ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر3 632
مشترکین
+124 ساعت
+3977 روز
+1 06030 روز
آرشیو پست ها
ሰውየው ደግሞ ሌላ የሚማረክ አዳዲስ መሣሪያ ለማምጣት ወደ አዘርባጃን ሄዷል‼️
አርበኛ ሚናስ አለማየሁን ጨምሮ ሌሎች የበላይ ዘለቀ ዕዝ ወታደራዊ አመራሮች ከሰራዊታቸው ጋር በመሆን በሻሁራ ግንባር ከማረኳቸው ዶሽቃ መሣሪያዎች መካከል።
20/ዐ6/2018 ዓ.ም
+1
በኤፍራታና ግድም ወረዳ (አጣዬ) የሚኖረው ሕዝብ፣ ከጦርነት እሳት ተርፎ ዛሬም በቁም መከራውን እየበላ ይገኛል። ላለፉት ዓመታት ቤቱ በአመድነት ተቀይሮ የከረመው ይህ ምስኪን ሕዝብ፣ ዛሬ ካገገመበት የተስፋ ጭላንጭል ይልቅ የመከራ ማዕበል እየተደገመበት ነው።
ወቅታዊው የአጣዬ ሕዝብ ሰቆቃ በሦስት ነጥብ፦
1ኛ ያልተገደበ እንግልት፦ ራሱን ለመቻልና ኢኮኖሚውን ለማቃናት በሚደክምበት ወቅት፣ ያላግባብ የሚደረግ እንግልትና የሀብት ማውደም ተግባር ሰለባ ሆኗል።
2ኛ ስልታዊ የመሬት ወረራ፦ ሕዝቡ በስጋትና በጦርነት ቁስል ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ግልጽ የሆነና የሕዝቡን ነገ የሚያጨልም የመሬት ወረራ እየተካሄደ ይገኛል።
3ኛ ቤት ማፍረስ (በቆሰለ ቁስል ላይ ጨው መነስነስ)፦ ጦርነት ያቃጠለበትን ቤት መልሶ ለመገንባት ከልጆቹ ጉሮሮ ቆጥቦ የሰራው መጠለያ "ሕገ-ወጥ" በሚል ሰበብ በላዩ ላይ እየፈረሰበት ነው።
4ኛ ያለ አግባብ አስር፦ከዚህ በፊት ኦነግ ሸኔ እያጠቃቸው ስለነበር እራሳችንን እንድንከላከል መደራደት አለብን የሚሉትን እና የፈረሰ ቤታችንን እየቀለስን ነው ለምን ዳግም ይፈርስብናል ብለው የሚሞግቱትን ያለ አግባብ እያሰሩ ይገኛሉ
ጦርነት ያደቀቀውን ሕዝብ መልሶ ማቋቋም ሲገባ፣ በገዛ ሀገሩ የሰራውን መጠለያ ማፍረስ ምን ይባላል? "ሕገ-ወጥ" የሚለው ስያሜ ከጦርነት ለተረፈ ምስኪን ህዝብ ነው ወይስ መሬት ለሚወርሩ ኃይሎች? አጣዬ መከራዋ ይብቃ!
አርበኛ ሽመል ንጉሴ ከአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሽዋ ሰማይ ስር
ሰበር ዜና!...በቆቦ ከተማ ሰኞ ገበያ ላይ የአገዛዙ ሚኒሻ አባላት በከፈቱት የተኩስ እሩምታ እስካሁን ባለው ሁለት ንፁኋኖች ሕይወታቸው ማለፉ ሲታወቅ በርካቶች መቁሰላቸውን የመረብ ሚዲያ የቀጠናው ዘጋቢ ለማረጋገጥ ችሏል።
የሚኒሻ አባላቱ ተኩሱን የከፈቱት በሰኞ ገበያ ውስጥ አትክልት ተራ ላይ ሲሆን፡ እረብሻና ግርግሩ ተባብሶ ቀጥሏል። ሕዝቡም "እስከመቼ እናልቃለን" በሚል አፀፋዊ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል። በዚህም እስካሁን በርካታ የሚኒሻ አባላት ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል።
በሚኒሻ አባላቱ ተመትተው ሕይወታቸው ያለፈ ንፁኋኖች አስ*ከ*ሬን አሁንም በገበያው መሀል እንደወደቀ ነው።
ሕዝቡም "በተገደለብን ልክ እጥፍ ድርብ የሚኒሻ አባል ካልገደልን የንፁኋኑን አስከሬን አናነሳም" በሚል የሚወስደው አፀፋዊ እርምጃ አይሏል።
ጣቢያችን ፍኖተ አማራ ሚዲያ በከተማዋ ስለተፈጠረው ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ተከታትሎ የሚያደርሳችሁ ይሆናል!
የቴሌግራም ገፃችን👉
ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር በደራ/አምበሳሜ ከተማ ሕዝባዊ ውይይትን አከናወነ❗
[የካቲት 19/2018ዓ.ም]
ጣና ገላውዲዎስ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድረው ባሕር ዳር በቅርብ ርቀት በሚገኘው በደራ ወረዳ አምበሳሜ ከተማ ከማህበረሰቡ ጋር በዛሬው ዕለት በ19/06/2018 ዓ.ም የአፋብን በላይ ዕዝ አደረጃጀት ዘርፍ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደምሰው አባተ፣ በአፋብን ሰ/አ/ቀ/ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎዮስ ክፍለጦር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ሙሉቀን አለኸኝ፣ ም/ሰብሳቢ አርበኛ ባበይ፣ የጣና ገላውዴዎሥ ክ/ጦር ዋና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ጋሻዬ እንግዳን ጨምሮ ሌሎች የክፍለጦር ሥራ አሥፈጻሚዎችና የብርጌድ ሥራ አሥፈጻሚዎች እንዲሁም የፋኖ ጊዜያዊ የመንግስት አስተዳደሮች በተገኙበት የህዝብ ውይይት ተካሄዶል።
👉 በሕዝባዊ ውይይቱም ለሕብረተሰቡ ዋና ዋና ጉዳዮችን በማንሳት ስፊ ግንዛቤ መሰጠት ተችሏል።
👉 የወረዳው ህዝብ በመደራጀት ከአገዛዙ ወራሪ ኃይል ራሱን እንዲጠብቅ ግንዛቤ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
👉 የፋኖ ትግል አሁናዊ ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
👉 በፋኖ ስም በየ ቦታው ሕዝብ የሚዘርፉ እና የሚያሰቃዩ ግብረ ነውረኞችን ተመጣጣኝ ርምጃ በመውሰድ ሕዝቡ በነፃነት እንደሚንቀሳቀስ እና የቀበሌ፣ የወረዳና የዞን መዋቅር በመዘርጋት የሥራ አቅጣጫ በመስጠት በተለያዩ ጉዳዮች ምክክር ሲያደርግ ውሏል።
👉በመጨረሻም በመድረኩ የተሳተፉ የሕብረተሰብ ክፍሎች ያነሷቸውን ሐሳብና ጥያቄ በፋኖ አመራሮች ተገቢ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የዕለቱ የውይይት መድረክ በሞቀና በደመቀ ሁኔታ ተጠናቅቋል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን‼️
አፋብን ሰ/አ/ቀ/ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
በርካታ ቁጥር ያለው መኪናና እግረኛ ሁኖ መከላከያ ሰራዊት 12:40 ከደብረታቦር ተነስቶ አለምበር ላይ ደርሶል ጥንቃቄ !!
ቀን 20/6/2018ዓ.ም
በ201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር የቢቡኝ ወረዳ አባት አርበኞች በተጠንቀቅ ላይ ነዉ‼️
➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾
የካቲት 19/2018 ዓ.ም
በቢቡኝ ወረዳ አባት አርበኞች ጦር ለግዳጅ ዝግጁ መሆናቸዉን የ201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊዉ፣ የቢቡኝ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት ፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዉ እና አስፈፃሚ ኮሚቴዎች በተገኙበት ገለፁ።
በተጠንቀቅ ላይ ያሉ የቢቡኝ ወረዳ አባት አርበኞች ጦር የድርጅታችን እና የትግሉ ቁመና በቂ ግንዛቤ ከተሰጠ በኋላ ከትግሉ ጎን በመሆን የአማራ ታሪካዊ ጠላት የሆነው የብልፅግና አሸባሪ መንግስት ነኝ ባይ የአረመኔ ስብስብ ቡድን እስከ መጨረሻዉ ድረስ እንታገላለን ሲሉ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ትግሉ በአጭር መቋጨት እንዳለበት ገልፀዉ ህዝቡ ከፋኖ ጎን መቆም እንዳለበት በመረዳት ለቀጣይ ግዳጆች ትጥቅ እና ስንቅ በማዘጋጀት የድርጅታችን ትዛዝ በመጠባበቅ ላይ ነን ብለዋል። አሁን ላይ አምባገነኑ የብልፅግና ስርዓት በማንነታችን እየፈፀመብን ያለውን በሌሎች አካባቢ እያየን ስለሆነ ቀድመን እራሳችን የመከላከል እና ቀጠናችን መጠበቅ አለብን በማለት የወረዳው የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ የጀርባ ደጀን ህዝቡን በመጠርነፍ ትዛዝ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
"አርበኝነት ያለ የነበረ የሚኖርም ነዉ!"
የካቲትና 20/2018 ዓ.ም
አዲስ ትውልድ፣አዲሰ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 2ዐ1ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር የቢቡኝ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት ሚዲያና ግንኙነት
የድል ዜና 💪‼‼
"... አፋብን አፄ ቲዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦር ከክፈለ ጦሩ አሃዶች አንዷ የሆነችው መማር ጌትነት 2ኛ ሻለቃ ከሌሎች አጋር ክፍለጦሮች እና ሻለቆች ጋር በመተባበር ቀጥታ ከሜጫ ተወርውራ ከሌሎች ጓዶች ጋር በመሆን በተለያዩ አቅጣጫወች በመግባት ሰሜን አቸፈር ወረዳ ይስማላ ከተማንና ሌሎችንም የሳተላይት ከተሞች መቆጣጠር ተችሏል ።
ዛሬ የካቲት 19/2018 ዓ/ም በተካሔደው ኦፕሬሽን በ102ኛ ኮር ዘመቻ መሪ ታጋይ ከማንዶ ፋኖ ላመነው ሰጤ ሰጤ የተመራ የሜጫ ጥር ወደ አጎራባች ወረዳወች በመግባት ከሌሎች አጋር ጓዶቻችን ጋር በመተባበር የሠሜን አቸፈር ዋና ከተማ የሆነችውን ይስማላ ከተማን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ተችሏል ።
የወገን ጦር በዐብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ የጥላት ሀይል ላይ ከፍተኛ ምት በማሳረፍ ከመደምሰስ የተረፈው ሲፈረጥጥ በርካታው ተደምሷል ።
በተካሄደው ኦፕሬሽንም በርካታ ምርኮ የተገኘ ሲሆን በቀጣይ ምን ያክል ተተኳሽ እና መሳሪያ እንደተገኘ በዝርዝር የምንመለስበት ይሆናል ።
ፋኖ በተለያዩ አቅጣጫዎች እንደንስር ታደሶ እየመጣ ነው ።
እንዳዲስ በተቀጣጠለው አውደ ውጊያውም በርካታ የወረዳ ከተሞች ነጻ እየወጡ ይገኛሉ !!
ጥላትን እስከመጨረሻው እንፋለመዋለን !!
ድል ለተገፋው አማራ!
ድል ለጀግናው ፋኖ💪!!
ሁለቱ ግዙፍ ኮሮች በጥምረት በሞርተር የታገዘ ውጊያ አካሄዱ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር እና የ102ኛ ኮር በጥምረት ይስማላ ላይ የጠላትን ሀይል በሞርተር ሲበትኑት ውለዋል።
የካቲት 19/2018 ዓ/ም የጠላት ሀይል በየቀጠናው በመንጋ በመንቀሳቀስ የአማራን ህዝብ ሀብትና ንብረቱን በመዝረፍ፣በማውደምና ህልውናውን ለማጥፋት ያለየሌለውን አቅም እየተጠቀመ ይገኛል።
የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ሁለቱ ግዙፍ ኮሮች በጋራ ጥምረት በመፍጠር በጠላት ላይ በሞርተር በመታገዝ ጠላትን ሃይል ቁስለኛና ሙት በማድረግ ያሰበውን ዘረፋ ሳያሳካ እንዲመለስ አድርገውታል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር በደራ/አምበሳሜ ከተማ ሕዝባዊ ውይይትን አከናወነ❗
[የካቲት 19/2018ዓ.ም]
ጣና ገላውዲዎስ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድረው ባሕር ዳር በቅርብ ርቀት በሚገኘው በደራ ወረዳ አምበሳሜ ከተማ ከማህበረሰቡ ጋር በዛሬው ዕለት በ19/06/2018 ዓ.ም የአፋብን በላይ ዕዝ አደረጃጀት ዘርፍ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደምሰው አባተ፣ በአፋብን ሰ/አ/ቀ/ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎዮስ ክፍለጦር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ሙሉቀን አለኸኝ፣ ም/ሰብሳቢ አርበኛ ባበይ፣ የጣና ገላውዴዎሥ ክ/ጦር ዋና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ጋሻዬ እንግዳን ጨምሮ ሌሎች የክፍለጦር ሥራ አሥፈጻሚዎችና የብርጌድ ሥራ አሥፈጻሚዎች እንዲሁም የፋኖ ጊዜያዊ የመንግስት አስተዳደሮች በተገኙበት የህዝብ ውይይት ተካሄዶል።
👉 በሕዝባዊ ውይይቱም ለሕብረተሰቡ ዋና ዋና ጉዳዮችን በማንሳት ስፊ ግንዛቤ መሰጠት ተችሏል።
👉 የወረዳው ህዝብ በመደራጀት ከአገዛዙ ወራሪ ኃይል ራሱን እንዲጠብቅ ግንዛቤ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
👉 የፋኖ ትግል አሁናዊ ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
👉 በፋኖ ስም በየ ቦታው ሕዝብ የሚዘርፉ እና የሚያሰቃዩ ግብረ ነውረኞችን ተመጣጣኝ ርምጃ በመውሰድ ሕዝቡ በነፃነት እንደሚንቀሳቀስ እና የቀበሌ፣ የወረዳና የዞን መዋቅር በመዘርጋት የሥራ አቅጣጫ በመስጠት በተለያዩ ጉዳዮች ምክክር ሲያደርግ ውሏል።
👉በመጨረሻም በመድረኩ የተሳተፉ የሕብረተሰብ ክፍሎች ያነሷቸውን ሐሳብና ጥያቄ በፋኖ አመራሮች ተገቢ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የዕለቱ የውይይት መድረክ በሞቀና በደመቀ ሁኔታ ተጠናቅቋል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን‼️
አፋብን ሰ/አ/ቀ/ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ጣና ገላውድዮስ ክፍለ ጦር ሕ/ግንኙነት ኃላፊ💪
አርበኛ ፍቅሩ ባዬ
ማሳሰቢያ
===+++
ተቋማትን የሚያድመው እና የሚያቃጥለው አገዛዙ እንጅ ፋኖማ የጠላትን ተቋም ለራሱ እየተጠቀመበት ነው።
ቋሚ ምሥል፦ ከመርሐ ግብሩ ላይ የተወሰደ
የአማራ ህዝብ የህልውና ታጋድሎ ተተርኮ የማያልቅ ገድል እና ጀግንነት የተፈፀመበት ነው። በእያንዳንዱ ድል ጀርባ አስደናቂ ተጋድሎ አድርገው የወደቁ ጀግኖች አሉ። ከእነኝህ መካከል የፋግታ ለኮማዋ ፋኒት ዘመናይ ደጉ አንዷ ነች።
የካቲት 07 ቀን 2018 ዓ/ም አዲስ ቅዳም አቅራቢያ ሰምቡ ግሸን ተራራ ላይ ከጓዶቿ ጋር በጠላት የተከበበችው ፋኒት ዘመናይ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ በማድረግ ጥይቷ ሲያልቅ የመጨረሻዋን ጥይት ወደራሷ ተኩሳ እራሷን በክብር ሰውታለች።
ራሷን በጀግንነት የሠዋችው ድንቅ አማራዊት ፋኒት ዘመናይ ደጉ የ105ኛ ክፍለ ጦር 44ኛ ክፍለ ጦር አርበኛዋ ወደ ራሷ ከመተኮሷ በፊት '"ሚጣ ተይ እራስሽን አታጥፊ ብትማረኪ ይሻላል..." የሚሉ ድምፆች ወደ ጆሮዋ ቢመጡም በጠላት ከመማረክ ይልቅ በራሷ እጅ ሰማዕት የመሆንን ክብር አስቀድማለች። ትውልዱ የፋኒት ዘመናይ እና መሰሎች እዳ አለበት።
ብዙወች በተራ ነገር ትግሉን በሚሸጡበት ሁኔታ ውስጥ ዓላማቸውን ከህይወታቸው ያስቀደሙ ጀግኖች በሚከፍሉት መስዋዕትነት የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ግቡን ይመታል።
አገዛዙ የራሱን ሚሊሻና ከድማ በትን ላይ የድሮን ጥቃት አደረሰ
================
አገዛዙ ደልጊ ላይ ተደጋጋሚ በፈፀመው የድሮን ጥቃት ከፋኖ ጥይት የተረፈውን የራሱን አድማ ብተናና ሚሊሻ ወደ አመድነት ቀይሮታል።
ጎንደር በለሳ ላይ ብልጽግናን አምነው በተሰበሰቡ ሚሊሻዎች ላይ በተቀነባበረ ሴራ በአደረሰው የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሚሊሾች መሞታቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። በአማራ ሚሊሾችና አድማ ብተና ላይ ተደጋጋሚ በሚደረግባቸው ክህደት ብዙ ሚሊሾች መሞታቸው ይህ የመጀመሪያው አይደለም።
ብልጽግና የሌቦች የሴረኞች የሀገር ሻጮች ስብስብ ነው። ስለዚህ ሚሊሻ፣ፖሊስ፣አድማበትን እና መከላከያ የወረደላችሁን የምህረት ሲሳይ በቶሎ መጠቀም ብልጠት ነው።
⛔️የብልጽግና ክፋቱ ክህደቱ፤
የካቲት 19/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር በታሪካዊት ማጀቴ ህዝባዊ ወይይት አካሔደ!!
በታሪካዊቷና የጥንታዊቷ ስልጣኔ መገኛ በሆነችው ማጀቴ ከተማ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ስር የሚገኘው የዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር ከከተማዋና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ባደረገው በዚህ ውይይት የፋኖ ወቅታዊ ቁመናና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
1, ድርጅቱ የተመሰረተው በአማራ ሕዝብ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስና ፍትህ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባትም ነው ሆኖም የአማራ ህዝብ የታሪክ አደራን ለመሸከም ሲሉ የክፍለ ጦሩ አመራሮች የድርጅቱን ስርወ-መሠረትና ጽኑ ዓላማ ለሕዝቡ አስረድተዋል።
2, በወታደራዊ ረገድ ፋኖ አሁን ካለበት መከላከል ወደ ማጥቃትና ቁልፍ ይዞታዎችን ወደ መቆጣጠር" መሸጋገር ላይ ይገኛል።
3, የዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር በማጀቴና በዙሪያዋ ባሉ ስትራቴጂካዊ ስፍራዎች ላይ ያለውን ሙሉ ቁጥጥር ያሳየበትና ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው የአማራ ፋኖ የሕዝብ ጋሻ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠበት ወቅት መሆኑ ተነግሯል። ፋኖ አሁን ላይ ዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስን የታጠቀና የተቀናጀ ዕዝ ያለው ኃይል መሆኑ በዝርዝር ቀርቧል።
4, ወታደራዊ ብቻ ሳይሆን ግልጽ ፖለቲካዊ ራዕይ እንዳለው ለነዋሪው ተብራርቷል፦ ፖለቲካዊ ሁሉንም ያካተተ፣ የአማራን ሕዝብ ጥቅምና ክብር የሚያስከብር የፖለቲካ ስርዓት በመገንባት ላይ ያለውን ቁመናም ተገልጿል።
በመጨረሻም በአሁኑ ሰዓት ፋኖ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነቱን ያጠናከረ፣ በዲሲፕሊን የታነፀና ከሕዝብ ጋር በደም የተሳሰረ በመሆኑ። ፋኖ የሕዝብ ልጅ ነው በማለት ዛሬ በማጀቴ የተደረገው ውይይት በሕዝብና በታጋዩ መካከል ያለውን አጋርነት ይበልጥ አጠናክረዋ። ሆኖም ይህ ውይይት ለቀጣዩ ድል ትልቅ ስንቅ ነው በሚል በአካል ከማህበረሰቡ አስተያየት ተሰጥቷል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !!
የካቲት 19 /06/2018 ዓ.ም
በዚህ ትግል ሁሉም ታጋይ የራሱን የማይረሳ ጀብድ ሰርቷል
ከጀብዶች ጀብድ ግን ያች ነሐሴ 2 ቀን 2015 ዓ.ም የባሕር ዳር ሰባታሚቱ እስር ቤት አትረሳኝም። በነ ማንችሎት የሚመራ ከቋሪት፣ ከአዴት፣ ከጭስ አባይ፣ ከባሕርዳር ከተማና ዙሪያ ኃይል እየመጣ ነው። ከሰዓታት በኋላ ይሰበራል ዛሬ ትወጣላችሁ ተባልን። በወቅቱ አሁን የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አመራር የሆነው አርበኛ አበበ መልኬ "ኧረ ወዲያ ከጎንደር የመጣ ኃይል ካልሆነ እኔ የነ ማንችሎትን ኃይል አላምንም ወሬ ብቻ ነው" አለ። ይችን አሁንም አቤ አይክድም😁
የሆነው ሁኖ እነ ማንቼ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁን ፣ ድንጋይ እንዳትወረውሩ ፣ እንዳትንጫጬ፣ እኛ ወደ ግቢው ሳንገባ ለመውጣት እንዳትሞክሩ ብለው በቀጠሯቸው ሰዓት መጠው በአናት በአናቱ ላይ ያዘንቡት ጀመር። ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ አማራ በግፍ ከታጎረበት ከትልቁ የክልሉ ሰባታሚት ማረሚያ ቤት የአማራን ወጣት የእስር ቁልፍ ሰብረው የነፃነትን ቁልፍ አስረከቡን።
