🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
Открыть в Telegram
Больше
Страна не указанаКатегория не указана
1 381
Подписчики
+624 часа
+3437 дней
+63530 дней
Архив постов
የአሏህ መልእክተኛ ሰለላሁአለይሂ ወሰላም እንድህ አሉ
*ሳቅን አታብዙ ብዙ ሳቅ ልብን ይገላል*
_ኢብኑ ማጅህ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል_
አንድ እናት ለልጇ እንድህ ስትል መከረች
እየውልህ ልጀ ከባድ የሆኑ ነገሮችን ፊትለፊት ተጋፈጣቸው ብዙተማሪወች የቀለላቸውንና የሚያውቁትን ነገር ደጋግመው ማንበብ ይመርጣሉ ምክናየቱም ያንን ሲያነቡ ብዙ ያወቁ ይመስላቸውና እኔኮ ሁሉንም አውቀዋለሁ የሚል በራስ የመተማመን የውሸት ስሜት ይሰጣቸዋል
ነገር ግን ከባድ የሆነውን እና የማይረዱትን ትምህርት ሲያው ስለሚጨንቃቸው ይሸሹታል
እናማ ልጀ የሚከብድህን ነገር ደጋግመህ አድርገው ምክናየቱም እድገትህ የተሸሸገው እዛ እከበደህ ነገር ውስጥ ነው፡፡
ምነኛ ድንቅ የሆነ ምክር ነው ቁርአን ከበደን ብለን ስንቶቻችን ነን ሸሽተን የተውነው ኪታብ ጀምረን ስንቶቻችንን ነን አይገባኝም ብለን በመንገድ የቀረነው
ስንቶቻችን ነን ሙሲባ ሲደርስብን የሙሲባችን አጅር በሶብር ውስጥ ሆኖ ሳለ ሶብርን አተን ከአሏህ ጋር የተጣላነው
መልሱን ከራሳችን ለራሳችን ፡፡
_ተደዋውለን ለረጅም ስአት ስላላወሩን!
በየሥቶሪያቸው በየፕሮፋይላቸው ማሬ ውደ የኔልዩ ጓደኛ ስላላሉን!
ተመቻችቶላቸው ስጦታስላልሰጡን!
ስለኛአይጨነቁም አያስቡም ማለትአይደለም
ስንቶች አሉ በአፍደልለው በተግባር *ዜሮየሆኑ* ስንቶችስ ናቸው ሲያሽቃብጡልን በስቶሪ በፕሮፋይል እንዳ እንዳልሰቀሉን እንደዛ እንዳላመገሱን በአንድ ስህተታችን ገደል የሰደዱን
*ደግሞስ* በተቃራኒው ስንቶች አሉ ማሰባቸውን መጨነቃቸውን በልባቸው ደብቀው ለችግራችን ቀድመው የሚደርሱ ከወደቅንበት የሚያነሱን፡፡ አሏህ ሆይ የአፍ ከልባቸው ተዋደው ውደታቸውን በተግባር ከሚያሳዩ ባሮችህ አድርገን
ስናደርግም ያደርጉልናል ብለን ሳይሆን ከአንተ ዘንድ የማያልቀውን አጅር ፈልገን የምናደርግ አድርገን
```መልካም መሆን ለራስነውና ለምናውቀውም ለማናውቀውም በቻልነው መልካም እንሁን መልካምነት ይከፍለናልጅ አንከፍልበትም፡፡```_
📚በኮበልቻው ኮርስ ላይ የሚቀሩ ኪታቦች🌿📚
ይህ ደውራ በሐበሻ ምድር ለምትገኙ የእውቀት ፈላጊዎችና የሱና ወዳጆች የቀረበ ታላቅ የምስራችና መለኮታዊ ስጦታ ነው! የጥንቁቅ ሰለፎችን ፈለግ የተከተሉ የዒልምና የዚክር መድረኮችን ለሚናፍቁ፣ በሱና ጥማት ለደረቁ ልቦች እነሆ የዒልም
ብርሃን በሀገራችሁ መጥቶላችኋል።
በኮንቦልቻ ከተማ የሚካሄደውን ታላቅና የተባረከ የዒልም ዑደት (ደውራ) ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው፦
🏛️ ቦታ– ኮምቦልቻ ከተማ – መስጂደል አንሷር ነው
ይሄን ኮርስ የሚሰጡት ታዋቂው የሐዲስ ሊቅ፣ አስተማሪና መካሪው ሸይኽ አል-ሙሐዲስ አቡል ሐሰን ዐሊ ቢን አሕመድ አል-ራዚሒ (አላህ ይጠብቃቸው) ናቸው።
ሸይኹ በሐዲስ፣ በዐቂዳና በመንሐጅ ዙሪያ ጠቃሚ የሆኑ እውቀቶችንና መሠረታዊ ግንዛቤዎችን በሚከተሉት ኪታቦች ማብራሪያ አማካኝነት ለተማሪዎች ያካፍላሉ፦
📚በኮርሱ ላይ የሚቀሩ የኮርሱ ኪታቦች
1️⃣ «ኑኽበቱል ፊከር» «نخبة الفكر في مصطلح أهل الأثر»
(በሐዲስ የቃላት መፍቻ/መስፈርት ዙሪያ) – በታላቁ የሐዲስ ሊቅ ኢብኑ ሐጀር አል-ዐስቀላኒ።
2️⃣ «አል-ቀዋዒዱል ሙስላ» «القواعد المثلى في صفات الله وأسمائه الحسنى»
(ስለ አላህ ውብ ስሞችና ባህሪያት) – በታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን።
3️⃣ «መታ የኩኑ አር-ረጁሉ ሚን አህሊስ-ሱና» متى يكون الرجل من أهل السنة وبمَ يخرج منها»:
(አንድ ሰው መቼ ከሱና ሰዎች ይመደባል? በምንስ ይወጣል?) – በታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐብዲላህ አል-ኢማም ተፅፎ፣ በሸይኽ ዐሊ አል-ራዚሒ ሸርህ የተደረገው።
⚠️ እነዚህ ኪታቦች በቤታችሁ ያሏችሁ ይዛችሁ ኑቶሎ ለሌላችሁ ደግሞ ኪታቦችን ስላዘጋጄን እኛ እንሰጣችኋለን ምንም ክፍያ የለውም
🎙️ በተጨማሪም በመድረኩ ላይ የተለያዩ ታላላቅ መሻይኾችና የእውቀት ተማሪዎች የሚሳተፉባቸው ወቅታዊ ምክሮችና የዒልም ውይይቶች ይካሄዳሉ።
🌱 የዒልም ፈላጊ ሆይ! ና ተቀላቀል።
🌱 የሐዲስና የአሠር ተማሪ ሆይ! ዕድሉን ተጠቀም።
🌱 የሱና ወዳጅ ሆይ! ለመገኘትና
ለመቅሰም ትጉ።
የሸይኽ አል-ሙሐዲስ ዐሊ ቢን አሕመድ አል-ራዚሒ በእነዚህ ቀናት በሀገራችን መገኘት እጅግ ውድ አጋጣሚ ነው። እርሳቸው ለነቢዩ (ﷺ) ሐዲሶች ባላቸው ጥንቃቄ፣ ለሱና ባላቸው ጽናትና ትክክለኛውን የሰለፊያ ደዕዋ በማሰራጨት የሚታወቁ በመሆናቸው፤ ማንኛውም ተማሪ ይህንን ታላቅ ዕድል ሊያመልጠው አይገባም።
📅 የደውራው ጊዜ፦ ከቅዳሜ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀን የሚቆይ ይሆናል።
🕌 ይሄ ጥሪ፦ ለሁሉም ሙስሊሞች
ክፍት ነው። ለሴቶችም በቂ ቦታ አለን
አላህ ይህንን የዒልም መድረክ የተባረከ እንዲያደርግልን፣ ሸይኻችንንም በጤናና በስኬት እንዲጠብቅልን እንለምነዋለን። ይህ ደውራ ጠቃሚ እውቀት የሚሰራጭበት፣ ሱና ሕያው የሚሆንበት፣ ቢድዓና መከፋፈል የሚከሽፍበት ሰበብ እንዲሆን ምኞታችን ነው። ለዚህ ስራ አስተዋጽኦ ላደረጉ፣ ላገዙና ለጠቆሙትም አላህ ታላቅ ምንዳን ይክፈላቸው።
ይሄን ፕሮግራም በLIVE መካታተል ለምትፈልጉ በዚህ በሌሎችም ቻናሎች ይተላለፋል፦
🌹t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
🌹t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
📣 ታላቅ ብስራት የደውራ ፕሮግራም ጥሪ!
✅ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የአንሷር መስጂድ ለ 4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ እጅግ ደማቅ እና ታላቅ የኮርስ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለመላው ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች ጥሪውን ያቀርባል።
📚 የፕሮግራሙ ልዩ እንግዳ፦
ታላቁ የ-የመን ሙሓዲስ ፈደይለቱ ሸይኽ ዐሊ አል-ራዚሒ (ሀፊዘሁላህ) —(በየመን የሚገኘውና በርካታ ተማሪዎችን ያፈራው የታዋቂው የመዕበር መርከዝ አስተማሪ)
◈እንድሁም ትልቁ አባታችን ፈደይለቱ ሸይኽ ሙሳ አል-ቀጧን (ሀፊዘሁላህ) ይገኛሉ።
🎙️ በፕሮግራሙ ላይ የሚታደሙ መሻይኾች እና ኡስታዞች፦
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ መኪን ከደሴ
▪️ ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ይማም ሰዒድ ከደሴ
▪️ ሸይኽ አሕመድ አወቀ ከደሴ
▪️ ሸይኽ በድሩ ዩሱፍ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሁሴን ከቢስቲማ
▪️ ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሐሰን አሊ ቃዲ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሁሰይን አቡ ሶላሑዲን ከደሴ
▪️ ሸይኽ አወል አሕመድ መነዮ ከመረሳ
▪️ ሸይኽ አወል አህመድ ከከሚሴ
▪️ሸይኽ ዒሳ አደም ከደሴ
🔸 ዶክተር /ኡ ሁሴን አሊ ከከላላ
🔸 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ከአ.አበባ
🔸 ዶክተር/ኡ ሰዒድ ሙሳ ከአ.አበባ
🔸 ኡስታዝ ኸድር አሕመድ ከከሚሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሒዛም ከአዳማ
🔸 ኡስታዝ ዐብደሽኩር ከአሶሳ
🔸ኡስታዝ ዐብዱሰላም ሐሰን ከአዳማ
🔸 ኡስታዝ አቡ ዒምራን ከሀርቡ
🔸 ኡስታዝ አቡ አዩብ ከኮቦልቻ
🔸 ኡስታዝ ሙርሰል ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሻኪር ከኮንቦልቻ
🔸 ኡስታዝ አቡ ረያን ከመርሳ
🔸ኡስታዝ መሀመድ አያሌው ከወልዲያ
🔸ኡስታዝ አቡ ዓብዱ ረዛቅ ጅረሳ ከመርሳ
🔸 ኡስታዝ አቡ ዑበይዳ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ ዐብዱልመሊክ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሐሳን ከኮቦልቻ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሃኒፋ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ መ/ሲራጁ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ ዐሊይ ሰይድ ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አንሷር መሀመድ ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሐፍሷ ከደሴ
🔸ኡስታዝ ጀውሀር ክፍሌ ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ዐብዲረሕማን ከመርሳ
🔸 ኡስታዝ አቡል መዓሊ ከመርሳ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሹራ ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ማሂ ከኮንቦልቻ
🔸 ወንድም አቡ ሂበቲላህ ከደሴ
👥 የአንሷር መስጅድ ኢማምና ጀመዓዎቹ ባጠቃላይ...
👤እንዲሁም ሌሎች ከተለያየ ሀገር በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው መሻይኾችና ኡስታዞችም በቦታው ይገኛሉ!
📆 የፕሮግራሙ ቀናት፦
የመጀመሪያ ቀን፦ ሰኔ 6/2018 (ከፊታችን ቅዳሜ ጧት 3:00) ጀምሮ ለ 4 ተከታታይ ቀናት ይቆያል።
🏘 ማሳሰቢያ፦
ለታዳሚዎች በቂ የምግብ እና የመኝታ ቦታ ተዘጋጅቷል።—የሌሊት ብርድ ልብስ ይዛችሁ ብትመጡ መልካም ነው።—
🤩በእነዚህ የቴሌ ግራም አድራሻ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ ይመዝገቡ፦
📝ኡስታዝ አቡ ሻኪራ አህመድኑር
@Abuhureirehonline
0923467646
📝 ኡስታዝ አቡ ዐዩብ
092 588 7118
@Attewhid11
📝 ወንድም አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን
@Abu_Hibetillah_Al_aseriy
0942819970
💙የቦታው አቅጣጫ ካስቸገራችሁ በነዚህ የእንግዳ ተቀባይ ወንድሞች ስልክ ቁጥሮች ላይ ይደውሉ፡
📞 ወንድም አንዋር
0916582567
📞 ወንድም አቡ አማር
0913803997
📞 ወንድም ሰኢድ
0935568513
ጥብቅ ማሳሰቢያ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
የቴሌግራም ሃከሮች (ጠላፊዎች) በሚሊኩት ሊንክ አትግቡ የሳይበር ጥቃት ሰለባ አትሁኑ;
በሰሞኑ ብዙን ሰው ጠልፎ በግሩፖች ላይ አፀያፊ ፋይሎችን እየለቀቁ ነው
ተጠንቀቁ
Share አዳርሱት
❤️🔥❤️🔥❤️🔥❤️🔥❤️🔥❤️🔥
የሰዋ ሸሪሃ ያላችሁ ካርድ እምፈልጉ የተሞላ የባለ 100 "ካርድ የተነየተ የንያ ገንዘብ አለ ባረከላሁ ፊኩም የምፈልጉ ኑ
@umureyan_33👇
አንዳንድ ጊዜ «ኡስታዝ» ወይም «ቀርተዋል»ከሚባሉ ወገኖች ይልቅ፣ የሸሪዓ እውቀት የሌላቸው ተራ ሰዎች ለአላህ ህግጋት ይበልጥ ሲጠነቀቁና ሲፈሩ
ይስተዋላል።
የዋሁና ተራው ማህበረሰብ ፣ ለአላህ ህግጋት ያለው ታዛዥነት የንጹህ ልብ ውጤት ነው። «ይህ ነገር ሀራምነው» ሲባል፣ ለመሸሽ ቀዳዳ አይፈልግም፤ ህጉን ለማለፍ ሰበብ አይደረድርም። «ሀራም ነው» ከተባለ ሀራም ነው—አራት ነጥብ።ጥቂት እውቀት አለኝ የሚለው ግን፣ ሀራሙን ሀላል ለማድረግ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ይጓዛል።
እንዲሁም በማህበረሰቡ እይታ «ዱርዬ» ተብሎ የተናቀው፣ ውጫዊ ምግባሩ ያልተስተካከለው ግለሰብ፣ የእምነቱ ክብር ሲነካ ግን እንደ አንበሳ ተቆጥቶ ከፊት ሲቆም ታየዋለህ።
በእርግጥም፣ ጉዳዩ የልብ ነው!
🙌
ከማቃለ አቡ ሶፍያን
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ሰዋ ካርድ ከኔጋ አለ የምፈልጉ በዉስጥ አናግሩኝ
የ20 የ57 አለ
@Riiche1
Repost from ስለ ቀልባችን
ክፍል--7--
📚 የኪታቡ ስም፦
❞ذَمُّ قَسْوَةِ الْقَلْب❝
(የቀልብ መድረቅ አደገኝነት፣ መንስኤውና መፍትሔው)
🎙 በኡስታዝ፦ ዐብዱ ረዛቅ አል-ባጂ (ሐፊዘሁላህ)
➡️ t.me/Sle_qelbachn1
ናልኝ በማለዳ ሀላሌ
ፅሀይ ስትወጣ ሲነጋ ማለዳ
ወደቤቴ መተህ ሁንልኝ እንግዳ
ደስ ያለችው ፅሀይ የጨረር ውበቷ
ከበሬ ፊት ለፊት ሲሆን ጥልማሞቷ
ወደ ፅሀይ ስታይ በደስታ ፈክተህ
እኔም ልቁምና ደስ ብሎኝ ልይህ
የናፈቁ አይኖቸ የተንከራተቱት
እንደ ጅረት ውሀ ሁሌ የሚጓዙት
ከደጀ ላይ ሁነህ ከበሬ ፊት ለፊት
በደስታ ልይህ ናልኝ በወጋገት
በስስት እያዬሁ በድምፄ ልጠራህ
ናልኘ በማለዳ አይኖችህን ልይህ
ናልኝ ልይህ እና ይውጣልኝ ናፍቆቴ
በማለዳ መተህ ግባ ወደ ቤቴ
*አለች አፍቃሪዋ🙌*
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
የጓደኝነት መስፈርቶች
———
አል ፈቂህ ኢብኑ ጁዚይ አል'ማሊኪይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
የጓደኝነት መስፈርቶችማ ሰባት ናቸው
1ኛ, በእምነቱ ሱኒይ ሊሆን ግድ ነው።
2ኛ, በዲኑ ላይ አላህን የሚፈራ ሊሆን ነው። እርሱ የቢድዐህ ሰው ከሆነ አለያም ፋሲቅ አመፀኛ ሰው ከሆነ ባልደረባውን ወዳለበት አካሄድ ሊጎትተው ይችላል፣ አለያም ሰዎች በዚህ ይጠረጥሩታል፣ አንድ ሰው በጓደኛው ዲን ላይ ነውና።
3ኛ, የጥሩ አዕምሮ ባለ ቤት ሊሆን ይገባል። የሞኛሞኝ ሰው ጓደኝነት በላእ ነው።
4ኛ, የጥሩ ስነ-ምግባር ባለ ቤት ሊሆን ይገባል። መጥፎ ስነ-ምግባር ያለው ሰው ጠላትነቱ አይታመንም፣ ይህንም በምታስቆጣው ጊዜ ትፈትነዋለህ፣ ከተቆጣ ጓደኝነቱን ተወው።
5ኛ, ከሀሜት፣ ከምቀኝነት፣ ከሸር ፈላጊነትና ከሁለት ፊትነት ልቡ ንፁህ መሆን አለበት።
6ኛ, በቃሉ የሚፀና የማይዋልልና የማይቀያየር መሆን አለበት።
7ኛ, ለእርሱ ሐቅ እንደምትቆመው ለአንተም ሀቅ የሚቆምልህ መሆን አለበት። በአንተ ላይ ሀቅ እንዳለው እየተመለከትከለት ለአንተም ሀቅ አለህ ብሎ የማይመለከትልህ (ለሀቁ እንደምትቆምለት ለሀቅህ የማይቆምልህ) ጓደኛ ኸይር የለውም።
[አል-ቀዋኒን አል-ፊቅሂየህ ገፅ 460]
➥ በዚህ ዘመን እነዚህን መስፈርቶች ያሟላ ጓደኛ ያለው ሰው ምንኛ ታድሏል!! ዋና ዋና መስፈርቶችንም ያሟላ ማግኘት ትልቅ ነገር ነው!!
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
🔭 ዛሬ ምሽት 3:00 እንዳያመልጥዎ!
ሳምንታዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ ይቀጥላል።
✅ ይሳተፉ፣ ይማሩ፣ እውቀትዎን ይፈትሹ!
ለመቀላቀል እና ለመሳተፍ ከታች ይጫኑ 👇
👉 t.me/FKR_ESKE_JENET
እማዬ A
🌸 !እናቴ!🌸
ልቤንም በሀሴት መንፈሴን በደስታ፤
ህይወቴን የምትሞይ በሳቅ በፈገግታ።
ልክ እንደህፃን ልጂ ሁልጊዜ ቦርቄ፤
ደሞ እንደፈንድሻ ፈክቸ ፈንድቄ።
ከተሠጠኝ እድሜ አንድ የምጨምረዉ፤
አምሮብሽስትኖሪ ጥርሶችሽ ተከፍተዉ፤
ያንችን ዉብ ገፅታ ፈገግታሽን ሣይ ነዉ ።
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
*ትዳርሽ እንዴት አማረልሽ ከተባልሽ፣ በጥረቴ እንዲህ እንዲህ አድርጌ ነው ብለሽ ሳይሆን የጌታየ ችሮታ ነው ብለሽ መልሽ።*
*ትዳርሽ እንዴት ዘገየ ከተባልሽ ምክንያት ከመደርደር ጌታየ የወሰነው ጊዜ ስላልደረሰ ነው ብለሽ መልሽ።*
*ትዳርሽ እንዴት ፈረሰ ከተባለሽ ታሪክ ከመተረት አላህ ቢፈቅደው እኔንም እሱንም ማስተካከል ለእሱ ቀላል ነበር አብሮነታችንን ጌታየ ስላልፈቀደውና *ስላልወደደው ነው ብለሽ መልሽ።*
--- *ምክንያቱም በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጅ ማንም ሰው በራሱ ጥረት ህይወቱን በፈለገው መንገድ ማስኬድና ማስተካከል አይችልም።*
ፈጥኖ የመለሰ 🚀
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው ብዙ ጠቃሚ የሱና ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ።
ጥያቄ 1፦ በቁርአን ውስጥ ስማቸው ከተጠቀሱት 25 ነቢያት መካከል "ዑሉል ዓዝም" (የጽናት ባለቤቶች) ተብለው የሚጠሩት 7 ነቢያት ናቸው።
