fa
Feedback
ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

رفتن به کانال در Telegram

ለአስተያየታችሁ @Shedorka

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

کانال ከእለታት....📖📚📖📚📖📚 (@shewitdorka) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 13 103 مشترک است و جایگاه 2 890 را در دسته کتب و رتبه 2 592 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 13 103 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 29 ژوئیه, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 280 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 19 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 26.05% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 8.39% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 3 411 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 099 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 33 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
ለአስተያየታችሁ @Shedorka

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 30 ژوئیه, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته کتب تبدیل کرده‌اند.

13 103
مشترکین
+1924 ساعت
+577 روز
+28030 روز
آرشیو پست ها
ይሄ ክረምት በቶሎ ካላለፈ ከሶስት ኤክሶቼን እንደ ብርድ ልብስ መከናነቤ የማይቀር ነው..... (ብርዱ በአንድ ብርድ ልብስ የማይቻል ሆኖብኝ ነው😁) ደህና እደሩ....

ለራሳችሁ ደግ ሆናችሁ ዋሉ እሺ💙 መልካም ቀንተ

ቅዳሜያችሁ እንዴት እያለፈ ነው....?

እንደምን አላችሁ ወዳጆቼ

Price:-2950 Available on hand 👉@magiy
Price:-2950 Available on hand 👉@magiy

ዛሬ በትክክል አንድ ዓመት ሞላሽ :: ለዓለም አንድ ዓመት ማለት 365  ቀናት ሊሆን ይችላል ለእኔ ግን እያንዳንዱ ቀን ያንቺን ትንፋሽ ያንቺን እቅፍ እየለመንኩ የሞትኩበት እና የተነሳሁበት የዘመናት ያህል የረዘመ የጨለማ ጉዞ ነበር:: ጡትሽን እያጠባሽ በደረትሽ አታብከሽ ከሰው አስበልጠሽና አኩርተሽ ያሳደግሺኝ ውዷ አያቴ.... አንቺን ካጣሁሽ ዛሬ ሙሉ አንድ አመት ሆነኝ::ያንቺ መሄድ በህወቴ ላይ የጣለው ጥላ ምን ያህል ከባድ እና ጨለማ እንደሆነ መናገር የሚችሉት ቃላት በምድር ላይ የሉም :: ሰው ሲሞት አብሮት የሚቀበረው አስክሬኑ ብቻ ሳይሆን የቀሩት ሰዎች ደስታና ተስፋ ጭምር እንደሆነ የተረዳሁት አንቺን ባጣሁበት በዚያ መርዶ ቀን ነበር :: ከአንድ ዓመት በፊት አንቺን ሳይሆን የቀበርኩት የራሴን ነፍስ... የራሴን ነገዬን ጭምር ነው :: አንቺ ከሄድሽበት ቀን ጀምሮ በውስጤ የተፈጠረው ባዶነት እንደ ገደል እያስተጋባ በየቀኑ ያደክመኛል :: ሰዎች ጊዜ ሁሉንም ይፈውሳል ይላሉ ግን ውሸታቸውን ነው :: አንድ ዓመት ሙሉ ስባባ... ስታመም በናፍቆትሽ ሲቃጠል እንጂ የዳነ አንድም የውስጤ ክፍል የለም :: ይባስ ብሎ እያንዳንዱ ቀን የድምፅሺን ዜማ.....የፊትሺን ብርሃን ያንን እቅፍሽን ይበልጥ እየናፈቀኝ ውስጤን ያደማዋል :: ደስታ ሚባለው ነገር ለኔ የውጭ ሰው ሆኖብኛል :: መሳቅ እንኩዋን ስሞክር የውስጤ ስብራት እና ጩሀት ከውስጥ ይጎትተኛል :: ብቻዬን ስሆን ማንም በሌለበት ጨለማ ክፍል ውስጥ ቁጭ ብዬ ስላንቺ ሳስብ የሚሰማኝ ተስፋ መቁረጥና ብቸኝነት የትየሌሌ ነው :: መጠጊያዬ ብቻ አልነበርሽም አንቺ ለኔ መላው አለሜ... መኖሬ... የቆምኩበት ጠንካራ መረቴ ነበርሽ :: ያንቺ መሄድ መሰረቴን አናግቶ ባዶ ሜዳ ላይ ጥሎኛል :: እንደ እናት ሆነሽ ማንም ባልረዳኝ ጊዜ የልቤን ትርታ ተረድተሽ በፍቅርሽ ስታክሚኝ የነበርሽው ውድ እመቤቴ...ዛሬ እቅፍሽን ብመኝ የሚያቅፈኝ እንባዬን ብጠርግ የሚያብስልኝ አይዞሽ ልጄ የሚለኝ አጥቼ ተንከራታች ሆኛለው :: ሕይወት ካንቺ በሁአላ ትርጉም አጥታብኛለች :: ውስጤ ተሰባብሮ ተሰነጣትቆ እንደማይገኝ ዕቃ ሆኗል :: ምንም እንኩዋን እኔ በዚህ ምድር ላይ ባዶነቴን ተሸክሜ በናፍቆትሽ እየታመምኩ ቢኖርም ያሳየሺኝ ፍቅር ግን ሁሌም ቢሆን በልቤ ውስጥ ሕያው ሆኖ ይኖራል :: ላንቺ ያለኝ ፍቅር ከሞት በላይ ጠንካራ ነው :: ፈጣሪ መፍስሽን በቅዱሳን እቂፍ በገነት ያኑርልኝ እኔ እዚህ በምድር ላይ እስክከተልሽ ድረስ ሁሌም በናፍቆትሽ በታላቅ ክብር ሳስብሽ እኖራለሁ :: ✍Betsi

"ዶሮ አማረኝ" ሲሉ ሁሉንም እንዳልሆነው ነው የምትናፍቀኝ....አለ አይደል አንድ የዶሮ ብልት በልተው እንደሚያስጠላቸው አይነት....ፈረሰኛውን በልተው መረቁን "ሽንኩርት ምን ያደርግልናል" ብለው ለኔ ቢጤ እንደሚያከፋፍሉት አይነት.... ያንተ ናፍቆትም እንዲህ ነው.... ጣዕምህም እዚህ ድረስ ነው.... እንደ ዶሮው.... ጥቅም አልባ መረቅ እንደሚበዛው ዶሮ ነው ያንተ መልክ.... ሊበሉት አሰፍስፈው እንደሰፈሩበት ቅባታማ ጥብስ....ጥቂት በልተውት ብዙ እንደሚዘጋ.... ሙሉውን አትናፍቀኝም....ጉርሻህ ብቻውን ይናፍቀኛል....በእጄ መጉረስ ሲያንገሸግሸኝ እንደናፈቅከኝ ይሰማኛል....መለስ እልና ደግሞ 'ጉርሻ ለይቶ መናፈቅ ምንድን ነው' እላለሁ.... "እሱ አልናፈቀሽም....Act of service ነው የናፈቀሽ....".....ያለችኝ ጓደኛዬን ላምናት ጫፍ እደርሳለሁ.... (ልክ ልኩን ነገርኩት😁) ✍Shewit https://t.me/shewitdorka https://t.me/shewitdorka https://t.me/shewitdorka

በእናንተ አልጨክንም..... ከደቂቃዎች በኃላ አደርሳለሁ..... (አሁን ከስራ እንደገባሁ ከግምት ውስጥ ይግባልኝ)

አሁን እኮ ለ exኤ በፅሁፍ የሆነ ነገር ማለት ፈልጌ ነበር...... "በቀጥታ ንገሪው...."....ያለችኝ ጓደኛዬ ሀሳቤን አስቀየረችኝ እና ፅሁፉ ቀረ..... ደህና እደሩ😁

Have you ever say this to yourself?
Have you ever say this to yourself?

የ self development መፅሀፍ ይፈልጋሉ እንግዲያውስ ይቀላቀሉ https://t.me/Amharic_Books_storee
የ self development መፅሀፍ ይፈልጋሉ እንግዲያውስ ይቀላቀሉ https://t.me/Amharic_Books_storee

ይሄን አጋጣሚ ያጋራሁት ቻናሌ የተከፈተ አመት ነው.... መሀል ላይ እድሜዬን ደቅ አድርጌም የለ....😁 እስቲ ከበፊትም አብራችሁኝ የነበራችሁ ተከታዮቼ go to the first message ሳትሉ እድሜዬን ስንት እንደደረሰ ከነገራችሁኝ እመርቃችኃለሁ....good luck😁

ለፈገግታ😁 Based on true story😁 ሰላም ትባላለች...አብሮ አደጌ ናት...ትናንትና በበራችን እልፍ ስትል ሲያንቀለቅለኝ መጥራት...ከዛ እሷም ሱቅ እንደተላከች እና አብረን እንድንሄድ መጠየቅ...እኔም እሺ ማለት.... ሱቅ ሳንደርስ ስልኳ ጠርቶ ማውራት ጀመረች....ችግሩ የተፈጠረው ይሄን ጊዜ ነው...ሱቁ ጋር ስንደርስ እንድናልፈው በአይኗ ምልክት ሰጠችኝ...ከስልኩ ጥሪ በፊት ወሬያችንን ስንቀድ ምን እንደተላከች አልጠየቅኳትም ነበር...በውስጤ በቃ አብዲ ሱቅ የሌለ ነገር ተልካ ይሆናል ብዬ ደመደምኩ...(በ 22 አመታችን ሱቅ የምንላክ ብርቅዬ ወጣቶች ነን በዚህ አጋጣሚ😁)....ከዛላችሁ ብንጓዝ ብንጓዝ ጀለስ ምንም አትልም... ሰፈራችን አውቶቢስ ተራ ነው...ከአስፋልቱ ገባ ብሎ....ወደ ስድስት ሱቅ አልፈን አዲሱ ሚካኤል ደረስን...አሁንም ልጅት ደዋዩ የሚያያት ይመስል እየተሽኮረመመች ታሽካካለች...ታምኑኛላችሁ ፓስተር ደረስን...አሁንም የተቀየረ ነገር የለም... ጳውሎስ ሆስፒታልን ማለፍ ስንጀምር ስልኩ ተዘጋ... "ወይኔ ቻርጅ ዘጋብኝ"....ብላ ስትበሳጭ እኔ ደግሞ "ተመስገን"  አልኩኝ... "በዚህ አያያዛችን ቡራዩ መድረሳችን ነበር...ያምሻል እንዴ ምንድን ነው ምንገዛው ይሄን ያህል...." "በቃ አብዲ ሱቅ እንሂድ...."...አለችኝ አይኔን ማየት እያፈረች.... "አብዲ ...አብዲ...የኛ አብዲ..."...ጆሮዬን ማመን አልቻልኩም....አብዲ ማለት እኮ በራችን ላይ ያለ ሱቅ ነው... "ምን መሆንሽ ነው...ያምሻል...እንዴ እሺ ለምን ስናልፈው ዝም አልሽ...እዚ ድረስ....".....የምሬን ነው የተበሳጨሁት....መልሷን ስሰማ ግን የተበሳጨሁትን ያሀል አሽካካሁ... ምን ብትል ደስ ይላችኃል....😁 "እና ስልኩን ሳልዘጋው የ 10 ብር ስኳር ልበልልሽ ደፋር..."....😂 እንደዚህ አይነት ጓደኛ አይስጥ😂😂😂😂 ✍Shewit dorka https://t.me/shewitdorka

"እንደልቤ የምሆነው አንተ ላይ ቦቻ እኮ ነው...."....አለችውና ፈገግ አለች....ጅል ነውና አብሯት ፈገገ.... እሱን ላለማክበሯ የሰጠችው ምክንያት 'እንደልቤ እሆንብሀለሁ' ነው....ፍቅር መሰለው....'ልቧ ምን የሚሉት ንቀታም ነው' አላለም....'አንተ ብቻ' መባሉ አስፈነደቀው........ ጅል! ✍Shewit

እንዴት ናችሁልኝ