fa
Feedback
የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

رفتن به کانال در Telegram

📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!! https://t.me/ibnbaz1212

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
3 440
مشترکین
+4224 ساعت
+2007 روز
+35230 روز
آرشیو پست ها
+1
ልዩ የዐቂዳ ደርስ 📚 የሚቀራው ሪሳላ:- ለሸይኽ ዱክቱር አቡ ሙዓዝ ሀሰን ኢብን ዓሊ አልመርዳዊ አልዒራቂይ የሆነችው: "ከኢማሙ አሕመድ ኡሱሉ ሱንና የተውጣጡ አጫጭር ጠቃሚ ዐቂዳዊ ት/ቶችና መንሀጃዊ መርሆዎች" "مختصر الفوائد العقدية والقواعد المنهجية المستنبطة من أصول السنة للإمام أحمد" pdf للشيخ: أبو معاذ حسن بن علي المرداوي العراقي Pdf ⤵️⤵️ https://t.me/ibnbaz1212/353 ⏯ ክፍል 00 (መግቢያ) በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ነጥቦች: —ስለሪሳላዋ  ትውውቅ —የኡሱሉ ሱና ይዘት ጥቅል ዳሰሳ —ሸይኽ አቡ ሙዓዝን በሚመለከት —የኢማሙ አህመድ አጭር ታሪክ... 🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ   📆ዕለተ ጁሙዓ ሰፈር 03, 1448          🕌 በመድረሰቱል ኢኽላስ ለሁልባረግ የሴቶች ጀመዓ የተሰጠ ኮርስ የቴሌግራም ቻነል https://t.me/ibnbaz1212

🔷የተረጋጋች ነፍስ ነፍስ በጌታዋ ከተረጋጋች ፣ እርሱን በማስታወስ ካረፈች ፣  ጸጸት አድርጋ ወደርሱ ከተመለሰች ፣ እርሱን ለመገናኘት ከናፈቀች ፣ ወደእርሱ በመቅረቧ ከተጽናናች ሰላም ትሆናለች። እንዲህ አይነቷ ነፍስ ስትሞት እንዲህ ትባላለች :- يَا أَيَّتُهَا النَّفْسُ الْمُطْمَئِنَّةُ ارْجِعِي إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِيَةً مَّرْضِيَّةً  "(ለአመነች ነፍስም) «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ! «ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡" (ፈጅር :27-28) ኢብን አባስ እንዲህ ብለዋል :- "አንች የረካሽው ነፍስ ሆይ!" - "አማኝ የሆነች ነፍስ" ማለት ነው። ቀታዳ እንዲህ አለ :- "አንች የረካሽው ነፍስ ሆይ!" - "እርሷ አማኝ ሆና ፤ አላህ ቃል በገባው ነገር የረካች ነፍስ" ማለት ነው። ሐሰን እንዲህ አለ:- "አንች የረካሽው ነፍስ ሆይ!" - "አላህ በተናገረው የረካች ፣ እውነት ያለች ነፍስ" ማለት ነው። ሙጃሂድ እንዲህ አለ :- "አንች የረካሽው ነፍስ ሆይ!" -   "ጌታዋ አሏህ መሆኑን ያረጋገጠች ፣ ወደርሱ የተጸጸተች ፣ ለእርሱ የተዋደቀች ፣ እርሱን እንደምትገናኝ ያረጋገጠች ትሁት ነፍስ" ማለት ነው። طب القلوب  (ص/٨٠) https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

Share 'مختصر الفوائد العقدية والقواعد المنهجية المستنبطة من أصول السنة للإمام .pdf'

قال الله تعالى: يا أيها الذين آمنوا اتقوا الله وكونوا مع الصادقين قال ابن تيمية : "الصدقُ مُستَلزم للعدل والإحسان إلى الخلق، ومن جُمِعَ فيه الصدقُ والعَدلُ والإحسانُ؛ لم يَكن ممّن يُخزِيه الله!. [ينظر شرح العقيدة الأصبهانية: (٢/٦٦٦)]

🔷አህለሱናዎች ተዋደዱ ከሸይኽ ረቢዕ - ረሂመሁሏህ - መልዕክት "እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ ፣ ወንድማማች ሁኑ። በኢስላማዊ ስነ-ምግባርና ስርዓት ተከባበሩ። እርስ በርሳችሁ ምህረትና ርህራሄ አሳዩ። ምክንያቱም የፈጠራና የስህተት ባለቤቶች ፣ የተለያዩ የእምነት አንጃዎች  በሱና ሰዎች ላይ አንድ ሆነው እየተዋጉ ነው። ሀዳድያ የሱና ሰዎችን በመዋጋት የአንበሳውን ድርሻ ይዟል። ነገር ግን አሏህ ቀደም ሲል ጦራቸውን እንደሰበረው - ኢንሻአሏህ - አሁንም ይሰብራል በኋላም ይሰብራል።" المجموع ٤٤٣/٩ العلامة ربيع بن هادي عمير https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

‏صورة من حسين عبد الله
‏صورة من حسين عبد الله

بسم الله الرحمن الرحيم ​ውድ የሰለፊያ ቻናል ቤተሰቦች፤ ​በተውሂድና በሱና ዙሪያ ጥርት ያለ እውቀት ለማግኘት ቻናላችንን ጆይን (Join) አድርጉ! ​🔗 ለወዳጅ ዘመድዎም ሼር በማድረግ
بسم الله الرحمن الرحيم ​ውድ የሰለፊያ ቻናል ቤተሰቦች፤ ​በተውሂድና በሱና ዙሪያ ጥርት ያለ እውቀት ለማግኘት ቻናላችንን ጆይን (Join) አድርጉ! ​🔗 ለወዳጅ ዘመድዎም ሼር በማድረግ የኸይር ሰበብ ይሁኑ። ​#ተውሂድ #ሱና #ሰለፊያ

👈السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ➤የተከበራችሁ የኢብኑ ባዝ መድረሳ ደርስ ተከታታዮች ነገ ሐሙስ ከፈጅር ሶላት በኋላ የሚሰጠው ደርስ ኢንሻአላህ የዑምደቱል አህካም ኪታብ ይሆናል ።

🚫በወንድማሞች መካከል ምቀኝነትን የሚያስወግዱ 4 ነገሮች❕ ➽ሓቲም አስ'ሶም (237 የሞቱ ) እንዲህ ይላሉ ፦ አራት ነገሮች በወንድማሞች መካከል ምቀኝነትንያስወግዳሉ፦ ➀" በአካል መተጋገዝ ➁ በንግግር መለሳለስ ⓷ በንብረት መተባበር ⓸  በሩቅ ዱዓእ መደራረግ" 📚 አስ'ሶዳቀቱ ወስ'ሰዲቅ (364) 📝ተጨማሪ  ትምህርቶችን   ለማግኘት የቴሌግራም➷➴ Channeሉን  ይቀላቀሉ !!! https://t.me/MisbahMohammed_6682

ልብህ የት ነው?! ምን ላይ ተንጠልጥሏል?! ————— የአደም ልጅ ልብ ሁሉ በአር-ረህማን ሁለት ጣቶች መካከል ነው፣ እንደፈለገ ይገለባብጠዋል። ከፈለግ ያጠመዋል ከፈለገም ቅኑን መንገድ ይመረዋል። የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይህን ሀዲስ በተናገሩ ጊዜ እንዲህ አሉ:- “ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው አላህ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አፅናው።” [ትርሚዚይ 2140 ላይ እና ሌሎችም የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።] ልብ የሚደንቅ የሆነ ባህሪ አላት!። አንዳንዴ ልብ በዱኒያ ላይ ይንጠለጠላል። አንዳንዴ ደግሞ በከፊል በዱኒያዊ ጥቅማጥም ይንጠለጠላል። አንዳንዴ በገንዘብ ይንጠለጠላል፣ ትልቁ ጭንቀቱ ገንዘብ ላይ ይሆናል። አንዳንዴ ደግሞ በሴት ላይ ይንጠለጠላል፣ ትልቁ ጭንቀቱ ሴት ማገኘት ይሆናል። አንዳንዴ ደግሞ በህንፃዎችና ውብ በሆኑ መኖሪያ ቤቶች ላይ ይንጠለጠላል፣ ትልቁ ጭንቀቱ ህንፃና ቤት ላይ ይሆናል። አንዳንዴ ደግሞ መጓጓዣዎች ላይ መኪና ላይ ይሆናል፣ ትልቁ ጭንቀቱም (ዘመናዊ መጓጓዣዎችን ማግኘት) ላይ ይሆናል። ሌላው ደግሞ ልቡ አላህ ላይ ይንጠለጠላል፣ ሁል ጊዜ ከአላህ ጋር ይንጠለጠላል፣ ዱኒያ ሁለመናዋ አላህን ወደ ማምለክና መታዘዝ መዳረሻ ናት ብሎ ያስባል። ዱኒያን አላህን ለማምለክ ለሚረዳው ነገር ይጠቃቀማታል ትንከባከበዋለች፣ ምክንያቱም የተፈጠረችው ለእርሱ ነው። እሱ ግን አይንከባከባትም። የዱኒያ ወዳጆች (ሰዎች) ማለት እነዚያ ዱኒያን የሚንከባከቧትና ዱኒያን ለማግኘት ራሳቸውን ያደከሙት ናቸው። የአኼራ ሰዎች ማለት ደግሞ እነዚያ ዱኒያ እንድትንከባከባቸው ያደረጉና የተንከባከበቻቸው ናቸው። ለዚያም ነው ዱኒያን ሲይዟት አላህ በሚፈቅደው መንገድ እንጂ አይዟትም!። የአላህን ውዴታ በሚያስገኝ ነገር እንጂ አያንቀሳቅሷትም። በአያያዝም ሆነ በአጠቃቀም አላህ በሚወደው መልኩ ያንቀሳቅሷታል። የዱኒያ ወዳጆች ግን እነዚያ ራሳቸውን ለዱኒያ ያደከሙ ናቸው። ሌሊቶችን ይነሳሉ መዝገቦችን ያጠናሉ። እዳ ያለባቸውን ያጠናሉ፣ የተከፈለውን ያጠናሉ፣ በእጃቸው ያለውንና ያገላበጡትን ያጠናሉ። በእውነቱ ከሆነ እነዚህ ዱኒያን ተንከባክበዋታል እንጂ ዱኒያ አልተንከባከበቻቸውም። ነገር ግን አላህ ሪዝቁን ከሰዎች መብቃቂያ ያደረገለት ልቡ የተረጋጋ የሆነ ሰው፣ አላህን ከመታዘዝ የማያምፅበት የሆነን ሪዝቅ አላህ የሰጠው ሰው፣ ይህ ነው ዱኒያ የተንከባከበችው ሰው ማለት። በመሆኑም በሁላችንም በሁሉም ሰኣትና በየ ቅፅበቱ ልባችን ወዴት እንደዞረች ልናጠናትና ልንከታተላት ግዴታ ይሆንብናል። ወዴት እንደሄደች? ለምንድነው ከአላህ የምትዞረው? ለምን ወደ ቀኝና ግራ ትዞራለች? (ብለን ማጥናትና መጠባበቅ ይኖርብናል።) ነገር ግን ሸይጧን በአደም ልጅ የደም ጅማቶች ልክ እንደ ደም በመዘዋወሩ ብዙ ሰዎችን አሸንፏል። ጭራሽ አንዳንድ ሰዎችን ከሁለቱ የምስክርነት ቃል በኋላ ዋና ንብረታቸው ከሆነው ሶላት ሁሉ ልባቸውን እስከ ማዞር ደርሷል። ሶላቱ ውስጥ ከገባ (ከቆመ) በኋላ ልቡ ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ ታገኘዋለህ። [ተፍሲሩል ቁርኣን ኢብኑ ዑሰይሚን 10/22] ✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው አላህ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አፅናው!! የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

‏صورة من حسين عبد الله
‏صورة من حسين عبد الله

"ሆን ብለው ካማሰሉት እንኳን የመንሃጅ ወንድማማችነት ትስስር ድስትም አይረጋም።" አስመሳይነት (ሁለት ፊት፣ ሁለት ምላስ)፣ ሚስጥራዊ የሴራ እና የጥፋት ሰንሰለት ብሎም የወቃሽን ወቀሳ የሚፈራበት ጉዞ የሰለፍዬችን አንድነት ወጥ አማሳይ ወጡን በማማሰል ከሚበጠብጠው በላይ ይበጠብጠዋል። አንድነቱ እንዳይረጋ ከባድ ፀር ይሆናል እናም ኢንተቢሂ ያ አኺ!!! በህብሪተኝነት የምተገነባው መሰረት ሳይሆን የምትንደው መሰረት ብቻ እንዳለ ተገንዝበክ ወደ ቀልብክ መለስ በልና ለሰለፍያም ለነፍስክም ኸይር ሚናን አበርክት። በሰለፍይ ወንድሞች ላይ ከምሰራው ደባና ሴራ አላህን በመፍራት ተቆጠብ።ከጀርባክ ብዙ ምስኪን የሆኑ ሰለፍይ ወንድሞችና እህቶች በዲናቸው ጉዳይ አንተን አምነው እየተከተሉክ ነውና ከአላስፈላጊ እልክ ብሎም ወገንተኝነትና እብሪተኝነት ነፃ ሆነ በፍትህ ላይ ቁም!!! بارك الله فيك ✍أبو معاذ

🚫ታማኝነትን ማጎደል እና ክህደት በጣም አስከፊና እኩይ ተግባራት መካከል ናቸው ከእስልምና ታላላቅና ድንቅ መገለጫዎች አንዱ ቃልኪዳንን ማክበር ለካፊሮችም ቢሆን እንኳ ቃልን መሙላት  ነው። ከሙስሊሞች በጎ ባህሪያት መካከል አለማታለል እነ ታማኝነትን አለማጎደል ይገኙበታል። 👈عن مغيرة بن شعبة -رضي الله عنه-, أنه رافق جماعة من المشركين وكان ذلك في حال شركهم وسافروا إلى مصر في تجارة, وحصلوا على مال فباتوا ليلة، فهجم عليهم فقتلهم وأخذ مالهم, وجاء إلى النبيّ -صلى الله عليه وسلم- مسلمًا وقدَّم له المال، وأخبره بالقصة, فقال -صلى الله عليه وسلم-: أما الإسلام فقد قبلناه, أما المال فإنه مال غدر لا حاجة لنا فيه 📚أخرجه البخاري 2731 ሙጚረህ ቢን ሹዕበህ ረዲየ አላሁ ዐንሁ   ገና በሽርክ ለይ በነበረበት ጊዜ ከመካ ሙሽሪኮች  ጋር ወደ ግብፅ ለንግድ ተጓዙ በዚህ ጉዞዋቸው ብዙ ገንዘብም አተረፉ ሙጚረህ ቢን ሹዕበህ ሌሊት በተኙበት በድንገት ተነስቶ ጥቃት በማድረስ ገደሏቸው ገንዘባቸውን ወሰደ ። ከዚያም ወደ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እስልምናን ተቀብለው በመምጣት ገንዘቡን አቀረቡላቸው የሆነውንም ታሪክ ነገሯቸው ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሏቸው፦‘እስልምናህን ተቀብለነዋል ገንዘቡ ግን በክህደት እነ በማታለል የተገኘ ስለሆነ ገንዘቡ ለይ ምንም ፍላጎት  የለንም።’ 📚ኢማሙል ቡኻሪ 2731 👈أنه كان عهد بين الروم والمسلمين, ولَمَّا أشرف هذا العهد على النهاية تحرك معاوية رضي الله عنه بجيشه يقول: إذا انتهى الوقت المحدد نهجم على العدو، فركب شيخ على فرسه وكان يصيح: الله أكبر وفاء لا غدر, الله أكبر وفاء لا غدر, فسأله معاوية -رضي الله عنه- فقال: سمعت رسول الله -صلى الله عليه وسلم- يقول: «من كان بينه وبين قوم عهد فلا يشد عقدةً ولا يحلها حتى ينقضي أمدها أو ينبذ إليهم على سواء» فتوقف معاوية  -رضي الله عنه 📚أخرجه أحمد (17015) وأبو داود (2759)، والترمذي (1580) وقال: حسن صحيح، وصححه الألباني في الصحيحة (2357). በሮማውያን እና በሙስሊሞች መካከል የሰላም ስምምነት ቃልኪዳን ነበራቸው። ይህ ስምምነት ሊጠናቀቅ ሲቃረብ ሙዓውያህ ረዲየ አላሁ ዐንሁ ከሰራዊቱ ጋር በመንቀሳቀስ "የተወሰነው የስምምነት ጊዜ እንዳበቃ ጠላትን እናጠቃለን" አለ። በዚህ ጊዜ አንድ ሸይኽ በፈረሱ ላይ ሆኖ "አላሁ አክበር! ቃልን ማክበር እንጂ ክህደት የለም! አላሁ አክበር! ቃልን ማክበር እንጂ ክህደት የለም!’ እያሉ ይጮሁ ነበር። ሙዓውያም ጠየቃቸው ፤ ሸይኹም፦ ‘የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም  እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡ “በእርሱና በሕዝቦች መካከል ስምምነት ያለው ሰው፦ ጊዜው እስኪያበቃ ወይም በግልጽ ለሁለቱም ወገን እኩል መሆኑን እስኪያሳውቅ ድረስ ስምምነቱን አይሰርዝም አያፈርስም ።" አላቸው ። ሙዓውያህም ረዲየ አላሁ ዐንሁ ጉዞውን አቆመ። 📚ኢማሙ አሕመድ 17015 📚 ኢማሙ አቡ ዳዉድ 2759 📚አት-ቲርሚዚ 1580 📚ኢማሙ አል'አልባኒ በ‘ሶሒሐህ’ 2357 ላይ ሶሒሕ ብለውታል:: ➽ማታለልና ክህደት ከፊሮችንም ቢሆን አይፈቀድም።በማታለል የተገኘ ገንዘብም ፣ ዝና (እውቅና) እንዲሁም ስልጣን  በእስልምና የተወቀሰ ተግባር ነው ። ➤ማታለልንና ክህደት በምንም ዓይነት ሁኔታ  አይፈቅድም። ➠ በዚህ መልኩ ቃልን ማፍረስ  የአንድ ሙስሊም እስልምና ለይ ትልቅ ግድፈት ነው በዚህ የተነሳ ትልቅ ትችትና ጌታውም ጋ ትልቅ ወንጀል ይሆንበታል ። ➲የባሰ የሚከፋው የዲን እውቀትና ወደ መስተካከል ይጣራል የሚባል አካል በሴራ ሽረባ የአንዱ የልፋት ውጤት የሆነው ለሌላው መስጠትና ባልሰራው ስራ በማወደስ በስራው የደከመውን በማፈናቀል ስሙን በማጥፋት ሌት ተቀን የሚባትነው ነው 📝ተጨማሪ  ትምህርቶችን   ለማግኘት የቴሌግራም➷➴ Channeሉን  ይቀላቀሉ !!! https://t.me/MisbahMohammed_6682

🔷እውነተኛ ሰለፍይ ሐቅ በዞረበት ሁሉ ይዞራል ሸይኽ ዶክተር ሁሴን ብን ሙሐመድ አስስልጢ - ሀፊዞሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "የሰለፎችን መንገድ የሚከተል እውነተኛ ሰለፍይ ሐቅ በዞረበት ሁሉ ይዞራል። ውዳሴን ከሚሰጥ ሰው ይልቅ ፣ በትንታኔ ላይ ተመስርቶ ትችት የሚሰነዝርን ሰው  ያስቀድማል። ከአስረጅና ማስረጃ ባለቤት ጎን ይቆማል።" الجامع لشبهة المميعة ودحضها ص ١٠٦ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

🔷እውነተኛ ሰለፍይ ሐቅ በዞረበት ሁሉ ይዞራል ሸይኽ ዶክተር ሁሴን ብን ሙሐመድ አስስልጢ - ሀፊዞሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "የሰለፎችን መንገድ የሚከተል እውነተኛ ሰለፍይ ሐቅ በዞረበት ሁሉ ይዞራል። ውዳሴን ከሚሰጥ ሰው ይልቅ ፣ በትንታኔ ላይ ተመስርቶ ትችት የሚሰነዝርን ሰው  ያስቀድማል። ከአስረጅና ማስረጃ ባለቤት ጎን ይቆማል።" الجامع لشبهة المميعة ودحضها ص ١٠٦ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

🔷አንድ ሰው ዱዓ ሲያደርግ ወደ አሏህ ለመቃረብ እና ጉዳዩ እንዲፈጸምለት አላማ ያድርግ ሸይኽ አብዱረህማን አስ'ዕድይ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "ተፈላጊውን  ለማግኘትም ይሁን አስፈሪውን ለማስወገድ ጌታውን ለሚማጸን ሰው ፣ እርሱን ለማግኘት ሲል  ዱዓ ባደረገበት ጉዳይ ላይ አላማውና ኒያው ቁንጽል አይሁን። ይልቁንም በዱዓው  ወደአሏህ ለመቃረብና ከፍተኛ ግቡ የሆነውን   ኢባዳ አላማ ያድርግ። ዱዓው እንደሚጠቅመው እርግጠኛ ይሁን - ምክንያቱም ዱዓ የአምልኮ ዋና አስኳሉ ነውና። እርሱ ልብን ወደ አሏህ ይጎትታል ፤ ሀጃው ለአምልኮ ትልቁ ግብ ለሆነው  ለአላህ መተናነስና መዋረድ ይስበዋል። ዱዓ ሲያደርግ  አላማውና ግቡ  ወደ አላህ መቃረብ እና የሚፈልገውን ለማግኘት የሆነ ሰው የሚፈልግውን ለማግኘት ብቻ አላማ ካደረገ ሰው በብዙ የተሟላ ነው - ልክ እንደ በርካታው ሰው ባህሪ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ለዚህ ታልቅ ችሮታ ጉድለትና ክልከላ ነው። ለእንዲህ አይነቱ ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ። ይህ የጠቃሚ እውቀት ፍሬ ነው። ማህይምነት በርካታውን ሰው ታላቅ ከሆነው አላማ ፣ እንዲሁም ውብ ከሆኑ መዳረሻዎች ከልክሎታል። ቢያውቁና ቢገነዘቡ ኖሮ እርሷን አላማ ባደረጉ ፣ ወደርሷ በተዳረሱ ነበር።" مجموع الفوائد واقتناص الأوابد ص ٦٤ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة