ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر3 632
مشترکین
+124 ساعت
+3977 روز
+1 06030 روز
آرشیو پست ها
አሳምነው ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ ጉባላፍቶ ወረዳ ዶሮ ግብር ከተማ በጨለማ ሰርገው በመግባት ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዘገቡ!
አሳምነው ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ የተወሰኑ አባላቶች ጉባላፍቶ ወረዳ ዶሮ ግብር ከተማ የካቲት 20/2018 ዓ.ም ምሽት ሰርገው በመግባት አንድ ጓድ (ቲም) ሙሉ የጠላት መንገድ መሪ ባንዳ ሚሊሻ ላይ እርምጃ በመውሰድ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::
አፋብን ያወጀውን የምህረት አዋጅ መጠቀም ሲገባቸው ሆዳቸውን መርጠው የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለውን የኦሆዴድ ብልፅግና ሰራዊት መንገድ በመምራት ላይ የተሰማሩ እስከ ስምንት የሚደርሱ (አንድ ጓድ) ሚሊሻዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 21/2018 ዓ.ም
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከምሽቱ 1:45 ጎዛምን ፖሊስ ጣቢያ ላይ በፈጠመው ጥቃት 4 (አራት) ሚኒሻዎች ሲገደሉ 4 (አራት )ሚኒሻዎች ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል።
የካቲት 21/2018 ዓ.ም
===============================
ጀብደኛዋ አነፍናፊ የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ዘ-13 ፈንጅ በመጠቀም በፈፀመው የተጠና ጥቃት በጎዛምን ፖሊስ ጣቢያ በህብረት እየወጡ የነበሩ 4(አራት) ሚኒሻዎች የተገደሉ ሲሆን 4(አራት) የሚሆኑት ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል።
የአዲሱ ትውልድ የምርምር ማዕከል በሆነው የዘ-13 ምርት በተገኘ ፈንጅ በመጠቀም የተሳካ ኦፕሬሽን መስራት የቻለው የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ቅስም የሚሰብር ተጨማሪ ጉዳት በተመረጡ የጠላት ኃይል ላይ ማድረሱን አረጋግጧል።
የአረመኔው ሰራዊት ለመንቀሳቀስ እስከ ሚሳቀቅ ድረስ አሸማቃቂ ተከታታይ ጥቃት እየፈፀመ የሚገኘው አዳኝ ቡድኑ በትናት እለት ብቻ 8 ሚኒሻዎችን ሙትና ቁስለኛ ማድረጉን አክሎ ገልጿል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሰበር ዜና
የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ሁለት ብርጌዶች ሁለት ከተሞች ላይ የነበረ ጠላትን ሲያተራምሱት አደሩ ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው የግዙፋ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አሀድ የሆኑት አጥናፋ ብርጌድ በወርቅ ደሞ ከተማ ይታየው ብርጌድ ደግሞ በገደብየ ከተማ ሰፍሮ የነበረውን የአገዛዙን ቅልብ ሀይል ጥይት በማጠጣት እንደ ሰካራም ከወዲያ ወዲህ ሲያሯሩጡት አድረዋል ። የሁለቱ ብርጌድ ጀግኖች ከቀኑ አስር ሰዓት ጀምሮ ወደ ከተሞቹ ዘልቀው በመግባት በእየ ቦታው ሲንቀሳቀስ የነበረን ጥምር ጦር ሲለቃቅሙት ያመሹ ሲሆን በርካታውን በ*ሙ* ት ሸኝተውታል ።
የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አንበሶች ዛሬም እንደተለመደው የብርሃኑን ጁላ ጦር ምሽቱን እንደ እሳት እራት ሲለበልቡት ሲያድሩ በአውደ ውጊያ ላይ የተገኙ ድሎች :-
🗡 15 በ*ሙ*ት የ*ተ*ደ*መ*ሰ*ሰ
🗡 12 በላይ የቆሰለ
🗡ሶስት መከላከያና አንድ አጥቦ አይለብሴ እስከ ነብሱ የተማረከ በይታየው ብርጌድ አባላት
🗡4 ክላሽ 1 አብራራው መሳሪያ ፣ 600 የክላሽ ተተኳሽ እና 5 ቦንብ ተ*ማ*ር*ኳ*ል ። በጎንደሬዎች እርምጃ የተደናገጡ የአገዛዙ ብልፅግና ካድሪዎች ፋኖዎች ባልተጠበቀ አቅጣጫ ሰብረው ሌላ ከተማ ሊቆጣጠሩ ይችላሉ በማለት በስጋት ያለ እንቅልፍ ሲያድሩ የፀጥታው መዋቅር ደግሞ ከአምባጊወርጊስ እስከ ደባርቅ ድረስ ያሌ የሌለ ሀይሉን ሰብስቦ ከተሞችን ሲጠባበቅ አድሯል ። ጀግኖቻችን ግን ስራችን በሚገባ ሰርተው ወደ መጡበት ያለ ጉዳት በሰላም ተመልሰዋል ።
አንድነት ሀይልም መዳህኒትም ነው !!!!
አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ
የካቲት 21/2018 ዓ/ም
ህቅታችን እስከ አለች ድረስ ጠላትን አፈራርሰን የአማራን ነፃነት በአሸናፊነት እናውጃለን።
በእየለቱ የምንጨነቀው አማራን ለማጥፋት የመጣውን ጠላት ለማፈራረስ ስለምንጠቀመው ስትራቴጅያዊ ተግባሮቻችን ነው።
የአፈሙዛችን አረር የጠላትን መቋጠሪያ እየበታተነ ይቀጥላል። ጎን ለጎን በፍቅር ወደ እኛ የሚመጣ የጠላት ሰራዊትን በማይነጥፍ ፍቅር የሚጨብጥ የጀግና መዳፍ አለን።
የአብይን ስልጣን ለማስቀጠል እየታፈሰችሁ ወደ ጠላት ካምፕ የገባችሁ ወገኖቻችን ድርጅታችን አፋብን የሰጠውን የምህረት አዋጅ ተጠቅማችሁ ብትመጡ ሁሌም ምላጭ ላይ የሚውለው ጣታችን በጥልቅ ወንድማዊ ፍቅር ለመጨበጥ ዝግጁ ነን። ብልሆች እየተጠቀሙበት ነው።
ጠላት በውጭም በውስጥም በተናባቢ ፕሮፖጋንዳ የሃሰት የስብዕና ገደላ ዘመቻ ሲፈፅምብን ቢከርምም ለአማራ ነፃነት ስንል ለሞት የወጣን ጀግና የአማራ ልጆችን ከአላማችን ማስቀየስ ፈፅሞ አይችልም።
ወራሪው ስርአት በብድርና በልመና የሚያመጣውን ነፍጥ አስታጥቆ የላካቸውን ሰራዊቶች እየደመሰስን፣ እጅ የሚሰጠውን በፍቅር እየተቀበልን እያፈራረስን በድል እየገሰገስን።
ይሄንን የወራሪውን ሽንፈትና የፋኖን ድል ከ 50ሺህ በላይ የሚዲያ ሚሊሻ Fake Accounts አሰማርቶ የፋኖን መሪዎች እየመረጡ የስብዕና ገደላ ዘመቻ ሲፈፅም ከርሟል። እየፈፀመም ይገኛል። ከንቱ መንፈራገጥ ላይትርፍ መወራጨት ልማዱ መሆኑን ስለምናውቅ ሁሌም በፅናት ስራችንን ብቻ በመስራት አሸንፈነዋል።
ፅናታችን ፣ ጀግንነታችንና ሃቀኝነታችን ሁሌም በድል እና በስራ ይገለጣል።
ቶሎ ቶሎ ኑ ጊዜ የለም።
ሁሉም የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ናቸው በፍቅር በሠላም በእንክብካቤ ወደ ሀገራቸው ገብተዋል።
@@@ የ73ኛ ክፍለጦር 3ኛ ሬጅመንት አባል ሲሆኑ
1,ኦብሣ ሃላፊነት፣ጋንታ መሪ
2,ገላሣ፣ሃላፊነት ቲም መሪ
3,ቶሌ ሃላፊነት ቃኝ
4,ሀሠን አባል
5,አማኑኤል አባል
6,ፍሩምሣ ቲም መሪ
7,ብሩክ አባል
8,ደጃስ አባል
9,አላሙዲን አባል
እነዚ በሙሉ የ73ኛ ክፍለጦር አዛዥ ድባቤ አበራ ከሚመራው 3ኛ ሻለቃ በክብር እጃቸውን ሠጥተው ወደ ሀገራቸው የገቡ ናቸው፣እኛ ተልኮ ተሠጥቶት እኛ ውስጥ ቆይቶ 1እና 2ሌባ ስትቀበሉ እንደምትቦርቁት አንፈነጥዝም እንጅ ሠራዊቱን በየ ቀኑ እያፈራረስነው ነው።ከኦሮሚያና ከደቡብ ብሎም ከሌሎች ክልሎች በስተት ታፍሠው የመጡ የመከላከያ አባላት ገብቷቸው ወደ ሀገራቸው ሲመለሡ፣የኛ ሆዳም ካድሬ የራሡን ህዝብ ሲያስጨፈጭፍ፣እናትና እህቱን ሲያስደፍር ይውላል ።ጭራሽ ደግሞ ጌች በቅርቡ እጁን ይሠጣል ልናመጣው ነው እያላችሁ ታስወራላችሁ።እኔ አደራ የጣለብኝን የአማራ ህዝብ ነፃ ሣላወጣ ከአቋሜ ዝንፍ አልልምና ፣ይልቁንስ የንስሀ ጊዜ ተሠጥቷችኋል ኑ በክብር እንቀበላችሁ!!ኑ የአማራን ህዝብ ነፃ እናውጣ!!
በሁለት ሣምንት ብቻ ከ12በላይ መከላከያ ሠራዊቱን ከእሁዲት ካምፕ ያፈራረሣችሁት ፋኖ አንዷለም ጌቴ እና ፋኖ ቻቻ መከተ ክብር ይገባችኋል።
የጠዋቱ ፀሐይ በደጋማው የአማራ ምድር ላይ ስትወጣ፣ በየካምፑ የሚስተዋለው የጀግኖች እንቅስቃሴና የጠመንጃ አዝማሪ ድምፅ የአካባቢውን ወኔ ይቀሰቅሳል። በዚህ የጦር ግንባር፣ የ"ፍኖተ አማራ ሚዲያ" የጋዜጠኞች ቡድን ከፋኖዎች ጎን በመሆን፣ የጀግንነት ታሪኮችንና የጦር ሜዳ ውሎዎችን ለመመዝገብ ሌት ተቀን እየተጋ ነው።
"ለተከበራችሁና ለአገራችሁ የቆማችሁ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በስደት በምትኖሩ የአማራ ፋኖ ደጋፊዎችና አጋሮች ሁሉ፤ በመጀመሪያ የፈጣሪ ሰላም በያላችሁበት ይድረሳችሁ። እኔ እግዚአብሔር ይመስገን፣ ሰላም ነኝ።
እኛ ፍኖተ አማራ ሚዲያ፣ አላማችንን የፋኖን አንድነት መሰረት አድርገን፣ የጀግኖችን ገድል በቀጥታ ከግንባር በመገኘት ለታሪክና ለትውልድ እየመዘገብን እንገኛለን።
ስለዚህ፣ ይህ እውነተኛው የፋኖ ድምፅ ለሁሉም አማራና ለወዳጆች እንዲደርስ፣ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫንና ሼር በማድረግ ትብብራችሁን እንድታሳዩን፣ በአክብሮት እንጠይቃለን።"
+1
የአገዛዙ ወታደሮች ፋኖን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል!
አባትና ልጅን ጨምሮ ሦስት የሚሊሻ አባላት 2 ክላሽ 1 እስኬስ ከነ ሙሉ ተተኳሹ በመያዝ በአፋብን በላይ ዕዝ ሜ/ጄነራል ውባንተ አባተ ኮር ጉና ክፍለ ጦር አንዳቤት ብርጌድን ተቀላቅለዋል ሲል የክፍለጦሩ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ለፍኖተ አማራ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።
ለእኛ አድዋ እንዘጋጅ !
የአድዋ ድል መሠረቱ ነፃነት፣ ክብር እና እኩልነት ነው። ኢትዮጵያውያን በአድዋ የተዋጉት የባዕድ ወራሪን "አልገዛም" ብለው ነው። በገዛ ህዝቡ ላይ ከህግ ውጭ እስር፣ ጅምላ ግድያ እና ዘር ተኮር በደል የሚፈጽም አገዛዝ ግን ራሱ የውስጥ ወራሪ (Internal Colonizer) ሆኗል ማለት ነው። ስለዚህ አድዋን አክብራለሁ ማለቱ ድሉን ሳይሆን፣ ድሉን የፈጠረውን የነፃነት መንፈስ እንደመሳለቅ ይቆጠራል።
አምባገነን አገዛዞች ህዝባዊ ተቀባይነት (Legitimacy) ሲያጡ፣ የታሪክ ስኬቶችን እንደ ጋሻ መጠቀም ይወዳሉ። የአድዋን ድል ማክበር የሚፈልጉት ለድሉ ክብር ኖሯቸው ሳይሆን፤ የህዝብን ስሜት ለመግዛት እና ትኩረት ለማስለወጥ እና "እኛም እንደ አባቶቻችን ጀግኖች ነን" የሚል የሐሰት ምስል ለመገንባት እንዲቲም "ኢትዮጵያዊነትን" ለራሱ የፖለቲካ ፍጆታ ለመጠቀም ነው።
አንድ አገዛዝ በአንድ በኩል የአድዋን ድል ሲያወድስ፣ በሌላ በኩል ግን ዜጎችን በዘራቸውና በማንነታቸው ሲያገልና ሲያሳድድ ትልቅ የሞራል ዝቅጠት ውስጥ ይወድቃል። አድዋ የኢትዮጵያውያን የጋራ የድል ምልክት ሆኖ ሳለ፣ አገዛዙ ህዝብን በዘር ከፋፍሎ ሲያቆስል "አድዋን አከብራለሁ" ማለቱ በቁስል ላይ ጨው የመነስነስ ያህል ነው።
እውነተኛ የአድዋ በዓል አከባበር የሚገለጸው በታላቅ ሰልፍ ወይም በወታደራዊ ትርኢት ሳይሆን፣ ድሉ የተገኘለትን "የሰው ልጅ ነፃነት" በተግባር በማረጋገጥ ነው። አድዋ የሚከበረው ፍትህ ሲነግስ፣ ከህግ ውጭ እስር ሲቆም፣ የንጹሃን ግድያ ሲቆም እና ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ባዕድ ሳይሆኑ በእኩልነት ሲኖሩ ነው።
አንድ አገዛዝ በገዛ ህዝቡ ላይ ግፍ እየፈጸመ አድዋን ሲያከብር፣ በዓሉን ለትርኢት እንጂ ለትርጉሙ አልፈለገውም። ይህ ድርጊት በታሪክም ሆነ በህዝብ ፊት የታሪክ ስላቅ (Historical Sarcasm) ተብሎ ይመዘገባል። አረመኔው የብልጽግና አገዛዝ እያደርጉው ያለው ይኽን የታሪ ስላቅ ነው። ነገር ግን፤ የአድዋ መንፈስ ዛሬም የሚጠይቀው ከባዕድ ቀንበር ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ጭቆናም ነፃ መውጣትን ነው።
የእኛ አድዋ ይህን የጭቆና እና ዘር አጥፊ ስርዓት በማስወገድ ነፃነት፣ ፍትህ እና እኩልነት የሰፈነባት ሀገረ ኢትዮጵያን ልጆቻችን ማስረከብ ነው እና ለእኛ አድዋ እንዘጋጅ።
©አርበኛ አስቲበል ዓለሙ የቴዎድሮስ ዕዝ ምክትል ሕዝብ ግንኙነት
#ጥንቃቄ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለ ጦር ቀጠና በተለይ ማቻክልና ደምበጫ የፋኖ ቀጠናዎች ላይ የአገዛዙ አመሻሽ ጀምሮ ስምሪት እያደረገ መሆኑን ቀኜዎች ለፍኖተ አማራ ገልፀዋል በቀጠናው ያለህ የወገን ኃይል እንግዶችን በተጠንቀቅና በደፈጣ ጠብቅ ሲሉ ምንጮች መልዕክት አስተላልፈዋል‼️
#ሲሪንቃ💪
የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ስሪንቃ ከተማ ዙሪያ ድል አስመዘገቡ‼️
ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦርና ምስራቅ አማራ ኮር1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በጋራ በመሆን በሀብሩ ወረዳ በሲሪንቃ ከተማ ከወልደያ ለማጥቃ የተንቀሳቀሰዉን 46ኛ ክፍለ ጦር የጠላት ሃይል ድባቅ በመምታት ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዘገቡ።
አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮርና ምስራቅ አማራ ኮር 1 በለሽርጡ ክፍለ ጦር በጋራ በመናበብ የብልፅግናን ወንበር አስጠባቂ 46ኛ ክ/ጦር የጥላት ሀይል ከወልደያ ከተማ አናብስቶቹ ወደ ሚንቀሳቀሱበት ወደ ሲሪንቃ ከተማ ለማጥቃት እንቅስቃሲ ቢደርግም ከወደ መርጦ ሚካኤል አቅጣጫ በሞላ ጊወርጊስ አቅጣጫ የምስራቆቹ ኮኮብ ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር ማጥቃት ሲገቡ እንደሁም አይበገሪዎቹ 24ኛ ክፍለ ጦር ከወደ ቱላንባ ጥላት ባለበት በስተቀኝ አቅጣጫ አሰላለፋቸዉን በማስተካከል የአብይን ወንበር አስጠባቂ ሀይል አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አሰመዝግበዋል።
ተናበዉ አሰላለፋቸዉን አሳምረዉ የገቡት አናብስቶቹ ለማጥቃት በቅዥት የመጣዉን ሃይል ቅዥት አድርገዉ ሀሳቡን አንኮላሽተዉበት ሙትና ቁስለኛ በማድርግ ቁስለኛዉንና እሬሳዉን ሳያነሳ ወደመጣበት ወደ ወልደያ እግሬ አዉጭኝ ብሎ ፈርጥጧል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 20/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና‼️
አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር ሰላም ሰው ሻለቃ ቃኘዎች በፊቼ ከተማ ጠላት ካምፕ ውስጥ ሰርጎ በመግባት ታሪካዊ ድል ተቀዳጀ ።
የካቲት 20/2018 ዓ.ም፡ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የኃይለማርያም ማሞ ሰላም ሰው ሻለቃ ቃኘዎች በኦሮሚያ አሌልቱ ወረዳ ፍቼ ቀበሌ ከንገቱ 2:00 ሰዓት ላይ ከተማ ውስጥ በጠላት ካምፕ ላይ የክፍለ ጦሩ ቃኘዎች በጠላት ቀጠና ውስጥ ሰርገው በመግባት የብልጽግናውን ስርዓት አስፈፃሚዎች ላይ፤ የአብይ አህመድ የሽመል አብዲሳ የከተማ ጠባቂ ሚሊሻዎች ወይም "ተጠባባቂ ኃይል" ብሎ የሚጠራቸውን፤
➣ አቶ በላይነህ ለማ (ሚሊሻ) እና
➣ አቶ ወርቃዬ ደመቀ (ሚሊሻ)
የተባሉ ሁለት ሚሊሻዎች በአካባቢው ያሉትን ነዋሪ ማህበረሰቡን ለአመታት ሰላም ሲያውኩ የቆዩ ኃይሎችን በደፈጣ በመያዝ አልያም በመማረክ ድል መመዝገቡ ተገልጿል ።
የኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር ቃኘዎች በኦሮሚያ ቀጠናም ይሁን በሌሎች የደፈጣ ውጊያዎች ሰርገው በመግባት፤ የአማራን ሕዝብ ደህንነት ለማቃወስ የሚንቀሳቀሱትን ኃይሎች ላይ በተደጋጋሚ አስገራሚ ጀብድ ሲፈፅም የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ኃቅ ነው ።
ሆኖም በዛሬ ዕለት ማለትም በቀን 20/6/2018 ዓ.ም የተካሄደው ልዩ ኦፕሬሽን የአማራን የነፃነት ተጋድሎ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያወጣና የጠላትን የመጨረሻ ውድቀት የሚያሳይ ስልት ሲሆን፤ ፋኖን "በአራት ቀን አጠፋለሁ" ብሎ በአማራ ግዛት የገባው የአገዛዙ መከላከያ ሰራዊትና የሽመልሽ አብዲሳ ሚሊሻ ኃይልን ጨምሮ የፋኖ ኃይሎች በገባበት ገብተው ድባቅ እየመቱት ይገኛል ።
በመጨርሻም፤ ይህ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት የሰርጎ መግባት ዘመቻ በአብይ አህመድ ኃይሎች ላይ ከፍተኛ የሞራል ስብራት የፈጠረ ሲሆን ። ክፍለ ጦሩ በየትኛውም የግዳጅ ቀጠና ዝግጁ የሆነ ሲሆን በኦሮሚያ ቀጠናም ይሁን በደፈጣ የጠላትን እንቅስቃሴ አስቀድሞ በመገንዘብና አቅጣጫውን በመቀየር ከፍተኛ ጀብድ እየፈፀመ እንደሆነ ታውቋል ።
ይህ ድል የአማራን ህዝብ የነፃነት ተጋድሎ ወደ ከፍተኛ ማማ የሚያወጣ እና የጠላትን ውድቀት የሚያረጋግጥ ስልት ነው፤ ሲል ከሰም ፪ኛ ኮር የኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር ሪፖርተራችን አርበኛ ኃቀኛው ይታፈሩ መረጃውን ከግምባር አድርሶናል።
- አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ ።
የ12ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ አባላቶች ቆቦ ከተማ ሰርገው በመግባት የፋሽስቱን አገዛዝ አመራር አቶ አያሌው ጌታሁንን ደመሰሱ::
ምስራቅ አማራ 102ኛ ኮር 12ኛ ክፍለ ጦር የ2ኛ ሻለቃ አባላቶች ቆቦ ከተማ ሰርገው በመግባት ዛሬ የካቲት 20/2018 ዓ.ም ጧት የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ጋር ወግኖ የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ የነበረው የራያ ቆቦ ወረዳ የታጠቀው ሃይል ዋና አስተባባሪና የገደመዩ ሊቀመንበር አቶ አያሌው ጌታሁን እና ሁለት ግብረ አበሮቹ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::
በቀድሞው ዞብል አምባ በአዲሱ አደረጃጀት በ12ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ አባላቶች ከሁለት ግብረ አበሮቹ ጋር መሃል ቆቦ ከተማ ሰኞ ገበያ ላይ የተደመሰሰው አቶ አያሌው ጌታሁን ባለፉት ሶስት አመታቶች የበርካታ ንፁሃን አማራዎችን ነፍስ የቀጠፈ ሲሆን የፋኖን ፍፁም ትግስትና የምህረት አዋጅም ጭምር ባለመቀበሉ ጊዜውን ጠብቆ በህዝብ ልጆች የማያዳግም እርምጃ ተወስዶበታል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም የራያ ቆቦ ወረዳ ሚሊሻዎች ፋኖ ወዳለበት ቀጠና ሄደው መዋጋት ስለማይችሉ ቆቦ ከተማ ሰኞ ገበያ እና ሌሎች የተለያዩ ቦታዎች ላይ ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃኖችን እየረሸኑ ይገኛሉ:: በዚህም እስካሁን ሶስት ንፁሃኖች በጥይት መትተዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 20/2018 ዓ.ም
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር እና አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አፋብን ስሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ ላይ ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል።
አማራነት አንድነት ፣ አማራነት ቃል ለገቡለት ዓላማ ርዕይ መስዋትነት መክፈልን ፣ ለኢትዬጵያዊነት አንድነት መታገል ክብርና ሞገስ እንደሚያላብስ ተረድቶ ከትናት ልዩነት ወደ ተቋማዊ አንድነት በማምጣት የጋራ ትግል እና ቀጠናዊ ትስስር በማድረግ በርካታ ወረዳዎች እና ከተሞች ነጻ እየወጡ ነው በቀጣይም ነጻ ይወጣሉ።
ባለፉት ቀናቶች በሁለቱም ኮሮች ነጻ በወጡ ከተሞችና ወረዳዎች ውይይት ማድረጋችን እሚታወስ ሆኖ በዛሬው ዕለት የካቲት 20/2018 ዓ.ም ነጻ ከወጡት ቀጠናዎች መካከል ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ የሐይማኖት አባቶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች በተገኙበት ውይይት ማድረግ እና ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት የጋራ ተደርጓል ።
ስለሆነም ከህዝብ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች፦
[ ] የማህበረሰብ አገልግሎት ሰጭነትና የተቋም ጥበቃን በተመለከተ ፤
[ ] በቀጠናው ላይ ስላለው የመዋቅር ልዩነት ወደ አንድ ስለመምጣትና ተቋማዊ ቅርጽ እንዲይዝ የማድረግ ልዩ ተልኩዎች፤
[ ] በውጊያ ውስጥ ስለተማርኩ እና እጅ ስለሰጡ የአገዛዙ አገልጋዬች የምርኮ ሰባዊ መብት አያያዝ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ወደ አንድ መሐከል ገብተው የፖለተካ ትምህርት ተሰጥቷቸው እንዲወጡ ስለመስራት እና
[ ] ከተማውን በሁለቱም ኮሮች የጋራ ኮማንድ ህዝባዊ አስተዳደር ስለሚመራባቸው ስነ ስርዓታዊ ህጎች ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በዚህ ህዝባዊ የውይይት መድረክ የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ልዩ ኦፕሬሽን ኃላፊ አርበኛ የቆዬ አበጀ ፣ ጀኔራል ኃይሌ ዘ ውባንተ ክፍለ ጦር ዋና ወታደራዊ አዛዥ ኮሚሽነር አበበ መልኬ እንዲሁም አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች አርበኛ አራጋው እንዳለ የአፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ምክትል የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ ፣ አርበኛ አንተነህ ድረስ የአፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ዕቅድና ስትራቴጂ መምሪያ ኃላፊ እና የአፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አመኑ በተገኙበት በተነሱ ዝርዝር ጥያቄዎችና ሀሳቦች የጋራ መግባባት ተደርጎባቸው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት መድረኩ ተቋጭቷል።
ድል ለአማራ ፋኖ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፊያለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት !!!
የካቲት 20/ 2018 ዓ.ም
