fa
Feedback
ሲግማ ሀበሻ | 𝚂𝙸𝙶𝙼𝙰 𝙷𝙰𝙱𝙴𝚂𝙷𝙰

ሲግማ ሀበሻ | 𝚂𝙸𝙶𝙼𝙰 𝙷𝙰𝙱𝙴𝚂𝙷𝙰

رفتن به کانال در Telegram

ይሄ የኢትዮጵያ የሲግማ ቻናል ነው Tiktok : tiktok.com/@sigmahabesha_official Owner : @Ethmemnon Co-Owner : @Birukx23 Buy ads: https://telega.io/c/Ethio_Sigmas

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام ሲግማ ሀበሻ | 𝚂𝙸𝙶𝙼𝙰 𝙷𝙰𝙱𝙴𝚂𝙷𝙰

کانال ሲግማ ሀበሻ | 𝚂𝙸𝙶𝙼𝙰 𝙷𝙰𝙱𝙴𝚂𝙷𝙰 (@ethio_sigmas) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 55 569 مشترک است و جایگاه 868 را در دسته تجارت و رتبه 574 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 55 569 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 22 ژوئیه, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -1 363 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -57 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 7.25% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 3.08% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 031 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 710 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 67 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
ይሄ የኢትዮጵያ የሲግማ ቻናል ነው Tiktok : tiktok.com/@sigmahabesha_official Owner : @Ethmemnon Co-Owner : @Birukx23 Buy ads: https://telega.io/c/Ethio_Sigmas

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 23 ژوئیه, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته تجارت تبدیل کرده‌اند.

55 569
مشترکین
-5724 ساعت
-3277 روز
-1 36330 روز
آرشیو پست ها
+1
ትልቁ ጠላትህ ሌላ ሰው ወይም ሁኔታ ሳይሆን፣ የራስህ ያልተፈቱ ፍርሃቶችና እምነቶች ሊሆኑ ይችላሉ። እነሱን ስትገነዘብና ስትለውጥ፣ ሕይወትህም ይለወጣል። ይህ መጽሐፍ ለራስ እድገት፣ ስሜታዊ ጤና እና እራስን ለማሻሻል ፍላጎት ላላቸው አንባቢዎች በጣም ተቃሚ መፅሀፍ ነው። እኛም ይህንን መፅሀፍ በትልጉም ጭምር ለቀንላችሀል! 📲 @Ethio_Sigmas 📲 @Ethio_Sigmas

መፅሀፍ በትርጉም እና English የምትፈልጉ 90+ react

The Mountain Is You አንዳንድ ጊዜ ስኬትን እንፈልጋለን፣ ነገር ግን በፍርሃት፣ በድሮ ልምዶች ወይም በራሳችን ላይ ባለ አሉታዊ እምነት ምክንያት ራሳችንን እናግዳለን። ለምሳሌ፣ "አልችልም"
The Mountain Is You አንዳንድ ጊዜ ስኬትን እንፈልጋለን፣ ነገር ግን በፍርሃት፣ በድሮ ልምዶች ወይም በራሳችን ላይ ባለ አሉታዊ እምነት ምክንያት ራሳችንን እናግዳለን። ለምሳሌ፣ "አልችልም"፣ "እኔ ለዚህ አልተፈጠርኩም" የሚሉ አስተሳሰቦች ሰውን ወደ ኋላ ይጎትታሉ። ደራሲዋ እነዚህን እምነቶች በአዳዲስ እና በጤናማ አስተሳሰቦች መተካት እንዳለብን ታብራራለች። ስሜቶቻችንን ከመሸሽ ይልቅ መረዳት እንዳለብን ትነግራናለች ። ሀዘን፣ ፍርሃት ወይም ቁጣ ሲሰማን እነዚህን ስሜቶች መደበቅ ሳይሆን ምን እንደሚያስተምሩን መጠየቅ አለብን። እነዚህ ስሜቶች ብዙ ጊዜ ለመፈወስ ወይም ለመለወጥ የሚያስፈልገንን ነገር ያሳያሉ። ደራሲዋ እውነተኛ ለውጥ በአንድ ሌሊት እንደማይመጣ ታስገነዝባለች። በየቀኑ የምናደርጋቸው ትናንሽ ውሳኔዎች፣ ልምዶች እና እርምጃዎች በጊዜ ሂደት ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ። ስለዚህ ራሳችንን መቀየር ማለት ፍጹም ሰው መሆን ሳይሆን፣ በየቀኑ ከትናንት የተሻለ ሰው ለመሆን መጣር ነው። 📲 @Ethio_Sigmas

ሀላፊነቱን ውሰድ! ለውጥ መጀመር የሚፈልግ ሁሉ ስለ ራሱ ህይወት ሀላፊነት ይውሰድ! ከተለወጥኩ በራሴ ጥንካሬ ነው፤ ቆሜ ከቀረውም በራሴ ጥፋት ነው በልና መቀየር የምትችላቸው ነገሮች ላይ ትኩረትህንና
ሀላፊነቱን ውሰድ! ለውጥ መጀመር የሚፈልግ ሁሉ ስለ ራሱ ህይወት ሀላፊነት ይውሰድ! ከተለወጥኩ በራሴ ጥንካሬ ነው፤ ቆሜ ከቀረውም በራሴ ጥፋት ነው በልና መቀየር የምትችላቸው ነገሮች ላይ ትኩረትህንና ጉልበትህን አሳርፍ። ወዳጄ አንተ ብቻ ቆርጠህ ወደ ተግባር ግባ እንጂ የማይቀየር ነገር የለም! 📲 @Ethio_Sigmas

እንዴት አደገኛ መሆን ትችላለህ: 1, ብቻህን መሆንን ተማር -ሁልጊዜ የሚከበረው ሰው በሰዎች የተከበበ ሰው ሳይሆን ለብቻው ጠንካራ የሆነ ሰው ነው። -ለብቻህ ተንቀሳቅስ -ብቻህን caffe ተቀመጥ በራስ መተማመንህም ይጨምራል, ሰዎችም ላንተ ትልቅ value ይሰጣሉ፣ እናም አብዛኛዎቹ ካንተ ጋር መሆን ይፈለጋሉ 2, ስሜትህን ተቆጣጠር -ለሌሎች ወደ ስሜታቸው እንዲጎትቱህ በፍፁም አትፍቀድ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መረጋጋትን ተማር። 3, በመስመሮቹ መካከል ማንበብን ተማር -የሚባለውን ብቻ አትስማ ለምን እንደተባለ እራስህን ጠይቅ፣ በጥሞና በማዳመጥ ብቻ የሰዎችን ፍላጎት ማወቅ ትችላለህ። ወንድ አትምሰል ሁን እንጂ 😈 📲 @Ethio_Sigmas

Benefits of Early Rising (Waking Up Early) Waking up early has numerous advantages for physical health, mental well-being, productivity, and overall quality of life. Here are the key benefits: 1. Increased Productivity - Early risers have more uninterrupted time to plan their day. - The quiet morning hours allow for better focus on important tasks. 2. Better Mental Health - Reduces stress and anxiety by providing a calm start to the day. - Exposure to morning sunlight boosts serotonin, improving mood. 3. Improved Sleep Quality** - Aligns with the body’s natural circadian rhythm, leading to deeper, more restful sleep. - Helps regulate sleep patterns, preventing insomnia. 4. Enhanced Physical Health - More time for morning exercise, boosting energy and metabolism. - Lowers risks of heart disease, diabetes, and obesity. 5. Healthier Eating Habits - Early risers tend to eat a nutritious breakfast, improving metabolism. - Reduces late-night snacking and junk food cravings. 6. More Time for Self-Improvement - Extra morning hours can be used for reading, meditation, or learning new skills. - Helps in setting and achieving personal goals. 7. Better Decision-Making - A fresh mind in the morning improves focus and critical thinking. - Reduces rushed decisions made under stress later in the day. 8. Connection with Nature - Enjoying the sunrise, fresh air, and birdsong enhances relaxation. - Boosts creativity and inspiration. 9. Builds Discipline & Consistency - Develops a strong routine, leading to success in other areas of life. - Strengthens willpower and self-control. 10. Positive Start to the Day - Beginning the day peacefully sets a positive tone for the rest of the day. - Reduces procrastination and increases motivation. ወንድ አትምሰል ሁን እንጂ 😈 📲 @Ethio_Sigmas

አንድ አባት ለልጁ እንዲህ አለው ልጄ ውስጤ አንድ ጥሩና መጥፎ ውሻ ይጣላሉ አለው ልጅም ግን ማን የሚያሸንፍ ይመስልሀል አለው አባትም አብዝቼ የመገብኩት ብሎ መለሰለት ሁሌም አብዝተን ያሰብነውና ቦታ
አንድ አባት ለልጁ እንዲህ አለው ልጄ ውስጤ አንድ ጥሩና መጥፎ ውሻ ይጣላሉ አለው ልጅም ግን ማን የሚያሸንፍ ይመስልሀል አለው አባትም አብዝቼ የመገብኩት ብሎ መለሰለት ሁሌም አብዝተን ያሰብነውና ቦታ የሰጠነው ሀሳብ ያሸንፋል። ወንድ አትምሰል ሁን እንጂ 😈 📲 @Ethio_Sigmas

የሰው ልጅ ትልቁ ፍርሀት በህይወት መኖር በራሱ ትልቅ ፍርሃት ነው። ትልቁ ፍርሃት ሞት አይደለም፤ በሕይወት የመኖርን አደጋ (risk) መጋፈጥ እንጂ፡፡ የሰው ልጅ ትልቁ ፍርሀት እራሱን የመሆን ፍርሃ
የሰው ልጅ ትልቁ ፍርሀት በህይወት መኖር በራሱ ትልቅ ፍርሃት ነው። ትልቁ ፍርሃት ሞት አይደለም፤ በሕይወት የመኖርን አደጋ (risk) መጋፈጥ እንጂ፡፡ የሰው ልጅ ትልቁ ፍርሀት እራሱን የመሆን ፍርሃት ነው። ከልጅነታችን ጀምረን የተማርነው የሌሎች ሰዎችን ፍላጎት ለማሟላት መኖርን ነው። ተቀባይነት ማጣትን እና በሌሎች አይን በቂ ሆኖ አለመታየትን አምርረን ስለምንጠላ፣ በሌሎች ሰዎች አመለካከት ታስረን መኖር እጣ ፈንታችን ሆኗል፡፡ ትልቁን ፍርሀት ለማስወገድ ደግሞ የሕይወት ፍልስፍና መጽሐፍ ይረዳናል። ከ ሕይወት ፍልስፍና መጽሐፍ የተወሰደ ወንድ አትምሰል ሁን እንጂ 😈 📲 @Ethio_Sigmas

ከሜሲ ይህን ተማር! ታላቁ አሰልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ በአንድ ወቅት ስለምን ሜሲ በጫወታ ውስጥ ብዙ እንደማይሮጥ ተጠይቆ የመለሰው መልስ ነበር። ፊት ለፊቱ የተከፈተን አንድ የጫወታ ቪዲዮን እየተመለከተም
ከሜሲ ይህን ተማር! ታላቁ አሰልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ በአንድ ወቅት ስለምን ሜሲ በጫወታ ውስጥ ብዙ እንደማይሮጥ ተጠይቆ የመለሰው መልስ ነበር። ፊት ለፊቱ የተከፈተን አንድ የጫወታ ቪዲዮን እየተመለከተም ፔፔ መናገር ጀመረ - "አያችሁት በቀስታ እየተራመደ ነው... አይሮጥም በቃ አብዛኛውን ሰዓቱን በመራመድ ያሳልፋል። ከጫወታው ውጪ አይደለም፣ ጨዋታውን በአይኖቹ እየተከታተለ ነው። ቀጣይ ምን እንደሚከሰት ያውቃል። አይኖቹን ከግራ ወደ ቀኝ ከላይ ወደ ታች ያንከራታቸዋል። ጭንቅላቱ መንቀሳቀሱን አላቆመም፣ ከግራ ወደ ቀኝ ይመለከታል። "እየሮጠ አይደለም። ሆኖም ምን እየተከሰተ እንደሆነ በአስተውሎ ይመለከታል። አራቱ ተከላካዮች ላይ ያለው ድክመት ምን እንደሆነ ያነፈንፋል። ከአምስት ወይም አስር ደቂቃዎች በኋላ፣ ሁሉንም ሁኔታ በአእምሮው መዝግቦ ይጨርሳል። ምን ማድረግ እንዳለበት፣ ወዴት መሄድ እንዳለበት በአእምሮው ሰርቶ ጨርሷል። ልክ በጫካ ውስጥ እንዳለ ሁሉ እንዴት ማምለጥ እንዳለበት ያስባል። በዚህ ጋር ብሮጥ ይህ ይሆናል የሚለውን ቀድሞ አውቋልና በቀላሉ ማጥቃት ይችላል። ማንምም አይዘውም።" ከሜሲ ምን ትማራለህ? አንተም በህይወትህ ውስጥ ያሉትን ችግሮች በአስተውሎት ተመልከት፤ ችግሩና ክፍተቱ ምን ጋ እንደሆነ አነፍንፍ፤ ሁሉንም ክፍተት በደንብ ቃኝ፡፡ ምን ማድረግ እንዳለብህና ወዴት መሄድ እንዳለብህ በአእምሮህ ሰርተህ ጨርስ፡፡ ቀጣዩ ታሪክ ነው- ተግባራዊ በማድረግ ማጥቃት ብቻ ነው! ወንድ አትምሰል ሁን እንጂ 😈 📲 @Ethio_Sigmas

ተነስና አድርገው! አሁን ልረፍደህ ብትተኛ ወይ ስፖርቱን ለዛሬ ቢያልፍህ በዛው ቅፅበት ደስ ሊሰኝህ ይችላል፤ ግን መጨረሻው የማያመር ጊዜያዊ ደስታ ምን ያርግልሃል? በጠዋት መነሳት በጣም ያስጠላል ፤
ተነስና አድርገው! አሁን ልረፍደህ ብትተኛ ወይ ስፖርቱን ለዛሬ ቢያልፍህ በዛው ቅፅበት ደስ ሊሰኝህ ይችላል፤ ግን መጨረሻው የማያመር ጊዜያዊ ደስታ ምን ያርግልሃል? በጠዋት መነሳት በጣም ያስጠላል ፤ ግን ለስኬትህ ፣ ለውጤታማ ቀን መሰረት ይሆንሀል ። ስፖርቱንም፣ ስራውንም፣ ማንበቡንም፣ መማሩንም ልትጀምረው ስትል ሊደብርህ ይችላል ግን ማረግ አለብህ ለህልምህ ስትል አሁኑኑ ደስ ይበለኝ የሚለው ስሜት ሰነፍ ነው የሚያሰርግህ! ጊዜያዊ ደስታ ከጉዞህ ያስቀርሀል ወዳጄ ማረግ የለብህን አሁኑኑ ተነስና አድርገው! ወንድ አትምሰል ሁን እንጂ 😈 📲 @Ethio_Sigmas

የ David Goggins የሕይወት ታሪክ ትግል(መከራን ማሸነፍ) David Goggins ያደገው በአባቱ ከፍተኛ በሆነ ስቃይ እና ችግር እየደረሰበት ቆይቶ ነበር። ይህም ደሞ፣በራሱ ያለመተማመን ሁኔታ
የ David Goggins የሕይወት ታሪክ ትግል(መከራን ማሸነፍ) David Goggins ያደገው በአባቱ ከፍተኛ በሆነ ስቃይ እና ችግር እየደረሰበት ቆይቶ ነበር።  ይህም ደሞ፣በራሱ ያለመተማመን ሁኔታ ውስጥ ገባ።  በወጣትነት ዕድሜው ከመጠን በላይ ክብደት መጨመር እና በጭንቀት ውስጥ እንዲቆይ ተገዶ ነበር።
በ 24 ዓመቱ ወደ 300 ኪሎ ግራም ይመዝናል እና እራሱን እንደ ውድቀት ተመለከተ።
አንድ ቀን David ስለ Navy SEALs ዘጋቢ ፊልም አይቶ ህይወቱን ለመለወጥ ወሰነ(Seal የባሕር፣ የአየር እና የመሬት ቡድኖች በUSA ውስጥ የሚገኙ ልዩ ኦፕሬሽን ኃይል ናቸው።  ባልተለመደ ጦርነት፣ ፀረ ሽብርተኝነት፣ ቀጥተኛ እርምጃ እና በልዩ ስለላ የተካኑ ከፍተኛ የሰለጠኑ ተዋጊዎች ናቸው) ታዲያ ያኔ ነበር በሶስት ወራት ውስጥ ከ100 ኪሎ ግራም በላይ ጭካኔ በተሞላበት ስልጠና ኪሎውን ሊቀንስ ችላል። ሶስት የሲኦል ሳምንታትን (ማለትም የSEAL ስልጠና በጣም አስቸጋሪውን ምዕራፍ) ተቋቁሟል። በጉዳት ምክንያት ሁለት ጊዜ ወድቋል ነገር ግን አላቆመም።ሊታሰብ በማይችል ህመም ውስጥ ቀጠለ። ወንድ አትምሰል ሁን እንጂ 😈 📲 @Ethio_Sigmas

አለም መጥፎም ጥሩም ጎን አላት ሁሉም ጥሩ ነገር ከጎኑ መጥፎ ሁሉም መጥፎ ነገር ከጎኑ ጥሩ ነገር አለው አለም አስቀያሚ ነች ህይወት አሰልቺ ነው አለም ውብ ነች ህይወት ደግሞ ጣፋጭ በብዙ ጥሩ ነገሮ
አለም መጥፎም ጥሩም ጎን አላት ሁሉም ጥሩ ነገር ከጎኑ መጥፎ ሁሉም መጥፎ ነገር ከጎኑ ጥሩ ነገር አለው አለም አስቀያሚ ነች ህይወት አሰልቺ ነው አለም ውብ ነች ህይወት ደግሞ ጣፋጭ በብዙ ጥሩ ነገሮች በብዙ መጥፎ ነገሮች የተሞላች ነች በየት በኩል ታያታለህ በጥሩ ጊዜ ብቻ አይደለም ስለ ህይወት ጣፋጭነት ጥሩነት ማሰብ ያለብህ ህይወት ጥሩ ስትሆን ህይወት ደስ ይላል ህይወት መጥፎ ስትሆን ህይወት መረረኝ አትበል ጥሩ ስትሆን ያጥሩ ጊዜ ማጣጣም መጥፎ ስትሆን የህይወት አንድ አካል መሆኑን አውቀህ ያመጥፎ ነገር ሊያስተምርህ የፈለገውን ነገር ተምረህ ማለፍ ነው የጥሩን ጥሩን ነገርማ ማንም መፈለግ አያቅተውም ማንም የጥሩን ነገር ጥሩነት ማየት አያቅተውም እውነተኛ ጠቢብነት የጥሩን ነገር ጥሩነት ብቻ ሳይሆን የመጥፎ ነገር ጥሩነትንም ማየት ነው ........ ወንድ አትምሰል ሁን እንጂ 😈 📲 @Ethio_Sigmas

እምቢ ማለትን ተማር!! ጠቃሚ ላልሆነ ነገር ይሁንታህን በምትገልጽ ጊዜ ሁሉ ጠቃሚ ለሆነ ነገር እምቢተኛ ትሆናለህ፡፡ ‹‹እሺ›› ብቻ ከአፋቸው የሚወጣ ሰዎች ታላቅ የሆነ ነገር ሊፈጽሙ አይችሉም፡፡ ‹
እምቢ ማለትን ተማር!! ጠቃሚ ላልሆነ ነገር ይሁንታህን በምትገልጽ ጊዜ ሁሉ ጠቃሚ ለሆነ ነገር እምቢተኛ ትሆናለህ፡፡ ‹‹እሺ›› ብቻ ከአፋቸው የሚወጣ ሰዎች ታላቅ የሆነ ነገር ሊፈጽሙ አይችሉም፡፡ ‹‹እምቢ!›› ማለት ታላቅ እሴት ነው፡፡ ለሀሜተኛ ሰው ፊት አትስጥ፡፡ በሥራ ቦታ አሉታዊ መንፈስና ጨለምተኛነት እንዲሰፍን ከሚፈልግ ባልደረባ ጋር አትወዳጅ። በሕልሞችህ ከሚሳላቅና ራስህን እንድትጠራጠር ከሚያደርግህ ዘመድህ ራቅ፡፡ የሥራ ጊዜህን ከሚያጣብቡ የማህበራዊ ሕይወት ግዴታዎች ተቆጠብ፡፡ ለሁሉም ሰው ሁሉንም ነገር ልትሆን አትችልም፡፡ ከእኛ መካከል ምርጥ የሆኑት ይህን ያውቁታል፡፡ ለምን ቅድሚያ መስጠት እንዳለብህ እወቅ። ግቦችህን እወቅ፡፡ ሕይወትህን በአግባቡ ለመምራት በመጪዎቹ ሳምንታት፣ ወራትና ዓመታት ምን ማድረግ እንደሚኖርብህ በሚገባ እወቅ፡፡ ከዚያ ውጭ ለሆነው ለተቀረው ነገር ሁሉ ‹‹እምቢ!» በል። እርግጥ ነው በእምቢተኛነትህ በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ቅሬታ ሊሰማቸው ይችላል። ነገር ግን ሕይወትህን ለመምራት የምትሮጠው ለሌሎች ፈቃድ ተገዢ ሆነህ ነውን ወይስ የራስህን እውነትና ሕልም ተከትለህ? ወንድ አትምሰል ሁን እንጂ 😈 📲 @Ethio_Sigmas

ሰባት ምርጥ ትምህርቶች ከ የአመራር ጥበብ መፅሀፍ 1, ራስህን ምራ ስኬት አጣሁ፣ ሀብት ራቀኝ የምትለው ወዳጄ የብዙ ችግሮችህ ምንጭ ራስህን በትክክልና በአግባቡ መምራት አለመቻልህ እንደሆነ ብነግርህስ?! በእንዝላልነት አትኑር፣ በስሜቶችህ አትመራ፣ በሰዎች ሐሳብ እንደ እንስሳ አትነዳ። ጨክን፤ ራስህን ልክ እንደ ወታደር በዲሲፕሊን ምራው! ለጊዜያዊ እርካታ እጅ አትስጥ!! መሪ ነህ፣ የራስህ መሪ ነህ እንጂ ተመሪ ባሪያው አይደለህም! 2, ቤተሰብህን ምራ! የቤተሰብህ ሰላምና ስኬት በአንተ በመሪው እጅ ነው። ለሚስትህ ምን ዓይነት ባል፥ ለልጆችህ ምን ዓይነት አባት ነህ? ቤተሰብህ ተለይቶ የሚታወቀው በሰላም፣ በፍቅር፣ በሐብት ነው ወይስ በጸብና በድህነት? አሁን ቤተሰብህ ያለበት ሁኔታ ያንተን የመምራት አቅም ያመለክታል። ቤተሰብን መምራት ሀገርን እንደ መምራት ነው፤ ምክንያቱም ቤተሰብ ሀገር ነውና! 3, ድርጅትህን ምራ! መሪ ማለት መንገዱን የሚያውቅ፣ በሚያውቀው መንገድ የሚጓዝ፣ የተጓዘበትን ለሌሎች የሚያሳይ ነው ይባላል። ድርጅትህ የአንተ ሌላ መልክ ነው። አንተ ከወደቅክ፣ ድርጅትህ ይወድቃል። አንተ እንደ ንስር ከፍ ካልክ ድርጅትህም ከፍ ይላል። ለሰራተኞችህ እንደ አባት የሚመክር፣ እንደ እናት የሚራራ፣ እንደ ወንድም የሚጠብቅ፣ እንደ እህት የሚንከባከብ፣ እንደ ኃላፊ ሰርቶ የሚያሳይ መሪ እንጂ— በአፉ የሚመርዝ፣ በትዕዛዙ የሚያስደነግጥ ክፉ አለቃ አትሁንባቸው። ድርጅትህን እንደ ድርጅታቸው እንዲያዩ እንጂ ለባዳ እንደሚለፉእንዲሰማቸው አታድርጋቸው። 4, አካባቢህን ምራ አካባቢህን ምራው እንጂ በእሱ ልክ ሆነህ አትገኝለት። በሰዎች ከንቱ  ሐሳብ፣ በዘልማዳዊ አስተያየት አትደንግጥ፣ አትወሰን። ሁልጊዜም በሐሳብና በስራ የሚመራ ባለራእይና ደፋር ሆነህ ተገኝ። 5, ተከታዮችህን ምራ ተከታዮችህ ነገ እንዳንተ የሚሆኑ ልጆችህ ማለት ናቸው። ለልጆችህ ትልቅ ምሳሌ መሆን እንደሚጠበቅብህ ሁሉ፣ ለተከታዮችህም ግዴታ አለብህ። መሪነትህ እንደ ታላቅ ወንድም ይሁን። ሰርተህ አሳያቸው፤ ሲያጠፉ ምከራቸው፤ ሲናገሩ ስማቸው። ተከታዮችህን ምራ፣ ተከታዮችህን አፍራ! 6, ሀገርህን ምራ በሀሳብ፣ በተግባር፣ በእውቀትና በጥበብ ሁሉ ሀገርህን ምራ እንጂ በሀገርህ ሁኔታ አትመራ። ፍጥነትህ በዓለም እርምጃ ልክ እንጂ ባለህበት ቦታና ሀገር ብቻ አይወሰን። ሀገር የመሪ ያለህ እያለች ነው። አንተ እንድትመራት፣ እንድታስተዳድራት፣ ታላቅ ነገርን እንድትሰጣት ትፈልጋለች። ሀገር የምትመራህ ብቻ ሳይሆን አንተም ሀገርን የምትመራ ሁን! 7, ዘመንህን ምራ! ዘመኑን የሚቀርጽ እንጂ ዘመኑ የሚቀርጸው አትሁን። ዘመንን የሚመሩት፣ መልክ የሚሰጡት ጥቂት መሪዎች ናቸው። አንተ ከእነዛ መሐል ለመሆን ምን ያግድሃል? ምንም አያግድህም!! ማሰብ ትችላለህ፣ መስራት ትችላለህ፣ መፍጠር ትችላለህ። ✍️ደራሲ : የጆን ሲ.ማክስዌል 📙ዕርስ : LAWS OF LEADERSHIP ወንድ አትምሰል ሁን እንጂ 😈 📲 @Ethio_Sigmas

በእድሜህ መጨረሻ የምትረዳቸው ነገሮች:- 1.ህይወትህን የመቀየር ኃላፊነት ያንተ እንደነበረ 2.የሆነ ጊዜ ምን ይለኛል ብለህ የፈራሃቸው ሰዎች አሁን ከጎንህ እንደሌሉ 3.በሙሉ አቅምህ ብትኖር ህይወት
በእድሜህ መጨረሻ የምትረዳቸው ነገሮች:- 1.ህይወትህን የመቀየር ኃላፊነት ያንተ እንደነበረ 2.የሆነ ጊዜ ምን ይለኛል ብለህ የፈራሃቸው ሰዎች አሁን ከጎንህ እንደሌሉ 3.በሙሉ አቅምህ ብትኖር ህይወትህ ምን ሊመስል እንደሚችል ማሰብ ትጀምራለህ 4.ሁሉም ደስታ ስኬት ውስጥ ሳይሆን እያንዳንዱ የህይወትህ መንገድ ላይ እንደነበር 5.ለጤናህ ትኩረት መስጠት እንደነበረብህ ይገባሃል 6.እናትና አባትህ ምን ያህል ይሳሱልህ እንደነበር ይገባሃል -ሳይረፍድ በጊዜ እያንዳንዱን ቀን በሙሉ አቅም፣ ፍቅር፣ ተስፋ፣ ትኩረት ኑር። ወንድ አትምሰል ሁን እንጂ 😈 📲 @Ethio_Sigmas

ማን ነው ትክክል ከሚለው በላይ ምንድን ነው ትክክል የሚለው ጠቃሚ ነው! —Aldous Huxley
📲 @Ethio_Sigmas

ዲሲፕሊን በግብ እና በስኬት መካከል የሚገኝ ድልድይ ነው! — Jim Ron — 📲 @Ethio_Sigmas
ዲሲፕሊን በግብ እና በስኬት መካከል የሚገኝ ድልድይ ነው! — Jim Ron —
📲 @Ethio_Sigmas

ከሰው ጋር በሰላም ለመኖር፣ ከራሳችን ጋር ሰላም ለመፍጠር፣ በስኬት ጎዳና ላይ ወደ ፊት ለመገስገስ የሚረዱ ሰባት የህይወት ህጎችን እንሆ :- 1.ከትላንትህ ጋር ሰላም ፍጠር፤ አሁንህን እንዳይረብሽ።
ከሰው ጋር በሰላም ለመኖር፣ ከራሳችን ጋር ሰላም ለመፍጠር፣ በስኬት ጎዳና ላይ ወደ ፊት ለመገስገስ የሚረዱ ሰባት የህይወት ህጎችን እንሆ :- 1.ከትላንትህ ጋር ሰላም ፍጠር፤ አሁንህን እንዳይረብሽ። 2. ሌሎች ሰዎች በአንተ ዙሪያ ስላላቸው ሀሳብ ያንተ ሀላፊነት አይደለም። 3. ጊዜ ማይሽረው ቁስል የለም። 4. ደስታ በማንም እጅ ላይ አይደለችም፤ በአንተ እጅ እንጂ። 5. እራስህን ከሌሎች ጋር አታነጻጽር፤ ሰዎች ላይም አትፍረድ፤ ያለፉበትን የህይወት ውጣ ውረድ አንተ አታውቅም። 6. አብዝተህ መጨነቅህን አቁም፤ ለጥያቄዎች ሁሉ መልስ ሊኖርህ አይጠበቅብህም። 7. ፈገግ በል በዓለም ላይ ያለው ችግር በሙሉ ያንተ አይደለም።
📲 @Ethio_Sigmas

ያላመናችሁብኝን ሰዎች ሁሉ አመሰግናለሁ! የUS Open በመባል የታወቀውን የመሬት ላይ ቴኒስ ጨዋታ በማሸነፍ ዋንጫን የተረከበችው የመጀመሪያዋ የ19 ዓመት ወጣት ኮኮ (Coco Gauff) ነች፡፡ ይህ
ያላመናችሁብኝን ሰዎች ሁሉ አመሰግናለሁ! የUS Open በመባል የታወቀውን የመሬት ላይ ቴኒስ ጨዋታ በማሸነፍ ዋንጫን የተረከበችው የመጀመሪያዋ የ19 ዓመት ወጣት ኮኮ (Coco Gauff) ነች፡፡ ይህን ጨዋታ ሙሉ ለሙሉ ተከታትየዋለሁ፡፡ ይህች ወጣት አስገራሚ ብቃቷን የገለጸችበት ጨዋታ ነበር፡፡ ከሁሉም ነገር አስራሚ ሆኖ ያገኘሁት ግን ጨዋታውን ካሸነፈች በኋላ በነበራት ቃለ-መጠይቅ ላይ ባደረገችው ንግግር ላይ የሰነዘረችው አንድ ሃሳብ ነው፡፡ “ይህንን ውድድር እንደማሸንፍ ያላመናችሁብኝን ሰዎች ሁሉ አመሰግናለሁ” አለች በንግግሯ መካከል፡፡ ይህንን ያለችው እነሱ አትችልም ብለው ስላሰቡና እንደምታሸንፍ ያለማመናቸው ሁኔታ የበለጠ ውስጧን እንዳነሳሳውና ለማሸነፍ ቁርጠኛ እንድትሆን እንዳበረታት ለመግለጽ ነው፡፡ በማንነታችሁና በችሎታችሁ ያላመኑባችሁ ሰዎች አትችሉም በማለት የሚያወሩትን ወሬ ለመድከም ሳይሆን ለመበርታት፣ ለማቆም ሳይሆን ለመቀጠል፣ ለመሸነፍ ሳይሆን ለማሸነፍ፣ ወደኋላ ለመቅረት ሳይሆን ወደፊት ለመገስገስ . . . ተጠቅማችሁ ያሰባችሁበት ጋር ስትደርሱ ዛሬ ያላመኑባችሁን ሰዎች ለማመስገን ያብቃችሁ!!! መልካም ቀን ይሁንላቹ ከፈጣሪ ጋር
📲 @Ethio_Sigmas