ar
Feedback
ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

الذهاب إلى القناة على Telegram

ለአስተያየታችሁ @Shedorka

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

تُعد قناة ከእለታት....📖📚📖📚📖📚 (@shewitdorka) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 12 793 مشتركاً، محتلاً المرتبة 2 938 في فئة الكتب والمرتبة 2 622 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 12 793 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 27 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 248، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 15، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 20.65‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 9.65‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 2 643 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 235 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 62.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
ለአስተያየታችሁ @Shedorka

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 28 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الكتب.

12 793
المشتركون
+1524 ساعات
+937 أيام
+24830 أيام
أرشيف المشاركات
በቅንነት ልጠይቃችሁ(ቲክቶክ ላይ ሲሉ ሰምቼ ነው😁)....ለምንድን ነው ይሄን ፔጅ ሰብስክራይብ ማታደርጉት.... ፀብ ነው እንዴ የምትፈልጉት....😁 ተማምኜባችኃለሁና አታሳፍሩኝ....አንድ ሺህ እናስገባት በጣም ጠንካራ ሴት ናት💙

Order እየተቀበለች ስለሆነ ማዘዝ ትችላላችሁ

photo content
+6

Dying for someone is a moment. Living for someone is a lifetime.
Dying for someone is a moment. Living for someone is a lifetime.

አንዱ ምን ሲል ሰማውት መሰላችሁ "አስራዎቹ መጨረሻ እና ሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ ያለች ሴት ዴት አድርግ...ሴቶች በሞኝነት የሚያፈቅሩት በዚህ ጊዜ ነው...ይሄ ካለፈማ ካልኩሌትድ ነው...ተወዳድረህ ነው..."....የሚገርመው ደግሞ አንገቱን ከላይ እስከ ታች እየወዘወዘ የሚያዳምጠው ማይክ የጨበጠ ሰውዬ ነው... እንዴት እንዴት ነው ነገሩ.....'ሞኝነቷ ሳይለቃት....በቅጡ ማገናዘብ ያልጀመረችን ሴት ያዝ' ማለት እኮ በራስ አለመተማመን ነው...ፈተና የሚፈራው በደንብ ያላጠና ሰው እንደሆነው ሁሉ ውድድር የሚፈራው ያልበቃ ወንድ ነው...አውቃ አገናዝባ ከብዙዎቹ ብትመረጥ አይሻልህም.... እንደ ሀገራችን ህዝባዊ ምርጫ ከራስ ጋር ወድድር አያስጠላም....?...ሞኝነቷስ ተጣብቆባት የሚቀር ይመስልሀል....?...ለነገሩ ሞኝነቷ ሳይለቃት ሁለት ልጅ ታስታቅፋታለህ....ቆንጆ የሰነፍ ቀመር ቀምረሀል.... ፈሪ! https://t.me/shewitdorka https://t.me/shewitdorka https://t.me/shewitdorka

ይሄን ቻናል 1000 subscribers አስገባለሁ ብዬ ደረቴን ነፍቼ የተቀበልኩት ነውና እንዳታሳፍሩኝ....join በሉልኝ💙

ጦር-2 :- ከህልም ጋር ሩቅ ለሩቅ መሆን..... ጫፍ እና ጫፍ እየተያዩ እንደሚላቀሱ ወዳጆች ህልሜ እና እኔ ተላቀስን....ህልሜ እንኳን ወዳጀ ብዙ ነው መሰል እንደ እኔ በአንድ አይኑ አላለቀሰም....በአንድ አይን የተለቀሰ እምባ መራር ነው.... የፅሁፍ ቆሌ ሸሸኝ....እንኳን ለመፃፍ አይደለም የተፃፈ ለማንበብ ሰነፍኩ....መነሳት....ለታክሲ መጋፋት....ስራ ገብቶ የሰውን ህልም ማስፈፀም ሆነ ኑሮዬ....ህልሜ የተፃፈበት ሰሌዳ ላይ የሌሎች ህልም....የተመታ ፖሊሲ....አለመረጋጋት...ማሸነፍ የሌለው ሩጫ....ዙሩ የማያልቅ ማራቶን ስርዝ ድልዙን ሰራበት..... እዚኛው የጥበብ ምሽት ላይማ አልቀርም...ቆይ ይሄኛው መድረክ ላይ ማይክ ተውሼ አቀርባለሁ ብዬ ያሰመርኩበትን ሁሉ 'ከስራ አምሽተሽ ትወጫለሽ' በሚል ቀጭን ትዕዛዝ እሰርዛለሁ..... በዚህ ሁሉ ውጥረት ውስጥ የሆነ ኮሚዩኒቲ አለኝና እናንተ ጋር መጥቼ 'እኧ ሞንደል ሞንደል ትላላችሁ አይደል' ብዬ ሰላምታ ሰጥቼ እወጣለሁ...ባልተረጋጋ ጭንቅላት ለአይን የማይመጥን ፅሁፍ እንዳልፅፍ በዝምታዬ ፀናለሁ....ይሄን ዙር ለምናምነኛ ጊዜ እዞረዋለሁ..... ሸዊት ነበርኩ። https://t.me/shewitdorka https://t.me/shewitdorka https://t.me/shewitdorka

photo content
+6

ኪሴም ልቤም አልሞላ ሲል ላቃጥር መጣሁ.....እንደምን አላችሁ....? ከስንት ጦር አምልጬ እንደመጣሁ ብታውቁ መጥፋቴ ሳይሆን አለመሞቴ ያስገርማችኃል.... ለተከታታይ አምስት ቀናት የወጉኝን አምስት ጦሮች እነግራችኃለሁ....(በዚኛው ቃሌን አከብራለሁ...ከፈለጋችሁ ፈትኑኝ) ጦር-1:- ከኢንዶሚን የፈጠነ ሪሌሽን ሺፕ... እውነቱን ለመናገር ይሄ ጦር አገባቡንም አወጣጡንም ልብ አላልኩትም ነበር....ባጭሩ የሆነ ቢፕ ኮል የሚመስል እጥረት ነበረው....በስመአብ ብዬ ግንባሬ ላይ በጣቴ ያመለከትኩትን መስቀል ሳላወርድ ቀድሞኝ የወረደ አይነት ስሜት .... 'ምነው ተውከኝ'....ብሎ ለመጠየቅ የሚያሳቅቅ አይነት....አለ አይደል 'መች ያዝኩሽና' ቢለኝ ይሄን ቀን....በዚህ ደይቃ የማልለው ማይክሮ ሰከንድ.... ደሀ መሆኔ በጀኝ እንጂ ኑሮ ቢደላኝ ስለዚህ ፍቅር አስተጣጠር አምስት መቶ ፔጅ በፃፍኩ....የመጀመሪያው ገፅ ላይ 'ወይ ጉድ'....የምል ይመስለኛል....ሁለተኛው ላይ ደግሞ 'ወቸው ጉድ ስንት አይነት ሰው አለ ባካችሁ' የምል ይመስለኛል....ሶስተኛው ገፅ ላይ እናንተን ጠርቼ የማማው ይመስለኛል....በመገረምና በመደነቅ ብቻ ገፁን የምሞላው ይመስለኛል.... ያማለለኝ በመፅሀፍቶቹ ብዛት ነበር...በተሰጠችኝ አጭር ሰአት ነሆለልኩ... እንደ ስለስንት ቆነጃጅት ሴቶች አንብቦ እኔ ላይ መውደቁ አስፈነደቀኝ... ተንጠልጥሎ እንደሚቀር በምን ላውቅ እችላለሁ..... ኦሮማይ ትዝ አለኝ....እንደ ሮማን የቡና ቆሌ የሚያምርላትን ደርባባ ተመኝቶ ነበር ወይስ እንደ ፊያሜታ አፈ ቀላጤዋን....የትኛዋን እንደተመኘ ሳልደርስበት መለያያችን ደረሰ.... የሆነ ባስ አልመጣ ሲለው ዘሎ ራይድ ውስጥ እንደገባ እና ባሱ ሲመጣ ከራይዱ ተስፈንጥሮ እንደሚወርድ ደሞዝተኛ ነበር አኳሀኑ.... ለጥያቄም ለመልስም የማይመች አፈጣጠን ስለነበረው አፌን አላበላሸውም.....'በተወደደ ነዳጅ እንኳን ብዙ ነዳጅ ሳትጨርስ ወረድክልኝ' ብዬው ኑሮዬን ቀጠልኩ.... ✍ሸዊት ነበርኩ። https://t.me/shewitdorka https://t.me/shewitdorka https://t.me/shewitdorka

እዚህ ቤት የማጋራችሁ አለኝ...ልግባ ወይ...

አንተን ማጣት መልኩ ይሄ ነው....አንተ ከሄድክ ልነሳው የምችለው ብቸኛ ፎቶም ይሄ ነው...... "እንኳን እሱ ሀምሌና ነሀሴም ሄዷል..."....ይሉኛል መሄድህን ሲያለሰልሱት....አንደበታቸው እንዴት እንደሚሻክረኝ....ይቆረቁራል። 'ሀምሌ እና ነሀሴ' ሲሉህ አፋቸው ላይ ትንሽ እንኳን አይጎረብጣቸውም....መንፈቅ መስለሀቸው ነው....ዘመን መሆንህን የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ....? "ወንድ ቢሄድ ወንድ ይመጣል...."....ያሉት አንተን ነው...አይገርምም ካንጠለጠለው ጋር ሁሉ ሲያወዳድሩህ....አለማወቅ። "ከቤት መውጣት አለብሽ....እስከመቼ ተቀርቅረሽ...ድብርት በላሽ እኮ"....ይሉኛል በሌላኛው ቀን...ናፍቆትህ ቅርጥፍጥፍ አድርጎ እንደበላኝ ብነግራቸው በዚህ ልባቸው ይረዱኛል....አይኔ ላይ ስልባቦት የሰራው ምስልህን ይገፉልኛል...ካለህበት ያመጡልኛል.... ለምን ከናፍቆትህ ጋር አይተዉኝም.... ✍Shewit https://t.me/shewitdorka https://t.me/shewitdorka https://t.me/shewitdorka

photo content

photo content

ሲዋደዱ መተጣጣት ይህ እኮ ነው ክፉ ቅጣት..... ያለወቅቱ አግኝተኃኝ በስህተት አመለጥከኝ

"ምነው, ምነው ሆዴን ሆድ ባይብሰው ምን ያረጋል እኔም የሰው አንቺም የሰው" ከዳዊት መለሰ ዘፈኖችን ልብ ብዬ መስማት የጀመርኩበት ጊዜ ነው....ምን ጉድ ነው🤌

“....ጃዝ....ወይን...አሌክስ  አብርሀም....ክረምት.....ዝናብ....አንተ...እቅፍህ...ልብህ.....ፈገግታህ...ድርብ  ጥርስህ.....”……እሱ ጋ ምን አለ ላሉት መልሴ ነበረ። ✍Shewit

photo content

photo content
+1

እኔ ምለው ከአስራ ሁለት ሺህ ተከታዮቼ ፅሁፉን የሚያዩት ግፋ ቢል ሁለት ሺዎቹ ናቸው..... አስር ሺው ሰው ሞቶ ነው ወይ....😁?

በአንድ ፎቶ 2 ፅሁፍ የመፃፉ ቻሌንጅ ከተመቻችሁ ነገም ይቀጥላል.... ደህና እደሩ።