ባሪያ፣ የአላህ ምህረትና እዝነት ከአንደበቴ በላይ እጅግ የሚያስፈልገኝ ምስኪን ባሪያ ነኝ።
ነገር ግን ነፍሴንና እናንተን ባስታወስኩ ቁጥር “አላህ ሁላችንንም ይማረን፣ ይዘንልን” ከሚል የልብ ቁጭት የተነሳ የቀረበ የወንድማማችነት ጥሪ ነው።
አላህ እኔንም እናንተንም ከወንጀል እስራት አውጥቶ፣ በእውነተኛ ተውበት ልቦቻችንን ያድስልን፤ መጨረሻችንንም ያሳምርልን! 🤲»
✍️ የጌታው ምህረት ከጃይ አቡ ማሒ ሙሐመድ ብን ኢድሪስ
🔗 ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
https://t.me/Deewaselefyya1448.
https://t.me/BerhanFelega
https://t.me/BerhanFelega
Repost from Ustaz Kedir Ahmed Al—Kemisse (Abu Juweyriya)
ሙሐደራ 244
ለዕውቀት የተከፈለ መስዋዕትነት
🕌 በ መርከዝ ኢብኑ ዓባስ ከሚሴ
🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ
https://t.me/UstazKedirAhmed
ጥቂት ነጥቦች ከልጆች አያያዝ ጋር
~
1- ሰባት ዓመት የሞላቸውን ልጆች ሶላት እንዲሰግዱ ማዘዝ ላይ ልንዘናጋ አይገባም። አስር ከሞላቸው ካልሰገዱ መቅጣት ይገባል። በጊዜ ያልተያዘ ነገር ኋላ ተራራ ከመውጣት በላይ ሊከብዳቸው ይችላል። ከተዋሃዳቸው ግን ከራሳቸው አልፈው ለሌላ ይተርፋሉ።
2- ከልጆቻችን ጋር የተመጠነ አቀራረብ ሊኖረን ይገባል። አያያዛችን ጨካኝና አስበርጋጊ መሆን የለበትም። ይልቁንም እንደ ልጅ ብቻ ሳይሆን እንደ ጓደኛም ዘና ብለው የሚያማክሩን እንዲሆኑ ልናደርጋቸው ይገባል። በሌላ በኩል ምንም ቢያጠፉ፣ እንደፈለጉ ቢቀብጡም ቅጣት ቀርቶ ቁጣ እንኳ የማይከተላቸው ካደረግናቸው ይሄ ማዘን ሳይሆን ማጨማለቅ ነው። ልጆች እንግዳ የሚያከብሩ፣ ሌሎችን የማይበጠብጡ፣ ከትልቅ ሰው ፊት አደብ ያላቸው እንዲሆኑ መስራት ይገባል።
3- ልጆች ቁርኣን እንዲቀሩ፣ ቢያንስ መሰረታዊ ኢስላማዊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ትኩረት መስጠት ይገባል። ከዚህም ባሻገር ለሰው ህይወት ክብር ያላቸው፣ የሰው ሐቅ የሚፀየፉ እንዲሆኑ ማስተማር ጥሩ ነው። ይሄ በየ ጫካው ነፍስ እየነጠቀ፣ ሰው እያገተ ያለው፣ በየ ገበያው የሚያጭበረብረው፣ በየ ቢሮው ሰው የሚያጉላላውና የሚያንገላታው፣ ህዝብ የሚጨቁነው ባለ ሥልጣን ሁሉ በአብዛኛው አሳዳጊ የበደለው፣ ጤነኛ ተርቢያ ያላገኘ ስድ አደግ ነው። ልጆቻችን ነገ ሰው የሚያስለቅሱ እንዳይሆኑ ዛሬ አስተዳደጋቸውን እናሳምር።
4- በልጅ አስተዳደግ ላይ መታየት ካለባቸው ነገሮች ውስጥ ሌላው ነጥብ አንዳንዴ ለልጆቻችን ያለንን ፍቅር ደበቅ ማድረጉ አስፈላጊ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ነው። በተለይ ልጆች ይህንን ስስ ስሜታችንን ላልተገባ አካሄድ የሚያውሉት ሲሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። የኛ መንሰፍሰፍ የሚያቀብጣቸውና የሚያንዘላዝላቸው እንዳይሆን አንዳንዴ ፍቅራችንን ደበቅ፣ ኮስተር፣ አስፈላጊ ሲሆን ቆንጠጥ፣ እንደ ሁኔታው ከዚያም ያለፈ አቀራረብ ሊኖረን ይችላል።
5- ከምናደርጋቸው ጥረቶች ውስጥ መረሳት የሌለበት ወሳኝ ነጥብ ደግሞ ዱዓእ ነው። የምንደሰትባቸው እንጂ የምንከፋባቸው እንዳይሆኑ፣ በዱንያም ይሁን በኣኺራ ለኛም ለራሳቸውም የሚበጁ ሷሊሖች እንዲሆኑልን አላህ አዘውትሮ መለመን ይገባል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 29/2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Abu Hayder Aliy
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ዛሬ ጁሙዓ ነዉ የጁሙዓ ሱናዎች
➖➖➖➖➖➖➖
↩️💎 سنن يوم الجمعة🌿🌿🌿
➊ 💎الغسل
➋💎 الطيب
➌ 💎السواك
➍💎 لبس الجميل
➎💎 قراءة سورة الكهف
➏💎 التبكير لصلاة الجمعة
➐💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
➊ 🌺መታጠብ
➋ 🌺ሽቶ መቀባት
➌🌺 ሲዋክ መጠቀም
➍ 🌺ጥሩ ልብስ መልበስ
➎ 🌺ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን
➏ 🌺ለጁመዓ ሶላት መጣድ
➐ 🌺በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿〰
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ
🌺በሰለዋት በዚክር ያውለን ያረብ
ﷺ 🌹 .................🌹
ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ🌹🔹🔹🌹
ﷺ ﷺ ﷺ 🌹🔹🔹🌹
በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ !!
https://t.me/abu_hayder_aliy
https://t.me/abu_hayder_aliy
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።
አሏህ ስሙን የሰየመለት ነብይ የሕያ ይባላል ።
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
✨ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ህብረት✨
📜 ልዩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት! 📜
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
🌟 እንኳን ደስ አላችሁ ውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎች! 🌟
በታላቅ ደስታ ና ፍቅር፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲን በመምረጥ እኛን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ላላችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታችንን እናቀርባለን።
🗓 የቅበላ ጊዜና የአቀባበል መርሃ ግብር
የዩኒቨርሲቲያችን የተማሪዎች ቅበላ መርሃ ግብር የሚከናወነው ጥቅምት 3 እና 4 ቀን 2019 ነው።
በእነዚህ ቀናት፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ለእናንተ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሞቅ ያለና ደማቅ አቀባበል ያደርግላችኋል። በሰላም ወደ ግቢ እንድትገቡ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታገኙ የበኩላችንን እንወጣለን።
🤝 የእናንተ ትብብር ያስፈልገናል!
ውድ አዲስ ገቢዎች፣ እኛን በቀላሉ ለማግኘት፣ የተሟላ አገልግሎት ለማግኘት እና የአቀባበል ቡድናችን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግላችሁ፡
የምዝገባ ፎርሙን ይሙሉ:
https://forms.gle/F7gwvpVVsnsj843Z6
ውድ አዲስ ገቢዎች፣ እኛን በቀላሉ ለማግኘት እና የተሟላ አገልግሎት ለመቀበል፣ ማንነታችሁን ሙስሊም መሆናችሁን ለማሳወቅ የቀና ትብብራችሁን በአክብሮት እንጠይቃለን።እንዲሁም ሙስሊም መሆናችሁን ለማሳወቅ በቅድሚያ ከዚህ በታች ባሉት ስልኮች እየደወላችሁ የአቀባበል ቡድናችንን እንድታነጋግሩ በአክብሮት እንጠይቃለን።
📌 የአካባቢ ምደባ ማስታወሻ
ወደ ግቢ ከመምጣታችሁ በፊት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ይለዩ፡-
✅ Natural Science ተማሪዎች፡- ወደ Main Campus ትመጣላችሁ።
✅ Social Science ተማሪዎች፡- ወደ Techno Campus ትመጣላችሁ።
📞 ለግንኙነትና ድጋፍ የስልክ ቁጥሮች
ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ አስፈላጊውን መረጃ ለማግኘት ወይም የአቀባበል ቡድናችንን እንዲቀበሏችሁ ለማድረግ የሚከተሉትን ወንድሞች ማግኘት ትችላላችሁ፡-
📚 Main campus
=>ሀሰን
☎️ 090 632 6702
=>አቡዱረዛቅ
☎️ 0942213321
=>ነቢል
☎️ 096 999 0090
=>ጂፋር
affan orromo
☎️ +251972575000
💻 Techno campu
=>ዐማር ☎️+251925882521
=>መስዑድ affan oromo ☎️ +251937517651
=>አስዓድ ☎️ 0963298664
🧕 ለሴት እህቶች ልዩ ማስታወቂያ: የእህቶችን ስልክ ቁጥር ለምትፈልጉ እህቶች ብቻ፣ በስልክ ቁጥር
☎️ +251925882521
ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።
🌹 አላህ በሰላም ያገናኘን 🤲🌹
🎉መልካም የዩኒቨርሲቲ ቆይታ እንመኛለን!🎉
✨ የደስታችን ተካፋይ ይሁኑ!
— ታላቅ የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ✨
በአላህ ፈቃድ በደሴ ከተማ ልዩና ታላቅ የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶልዎታል!
📅 ቀን፦ እሁድ — ጥቅምት 1 / 2019 ዓ.ል
💢 ቦታ፦ ደሴ — መስጂደ አስ-ሱና
⏰ ሰዓት፦ ከጧቱ — 2:30
🎙 በፕሮግራሙ ላይ የሚገኙ የተከበሩ ዑስታዞች፣ ሸይኾችና ወንድሞች፦
1) ሸይኽ ሙሐመድ መኪን
2) ሸይኽ ሙሐመድ አሚን
3) ሸይኽ ሙሐመድ ኋዛል
4) ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ
5) ሸይኽ ሐሰን አሊ
6)ሸይኽ አሕመድ አወቀ
7) ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ
8) ሸይኽ ይማም ሰዒድ
9) ሸይኽ ሰዒድ ሙሐመድ ሚጢቆሎ)
10)ሸይኽ አብዱልአዚዝ
11)ሸይኽ በድሩዲን ዩሱፍ
12) ሸይኽ ሑሴን ኡመር
13) ሸይኽ ሐሰን ነጃሽ
( ከወንዲሞች)
14) ወንድም ሙርሰል ሰዒድ
15) ወንድም ኢዘዲን ሻፊ
16) ወንድም አቡ ሹራ
17) ወንድም አቡ ሒበቲላህ
18) ወንድም አቡ ሐፍሷ (ይማም)
19) ወንድም አሊ ሰዒድ
20) ወንድም አቡ ኢምራን
(እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው ዑስታዞችና ወንድሞች ይገኛሉ)
📢 ልዩ ጥሪ፦
ይህንን መልእክት ለሌሎች በማጋራትና በዕለቱ በአካል በመገኘት የዚህ ታላቅ በረካና ደስታ ተካፋይ ይሁኑ!
📌 ለሁሉም እንግዶች ጥሪያችን ክፍት ነው!
ቻናልhttps://t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
ግሩፕhttps://t.me/yedesse_selfyochi_group
ሼር ይደረግ‼
♦️♦️♦️የትዳር ውበት በግል ይጠበቃል
ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ…ተስማምታቹኋል አይደል? አደራ መልስ እጠብቃለሁ
📍ገና ወደ ትዳር እንደገባችሁ ለምን የቤታችሁን ውስጣዊ ሕይወት ለሁሉም ለማሳየት ትቸኩላላችሁ?
ወንዱም፦
“የኔ ሚስት እኮ ውብ ናት፣ የዲን እውቀት አላት፣ ታዛዥ ናት፣ አሳቢ ናት… እንደ እሷ ያለች የለችም!”
ሴቷም፦
“የኔ ባል እኮ ቆፍጣና ነው፣ በዲኑ ላይ ጠንካራ ነው፣ ለኔ እንደ አባት ነው፣ እንደ ወንድምም ነው፣ እንዲህ ያለ ባል በማግኘቴ …”
እንዲህ እያላችሁ የቤታችሁን ውስጥ ለምን ለሁሉም ታሳያላችሁ?
ለማን ነው? ምን ለማረጋገጥ ነው?
ሰዎች እንዲያደንቁአችሁ?
እንዲቀኑባችሁ?
ወይስ “የኔ ትዳር እንዲህ ነው” ብላችሁ ለማሳየት?
እስቲ ራሳችሁን ጠይቁ፦
በሚዲያ ላይ የምትጽፉትን ሕይወት በእውነት እየኖራችሁት ነው?
📍ሁሉም እንዲህ ነው አልልም። በእውነት የሚዋደዱ፣ የሚከባበሩ፣ በዲንና በመልካም ሕይወት የሚኖሩ ባለትዳሮች ብዙ ናቸው።
ነገር ግን ከሚናገሩት ተቃራኒ የሚኖሩ፣ በሚዲያ ላይ ፍጹም ትዳር የሚያሳዩ እና በቤታቸው ግን የተለየ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎችም አሉ።
አንዳንዶቹንም ከጥቂት ጊዜ በኋላ በመለያየት ይታያሉ።
ያኔ የሚያሳዝነው መለያየታቸው ብቻ አይደለም፤ ትናንት ለሰዎች ያሳዩት ምስልና ዛሬ የሚኖሩት እውነታ ሲጋጭ መታየቱ ነው።
ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ትዳር መድረክ አይደለም። የሚያጨበጭብልህ ታዳሚ አያስፈልገውም።
📍ትዳር ሁለት ሰዎች በግል የሚገነቡት ቤት ነው። ፍቅሩም በሰዎች አይን ሳይሆን በሁለቱ ልብ ውስጥ የሚኖር ነው።
ሌሎችን ማስተማር ከፈለጋችሁ፣ በግል የቤታችሁን ሚስጥር ከማውጣት ይልቅ ጠቃሚ ምክር ስጡ፦
“ባልና ሚስት እንዲህ ይከባበሩ፣ እንዲህ ይተዛዘኑ፣ ከዚህ ይታቀቡ፣ በዲናቸው ላይ እንዲህ ይተባበሩ…”
ይህ ሌሎችን ይጠቅማል።
📍ነገር ግን የቤታችሁን ሚስጥር፣ የባለቤታችሁን የግል ባሕሪ፣ በእናንተ መካከል ያለውን ልዩ ቅርርብና የግል ነገር ሁሉ ለሰዎች አታውጡ።
ምክንያቱም አንዳንድ ውብ ነገሮች ለማሳየት ሳይሆን ጠበቀን ለናቆያቸው የሚገቡ ናቸው።
የባለቤትህን መልካምነት ለማወቅ ሰዎች ማወቃቸው አያስፈልግም።
የባልሽን መልካምነት ለማድነቅ የሰዎች ማጨብጨብ አያስፈልግም።
እሱ ለአንቺ መልካም ባል ከሆነ፣ አንቺም ለእሱ መልካም ሚስት ከሆንሽ፣ ያ በቂ ነው።
ሰዎች ሳያውቁትም ትዳራችሁ ሊያምር ይችላል።
ሰዎች ሳያደንቁትም ፍቅራችሁ ሊጠነክር ይችላል።
ሰዎች ሳያዩትም ቤታችሁ በሰላም ሊሞላ ይችላል።
እናም አደራ… የግል የሆነን ጉዳይ በሚዲያ ላይ አናውጣ።
ትዳራችሁን ለሰዎች ከማሳየት ይልቅ ለአላህ አስውቡት።
ፍቅራችሁን ለሰዎች ከመናገር ይልቅ እርስ በርሳችሁ ኑሩት።
የቤታችሁን ሚስጥር ለሕዝብ ከመንገር ይልቅ እንደ አደራ ጠብቁት።
ምክንያቱም የትዳር ውበት ሁሉም ሰው ሲያየው አይደለም፤ ባለቤቶቹ ብቻ እያዩት ሲጠብቁት ነው።
ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
