NABAWI TUBE [ነበዊ ቲዩብ]
رفتن به کانال در Telegram
4 127
مشترکین
-424 ساعت
-187 روز
-6630 روز
آرشیو پست ها
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
🎙የዳዕዋ ፕሮግራም!
🔻በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ!
https://t.me/IbnuMunewor?livestream=7b970bcacee9ec3de3
Repost from [] مركز أبي موسى الأشعري []
🆕 አስደሳች ዜና 🔴
ለ2019 የት/ት ዘመን ለአደሪ እና ተመላላሽ መርሐ ግብር ለሁለቱም ጾታዎች - ምዝገባ ተጀምሯል!
🗂መርከዝ አቡ ሙሳ አል አሽዐሪ ለ2019 የትምህርት ዘመን በአደሪ እና በተመላላሽ ፕሮግራሞች ለሁለቱም ጾታዎች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ ጀምሯል።
✅መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡
▫️እድሜ፡ ከ 9 እስከ 25 ዓመት
▫️ክፍያ፡ በአግባቡ መክፈል የሚችል / የምትችል
▫️ሕግና ደንብ፡ ለመርከዙ ሕግና ደንቦች ተገዢ መሆን የሚችል
▫️ጤና፡ ከቋሚና ተላላፊ በሽታዎች ነፃ መሆንን የሚያረጋግጥ ሜዲካል ሰርተፍኬት ማቅረብ
✅ አድራሻና የመገናኛ ስልክ ቁጥሮች፡
🗂ቦታ፡ አንፎ ድልድይ ከባጃጅ ተራው ወድ ውስጥ ገባ ብሎ ግሪን ኤሪያው አካባቢ
🗂ስልክ፡ +251913939993
+251955555545
+251930547776
💎Telegram :-
https://t.me/merkezabumussa1
"ኢሬቻ በ10ደቂቃ"
"Irreecha daqiiqaa 10 kessatti "
በፉኣድ ሙሐመድ
በኦሮምኛ ቋንቋ የቀረበ ትምህርት
ትምህርቱን በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል፦
https://t.me/fuadorodurus/1981
Repost from [] مركز أبي موسى الأشعري []
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
የመርከዝ አቡ ሙሳ የተለያዩ አስተማሪ መረጃዎች ለመከታተል የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ ገጾቻችንን ይከተሉ!
Follow us!
➤ Youtube :- http://youtube.com/@merkezabumusaalashari
➤ Instagram:- https://www.instagram.com/merkezabumusaalashari
➤ Facebook:- facebook.com/merkezabumusaalashari
➤ Tiktok :- tiktok.com/@merkezabumusaalashari
➤ Telegram:- https://t.me/merkezabumussa1
ማንኛውም ሐሳብ እና አስተያየትም ካሎዎት በኢሜል አድራሻችን ያግኙን :- merkezabumusaalashari@gmail.com
ስለ ሰይዪድ ቁጥብ ተከታታይ
~
ክፍል አንድ፦ የሰይዪድ ቁጥብን ኻሪጂነት እና ህዝበ ሙስሊሙን በጅምላ ከኢስላም ማስወጣቱን የሚመለከት ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቀጥታ ስርጭት!
◇ ሰይድ ቁጥብ ማን ነው?
https://t.me/IbnuMunewor?livestream=abaae191d35c62b5f9
ቀጥታ ስርጭት!
◇ ሰይድ ቁጥብ ማን ነው?
https://t.me/IbnuMunewor?livestream=abaae191d35c62b5f9
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አሰላሙ ዐለይኩም
~
ባለፈው ሳይመቸኝ በመቅረቱ የተላለፈው ሰይድ ቁጥብን የሚመለከተው ፕሮግራም ዛሬ ምሽት 3፡00 ላይ ይኖራል።
በዚህ የቴሌግራም ቻናል በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል፣ ኢንሻአላህ :-
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ያያያዝኩት ቪዲዮ የሑሢዮች እንቅስቃሴ መስራቹ ሑሴን በድረዲን አልሑሢ ንግግር ነው። ምን እያለ ነው? ህዝበ ሙስሊሙን ከጥንት ጀምሮ ላገኘው መከራ ሁሉ፣ ለደረሰበት ዝቅጠት ሁሉ ቁጥር አንድ ተጠያቂው ዑመር ነው ይላል። ለንዲህ አይነቱ እR ^ኩስ ነው ኢኽዋንና የኢኽዋን ቫይረስ ተሸካሚ መንጋዎች የሚሟገቱት። ይህንን እያዩም እየሰሙም የሚደነግጡ እንዳይመስላችሁ። ከዑመር ብኑል ኸጧብ ክብር ይልቅ የነዚህ ራፊዷዎች ክብር ነው የሚበልጥባቸው። ዲናቸውን ብሽሽቅ አድርገው የያዙ አተላዎች!
በነገራችን ላይ ይሄ ሰውዬ የዐብዱልመሊክ አልሑሢ ወንድም ነው። ዐብዱልመሊክ አልሑሢ አሁን ላይ ራሳቸውን "አንሷሩ'ላህ" እያሉ የሚጠሩት ዘይዲያ ሺዐዎች መሪ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ማነው ፖለቲካ የገባው?
~
የሰዎች የኋላ ዳራ (background)፣ ስሜት፣ ፍላጎት፣ የሚያራምዱት አስተሳሰብ፣ ቡድናዊ አመለካከት፣ የንቃት መጠን፣ የትምህርት ደረጃ፣ የዲን ግንዛቤና አቋም፣ ወዘተ ይለያያሉ። ይህንን ተከትሎም የሚደግፉትና የሚቃወሙት የፖለቲካ ኃይል ከሃገር ሃገር ይለያያል። እዚህ ድረስ መግባባት ይቻላል። የምንለያየው ይህንን እውነታ የሚያረጋግጥ ተግባራዊ ማሳያ ስንመዝ ነው።
የሚገርመው እነሱ የሚደግፉትን የማይደግፍ፣ እነሱ የሚጠሉትን የሚወድን አካል "አንተ ፖለቲካ አልገባህም" የሚሉ ሰዎች ሁኔታ ነው። ልክ ፖለቲካ መረዳት ማለት ከነሱ ስሜት ጋር መግጠም የሆነ ይመስል። ስለ ፖለቲካ ብዙ የለቀለቀ ወይም የፈተፈተ ሁሉ ፖለቲካ ገብቶታል ማለት አይደለም። ዝም ያለም ሁሉ አልገባውም ማለት አይደለም። ነጋ ጠባ ዜና መዘገብ ፖለቲካ መረዳት አይደለም። ትንሽ ትልቁን ከሴራ ጋራ እያስተሳሰሩ መጎንጎንም የፖለቲካ ችሎታ ሳይሆን የራስን ስንፍና መሸፈኛ ሰበብ የሚሆንበት ጊዜ አለ። ይሄ ነገር በጣም ከመብዛቱ የተነሳ "ዐረብ ልጁ ትምህርት ቤት ቢወድቅበት እንኳ የአይ^ ሁድ እጅ አለበት" ከማለት አይመለስም እስከማለት የተሳለቁ አሉ። ግነቱ በውስጡ የሆነ ያክል እውነት አለው።
ለምሳሌ ያክል የሀገራችንን የዘር ፌዴራሊዝም በፅኑ የሚያወግዝ ብዙ ኃይል አለ። ከዚህ በተቃራኒ አሀዳዊ ስርአትን ከሺርክ በላይ የሚኮንንም ብዙ ወገን አለ። አስቡት እንግዲህ ሁሉም እየተነሳ ሌላኛውን አካል ፖለቲካ አልገባህም እያለ ሲያጣጥል። በዚህ ጉዳይ ላይ አተያያችን የተራራቀው በዋናነት በግንዛቤዎችን መበላለጥ ምክንያት አይደለም። ይልቁንም በብልጣብልጥና ስግብግል ባህሪያችን ጭምር የተነሳ ነው። በትምህርት ዝግጅታቸውና ደረጃቸውም፣ በሚከተሉት እምነትም ተመሳሳይ የሆኑ ሁለት ከአማራና ከኦሮሞ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በዘር ፌዴራሊዝምና በአሃዳዊ ስርአት ላይ ያላቸው ምርጫ ተቃራኒ ነው። የአንዱ ከሌላው አይገጥምም። ለምን? ግልፅ ነው። ታሪክን የሚረዱት በተራራቀ መልኩ ነው። የዛሬ ምርጫቸውም እንዲሁ የተራራቀ ነው።
ልክ እንደዚሁ እኔና አንተ ኢስላማዊ ዐቂዳችንና መንሀጃችን እስከተለያየ ድረስ በሙስሊም ሀገራትና ቡድኖች ላይ ያለን ፖለቲካዊ አተያያችንና ውግንናችንም ይለያያል። ላንተ የዑመር ጠላት የሆኑ ሺዐዎችን መውደድ ኖርማል ነው። ለኔ ደግሞ ይሄ ፈፅሞ ሊያቀራርበን የማይችል ቀይ መስመር ነው። ላንተ አንድ ቡድን "ሙስሊም" የሚለው ስሙ እስካለ ድረስ የፈለገውን ቢያራምድ እንኳ ዋናው "ሞት ለአሜሪካ!" ማለቱ ነው። ከአሜሪካ ጋር አይንና ናጫ የሆነችው ሰሜን ኮሪያ ራሱ "የአሕመዲያ" መዝሀብ ተከታይ ብትሆን ኖሮ ሱኒ ሙስሊሞችን እያነቀች ብትገ ^ድል እንኳ ከመደገፍ አትመለስም ነበር።
ለማንኛውም እንደ ሙስሊም ነገሮችን ሁሉ የምንመለከትበት መነፅር ዲን ሊሆን ይገባል። የዲን መሰረቱ ደግሞ ከሐቂቃ የራቀ "ኢስላም" የሚለው ባዶ ስያሜ ሳይሆን ተውሒድ ነው፣ ዐቂዳ ነው። ወላእና በራአችን ዐቂዳን መሰረት ያደረገ ሊሆን ይገባል። ይህንን ነጥብ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከኢስላም ቋጠሮዎች ሁሉ ጠንካራው" ሲሉ ነው የገለፁት። የዐቂዳ ጉዳይ ላንተ ውሃ የማያነሳበት ምክንያት ለምን እንደሆነ ራስህን ጠይቅ፣ ልብህን አድምጥ። አንተ ሰፋ ቦርቀቅ ስላልክ ይመስልኝ ይሆናል። እውነታው እሱ አይደለም። ምናልባት ለማስተዋል ከጠቀመህ - እንዲያው ምናልባት - ሺዐ እና ሱኒን ለማቀራረብ በጣም ለረጅም ዘመናት የደከመው ዩሱፍ አልቀርዷዊይ በዚህ ጥረታችን ሺ0ዎች አተረፉበት እንጂ ለሱኒው ዓለም ከጉዳት በስተቀር ያተረፈው ፋይዳ የለውም ማለቱን ያዝ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"በሰሞኑ የሰይዪድ ቁጥብ ጉዳይ ከተመቸኝ ዛሬ ከመግሪብ በኋላ በድምፅ ለመግባት አስቤያለሁ" ብዬ ነበር። አሁን ላይ ስላልቻልኩኝ ከቻልኩ ምሽት 3:00 ላይ በቴሌግራም ቻናሌ ( https://t.me/IbnuMunewor ) በቀጥታ (live) ለማቅረብ እሞክራለሁ ኢንሻ አላህ።
ጥሪ ለሙስሊሙ ኡማ!
(የሃይማኖቱ ጉዳይ ለሚያሳስበው ሃላፊነት ለሚሰማው ሙስሊም ሁሉ!)
~
በአዲስ አበባ እና በአንዳንድ የክልል ከተሞች አሕ^ባሾች ድምፃቸውን አጥፍተው በተጠናከረ መልኩ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ አካሄዳቸውም ህፃናትን ከተለያዩ አካባቢዎች በመሰብሰብ ረዘም ላለ ጊዜ በማሰልጠን ስለሆነ አደጋውን ይበልጥ የከፋ ያደርገዋል፡፡ በቁርኣን ሒፍዝ ስም በሚሰበስቧቸው ልጆች ልቦና ውስጥ አደገኛ የሆነ መርዝ በመትከል ዐቂዳቸውን እየበከሉ ስለሆነ ወገናችንን ለመታደግ ከወላጆች ዘንድ አስፈላጊውን ግንዛቤ ልንፈጥር፣ የምንችለውን ሁሉ ልናደርግ ይገባናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በህዝብ እንደተተፉ የገባቸው አሕ^ባሾች መልካቸውን ቀይረው በአንዳንድ አካባቢዎች በተብሊጎች ስም እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ ሰዎችን በኹሩጅ ከሰበሰቡ በኋላ ቀስ በቀስ የራሳቸውን ብልሹ ዐቂዳ ለማስረግ እየተጉ ነው፡፡
ስለሆነም ነገ አላህ ፊት ከመጠየቃችን በፊት ዛሬ ፈጥነን ነገሮችን በሚገባ ማጤን እና ዙሪያ ገባችንን ማስተዋል የግድ ይለናል፡፡ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በሚገኙ የተለያዩ የቁርኣን የሒፍዝ ማእከላት ልጆቻችሁን ያስገባችሁ ወላጆች ሁሉ፡ ነገ አላህ ፊት ከመጠየቃችሁ በፊት፣ የልጆቻችሁንም ዘላለማዊ ህይወት ከማበላሸታችሁ በፊት ከወዲሁ አስፈላጊውን እርምጃ ውሰዱ። ያስገባችሁበትን መርከዝ ምንነት በሚገባ አስረግጡ፡፡ ያለበለዚያ ነገ ብዙ መስዋእትነት ያስከፍለናል፡፡ ከዚያ በላይ ግን ለዘላለማዊ ፀፀት ይጥለናል፡፡ ከዐርሹ በላይ ያለው ጌታችን እንዲህ ይለናል፡-
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنْفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከሆነችዋ (የጀሀነም) እሳት ጠብቁ፡፡ በርሷ ላይ ጨካኞች፣ ሃይለኞች የሆኑ መላእክት አልሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምፁትም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሰራሉ፡፡” [አት-ተሕሪም፡ 6]
ነብዩም ﷺ እንዲህ ይላሉ፡-
(كُلُّكُمْ رَاعٍ وَكُلُّكُمْ مَسْؤول عَنْ رَعِيَّتِهِ، الإِمَامُ رَاعٍ وَمَسْؤولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ، وَالرَّجُلُ رَاعٍ فِي أَهْلِهِ وَهُوَ مَسْؤولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ، وَالْمَرْأَةُ رَاعِيَةٌ فِي بَيْتِ زَوْجِهَا وَمَسْؤولَةٌ عَنْ رَعِيَّتِهَا، وَالْخَادِمُ رَاعٍ فِي مَالِ سَيِّدِهِ ومَسْؤولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ، قَالَ: وَحَسِبْتُ أَنْ قَدْ قَالَ: وَالرَّجُلُ رَاعٍ فِي مَالِ أَبِيهِ وَمَسْؤولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ- وَكُلُّكُمْ رَاعٍ وَمَسْؤولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ)
“ሁላችሁም እረኞች ናችሁ፡፡ ሁላችሁም ስለ እረኝነታችሁ (ስለ ሃላፊነታችሁ) ተጠያቂ ናችሁ፡፡ መሪ እረኛ ነው፤ ስለ እረኝነቱም ተጠያቂ ነው፡፡ ወንዱ (ባል) በቤተሰቡ ላይ እረኛ ነው፤ ስለ እረኝነቱም ተጠያቂ ነው፡፡ ሴቷም በባሏ ቤት ውስጥ እረኛ ነች፤ ስለ እረኝነቷም ተጠያቂ ነች፡፡ አገልጋይም በአለቃው ንብረት ላይ ተጠያቂ ነው፤ ስለ እረኝነቱም ተጠያቂ ነው፡፡ ‘አንድ ሰው በአባቱ ንብረት ላይ ተጠያቂ ነው፤ ስለ እረኝነቱም ተጠያቂ ነው’ ያሉም ይመስለኛል ይላል ዘጋቢው፡፡ ሁላችሁም እረኞች ናችሁ፡፡ ሁላችሁም ስለ እረኝነታችሁ ተጠያቂ ናችሁ፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ስለዚህ ከተጠያቂነት ለመዳን፣ እራሳችንን እና ወገናችንን ለማትረፍ ሃላፊነታችንን እንወጣ፡፡ ወገን ለወገኑ ደራሽ ነው፡፡ አላህ በዲናችን የመጣውን ፈተና ያንሳልን፡፡ የተሻለውንም ይምረጥልን፡፡ ኣሚን፡፡ ይህን መልእክት በሰፊው በማሰራጨት የምንችላትን እናድርግ፡፡ የአላህ ፈቃዱ ከሆነ የሚጠቀምበት ሰው ይኖራል፡፡
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 29/2007)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from [] مركز أبي موسى الأشعري []
3️⃣0️⃣ ቀዳሜ ነሐሴ 3️⃣0️⃣
🟩🟩🟩🟩🟩🟩
➡️ መርከዝ አቡ ሙሳ አል አሽዐሪ የቁርአን ሂፍዝና የተርቢያ ማእከል በበጋና በክረምት በአዳሪ መርሀግብር ሲያስተምራቸው የቆዩ ወንድና ሴት ተማሪዎችን የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 30 አጠና ተራ እፎይታ የገቢያ ማእከል በሚገኘው ትልቁ አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል ። ኢንሻአላህ
➡️ በፕሮግራሙ ከተመራቂ ተማሪዎች የተለያዩ ማራኪ ዝግጅቶች ይጠብቋቹሀላ ።
➡️ በፕሮግራሙም ላይ የተለያዩ መሻይኾችና ኡስታዞች አጫጭር ሙሐደራዎች ይኖሯቸዋል ።
ተጋባዥ እንግዶች ⤵️
➡️ሸይኽ ሙሐመድ አወል ባህርዳር
➡️ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
➡️ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ
➡️ኡሰታዝ ሳዳት ከማል
➡️ኡስታዝ አቡ ሙስሊም
ማሳሰቢያ:
➡️ ፕሮግራሙ የሚጀመረው ከጠዋቱ 2:30 ስለሆነ ፈጥነው እንዲደርሱ ለማሳሰብ እንወዳለን ።
➡️ ለሴቶችም በቂ ቦታ ያለ ሲሆን ፕሮግራሙንም በላይቭ ቀጥታ ስርጭት የሚከታተሉ ይሆናል ።
ነሐሴ 3⃣0⃣
★★★
Telegram : -
https://t.me/merkezabumussa1
https://t.me/merkezabumussa1
