fa
Feedback
👳🏽ባለዕዳው

👳🏽ባለዕዳው

رفتن به کانال در Telegram

ሁሉም ስለእኛ ነው ። መሆን ስለምፈልገው ፣ እንድትሆኑ ስለምፈልገው እና መሆን ስላለብን!

نمایش بیشتر
3 763
مشترکین
+424 ساعت
-47 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
በዚም አለ በዛ ሰው ደስ የሚል ነገር ነው ። ለጥቂት ጊዜያት ለተመሣሣይ ነገ ልንታገል ከመጣን አይቀር ተጋግዘንና ተዛዝነን ብናልፍ ... ሞት መምጫው አይታወቅም አይደል ? እስኪመጣ ሌላ ሞት ሆኑን ሰው ባናስጨንቅ መኖርን ባናጣብብ ። ሰው ሲደሰት ደስ አይልም ? ሰው ሲስቅ አያምርም ? ሰው ሲዋደድ አይስብም ? ለየትኛው ህይወት ነው ምንባላው ? ተውዋ ከእውነታው አንሽሽ ይህ ህይወት በጋራ እንጂ በግል አያምርም ። እስቲ እንዋደድ ..እንተሳሰብ ልንበሰብስ አይደል ? ቢያንስ ስንኖር እንኑር ።

ረሱል صلى الله عليه وسلم  እንዲህ አሉ የቂያም ቀን የእሳት ሰዎች ወደ ጀነት ይቀርባሉ፣ ያማረ መዓዛዋን ያሸታሉ ፣ ወደ ፎቆቿም ይመለከታሉ ፣አላህ ለነዋሪዎቿ ያዘጋጀውን ይመለከታሉ ። ከዛም ተጣሪ እንዲህ በማለት ይጣራል " ከጀነት አርቋቸው ከሷ ድርሻ የላቸውም" እነሱም ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ማንም ተቆጭቶ በማያውቀው መልኩ እየተቆጩ ይመለሳሉ። ጌታችን ሆይ ምናለ ይህንን ምንዳ ፣ ያዘጋጀኸውን ሳታሳየን እሳት ብታስገባን ይቀለን ነበር ይላሉ። አላህም ይላቸዋል"እሱን ፈልጌ ነው ያሳየኋቹ። ብቻችሁን ስትሆኑ በትላልቅ ወንጀል ከኔ ጋር ትዋጋላቹ፤ከሰዎች ጋር ስቶኑ በተቃራኒው ትሆናላቹ፣ ሰዎችን ፈራቹ እኔን ግን አልፈራቹኝም፣እነሱን አላቃቹ እኔን ግን አላላቃቹኝም፣ሰዎችን አፈራቹ እኔን ግን አላፈራቹኝም፣ ለሰዎች ብላቹ ወንጀል ተዋቹ ለኔ ብላቹ ግን አልተዋቹም። ዛሬ ይህንን ፀጋ ከመከልከሌ ጋር አሳማሚ ቅጣት አቀምሳቹሀለው። ©️

ሲሰዋ እንደትላንት ትዝ ይለኛል .... ግን አንድ አመት አለፈው አላህ ቀብሩን ኑር ያርግለት ።
ሲሰዋ እንደትላንት ትዝ ይለኛል .... ግን አንድ አመት አለፈው አላህ ቀብሩን ኑር ያርግለት ።

አንዳንዴ ኡማው የወከላቸው ሰዎች ያላቸው እሳቤ ሲታይ ተስፋ ያስቆርጣል ። የሆነ ቀን "ለምሳሌ 1 ሚሊየን ህዝብ ቢሞትብንም 119 ሚሊየን ያልሞተ ህዝብ አለንና እንደሰት " የሚል ሀሳብ ይዞ የሚያብራራ ሰው ( ሀላፍትና የተሰጠው ) ሰው አይቼ ብርግግ እንዳልኩ አለሁኝ ። ትላልቅ ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች በግል እሳቤያቸው ብዙሀኑን ሲያስጠቁም አይተናል.... ለወረዱ መጠቃቀሚያዎች ሲበላሉም አይተናል ። ብቻ ሲወራ የሚቀፍ ርዕስ ነውና እንተወዉ እኛው ነን የነገ ተረካቢዎቹ .. እኛው ነን ብዙ ሀላፍትና ያለብንና በዲኑም በዱንያ እንበርታ በተለይ በተለይ በዲን ... አኽላቅና ትምህርት ላይ አደራ ።

!!!
!!!

ሰው ሲደሰት ማየት የሚያመነጨው እርካታ እንዴት ያለ ውብ ነው በአላህ ። ሀቢቢ ﷺ ከሰው ሁሉ ምርጡ ማነው ተብለው ተጠየቁና በመጨረሻም " ሰዎችን ከክፋቱ የጠበቀ " አሉ ። ለሰዎች ደስታ ሰበብ የሆነስ ምን ይሆን ደረጃው ? -አለምን ከሞላው የኔነት ጭጋግ እንራቅ -ካልጠቀመኝ ምናገባኝ ከሚል አስጠሊ እሳቤ እንሽሽ - ለሰዎች በጎ መዋል ..ሰዎችን ማስደሰት የትርፍ ጊዜ ተግባር እስኪመስል ህይወት ተጨማላልቃለችና እሳቤያችንን እናፅዳ ። ህይወትን የአመታት ትግል አናድርገው በአላህ ... በቃ ሰው ሄዶ ሄዶ ሰው ነው ! አስደስቱ ተደሰቱ ኑሩ ተኗኗሩ ። ደስታችሁን በሌሎች ውብ ሰዎች ደስታ ስር ፈልጉ🤍

አንዳንዱ በሚሰራት ትንሽ ስራ ለቤተሰቡ የሚችለውን እያረገ የተረጋጋና ሰላማዊ ህይወት ይመራል .... ከፊሉ በየቀኑ ብዙ ሺዎችን እያዘዋወረ የቤተሰብነትን ጣዕም ትቶ የተቻኮለ ሀያት ይኖራል ። ልክ እንዲሁ አንዳንዱ ከእጦቱም በተጨማሪ የሰዎችን ጓዳ እያየ መብቃቃትም ደስታም አጥቶ ይኖራል ... ከፊሉ አላህ ሀብት ሰጥቶት በአግባቡ እየተጠቀመ ተረጋግቶ በደስታ ይኖራል ። ደስታና መረጋጋት በገንዘብ መጠን የሚወሰኑ ሳይሆኑ ሁሉም ለህይወት ባለው ፍልስፍና የሚገሩ ናቸው ። ዱንያ ለናንተ ምንድናት ? እሱ ነው ዋናው ነገር ።

ዜናው " -የዋጋ ግሽበቱ በዚ በዚ ፐርሰንት ጨምሯል - በዚ በዚ አካባቢ ድርቅ ተከስቶ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ህዝቦች ረሀብ ተደቅኖባቸዋል - ይህን ያክል ሰዎች ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለው እንዲህ የሚሆኑት ታግተዋል -እዚ እዚህ አካባቢ ለአመታት የቀጠለው ጦርነት ተባብሷል " ህዝቡ "- በእግሬ ሄጄ የታክሲውን ለቤተሰቤ ዳቦ ልግዛበት ? - በየት በኩል ሄጄ ቤተሰቤን ከርሀብ ልታደግ - ልጆቼን እንዴት ላስተምር መንግስት " -ግብር ጨምሩ - ጦቢያ ለአለም አርዓያ የሚሆን እድገት አስመዝግባለች - ጦቢያ ለነዋሪዎቿ ምቹና ለቱሪስቶች ተመራጭ ሆናለች - ቢሊየን መድበን የሆነ ጫካ እናለማለን " ኧረ መንግስትና ኑሮ - መንግስትና ህዝቡ አልስማማ አሉኮ .... ዱባይ እየኖሩ ነው እንዴ የሚመሩን😭

የምትጓጉለት ነገ " ድካም ፣ አለመቻል እና መገደብ'ን " የያዘ ነው ። አሁንን ለመኖር እንጣር ... ሲደክመን እንረፍ ስንሰበር ስብራታችንን እየሰነጠቅን መታመማችንን አቁመን ወደመፍትሄ እንሩጥ ።
የምትጓጉለት ነገ " ድካም ፣ አለመቻል እና መገደብ'ን " የያዘ ነው ። አሁንን ለመኖር እንጣር ... ሲደክመን እንረፍ ስንሰበር ስብራታችንን እየሰነጠቅን መታመማችንን አቁመን ወደመፍትሄ እንሩጥ ። በሉ ዛሬን እንኑር🤍

በጣም ዛልና ? ሰዎች ተስፋ እየቆረጡ አንገታቸውን ለገመድ እየሰጡ ነው .... ወጣቶች ብዙ አልመው እርምጃ ለመጀመር ሲያስቡ ተተብትበው እየወደቁ ነው ። ውስጡም ውጪውም ለውድቀት የሚጣራ አልፎም የሚጠልፍ ጩኸት ሆኖባቸው ደክሟቸዋል ። አቃጆች አቅደው አቅደው ማህበረሰቡን በማያልቅ አስከፊ አዙሪት ነክረውት ተስፋውን በየዙሩ በየከፍታና ዝቅታው እያሳሱት ነው ..... ግን ይሁን ግድ የለም ። ከአቃጆችም በላይ አቃጁ አላህ አለ አብሽሩ .... ሴራዎቻቸው ሁሉ ፈርሰው የተሻለ ነገር ይመጣል። ብቻ ታገሉ አትድከሙ....ነፍሳችሁን አበርቷት አላህ አለ.... ነገ አለ በሏት ። አብሽሩማ የልፋታችሁ ውጤት ህመም እንኳ ቢሆን አላህ ጋር ሚዛን አለው .... ጊዜው እስኪመጣ ግን ታገሱ በምትችሉት ሁሉ ታገሉ .... ጊዜው ቀርቧል ኢንሻአላህ ።

ለመኖር ስል እየነካካው ያለኋቸው ርዕሶች ሁላ ከመኖር ሲያርቁኝ ነው የማስተውለው ። አማኝ ለመሆን ስጥር ከጌታዬ መራቅ ለምን ይሰማኛል ? ለማወቅ ስጥር የውሸት ትርክት የማጎር አይነት ስሜት....ለመጠንከር ስሞክር ድካም... ለምን ? ጊዜያቶች ባለፉ ቁጥር እቺ አለም የውሸት ሹራብ እየደረበች ...የእውነትን ብርሀን እያደበዘዘች ...የመኖርን ጣዕም እያጎመዘዘች ነው ። እቺ አለም እንደነበረችው አይደለችም...መሆን እንዳለባትም አይደለችም ። ከዘመናት በፊት የተቀየሰ አዲስ መንገድ ሳይኖር አይቀርም ። ይህ መንገድ ሁሉን ነገር አሳጥቶናል ...እምነታችንን ፣ ህይወታችንን ፣ እኛነታችንን ሁሉ ነጥቆናል ። አማኝነትን በራስ ወዳድነትና በተጨቃጫቂነት ለውጦብናል...ህይወታችንን ለሌሎች በማቀበል ስለሌሎች የሚገበር ተራ የጊዜያት ጥርቅም አድርጎብናል...እኛነታችንን ለማናውቀው እና ፍፁም ደስታችንን ለሚመጠው ሌላ ነገር አሳልፎ ሰጥቶብናል ። ይህ ሌላ ነገር ግን ምንድነው ? እየኖርን ያለነው ምንድነው ? ምን እየተፈጠረ ነው ግን? ብቻ መኖር ያለብን ህይወት አለ ....ያን ህይወት ፈልገን ማግኘት አለብን ።

ሁለት ወፎች በአንድ ሽቦ አጥር ውስጥ ታስረዋል ... ወፎቹ በተጣሉ ቁጥር አሳሪው ላባቸውን ይነቅላል ። በዛ ቅፅበት መጣላታቸውን ትተው ያጉረመርማሉ ...ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደጥላቸው ይመለሳሉ አሳርያቸውም ላባቸውን መንቀል ይቀጥላል ። ከረጅም ጊዜ በኋላ የማሰሪያውን በር ከፈተላቸው ግን ... ግን አልበረሩም አላመለጡም ... አዎ ክንፍ አልነበራቸውም ። እኚህ ወፎች እኛው ነን ... እኛው ሙስሊሞች ! ሀቢቢﷺ እንዲህ ቅጡ የጠፋውን ኡማቸውን ቢያዩ እንዴት ያማቸው ይሆን ... የማንም መጫወቻ ሆኖ እርስ በርሱ ለመቶ አመታት ሲታገል የከረመውን ኡማ ቢያዩ ምን ያህል ያማቸው ይሆን ? ጠላቶቻቸው ለመቶ አመታት የሚዘልቅ ሴራ አሲረው ኢስላምን ያፈራርሳሉ የነሱ ኡመት እርስ በርስ ይፋተጋል ... ያለአላማ የርስ በርስ ትግል ራሱንና ዲኑን ያደክማል ።

ውጤት ጠባቂዎች ...... አላህ ኸይሩን ያሰማችሁ🤍

መጨረስ አልቻልኩም ማለት የፈለኩትን አላልኩም ...ቢሆንም ይሁን በቃ

በቁሙ የጊዜ ክምር ማንነቱን በከንቱነት ወዳለመኖር እንዲሄድ የፈቀደው ትውልድ ከምን ጊዜውም በላይ ለእምነቱ ተቆርቋሪ ሆኗል ¡ ሁላችንም አንድ ቁስል ተሸክመናል ..... አለመኖር። ይህን ቁስል የምናስተናግድበት ሂክማውም ...የመኖር አቅሙም የለንም ምክንያቱም አለመኖራችንን ለመርሳት ሄደን የተጠለልንበት ጥላ "ዲን" ነው ። የእምነታችንን መሠረቶች ሁሉ ከማመን በዘለለ ወደነፍሳችን አላስገባንም .... አምልኮ የምንለው ሁሉ አድካሚ ድርጊት ሆኖብን የጊዜ ክምራችንን ሁሉ በባዶነት ውስጥ እየፈረካከስን እየሞላን ነን ። ነፍሳችንን አለማችንን የምንዋጋበት አንድ ተራ መሣሪያ የሌለን ጦረኛ ነን .... ሀሳባችንን አስገዝተን ያለ አንድ መሣሪያ ከተመሣሣዬ "የሀሳብ ባርነት" ውስጥ ካለ አካል ጋር እየተዋጋን አለመኖራችንን ...ባርነታችንን የዘነጋን ። እያልኖርን ያለነውን ዲን ሽሽት ዲን ስር የተጠለልን ... መገዛት ጠንቶን ተገዢ በሚያስመስል ርዕስ ውስጥ የምንርመሰመስ አመፀኞች ። ሌት ተቀን ሰዎችን አተልቀን አላህን አሳንሰን በ አመፅ ባህር ውስጥ የምንዋኝ ግና በእምነታችን ፍፁማዊ ለመምሰል ሌላ የማስመሰል ትግል የምንታገል ወዳቂዎች ። በጌታችን ትዕዛዝ ውስጥ መኖር ጠንቶን የአለመኖርን መራራ ፅዋ እየቀመስን አለመታዘዛችንን ሽሽት ወደዲኑ ተሸጉጠን ለመርሳት የምንጥር እፍረት የለሾች ። ማነን ? ቆይ ማነን ? ቁርጭራጭ የህክምና ፅሁፎችን አንብበን ሀኪም የሆንን ? የሆነ ቦታ ስለግንባታ አንብበን ኢንጂነር የሆንን ? እስቲ ማነው በቁርጥራጭ ንባብ ዶክተር የሚጋፈጠው ? ማነው በሶስት ቀን ፖድካስት እራሱን አዋቂ አርጎ ኢንጂነር የሚከራከረው ? እስልምናና አስተምህሮቱ ከህክምና ያነሰ ቦታ ነው ያላቸው ? የእስልምና አስተምህሮት ከኢንጂነሪንግ ያነሰ ቦታ ነው ያለው ? ምነው ዲናችን ላይ ሲሆን ደረታችን አበጠ ? የኪታብ ስም የማያነበው ሁሉ ምንው አዋቂ ነኝ ብሎ ቁጭ አለ ! " ያወከውን አስተላልፍ " የሚል ሀዲስ ስላለ ነው ? እሺ ልክ ነው ግን መች አወቅን ?ለእያንዳንዱ መረጃ ወደ ሰርች ባር የሚሮጥ ሁሉ ዲን ላይ ቃዲ ይመስል ሲያከፍር ሲያሰልም ... ለዲኑ ሲታገል ሲሳደ* ይውላል ። ኧረ ምን አይነት እፍረት የለሽ ትውልድ ነን በአላህ ።

አሁን ረጅጅም ፅሁፍ ልለቅ ነው ወይ ደግሞ አጭር ። ወይ ወቀሳ ነው ወይ ሌላ ነገር ነው .... ለማን እንደምፅፍ አላቅም ለራሴ ...ለናንተ ? እንጃ ብቻ

©️©️©️ ቁድወቱና ፊል ኢብቲሳመህ ስለ ዉዱ ነብያችንﷺ ሌሊት አብዛኞቻችን እንሰማለን እንዲህ ሲባል... "ረሱል ﷺ ለሊት እግራቸው እስኪሰነጠቅ ድርስ ይቆሙ ነበር... ኡመቴም እያሉ ያለቅሱ ነበር።" በዚህ መንገድ ግን አስበነው እናውቃለን? እንደዚያ ሌሊቱን በእንባ ሚያሳልፉት ነብይﷺ ፤ ቀኑን በፈገግታ እንጂ አይታዩም ነበር። ጀሪር ኢብኑ ዓብዲላህ እንዲህ ይላል... "በሕይወቴ አንድም ቀን አላለፈም የኔው ነብዬ ﷺ ሲያዩኝ ፈገግ ያሉ ቢሆን እንጂ" በፈገግታቸው ነው ከሰው ሁሉ ልብ የገቡት። በፈገግታቸው ነው ያነባን አይን ያበሱት በፈገግታቸው ነው የሰሃባን ተስፋ ያለመለሙት ፈገግታቸው አንድ የጥሪ መንገድም ነበር። ፈገግታቸው የመሃባ መንገድም ነበር። ፈገግታቸው ብዙ ብዙ ነገር ሆኖ አልፏል። ለዚያም ነው በኛ ዉስጥም ሱና ሊሆን የቻለው ፈገግ እንበል ፣ የሰዎችን ሕይወት በፈገግታችን እናድሰው የቁድዋችን የተፈቃሪያችን ነብይ ﷺ መንገድ ነዉና ሰሉ ዓለል ሀቢብ

ሀቢቡና ﷺ እጅግ ጠንካራውና ልስልሱ ፍጡር ነበሩ ። ምድርን ከረገጡ ባለምሉዕ ስብዕና ግለሰቦች ቁንጮው ናቸው ። በነሱ መላክ ከተደረማመሰው የክህደት ተራራ ዘወር ብለን አኗኗራቸውን ብቻ ብናይ ..... ነብይ ከመሆናቸው በፊት ያለውን ረጅም ዘመናቸውን ብንቃኝ ታሪካቸው እጅግ ውብ ነው ። ሰው የመሆን ስርዓት የሚቀዳባቸው ... ሰው ሆኖ መኖር የሚኮረጅባቸው ሰው ሆነው የኖሩ መኖርን አሳምረው አለምን ያበሩ እጅግ ውቡ ሰው! ሀቢቡና ﷺ ነብይ ከመሆናቸው በፊትም ሆነ በኋላ ለፍጡር ሁሉ ሞዴል የሚሆኑ ... ለኡማቸው ኮቴያቸውን መከተል አስገዳጅ የሆኑ ድንቁ ስብዕና ናቸው ። እነሱ የስርዓት መለኪያ...የመኖር መስታወት ናቸው ። ለእያንዳንዱ የመኖር ቅያሳችን ትክክለኛ መንገዱ መምረጫችን ... ከጠፋንበት የበታችነት በረሀ የመውጫ ኮንፓሳችን ናቸው ። አደበ ቢስነት ... ንቀት ... ጨቅጫቃነት...አርቆ አለመመልከት... ትላልቅ ነገር አለማሰብ ... የመኗኗር ስርዓት አለማወቅና ሌሎች መጥፎ ባህሪዎች ሁሉ ከአለሙ ብርሀን ፍፁም ተቃራኒ የሆኑ ነገራቶች ናቸው ። አዎ ሁላችን በጎ ከሚመስለን ባህሪያችን ጋር ከሀቢባችን ፍፁም ተቃራኒ ፍጥረት ነን ። ለዲኑ የምንቆረቆርበትና ዲኑን ለመጠበቅ የምንሞክርበት መንገድ ሁሉ የነሱ ተቃራኒውና አስቀያሚው ማንነት ነው ። ሰው እንሁን ! ሰውነት ላይ ክፋት የለም ... ሰው እንሁን ! ሰውነት ላይ ጭካኔ የለም ...ሰው እንሁን ! ሰውነት ላይ በጎነት እንጂ የለም ። በመንገዳቸው አኑሮ ይግደለና 🙌

🔺
🔺

ደህና አደራችሁ?
ደህና አደራችሁ?