ሳይኮሎጂ | Psychology
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 ሳይኮሎጂ | Psychology 的分析概览
频道 ሳይኮሎጂ | Psychology (@psychologycentral) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 61 104 名订阅者,在 商业 类别中位列第 762,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 541 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 61 104 名订阅者。
根据 16 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -211,过去 24 小时变化为 -47,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 9.35%。内容发布后 24 小时内通常能获得 5.55% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 718 次浏览,首日通常累积 3 396 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 55。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“በየቀኑ ስለ Psychology የሚለቀቅበት ቻናል ነው!
Owner : @BirukXL”
凭借高频更新(最新数据采集于 17 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 商业 类别中的关键影响点。
61 104
订阅者
-4724 小时
-1737 天
-21130 天
帖子存档
61 134
ለጓደኝነት ብቁ አይደለህም!
በጓደኝነት ውስጥ ሰዎች አንተን እንደ ተራ ነገር ቆጠሩህ ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ማለት ሌሎች ያለ ምንም መሠረት ከአንተ ብዙ ይጠብቃሉ ማለት ነው።
ለምሳሌ፣ ለምታውቃቸው ሰዎች ደግ እየሆንክ ከሆነና በማናቸውም ምክንያት የግል ህይወትህ ውስጥ እንዲገቡ ከፈቀድክ፣ ሁኔታውን እንደ ቀላል ነገር ሊወስዱትና ወሰናቸውን ማለፋቸውን ሊቀጥሉ ይችላሉ። በፍቅር ግንኙነት ውስጥም ትልቅ ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡ ለትዳር አጋርህ ማድረግ እንዳለብህ ስለሚሰማህ ወይም ማድረግ ስለምትፈልግ አንድ ነገር ታደርጋለህ፤ ግን በኋላ የትዳር ጓደኛህ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ሁልጊዜ እንድታደርግ ልትጠብቅህ ትችላለች።
ነገር ግን ጓደኝነት ስትመሰርት ጓደኞችህ የሚሆኑት አንተ እንዳደረግካቸው እንደሆነ ማወቅ ይገባሃል።
አንተ ጊዜህን በነጻነት የምትሰጥና ሁልጊዜ ለሌሎች አሳቢነትን የምታሳይ ዓይነት ጓደኛ ከሆንክ፣ ጓደኞችህም ለጋስና ደግ ይሆናሉ።
ጓደኞችህ የሚያደርጉልህን አቅልለህ የምትቆጥር፣ በምላሹም ብዙም የማትሰጥ ወይም የማትጠብቅ ዓይነት ሰው ከሆንክ የምትስበው ተመሳሳይ ባሕርያትን የሚያሳዩ ጓደኞችን ነው። ምክንያቱም በጓደኝነት ውስጥ የምትስበው ተመሳሳይ ነገሮችን ነው፡፡ ምን አይነት ጓደኛ እንደሆንክ ለማወቅ አልፎ አልፎ ባህሪህን መገምገም ያስፈልግሃል።
ለመሆኑ ሰዎች ጓደኛቸው እንድትሆን የሚፈልጉት ዓይነት ሰው ነህ?
በምላሹ ምንም ሳትጠብቅ በነጻ ትሰጣለህ ወይስ ሁልጊዜ የምትጠይቅ ግን የማትሰጥ ነህ?
ከጓደኞችህ ጋር ለመገናኘት ወይም የጓደኞችን ልዩ አጋጣሚዎች ለማስታወስ ጊዜ ትወስዳለህ?
በራስህ ፍላጎት በተዋጥክና ስለ ጓደኞችህ በረሳህ ጊዜ፣ ጓደኛ የለሽ ለመሆን መንገድ ላይ መሆንህን አስብ።
@PsychologyCentral✅
61 134
📚ተአምረኛው አእምሮህ
ከእለታት በአንዱ እለት አንድ ወጣት ብስክሌት እየነዳ ሳለ... በጎን የመጣ መኪና ገጨው። በአደጋው ስድስት የጀርባ አጥንቶቹ ተሰበሩ፤ ዶክተሮችም ተስፋ እንደሌለውና ዳግም መራመድ እንደማይችል ነገሩት።
ሆኖም የዚህ ወጣት ታሪክ እዚህ ላይ አላበቃም። ወጣቱ ከቀናት ስቃይ በኋላ አንድ ሃሳብ ተገለጠለት
"ሰውነቴን የፈጠረ አምላክ፤ መዳኛዬንም በውስጤ ቀብሮታል"
በአእምሮውም ደጋግሞ- ፍጹም ሲሻለውና እያንዳንዷ የጀርባ አጥንት ስባሪ መልሳ ስትገጥም አሰበ። ልክ መዳኑ እንደሆነለትም በፍጹም እምነት ሃሳቡን አመነ።
በመጨረሻም ተዓምር ሆነ - ከጥቂት ሳምንታት በኋላ "ድኛለሁ" ብሎ በማመኑ ብቻ ፈውስን አገኘ።
የዛኔው ወጣት፣ የአሁኑ የኒውሮሳይንስ ሃኪም ጆዊ ዴስፓንዛ፤ የአእምሮውን ኃይል በመጠቀም ፈውስን ካገኘ በኋላ፣ በዓለም ሁሉ እየዞረ አስተማረ፤ ብዙዎችንም በህይወታቸው ላይ ተአምራትን እንዲያመጡ አስቻለ።
@PsychologyCentral✅
61 134
💶የሚቀያየረው ማንነትህ
በተለያዩ ቀናት፣ በተለያዩ ሳምንታት ወይም በተለያዩ አመታት ውስጥ የተለያዩ ማንነቶች እንዳሉህ ተሰምቶህ አያውቅም? በአንደኛው ቀን ጨዋታ ወዳድ ተጫዋች ትሆንና በሌላኛው ቀን ቁጥጥርን የሚያበዛ ቁጡ ሰው ትሆናለህ። ሲግመንድ ፍሮይድ ስለ ባህሪ መለዋወጥ የሚለን ነገር አለ።
ፍሮይድ የእኛ ማንነት በሶስት ይከፈላል ይለናል፡፡
ለምሳሌ ለፈተና ልታጠና ተቀመጥክ እንበል - ኢድ መጨናነቅ አይወድም፤ እናም በቀስታ ፈታ በል አትጨናነቅ ይልሃል። ወይ ስልክህን እንድታነሳና ፌስቡክ እንድትጠቀም አልያም ከጓደኞችህ ጋር ሄደህ እንድትዝናና ይመክርሃል።
ሱፐር ኢጎ፤ ከኢድ በተቃራኒ፣ ነገሮችን አጋኖ እና መጥፎ አድርጎ ያቀርብልሃል። ዛሬ ካላጠናህ ፈተና ትወድቃለህ ፈተናንም ከወደቅክ ይህን አመት ትደግማለህ… እያለ ያስፈራራሃል።
በመሃል ኢጎ ወይም ‘ምክንያታዊ ማንነትህ’ ለማስታረቅ ይመጣል። ራሴን እስክጥል ድረስ መጨናነቅ የለብኝም፤ ሆኖም ግን ለአንድ ሰዓት ያህል አጥንቼ ወደ ጫወታ እሄዳለሁ ይላል።
ፍሮይድ የማንነት ቀውስ የሚመጣው ሶስቱን አጣጥመን ሳንሄድ ስንቀር ነው ይለናል። ሰካራም፣ ሴሰኛ ሰው አይተህ ታውቃለህ… ይሄ ሰው የኢድ (የእንስሳነት) ማንነቱ በርትቶበታል። በተቃራኒው ስለ ሁሉም ነገር የሚጨነቅ እና ፍጹም ለመሆን የሚጥር ሰው ገጥሞህ ያውቃል? ቋጣሪ፣ ጥንቁቅ አልያም አብዝቶ የሚጨነቅ ይሆናል … ይህ ሰው የሱፐር ኢጎ (የዳኛው) ማንነት በርትቶበታል።
ሁሌም ቢሆን በሁለቱ ማንነቶቻችን ውስጥ እንዳንዋጥ ራሳችንን ልንቆጣጠረው ይገባል። ነገር ሁሉ በጊዜው እና በአግባቡ ሲሆን ያማረ ይሆናል። ጠቢቡ ሰለሞን እንዳለው፡-
“ለማልቀስ ጊዜ አለው፥
ለመሳቅም ጊዜ አለው፤
ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥
ለመዝፈንም ጊዜ አለው
ከፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጥስ መጽሐፍ ላይ
@PsychologyCentral✅
61 134
በ30 ዓመቱ ሞተ በ60 ዓመቱ ተቀበረ!
“አንድ ሰው በትርፍ ጊዜው ብዙ ሙታን ወደተቀበሩበት የመቃብር ስፍራ ሄዶ በሰዎች መቃብር ላይ የተጻፉትን ጽሑፎች በማንበብ ላይ ሳለ፣ በአንድ ሰው መቃብር ላይ አንድ ግር የሚል ጽሑፍ አነበበ፡ ጽሑፉ በ”30 ዓመቱ ሞተ፣ በ60 ዓመቱ ተቀበረ” ይላል፡ ጽሑፉ ግር ብሎት ቆሞ ማሰላሰል ጀመረ፡፡ “አንድ ሰው በ30 ዓመቱ ሞቶ እንዴት ለ30 ዓመታት ሳይቀበር ሊቆይ ቻለ?” ይህንን እያሰበ የጽሑፉን ትርጉም የሚያውቅ አንድ ሰው ደረሰ፡፡ “ምን እንደምታስብ ገብቶኛል” አለው ሃሳቡን አንብቦ፡፡
ጥያቄውን በግምት ደርሶበት ኖሮ በቀጥታ መልሱን ነገረው፡፡ “ይህ ሰው እጅግ በጣም የሚያስገርም ራእይና ዓላማ የነበረው ሰው ነበር፡፡ ብዙ ነገሮችን የመስራት እቅድ የነበረውና በዚህም ትጋቱ በሕብረተሰቡ ዘንድ እጅግ የታወቀና ለትልቅ ነገር የሚጠበቅ ሰው ነበር፡፡ ልክ 30 ዓመት ሲሞላው በተለያዩ ውጣ ውረዶች በማለፉ ምክንያት ተስፋ በመቁረጥ ዓላማውን ሁሉ ትቶ ከርታታ ሰው ለመሆን በቃ፡፡ የሚቀጥሉትን 30 ዓመታት እንዲሁ በየቦታው ሲንቀዋለል ነው ያሳለፈው፤ ካለምንም ዓላማ፡፡ የጽሑፉ ትርጉም ይህ ነው፡፡ ሰውዬው ሞተ ብለው የሚያምኑት ራእዩን በጣለበትና ጊዜውን በተራ ነገር ማሳለፍ በጀመረበት በ30 ዓመቱ ነው - በአካል ቢኖርም ሞቷል ነው አባባላቸው፡፡ ልክ በ60 ዓመቱ ታምሞ አካላዊ ሞትን ሲሞት ያን ጊዜ ተቀበረ ማለታቸው ነው”
በአካል መኖር ብቻውን ኖሯል አያስብልም ነው ነገሩ፡፡ ህያው የሚያደርገን ራእይና የመኖር ዓላማ እንጂ ቆሞ መሄድ አይደለም፡፡ ቆሞ ለመሄድ በአራት እግር ሆነ እንጂ አህያም ይሄዳል፡፡ አህያ ግን የሰውን ስራ ከማቅለሉ ውጪ የራሱ ራዕይ የለውም፡፡ ስለሌለውም የሌሎች ባሪያ ሆኖ ይኖራል፡፡ በሰው ራእይና ዓላማ የለሽ ህይወት ህይወት ሳይሆን ሞት ነው፡፡ ዓላማ አልባው ሰውም ለመቀበር ነፍሱ ከስጋው እስክትነጠል ይጠበቃል እንጂ ሙትማ ሙት ነው፡፡ ሰውን ህያው የሚያደርገው ህልሙ ነው የሚሉ ይመስላሉ ፀሐፊው፡፡ ልክ ነው! ዓላማ ያለው ሰው መሆንና በዓላማው የሚፀና ሰው መሆን ሁለት የስኬት ቁልፎች ናቸው፡፡
ስኬታማ ሰዎች ባለራዕይ ናቸው፡፡ ለራዕያቸውም ታማኝና ፅኑ ናቸው፡፡ ለፈተናም ሆነ ለየትኛውም ነገር በቀላሉ እጅ አይሰጡም፡፡ እጅ አለመስጠታቸው የህያውነታቸው ምልክት፣ የስኬታቸው ጠቋሚ ነው፡፡
ከዓላማ ውጪ የሚኖር ህይወት ከህይወት አይቆጠርም፡፡ ዓላማ ቢስ ወይም ከባለራዕይነት ወደ ዓላማ የለሽነት የመጣ ሰው ኖሯል ለማለት ከባድ ነው።
ምንጭ፦ “25 የስኬት ቁልፎች” የተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ
@PsychologyCentral✅
61 134
ራስን መቅረጽ
ጣልያናዊው ቀራጺ እና ሰዓሊ ማይክልአንጀሎ አንድ እለት እንዲህ ተጠየቀ፤ "እነዚህን ውብ ቅርጾች እንዴትስ ነው የቀረጽካቸው?"
ቀራጺውም መለሰ፤ "ቀድሞውኑ ቅርጾቹ በድንጋይ ውስጥ ነበሩ፤ እኔ ያደረግኩት አላስፈላጊ ቅርፊቶችን ከድንጋዩ ላይ ጠርቦ ማንሳት ብቻ ነው"
በሁላችንም ውስጥ ውብ የሆነ ጥበብ አለ፤ ሆኖም ለአመታት በተጠራቀሙ ጸጸቶች እና ፍርሃቶች ተሸፍኗል፤ እነርሱም በራስ መተማመናችን ከኛ አራቁት... ራሳችንን እንድንጠረጥር ሆንን.... ፍርሃት ሸፍኖ አስቀረን... ወደፊትም መጓዝ አቃተን...
ሙሉ አቅምህን አውጥተህ ለመጠቀም ሸፍነው የያዙህን አላስፈላጊ ቅርፊቶችህን ጠርበህ አንሳ...
@PsychologyCentral✅
61 134
በቅርቡ ትሞታላችሁና ብሉ ጠጡ ተደሰቱ
ሕይወት ከባድ ነች - በጭንቀቶች፣ በውጥረት፣ በአስፈሪ ክስተቶች የተሞላች። እና ይህንን ሁሉ ጠራርጎ ለማስወገድ ምን ማድረግ ይኖርብናል? እንዴትስ እነዚህን ሁሉ ችግሮች እንደ ተራ ነገር ንቀን ልናልፋቸው እንችላለን?
ፍልስፍና ቀላል ሆኖ ሊተገበር የሚችል መፍትሄ ያቀርብልናል - ሜሜንቶ ሞሪ
ሜሜንቶ ሞሪ የላቲን ሃረግ ሲሆን ትርጓሜውም “እንደምትሞት አስታውስ” ማለት ነው። አይቀሬ ስለሆነው ሞት ስታስብ ለዚህ ሁሉ ጉዳይ መጨነቄ አግባብ ነው ወይ? የሚል ጥያቄን ታነሳለህ።
የሮም ንጉስ እና ፈላስፋ የነበረው ማርክስ አውሬሊየስ ይህን ሃሳብ አጥብቆ ይወደዋል። ሞት ተፈጥሯዊ እና አይቀሬ ነው ንብረትን ለማፍራት መሮጥ፣ አለማዊ ሃብትን ማሳደድ… ይህ ሁሉ ልፋታችን ይዘነው ለማንሄደው ኮተት ነው ይለናል። አንድ ቀን አፈር እንሆናለን፤ ስለምንስ ምድራዊ ጊዜያችንን በጭንቀት ውስጥ እናሳልፋለን?
በጥንታዊ ግብጻውያን ዘንድ አንድ ባህል አለ፤ በታላቅ ግብዣ ወቅት ግብር አሳላፊው በማድረቂያ መድሃኒት የደረቀ የሞተ ሰው አስክሬን ይዞ ይመጣል፤ በታዳሚዎችም ፊትም ይዞት ይዞራል፤ እንዲህም እያለ ይጣራል -
“በቅርቡ እንደዚህ ትሆናላችሁና … ብሉ … ጠጡ… ተደሰቱ”
በሞት ላይ በጥልቀት ካሰብክበት፤ የእለት ተዕለት ጥቃቅን ጭንቀቶችህ ተጠራርገው ይሄዳሉ። አለቃህ ምንስ ቢያስብ ምን ያስጨንቅሃል? ከሚስትህ ጋር የሚያጋጩህ ሃሳቦች ስለምን ያስጨንቁሃል? ስለምን የሚወዱህን በመጥፎ ቃላት ታስከፋለህ?
ሕይወት በዘላለማዊ ጨለማ መሃል የምታበራ የአጭር ጊዜ ሻማ ናት፤ ዋጋ በሌላቸው ነገሮች ስለምን ታባክናታለህ? … ይህ ሁሉ መጨነቅህ … ሻማዋ በጠፋች ቅጽበት ያበቃል…
@PsychologyCentral✅
61 134
ራስን ማድመጥ!
ታላቅነት የሚፀነሰው መፃህፍትን በማንበብ፣ የሚበልጡህን ሰዎችን በማማከርና ልምድ በመውሰድ ሲሆን ታላቅነት የሚወለደው ግን ራስን በማድመጥ ነው።
ምን እንደምትፈልግ ለማሰብ ጊዜ ውሰድ፤ የሚያስደስትህን የምታምንበትን ለማድረግ አንድ እርምጃ ጀምር ከዛ የምትፈልገው ነገር እስኪፈጠር ድረስ ጥረትህን አታቁም ምክንያቱም የተሸነፍከው ያቆምክ ዕለት ነው!
@PsychologyCentral✅
61 134
🎤 GEMINI PRO- የ 18 ወር Premium Subscription በ 400 ብር ብቻ !
📌 የGoogle እጅግ ዘመናዊው(Future of AI) Gemini Advanced (Pro) አሁን በ 400 ብር ብቻ ያገኙታል።
ምን ምን ጥቅሞችን ያገኛሉ?
🧠 Coding and Web Dev.t Tools: especially for CS & software students 🎬 AI Video, VEO3 & Media Creation and editing (Sample) 📚 Deep Research & NotebookLM Plus: for analizing large size pdfs ☁️ Massive Cloud Storage(5TB): for photos, videos& documents. ✉️ Workspace Superpowers📌 በተጨማሪም ለ video ኢዲተሮች capcut pro ለወር በቅናሽ በ750 ብር ብቻ ያገኙታል። - But The Orginal price is 19$/ month 🔒 100% አስተማማኝ — በራስዎ የግል Gmail ላይ የሚሰራ (No Shared Account)! ✉️ አሁኑኑ ይዘዙ: @climbtogether21✅ 📌 'Synergy squad' channel 👉 PROOF ✔️
61 134
ከጎዳና ተዳዳሪነት እስከ ሚሊየነርነት ! : የክሪስ ጋርድነር እውነተኛ የህይወት ታሪክ
በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ በሳን ፍራንሲስኮ ጎዳናዎች ላይ አንድ አባት የታቀፈውን ህጻን ልጁን ይዞ የሚያድርበት ቦታ ይፈልጋል። ይህ ሰው ክሪስ ጋርድነር ይባላል። በወቅቱ ምንም አይነት ገቢ አልነበረውም፤ ሚስቱ ጥላው ጠፍታለች፤ እሱና ገና የአንድ አመት ህጻን ልጁ መጠለያ በማጣታቸው በየቀኑ ይንከራተቱ ነበር።
አንዳንድ ቀናት በሕዝብ መጸዳጃ ቤት ውስጥ በሩን ዘግተው መሬት ላይ ይተኛሉ። ሌላ ጊዜ ደግሞ በባቡር ጣቢያዎችና በእምነት ተቋማት መጠለያዎች ውስጥ ያድራሉ። ልጁን በቀን ማቆያ ጥሎ እሱ ያለ ደሞዝ የሚሰራበትን የትርፍ ጊዜ የሽያጭ ስልጠና ይከታተላል።
ክሪስ የሰለጠነበት ድርጅት የሚቀጥረው ለአንድ ሰው ብቻ ነበር። ክሪስ ግን ተስፋ አልቆረጠም። ሌሎቹ ሰራተኞች በቀን 6 ሰአት ሲሰሩ፣ እሱ ግን ልጁን ለመመገብና ለመታደግ ሲል በቀን 10 ሰአት ያለ እረፍት ስልኮችን እየደወለ ደንበኞችን ይፈልግ ነበር።
በመጨረሻም ያን ብቸኛ የስራ እድል እሱ አገኘው! ያ የስራ እድል የህይወቱን በር ከፈተለት።
ከዓመታት ጠንካራ ስራ በኋላ፣ ይህ የሳን ፍራንሲስኮ ጎዳናዎች ላይ ይተኛ የነበረው ሰው የራሱን ትልቅ የካፒታል ድርጅት (Gardner Rich & Co) ማቋቋም ቻለ። በአጭር ጊዜ ውስጥም አለም ላይ ካሉ ታላላቅ ሚሊየነሮች ውስጥ አንዱ ሆነ።
ይህ እውነተኛ ታሪክ እጅግ በጣም ተወዳጅ ከመሆኑ የተነሳ "The Pursuit of Happyness" በሚል ስም ታዋቂው ተዋናይ ዊል ስሚዝ የተወነበት ፊልም ተሰርቶለታል።
ክሪስ ጋርድነር ዛሬ ላይ ቆሞ ለሰዎች እንዲህ ይላል. . . . .
"ሰዎች አንተ መሆን የማትችለውን ነገር እነሱም መሆን ስለማይችሉ 'አትችልም' ይሉሃል። ህልም ካለህ ጠብቀው፤ ልታሳካውም ተጋደል!"©@PsychologyCentral✅
61 134
ለመኖር በመዘጋጀት ረገድ በጣም ጎበዝ ነን፣ ነገር ግን ለመኖር ብዙም ጎበዝ አይደለንም። ለዲፕሎማ አስር ዓመታት እንዴት መስዋዕትነት እንደምንከፍል እናውቃለን፣ እና ሥራ፣ መኪና፣ ቤት ወዘተ ለማግኘት በጣም ጠንክረን ለመሥራት ፈቃደኞች ነን። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሕይወት እንዳለን ማስታወስ ይከብደናል፣ በሕይወት ለመኖር ብቸኛው ጊዜ አሁን ነው!
—Thich Nhat Hanh —
@PsychologyCentral✅
61 134
አብዛኛዎቹ የዋና ሚዲያ አውታሮች እና ዜና አቅራቢዎች መረጃን ለማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን፣ የተመልካቹን አስተሳሰብ፣ ስሜት እና አቋም ለመቅረጽ ይሰራሉ። ይህንንም የሚያደርጉት በግልጽ በማዘዝ ሳይሆን፣ በረቀቀ የስነ-ልቦና ጨዋታ (Dark Psychology) እና በአእምሮ ግፊት ተመልካቹ የነሱን አጀንዳ እንደራሱ እውነት አድርጎ እንዲቀበል በማድረግ ነው።
አንድ ሚዲያ ወይም ዜና አቅራቢ በተመልካቹ ላይ የስነ-ልቦና የበላይነትን ለመቀዳጀት እና አስተሳሰብን ለመቆጣጠር የሚጠቀምባቸውን 10 የጨለማ ሳይኮሎጂ ስልቶች ልንገርህ፦
ፍርሃትን መሸጥ (Fear Mongering)፡ ሚዲያዎች ሰዎችን ለማስተሳሰር እና ትኩረታቸውን ለመያዝ ሁልጊዜ አደጋን፣ በሽታን ወይም ግጭትን አጋንነው ያቀርባሉ። የሰው ልጅ ሲፈራ ምክንያታዊ አስተሳሰቡ (Logical thinking) ይዘጋና መፍትሄ ፍለጋ ወደ እነሱው ማየቱን ይቀጥላል።
የተመረጠ እውነት ማቅረብ (Cherry-Picking & Framing)፡ አንድን ክስተት ሙሉ ለሙሉ ከማቅረብ ይልቅ፣ ለነሱ አጀንዳ የሚስማማውን አንድ ክፍል ብቻ ቆርጠው ያሳያሉ። በዚህም ተመልካቹ የተሟላ መረጃ እንዳለው እያሰበ፣ በተጨባጭ ግን የተዛባ ድምዳሜ ላይ እንዲደርስ ያደርጉታል።
የውሸት አጣዳፊነት (False Urgency)፡ ቀይ ቀለም፣ ትልልቅ "ሰበር ዜና" የሚሉ ፅሁፎች እና የሚያስደነግጡ ድምፆችን በመጠቀም በተመልካቹ ላይ አርቲፊሻል ጭንቀት ይፈጥራሉ። ይህ አእምሮህ ለማመዛዘን ጊዜ እንዳያገኝ እና በስሜት ብቻ ውሳኔ እንዲያሳልፍ የሚያደርግ ወጥመድ ነው።
ስሜት ቀስቃሽነት (Appeal to Emotion)፡ ከእውነታ እና አሀዝ ይልቅ፣ የሚያሳዝኑ ምስሎችን ወይም የሚያበሳጩ ቃላትን በመጠቀም የተመልካቹን ስሜት ይጫወቱበታል። ስሜትህ ከተነካ አእምሮህ በቀላሉ ለፕሮፓጋንዳ ክፍት ይሆናል።
ተደጋጋሚ እውነትነት (Illusory Truth Effect)፡ አንድን ውሸት ወይም የተዛባ መረጃ ደጋግመው ሲያቀርቡት፣ የሰው ልጅ አእምሮ በሂደት ያንን መረጃ እንደ እውነት መቀበል ይጀምራል። ሚዲያዎች ይህንን "ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል" የሚለውን ስልት አብዝተው ይጠቀሙበታል።
የመንጋ ስነ-ልቦና (Bandwagon Effect)፡ "አብዛኛው ህዝብ እንዲህ እያለ ነው"፣ "ሁሉንም ያስቆጣው ጉዳይ" በማለት አንድን ሀሳብ የሁሉም ሰው አቋም አስመስለው ያቀርባሉ። የሰው ልጅ በተፈጥሮው ከማህበረሰቡ መነጠልን ስለሚፈራ፣ ሳያስበው የተባለውን የአብዛኛውን ሀሳብ ይደግፋል።
የአእምሮ ማዛባት (Gaslighting)፡ ተመልካቹ በዓይኑ ያየውን እና በጆሮው የሰማውን እውነት ውድቅ በማድረግ፣ "አይ ያያችሁት ልክ አይደለም፣ ትክክለኛው ይሄ ነው" ብለው የገዛ እራሱን ማመዛዘን እንዲጠራጠር እና በሚዲያው ብቻ እንዲታመን ያደርጉታል።
እነዚህን የሚዲያ እና የዜና አቅራቢዎች የጨለማ ሳይኮሎጂ (Dark Psychology) ስልቶች ስትረዳ፣ የምታየው እና የምትሰማው ሁሉ ንፁህ እውነት እንዳልሆነ ትገነዘባለህ። ከ"ሰበር ዜናዎች" እና ከስሜት ቀስቃሽ ርዕሶች ጀርባ ያለውን ድብቅ ወጥመድ (Hidden Agenda) ማንበብ ትጀምራለህ። የራስህን አእምሮ ከሚዲያ ማእበል ነፃ አድርገህ፣ ትኩረትህን ትልቁን ስዕል (The Bigger Picture) በማየት እና ራስህን በማጠንከር ላይ ታደርጋለህ!
@PsychologyCentral✅
61 134
ምን ማንበብ ትፈልጋላችሁ? 👀
ግጥም፣ አጭር ጽሁፎች ወይስ ድርሰቶች?
ሁሉንም አንድ ቦታ፣ ራሳችሁን የምታገኙበት፣ ልባችሁን የሚነካ ጽሁፍ ከፈለጋችሁ…
✨ በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀውን ቻናል አሁኑኑ ይቀላቀሉ! 👇👇👇
🔗➡️ @ke_kaloche1
🔗➡️ @ke_kaloche1
61 134
🚀 ቴሌግራም ላይ ሊያመልጣችሁ የማይገቡ ቻናሎች:
1️⃣@PsychologyCentral✅ : የተለያዩ ሳይኮሎጂ መፅሐፎች እና ፅሑፎች የሚለቀቁበት ምርጥ ቻናል
2️⃣@Yemesahft_Alem✅ : ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ያሉ መፅሐፎች በPDF የሚለቀቁበት
3️⃣@PandoraPDF✅ : መፅሐፍት በPDF ብቻ የሚለቀቁበት ቻናል
4⃣@AmbaBooks☑️: የትኛውን መጽሐፍ ማንበብ ይፈልጋሉ? ልቦለድ ፣ ታሪክ ፣ሳይኮሎጂ ፣ቢዝነስ ሀይማኖታዊ ፣ሁሉንም አይነት በሽ በሽ ነው አሁኑኑ ይቀላቀሉን 🙏
61 134
ስለ ስምና ዝናህ ሳይሆን ስለ ባህሪህ ተጨነቅ ! ምክኒያቱም ባህሪ ማንነትህ ሲሆን ዝናህ ግን ሌሎች ስላንተ እሚያስቡት ነውና !
@PsychologyCentral✅
61 134
🚀 ቴሌግራም ላይ ሊያመልጣችሁ የማይገቡ ቻናሎች:
1️⃣@PsychologyCentral✅ : የተለያዩ ሳይኮሎጂ መፅሐፎች እና ፅሑፎች የሚለቀቁበት ምርጥ ቻናል
2️⃣@Yemesahft_Alem✅ : ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ያሉ መፅሐፎች በPDF የሚለቀቁበት
3️⃣@PandoraPDF✅ : መፅሐፍት በPDF ብቻ የሚለቀቁበት ቻናል
4⃣@AmbaBooks☑️: የትኛውን መጽሐፍ ማንበብ ይፈልጋሉ? ልቦለድ ፣ ታሪክ ፣ሳይኮሎጂ ፣ቢዝነስ ሀይማኖታዊ ፣ሁሉንም አይነት በሽ በሽ ነው አሁኑኑ ይቀላቀሉን 🙏
