ru
Feedback
የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

Открыть в Telegram

📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!! https://t.me/ibnbaz1212

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
3 433
Подписчики
+4224 часа
+2007 дней
+35230 дней
Архив постов
بسم الله الرحمن الرحيم ​ውድ የሰለፊያ ቻናል ቤተሰቦች፤ ​በተውሂድና በሱና ዙሪያ ጥርት ያለ እውቀት ለማግኘት ቻናላችንን ጆይን (Join) አድርጉ! ​🔗 ለወዳጅ ዘመድዎም ሼር በማድረግ
بسم الله الرحمن الرحيم ​ውድ የሰለፊያ ቻናል ቤተሰቦች፤ ​በተውሂድና በሱና ዙሪያ ጥርት ያለ እውቀት ለማግኘት ቻናላችንን ጆይን (Join) አድርጉ! ​🔗 ለወዳጅ ዘመድዎም ሼር በማድረግ የኸይር ሰበብ ይሁኑ። ​#ተውሂድ #ሱና #ሰለፊያ

👈السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ➤የተከበራችሁ የኢብኑ ባዝ መድረሳ ደርስ ተከታታዮች ነገ ሐሙስ ከፈጅር ሶላት በኋላ የሚሰጠው ደርስ ኢንሻአላህ የዑምደቱል አህካም ኪታብ ይሆናል ።

🚫በወንድማሞች መካከል ምቀኝነትን የሚያስወግዱ 4 ነገሮች❕ ➽ሓቲም አስ'ሶም (237 የሞቱ ) እንዲህ ይላሉ ፦ አራት ነገሮች በወንድማሞች መካከል ምቀኝነትንያስወግዳሉ፦ ➀" በአካል መተጋገዝ ➁ በንግግር መለሳለስ ⓷ በንብረት መተባበር ⓸  በሩቅ ዱዓእ መደራረግ" 📚 አስ'ሶዳቀቱ ወስ'ሰዲቅ (364) 📝ተጨማሪ  ትምህርቶችን   ለማግኘት የቴሌግራም➷➴ Channeሉን  ይቀላቀሉ !!! https://t.me/MisbahMohammed_6682

ልብህ የት ነው?! ምን ላይ ተንጠልጥሏል?! ————— የአደም ልጅ ልብ ሁሉ በአር-ረህማን ሁለት ጣቶች መካከል ነው፣ እንደፈለገ ይገለባብጠዋል። ከፈለግ ያጠመዋል ከፈለገም ቅኑን መንገድ ይመረዋል። የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይህን ሀዲስ በተናገሩ ጊዜ እንዲህ አሉ:- “ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው አላህ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አፅናው።” [ትርሚዚይ 2140 ላይ እና ሌሎችም የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።] ልብ የሚደንቅ የሆነ ባህሪ አላት!። አንዳንዴ ልብ በዱኒያ ላይ ይንጠለጠላል። አንዳንዴ ደግሞ በከፊል በዱኒያዊ ጥቅማጥም ይንጠለጠላል። አንዳንዴ በገንዘብ ይንጠለጠላል፣ ትልቁ ጭንቀቱ ገንዘብ ላይ ይሆናል። አንዳንዴ ደግሞ በሴት ላይ ይንጠለጠላል፣ ትልቁ ጭንቀቱ ሴት ማገኘት ይሆናል። አንዳንዴ ደግሞ በህንፃዎችና ውብ በሆኑ መኖሪያ ቤቶች ላይ ይንጠለጠላል፣ ትልቁ ጭንቀቱ ህንፃና ቤት ላይ ይሆናል። አንዳንዴ ደግሞ መጓጓዣዎች ላይ መኪና ላይ ይሆናል፣ ትልቁ ጭንቀቱም (ዘመናዊ መጓጓዣዎችን ማግኘት) ላይ ይሆናል። ሌላው ደግሞ ልቡ አላህ ላይ ይንጠለጠላል፣ ሁል ጊዜ ከአላህ ጋር ይንጠለጠላል፣ ዱኒያ ሁለመናዋ አላህን ወደ ማምለክና መታዘዝ መዳረሻ ናት ብሎ ያስባል። ዱኒያን አላህን ለማምለክ ለሚረዳው ነገር ይጠቃቀማታል ትንከባከበዋለች፣ ምክንያቱም የተፈጠረችው ለእርሱ ነው። እሱ ግን አይንከባከባትም። የዱኒያ ወዳጆች (ሰዎች) ማለት እነዚያ ዱኒያን የሚንከባከቧትና ዱኒያን ለማግኘት ራሳቸውን ያደከሙት ናቸው። የአኼራ ሰዎች ማለት ደግሞ እነዚያ ዱኒያ እንድትንከባከባቸው ያደረጉና የተንከባከበቻቸው ናቸው። ለዚያም ነው ዱኒያን ሲይዟት አላህ በሚፈቅደው መንገድ እንጂ አይዟትም!። የአላህን ውዴታ በሚያስገኝ ነገር እንጂ አያንቀሳቅሷትም። በአያያዝም ሆነ በአጠቃቀም አላህ በሚወደው መልኩ ያንቀሳቅሷታል። የዱኒያ ወዳጆች ግን እነዚያ ራሳቸውን ለዱኒያ ያደከሙ ናቸው። ሌሊቶችን ይነሳሉ መዝገቦችን ያጠናሉ። እዳ ያለባቸውን ያጠናሉ፣ የተከፈለውን ያጠናሉ፣ በእጃቸው ያለውንና ያገላበጡትን ያጠናሉ። በእውነቱ ከሆነ እነዚህ ዱኒያን ተንከባክበዋታል እንጂ ዱኒያ አልተንከባከበቻቸውም። ነገር ግን አላህ ሪዝቁን ከሰዎች መብቃቂያ ያደረገለት ልቡ የተረጋጋ የሆነ ሰው፣ አላህን ከመታዘዝ የማያምፅበት የሆነን ሪዝቅ አላህ የሰጠው ሰው፣ ይህ ነው ዱኒያ የተንከባከበችው ሰው ማለት። በመሆኑም በሁላችንም በሁሉም ሰኣትና በየ ቅፅበቱ ልባችን ወዴት እንደዞረች ልናጠናትና ልንከታተላት ግዴታ ይሆንብናል። ወዴት እንደሄደች? ለምንድነው ከአላህ የምትዞረው? ለምን ወደ ቀኝና ግራ ትዞራለች? (ብለን ማጥናትና መጠባበቅ ይኖርብናል።) ነገር ግን ሸይጧን በአደም ልጅ የደም ጅማቶች ልክ እንደ ደም በመዘዋወሩ ብዙ ሰዎችን አሸንፏል። ጭራሽ አንዳንድ ሰዎችን ከሁለቱ የምስክርነት ቃል በኋላ ዋና ንብረታቸው ከሆነው ሶላት ሁሉ ልባቸውን እስከ ማዞር ደርሷል። ሶላቱ ውስጥ ከገባ (ከቆመ) በኋላ ልቡ ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ ታገኘዋለህ። [ተፍሲሩል ቁርኣን ኢብኑ ዑሰይሚን 10/22] ✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው አላህ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አፅናው!! የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

‏صورة من حسين عبد الله
‏صورة من حسين عبد الله

"ሆን ብለው ካማሰሉት እንኳን የመንሃጅ ወንድማማችነት ትስስር ድስትም አይረጋም።" አስመሳይነት (ሁለት ፊት፣ ሁለት ምላስ)፣ ሚስጥራዊ የሴራ እና የጥፋት ሰንሰለት ብሎም የወቃሽን ወቀሳ የሚፈራበት ጉዞ የሰለፍዬችን አንድነት ወጥ አማሳይ ወጡን በማማሰል ከሚበጠብጠው በላይ ይበጠብጠዋል። አንድነቱ እንዳይረጋ ከባድ ፀር ይሆናል እናም ኢንተቢሂ ያ አኺ!!! በህብሪተኝነት የምተገነባው መሰረት ሳይሆን የምትንደው መሰረት ብቻ እንዳለ ተገንዝበክ ወደ ቀልብክ መለስ በልና ለሰለፍያም ለነፍስክም ኸይር ሚናን አበርክት። በሰለፍይ ወንድሞች ላይ ከምሰራው ደባና ሴራ አላህን በመፍራት ተቆጠብ።ከጀርባክ ብዙ ምስኪን የሆኑ ሰለፍይ ወንድሞችና እህቶች በዲናቸው ጉዳይ አንተን አምነው እየተከተሉክ ነውና ከአላስፈላጊ እልክ ብሎም ወገንተኝነትና እብሪተኝነት ነፃ ሆነ በፍትህ ላይ ቁም!!! بارك الله فيك ✍أبو معاذ

🚫ታማኝነትን ማጎደል እና ክህደት በጣም አስከፊና እኩይ ተግባራት መካከል ናቸው ከእስልምና ታላላቅና ድንቅ መገለጫዎች አንዱ ቃልኪዳንን ማክበር ለካፊሮችም ቢሆን እንኳ ቃልን መሙላት  ነው። ከሙስሊሞች በጎ ባህሪያት መካከል አለማታለል እነ ታማኝነትን አለማጎደል ይገኙበታል። 👈عن مغيرة بن شعبة -رضي الله عنه-, أنه رافق جماعة من المشركين وكان ذلك في حال شركهم وسافروا إلى مصر في تجارة, وحصلوا على مال فباتوا ليلة، فهجم عليهم فقتلهم وأخذ مالهم, وجاء إلى النبيّ -صلى الله عليه وسلم- مسلمًا وقدَّم له المال، وأخبره بالقصة, فقال -صلى الله عليه وسلم-: أما الإسلام فقد قبلناه, أما المال فإنه مال غدر لا حاجة لنا فيه 📚أخرجه البخاري 2731 ሙጚረህ ቢን ሹዕበህ ረዲየ አላሁ ዐንሁ   ገና በሽርክ ለይ በነበረበት ጊዜ ከመካ ሙሽሪኮች  ጋር ወደ ግብፅ ለንግድ ተጓዙ በዚህ ጉዞዋቸው ብዙ ገንዘብም አተረፉ ሙጚረህ ቢን ሹዕበህ ሌሊት በተኙበት በድንገት ተነስቶ ጥቃት በማድረስ ገደሏቸው ገንዘባቸውን ወሰደ ። ከዚያም ወደ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እስልምናን ተቀብለው በመምጣት ገንዘቡን አቀረቡላቸው የሆነውንም ታሪክ ነገሯቸው ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሏቸው፦‘እስልምናህን ተቀብለነዋል ገንዘቡ ግን በክህደት እነ በማታለል የተገኘ ስለሆነ ገንዘቡ ለይ ምንም ፍላጎት  የለንም።’ 📚ኢማሙል ቡኻሪ 2731 👈أنه كان عهد بين الروم والمسلمين, ولَمَّا أشرف هذا العهد على النهاية تحرك معاوية رضي الله عنه بجيشه يقول: إذا انتهى الوقت المحدد نهجم على العدو، فركب شيخ على فرسه وكان يصيح: الله أكبر وفاء لا غدر, الله أكبر وفاء لا غدر, فسأله معاوية -رضي الله عنه- فقال: سمعت رسول الله -صلى الله عليه وسلم- يقول: «من كان بينه وبين قوم عهد فلا يشد عقدةً ولا يحلها حتى ينقضي أمدها أو ينبذ إليهم على سواء» فتوقف معاوية  -رضي الله عنه 📚أخرجه أحمد (17015) وأبو داود (2759)، والترمذي (1580) وقال: حسن صحيح، وصححه الألباني في الصحيحة (2357). በሮማውያን እና በሙስሊሞች መካከል የሰላም ስምምነት ቃልኪዳን ነበራቸው። ይህ ስምምነት ሊጠናቀቅ ሲቃረብ ሙዓውያህ ረዲየ አላሁ ዐንሁ ከሰራዊቱ ጋር በመንቀሳቀስ "የተወሰነው የስምምነት ጊዜ እንዳበቃ ጠላትን እናጠቃለን" አለ። በዚህ ጊዜ አንድ ሸይኽ በፈረሱ ላይ ሆኖ "አላሁ አክበር! ቃልን ማክበር እንጂ ክህደት የለም! አላሁ አክበር! ቃልን ማክበር እንጂ ክህደት የለም!’ እያሉ ይጮሁ ነበር። ሙዓውያም ጠየቃቸው ፤ ሸይኹም፦ ‘የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም  እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡ “በእርሱና በሕዝቦች መካከል ስምምነት ያለው ሰው፦ ጊዜው እስኪያበቃ ወይም በግልጽ ለሁለቱም ወገን እኩል መሆኑን እስኪያሳውቅ ድረስ ስምምነቱን አይሰርዝም አያፈርስም ።" አላቸው ። ሙዓውያህም ረዲየ አላሁ ዐንሁ ጉዞውን አቆመ። 📚ኢማሙ አሕመድ 17015 📚 ኢማሙ አቡ ዳዉድ 2759 📚አት-ቲርሚዚ 1580 📚ኢማሙ አል'አልባኒ በ‘ሶሒሐህ’ 2357 ላይ ሶሒሕ ብለውታል:: ➽ማታለልና ክህደት ከፊሮችንም ቢሆን አይፈቀድም።በማታለል የተገኘ ገንዘብም ፣ ዝና (እውቅና) እንዲሁም ስልጣን  በእስልምና የተወቀሰ ተግባር ነው ። ➤ማታለልንና ክህደት በምንም ዓይነት ሁኔታ  አይፈቅድም። ➠ በዚህ መልኩ ቃልን ማፍረስ  የአንድ ሙስሊም እስልምና ለይ ትልቅ ግድፈት ነው በዚህ የተነሳ ትልቅ ትችትና ጌታውም ጋ ትልቅ ወንጀል ይሆንበታል ። ➲የባሰ የሚከፋው የዲን እውቀትና ወደ መስተካከል ይጣራል የሚባል አካል በሴራ ሽረባ የአንዱ የልፋት ውጤት የሆነው ለሌላው መስጠትና ባልሰራው ስራ በማወደስ በስራው የደከመውን በማፈናቀል ስሙን በማጥፋት ሌት ተቀን የሚባትነው ነው 📝ተጨማሪ  ትምህርቶችን   ለማግኘት የቴሌግራም➷➴ Channeሉን  ይቀላቀሉ !!! https://t.me/MisbahMohammed_6682

🔷እውነተኛ ሰለፍይ ሐቅ በዞረበት ሁሉ ይዞራል ሸይኽ ዶክተር ሁሴን ብን ሙሐመድ አስስልጢ - ሀፊዞሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "የሰለፎችን መንገድ የሚከተል እውነተኛ ሰለፍይ ሐቅ በዞረበት ሁሉ ይዞራል። ውዳሴን ከሚሰጥ ሰው ይልቅ ፣ በትንታኔ ላይ ተመስርቶ ትችት የሚሰነዝርን ሰው  ያስቀድማል። ከአስረጅና ማስረጃ ባለቤት ጎን ይቆማል።" الجامع لشبهة المميعة ودحضها ص ١٠٦ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

🔷እውነተኛ ሰለፍይ ሐቅ በዞረበት ሁሉ ይዞራል ሸይኽ ዶክተር ሁሴን ብን ሙሐመድ አስስልጢ - ሀፊዞሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "የሰለፎችን መንገድ የሚከተል እውነተኛ ሰለፍይ ሐቅ በዞረበት ሁሉ ይዞራል። ውዳሴን ከሚሰጥ ሰው ይልቅ ፣ በትንታኔ ላይ ተመስርቶ ትችት የሚሰነዝርን ሰው  ያስቀድማል። ከአስረጅና ማስረጃ ባለቤት ጎን ይቆማል።" الجامع لشبهة المميعة ودحضها ص ١٠٦ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

🔷አንድ ሰው ዱዓ ሲያደርግ ወደ አሏህ ለመቃረብ እና ጉዳዩ እንዲፈጸምለት አላማ ያድርግ ሸይኽ አብዱረህማን አስ'ዕድይ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "ተፈላጊውን  ለማግኘትም ይሁን አስፈሪውን ለማስወገድ ጌታውን ለሚማጸን ሰው ፣ እርሱን ለማግኘት ሲል  ዱዓ ባደረገበት ጉዳይ ላይ አላማውና ኒያው ቁንጽል አይሁን። ይልቁንም በዱዓው  ወደአሏህ ለመቃረብና ከፍተኛ ግቡ የሆነውን   ኢባዳ አላማ ያድርግ። ዱዓው እንደሚጠቅመው እርግጠኛ ይሁን - ምክንያቱም ዱዓ የአምልኮ ዋና አስኳሉ ነውና። እርሱ ልብን ወደ አሏህ ይጎትታል ፤ ሀጃው ለአምልኮ ትልቁ ግብ ለሆነው  ለአላህ መተናነስና መዋረድ ይስበዋል። ዱዓ ሲያደርግ  አላማውና ግቡ  ወደ አላህ መቃረብ እና የሚፈልገውን ለማግኘት የሆነ ሰው የሚፈልግውን ለማግኘት ብቻ አላማ ካደረገ ሰው በብዙ የተሟላ ነው - ልክ እንደ በርካታው ሰው ባህሪ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ለዚህ ታልቅ ችሮታ ጉድለትና ክልከላ ነው። ለእንዲህ አይነቱ ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ። ይህ የጠቃሚ እውቀት ፍሬ ነው። ማህይምነት በርካታውን ሰው ታላቅ ከሆነው አላማ ፣ እንዲሁም ውብ ከሆኑ መዳረሻዎች ከልክሎታል። ቢያውቁና ቢገነዘቡ ኖሮ እርሷን አላማ ባደረጉ ፣ ወደርሷ በተዳረሱ ነበር።" مجموع الفوائد واقتناص الأوابد ص ٦٤ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

እወቅ አላህ ይግጠምህና!! ——— ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:- “እወቅ አላህ ይግጠምህና… ጀርህና ተዕዲል ማለት ሸሪዓን ለመጠበቅና ለአላህ ዲን ለመቆርቆር ነው የተደነገገው!!። እውቀቱ አናሳ የሆነ፣ እንዲሁም በዚህ ርእስ የተዘጋጁ ኪታቦች ላይ እውቀቱ አጭር የሆነና የሱንና ሊቃዎንቶች ንግግሮች ላይ አላዋቂ የሆነ ሰው እንደሚያስበው ያለ ግልፅ ማስረጃና በቂ ምክንያት የሰዎችን ክብር ለመተቸት አይደለም!!። = እንዲህ ያለው (በጀርህና ተዕዲል ላይ ግንዛቤው የሳተ ሰው) ያለ ምንም እቅድና ዝግጅት በዘፈቀደና በድፍረት የሚጓዝ፣ ሳይለይ እንደሚያደበላልቅ ዓይነ ስውር ነው።” [አል'ጃሚዕ ሊሹብሃት አል'ሙመይዐህ… ገፅ 3] ✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

🛑ቀጥታ ስርጭት ╰┈➢ ተ ╰┈➢ ጀ ╰┈➢ም ╰┈➢ ሯ ╰┈➢ል 📒 رياض الصالحين من كلام سيد المرسلين 📒ሪያዱ አስ-ሳሊሂን 🎙በኡስታዝ አቡ ኢልሀም ሙሀመድ ኑር (حفظه الله
🛑ቀጥታ ስርጭት              ╰┈➢ ተ                    ╰┈➢ ጀ                         ╰┈➢ም                            ╰┈➢ ሯ                                ╰┈➢ል 📒 رياض الصالحين من كلام سيد المرسلين 📒ሪያዱ አስ-ሳሊሂን 🎙በኡስታዝ አቡ ኢልሀም ሙሀመድ ኑር                           (حفظه الله) https://t.me/sunah123 🕌በአልሙሐጂሪን መድረሳ🕌    https://t.me/sunah123 https://t.me/sunah123

ሳምንታዊ የዳር አስ-ሱንና የእለተ እሁድ ደርስ 🕰 ከረፋዱ 3:50 እስከ ዙህር የሚቆይ በኡስታዝ አቡ ሙዓዝና በኡስታዝ ሻኪር የሚሰጥ ኪታቦች:- ኪታብ ① الحث على المودة والإئتلاف والتحذير من الفرقة والاختلاف በመወዳጀትና በመግባባት ላይ ማነሳሳትና ከልዩነትና ከቡድንተኝነት ማስጠንቀቅ!! لفضيلة الشيخ الدكتور ربيع بن هادي عمير المدخلي رحمه الله የኪታብ pdf ↘️ https://t.me/DarASSunnah1444/15820 🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ - ታጁዲን (ሀፊዘሁላህ) ኪታብ ② كتاب نور التوحيد وظلمات الشرك في ضوء الكتاب والسنة የተውሒድ ብርሃንነትና የሺርክ ጨለማነት በቁርኣንና በሀዲስ ብርሃን ሲቃኝ የኪታብ pdf ↘️ https://t.me/DarASSunnah1444/15819 🎙በኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን (ሀፊዘሁላህ)

" التعليقات الأثرية على شرح عقيدة الواسطية " " አተዕሊቃቱል አሰሪያህ አላ ሸርሂ አቂደቲል ዋሲጢያህ "
አዘጋጅ :- ሸይኽ አህመድ ብን የህያ አንነጂሚ ደርሱን የሚሰጠው :- በሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ክፍል - 24 የባህርዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq የኪታቡ ሊንክ https://t.me/alateriqilhaq/6761 كن على بصيرة

Voice 001_114957203.mp39.37 MB

🚫በሰለፊያ ሚንሓጅ ለይ ያለ ወንድምህን  ቀርቶ ከሚንሓጅ ውጪ ያሉ ሰዎችን እንኳን መበደል አይቻልም። 👉የላቀው ጌታችን እንዲህ ይላል፦ 👈يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ } المائدة ( 8 ) ➳ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ ሕዝቦችንም መጥላት ፍትሕን መጓደል ላይ አይገፋፋችሁ  ፍትሓዊ ሁኑ፡፡ እርሱ ፍትሓዊ መሆን ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው አላህንም ፍሩ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው ፡፡ ➪እናም አንተ ሰውዬ ጥያቄ ልጠይቅህ የምር የሚንሓጅ ሰው ከሆንክ ፦ ➛እንዴት በሚንሓጅ ወንድም ለይ ትዋሽበታለህ ? ➙እንዴት በሚንሓጅ ወንድም ለይ በደልን ተሴራለህ? ➠እንዴት ለሚንሓጅ ወንድምህ ጥሩን ነገር ትጠላለህ ? ➜እንዴት በሚንሓጅ ወንድም ጥሩ እንቅስቃሴ የተነሳ ትታመማለህ ? ➛እንዴት በሚንሓጅ ወንድም ለይ ክፉ ነገረ ስደርስበት ትደሰታለህ ? ➠እንዴት በሚንሓጅ ወንድም ለይ ጓሮ ለጓሮ እየተሽለኮለክ ተሴራለህ  ለምን ውስጥ ለውስጥ ሰላማዊ ወንድሞች በሱ ለይ አቋም ለማስያዝ እየጨቀጨቅክ እረፍት ትነሳቸዋለህ ? ➧ግን አንተ የምር የሚንሓጅ ሰው ነህን ?እውነቴን ነው የምልህ አንተ ጤነኛ ነህ ወይስ ምቀኛ ? ወይስ አስመሳይ የጠላት ቅጥረኛ ነህ ? ➨ዛሬ ለመርሐግብር መሟያ ፍትሕ ፍትሕ እያሉ የሚጮሁ  ውስጥ ለውስጥ ለደረሳቸው መርዝን የሚረጩ ደባን የሚሸርቡ ሰዎች ምን አበዛቸው ❔ጥፋታቸው ሲነገራቸው እነ ከጥፋታችሁ ተመለሱ ስባሉ በማኩረፍ ውስጥ ለውስጥ በማሴር ተንኮል በመሸረብ ወዘተ  ዝም ለማስባልና ከሱና እንደወጣ አድርገው ይዘምቱበታል ።በማን አለብኝነት እንደፈለጉ ለመሆን የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ለራሳቸው ጉዳይ ስሆን አላህን እንፍራ የሚሉ ነገር ግን በሌላ ሰው ጉዳይ ባልሰማ የሚያልፉ ብሎም በክብሩ የሚረማመዱ ከአጥፊዎች ሆነው ስሙን የሚያጠፉ ለይስሙላ አላህን ፍሩ በዮች ፣ የሚያውቁትን እውነታ በመናገር አላህን የማይፈሩ ሰዎች ነገር በጣም ያስፈራል ። ግን ሁሉም ከልኩ አያልፍም ፍትሓዊው የአለማቱ ጌታ አላህ አስተካካዩን ከሚያበላሸው ለይቶ ያውቀዋል ። سوف ترى إذا إنجلى الغبار أفرس تحته أم الحمار ➥በመጨረሻም ልብ ያለው ልብ ይበል 📝join #ቴሌግራም Channeል https://t.me/MisbahMohammed_6682

አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [ Misbah Mohammed ]: 🚫በሰለፊያ ሚንሓጅ ለይ ያለ ወንድምህን  ቀርቶ ከሚንሓጅ ውጪ ያሉ ሰዎችን እንኳን መበደል አይቻልም። 👉የላቀው ጌታችን እንዲህ ይላል፦ 👈يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ } المائدة ( 8 ) ➳ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ ሕዝቦችንም መጥላት ፍትሕን መጓደል ላይ አይገፋፋችሁ  ፍትሓዊ ሁኑ፡፡ እርሱ ፍትሓዊ መሆን ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው አላህንም ፍሩ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው ፡፡ ➪እናም አንተ ሰውዬ ጥያቄ ልጠይቅህ የምር የሚንሓጅ ሰው ከሆንክ ፦ ➛እንዴት በሚንሓጅ ወንድም ለይ ትዋሽበታለህ ? ➙እንዴት በሚንሓጅ ወንድም ለይ በደልን ተሴራለህ? ➠እንዴት ለሚንሓጅ ወንድምህ ጥሩን ነገር ትጠላለህ ? ➜እንዴት በሚንሓጅ ወንድም ጥሩ እንቅስቃሴ የተነሳ ትታመማለህ ? ➛እንዴት በሚንሓጅ ወንድም ለይ ክፉ ነገረ ስደርስበት ትደሰታለህ ? ➠እንዴት በሚንሓጅ ወንድም ለይ ጓሮ ለጓሮ እየተሽለኮለክ ተሴራለህ  ለምን ውስጥ ለውስጥ ሰላማዊ ወንድሞች በሱ ለይ አቋም ለማስያዝ እየጨቀጨቅክ እረፍት ትነሳቸዋለህ ? ➧ግን አንተ የምር የሚንሓጅ ሰው ነህን ?እውነቴን ነው የምልህ አንተ ጤነኛ ነህ ወይስ ምቀኛ ? ወይስ አስመሳይ የጠላት ቅጥረኛ ነህ ? ➨ዛሬ ለመርሐግብር መሟያ ፍትሕ ፍትሕ እያሉ የሚጮሁ  ውስጥ ለውስጥ ለደረሳቸው መርዝን የሚረጩ ደባን የሚሸርቡ ሰዎች ምን አበዛቸው ❔ጥፋታቸው ሲነገራቸው እነ ከጥፋታችሁ ተመለሱ ስባሉ በማኩረፍ ውስጥ ለውስጥ በማሴር ተንኮል በመሸረብ ወዘተ  ዝም ለማስባልና ከሱና እንደወጣ አድርገው ይዘምቱበታል ።በማን አለብኝነት እንደፈለጉ ለመሆን የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ለራሳቸው ጉዳይ ስሆን አላህን እንፍራ የሚሉ ነገር ግን በሌላ ሰው ጉዳይ ባልሰማ የሚያልፉ ብሎም በክብሩ የሚረማመዱ ከአጥፊዎች ሆነው ስሙን የሚያጠፉ ለይስሙላ አላህን ፍሩ በዮች ፣ የሚያውቁትን እውነታ በመናገር አላህን የማይፈሩ ሰዎች ነገር በጣም ያስፈራል ። ግን ሁሉም ከልኩ አያልፍም ፍትሓዊው የአለማቱ ጌታ አላህ አስተካካዩን ከሚያበላሸው ለይቶ ያውቀዋል ። سوف ترى إذا إنجلى الغبار أفرس تحته أم الحمار ➥በመጨረሻም ልብ ያለው ልብ ይበል 📝join #ቴሌግራም Channeል https://t.me/MisbahMohammed_6682