የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ
Открыть в Telegram
📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!! https://t.me/ibnbaz1212
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
2 028
Подписчики
+1624 часа
+1987 дней
+47730 день
Архив постов
2 038
🌟 ታላቅ የደዓዋ ፕሮግራም 🌟
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
አስደሳች ዜና ዛሬ ዕለተ እሁድ ከምሽቱ 3:00 እስከ 6:00 ሰአት(በኢትዮ) የውዱ ወንድማችን ሙሒዲን እና የእህታችን ራህመት የኒካህ ፕሮግራም ታሳቢ በማድረግ ልዩ የሆነ የደዓዋ ፕሮግራም መዘጋጀቱን በደስታ እናበስራለን።
ለዚህ ልዩ ፕሮግራም ተጋባዥ እንግዶቻችን፦
🎙 ሸይኽ አህመድ (ከአዲስ አበባ)
🎙 ኡስታዝ አቡ ፋሩቅ (ከአዲስ አበባ)
🎙 ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ (ከወራቤ)
🎙 ኡስታዝ ዐብዱረዛቅ (ከሁልባረግ)
🎙 ኡስታዝ አቡ ኑሁ (ከወራቤ)
🎙 ኡስታዝ ጁሃር (ከወራቤ)
🎙 ኡስታዝ አቡ ዐብዱልሐሊም (ከወራቤ)
🎙 ኡስታዝ አቡ ፈርሃን (ከወራቤ)
🎙 ኡስታዝ አቡ ሚፍታሕ (ከሐረር)
🎙 ይህን በጉጉት የሚጠበቀውን ፕሮግራም በጣፋጭ አንደበቱ እያዋዛ የሚመራው ውዱ ኡስታዝ አቡ ሙስሊም (ከዱባይ) ይሆናል።
እንዲሁም፦
✨ በተወዳጁ ወንድማችን አቡ ማኢዳ አቡኪ ልዩ የሆነ ግጥም ይቀርብልናል።
📌 ቦታ፦ በመድረሰቱ አልፊርቀቲናጂያ የወንዶች የቂርአት መሀከል ኢሞ ግሩፕ
📅 ቀን፦ እሁድ ግንቦት 23/2018
⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ለሊቱ 6:00 ሰዓት
"መልካምን ነገር አመላካች እንደ ሰሪው ነውና" ለሌሎች በማጋራት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ! መቅረት በፍፁም አይፈቀድም!
🔗 የኢሞ ግሩፕ ሊንኩን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/ibnbaz1212/120
2 038
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
አስደሳች ዜና ዛሬ የውዱ ወንድማችን ሙሒዲን እና የእህታችን ራህመት የኒካህ ፕሮግራም ታሳቢ በማድረግ ልዩ የሆነ የደዓዋ ፕሮግራም መዘጋጀቱን በደስታ እናበስራለን።
Click the link to join us! https://s.imoim.net/4JiEzp?from=copy_link
2 038
Repost from ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa
እውነተኛ ሱኒይ የሆነ ሰው የቢድዐ ሰው ሲነካ አይቆጣም!!
—————
እውነተኛና በአላህ ዲን ላይ ፅናት ያለው ሱኒይ (ሰለፊይ) የሆነ ሰው ለየትኛውም ስሜታዊ (ቢድዐና ሙብተዲዕ) ለሆነ አካል መነካት አይቆጣም!!።
ሁመይድ ኢብኑ ሙንሂብ (ረሂመሁላህ) አንድ ሰው አባበክር ኢብን ዐያሽን እንዲህ ብሎ ሲጠይቀው ሰምቻለሁ አለ:- “አባበክር ሆይ! ሱኒይ ማለት ማን ነው? አባበክርም እንደሚከተለው መለሱ:- ስለ ስሜት (የስሜት ባለ ቤት በክፉ) ሲጠቀስ አንዳችም የማይወግን የሆነ አካል ነው። አሉ” [ሸርህ ኡሱል ኢዕቲቃድ አህሊሱና አላለካኢይ 1/82]
በአሽ-ሸሪዐህ ዘገባ አቡበክር ኢብኑ ዐያሽ እንዲህ ብለዋል:- “ሱኒይ ማለት እርሱ ፊት ስለ ቢድዐ ሲወሳ የማይቆጣ ነው።” [አሽ-ሸሪዐህ ሊል ኣጁሪ 5/550]
ሱኒይ ሰለፊይ የሆነ አካል ሺርክና ቢድዐ ሲስፋፋ፣ አላህ እርም ያደረጋቸው ነገሮች ሲደፈሩ ይቆጣል!!። ሱኒይ ሰለፊይ የሆነ ሰው ስለ ሺርክና ቢድዐ ባለየ ቤቶች ከመናገር ተቆጥበናል አይልም!!።
ኢብኑ ዐሳኪር - ረሂመሁላህ - ታሪኹ ዲመሽቅ በተሰኘው ኪታባቸው ከዑቅባ ኢብኑ ዐልቀመህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ የሚል ዘግቧል:- “አርጣአ ኢብኑል ሙንዚር ዘንድ ነበርኩና ከተቀማመጡ ሰዎች ከፊላቸው እንዲህ አለ:- ከሱና ሰዎች ጋር የሚቀማመጥና የሚቀላቀል ሆኖ ሳለ፣ ስለ ቢድዐ ሰዎች ሲወሳ ደግሞ ተውን! ስለነሱ እዚህ አታውሩ። የሚል ስለሆነ ሰው ምንትላላችሁ? አለ፣ አርጠአ ኢንዲህ በማለት መለሰ:- እሱ ከነርሱ ጋር ነው (ከቢድዐ ሰዎች ነው) የእርሱን ነገር አያምታታባችሁ፣ አለ። አልቀማ - ረሂመሁላህ- የአርጠአን ንግግር በወቅቱ አልተቀበልኩትምና ወደ ታላቁ ሰለፍ ኢማሙል አውዛዒይ - ረሂመሁላህ- ዘንድ ሄድኩኝ አሉ። አውዛዒይ ደግሞ እንዲህ ያለ ነገር ከደረሰው ግልፅልፅ የማድረግ ልዩ ተሰጥኦ የነበረው ገላጭ ሰው ነበር። (ጉዳዩን ሳወሳለትም) አውዛዒይ:- አርጠአ እውነት አለ፣ (የተናገረው እውነት ነው)፣ ይህ ስለነሱ ከመናገር ይከለክላልን?፣ ታዲያ እነሱን በመጥቀስ ጠንከር ካልተባለ መች ነው ከነሱ ማስጠንቀቅ የሚቻለው?!።” [ታሪኹ ዲመሽቅ 8/15]
ኢማሙል አውዛዒ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “አንድ ሰው ከቢድዐ ባለቤት ጋር ሲጓዝ አይተሀው፣ (የዚያን የቢድዐ ሰው) አስተሳሰብ እንደማይቀበለው በመሃላ አስረግጦ ቢነግርህ እንኳ እውነት ብለህ አትቀበለው!።”
አቡ ሷሊህ አል-ፈራእ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አለ:- ለዩሱፍ ኢብኑ አስባጥ ስለ ወኪዕ አንስቼ የተወሰነች ስለተከሰተች ፊትና አወራሁት፣ ይህን ጊዜ ዩሱፍ እሱ ራሱ እንደ ኡስታዙ ነው አለኝ፣ (ኡስታዙ ሀሰን ኢብኑ ሀይን) ማለቱ ነው። ለዩሱፍም መልሼ ይህ ሀሜት እንዳይሆን አትፈራም? አልኩት፣ አንተ ሞኝ እንዴት ሀሜት ይሆናል?፣ እኔ እኮ ለእነዚህ ከወላጆቻቸው የበለጠ መልካም ነኝ!፣ እኔ እነሱ በፈጠሩት አዲስ ፈጠራ (ቢድዐ) ሰዎች ተከትለዋቸው እንዳይሰሩበትና በወንጀሉም ተጠያቂ እንዳይሆኑ ነው የምከላከለው፣ እነሱን ከፍ ከፍ እያደረገ የሚያወድሳቸው ሰው በነሱ ላይ እጅግ በጣም አደገኛ ነው!፣ አለ።” [አስ-ሰይር 7/364]
ትክክለኛ ሱኒይ ሰለፊይ የሆነ ሰው ስለ አህሉል ቢድዐህ እና ከቢድዐህ ሰዎች መደረግ ስላለበት ተመዩዝ ሲነገር አይጨንቀውም!! ልቡ አይጠብም!!
✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን 👇👇 #join ያድርጉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
2 038
Repost from የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
🔷ይቅር ያለ ፣ (ስራዎቹን) ያሳመረ ምንዳው በአላህ ላይ ነው
ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል ፡ -
“ነፍስ አንድ ሰው የበደለውን አካል ይቅር ማለቱን በዳዩ በእርሱ ላይ እንዲዳፈር ያደርገዋል በማለት ለእርሱ ትሸልምለታለች፡፡ ነገሩ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡
በትክክለኛ ሐዲስ ከረሱል - ዓለይሶላቱ ወሰላም - የሚከተለው ተዘግቧል:-
“በእነርሱ ላይ (በአሏህ) የምምልላችሁ ሶስት ነገሮች አሉ ፡ ይቅር ማለት ለባሪያ አይጨምርለትም ፣ ልቅናን እንጅ ፤ መመጽዎት ገንዘብን አይቀንሰውም ፤ ማንም ሰው ራሱን ለአላህ ብሎ ዝቅ አያደርግም ፣ አላህ ከፍ የሚያደርገው ቢሆን እንጅ”
በመበቀል ከሚያገኘው ልቅና በይቅርታ የሚያገኘው ክብር ለእሱ የበለጠ የተወደደ ለእርሱም በጣም ጠቃሚው ነው፡፡ ምክንያቱም መበቀል በውጭ ልቅና ቢመስልም በውስጥ ውርደትን ያወርሰዋል፡፡ ይቅር ማለት ግን በውጭ ውርደት ቢመስልም በውስጡ ልቅናን ያወርሰዋል፡፡
القواعيد النورانية : 1/ 483-484
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة
2 038
Repost from قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
فمن عفا وأصلح فأجره على الله
قال شيخ الإسلام ابن تيمية — رحمه الله —:«وَالْإِنْسَانُ تُزَيِّنُ لَهُ نَفْسُهُ أَنَّ عَفْوَهُ عَنْ ظَالِمِهِ يُجَرِّئُهُ عَلَيْهِ، وَلَيْسَ كَذَلِكَ؛ فَقَدْ ثَبَتَ عَنْهُ ﷺ فِي الصَّحِيحِ أَنَّهُ قَالَ: «ثَلَاثٌ إِنْ كُنْتُ لَحَالِفًا عَلَيْهِنَّ: مَا زَادَ اللَّهُ عَبْدًا بِالْعَفْوِ إِلَّا عِزًّا، وَمَا نَقَصَتْ صَدَقَةٌ مِنْ مَالٍ، وَمَا تَوَاضَعَ أَحَدٌ لِلَّهِ إِلَّا رَفَعَهُ اللَّهُ». فَالْعِزُّ الْحَاصِلُ لَهُ بِالْعَفْوِ أَحَبُّ إِلَيْهِ وَأَنْفَعُ لَهُ مِنَ الْعِزِّ الْحَاصِلِ لَهُ بِالِانْتِقَامِ؛ فَإِنَّ هَذَا عِزٌّ فِي الظَّاهِرِ، وَهُوَ يُورِثُ ذُلًّا فِي الْبَاطِنِ، وَالْعَفْوُ ذُلٌّ فِي الظَّاهِرِ، وَهُوَ يُورِثُ عِزًّا فِي الْبَاطِنِ».
«القواعد النورانية» (١/ ٤٨٣–٤٨٤).
الله اكبر الله اكبر لا اله الا الله والله أكبر الله أكبر ولله الحمد
الله اكبر الله اكبر الله اكبر كبيرا
2 038
Repost from አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [ Misbah Mohammed ]
🟢❝ የዒዱና የአያሙ አትተሽሪቅ ቀናቶች የመደሰቻ የዚክር የጫወታ ቀናቶች ናቸው❞
➢ አያሙ ተሽሪቅ የሚባሉት ቀናት ከእርዱ ቀን በመቀጠል ያሉ ሶስቱ ቀናቶች ናቸው።
☑️وعن عُقبَة بن عامرٍ رضي الله عنه قال قال رسول الله ﷺ يومُ عرفةَ ويوم النحرِ وأيامُ التشريقِ عيدنا أهل الإسلامِ وهي أيامُ أكلٍ وشربٍ
📚رواه الترمذي 773 وصححه الألبانيُ
➧ ዑቅበተ ቢን ዓሚር በስተላለፈው ሀዲስ
ረሱል ﷺ እንዲህ አሉ
➽የአረፋ ቀን ፣ የዒዱ ቀንና አያሙ አትተሽሪቅ የእኛ የኢስላም ባልተቤቶች አመት በዓሎቻችን ናቸው
እነሱም የመብላትና የመጠጣት ቀኖቻችን ናቸው ።
📚እማሙ አትቲርሚዚይ ዘግበውታል ( 773 )
እማሙ አልባኒይ ሷሂህ ብለውታል
☑️ عن مسعود بن الحكم عن أمه أنها رأت وهي بمنى في زمان رسول الله ﷺ راكبا يقول أيها الناس إنها أيام أكل وشربٍ ونساء وبعال وذكر الله قالت قلت من هذ ؟ قالوا علي بن ابي طالب ،
أخرجه النسائي في الكبرى 2878
➤ መስዑድ ቢን ሐኪም ከእናቱ ይዞ እሷ እናቱ በረሱል ዘመን ሚና ላይ በግመል ላይ ሆኖ እንዲህ የሚል ሰው አየች እናንተ ሰዎች ሆይ እነዚህ
( የአያሙ አትተሽሪቅ ) ቀናቶች የመብላት ፣ የመጠጣት ፣ ባሎች ከሚስቶቻቸው የሚጫወቱበት ፣ ሚስቶች የባሎቻቸውን ሀቅ መጠበቅን የሚያሳምሩበት እነ አላህን የሚያስታውሱበት ቀናት ናቸው ስል
➼ ማን ነው ይህን የሚናገረው ?
ስትል ጠየቀች ዐሊ ቢን አቢይ ጣሊብ ነው ተባለች ።
📚እማሙ አንነሳኢይ አንነሳኢይ አልኩብራ ለይ ዘግበዉታል ( 2878 )
يقول ابن الحجر رحمه الله تعالى
• إظهار السرور في الأعياد من شعائر الدين
📚فتح الباري 2/443
ሐፊዝ ኢብን ሐጀር ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላሉ ፦
በባዐል ቀናት ደስታን መግለጽ ከዲን መገለጫዎች መካከል ነው ።
➤ ኡዱህያ እርድ ማረድ የሚቻልበት ግዜ የሚያበቀው የቅዳሜ ቀን ፀሐይ ስትገባ ነው ።
➤ ተክቢራውም የሚቀጥለው እስከ ቅዳሜ ቀን ዐስር ሶላት ድረስ ነው
የቴሌግራም ቻነል➷➴➘➷➴➘➷➴➘
https://t.me/MisbahMohammed_66822 038
التهنئة: وإن كان الأفضل بعد الصلاة، إلا أنه لا بأس بها ليلة العيد؛ لأن التهنئة تخضع للعادات والناس فيها في سعة.
2 038
Repost from ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa
የሁለቱን ዒዶች ስርኣት የሚመለከቱ ጥቂት ነጥቦች ከማስረጃዎቻቸው ጋር
—————ክፍል 2
የተክቢራ አደራረግንና የዒድ ሶላት አሰጋገድን ያካተተ
ክፍል 1 ለማግኘት ⤵️
https://t.me/IbnShifa/6788
ሴቶች የዒድ ሶላት ወደ ሚሰገድበት ቦታ ሲወጡ…
»-» ሴቶች ሲወጡ ማንኛውም አይነት ማራኪ ሽታ ያለውን ነገር መቀባትና ጌጣ ጌጥ ያለውን ልብስ ለብሰው መውጣት ሀራም ይሆንባቸዋል። ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) የሴቶችን ወደ ዒድ ቦታ መውጣት በተመለከተ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ:- “ሴቶች የዒድ ቦታ ላይ ማንኛውም አይነት ሽታ ያለውን ነገር ሳይጠቀሙ፣ የጌጣ ጌጥና የዝነኞችን ልብስ ሳይለብሱ ቢወጡ ችግር የለውም። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋልና:- ምንም አይነት ሽታ ያለውን ነገር ሳይጠቀሙ ይውጡ…።” [ተውዲሁል አህካም ሸርህ ቡሉግ…]
ይህ በሴቶች ላይ የተቀመጠ መስፈርት ነው። ይህን መስፈርት ስሜቴንና ሸይጧንን አሸንፌ ማሟላት አልችልም የምትል ሴት ከቤቷ ትቀመጥ!። ወደ ዒድ ቦታዎች እየወጣች ለጌታቸው ሊሰግዱና ጌታቸውን አላህን ሊያወድሱ የወጡ ወንዶችን ወንጀል ውስጥ እየጣለች ለራሷም ወንጀል ሸምታ ከመግባት ልትቆጠብ ይገባል!!። ሽቶ ተቀብተውና ተጋግጠው የሚወጡ እህቶች አላህን ሊፈሩት ይገባል!!። በደስታ ቀን አላህን ከማመፅ ሊቆጠቡ ይገባል። እህቴ ሆይ! በደስታ ቀን አላህን ካመፅሽ በዱኒያና ነገ በጭንቁ ቀን ጭንቀት እንዳይጨምርልሽና ስቃይሽን እንዳያበረታው ልትፈሪና ልትጠነቀቂ ይገባል!!
እህቴ ወደ ዒድ ቦታ መውጣት ከፈለግሽ ሽቶና ዲዮድራንት… መሰል ነገሮችን ከመቀባት ርቀሽ፣ የሰውነት ቅርፅሽን የሚያሳዩ የተጣበቁና የተጋጌጡ ልብሶችን አሽቀንጥረሽ ጥለሽ ሰፋፊ ሸሪዓዊ አለባበስ ለብሰሽ ድምፅሽን አጥፍተሽ ወጥተሽ አምላክሽን አላህን አወድሰሽና አልቀሽ ለእርሱም ሰግደሽ ተመለሺ። ይህን ማድረግ ካልቻልሽ ግን አላህን ፈርተሽ ቤትሽ ይስፋሽ!!።
»-» ወደ ዒድ ቦታ ሲኬድ ድምፅን ከፍ አድርጎ ተክቢራ ማለት ተደንግጓል። አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል:-
وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
«ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)፡፡» አል-በቀረህ 185
ከዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ተይዞ፣ የአላህ መልእክተኛ ﷺ በሁለቱ ዒዶች ከፈድል ኢብኑ ዐባስ፣ ከዐብደላህ፣ ከዐባስ፣ ከዐሊይ፣ ከጀዕፈር፣ ከሀሰንና ሁሰይን፣ ከኡሳማ ኢብኑ ዘይድ፣ ከዘይድ ኢብኑ ሃሪሰህ፣ ከአይመን ኢብን ኡሙ አይመን (ረዲየላሁ ዐንሁም) ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ተክቢርና ተህሊል እያሉ ይወጡ ነበር። [በይሀቂይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ በኢርዋእ አልገሊል 3/123 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]
የተክቢራውን አደራረግ በተመለከተ ከነቢዩ ﷺ የተረጋገጠ ሶሂህ የሆነ ዘገባ የለም። ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ግን የሚከተለውን የተክቢራ አይነት ይጠቀም እንደነበር ተረጋግጧል:- “አላሁ አክበር አላሁ አክበር፣ ላ! ኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር አላሁ አክበር ወ ሊላሂል ሀምድ” [ኢብኑ አቢ ሸይባ በሶሂህ ሰነድ ዘግበውታል።]
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስም እንደሚከተለው ይል እንደነበር ተዘግቧል:- “አላሁ አክበር አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር ወ ሊላሂል ሀምድ፣ አላሁ አክበር ወ አጀልሉ፣ አላሁ አክበር ዐላ ማ ሐዳና” [በይሀቂይ ሶሂህ በሆነ ሰነድ ዘግበውታል።]
»-» የተክቢራ ጊዜን በተመለከተ የዒደል ፊጥር ተክቢራ የዒዱን ቀን ተሰግዶ እስኪያበቃ ነው። የዒዱል አድሃ ተክቢራ ደግሞ ከዐረፋ ንጋት ሶላት ጀምሮ በተከታታይ አያሙ ተሽሪቅ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው። (የውሙ ዐረፋ ማለት ከዙል ሒጃ 9ኛው ቀን ነው።) ይህ አጠቃላይ ሰለፎች፣ ሶሃባዎች፣ አራቱ መሪዎችና ፉቅሃዎች የተጓዙበት መንገድ ነው። [ሶሂህ ፊቅህ አስ-ሱና አቡ ማሊክ ከማል]
»-» አንዳንድ ሰዎች ዒድ ሚሰገድበት ቦታ ሲደርሱ ሱና ብለው ይሰግዳሉ። ይህ ትልቅ ስህተት ነው። ለሁለቱም ዒዶች ከፊታቸውም ሆነ ከኋላቸው ሱና ሶላት የላቸውም። ነገር ግን ነቢዩ ﷺ ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ 2ረከዓ ይሰግዱ ነበር። ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከዒድ በፊት ምንም አይሰግዱም ነበር፣ ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር።” [ኢብን ማጀህ 1076 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ነው ብለውታል።] ለሁለቱም ዒዶች አዛንም ሆነ ኢቃም ማለት የለም።
»-» የዒድ ሶላት የአሰጋገድ ሁኔታን በተመለከተ እንደሚከተለው ነው:- የዒድ ሶላት 2ረከዓ ነው። ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብሏል:- “የተጓዥ (የጉዞ) ሶላት 2ረካዓ ነው። የዒደል አድሃ ሶላትና የዒደል ፊጥር ሶላትም ሁለት ሁለት ረከዓ ነው። እርሱም አጥሮ ሳይሆን ሙሉው ነው 2ረከዓ በነቢያችሁ አንደበት የተደነገገ ነው።” [ነሳኢይ እና ኢማሙ አህመድ የዘገቡት ሲሆን ሀዲሱም ሶሂህ ነው።]
» የመጀመሪያውን ረከዓ ልክ እንደሌላው ሶላት በኢህራም ተክቢራ ይጀምራል። ከዚያ በኋላ ሰባት ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል። ሰባቱ ተክቢራ በሚደረግበት ወቅ እጅ ማንሳቱ ከነቢዩ ﷺ የተረጋገጠ ነገር የለም። ነገር ግን ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር የነቢዩን ﷺ ሱንና አጥብቆ የሚከተል ከመሆኑም ጋር በሰባቱም ተክቢራ ጊዜ እጁን ያነሳ ነበር ይላል። ሌላው በየ ተክቢራው መሃል የሚባል ዚክር ከነቢዩ ﷺ የተረጋገጠ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ነቢዩ ﷺ በየ ተክቢራው መሃል "አላህን ያወድሱም ያመሰግኑም ነበር” ብሏል። [በይሀቂ የዘገቡት ሲሆን ሰነዱ ሀሰን ነው።]
ከሰባቱ ተክቢራዎች በኋላ ፋቲሃ ይቀራል ከዚያም ሱራዎች ይቀራሉ። ተወዳጅ ሱራዎች "ቃፍ፣ ወል ቁርኣኒል መጂድ፣ የሚለውና ኢቅተረበቲ ሰኣቱ… እንዲሁም ሰቢህ እስመ ረቢከል አዕላና ሐል አታከ ሀዲሱል ጋሺየህ…" ሱራዎች ናቸው። [ሙስሊምና ነሳኢይ ሌሎችም ዘግበውታል።]
ከዚያም በሁለተኛው ረከዓ ተነስቶ ለመቆም ከሚለው ተክቢራ ውጭ አምስት ተክቢራዎችን ይላል። ከዚያ በኋላ ልክ በመጀመሪያው ረከዓ እንዳደረገው ፋቲሃን እና ሌሎችን ሱራዎች ይቀራል። ከዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ተይዞ፣ “የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዒደል ፊጥርና በዒደል አድሃ ሶላት በመጀመሪያው ረከዓ ሰባት ተክቢራዎችን በሁለተኛው ረከዓ ደግሞ አምስት ተክቢራዎችን ይሉ ነበር።” ብላለች። [አቡዳውድ የዘገቡት ሲሆን ሀዲሱም ሶሂህ ነው።] በመጨረሻም ከተሸሁድ በኋላ ያሰላምታል።
»-» ወደ ዒድ ቦታ ከተጓዙባቸው መንገዶች በተቃራኒ መንገድ መመለስ ሱንና ነው። ከጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ እንዲህ አለ:- “ነቢዩ ﷺ የዒድ ቀን ከሆነ በተቃራኒ መንገድ ይጓዙ ነበር።” [ቡኻሪ ዘግበውታል] አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- “ነቢዩ ﷺ ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ ከወጡ መጀመሪያ ከወጡበት መንገድ በተቃራኒው ይመለሱ ነበር።” [ኢብን ማጀህ ዘግበውታል]
አላህ ዒዳችንን አላህን የምንታዘዝበትና አላህ በሚፈቅደው መልኩ የምንደሰትበት ዒድ ያድርግልን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን👇👇 #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
2 038
Repost from አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [ Misbah Mohammed ]
"ኩራተኛ ጀነት አይገባም!"
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
«በልቡ ውስጥ የብናኝ ያክል ኩራት ያለበት ሰው ጀነት አይገባም።»
📔[ሶሒሕ ሙስሊም፡ 91]https://t.me/HussinAssilty/3250
2 038
Repost from Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}
📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!!
https://t.me/ibnbaz1212
