ar
Feedback
Ethio Power Academy

Ethio Power Academy

الذهاب إلى القناة على Telegram

Training, Research & Development, Leadership Development, Knowlegde management and Competency assessment. ___ We strive to create a learning organization!! — Ethio Power Academy — ethiopoweracademy@gmail.com

إظهار المزيد
2 383
المشتركون
+124 ساعات
+37 أيام
+4230 أيام
أرشيف المشاركات
🎚 UPDATE YOURSELF - OLD KEYS WON'T OPEN NEW DOORS. 🔔 The world is changing. Industries are changing. Technology is changing
🎚
UPDATE YOURSELF - OLD KEYS WON'T OPEN NEW DOORS.
🔔 The world is changing. Industries are changing. Technology is changing. Customer expectations are changing. ⚠️ If you are still relying on old methods, old thinking, and old habits, you may find yourself struggling in a world that has already moved on. 🚛 What worked for you five years ago may not work today. What made you successful yesterday may not be enough tomorrow. ✅ Be intentional about your growth. Learn new skills. Upgrade your knowledge. Adapt to change. Challenge yourself to think differently and do better. ⏰ Whether you are a professional, entrepreneur, manager, or business owner, your ability to grow and evolve will determine how far you go. ✅ The people who keep learning stay relevant. The people who stop learning get left behind. ✍️ Old keys won't open new doors. Become the person who can. 🟣 Emmanuel Mukula Trainer. Facilitator. Speaker. Counsellor

ለግልጽነት - ሰላም ወዳጆች በቅርቡ በሞት ለተለየን ወንድማችን ብርሃኑ ሊቁ ልዩ ልዩ ድጋፎች ሲደረጉ መቆየቱ ይታወሳል… በተለይ ደግሞ - የፋይናንስ ዘርፍ አፋጣኝ ብድር እንዲመቻች በማድረግ፣ የክሊኒ
ለግልጽነት -   ሰላም ወዳጆች   በቅርቡ በሞት ለተለየን ወንድማችን ብርሃኑ ሊቁ ልዩ ልዩ ድጋፎች ሲደረጉ መቆየቱ ይታወሳል… በተለይ ደግሞ - የፋይናንስ ዘርፍ አፋጣኝ ብድር እንዲመቻች በማድረግ፣ የክሊኒክ አስተዳደር አምቡላንስ በማቅረብና የሙያ ኃላፊነት በመወጣት፣ የፍሊት አስተዳደር ተሽከርካሪ በማቅረብ፣ በሁሉም ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ ባልደረቦች በቅንነትና በታማኝነት መዋጮ በማሰባሰብ፣ እናንተ ደግሞ ያላችሁን ሁሉ በመስጠት ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል…   በዚሁ መሰረት፡- ·         አጠቃላይ የተሰበሰበ የብር መጠን - 192,300.00 ·         ለልዩ ወጪ (የአስክሬን ሳጥንና ካርጎ ጭነት) – 25,700.00 ·         የአየር ቲኬት (ሦስት ሰው) – 29,751.00 ·         ለወላጅ አባት እገዛ (የ 40 ማውጫ) – 30,000.00 ·         እንዲሁም ለባለቤቱ - 106,849.00   በጊዜያዊው ኮሚቴ በኩል እንዲሰጥ አድርጎ ኃላፊነቱን ተወጥቷል፤   በወንድማችን ብሬ ስም ሁላችሁንም ከልብ እናመሰግናችኋለን፤ የኮሚቴው አባላት በሃገር ወግ - “ሃዘን ከቤታችሁ አይግባ” ብለዋችኋል፤   @eepderash

📣 Update… "Never send to know for whom the bell tolls; it tolls for thee." - John Donne -- እንግዲህ እንደምታውቁት በአንድ ተቋም ውስጥ ብንሰራም
📣 Update…
"Never send to know for whom the bell tolls; it tolls for thee." - John Donne
-- እንግዲህ እንደምታውቁት በአንድ ተቋም ውስጥ ብንሰራም ከአንድ አካባቢ አልተሰባሰብንም… በሌላ ቋንቋ አሁን በምንሰራበት ቦታ ብንገኝም በአብዛኛው በዚያ አልተወለድንም… አንዱ ከምዕራብ ሸክፎ ወደ ደቡብ ዘልቋል፣ ሌላው ከሰሜን በቅሎ ምስራቅ ተሻግሯል፣ አንዱ ከዳር ተነስቶ መሐል ሲከትም፣ ከመሐል የወጣው ወደ ሌላ ጫፍ ተጉዟል… እንጀራና ሕይወት በየአቅጣጫው በትኖናል… ሆኖም በተቋማችን በኩል አንድ ማዕድ፣ በሃገራችን በኩል መፃዒ ዕድል፣ በመኖር በኩል ደግሞ ተመሳሳይ ዕጣፈንታ እንጋራለን… ⏳ አንደኛው ዕጣፈንታችን - ሞት ነው!!... ከሞት ጋር ቀጠሮ ይዘህ አትሞትም!!... ከሞት ጋር በዚህ ጊዜ፣ ቦታና ሰዓት እንገናኝ ተባብለህ አትጨባበጥም… ወይ በድንገት ሸርተት፣ ወይ በዝግታ ጥፍት ትላለህ… ይህ የማይቀር ጉዳይ ነው… ከላይ የጠቀስነው ገጣሚ እንዳለው - "የሞት ደወል ሲደወል ለማን ነው አትበል፤ ጥሪው ያንተም ነው።" የሚባለውም ለዚህ ነው… እና እንደነገርኩህ… ያለህበት ቦታ የሃገርህ አንድ ክፍል ቢሆንም የምትቀበርበት ላይሆን ይችላል… ባሕል፣ ልማድ፣ ወግ የሚባል ነገር አለን አይደል? - ቤተሰቦችህ አልቅሰው ከሚቀብሩበት፣ አይተውህ ሃዘን ከሚያወጡበት ቦታ መቀበር አለብህ… ግን አንተ ሞተሃል!!... ማን ከምትሻው ዳርቻ ያድርስህ?... ከእትብትህ መቀበሪያ ማን ያገናኝህ?... በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ሊረዱህ ቢሞክሩም የልባቸው አይደርስ ይሆናል… የሚያዋጡት ባይጠፋም ግን ሁሌ አይሞላ ይሆናል… 🏃‍♀️‍➡️🏃‍♂️‍➡️ ስለዚህ አቅም ያለው ደራሽ ያስፈልግሃል!!... በሥጋ ባትኖርም በአንተ ምክንያት ቤተሰብ እንዳይሳቀቅ… ሞትህን ማስቀረት ባይቻልም የክብር ቀብር ብርቅህ እንዳይሆን… አጋዥ ያስፈልግሃል… በቁም ትንሽ አውጥተህ የምታቆመው ሕብረት ስትሞት እንዲቆምልህ፣ እንደ ዘበት የወረወርካት ጎልብታ ክንድ እንድታበቅልልህ… ደራሽ ያስፈልግሃል!! ነገሩ ግን በዚህ ብቻ አያበቃም - እንደ መጠነ ዳሩ፣ እንደ አቅም እንደ ጅምሩ - ሩቅ ተጉዞ የደስታህ ተጋሪም ይሆናል…
እናም ደራሽ ስለነ እከሌ አይደለም - ስላንተ ወይም ስላንቺ እንጂ!...
--- አዎን - ደራሽን ደራሽ የማድረጊያው ጊዜ አሁን ነው!! --- በነገርህ ላይ ትናንት በርከት ያሉ ተሳታፊዎችን ያካተተ መስራች ጉባኤ ተደርጎ ምስረታው እንዲፈቀድ በምንጠይቅበት ረቂቅ Proposal (ምክረ-ሃሳብ) ላይ ግብዓት የመሰብሰብ ስራ የተሰራ ሲሆን ሰራተኞች በያሉበት የሚነጋገሩበትን አጀንዳዎች የሚቀርጹ፣ መመሪያ የሚያዘጋጁ እንዲሁም ጉዳያችንን ወደፊት የሚያስኬዱ 9 (ዘጠኝ) አባላት ያሉት ጊዜያዊ አደራጅ ተቋቁሞ ወደ ስራ ተገብቷል… ቀሪው የአንቺ/ የአንተ ተሳትፎ ነው!!... ደራሽ ስላንተ/ቺ ነውና!! ደራሽ ባንተ/ቺ ነውና!! ደራሽ ላንተ/ቺ ነውና!! --- ደራሽ ምርጫ እንጂ ግዴታ አይደለም… ሞት ግን ግዴታ እንጂ ምርጫ አይደለም… ስለ ደራሽ ሲነገር ስለሌሎች አታስብ - ስለራስህ እንጂ… 🔸 የደራሽን ቻናል እየተቀላቀላችሁ ቆዩ… ሃሳባችሁን በተቻለ መጠን በኮሜንት መስጫው በኩል ላኩ… በቅርቡ ዝርዝር ጉዳዮችን ይፋ እናደርግላችኋለን!! https://t.me/eepderash 🟢 ደራሽ - አዎን በቅርቡ ዕውን ይሆናል!!

🟢 Are We All Moving In The Same Direction? —
🟢 Are We All Moving In The Same Direction? —

⚙️ ከወረቀት ቁልል ወደ ዲጂታል ጎዳና - አዲስ የሥራ ባህል የድሮውን ጊዜ እስቲ እናስታውስ... የአንድ ደብዳቤ ከመፃፍ እስከ መፈጸም የነበረው ጉዞ እጅግ አሰልቺና አድካሚ ነበር… ➡️ ማስታወሻ (
⚙️ ከወረቀት ቁልል ወደ ዲጂታል ጎዳና - አዲስ የሥራ ባህል   የድሮውን ጊዜ እስቲ እናስታውስ... የአንድ ደብዳቤ ከመፃፍ እስከ መፈጸም የነበረው ጉዞ እጅግ አሰልቺና አድካሚ ነበር…   ➡️ ማስታወሻ (Memo) ይታተማል፣ ይፈረማል፣ ኮፒ ይደረጋል፣ ይመዘገባል፣ ከቢሮ ቢሮ በእጅ ይዞራል፣ በጠረጴዛዎች ላይ ይደረደራል... አንዳንዴም በወረቀቶች ክምር ሥር ተደብቆ ይረሳል… የሥራ ኃላፊዎች «ደብዳቤው አሁን የት ደረሰ?» ብለው ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ስልክ መደወል ነበረባቸው… ሠራተኞችም የቆዩ መረጃዎችን ለመፈለግ በየፋይሉና በየካቢኔው ውስጥ ይኳትኑ ነበር… ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ፣ ወረቀትን ተከትሎ በመሮጥ ውድ ጊዜ ይባክን ነበር…   👉 ዛሬ ግን ያ ጉዞ ሙሉ በሙሉ እየተቀየረ ነው!   ➡️ በተቋማችን የዲጂታል ደብዳቤ እና የሥራ አመራር ሥርዓት Digital Letter and Task Management System (E-Service) አማካኝነት፣ ግንኙነታችን ከአሁን በኋላ በወረቀት፣ በአካል በመንቀሳቀስ ወይም በቢሮ ግድግዳዎች አይገደብም…   ➡️ አሁን አንድ ደብዳቤ ከአንድ የሥራ ክፍል ወደ ሌላው በሰከንዶች ውስጥ መጓዝ ይችላል… አንድ የሥራ መመሪያ ያለ አንድ ወረቀት ንክኪ ይመደባል፣ ይከታተላል፣ ቁጥጥር ይደረግበታል፣ ያላንዳች የወረቀት ንብርብር በስኬት ይጠናቀቃል።   ⬇️ ነገር ግን የዚህ ሥርዓት እውነተኛ ዋጋ ፍጥነት ብቻ አይደለም፤ ከፍጥነት በላይ የሆኑ አምስት ታላላቅ ምሶሶዎች አሉት፦   🟢 ግልጽ እይታ (Visibility)፦ የሥራ ኃላፊዎች የደብዳቤዎችንና የሥራዎችን ሁኔታ በቀጥታ (Real-time) ማየት ይችላሉ። መዘግየቶች ወደ ችግር ከመቀየራቸው በፊት አስቀድመው ይታያሉ። ኃላፊነቶች ግልጽ ናቸው፤ ዕድገቶችም ይለካሉ። መረጃ በሚፈለግበት ጊዜ ወዲያውኑ ስለሚገኝ ውሳኔዎች ይፈጥናሉ።   🟢 ግልጽነት (Transparency)፦ እያንዳንዱ እርምጃ ይመዘገባል። እያንዳንዱ የተሰጠ ሥራ ባለቤት አለው። እያንዳንዱ ሂደት ዲጂታል አሻራውን ጥሎ ያልፋል። ይህ ደግሞ በመካከላችን እምነትን፣ ተጠያቂነትን እና ጠንካራ የኃላፊነት ባህልን ይፈጥራል።     🟢 ተደራሽነት (Accessibility)፦ በዋናው መ/ቤት፣ በኃይል ማመንጫ ጣቢያ፣ በሪጅን ቢሮዎች ወይም በሩቅ ሆነው በሥራ ላይ ቢሆኑም፤ ሠራተኞች የኩባንያቸውን የኢሜይል አካውንት በመጠቀም በኮምፒውተር፣ በላፕቶፕ ወይም በሞባይል ስልኮች ሥርዓቱን መጠቀም ይችላሉ። መረጃ በተፈለገበት ጊዜና ቦታ ሁሉ ዝግጁ ነው።   🟢 አብሮነትና ትብብር (Collaboration)፦ ቡድኖች በአንድ መድረክ ላይ መገናኘት፣ አዳዲስ መረጃዎችን መለዋወጥ፣ ሰነዶችን መገምገም እና ሥራዎችን መከታተል ይችላሉ። «ሰነዱ የት አለ?» ብሎ ከመጨነቅ ይልቅ፣ ትኩረታችን መከናወን ባለበት ሥራ ላይ ብቻ ይሆናል።     🟢 ውጤታማነት (Efficiency)፦ የህትመት ወጪ የለም፤ የሰነድ ክምችት ስጋት የለም፤ በአካል የሚደረግ ተደጋጋሚ ክትትል ቀርቷል፤ የጠፋ ሰነድ ወይም አላስፈላጊ መዘግየት ታሪክ ሆኗል።   ☀️ ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ ይህ ወደ መጻኢው ዘመን የሚሰነዘር  ትልቅ እርምጃ ነው!   ➡️ የዲጂታል ሽግግር የሚረጋገጠው ሶፍትዌር በመጫን ብቻ አይደለም፤ ሰዎች አዲስ የአስተሳሰብና የሥራ መንገድን በቅንነት ሲቀበሉ እንጂ… በእያንዳንዱ የ E-Service ማስታወሻ፣ በዲጂታል መንገድ በሚከታተሉት ሥራ ወይም በሥርዓቱ በኩል በሚሰጡት ምላሽ—እርስዎ ይበልጥ ብልህ፣ ፈጣን እና እርስ በእርሱ የተገናኘ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ለመገንባት የበኩልዎን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው…   🔸 ያለ ወረቀት የመጓዝ ጉዟችን ቀድሞውኑ ተጀምሯል…   ❓ አሁን ላይ ጥያቄው «ወደ ዲጂታል እንቀየራለን ወይ?» የሚለው አይደለም፤ ጥያቄው «ምን ያህል በፍጥነት እንቀበለዋለን?» የሚለው ነው!   🚀 ይጠቀሙበት! 🚀 ይመኑበት! 🚀 ያሻሽሉት!   ☀️ ምክንያቱም ዛሬ በዲጂታል የምናደርጋት እያንዳንዷ እርምጃ፣ ነገ ማየት የምንፈልገውን ታላቅ ተቋም የምንገነባባት መሠረት ናትና! —— Digital tools don’t transform an organization. People who know how to use them do. 🙏

📣 . . . ከቀናት በፊት ከነስሙም ያልነበረው ደራሽ ዛሬ የብዙዎችን ቀልብ ስቦ “የምን እናድርግ?” ጠያቂዎችን አበርክቷል… በርከት ያሉ መልዕክቶች በውስጥ መስመር ደርሰውናል፣ ስልኮች ተደውለውልና
📣 . . . ከቀናት በፊት ከነስሙም ያልነበረው ደራሽ ዛሬ የብዙዎችን ቀልብ ስቦ “የምን እናድርግ?” ጠያቂዎችን አበርክቷል… በርከት ያሉ መልዕክቶች በውስጥ መስመር ደርሰውናል፣ ስልኮች ተደውለውልናል፣ በአካል ቢሮ ድረስ በመምጣትም ሃሳብ ያጋሩን አሉ… አሁን ደራሽ የሁሉም ወደመሆን አድጓል… በግል ውይይት የሰው ኃይል ዘርፍና የሰራተኛ ማሕበር አመራሮች ለስኬቱ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸውልናል… ⭐️ ቀሪው የእናንተ ውሳኔ ነው!!... ‘ሞትን ማስቀረት ባንችልም የክብር ቀብር ብርቅ ሊሆንብን አይገባም’ ብለን የጀመርነው ሃሳብ፡- ☀️ ሰዎች ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ውስጥ ሲገኙ አለሁ የሚል ☀️ በድንገተኛ ሞት ጊዜም ሙሉ ወጪዎችን ከመሸፈን ተሻግሮ የሟች ቤተሰቦችን የሚደግፍ ☀️ ሰራተኞች ተቋሙን አገልግለው በጡረታ ሲሸኙ እናመሰግናለን የሚል . . . ወዘተ… ሊሆን ይገባዋል የሚሉ ሃሳቦች እየተስተናገዱ ነው… ሁሉንም ሃሳቡ በተቋም ደረጃ እውቅና ካገኘ በኋላ በሚዘጋጀው መመሪያ ላይ በግልጽ እናሰፍራለን… በዚህ በኩል ልምዶች ያላችሁ አካፍሉን… የሚቋቋመው ፈንድ ሰራተኞችም ሆነ የስራ ኃላፊዎች በእኩልነት የሚታዩበትና ከሰራተኞች ማሕበርና ሰው ኃይል በተጨማሪ ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች ድርሻ ወስደው የሚሰሩበት፣ በሰራተኞች - ለሰራተኞች የሚቋቋም ሰፊ የማሕበራዊ አገልግሎት ፈንድ ነው… ዛሬ በትንሽ እንጀምረዋለን!... ነገ በራሱ ገዝፎ እንደነቅበታለን!! ከዛሬ ጀምሮ ከደራሽ ጋር በተያያዘ የምንጨዋወትበት ቻናል ተዘጋጅቷል፤ ተቀላቀሉት፣ ፤ሌሎችንም ጋብዟቸው… @eepderash https://t.me/eepderash በሚቀጥለው ሳምንት ከሚደረግ የጅማሬ ስብሰባ በኋላ የሚኖሩ ማናቸውንም ለውጦች በአዲሱ ‘ደራሽ ቻናል’ እናጋራችኋለን… . . . በያለንበት ስለ ደራሽ እንነጋገር!!

. . . ❗️❗️❗️
. . . ❗️❗️❗️

☀️ The Dawn of DERASH ☀️ 💡 Sometimes the most meaningful ideas are born not from plans, budgets, or directives, but from rea
☀️ The Dawn of DERASH ☀️ 💡 Sometimes the most meaningful ideas are born not from plans, budgets, or directives, but from real human experiences. Over the past few days, something remarkable has happened. 📞 A simple conversation about how we support one another during life's most difficult moments has grown into a shared vision. 🔹 Employees from different work units, professions, and locations have expressed their support for the idea of establishing DERASH – EEP Employees Social Affairs Fund.   🔺 This response tells us something important: 🔺The need is real. 🔹The time is now.   ✅ DERASH is more than a fund. ❕ It is a promise. ✅ A promise that when hardship comes, someone will arrive. ✅ A promise that when a family is struggling, someone will stand beside them. ✅ A promise that when an employee falls, they will not face the challenge alone.   ☀️ For years, many of us have contributed individually whenever colleagues experienced loss, illness, accidents, or other emergencies. ☀️ We have done so with compassion and goodwill. DERASH seeks to transform that same spirit into a sustainable institution that serves all employees, fairly and consistently.   🔘 What makes this initiative special is that it belongs to all of us. ❌ It is not an HR initiative. ❌ It is not a management initiative. ❌ It is not a labor union initiative. ✅ It is an employee initiative. ✅ A collective expression of who we are and how we choose to stand together.   ➡️ As discussions continue, let us focus on building something that future generations of EEP employees will be proud of. Let us create a system founded on solidarity, transparency, trust, and shared responsibility.   🟢 Years from now, people may not remember where the idea started.   🟢 But if DERASH becomes a reality, there will be families who receive support when they need it most, colleagues who are treated with dignity, and employees who find comfort in knowing that they belong to a community that cares.   ✅ That is the legacy we can build together. ✅ That is the dawn of DERASH.   Together, we stand. Together, we rise. DERASH — Coming Soon.

2️⃣ አስቸኳይ ጥሪ ያው እንደሰማችሁት ሰሞኑን አንድ ምርጥ ሰው አጣን... ዝምታ ራሱ የሚቀናበት ጸጥ ያለ ሰው... ከእርጋታ እንኳን የሚረጋ ልዩ ሰው... አንዳንዴ ምልክት የምታጡለት ሰው የለም?.
2️⃣ አስቸኳይ ጥሪ ያው እንደሰማችሁት ሰሞኑን አንድ ምርጥ ሰው አጣን... ዝምታ ራሱ የሚቀናበት ጸጥ ያለ ሰው... ከእርጋታ እንኳን የሚረጋ ልዩ ሰው... አንዳንዴ ምልክት የምታጡለት ሰው የለም?... ስለ እርሱ ልትናገሩ ብላችሁ 'እንዲህ ሚሆነው፣ እንዲያ ሚያደርገው' የምትሉለትን የሚያሳጣችሁ ዓይነት ሰው የለም?... ባለፈበት መንገድ መጓዙን እርግጠኛ ሆናችሁ የማትናገሩለት፣ ወንበሩ ላይ መኖሩን እስክትረሱ የማታስተውሉት፣ ማስቀየም የማያውቅ፣ ለቃሉ የሚጠነቀቅ፣ ፍጹም ሌላ ዓይነት ሰው... [ከትናንት በስቲያ እንደዚህ ዓይነት ሰው አጣን...] ልንረዳው ሳንሞክር... ልናስተውለው ሳንጥር... ልናደምጠው ጊዜ ሳንቸር - አመለጠን... --- ዌል... ሞቱን ማስቀረት አንችልም!!... ሰው የመሆን ዕጣ ነው… "In every breath we are nearing to death" እንዲሉ... በሰዓቱ፣ ከሞቱ ድንገተኛነት እኩል ድንጋጤ የፈጠረብን 'እንዴት አስክሬን ወደ ቤተሰብ እንሸኝ?' ለሚለው ጥያቄ ገንዘብ ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ሲከሰት ነው... በዚህ ምክንያት ረጅም ሰዓታት ባከኑ... ጭንቀት፣ ድካም፣ ለቅሶ... [አስከሬኑ ጸበል ተቀምጦ የኛን መምጣት ይጠብቃል... ምንም ማድረግ ያልቻለ ቤተሰብ አስሬ ወደኛ ይደውላል... ይህ ከሞቱ በላይ ህመም አለው... ከህልፈቱ በላይ አቁሳይ ነገር አለው...] 🔸 ረጅሙን ታሪክ ስናሳጥር፣ የፋይናንስ ዘርፍ ርብርብ፣ የክሊኒክ ሰዎች ደግነት፣ የፍሊት ቢሮ ቀናነት፣ የጓደኞቹና ባልደረቦቹ ድካም፣ እስከ ምሽት 2:00 ሰዓት የተደረገና ከአዲሳባ እስከ መቀሌ/ አሸጎዳ የሚዘረጋ የብዙ ባልደረቦችና ወዳጆች ርብርብ ትናንት አስክሬኑን በሰላም ወደ ትውልድ መንደሩ አድርሶ ለዘላቂ ማረፊያው አበቃው... [እዚህ ላይ አትርሱ - አቅም የሌለው ቤተሰብ ከፍ ያለ ወጪ አውጥቷል፤ ተያያዥ ወጪዎች ገና ወደፊትም ይጠብቁታል...] ጥያቄው ግን ይህ ነው... እስከመቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምንቀጥለው?... እስከመቼ ነው በመዋጮ ቀብራችን የሚፈጸመው?... እስከመቼስ ነው በቅርብ የሚያውቁን ብቻ ተሯሩጠውልን፣ ራቅ ብለው ያሉ ባልደረቦቻችን በወሬ ብቻ የሚያውቁን?... ለምንድነው ደራሽ የሰራተኞች ማሕበራዊ አገልግሎት ፈንድ የማይኖረን?... ለምንድነው ከወር ደመወዛችን የምትሸረፍ ድቃቂ ብር ተደማምራ የቁርጡን ቀን ጣጣ የማትከድነው?... ለምንድነው በተቆራረጠ መንገድ፣ የዘርፍ ወይም የስራ ክፍል ዕድር የምንፈጥረው?... የአንዳችን ሃዘን ስለምን የሁላችን ሃዘን አይሆንም?... የአንዳችንስ ደስታ ስለምን ሁላችንን ደስ አይልም?... "ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፣ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው" ይባል አይደል?... መች ነው ቤተሰብም ሆነ ባልደረባ ሳይሳቀቅ፣ በድንገተኛ ወጪ ጎጆው ሳይነቀነቅ፣ ተሽከርካሪ መድበን፣ የፕሌን ወጪ ሸፍነን፣ ሳጥን ገዝተን፣ የሞት ምስክር ወረቀት (Death certificate) እና ተያያዥ የህክምና ሰነድ ጨርሰን፣ ቤተሰብ ቀብር እስኪያስፈጽም ድረስ የሚጠብቁትን ወጪዎች በሙሉ ዘግተን ቀብር የምናስፈጽመው?... [የተጋነነ ይመስላል አይደል?... 7800 ሰራተኛ ከደመወዙ ላይ፣ በስፖርትና HIV መዋጮ መንገድ 50 ብር እየተቀነሰ ወደ ፈንዱ አካውንት ቢገባ ብላችሁ አስቡት... በቀላሉ በወር 390,000 ብር ይገኛል... ለእያንዳንዳችን በዓመት 600 ብር ብቻ የሚያስወጣን ይህ ተግባር 4,680,000 ብር ያስገኛል...] ታዲያ ይህ ብር የባንክ ወለድና ሌሎች የቢዝነስ ሃሳቦች ተጨምረውበት ሌላ ታሪክስ አይሰራም?... ስንት ቤተሰብ ነው በእኛ ባልደረቦች ሞት ተጎሳቁሎ ያለው?... ስንት ልጆች ናቸው ከትምህርት ቤት ደጅ የጠፉት?... ስንቶቹስ የሚበላ የሚቀመስ አጥተው በየቤቱ ተቆራምደው ይሆን?... ጎበዝ - ይህን ታሪክ የምንቀይርበት ጊዜው አሁን ነው!!... አሁኑኑ በየስራ ክፍላችን፣ በየመገናኛ ቦታችን በዚህ ጉዳይ ላይ እንነጋገር... ሰራተኛ ማሕበር በዚህ ጉዳይ ውይይት ይጥራ... የሰው ኃይል አስተዳደሮች ይህን አጀንዳ በቡድኖቻቸው መሐል ያንሱ... ስንስማማ - በአዲሱ በጀት ዓመት እውን እናድርገው!!... 📣 ሞት በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የሁላችንንም በር ያንኳኳል - ልናስቀረው አንችልም... የክብር ሞት ግን ብርቅ ሊሆንብን አይገባም... በእኛ መለየት ማግስት የሚበተን ቤተሰብም መኖር የለበትም... 📌 ቤተሰብ እኮ ነን ጎበዝ!... አንድ ማዕድ ነው ያለን... ቸግሮኝ ብጮህ ከእናቴ በፊት የእናንተ ጆሮ ነው የሚሰማኝ... ብትደክሙ ከወንድማችሁ ይልቅ የእኔ ትከሻ ነው ቅርባችሁ... I’m here for you, and I know you're here for me. We can be each other's strength. እያንዳንዲቷን ጉዳይ ተቋሙ እንዲፈታልን መጠበቅ የለብንም... የራሳችንን ጠጠር መወርወር ደግሞ ይጠበቅብናል... እንደ ግለሰብ የሕሊና እርካታ ምንጭ ነው - ትንሽ አውጥተን ብዙ እናግዛለን... እንደ ሰው በእኛ ማለፍ ቋሚ እንዳይሳቀቅ ጥሪት ማኖሪያ ነው - ለሌሎች እያዋጣን ለራስ እንተርፋለን... ትናንት - አባደራሽ በመሰረቱት ብድርና ቁጠባ ተቋም፣ ዛሬ (ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ሳይቀር) ከብዙ ችግር ያመለጡ፣ ቁምነገር የጨበጡ ሰዎች ሲያመሰግኑ እንሰማለን... አሁን ያለን እኛ ደግሞ የሰራተኞች ማሕበራዊ አገልግሎት ፈንድ መስርተን [ለምን ለሃዘን ብቻ?] በደስታችንም ከጎናችን የሚቆም አጋር እንፈጥራለን... --- ደራሽ!! ____ ዕድሜ ለመጨመር ብቻ ሳይሆን ለመኖርም ያብቃን!! ____ በያለንበት እንበርታ!!

1️⃣ እናም ተቀበረ... ቆይቶ ትውስታ ይሆናል... ቆይቶ ይዘነጋል... ቆይቶ ይረሳል - ይህ የሁላችንም ዕጣ ነው!!... ከዚህ በፊት በብዙ ሰዎች ህልፈት ደንግጠናል፣ በብዙ ወዳጆቻችን ሞት አዝነና
1️⃣ እናም ተቀበረ... ቆይቶ ትውስታ ይሆናል... ቆይቶ ይዘነጋል... ቆይቶ ይረሳል - ይህ የሁላችንም ዕጣ ነው!!... ከዚህ በፊት በብዙ ሰዎች ህልፈት ደንግጠናል፣ በብዙ ወዳጆቻችን ሞት አዝነናል፣ በብዙ ባልደረቦቻችን ሞት ተከፍተናል... ግና የማንመልሳቸው ጥያቄዎች ዛሬም አሉ... 🔴 ስንቶቹን ስለ ደግነታቸው እናስብ ይሆን?... 🔴 ስንቶቹን ስለ ንጽሕናቸው እናስታውስ ይሆን?... 🔴 የነማን ቅንነት ከአዕምሮአችን ይደቀን ይሆን?... 🔴 የስንቱ ሰው ርህራሄ የትውስታችን አካል ይሆን? [የአንድ?.. የሁለት?.. እንጃ... ምናልባት የማንም!!] ይህ እውነት ነው... ስንጎድል ለጊዜው የምንጎድልበት አለ... ለውስን ጊዜ የምንቸግረው አለ... ለቀናት ትውስታው የምንሆንበት አለ... ከዚያ ግን የለንም... የኑረት ውክቢያ፣ የማይሞላ ሩጫ፣ የጥረህ ግረህ ግፊያ የሰውን አዕምሮ ይሞላዋል... እንደበዝዛለን... እንተናለን... የጊዜ ቀስት ወደፊት ብቻ እንደሾለ ነው... ወደኋላ ማየት ለሁሉ አልተሰጠም... 🔸 እየጣልን እናልፋለን!... 🔸 እያነጠብን እንሄዳለን!... 🔸 እያጎደልን እንጓዛለን!... ግና በአንዳንዱ ልብ... የማንበርድ ግለት፣ የማንጠፋ እሳት፣ የማንሰወር ላምባዲና መሆናችን አይቀርም... ከእናትህ ልብ ሞት በቀላሉ አይፍቅህም... [እያነባች ታስብሃለች!]... ወይም ደግሞ የእናትህ ሞት እንደ ተራ ውልብታ አይዘነጋህም... [ትመላለስብሃለች!]... ከልጅህ ልቡና እንደ ቀላል ነገር አትጠፋም... ወይም ደግሞ የልጅህ ሞት የዕድሜ ልክ የእግር እሳትህ ከመሆን አይቀርም... የሆነስ ሆነና እየኖርክ ነው?... እየኖርሽ ነው?... እየኖራችሁ ነው?... በሩጫዎች መሐል መካከለኛ አላችሁ?... የእፎይታ ታዛ - ትንሽዬ ማረፊያ - አፍታ ቅጽበት አለቻችሁ?... ትንፋሽ እየወሰዳችሁ ነው?... በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች እንዴት ናቸው?... ያጎበጣቸው ሸክም፣ ያጠወለጋቸው ህመም የለም?... ያስከፋቸው የጎጆ ደመና፣ ያደከማቸው የኑሮ ጫና የለም?... ስንቱን ሰው አስተዋላችሁ?... የስንቱን ፊት አነበባችሁ?... የስንቱን ቀንበር አሳረፋችሁ?... ችግራችሁን በግልጽ ትናገራላችሁ ወይስ ሰቆቃችሁን ከራሳችሁ ጋር ብቻ ትጋፈጣላችሁ?... የምትሸሸጉበት ጥግ አላችሁ ወይስ ለብቻ ማልቀስን ተላምዳችኋል?... እንደሚያልፍ አመናችሁ ወይስ ሳይገፋን መች አልፎን አላችሁ?... [ተስፋ ነው ወረፋ ከዓይናችሁ ፊት ያለው?...] እየኖራችሁ ጎበዝ... ሳብ - ለቀቅ፣ ሳብ - ለቀቅ፣ ሳብ - ለቀቅ፣ - እየተነፈሳችሁ... ሞት አዲስ ነገር የለውም - ሳይኖሩ መሞት ግን ህመም አለው፤ ለአፍታ ሳቅ፣ ለቅጽበታትም ደስታ እጅ ሳይሰጡ ማለፍ ጉድለት አለው... After all, we are not here merely to survive — we are here to thrive. . . .

Digital mindset Round 6 trainees list.xlsx0.43 KB

Digital mindset Round 6 trainees list.xlsx0.43 KB

6️⃣ Learn it. Use it. Live it. Digital is the new normal. ሰላም ወዳጆች… 🙏 እንዴት ናችሁ ⁉️ -- 🟢 የተቋማችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ በዕውቀት፣ በክ
6️⃣ Learn it. Use it. Live it. Digital is the new normal. ሰላም ወዳጆች… 🙏 እንዴት ናችሁ ⁉️ -- 🟢 የተቋማችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ በዕውቀት፣ በክህሎት እና በአመለካከት ግብዓት ለመደገፍ የተቀረጸው የምዕራፍ አንድ የ Digital mindset, Digital Literacy እና Digital work tools ስልጠና፣ ✔️ በተሳታፊዎች እጅግ የሚያስደስት የማወቅ ጉጉትና ዲሲፕሊን፣ ✔️ በአሰልጣኞች ከፍ ያለ ብርታትና ጥረት፣ ✔️ በዲጂታል ትራንሰፎርሜሽን እና በኦፕሬሽን ዘርፍ (ሪጅንና ማመንጫ) የስራ ኃላፊዎች የቅርብ ክትትልና ከፍ ያለ ድጋፍ ከስድስተኛ ዙር ደርሶ እነሆ ሊጠናቀቅ ነው… 👀 ምዕራፍ ሁለትና ምዕራፍ ሦስት መርሃግብሮች በቅርቡ (በአዲሱ በጀት ዓመት) ይጀመራሉ… -- 📝 የምዕራፍ አንድ፣ የስድስተኛ ዙር ሰልጣኞች ከሦስቱ ማዕከላዊ ሪጅኖችና ከረጲ ደ/ቆ/ኃ/ማመንጫ ጣቢያ በተላከልን መሰረት ስም ዝርዝራቸው ከዚህ በታች ተያይዟል… -- 📆 የስልጠና ቀን - ማክሰኞ 25/09/2018 📍 የስልጠና ቦታ - ኢትዮ ፓወር አካዳሚ የስልጠና ማዕከል 🏠 የስልጠና ክፍል - ኮምፒውተር ላብ - 2 ⏳ ሰዓት - ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ -- 🖥 Digital mindset builds awareness, digital literacy builds capability, and digital tools build results. -- EPA – Training Center We Strive to Create a Learning Organization!!

➡️ ለመማር የተዘጋጀ ከጫማው ስር ያለውን መርመስመስ ያስተውላል - ከጉንዳን ይማራል!! 📌 The Best Master Class in Leadership Is Under Our Feet Right now: t
➡️ ለመማር የተዘጋጀ ከጫማው ስር ያለውን መርመስመስ ያስተውላል - ከጉንዳን ይማራል!! 📌 The Best Master Class in Leadership Is Under Our Feet Right now: the Ant. 🐜🐜🐜 🔻 Ants don’t have a boss micromanaging them (the Queen only lays eggs), yet they achieve flawless execution through three powerful habits: ✅ Collective Brain: Each one alone cannot produce much effect; together they create exponential power which individual power doesn’t possess. ✅ Radical Initiative: If one ant spots something problematic, they don't ask for an order to do what’s necessary; they just do it. ✅ Industrial Persistence: Once they become aware of their purpose, they start creating an unstoppable path for reaching it, unaffected by any distractions. ⬇️ The Message: Create a high-trust environment in which people feel empowered to act independently and concentrate on achieving goals as a team. -- “አንተ ታካች፣ ወደ ግብረ ጉንዳን ሂድ!” - ንጉስ ሰለሞን -- Have a good day 💖

💠 (የቀጠለ…) ኃይል ማምረት፣ ኃይል ማስተላለፍ፣ Grid ማስተዳደር ብቻውን ግብ አይደለም... ይህ ኃይል መሰራጨት አለበት... ለዚህም ሲባል የ Distribution ስርዓትና የአገልግሎት መ/ቤቱ
💠 (የቀጠለ…) ኃይል ማምረት፣ ኃይል ማስተላለፍ፣ Grid ማስተዳደር ብቻውን ግብ አይደለም... ይህ ኃይል መሰራጨት አለበት... ለዚህም ሲባል የ Distribution ስርዓትና የአገልግሎት መ/ቤቱ ትኩረት ያስፈልጋል... EEP 'ጅምላ ሻጭ ነኝ፣ ኃይሉን ሰብስቴሽን ካደረስኩ በኋላ ምን አገባኝ፣ ቀሪው የ EEU ድርሻ ነው' ምናምን ቢል አያዋጣውም... ስርጭቱን ማገዝ አለበት... ያመረተውና ያስተላለፈው ኃይል ተጠቃሚው ጋ ካልደረሰ፣ ደርሶም ካልተሸጠ፣ ተሽጦም ፈረንካ ካላመጣ ሕልውና የለውም... 📌 በጥሬ ቋንቋ እናውራ ከተባለ የ EEP ጅምላ ሻጭነት ከቲማቲም ነጋዴም በላይ Risk አለበት... Energy ፍሪጅ ውስጥ የሚቆይ ወተት፣ ቋንጣ ተደርጎ የሚቀመጥ ሥጋ አልያም በቅቤ ታሽቶ የሚሰነብት ጭኮ አይደለም... በተመረተበት ቅጽበት አገልግሎት ላይ ካልዋለ 'የሚሸት' ወይም 'የሚበሰብስ' ቅሪት እንኳ የለውም - ትነት በለው... የለም - Period!! 📣 ስለዚህ ለ EEP እየሰራህ ለ EEU የምታግዘው ለራስህ ስትል ነው... መኖር ስላለብህ!!... ነገሩን በቢዝነስ ዓይን ካየኸው ያንተ ጥቅም የሚመነጨው ከተቋምህ የማምረት አቅም ብቻ ሳይሆን ከደንበኛህ የመግዛት ጥንካሬም ጭምር ነው… ነገሩ እንደ Loop ነው - ይመጋገባል... አንዱ ያለሌላው ሕልውና የለውም… 🟢 አሁን ምስሉ ጎላ ማለት ይጀምራል... ኃይሉ ተሰራጭቶ ሲሸጥ፣ ተጠቃሚው ዘንድ ደርሶ አገልግሎት ላይ ሲውል... ደንበኛ ላገኘው አገልግሎት ተገቢ ክፍያ ሲፈጽም... ክፍያው ተመልሶ አዲስ ፕሮጀክትና ነባር ክዋኔን ሲደግፍ... በዚህ ስርዓት ውስጥ አጥር የሌለው መስተጋብር፣ ቅንጅትና መደጋገፍ ሲገዝፍ የሸራው ምስል ምንነት እየተለየ ይመጣል... ❓ ለምን ይመስልሃል የለስላሳ መጠጥ አምራቾች ለቸርቻሪው ቤቱ ድረስ ምርታቸውን የሚወስዱለት?... ለምን ይመስልሃል ፍሪጅ፣ ጃንጥላና የድርጅት ስያሜ ባነር በነፃ የሚያሰሩለት?... ሱፐር ማርኬቶች፣ ሱቆችና አገልግሎት አቅራቢዎች ልዩ ልዩ ምርቶች በራቸው ድረስ የሚቀርብላቸው ለምንድነው?... 🔑 መልሱ ግልጽ ነው - የአምራች ሕልውና ከቸርቻሪ ጤና ስለሚመነጭ የሚል ነው... አዎን - የኢነርጂ ሴክተርም እንዲሁ ነው... ነጠብጣቦቹን ሳንገጣጥም ምስሉ አይወለድም... ምስሉ ሳይወለድ ነጥብ ትርጉም አያገኝም... አሁንም ግን ምስሉ አልተሟላም... ❓ መች ነው ታዲያ የሚሞላው?... ሃገርህ የኢነርጂ ጥምዋን ስታረካ... በቂ ኃይል ለዜጎች ሁሉ ሲደርስ፣ አስተማማኝ አቅርቦት ሲፈጠር... እኔና አንተ በዚህ ያለነው ይህን ዕውን ለማድረግ ነው... እኔና አንተ ነጥብ የሆነው ይህን ስዕል ለመውለድ ነው... ደስ አይልም ግን?... ነጥብ ሆኖ በትኩረት፣ ስዕል ሆኖ በቅንጅት መቆም... ደስ ይላል!... ለመኖር ትርጉም ይሰጣል!!... ➡️ ማቀድ፣ መንደፍ፣ መገንባት፣ መከወን፣ ማስተላለፍ፣ መቆጣጠር፣ ማሰራጨት፣ መሸጥ፣ ለሁሉ መድረስ፣ መሻገር - የተሟላ ምስል፣ ግዙፍ ስዕል... ሃገር!! ___ 🕹 በመግቢያዬ ላይ ያነሳሁትን ጥያቄ ደግሜ ልጠይቅህ... አንድን ጉዳይ ከግዙፉ ስዕል አንፃር ትመለከተዋለህ ወይስ በቁንጽል ገጹ ትመዝናለህ?... "ይጠቅመኛል" በምትለው ላይ ታተኩራለህ ወይስ "ይጠቅመናል" ለምትለው ታዋጣለህ?... "ይመለከተኛል" ባልከው ላይ ትወሰናለህ ወይስ ስለ "ጋራ ጉዳይ" ትደክማለህ?... 💠 የእይታህ ጠገግ አጠቃላይ ውጤቱን ይወስነዋል... It's all about Mindset!! ___ 🔠 እንደ ነጥብነታችን ከሸራው እንነጥባለን - በነጠብጣብ ሕብር የተሟላ ምስል እንፈጥራለን!!!... ሙሉውን ስዕል ሳናይ ዓይናችን እንዳይከደን መሃላ አጽንተናልና... ___ Systems thinking is the discipline of seeing an organization as a dynamic, interconnected living system where people, processes, culture, structure, and decisions continuously influence one another over time. ---- በያለንበት እንበርታ!!

⚙️ System Thinking 1O1 💡 የምስል አተያይህ እንዴት ነው?... አንድን ጉዳይ ከግዙፉ ስዕል (Big picture) አንፃር ትመለከታለህ ወይስ በቁንጽል ገጹ ትመዝናለህ?... "ይጠቅመኛል
⚙️ System Thinking 1O1 💡 የምስል አተያይህ እንዴት ነው?... አንድን ጉዳይ ከግዙፉ ስዕል (Big picture) አንፃር ትመለከታለህ ወይስ በቁንጽል ገጹ ትመዝናለህ?... "ይጠቅመኛል" በምትለው ላይ ታተኩራለህ ወይስ "ይጠቅመናል" ለምትለው ታዋጣለህ?... "ይመለከተኛል" ባልከው ላይ ትወሰናለህ ወይስ ስለ "ጋራ ጉዳይ" ትደክማለህ?... ✅ የእይታህ ጠገግ ውጤቱን ይወስነዋል... እርስ በእርሱ በተያያዘ ዓለም ውስጥ ስለምንኖር የማይመለከተን ጉዳይ የለም... የምናተኩርበት ነጥብ ግን ሊለያይ ይችላል... ምን ማለት ነው?... እንደ ሰው ባለህ ውስንነት ምክንያት ሁሉን ነገር ልትሆን አትችልም - ስለዚህም ልታሳካ በምትችለው ነገር ላይ ይበልጥ ታተኩራለህ... ነገርግን ያተኮርክበት ነጥብ የሁለንተናዊው ስዕል አካል እንደመሆኑ ባንተ እንከን ሌላኛው የስዕል ክፍል እንዳይጎዳ ጥንቃቄ ታደርጋለህ... ያም ማለት... 🔥 'የራሴን ኃላፊነት ከተወጣሁ ቀሪው አያገባኝም' ሳይሆን 'ሌሎች የተሻለ እንዲያዋጡ ልረዳቸው ይገባል' ትላለህ፤ 🔥 'የፈለግሁትን የማድረግ መብት አለኝ' ሳይሆን 'ተግባሬ በሌሎች ላይ ለሚያስከትለው ችግር ኃላፊነት አለብኝ' ትላለህ፤ 🔥 'እኔ እስከተጠቀምኩ ስለ ሌላው አያገባኝም' ሳይሆን 'ሁሉም የሚገባውን ድርሻ ሲያገኝ የመስተጋብር ሚዛን ይስተካከላል' ትላለህ፤ 📣 [ይህ ገጽ ስለ ስራ የምናወራበትም አይደል?...] ይህን ሃሳብ በስራችን በኩል አስታከን ብንጨዋወተው ተጨባጭ ቅርጽ መፍጠር እንችላለን... ለምሳሌ - የ Generation Operation ዘርፍ ባለሙያ ብትሆን በስራህ ምክንያት የምትወስደው ኃላፊነት ውስን እንደሚሆን ግልጽ ነው... ከዘርፉ ሥ/አስፈፃሚ እስከ ጽዳት ሰራተኛዋ ድረስ በርካታ ነጥቦች እንደመኖራቸው ያንተ ድርሻ አንዱ ኑጥብ ላይ ብቻ ማተኮር መሆኑ ተጠባቂ ነው... ይሁን እንጂ ማተኮርን ከማዋጣት ጋር መነጣጠል አትችልም... የ GO ዘርፍ ውጤታማ የሚሆነው በሁሉም ነጥቦች ትስስር ውስጥ ነው... በሌላ አነጋገር GO የሚባል አንድ ትርጉም ያለው ምስል የሚፈጠረው በነዚህ ነጠብጣቦች ውህድ ነው... ከነጠብጣቦቹ ውስጥ የሚጎድል ማንኛውም ነጥብ ስዕሉን ጎደሎ እንደሚያደርገው ሁሉ ከሌሎች ነጥቦች ጋር አልቀናጅ ያለ አንድ ነጥብ መኖርም ስዕሉን ያበላሸዋል... ስለዚህ - ጽዳቷ ለኦፕሬሽን ክፍሉ መነቃቃት፣ ኦፕሬሽኑ ለሜንቴናንስ ቲሙ ስራ መቃናት፣ ሜንቴናንሱ ለአጠቃላይ ሲስተሙ ብቃት፣ አስተዳደሩ ለመስተጋብሩ ምቹነት፣ ፋይናንሱ ለክንውኑ ቀጣይነት፣ ጥበቃው ለሰውና ንብረት ደህንነት፣ በየደረጃው ያሉ የስራ ኃላፊዎች ለጤናማ የኃይል ማመንጨት ስርዓት ብዙ ያዋጣሉ... በትኩረት መስካቸው - በኃላፊነት፣ በመዋጮ ቅንጅት - በባለቤትነት... ይህ የአንድ ማመንጫ ትስስር ግን GO የሚባለውን ምስል ሙሉ አያደርገውም... ሁሉም ማመንጫዎች ደግሞ መጣመር አለባቸው... ለዚህም እስከ ሥ/አስፈፃሚው የሚደርስ የነጥቦች ስብስብ ያስፈልገናል... ነገሩ በዚህ አያበቃም... ምክንያቱም ኃይል ማምረት ብቻውን ግብ አይደለም... መተላለፍ አለበት... ለዚህም ሲባል TSO የሚባል ዘርፍ አለን... ከ Janitor እስከ Executive ሌላ የነጥቦች ድምር - ከ Transmission እስከ Substation፣ ከሪጅን እስከ ዋ/መ/ቤት - ብዙ ነጠብጣብ... ይህም በቂ አይደለም... ኃይል ማስተላለፍ ብቻውን ግብ አይደለም - መቆጣጠር ደግሞ ያስፈልጋል... ለዚህም ብለን ግዙፉን የኃይል ትስስር (Grid System) የሚያቀናጅ Load Dispatch Center ፈጥረናል - እዚህ ደግሞ ሌላ ነጠብጣብ... ብዙ የዕውቀት ዘርፍ... ማምረትና ማስተላለፍን አመጣጣኝ ድልድይ... ☝️ ምስሉ ግን ገና አልሞላም... የማመንጨት ስርዓትን የሚወልደው የ Generation Construction እና የማስተላለፍ ሂደትን የሚፈጥረው Transmission Construction ሳይኖር ምስሉ እንደማይመጣ ሁሉ፣ ይህን የሚያቅደው Planning እና በንድፍ የሚያስቀምጠው Engineering ሳይኖር የምስሉ ሸራ እንደማይሞላው ሁሉ፣ የሰው ኃይሉ፣ ፋይናንሱ፣ ግዢውና ንብረቱ ሳይኖር የምስል ጥራቱ እንደማይታለመው ሁሉ - እነዚህን ሁሉ የሚያቀናጅ ስርዓት ከሌለም ነጥቦቹ በራሳቸው ትርጉም አይሰጡም... እርሱም EEP ነው... አሁንም ግን ነገሩ አያበቃም... የምናወራለትን ግዙፍ ምስል በምልዓት ማየት የሚያስችል ነጠብጣብ ገና ሸራው ላይ አልሰፈረም... ⬇️

🔤🔤🔤🔤🔤 - 🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤
🔤🔤🔤🔤🔤 - 🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤

📣 Reminder ➡️ Dear Work Unit Heads, Department Managers, and Division Leaders, 💠 As we are approaching the final stage of t
📣 Reminder ➡️ Dear Work Unit Heads, Department Managers, and Division Leaders, 💠 As we are approaching the final stage of the 2019 E.C. budget preparation period, we kindly remind all work units to give due attention to employee training and development budget allocation during your planning process. 💠 Training is not only an expense; it is an investment that strengthens operational performance, improves productivity, enhances safety, builds leadership capacity, and supports the successful implementation of organizational strategies. Well-trained employees contribute directly to service quality, efficiency, innovation, and institutional sustainability. 💠 Therefore, all work units are encouraged to allocate sufficient budget for: ✅ In-house training programs ✅ External trainings from recognized institutes ✅ Technical and professional skill development ✅ Leadership and competency enhancement programs ✅ Mandatory operational and safety trainings 💠 Proper planning today helps avoid future training budget shortages when urgent workplace skill gaps, operational changes, technology implementations, or capacity building needs arise. 💠 It also enables employees to participate in trainings delivered both at the workplace and at the Training Center without interruption. 💠 Let us strengthen our organization by planning ahead and investing in our people, because organizational transformation begins with capable and continuously developing employees. 🙏 Thank you for your cooperation and commitment toward building a strong learning culture within our institution. 🟣 EPA - Training Center We Strive to Create a Learning Organization!!

Digital mindset Round 5.xlsx0.42 KB

📣 Calling Announcement – Round 5 Digital Mindset, Digital Literacy & Digital Work Tools Training Dear Trainee. We are please
📣 Calling Announcement – Round 5 Digital Mindset, Digital Literacy & Digital Work Tools Training Dear Trainee. We are pleased to announce the commencement of the 5th Round of the Digital Mindset, Digital Literacy, and Digital Work Tools Training Program.   This initiative continues to strengthen our company’s digital transformation journey by building digitally aware, capable, and adaptable employees across all work units.   🕹 The list of selected trainees for Round 5 is attached in Excel format. Kindly check your names and training details carefully.   📆 Training sessions will begin as per the communicated schedule – Ginbot 10/2018 ⏳ All participants are requested to appear on time and attend the sessions properly.   This training is more than a classroom program — it is part of our transition toward a smarter, connected, and digitally empowered working culture.   💡 Learn. Adapt. Transform.   Thank you, and we wish all participants a productive and inspiring learning journey.   🔺🔺🔺 EPA – Training Center We Strive to Create a Learning Organization!!