Ethio Power Academy
رفتن به کانال در Telegram
Training, Research & Development, Leadership Development, Knowlegde management and Competency assessment. ___ We strive to create a learning organization!! — Ethio Power Academy — ethiopoweracademy@gmail.com
نمایش بیشتر2 418
مشترکین
+224 ساعت
+157 روز
+3430 روز
آرشیو پست ها
2 417
⚡️
Tumut 3: When Hydropower Becomes the Battery of the Grid
ዛሬ በአውስትራሊያ የነጭ የበረዶ ተራሮች (Snowy Mountains) ጥልቅ ውስጥ ስለሚገኝ አንድ የውሃ ኃይል ማመንጫ እናወራለን... እግረመንገዱን ለሃገራችን ልንኮርጀው የሚገባውን የምህንድስና ጥበብ እናነሳለን...
የስኖዊ ማውንቴንስ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ scheme አካል የሆነው የቱሙት 3 የኃይል ማመንጫ (Tumut 3 Power Station)፣ ወደ 1,800 ሜጋዋት (MW) የሚጠጋ የማመንጨት አቅም (generating capacity) አለው... የማመንጫው አስደናቂ ነገር ግን የኤሌክትሪክ ምርቱ አይደለም - የምህንድስና ጥበቡ እንጂ... ውሃን እንደተከማቸ ኃይል (stored energy) የሚጠቀምበት መንገድ እጅግ ይገርማል...
✅ ነገሩ እንዴት መሰላችሁ?...
ኤሌክትሪክ በሚፈለግበት ጊዜ ውሃ ከታልቢንጎ ግድብ (Talbingo Reservoir) በኃይል ማመንጫው በኩል ወደ ጁናማ ኩሬ (Jounama Pondage) ይፈስሳል... ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ፍላጎት (lower demand) በሚኖርበት ጊዜ ግን ከስድስቱ ማመንጫ ክፍሎች (generating units) ውስጥ ሦስቱ ወደ ኋላ ተመልሰው እንደ ፓምፕ (pumping units) በመስራት ውሃውን ወደ ላይኛው ግድብ ይመልሱታል...
[በቀላል አነጋገር...]
➡️ ውሃ ማከማቸት → ማመንጨት → ውሃን መልሶ መሰብሰብ (Recover) → እንደገና ማከማቸት → እንደገና ማመንጨት - ነው ነገሩ…
በዚህ መንገድ ያው ውሃ ኤሌክትሪክን ከአንዱ የቀኑ ክፍለ-ጊዜ ወደ ሌላው ለማሸጋገር የሚያስችል የኃይል ማከማቻ (energy storage medium) ሆኖ ያገለግላል...
ይህ - እንደ ኢትዮጵያ ባሉና ከፍተኛ የሃይድሮፓወር ግድቦችን (hydropower reservoirs) በታደሉ እንዲሁም የፀሐይ (solar) እንዲሁም የነፋስ (wind) ኃይል አቅማቸው በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በሚገኝ ሀገራት፣ ግድብ ከኤሌክትሪክ ማመንጫ የውሃ ምንጭነት ባሻገር ትልቅ ፋይዳ ያለው ነገር መሆኑን አመልካች ነው...
[ነገሩን ከነባር ልማዳችን ወጣ ብለን በተለየ መንገድ ለመመልከት እንድንችል እንዲህ እንጠይቅ...]
✅ ግድቦቻችን ለብሔራዊ የኤሌክትሪክ መረብ (national grid) ስልታዊ የኃይል ማከማቻ ሀብት (strategic energy storage assets) መሆን ይችላሉ ወይ?...
✅ በቂ የፀሐይ ወይም የነፋስ ኃይል የማመንጨት አቅም በሚኖርበት ጊዜ - ሃይድሮፓወሩን የማመንጨት አቅም በመቀነስ ውሃን በግድቡ ውስጥ ጠብቆ ማቆየት... እንዲሁም የታዳሽ ኃይል ምርት ሲቀንስና የኤሌክትሪክ ፍላጎት ሲጨምር ደግሞ ያንን የተከማቸ ውሃ በመልቀቅ ኤሌክትሪክ ማመንጨት... [ይቻላል ወይ?...]
🎓 ሳይንስና ተግባራዊ ተሞክሮዎች - 'አዎን... የመሬት አቀማመጥ (geography)፣ የውሃ ባህሪ (hydraulics)፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች በሚፈቅዱበት ቦታ፣ "ፓምፕድ ስቶሬጅ" (dedicated pumped storage) በመጠቀም ይህን ማድረግ ይቻላል' ይላሉ...
🔔 ነገሩ ለእኛ ሃገር ነባር የሃይድሮፓወር ስርዓት አዲስ የኢንጂነሪንግ አስተሳሰብ ነው...
Hydropower generation + reservoir storage + renewable energy + grid flexibility + regional interconnection
(የውሃ ኃይል ማመንጨት + የግድብ ማከማቻ + ታዳሽ ኃይል + የኤሌክትሪክ መረብ ተለዋዋጭነት/ተጣጣፊነት + ቀጠናዊ የኃይል ትስስር)
ሃሳቡ እያንዳንዱን የኃይል ማመንጫ ጣቢያ እንደ ተነጣጣይ ሀብት ከማየት ይልቅ፣ አጠቃላይ የግድብ ስርዓታችንን እንደ እምቅ የኃይል ማከማቻ እና የማመጣጠኛ ሀብት (balancing resource) አድርጎ መመልከትን ይጠይቃል... ከቱሙት 3 የኃይል ማመንጫ ምህንድስና የምንማረውም ይህንን ነው...
አዎን...
ኢትዮጵያ - የሃይድሮፓወር ሀብቶቿን ኤሌክትሪክ ከማመንጨት ባለፈ፣ የወደፊቱ የታዳሽ ኃይል መረብ (renewable grid) የሚፈልገውን ተጣጣፊነት (flexibility) ለማሟላት የኃይል ማከማቻ (energy storage) አገልግሎት ወደ መስጠት ማሸጋገር ትችላለች...
የሃይድሮፓወር ዕጣ ፈንታ ኤሌክትሪክ ከማመንጨትም በላይ መሆን አለበት... ይልቁንም ኃይልን ማከማቸት፣ ማሸጋገር (shifting generation)፣ ታዳሽ ኃይሎችን ማመጣጠን (balancing renewables) እና አገልግሎቱ በሚፈለግበት ጊዜ ኤሌክትሪክ ማቅረብ ላይ ማተኮር አለበት...
ያን ጊዜ - ግድብ ከግድብም በላይ ይሆናል!!...
____
📌 (አንባቢ ሆይ - ይህንን ከቱሙት 3፣ ስኖዊ ማውንቴንስ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ስኪም፣ አውስትራሊያ የተወሰደ የምህንድስና ትምህርት በጥልቀት ለመረዳት የሚሹ ከሆነ ተጨማሪ ነጥቦችን እንዲያስሱ እናበረታታዎታለን…)
____
We strive to create a learning organization.
2 417
.
.
.
➡️ A true team is built on:
🟢 Trust — knowing your colleagues will support you when challenges arise.
🟢 Respect — valuing different perspectives, experiences, and skills.
🟢 Communication — speaking openly, listening actively, and addressing issues early.
🟢 Accountability — taking ownership of commitments and results.
🟢 Shared Purpose — understanding that individual success contributes to collective success.
2 417
EVERY WORKPLACE HAS DIFFERENT TYPES OF PEOPLE. WHICH ONE ARE YOU?
___
Most of us are very good at identifying the people who frustrate us at work. We know who never pulls their weight, who always complains, who takes credit for other people's work, or who only seems busy when the boss is around.
___
What we rarely do is ask ourselves where we fit into the picture.
Every one of us contributes to the culture of the workplace in one way or another. Some people make work easier simply because they are around. They solve problems, support others, and raise the standard.
Others make work heavier. They drain the energy of the team, create unnecessary conflict, or leave everyone else carrying their share of the load.
Before pointing out the kind of colleagues you work with, take a moment to reflect on the kind of colleague you are.
❓ If your team had to describe you, what would they say?
____
@ethiopoweracademy
2 417
+7
የክረምት ጨዋታ… 🔥🔥🔥
.
.
.
ቀደም ሲል ያጋራናችሁን ሃሳብ ተከትሎ በርከት ያሉ አስተያየቶችና ልዩ ልዩ ተሞክሮዎች እየደረሱን ይገኛል… ከነዚህም ውስጥ ለዛሬ ከያዶት ሰብስቴሽን ያገኘነውን በጎ ተሞክሮ በአጭሩ እናጋራችሁ…
ያዶቶች ስራቸውን ከጀመሩ - 3 ዓመት አስቆጥረዋል… በሰብል ደረጃ ጤፍ፣ ማሾ (የቅባት እህል) እና በቆሎ የሚያመርቱ ሲሆን፤ ጎመን፣ ቲማቲምና ሌሎች የአትክልት ዝርያዎችንም ይተክላሉ…
እንደነገሩኝ የሚያርሱት መሬት 2 ሄክታር አካባቢ ይሆናል… ትራክተር ተከራይተው ነው የሚያሳርሱት… አቅምዋ አነስተኛ ቢሆንም ትንሽዬ የውሃ ፓምፕም አላቸው…
✅ ይሄ ጥረት በተቋም ስርዓት ቢታገዝ የሚያመጣውን ለውጥ አስባችሁታል?…
ከላይ ያሉትን ምስሎች በማየት ትንሽ ብትቀኑ - ብትነቃቁም ደስ ይለናል…
.
.
.
የሆነስ ሆነና ክረምቱ እንዴት ይዟችኋል?… እሸት በቆሎ እየበላችሁ ነው?… 😁
--
🙏 ለምስሎቹ - ታዘብ ባይሌ - ከያዶት ሰብስቴሽን እናመሰግናለን!!
ብራቮ ያዶቶች!! 👌
2 417
.
.
.
የሆነስ ሆነና ተቋም ከዚህ ምን ይጠቀማል?....
ዌል...
⚡️ ጣቢያዎች በውስጣቸው ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰራተኛ የሚያገኙበት ዕድል ይፈጥራል... አሁን ባለው የሰራተኛ ዕድገትና ዝውውር ስርዓት የዕውቀት ሽግግር መፍጠርም ሆነ ልምድ ያለውን ሰራተኛ በአንድ የስራ ክፍል ውስጥ ለረጅም ጊዜ ማቆየት ህልም ነው... መሰል ስራዎች ግን ሰራተኞች በጣቢያ ውስጥ በቂ ለሚባል ጊዜ እንዲቆዩ ተጨማሪ ምክንያት ይሆናቸዋል...
⚡️ ለረጅም ጊዜ ተራቁተው የቆዩና ለተቋሙ ቴክኒካል ተግባራት ቀጥተኛ ጥቅም የሌላቸውን ቦታዎች ወደ ስራ ለማስገባት ጠቃሚ ነው... ይህም ቦታውን በተሳሳተ መንገድ ለሚፈልጉ የውጭ አካላት በቂ ምላሽ ይሰጣል...
⚡️ ተጓዳኝ ተግባራቱ የሚያጎለብቱት የስራ ፈጣሪነት፣ የገንዘብ አስተዳደር፣ የቡድን ስራና የችግር አፈታት ክህሎት ለተቋም ሌሎች ኃላፊነቶች የተዘጋጁ ሰራተኞችን ያፈራል...
⚡️ የስራ ቦታዎችን ገጽታ ይቀይራል... ጣቢያዎቹን በሚጎበኙ አካላት ዘንድ የገጽታ ግንባታ ይፈጥራል... በተለይ የተክሎች መኖር አዋራ የመቀነስ አቅም ስላለው ንጹህና ውብ ግቢ እንዲኖር ያደርጋል...
⚡️ የተቋሙ ክበቦች አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት እንዲፈጥሩ ያደርጋል... ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ዋጋቸው እየናረ የመጣውን የአትክልትና የሥጋ ተዋጽዎች ኪስ በማይጎዳ ሳንቲም ለሰራተኛው ማቅረብ ያስችላል... ይህም በተራው የሰራተኞችን እርካታ ያሳድጋል...
ይህን ሁሉ ካወራን ወዲህ በጭራሽ የማንዘለው ጉዳይ የአተገባበር ስርዓቱን የተመለከተው ነው... ተቋም ውስጥ እንደመኖራችን ነገሮች ወጥነት ባለው መንገድ ስርዓት ባለው መልኩ መመራት ይኖርባቸዋል...
[ተከታዮቹ ሃሳቦች በዚህ መነሻነት የተጫሩ መስመሮች ናቸው...]
እንደሚታወቀው ሰብስቴሽንም ሆነ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የተገነባበት ተቀዳሚ ዓላማ አትክልት መትከል፣ ንብ ማነብ፣ ከብት ማደለብ ወይም ዶሮ ማርባት አይደለም... ስለሆነም ማንኛውም ተጓዳኝ እንቅስቃሴ ከጣቢያው ዋነኛ ተግባር ጋር በጭራሽ ሳይጋጭ መከወኑ መረጋገጥ ይኖርበታል...
ስለሆነም:
1️⃣) ደህንነት
ጣቢያዎች ለ Electrical safety እና Operational reliability ቅድሚያ የሚሰጥባቸው ቦታዎች እንደመሆናቸው የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራትንና የጥገና ስራ እንቅስቃሴዎችን የማይረብሽ አሰራር መከተል ግድ ይላል...
2️⃣) ጤና
ከእንስሳት ጋር ተያይዞ የሚሰሩ ስራዎች ለአላስፈላጊ ሽታና ለአንዳንድ ጎጂ ነፍሳት መሰባሰብ ምክንያት እንደመሆናቸው የሰራተኛውን ጤና አደጋ ላይ ሊጥሉ ይችላሉ... ስለሆነም ከእርባታ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ውጋጆችን የምናስተዳድርበት ስርዓት መዘርጋት ወሳኝ ነው...
3️⃣) ከኦፕሬሽን ስራው ያለው ርቀት
የግብርና ስራዎች ከኦፕሬሽን መከወኛ ስፍራ መራቅ አለባቸው... በተለይም ከኤሌክትሪክ ቁሳቁሶችና መስመሮች፣ ከትራፎ፣ ከስዊችያርድ፣ Underground cables፣ Earthing (grounding) systems፣ Cable trench እና ሌሎች የግንባታ መሰረተ ልማት መራቅ አለበት...
4️⃣) አስተዳደር
መሰል ስራዎች ለግጭትና ለብልሹ አሰራር ምክንያት የመሆን ዕድላቸው ሰፊ ነው... ስለሆነም አስቀድሞ ስርዓት ሊበጅላቸው ይገባል... እንዴት ይተዳደሩ? ምን ዓይነት ደረጃዎችን ያሟሉ?በጋራ ይሰሩ በግል?... የት ምን ይሰራ?... ሌሎችም ዝርዝር ጉዳዮች ግልጽ ፖሊሲና የአሰራር ደንብ ይፈልጋሉ...
5️⃣) ቅድመ ጥናት
ከላይ እንደተገለጸው ሁሉም ክፍት ቦታ ለዚህ ተግባር ሊውል አይችልም... በየጣቢያው ለደህንነት፣ ለወደፊት ማስፋፊያ፣ ለእሳት አደጋ መከላከያ፣ ለጥበቃ አመቺነት፣ ለቁሳቁስና ተሽከርካሪ መተላለፊያ እንዲሁም ለአንዳንድ የ engineering standards ሲባል የሚተው ቦታዎች አሉ... ስለዚህም "በየሰብስቴሽኑና በየማመንጫው ለኦፕሬሽንና ለደህንነት የማያስፈልጉ ክፍት ቦታዎች ምን ያህል አሉ? እነዚህንስ በጥንቃቄና በህጋዊ ስርዓት ለተጨማሪ እሴት መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?" ብሎ ማጥናት ይጠይቃል...
___
መውጫ ሃሳብ
📌 መልካም ጅምሮችን ማወደስ ሌሎችን ያነቃቃል... የአንዳንድ ሰው ብርታት የብዙዎችን ተነሳሽነት ያመጣልና... ትናንሽ ሙከራዎችን ስናይ ማደናቀፍ፣ ማወሳሰብና መከልከልን ከማሰባችን በፊት ከዚህ ጉዳይ ሰራተኛው ምን ይጠቀማል? ተቋሙስ ምን ያጣል? ምን ዓይነት እገዛ ብናደርግ የተሻለ ነው?... ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት በቀናነት መደገፍ፣ መከታተል፣ ማነቃቃት የብልህ መሪ ተግባር ነው...
[[በነገራችን ላይ ይህ ጉዳይ ለተቋማችን አዲስ ታሪክ አይደለም... ከጥቂት አስርታት በፊት በማሰልጠኛ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ከማመንጫዎች በሚገኝ ምርት ይሸፈን ነበር፣ አንዳንድ ማመንጫዎች ይህንኑ ስርዓት ዛሬም አስቀጥለውታል...]]
🔵 አዎን... ይህ ሃሳብ የሚመለከታቸውን አካላት ትኩረት ስቦ፣ ወደ መሬት ወርዶ በአሰራር ይደገፋል፣ በስርዓትና ሕግ ይመራል፣ ሰራተኛውን ይደግፋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን...
___
Viva Daniel - Keep on shining!!
___
ይቆየን!!
2 417
+2
.
.
.
Every organization has hidden opportunities. They become visible only to people who combine initiative, discipline, and the willingness to create value.. . ስንደርስ የበርካታ ዶሮዎች ኩልኩልታ ተቀበለን... አንድ ዓይነት ቀለምና መጠን ያላቸው ሴት ዶሮዎች ዘመናዊውን የእርባታ መንገድ ከባሕላዊው እንክብካቤ ጋር ባዛነቀ አግባብ በጎጆአቸው ውስጥ ሲቀለቡ አገኘን... ይህ ድንቅ የግብርና ስራ የሚከወነው በሰብስቴሽኑ የኦፕሬሽን ባለሙያ ወጣት ዳንኤል አማካይነት ነው... እጅግ ጠባብ በሆነች ቦታ ላይ ከአንድ ሺህ በላይ እንቁላል ጣይ ዶሮዎች ይርመሰመሳሉ... ልዩ ልዩ አትክልቶች ያሉበት እርሻ ደግሞ ከፊትለፊት ይታያል... ከጎን የዶሮ መኖ ማከማቻ፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ፣ የውሃ አቅርቦት ማሳለጫ - ቦታዎች ይታያሉ... በጣም ተገረምን... በውስን ቦታ ላይ ሰፋፊ ስራዎች የሚሰሩበት ጥንቃቄና ጥበብ ይገርማል... እንዴት ተጀመረ?... ምን ጥቅም ሰጠ?... ምን ችግሮች ገጠሙት?... ሞባይሌን አውጥቼ ከዳንኤል ጋር ቃለ-ምልልስ ማድረግ ጀመርኩ... ስራውን የጀመረው ሌላ ሰብስቴሽን ከሚሰራ ጓደኛው ባገኘው ተሞክሮ ነው - የዛሬ አራት ዓመት ገደማ... በወቅቱ ቤተሰቡን አስቸግሮና ከተቋሙ ብድርና ቁጠባ ተቋም ጥቂት ገንዘብ ወስዶ፣ 100 ዶሮዎችን ብቻ በመግዛት ጅማሬውን አደረገ... ጉዞው ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም... ዶሮዎች በወረርሽኝ ይሞታሉ፣ እንቁላሎች ድንገት ይሰበራሉ፣ ስራውን በበቂ ልምድ ካለመገንዘብ ብዙ ኪሳራዎች ይከተላሉ... ዳንኤል ግን የዋዛ ሰው አልነበረም... በወደቀ ቁጥር የሚማረውን ትምህርት እንጂ የሚከስሩውን ገንዘብ ቆጥሮ አያውቅም ነበር... ይህም ዛሬ ላይ ከፍሎታል... ዳኒ እንደርሱ ታታሪ ከሆነችው ባለቤቱ ሦስት ልጆች ወልዷል... ልጆቹን በሚገባ ያስተምራል፣ ራሱም ይማራል - በቅርቡ ዲግሪውን ይይዛል... በስራ ላይ ቀልድ አያውቅም - ጥንቅቅ አድርጎ ኃላፊነቱን ይወጣል... በወር ከሚያገኘው የተሻለ ገቢ በተጓዳኝ ስራው ከማግኘቱም በላይ መጠነኛ ካፒታልም መፍጠር ችሏል... ለወደፊት ደግሞ የወተት ላሞች እርባታን ያስባል... በዚህ ሂደት በሚተርፍ መኖ አማካይነትም በግና ፍየል ማድለብና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከተማ ውስጥ የእንስሳት ተዋጽዎ መሸጫ ሱቅ መክፈት ቀጣይ ዕቅዶቹ ናቸው... አሁን ኑሮው ሌላ መልክ ይዛለች... እዚያው ቆሜ ማሰብ ጀመርኩ... በየሰብስቴሽኑና በየማመንጫው ስንት ሁዳድ መሬት ፆሙን እያደረ ይሆን?... ስንት የውሃ ምንጭስ በከንቱ እየፈሰሰ ነው?... ስንት ዕድል እንዲሁ ያልፈን ይሆን?...
አዎን... ዓይኖች እንዲያዩዋቸው፣ እጆች እንዲዳብሱዋቸው፣ ልቦች እንዲያስተውሏቸው የሚፈልጉ በረከቶች ዛሬም ቢሆን በዙሪያችን ሞልተዋል... በብላሽ ግን ፍሬ አይሰጡም... ጎንበስ ማለት፣ አፈር መግፋት፣ ጭቃ ማቡካት ይፈልጋሉ... ከምንም በላይ ደግሞ በእጃቸው በረከትና በላባቸው ወዝ ብቻ ራሳቸውን መርዳት የሚሹ ንጹህ እጆችን ይፈልጋሉ...ይህም ብቻ አይደለም... አንድ ጣቢያ ውስጥ ሆነው፣ አንዱ ባልደረባ በርትቶ በፈጠረው አቅም በመነቃቃት የየፊናቸውን ዕድል የሚያጣጥሙ መኖር የሞራል ስንቅ የመሆኑን ያህል እጃቸውን አጣጥፈው የተቀመጡ መብዛት ደግሞ ለስራው እንቅፋት ነው... አንድ ሃቅ አለ!... የደመወዝ ጭማሪም ሆነ የጥቅማጥቅም ዳረጎት ፌሽታቸው ወር አይሻገርም - ተመልሰን እዚያው ነን... መሰል ተግባራት ግን ከመጠበቅ ነፃ ያወጡናል... ከፍ ባለ ሁኔታ የኑሮ ቀዳዳ ይደፍኑልናል፣ የቤተስብ ዕዳ ያቀሉልናል... ከምንም በላይ ደግሞ የተቋም ፍቅርና ባለቤትነትን ያሳድጉልናል... . . .
2 417
+1
.
.
.
እግረ መንገድ...
ክአምስት ወራት በፊት ወደ ሆለታ ሰብስቴሽን ተጉዘን ነበር...
በተቋማችን የተቀጠሩ ጀማሪ መሐንዲሶች ከስልጠና በኋላ የስራ ላይ ጉብኝት እንዲያደርጉ በያዝነው መርሃግብር መሰረት ከኃይል ማመንጫዎች እና ብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ጣቢያ ጉብኝት በኋላ ነበር ትልቁን የተቋማችንን ሰብስቴሽን ለማሳየት ጉዞ ያደረግነው...
___
ሆለታ ሰብስቴሽን የብረት ጫካ የምታዩበት ሰፊ የኢንጂነሪንግ አውድማ ነው... ከዚህም ባሻገር ከሕዳሴ ለምንቀበለው ኃይል ሁለተኛውንና ትልቁን የመቆጣጠሪያና ማስተዳደሪያ ስርዓት (System) የያዘ ባለ 500 KV ጣቢያ ነው...
እኛ በሄድንበት የየካቲት ወር አየሩ በጣም ሞቃታማ ነበር... በግቢው ውስጥ ለመስራት አይደለም ለመቆም የሚከብድ ሙቀት ቢኖርም በጣቢያው የሚገኙ ባለሙያዎች ግን አንዳች የሚበግራቸው ሳይኖር በየመስካቸው ሲታትሩ አይተናል...
🔤 የሙቀት ነገር ከተነሳ፣ በሃገራችን የአየር ሁኔታ ስብጥር እጅግ ከፍተኛ ሙቀት ባለባቸው አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰውነታቸው በላብ ተዘፍቆ፣ ፊታቸው በንዳድ ጠውልጎ፣ ቆዳቸው በጸሐይ ወይቦ፣ ከላይ በጸሐይ ግለት ከታች በምድር ረሞጫት እንደ ድፎ ዳቦ እየተለበለቡ፣ ፕሮጀክት የሚመሩ፣ ማመንጫ የሚያስተዳድሩ እንዲሁም ሰብስቴሽን የሚቆጣጠሩ ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች ያሉን መሆኑን ማሰብ ያበረታል... እኒህ ታታሪዎች የጽናትና ብርታት መቅሰሚያችን ናቸው... እናም - ትጉህ እንደሆኑ እያወቅን እንኳን - ዛሬም 'በርቱ' ልንላቸው እንወዳለን...🔤
ወደ ሆለታ ልመልሳችሁ...
የሰብስቴሽኑ ኃላፊ አቶ ጥላሁንን ጨምሮ ተዘጋጅተው ሲጠብቁን የቆዩ ባለሙያዎች ወዳጅነት የተሞላ አቀባበል አደረጉልን...
ወዲያውም አዲሶቹን ባልደረቦች በየምድቡ በመከፋፈል የስራ ላይ ስልጠና ወደሚወስዱበት ቦታ መሩልን... የደረስነው ምሳ ሰዓት ተቃርቦ ቢሆንም ያማረረብን አልነበረም፣ ጉብኝት የጠየቅነው በጠራራ ጸሐይ ቢሆንም ሲከፋ ያየነው የለም... ለማሳወቅ የማይሰንፉ ብርቱዎችን ለማወቅ ከሚጓጉ ጀማሪዎች ጋር አጣምረን ሂደቱን መከታተል ጀመርን... ጎብኚና አስጎብኝ በሁዳድ የብረት ጫካ ውስጥ ጠፉ...
በዚህ መሐል ከማሰልጠኛ የሄድን ሰራተኞች የሰብስቴሽኑን ዙሪያ ገባ መጎብኘት ያዝን... ይሄኔ ነው አንድ ቦታ ቀልባችንን የገዛው... ቦታው የዶሮ እርባታ የሚከናወንበትና ልዩ ልዩ የአትክልት ዓይነቶች የተተከለበት ነው...
.
.
.
2 417
⚡️ The China–Laos 500 kV transmission line demonstrates how cross border interconnections can maximize the value of different energy resources throughout the year.
⚡️ A unique feature of this project is its dual purpose. During the rainy season, Laos exports surplus hydropower to China. During the dry season, when hydropower generation declines, China supplies electricity back to Laos through the same transmission line.
⚡️ This two way power flow improves reliability, optimizes resource utilization, and ensures efficient use of the transmission infrastructure in every season.
⚡️ For us, (as E.E.P), this highlights the importance of designing future cross border interconnections for bidirectional power transfer, enabling countries to support one another according to seasonal generation patterns and demand.
⚡️ A transmission line is more than a corridor for electricity. It is a strategic asset for regional energy security, operational flexibility, and sustainable power trade.
2 417
.
.
.
Training isn't a perk.
It's a ceiling-setter.
🟢 The real cost isn't when trained people leave. It's when untrained people stay.
2 417
🎚
UPDATE YOURSELF - OLD KEYS WON'T OPEN NEW DOORS.🔔 The world is changing. Industries are changing. Technology is changing. Customer expectations are changing. ⚠️ If you are still relying on old methods, old thinking, and old habits, you may find yourself struggling in a world that has already moved on. 🚛 What worked for you five years ago may not work today. What made you successful yesterday may not be enough tomorrow. ✅ Be intentional about your growth. Learn new skills. Upgrade your knowledge. Adapt to change. Challenge yourself to think differently and do better. ⏰ Whether you are a professional, entrepreneur, manager, or business owner, your ability to grow and evolve will determine how far you go. ✅ The people who keep learning stay relevant. The people who stop learning get left behind. ✍️ Old keys won't open new doors. Become the person who can. 🟣 Emmanuel Mukula Trainer. Facilitator. Speaker. Counsellor
2 417
ለግልጽነት
-
ሰላም ወዳጆች
በቅርቡ በሞት ለተለየን ወንድማችን ብርሃኑ ሊቁ ልዩ ልዩ ድጋፎች ሲደረጉ መቆየቱ ይታወሳል… በተለይ ደግሞ - የፋይናንስ ዘርፍ አፋጣኝ ብድር እንዲመቻች በማድረግ፣ የክሊኒክ አስተዳደር አምቡላንስ በማቅረብና የሙያ ኃላፊነት በመወጣት፣ የፍሊት አስተዳደር ተሽከርካሪ በማቅረብ፣ በሁሉም ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ ባልደረቦች በቅንነትና በታማኝነት መዋጮ በማሰባሰብ፣ እናንተ ደግሞ ያላችሁን ሁሉ በመስጠት ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል…
በዚሁ መሰረት፡-
· አጠቃላይ የተሰበሰበ የብር መጠን - 192,300.00
· ለልዩ ወጪ (የአስክሬን ሳጥንና ካርጎ ጭነት) – 25,700.00
· የአየር ቲኬት (ሦስት ሰው) – 29,751.00
· ለወላጅ አባት እገዛ (የ 40 ማውጫ) – 30,000.00
· እንዲሁም ለባለቤቱ - 106,849.00
በጊዜያዊው ኮሚቴ በኩል እንዲሰጥ አድርጎ ኃላፊነቱን ተወጥቷል፤
በወንድማችን ብሬ ስም ሁላችሁንም ከልብ እናመሰግናችኋለን፤ የኮሚቴው አባላት በሃገር ወግ - “ሃዘን ከቤታችሁ አይግባ” ብለዋችኋል፤
@eepderash
2 417
📣 Update…
"Never send to know for whom the bell tolls; it tolls for thee." - John Donne-- እንግዲህ እንደምታውቁት በአንድ ተቋም ውስጥ ብንሰራም ከአንድ አካባቢ አልተሰባሰብንም… በሌላ ቋንቋ አሁን በምንሰራበት ቦታ ብንገኝም በአብዛኛው በዚያ አልተወለድንም… አንዱ ከምዕራብ ሸክፎ ወደ ደቡብ ዘልቋል፣ ሌላው ከሰሜን በቅሎ ምስራቅ ተሻግሯል፣ አንዱ ከዳር ተነስቶ መሐል ሲከትም፣ ከመሐል የወጣው ወደ ሌላ ጫፍ ተጉዟል… እንጀራና ሕይወት በየአቅጣጫው በትኖናል… ሆኖም በተቋማችን በኩል አንድ ማዕድ፣ በሃገራችን በኩል መፃዒ ዕድል፣ በመኖር በኩል ደግሞ ተመሳሳይ ዕጣፈንታ እንጋራለን… ⏳ አንደኛው ዕጣፈንታችን - ሞት ነው!!... ከሞት ጋር ቀጠሮ ይዘህ አትሞትም!!... ከሞት ጋር በዚህ ጊዜ፣ ቦታና ሰዓት እንገናኝ ተባብለህ አትጨባበጥም… ወይ በድንገት ሸርተት፣ ወይ በዝግታ ጥፍት ትላለህ… ይህ የማይቀር ጉዳይ ነው… ከላይ የጠቀስነው ገጣሚ እንዳለው - "የሞት ደወል ሲደወል ለማን ነው አትበል፤ ጥሪው ያንተም ነው።" የሚባለውም ለዚህ ነው… እና እንደነገርኩህ… ያለህበት ቦታ የሃገርህ አንድ ክፍል ቢሆንም የምትቀበርበት ላይሆን ይችላል… ባሕል፣ ልማድ፣ ወግ የሚባል ነገር አለን አይደል? - ቤተሰቦችህ አልቅሰው ከሚቀብሩበት፣ አይተውህ ሃዘን ከሚያወጡበት ቦታ መቀበር አለብህ… ግን አንተ ሞተሃል!!... ማን ከምትሻው ዳርቻ ያድርስህ?... ከእትብትህ መቀበሪያ ማን ያገናኝህ?... በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ሊረዱህ ቢሞክሩም የልባቸው አይደርስ ይሆናል… የሚያዋጡት ባይጠፋም ግን ሁሌ አይሞላ ይሆናል… 🏃♀️➡️🏃♂️➡️ ስለዚህ አቅም ያለው ደራሽ ያስፈልግሃል!!... በሥጋ ባትኖርም በአንተ ምክንያት ቤተሰብ እንዳይሳቀቅ… ሞትህን ማስቀረት ባይቻልም የክብር ቀብር ብርቅህ እንዳይሆን… አጋዥ ያስፈልግሃል… በቁም ትንሽ አውጥተህ የምታቆመው ሕብረት ስትሞት እንዲቆምልህ፣ እንደ ዘበት የወረወርካት ጎልብታ ክንድ እንድታበቅልልህ… ደራሽ ያስፈልግሃል!! ነገሩ ግን በዚህ ብቻ አያበቃም - እንደ መጠነ ዳሩ፣ እንደ አቅም እንደ ጅምሩ - ሩቅ ተጉዞ የደስታህ ተጋሪም ይሆናል…
እናም ደራሽ ስለነ እከሌ አይደለም - ስላንተ ወይም ስላንቺ እንጂ!...--- አዎን - ደራሽን ደራሽ የማድረጊያው ጊዜ አሁን ነው!! --- በነገርህ ላይ ትናንት በርከት ያሉ ተሳታፊዎችን ያካተተ መስራች ጉባኤ ተደርጎ ምስረታው እንዲፈቀድ በምንጠይቅበት ረቂቅ Proposal (ምክረ-ሃሳብ) ላይ ግብዓት የመሰብሰብ ስራ የተሰራ ሲሆን ሰራተኞች በያሉበት የሚነጋገሩበትን አጀንዳዎች የሚቀርጹ፣ መመሪያ የሚያዘጋጁ እንዲሁም ጉዳያችንን ወደፊት የሚያስኬዱ 9 (ዘጠኝ) አባላት ያሉት ጊዜያዊ አደራጅ ተቋቁሞ ወደ ስራ ተገብቷል… ቀሪው የአንቺ/ የአንተ ተሳትፎ ነው!!... ደራሽ ስላንተ/ቺ ነውና!! ደራሽ ባንተ/ቺ ነውና!! ደራሽ ላንተ/ቺ ነውና!! --- ደራሽ ምርጫ እንጂ ግዴታ አይደለም… ሞት ግን ግዴታ እንጂ ምርጫ አይደለም… ስለ ደራሽ ሲነገር ስለሌሎች አታስብ - ስለራስህ እንጂ… 🔸 የደራሽን ቻናል እየተቀላቀላችሁ ቆዩ… ሃሳባችሁን በተቻለ መጠን በኮሜንት መስጫው በኩል ላኩ… በቅርቡ ዝርዝር ጉዳዮችን ይፋ እናደርግላችኋለን!! https://t.me/eepderash 🟢 ደራሽ - አዎን በቅርቡ ዕውን ይሆናል!!
2 417
⚙️ ከወረቀት ቁልል ወደ ዲጂታል ጎዳና - አዲስ የሥራ ባህል
የድሮውን ጊዜ እስቲ እናስታውስ... የአንድ ደብዳቤ ከመፃፍ እስከ መፈጸም የነበረው ጉዞ እጅግ አሰልቺና አድካሚ ነበር…
➡️ ማስታወሻ (Memo) ይታተማል፣ ይፈረማል፣ ኮፒ ይደረጋል፣ ይመዘገባል፣ ከቢሮ ቢሮ በእጅ ይዞራል፣ በጠረጴዛዎች ላይ ይደረደራል... አንዳንዴም በወረቀቶች ክምር ሥር ተደብቆ ይረሳል… የሥራ ኃላፊዎች «ደብዳቤው አሁን የት ደረሰ?» ብለው ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ስልክ መደወል ነበረባቸው… ሠራተኞችም የቆዩ መረጃዎችን ለመፈለግ በየፋይሉና በየካቢኔው ውስጥ ይኳትኑ ነበር… ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ፣ ወረቀትን ተከትሎ በመሮጥ ውድ ጊዜ ይባክን ነበር…
👉 ዛሬ ግን ያ ጉዞ ሙሉ በሙሉ እየተቀየረ ነው!
➡️ በተቋማችን የዲጂታል ደብዳቤ እና የሥራ አመራር ሥርዓት Digital Letter and Task Management System (E-Service) አማካኝነት፣ ግንኙነታችን ከአሁን በኋላ በወረቀት፣ በአካል በመንቀሳቀስ ወይም በቢሮ ግድግዳዎች አይገደብም…
➡️ አሁን አንድ ደብዳቤ ከአንድ የሥራ ክፍል ወደ ሌላው በሰከንዶች ውስጥ መጓዝ ይችላል… አንድ የሥራ መመሪያ ያለ አንድ ወረቀት ንክኪ ይመደባል፣ ይከታተላል፣ ቁጥጥር ይደረግበታል፣ ያላንዳች የወረቀት ንብርብር በስኬት ይጠናቀቃል።
⬇️ ነገር ግን የዚህ ሥርዓት እውነተኛ ዋጋ ፍጥነት ብቻ አይደለም፤ ከፍጥነት በላይ የሆኑ አምስት ታላላቅ ምሶሶዎች አሉት፦
🟢 ግልጽ እይታ (Visibility)፦
የሥራ ኃላፊዎች የደብዳቤዎችንና የሥራዎችን ሁኔታ በቀጥታ (Real-time) ማየት ይችላሉ። መዘግየቶች ወደ ችግር ከመቀየራቸው በፊት አስቀድመው ይታያሉ። ኃላፊነቶች ግልጽ ናቸው፤ ዕድገቶችም ይለካሉ። መረጃ በሚፈለግበት ጊዜ ወዲያውኑ ስለሚገኝ ውሳኔዎች ይፈጥናሉ።
🟢 ግልጽነት (Transparency)፦
እያንዳንዱ እርምጃ ይመዘገባል። እያንዳንዱ የተሰጠ ሥራ ባለቤት አለው። እያንዳንዱ ሂደት ዲጂታል አሻራውን ጥሎ ያልፋል። ይህ ደግሞ በመካከላችን እምነትን፣ ተጠያቂነትን እና ጠንካራ የኃላፊነት ባህልን ይፈጥራል።
🟢 ተደራሽነት (Accessibility)፦
በዋናው መ/ቤት፣ በኃይል ማመንጫ ጣቢያ፣ በሪጅን ቢሮዎች ወይም በሩቅ ሆነው በሥራ ላይ ቢሆኑም፤ ሠራተኞች የኩባንያቸውን የኢሜይል አካውንት በመጠቀም በኮምፒውተር፣ በላፕቶፕ ወይም በሞባይል ስልኮች ሥርዓቱን መጠቀም ይችላሉ። መረጃ በተፈለገበት ጊዜና ቦታ ሁሉ ዝግጁ ነው።
🟢 አብሮነትና ትብብር (Collaboration)፦
ቡድኖች በአንድ መድረክ ላይ መገናኘት፣ አዳዲስ መረጃዎችን መለዋወጥ፣ ሰነዶችን መገምገም እና ሥራዎችን መከታተል ይችላሉ። «ሰነዱ የት አለ?» ብሎ ከመጨነቅ ይልቅ፣ ትኩረታችን መከናወን ባለበት ሥራ ላይ ብቻ ይሆናል።
🟢 ውጤታማነት (Efficiency)፦
የህትመት ወጪ የለም፤ የሰነድ ክምችት ስጋት የለም፤ በአካል የሚደረግ ተደጋጋሚ ክትትል ቀርቷል፤ የጠፋ ሰነድ ወይም አላስፈላጊ መዘግየት ታሪክ ሆኗል።
☀️ ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ ይህ ወደ መጻኢው ዘመን የሚሰነዘር ትልቅ እርምጃ ነው!
➡️ የዲጂታል ሽግግር የሚረጋገጠው ሶፍትዌር በመጫን ብቻ አይደለም፤ ሰዎች አዲስ የአስተሳሰብና የሥራ መንገድን በቅንነት ሲቀበሉ እንጂ… በእያንዳንዱ የ E-Service ማስታወሻ፣ በዲጂታል መንገድ በሚከታተሉት ሥራ ወይም በሥርዓቱ በኩል በሚሰጡት ምላሽ—እርስዎ ይበልጥ ብልህ፣ ፈጣን እና እርስ በእርሱ የተገናኘ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ለመገንባት የበኩልዎን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው…
🔸 ያለ ወረቀት የመጓዝ ጉዟችን ቀድሞውኑ ተጀምሯል…
❓ አሁን ላይ ጥያቄው «ወደ ዲጂታል እንቀየራለን ወይ?» የሚለው አይደለም፤ ጥያቄው «ምን ያህል በፍጥነት እንቀበለዋለን?» የሚለው ነው!
🚀 ይጠቀሙበት!
🚀 ይመኑበት!
🚀 ያሻሽሉት!
☀️ ምክንያቱም ዛሬ በዲጂታል የምናደርጋት እያንዳንዷ እርምጃ፣ ነገ ማየት የምንፈልገውን ታላቅ ተቋም የምንገነባባት መሠረት ናትና!
——
Digital tools don’t transform an organization. People who know how to use them do. 🙏
2 417
📣
.
.
.
ከቀናት በፊት ከነስሙም ያልነበረው ደራሽ ዛሬ የብዙዎችን ቀልብ ስቦ “የምን እናድርግ?” ጠያቂዎችን አበርክቷል… በርከት ያሉ መልዕክቶች በውስጥ መስመር ደርሰውናል፣ ስልኮች ተደውለውልናል፣ በአካል ቢሮ ድረስ በመምጣትም ሃሳብ ያጋሩን አሉ… አሁን ደራሽ የሁሉም ወደመሆን አድጓል…
በግል ውይይት የሰው ኃይል ዘርፍና የሰራተኛ ማሕበር አመራሮች ለስኬቱ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸውልናል…
⭐️ ቀሪው የእናንተ ውሳኔ ነው!!...
‘ሞትን ማስቀረት ባንችልም የክብር ቀብር ብርቅ ሊሆንብን አይገባም’ ብለን የጀመርነው ሃሳብ፡-
☀️ ሰዎች ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ውስጥ ሲገኙ አለሁ የሚል
☀️ በድንገተኛ ሞት ጊዜም ሙሉ ወጪዎችን ከመሸፈን ተሻግሮ የሟች ቤተሰቦችን የሚደግፍ
☀️ ሰራተኞች ተቋሙን አገልግለው በጡረታ ሲሸኙ እናመሰግናለን የሚል
.
.
.
ወዘተ… ሊሆን ይገባዋል የሚሉ ሃሳቦች እየተስተናገዱ ነው… ሁሉንም ሃሳቡ በተቋም ደረጃ እውቅና ካገኘ በኋላ በሚዘጋጀው መመሪያ ላይ በግልጽ እናሰፍራለን… በዚህ በኩል ልምዶች ያላችሁ አካፍሉን…
የሚቋቋመው ፈንድ ሰራተኞችም ሆነ የስራ ኃላፊዎች በእኩልነት የሚታዩበትና ከሰራተኞች ማሕበርና ሰው ኃይል በተጨማሪ ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች ድርሻ ወስደው የሚሰሩበት፣ በሰራተኞች - ለሰራተኞች የሚቋቋም ሰፊ የማሕበራዊ አገልግሎት ፈንድ ነው…
ዛሬ በትንሽ እንጀምረዋለን!... ነገ በራሱ ገዝፎ እንደነቅበታለን!!
ከዛሬ ጀምሮ ከደራሽ ጋር በተያያዘ የምንጨዋወትበት ቻናል ተዘጋጅቷል፤ ተቀላቀሉት፣ ፤ሌሎችንም ጋብዟቸው…
@eepderash
https://t.me/eepderash
በሚቀጥለው ሳምንት ከሚደረግ የጅማሬ ስብሰባ በኋላ የሚኖሩ ማናቸውንም ለውጦች በአዲሱ ‘ደራሽ ቻናል’ እናጋራችኋለን…
.
.
.
በያለንበት ስለ ደራሽ እንነጋገር!!
2 417
☀️ The Dawn of DERASH ☀️
💡 Sometimes the most meaningful ideas are born not from plans, budgets, or directives, but from real human experiences.
Over the past few days, something remarkable has happened.
📞 A simple conversation about how we support one another during life's most difficult moments has grown into a shared vision.
🔹 Employees from different work units, professions, and locations have expressed their support for the idea of establishing DERASH – EEP Employees Social Affairs Fund.
🔺 This response tells us something important:
🔺The need is real.
🔹The time is now.
✅ DERASH is more than a fund.
❕ It is a promise.
✅ A promise that when hardship comes, someone will arrive.
✅ A promise that when a family is struggling, someone will stand beside them.
✅ A promise that when an employee falls, they will not face the challenge alone.
☀️ For years, many of us have contributed individually whenever colleagues experienced loss, illness, accidents, or other emergencies.
☀️ We have done so with compassion and goodwill. DERASH seeks to transform that same spirit into a sustainable institution that serves all employees, fairly and consistently.
🔘 What makes this initiative special is that it belongs to all of us.
❌ It is not an HR initiative.
❌ It is not a management initiative.
❌ It is not a labor union initiative.
✅ It is an employee initiative.
✅ A collective expression of who we are and how we choose to stand together.
➡️ As discussions continue, let us focus on building something that future generations of EEP employees will be proud of. Let us create a system founded on solidarity, transparency, trust, and shared responsibility.
🟢 Years from now, people may not remember where the idea started.
🟢 But if DERASH becomes a reality, there will be families who receive support when they need it most, colleagues who are treated with dignity, and employees who find comfort in knowing that they belong to a community that cares.
✅ That is the legacy we can build together.
✅ That is the dawn of DERASH.
Together, we stand. Together, we rise.
DERASH — Coming Soon.
2 417
2️⃣
አስቸኳይ ጥሪ
ያው እንደሰማችሁት ሰሞኑን አንድ ምርጥ ሰው አጣን... ዝምታ ራሱ የሚቀናበት ጸጥ ያለ ሰው... ከእርጋታ እንኳን የሚረጋ ልዩ ሰው...
አንዳንዴ ምልክት የምታጡለት ሰው የለም?... ስለ እርሱ ልትናገሩ ብላችሁ 'እንዲህ ሚሆነው፣ እንዲያ ሚያደርገው' የምትሉለትን የሚያሳጣችሁ ዓይነት ሰው የለም?...
ባለፈበት መንገድ መጓዙን እርግጠኛ ሆናችሁ የማትናገሩለት፣ ወንበሩ ላይ መኖሩን እስክትረሱ የማታስተውሉት፣ ማስቀየም የማያውቅ፣ ለቃሉ የሚጠነቀቅ፣ ፍጹም ሌላ ዓይነት ሰው... [ከትናንት በስቲያ እንደዚህ ዓይነት ሰው አጣን...]
ልንረዳው ሳንሞክር... ልናስተውለው ሳንጥር... ልናደምጠው ጊዜ ሳንቸር - አመለጠን...
---
ዌል... ሞቱን ማስቀረት አንችልም!!... ሰው የመሆን ዕጣ ነው…
"In every breath we are nearing to death" እንዲሉ...
በሰዓቱ፣ ከሞቱ ድንገተኛነት እኩል ድንጋጤ የፈጠረብን 'እንዴት አስክሬን ወደ ቤተሰብ እንሸኝ?' ለሚለው ጥያቄ ገንዘብ ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ሲከሰት ነው... በዚህ ምክንያት ረጅም ሰዓታት ባከኑ... ጭንቀት፣ ድካም፣ ለቅሶ...
[አስከሬኑ ጸበል ተቀምጦ የኛን መምጣት ይጠብቃል... ምንም ማድረግ ያልቻለ ቤተሰብ አስሬ ወደኛ ይደውላል... ይህ ከሞቱ በላይ ህመም አለው... ከህልፈቱ በላይ አቁሳይ ነገር አለው...]
🔸
ረጅሙን ታሪክ ስናሳጥር፣ የፋይናንስ ዘርፍ ርብርብ፣ የክሊኒክ ሰዎች ደግነት፣ የፍሊት ቢሮ ቀናነት፣ የጓደኞቹና ባልደረቦቹ ድካም፣ እስከ ምሽት 2:00 ሰዓት የተደረገና ከአዲሳባ እስከ መቀሌ/ አሸጎዳ የሚዘረጋ የብዙ ባልደረቦችና ወዳጆች ርብርብ ትናንት አስክሬኑን በሰላም ወደ ትውልድ መንደሩ አድርሶ ለዘላቂ ማረፊያው አበቃው...
[እዚህ ላይ አትርሱ - አቅም የሌለው ቤተሰብ ከፍ ያለ ወጪ አውጥቷል፤ ተያያዥ ወጪዎች ገና ወደፊትም ይጠብቁታል...]
ጥያቄው ግን ይህ ነው...
እስከመቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምንቀጥለው?... እስከመቼ ነው በመዋጮ ቀብራችን የሚፈጸመው?... እስከመቼስ ነው በቅርብ የሚያውቁን ብቻ ተሯሩጠውልን፣ ራቅ ብለው ያሉ ባልደረቦቻችን በወሬ ብቻ የሚያውቁን?...
ለምንድነው ደራሽ የሰራተኞች ማሕበራዊ አገልግሎት ፈንድ የማይኖረን?... ለምንድነው ከወር ደመወዛችን የምትሸረፍ ድቃቂ ብር ተደማምራ የቁርጡን ቀን ጣጣ የማትከድነው?...
ለምንድነው በተቆራረጠ መንገድ፣ የዘርፍ ወይም የስራ ክፍል ዕድር የምንፈጥረው?... የአንዳችን ሃዘን ስለምን የሁላችን ሃዘን አይሆንም?... የአንዳችንስ ደስታ ስለምን ሁላችንን ደስ አይልም?...
"ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፣ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው" ይባል አይደል?...
መች ነው ቤተሰብም ሆነ ባልደረባ ሳይሳቀቅ፣ በድንገተኛ ወጪ ጎጆው ሳይነቀነቅ፣ ተሽከርካሪ መድበን፣ የፕሌን ወጪ ሸፍነን፣ ሳጥን ገዝተን፣ የሞት ምስክር ወረቀት (Death certificate) እና ተያያዥ የህክምና ሰነድ ጨርሰን፣ ቤተሰብ ቀብር እስኪያስፈጽም ድረስ የሚጠብቁትን ወጪዎች በሙሉ ዘግተን ቀብር የምናስፈጽመው?...
[የተጋነነ ይመስላል አይደል?... 7800 ሰራተኛ ከደመወዙ ላይ፣ በስፖርትና HIV መዋጮ መንገድ 50 ብር እየተቀነሰ ወደ ፈንዱ አካውንት ቢገባ ብላችሁ አስቡት... በቀላሉ በወር 390,000 ብር ይገኛል... ለእያንዳንዳችን በዓመት 600 ብር ብቻ የሚያስወጣን ይህ ተግባር 4,680,000 ብር ያስገኛል...]
ታዲያ ይህ ብር የባንክ ወለድና ሌሎች የቢዝነስ ሃሳቦች ተጨምረውበት ሌላ ታሪክስ አይሰራም?...
ስንት ቤተሰብ ነው በእኛ ባልደረቦች ሞት ተጎሳቁሎ ያለው?... ስንት ልጆች ናቸው ከትምህርት ቤት ደጅ የጠፉት?... ስንቶቹስ የሚበላ የሚቀመስ አጥተው በየቤቱ ተቆራምደው ይሆን?...
ጎበዝ - ይህን ታሪክ የምንቀይርበት ጊዜው አሁን ነው!!... አሁኑኑ በየስራ ክፍላችን፣ በየመገናኛ ቦታችን በዚህ ጉዳይ ላይ እንነጋገር... ሰራተኛ ማሕበር በዚህ ጉዳይ ውይይት ይጥራ... የሰው ኃይል አስተዳደሮች ይህን አጀንዳ በቡድኖቻቸው መሐል ያንሱ...
ስንስማማ - በአዲሱ በጀት ዓመት እውን እናድርገው!!...
📣 ሞት በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የሁላችንንም በር ያንኳኳል - ልናስቀረው አንችልም... የክብር ሞት ግን ብርቅ ሊሆንብን አይገባም... በእኛ መለየት ማግስት የሚበተን ቤተሰብም መኖር የለበትም...
📌 ቤተሰብ እኮ ነን ጎበዝ!... አንድ ማዕድ ነው ያለን... ቸግሮኝ ብጮህ ከእናቴ በፊት የእናንተ ጆሮ ነው የሚሰማኝ... ብትደክሙ ከወንድማችሁ ይልቅ የእኔ ትከሻ ነው ቅርባችሁ...
I’m here for you, and I know you're here for me. We can be each other's strength.
እያንዳንዲቷን ጉዳይ ተቋሙ እንዲፈታልን መጠበቅ የለብንም... የራሳችንን ጠጠር መወርወር ደግሞ ይጠበቅብናል... እንደ ግለሰብ የሕሊና እርካታ ምንጭ ነው - ትንሽ አውጥተን ብዙ እናግዛለን... እንደ ሰው በእኛ ማለፍ ቋሚ እንዳይሳቀቅ ጥሪት ማኖሪያ ነው - ለሌሎች እያዋጣን ለራስ እንተርፋለን...
ትናንት - አባደራሽ በመሰረቱት ብድርና ቁጠባ ተቋም፣ ዛሬ (ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ሳይቀር) ከብዙ ችግር ያመለጡ፣ ቁምነገር የጨበጡ ሰዎች ሲያመሰግኑ እንሰማለን... አሁን ያለን እኛ ደግሞ የሰራተኞች ማሕበራዊ አገልግሎት ፈንድ መስርተን [ለምን ለሃዘን ብቻ?] በደስታችንም ከጎናችን የሚቆም አጋር እንፈጥራለን...
---
ደራሽ!!
____
ዕድሜ ለመጨመር ብቻ ሳይሆን ለመኖርም ያብቃን!!
____
በያለንበት እንበርታ!!
2 417
1️⃣
እናም ተቀበረ...
ቆይቶ ትውስታ ይሆናል...
ቆይቶ ይዘነጋል...
ቆይቶ ይረሳል - ይህ የሁላችንም ዕጣ ነው!!...
ከዚህ በፊት በብዙ ሰዎች ህልፈት ደንግጠናል፣ በብዙ ወዳጆቻችን ሞት አዝነናል፣ በብዙ ባልደረቦቻችን ሞት ተከፍተናል...
ግና የማንመልሳቸው ጥያቄዎች ዛሬም አሉ...
🔴 ስንቶቹን ስለ ደግነታቸው እናስብ ይሆን?...
🔴 ስንቶቹን ስለ ንጽሕናቸው እናስታውስ ይሆን?...
🔴 የነማን ቅንነት ከአዕምሮአችን ይደቀን ይሆን?...
🔴 የስንቱ ሰው ርህራሄ የትውስታችን አካል ይሆን?
[የአንድ?.. የሁለት?.. እንጃ... ምናልባት የማንም!!]
ይህ እውነት ነው...
ስንጎድል ለጊዜው የምንጎድልበት አለ... ለውስን ጊዜ የምንቸግረው አለ... ለቀናት ትውስታው የምንሆንበት አለ... ከዚያ ግን የለንም... የኑረት ውክቢያ፣ የማይሞላ ሩጫ፣ የጥረህ ግረህ ግፊያ የሰውን አዕምሮ ይሞላዋል... እንደበዝዛለን... እንተናለን...
የጊዜ ቀስት ወደፊት ብቻ እንደሾለ ነው... ወደኋላ ማየት ለሁሉ አልተሰጠም...
🔸 እየጣልን እናልፋለን!...
🔸 እያነጠብን እንሄዳለን!...
🔸 እያጎደልን እንጓዛለን!...
ግና በአንዳንዱ ልብ... የማንበርድ ግለት፣ የማንጠፋ እሳት፣ የማንሰወር ላምባዲና መሆናችን አይቀርም...
ከእናትህ ልብ ሞት በቀላሉ አይፍቅህም... [እያነባች ታስብሃለች!]... ወይም ደግሞ የእናትህ ሞት እንደ ተራ ውልብታ አይዘነጋህም... [ትመላለስብሃለች!]... ከልጅህ ልቡና እንደ ቀላል ነገር አትጠፋም... ወይም ደግሞ የልጅህ ሞት የዕድሜ ልክ የእግር እሳትህ ከመሆን አይቀርም...
የሆነስ ሆነና እየኖርክ ነው?... እየኖርሽ ነው?... እየኖራችሁ ነው?... በሩጫዎች መሐል መካከለኛ አላችሁ?... የእፎይታ ታዛ - ትንሽዬ ማረፊያ - አፍታ ቅጽበት አለቻችሁ?... ትንፋሽ እየወሰዳችሁ ነው?...
በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች እንዴት ናቸው?... ያጎበጣቸው ሸክም፣ ያጠወለጋቸው ህመም የለም?... ያስከፋቸው የጎጆ ደመና፣ ያደከማቸው የኑሮ ጫና የለም?... ስንቱን ሰው አስተዋላችሁ?... የስንቱን ፊት አነበባችሁ?... የስንቱን ቀንበር አሳረፋችሁ?...
ችግራችሁን በግልጽ ትናገራላችሁ ወይስ ሰቆቃችሁን ከራሳችሁ ጋር ብቻ ትጋፈጣላችሁ?... የምትሸሸጉበት ጥግ አላችሁ ወይስ ለብቻ ማልቀስን ተላምዳችኋል?... እንደሚያልፍ አመናችሁ ወይስ ሳይገፋን መች አልፎን አላችሁ?...
[ተስፋ ነው ወረፋ ከዓይናችሁ ፊት ያለው?...]
እየኖራችሁ ጎበዝ... ሳብ - ለቀቅ፣ ሳብ - ለቀቅ፣ ሳብ - ለቀቅ፣ - እየተነፈሳችሁ... ሞት አዲስ ነገር የለውም - ሳይኖሩ መሞት ግን ህመም አለው፤ ለአፍታ ሳቅ፣ ለቅጽበታትም ደስታ እጅ ሳይሰጡ ማለፍ ጉድለት አለው...
After all, we are not here merely to survive — we are here to thrive.
.
.
.
