fa
Feedback
Ethio Power Insight

Ethio Power Insight

رفتن به کانال در Telegram

Learn | Reflect | Share | Improve Sharing knowledge - Inspiring ideas - Building a Stronger Ethio Power. We strive to create a learning organization!!

نمایش بیشتر
2 375
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-397 روز
-5430 روز

در حال بارگیری داده...

ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
سپتامبر '26
سپتامبر '260
در 1 کانال‌ها
اوت '26
+57
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '26
+65
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '26
+67
در 1 کانال‌ها
Get PRO
مه '26
+109
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '26
+98
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '26
+43
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '26
+66
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '26
+41
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '25
+75
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '25
+83
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '25
+39
در 1 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '25
+63
در 1 کانال‌ها
Get PRO
اوت '25
+82
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '25
+21
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '25
+80
در 1 کانال‌ها
Get PRO
مه '25
+37
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '25
+55
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '25
+84
در 1 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '25
+31
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '25
+92
در 1 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '24
+110
در 1 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '24
+137
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '24
+203
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '24
+79
در 1 کانال‌ها
Get PRO
اوت '24
+81
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '24
+81
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '24
+94
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '24
+160
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '24
+82
در 1 کانال‌ها
Get PRO
مارس '24
+49
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '24
+94
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '24
+21
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '23
+26
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '23
+72
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '23
+61
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '23
+400
در 0 کانال‌ها
تاریخ
رشد مشترکین
اشارات
کانال‌ها
02 سپتامبر0
01 سپتامبر0
پست‌های کانال
🔔🔔🔔 በአዲስ አበባ ለምትገኙ የተቋማችን የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በሙሉ 📌 የደራሽ ምስረታ እውን ማድረጊያ ጉባኤ ጥሪ!! -- 🖥 ቀን ፡ ሐሙስ - 28/12/2018 ⏰ ሰዓት ፡ ከሰዓት 8፡
🔔🔔🔔 በአዲስ አበባ ለምትገኙ የተቋማችን የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በሙሉ 📌 የደራሽ ምስረታ እውን ማድረጊያ ጉባኤ ጥሪ!! -- 🖥 ቀን ፡ ሐሙስ - 28/12/2018 ⏰ ሰዓት ፡ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት 📍 ቦታ ፡ በተቋሙ ትልቁ አዳራሽ -- 💬 በዕለቱ በአገልግሎቱ ምስረታና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን ለምስረታ በተዘጋጀው ምክረ-ሃሳብ (Proposal) ላይ የተሳታፊዎችን ግብዓት የምንወስድበት የውይይት መርሃግብርም ተዘጋጅቷል፡፡ -- 🙏 በመሆኑም በዚሁ ዕለት በተቋማችን ትልቁ አዳራሽ ተገኝተው በደራሽ ምስረታ ጅማሬ ላይ የበኩልዎን አስተዋጽዎ እንዲያበረክቱ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡ -- የደራሽ ጊዜያዊ አደራጅ ኮሚቴ

2
. . . Quote of the day 💡 _____
. . . Quote of the day 💡 _____
696
3
🔖 . . . She doesn't climb to prove a point. She climbs because the job demands competence, and she has it in abundance. 💡 E
🔖 . . . She doesn't climb to prove a point. She climbs because the job demands competence, and she has it in abundance. 💡 Every cable she pulls, every connection she secures, every fault she diagnoses—it's not about gender. 💡 It's about skill, precision, and the quiet confidence that comes from knowing exactly what she's doing. 💡 The grid doesn't care who fixes it. It just works when she's done. And that's all the statement she needs. _ "Current doesn't ask for permission — it asks for capability. And she delivers both." _ 🔥 Yes - she can!! _
2 363
4
💡 ____ እግረመንገድ... ⚡️ ____ እነዚህን ሁለት Electrical terminologies በስራ ቦታችን ላይ እንደተመቸን ቀያይረን እንጠቀምባቸዋለን - Earthing እና Grounding...
💡 ____ እግረመንገድ... ⚡️ ____ እነዚህን ሁለት Electrical terminologies በስራ ቦታችን ላይ እንደተመቸን ቀያይረን እንጠቀምባቸዋለን - Earthing እና Grounding... ለመሆኑ ልዩነታቸው ምንድነው?... የቃል ብቻ ወይስ የአተገባበርም?... ልዩነቱን አስባችሁበት ለማታውቁ ይህች አጭር ቪዲዮ በቂ ግንዛቤ እንደምትፈጥር ተስፋ እናደርጋለን... ____
1 064
5
EPI_Newsletter_001.pdf
1 111
6
🔔 ማስታወሻ ------- ትናንት ያጋራነውን የ Iberdrola ታሪክ ያነበቡ የገጹ ተከታታዮች አቀራረቡን በተመለከተ ጥሩ ጥሩ ሃሳቦች አጋርተውናል… ገጹ ላይ የማይፈለጉ ማስታወቂያዎችን ያስተዋሉም
🔔 ማስታወሻ ------- ትናንት ያጋራነውን የ Iberdrola ታሪክ ያነበቡ የገጹ ተከታታዮች አቀራረቡን በተመለከተ ጥሩ ጥሩ ሃሳቦች አጋርተውናል… ገጹ ላይ የማይፈለጉ ማስታወቂያዎችን ያስተዋሉም እንድናስተካክል ነግረውናል... (በነገራችን ላይ ገጹ ከእኛ ፍላጎት ውጪ የሚያመጣውን ማስታወቂያ ለማስቀረት ያለው አማራጭ ሁለት ነው - ተፈላጊው Boost level ላይ መድረስ አልያም Private ማድረግ፤ Boost level ላይ ለመድረስ የአንባቢያኑን ተሳትፎ ይፈልጋል፣ Private ማድረግ ደግሞ Search ሲደረግ የመገኘት ዕድሉን ያጠባል - ለማንኛውም መፍትሔ እንፈልጋለን)   ሌሎች ወዳጆች ደግሞ EPI_Newsletter የት አለ ብለውናል… -------- ሁላችሁንም እናመሰግናለን!! 🙏 --------- እነሆ - EPI_Newsletter 001 ⬇️   --------- We Strive to Create a Learning Organization!!
1 101
7
⭐️ INSIDE THE WORLD'S POWERHOUSES 🗓️ EPISODE 01 __________ ⚡️⚡️ IBERDROLA ⚡️⚡️ __________ Iberdrola ዋና መሥሪያ ቤቱ በ Bilbao, Spa+2
⭐️ INSIDE THE WORLD'S POWERHOUSES 🗓️ EPISODE 01 __________   ⚡️⚡️ IBERDROLA ⚡️⚡️   __________   Iberdrola ዋና መሥሪያ ቤቱ በ Bilbao, Spain የሚገኝ ግዙፍ የኃይል አቅርቦት ድርጅት ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኤሌክትሪክ ኃይል በተለይም በ Renewable Energy ዘርፍ ከሚመሩ ታዋቂ ኩባንያዎች አንዱ ነው…     ኩባንያው የ125 ዓመታት ታሪክ ያለው ሲሆን፣ ከ25 ዓመታት በፊት Electrification፣ Renewable Energy እና Electricity Networks ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሚሄደውን አስፈላጊነት በማስላት የወሰደው ስትራቴጂያዊ እርምጃ ለገናናነቱ ትልቅ መሰረት እንደጣለ ይነገርለታል…     ዛሬ Iberdrola የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት፣ Networks፣ Renewable Energy፣ Storage እና የደንበኞች አገልግሎት ቢዝነሶችን በማቀናጀት በ14 አገራት ውስጥ ይንቀሳቀሳል…     ዋና ዋና ገበያዎቹ Spain፣ በ Scottish Power በኩል United Kingdom፣ በ Avangrid በኩል United States፣ በ Neoenergia በኩል Brazil፣ Mexico እና ሌሎች የ European ገበያዎች ናቸው።     🟢 Key Company Facts ✅ Headquarters: Bilbao, Spain   ✅ Ownership: Publicly listed private company   ✅ Core Focus: Electricity generation, Electricity networks, Renewable energy እና Electrification   ✅ Major Technologies: Wind, Solar, Hydro, Nuclear, Battery storage እና Pumped storage   ✅ Global Reach: በ14 አገራት ውስጥ ኤልክትሪክ አቅርቦት ስራ ይሰራል   ✅ Workforce: ከ 45,400 በላይ ሠራተኞች አሉት      🍀 Iberdrola in Numbers (ተቋሙን በውስን የቁጥሮች መስኮት እንመልከተው) ✅ 58,343 MW በ2025 ማጠቃለያ የኃይል ማመንጨት አቅሙ (Installed generation capacity) ደርሷል፤   ✅ 46,000+ MW የ Renewable አቅም አለው፤   ✅ 1.4 million km የ Electricity networks አለው፤   ✅ 45,400 ሠራተኞች ያስተዳድራል፤   ✅ €14.46 billion በ2025 ብቻ 14.46 ቢሊየን ዩሮ ለስራው ማስፋፊያ ኢንቨስት አድርጓል…   ሌላው አስደናቂ ቁጥር ደግሞ 85% ነው፤ ይህም በ2025 ማጠቃለያ ላይ ከካርቦን ልቀት ነፃ (Emission free) የነበረው የ Iberdrola የኢነርጂ አቅም ድርሻን ያሳያል…   ስለ ካምፓኒው ከዚህ በላይ በዝርዝር የማወቅ ፍላጎት ካላችሁ ከስር ያስቀመጥነውን EPI Newsletter - 001 እንድታነቡ እንጋብዛለን…   ❕ ከዝግጅቱ ጋር በተያያዘ ያላችሁን ማንኛውንም አስተያየት በገጹ DM (Direct message) በኩል ላኩልን… በሚቀጥለው Episode 2 የሌላ ግዙፍ ካምፓኒ ፕሮፋይል በ EPI Newsletter – 002 አማካይነት እናቀርብላችኋለን!!   ----   We Strive to Create a Learning Organization!!
1 164
8
🔵 "An organization's ability to learn, and translate that learning into action rapidly, is the ultimate competitive advantag
🔵 "An organization's ability to learn, and translate that learning into action rapidly, is the ultimate competitive advantage." — Jack Welch, Former Chairman & CEO of General Electric   የገፃችንን ትኩረት ሰፋ ለማድረግ ባለን ፍላጎት የስያሜ፣ ዓርማና ዓላማ ማሻሻያ አድርገናል…   በዚህም መሰረት ስለ ዓለማችን የኃይል ተቋማት በተከታታይ የምናወራበትን ማስታወሻ ዛሬ እንጀምራለን… በምድሪቱ የኢነርጂ አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ጉልህ ሚና ያላቸውን ታላላቅ ተቋማትንም እንተዋወቃለን… በዚህ ሂደት መነሻ የሚሆኑ አጫጭር ታሪኮችን በ Fact file መልክ በጥቅል እናጋራችሁና ዝርዝር መረጃ ስትፈልጉ የምታነቡትን ማስታወሻ ደግሞ በ PDF ፎርማት እናስቀምጥላችኋለን…   ያለነው በኢነርጂ ተቋም ውስጥ እንደመሆኑ የሌሎች ዓለም አቀፍ ታላላቅ ተቋማትን ታሪክ ማወቅ ለስራችን መዘመንና ለተቋማችን ለውጥ ወሳኝ ነው ብለን እናምናለን…   የአሜሪካውን Walmart የመሰረተው Sam Walton አንድ ወቅት፡   "Most everything I’ve done, I’ve copied from somebody else."     ሲል ተናግሮ ነበር… አባባሉ የግለሰቡን ትህትና ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ለመማር ያለውንም ትጋት የሚያመለክት እንደመሆኑ ከተቋማዊ መማማር ጋር ተያይዞ በየጊዜው ይነሳል…   "Foolish is the man who learns from his own mistakes. Wise is the man who learns from the mistakes of others." — Otto von Bismarck, Former Chancellor of Germany   ይህም ሆኖ መማር ብቻውን ትርጉም አይኖረውም፤ የተማሩትን ለመተግበር መሞከር የበለጠ ጠቃሚ ነው… በዚህ ፈጣንና ውድድሩ ከባድ በሆነበት ዓለም አዳዲስ ነገሮችን ፈጥኖ መማርና ያወቁትንም እንደየ አውዱ መተግበር ጠንካራ ተቋም ለመፍጠር መሰረት ነው…   "The only sustainable competitive advantage is an organization's ability to learn faster than the competition." — Peter Senge, Author of “The Fifth Discipline”     🎓 አንብቡ፣ ሃሳብ ስጡ፣ ጠቃሚ ማስታወሻዎችን ተለዋወጡ!!     📌 We look outward to understand how others operate, inward to understand ourselves, and forward to identify capabilities that may matter tomorrow.   ----   We Strive to Create a Learning Organization!!
1 099
9
. . . መስታወት የኃይል ምንጭ እንደሚሆን አስበው ያውቁ ኖሯል?... በዚህ ቪዲዮ - ሃገረ-ቻይና የመስታወቶችን ስብስብ ተጠቅማ እንዴት Energy እንደምታመርት ያያሉ... ነገርየው እንኳን የልጅነ+1
. . . መስታወት የኃይል ምንጭ እንደሚሆን አስበው ያውቁ ኖሯል?... በዚህ ቪዲዮ - ሃገረ-ቻይና የመስታወቶችን ስብስብ ተጠቅማ እንዴት Energy እንደምታመርት ያያሉ... ነገርየው እንኳን የልጅነት ጨዋታችን አካል ነበር... ዛሬ የ Energy source መሆኑን ስንረዳ ቢገርመንም... _ This is a concentrated solar power (CSP) station in northwest China's Gansu Province, and it works completely differently from the panels on your roof. Instead of turning sunlight straight into electricity, it turns sunlight into heat — over 560°C, concentrated onto a receiver tower 260 meters tall. That heat melts salt, and the molten salt stores it like a giant thermal battery. Why does that matter?... Because solar's biggest weakness has always been timing. The sun goes down right when electricity demand goes up.  CSP solves that and keeps generating power long after sunset.
1 777
10
⚡️⚡️⚡️ CNN Africa's largest hydroelectric project is reshaping Ethiopia's energy future. CNN's Victoria Rubadiri visits the G
⚡️⚡️⚡️ CNN Africa's largest hydroelectric project is reshaping Ethiopia's energy future. CNN's Victoria Rubadiri visits the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) to see how the megaproject is generating power and transforming the region's energy landscape.
1 813
11
. . . Most organizations don’t lose their best people because of salary. They lose them because of decisions. When the wrong
. . . Most organizations don’t lose their best people because of salary. They lose them because of decisions. When the wrong people get promoted, three things happen: ☀️ Trust erodes ☀️ Motivation drops ☀️ High performers disengage And eventually… they leave. Promotion should never be a reward for loyalty, tenure, or politics. It should be based on competence, behavior, and leadership potential. One of the biggest leadership mistakes I see in organizations is promoting the best technical performer into a management role without asking a simple question: ❓ Can this person lead people — or only tasks?... Because management is not about being the best individual contributor. It’s about: ⭐️ Developing others ⭐️ Creating clarity ⭐️ Making decisions ⭐️ Taking responsibility ⭐️ Building trust ⭐️ Setting standards Poor promotion decisions don’t just create weak managers. They create organizational damage. People don’t leave companies. They leave leadership. Great leaders understand something critical: ✅ Promotion is culture. ✅ Promotion is strategy. ✅ Promotion is retention. 🗓️🗓️🗓️ Choose wisely. ✅✅✅ _ _ _ Robertson Hunter Stewart
2 023
12
🍀 ክፍል 7 (የመጨረሻ ክፍል) የነገው የኃይል ሥርዓት… . . ለረጅም ጊዜ የኃይል ሥርዓቶች ሲቀረጹ የነበረው በዋናነት በታሪካዊ ተሞክሮዎች ዙሪያ ነበር… ያለፈው ዓመት የዝናብ መጠን፣ ያለፉት ጊዜ
🍀 ክፍል 7 (የመጨረሻ ክፍል) የነገው የኃይል ሥርዓት… . . ለረጅም ጊዜ የኃይል ሥርዓቶች ሲቀረጹ የነበረው በዋናነት በታሪካዊ ተሞክሮዎች ዙሪያ ነበር… ያለፈው ዓመት የዝናብ መጠን፣ ያለፉት ጊዜያት የኤሌክትሪክ ፍላጎት፣ ያለፉት አምስት ዓመታት የማመንጨት መጠን ወዘተ…   ነገር ግን ታሪክ ሁልጊዜ ራሱን አይደግምም… የአየር ንብረት መለዋወጥ (Climate variability)፣ ተቀያያሪ ፍላጎት፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና በፍጥነት የሚለዋወጠው የኃይል ገጽታ ተጨማሪ ነገር ይፈልጋሉ… እሱም አስቀድሞ የመተንበይና የመረዳት አቅም ነው… 🍎 ከግሪድ (Grid) ወደ አስተዋይ (Intelligent) ሥርዓት የተለመደው የኃይል ሥርዓት በዋናነት ኤሌክትሪክን ከማመንጫዎች ወደ ማስተላለፊያዎች ያጓጉዛል… እየመጣ ያለው አዲሱ የኃይል ሥርዓት ግን ከዚያ ይበልጥ ብዙ ነገር ያደርጋል… It senses - It communicates - It analyzes - It predicts - It responds.   የስማርት ግሪድ (Smart grid) ፍልስፍና መሠረት ይህ ነው!!...   ሴንሰሮች (Sensors) መረጃ ይሰጣሉ፣ የመገናኛ መረቦች ሥርዓቱን ያገናኛሉ፣ ዲጂታል መሰረተ ልማቶች መረጃዎችን በአንድ ላይ ይሰበስባሉ፣ ትንተናዎች (Analytics) ሁነቶችን እንድናውቅ ይረዱናል፣ አውቶሜሽን (Automation) ፈጣን ውሳኔዎችን ይደግፋል፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence / AI) ሰዎች ሊስቷቸው የሚችሏቸውን ትስስሮች እና ስጋቶች ለመለየት ይረዳል… The result is not simply a more digital grid. It is a more aware grid.   💡 የኃይል እይታ (Power Insight) የነገው የኃይል ሥርዓት የሚገለጸው በሚኖረን የማመንጨት መጠን ብቻ ሳይሆን፣ በተፈጥሮ፣ በቴክኖሎጂ እና በሰዎች መካከል ያለውን ትስስር ምን ያህል በአስተዋይነት፣ በዘላቂነት እና በህብረት ማስተዳደር እንችላለን በሚለው ነው…   🟢 ትልቁ ምስል የወደፊቱ ጊዜ ዝም ብሎ የሚከሰት አድርገን እናስባለን… ነገሩ ግን እንደዚያ አይደለም… ዛሬ በምናደርጋቸው ነገሮችና በምናሳልፋቸው ውሳኔዎች የወደፊቱን እንፈጥረዋለን…   💸 ጉዞው ይቀጥላል... የወደፊቱ ጊዜ ድርቅንም፣ የዝናብ ወቅትንም ይዞ ይመጣል… አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና አዳዲስ ፈተናዎችንም ያመጣል… ያልተጠበቁ ሁከቶችን እና አዳዲስ ዕድሎችንም ይፈጥራል… የሚመጣውን ሁሉ መቆጣጠር አንችልም… ነገር ግን የተሻለ ዝግጅት ማድረግ እንችላለን… መማር እንችላለን፣ መላመድ እንችላለን፣ የኃይል ምንጮቻችንን ማበዛት እንችላለን፣ በህብረት መስራት እንችላለን፣ ከግል ኃላፊነታችን ባሻገር በማሰብ ጠቅላላውን ሥርዓት ማየት እንችላለን… ምናልባትም የመቋቋም አቅም (Resilience) ማለት ይሄው ነው - ነገ ምን እንደሚያመጣ በጥቅሉ ባናውቅም፣ የሚመጣውን ለመጋፈጥ ብቁ ሆነን መገኘት!... ☎️ መውጫ ሃሳብ…   የኃይል ዘርፍ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በምናመርተው የኤሌክትሪክ መጠን ብቻ ሳይሆን፣ ያንን ኤሌክትሪክ በምን ያህል ብልህነት እናመርታለን፣ እናከማቻለን፣ እናጓጉዛለን እንዲሁም ጥቅም ላይ እናውላለን በሚለው ጭምር ነው…     🎯 ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence)፡ በሰለጠነው ዓለም ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የኃይል ሥርዓቶች አስቀድመው እንዲተነብዩ፣ አሠራራቸውን እንዲያሻሽሉ እና ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል… የታዳሽ ኃይል ምርትንና የኤሌክትሪክ ፍላጎትን አስቀድሞ ከመተንበይ ጀምሮ፣ የመሳሪያዎችን ብልሽት እስከመለየትና የኃይል ማሰራጫ መረብ (Grid) ሥራዎችን እስከመደገፍ ድረስ ያግዛሉ…     🎯 የኃይል ማከማቻ (Next-Gen Battery Energy Storage Systems)፡ የወደፊቱ የኃይል ማሰራጫ መረብ ኃይል ማጓጓዝ ብቻ ሳይሆን ማከማቸትም ያስፈልገዋል… ዘመናዊ ባትሪዎችና አዳዲስ የኃይል ማከማቻ ቴክኖሎጂዎች ኤሌክትሪክን በጊዜ ሂደት በማሸጋገር፣ ተለዋዋጭ የታዳሽ ኃይል ምንጮችን ለማመጣጠን እንዲሁም ሥርዓቱን የበለጠ ተለዋዋጭና ጽኑ ለማድረግ ያስችላሉ…     🎯 የኃይል መረብ አቅም ማሳደጊያ ቴክኖሎጂዎች (Grid-Enhancing Technologies)፡ የወደፊቱ ጊዜ ተጨማሪ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን በመገንባት ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም… የላቀ የኃይል ፍሰት ቁጥጥር፣ የኃይል መረብ ክትትል እና ሌሎች ዲጂታል መፍትሔዎች ያሉዋቸው ቴክኖሎጂዎች መጠቀምም እንጂ… እነዚህን ከተጠቀምን ከኃይል ማሰራጫ መረባችን የበለጠ አቅም እንድናወጣ፣ አስተማማኝነትን እንድናሻሽል እንዲሁም ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች በበለጠ ብልህነት ምላሽ እንድንሰጥ ይረዱናል…     🎯 የሚማማር ተቋም (The Learning Organization)፡ ቴክኖሎጂ ብቻውን የኃይል ዘርፉን ሊለውጠው አይችልም… ለውጡን የሚያመጡት ሰዎች ናቸው… የወደፊቱ ጊዜ ሁልጊዜ የሚማሩ፣ እውቀትን የሚያካፍሉ፣ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች ጋር አብረው የሚሰሩ፣ መረጃዎችን በሚገባ የሚያቀናብሩ፣ ፈጠራን የሚቀበሉ እና ከለውጥ ጋር የሚላመዱ ባለሙያዎችን ይፈልጋል… ተማሪ ተቋም ሰዎችን ለዛሬው ቴክኖሎጂ ብቻ አያዘጋጅም - ይልቁንም የነገውን ቴክኖሎጂ ለመማር ዝግጁ ያደርጋቸዋል…   ------ The energy transition is therefore not simply a transition from hydro to solar or from conventional grids to smart grids. It is a transition: from reactive to predictive, from isolated to interconnected, from fixed to flexible, from consuming knowledge to continuously creating it. The power system of tomorrow will be intelligent because of technology, resilient because of diversity, and sustainable because of people who never stop learning.   -----   በያለንበት እንበርታ!!   ------   We Strive to Create a Learning Organization!!
1 704
13
✅ ክፍል 6 ከግድብ ባሻገር አንድ ዓይነት የኃይል ምንጭ ግዙፍ የኢነርጂ ሥርዓት ሊፈጥር ይችላል፤ ስብጥሩ የሰፋ የኃይል ምንጭ ግን ስርዓቱን ይጠብቃል… ቀጣይነቱንም አስተማማኝ ያደርጋል… . . ሃገራ
✅ ክፍል 6 ከግድብ ባሻገር   አንድ ዓይነት የኃይል ምንጭ ግዙፍ የኢነርጂ ሥርዓት ሊፈጥር ይችላል፤ ስብጥሩ የሰፋ የኃይል ምንጭ ግን ስርዓቱን ይጠብቃል… ቀጣይነቱንም አስተማማኝ ያደርጋል…   . .   ሃገራችን ለዘመናት በታላቅ የሃይድሮ ፓወር (Hydropower) እምቅ ሃብት ታድላለች… ወንዞቻችን፣ ተራሮቻችን እና ግድቦቻችን ለሀገራችን ከፍ ያለ የኃይል ብልጫ ሰጥተዋታል… በዚህም ምክንያት ሃይድሮ ፓወር የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሥርዓት ዋና መሠረት ሆኖ ይቀጥላል…   ነገር ግን ኤል ኒኖ (El Niño) እና እየጨመረ የመጣው የአየር ንብረት መለዋወጥ (Climate variability) አንድን ትልቅ እውነት ያሳስበናል…   Even our greatest strength can become vulnerability when we depend on it too heavily.   አብዝተን ጥገኛ ስንሆንበት ትልቁ ጥንካሬያችን ራሱ ትልቁ ድክመታችን ሊሆን ይችላል…     ዝናብ ሲትረፈረፍ፣ ሃይድሮ ፓወር ግዙፍ የሆነ ኃይል ይሰጠናል… የዝናብ ሁኔታ እርግጠኛነቱ ሲጎድል ግን፣ ያው ጥገኝነት በሥርዓቱ ላይ ጫና ይፈጥራል… ስለዚህ ጥያቄው “ከሃይድሮ ፓወር መራቅ አለብን ወይ?” የሚለው አይደለም… የተሻለው ጥያቄ፦     “ከእሱ ጎን ለጎን ሌላ ምን መገንባት አለብን?” የሚለው ነው… ⭐️ የኃይል ስብጥር (Diversity) አቅም   አንድ ዓይነት ሰብል ብቻ የሚያመርትን ገበሬ አስቡ… ወቅቱ ጥሩ ሲሆን፣ ሁሉም ነገር ሰላም ነው… ነገርግን ድርቅ ያንን ሰብል ካጠፋው፣ ሙሉ ምርቱ ይወድማል… የተለያዩ ሰብሎችን የሚያመርት ገበሬ ከሆነ ግን ይህን ችግር መቋቋም ይችላል… ምክንያቱም ከሰብሎቹ ውስጥ ጥቂቶቹ የበዛ ውኃ፣ የተወሰኑት ደግሞ ያነሰ ውኃ ይፈልጋሉ… ይህም በሚፈራረቁ ወቅቶች መሃል ሳይቸገር እንዲያልፍ ያደርገዋል… ሁለተኛው ገበሬ በምርቶቹ ስብጥር አማካኝነት የመቋቋም አቅም (Resilience) ፈጥሯል… የኃይል ሥርዓታችንም ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ይችላል… ሶላር (Solar - የፀሐይ ኃይል)፣ ዊንድ (Wind - የነፋስ ኃይል)፣ ጂኦተርማል (Geothermal - የመሬት ውስጥ እምቅ ኃይል)፣ ሃይድሮ ፓወር (Hydropower - የውኃ ኃይል)፣ የኃይል ማከማቻ (Energy storage) እና የቀጠናው የኃይል ማስተላለፊያ ትስስር (Regional interconnection) በሰፊው ሊሰሩ የሚገባቸው የኃይል አማራጮች ናቸው… እነዚህ የኃይል ምንጮች እርስ በእርስ አይወዳደሩም - ይደጋገፋሉ እንጂ… 📌 የተለያዩ ምንጮች - አንድ ሥርዓት ⭐️ ሶላር (Solar)፦ በቀን በብርሃን ሰዓት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከት ይችላል፤   ⭐️ ዊንድ (Wind)፦ የነፋስ ሁኔታዎች አመች በሚሆኑበት ጊዜ ኃይል ያመነጫል፤   ⭐️ ጂኦተርማል (Geothermal)፦ አንጻራዊ በሆነ መልኩ ወጥ የኃይል ምንጭ ሊሆን ይችላል፤   ⭐️ ሃይድሮ ፓወር (Hydropower)፦ ተለዋዋጭ አቅም እና የኃይል ማከማቻ ይሰጠናል፤   ⭐️ የኃይል ማከማቻ (Energy storage)፦ ኤሌክትሪክን ከቀነሰበት ሰዓት ወደ ተፈለገበት የጊዜ ሰሌዳ ለማሸጋገር ይረዳል፤   ⭐️ የማስተላለፊያ ትስስሮች (Transmission interconnections)፦ የኤሌክትሪክ ኃይል በሪጅኖችና እና በሀገራት መካከል የፍላጎትና የምርት መጠንን መሰረት አድርገው እንዲንቀሳቀስ ይፈቅዳሉ…   ጥንካሬው የሚመጣው ከአንዱ የኃይል ምንጭ አይደለም… የኃይል ምንጮቹ አብረው ሲሠሩ ከሚፈጠረው ቅንጅት እንጂ… የጠንካራ የኃይል ሥርዓት (Resilient energy system) ሕያው ምስጢር ይህ ነው…   ✅ ተቋማችን (EEP) ምን ማሰብ አለበት?... የወደፊቱ የኃይል ሥርዓት ጥያቄ፦ “ምን ያህል ኤሌክትሪክ ማመንጨት እንችላለን?” የሚለው ብቻ ሳይሆን፦ “የማመንጨት አቅማችን ወቅቶችን የመቋቋም ብቃት (Resilience) ምን ያህል ጠንካራ ነው?” የሚለው ጭምር ነው…     ይህ ደግሞ ስለ ዕቅድ ዝግጅት የተለየ እይታ እንድንይዝ ያስገድደናል… በተለይም፦ ☀️ የኃይል ምንጮች ስብጥር (Resource diversity)   ☀️ የአየር ንብረት መለዋወጥ (Climate uncertainty)   ☀️ የኃይል ማከማቻ ግንባታ (Energy storage)   ☀️ ተለዋዋጭ የማመንጨት አቅም (Flexible generation)   ☀️ የማስተላለፊያ አቅም (Transmission capacity)   ☀️ የፍላጎት አስተዳደር (Demand management)   ☀️ ዲጂታል ክትትል (Digital monitoring)   ☀️ ቀጠናዊ የኃይል ትስስር (Regional power exchange) ላይ በብርቱ መስራት ይጠይቃል…     💡 የኃይል እይታ (Power Insight) እጅግ ጠንካራው የኃይል ሥርዓት በነጠላ የኃይል ምንጭ ላይ የተመሰረተው ግዙፍ የማመንጨት አቅም አይደለም… ይልቁንም እርግጠኛ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ የተለያዩ የኃይል ምንጮቹ እርስ በእርሳቸው መደጋገፍ የሚችሉበት ሥርዓት ማለት እንጂ…   💧 ትልቁ ምስል   ኤል ኒኖ ከክላይሜት ባለፈ ትምህርት እየሰጠን ሊሆን ይችላል… መትረፍረፍን ከደህንነት/ዋስትና ጋር እንዳናቀላቅል እያነቃን ይሆናል… ታላቅ ሀብት ማግኘት ቡራኬ ነው… በእሱ ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ መሆን ግን ተጋላጭነት ሊሆን ይችላል… እውነተኛ የመቋቋም አቅም የሚመጣው እስካሁን ያገለገለንን ሀብት እያከበርን፣ ለሚቀጥለው ሁኔታ ደግሞ ራሳችንን ስናዘጋጅ ነው…       ግድቡን መተው አያስፈልገንም፤ ከግድቡ ባሻገር ማሰብ ግን ግድ ነው!!   ---- የመጨረሻው ክፍል   “የነገው የኃይል ሥርዓት”   What happens when electricity becomes intelligent, the grid begins to think, and people become the most important part of the system?   -----   We Strive to Create a Learning Organization!!
1 474
14
🟢 ክፍል 5 እያንዳንዱ ኪሎዋት ልዩነት ያመጣል (ኤሌክትሪክን መቆጠብ በእርግጥ ውኃን ለማዳን ይረዳል?...) . . . አብዛኛውን ጊዜ ስለ ኤሌክትሪክ ስናስብ፣ እንደምንጠቀመው ፍጆታ እንቆጥረዋለን
🟢 ክፍል 5 እያንዳንዱ ኪሎዋት ልዩነት ያመጣል (ኤሌክትሪክን መቆጠብ በእርግጥ ውኃን ለማዳን ይረዳል?...)   . . .   አብዛኛውን ጊዜ ስለ ኤሌክትሪክ ስናስብ፣ እንደምንጠቀመው ፍጆታ እንቆጥረዋለን እንጂ እሱን ለማምረት ሲባል ምን እንደሚፈጅ አስበን አናውቅም…     ሃይድሮ ፓወር (Hydropower) ማዕከላዊ Source በሆነበት የኃይል ሥርዓት ውስጥ፣ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ሲባል በተርባይኖች በኩል የሚፈሰው ውኃ ለፍጆታ የምንጠቀመውን ኃይል ለማምረት የሚጠቅም ነዳጅ ነው…     ስለዚህም… አላስፈላጊ የኤሌክትሪክ ፍጆታን ስንቀንስ፣ በማመንጨት ሂደት ላይ የሚፈጠረውን አላስፈላጊ ጫና እንቀንሳለን… የሃይድሮ ፓወር ኃይል ተጨማሪ የኃይል ምንጭ (Marginal source) በሚሆንበት ቦታ ደግሞ ለማመንጨት ይፈስ የነበረውን ውኃ መቆጠብ እንችላለን…     ይህም የኃይል ተብቃቆትን (Energy efficiency) ገንዘብ ከመቆጠብ ያለፈ ትርጉም እንዲኖረው ያደርገዋል… የሥራ ቦታዎን ዞር ብለው ይመልከቱ… 🏪 ሌሊቱን ሙሉ ክፍት ሆኖ የሚያድር ኮምፒውተር... 🏪 ባዶ ክፍልን የሚያበሩ መብራቶች... 🏪 ያለ አንዳች አስፈላጊነት የሚሠራ ኤር ኮንዲሽነር (Air conditioner)... 🏪 አስፈላጊ ባልሆኑበት ሰዓት ጭምር ግድግዳ ላይ ተሰክተው የሚተው መሣሪያዎች... እያንዳንዱ ለየብቻው ሲታይ ኢምንት ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን እያንዳንዱ አላስፈላጊ ድርጊት በሺዎች በሚቆጠሩ ሠራተኞች፣ ቢሮዎች፣ ተቋማት እና የሥራ ቀናት ሲባዛ ትንሹ ነገር ግዙፍ ይሆናል…     ⭐️ እኛ ምን ማድረግ እንችላለን?...   💀. የማያስፈልጉ ነገሮችን ማጥፋት ከቢሮ፣ ከስብሰባ አዳራሽ፣ ከላቦራቶሪ፣ ከወርክሾፕ ወይም ከክፍል ከመውጣታችን በፊት፦ መብራቶችን መዝጋት፣ ኮምፒውተሮችን ማጥፋት ወይም ወደ Sleep mode መቀየር፣ አላስፈላጊ መሣሪያዎችን ማጥፋት…     ምክንያቱም አንዲት ቀላል ልማድ ወደ ተቋማዊ ባህል ልታድግ ትችላለች… 💀. የከፍተኛ ፍላጎት ሰዓት ጫናን (Peak Demand) መቀነስ የኤሌክትሪክ ፍላጎት ቀኑን ሙሉ እኩል አይደለም… ብዙ ደንበኞች በተመሳሳይ ጊዜ ኤሌክትሪክ ሲጠቀሙ፣ በሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጠራል… ስለሆነም የጫናውን ሰዓት መለየትና ደንበኞች በተለይም ትላልቅ ተቋማት ከፍተኛ ኤሌክትሪክ የሚወስዱ መሣሪያዎቻቸውን በአንድ ጊዜ ከመጠቀም እንዲቆጠቡ በማድረግ ጫናውን መቀነስ ይቻላል… 💀. የማቀዝቀዣዎችን አጠቃቀም ማሻሻል ኤየር ኮንዲሽነር ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ሊወስድ ይችላል… ይሁንና በሮችና መስኮቶችን በመጠቀም ጤናማ የአየር ዝውውር ለመፍጠር መሞከር ሁኔታውን ያሻሽለዋል… ከዚሁ ጋር የተበላሹ መሣሪያዎችን በወቅቱ መጠገን እና ተስማሚ የሙቀት መጠኖችን መጠቀም አላስፈላጊ ፍጆታን ይቀንሳል… 💀. የመሣሪያዎችን ቅልጥፍና ማሻሻል በጥሩ ሁኔታ ያልተያዙ መሣሪያዎች ኃይል ያባክናሉ… ቀልጣፋ (efficient) የሆኑ ሞተሮች፣ መብራቶች፣ ትራንስፎርመሮች፣ ፓምፖች፣ ኮምፕረሰሮች እና ሌሎች የኤሌክትሪክ መሣሪያዎች ግን ፍጆታቸው አነስተኛ ነው… ስለሆነም efficient ስለሆኑ ቁሶች ደንበኞች ግንዛቤ እንዲይዙ መስራት አስፈላጊ ነው…     ምክንያቱም…   Energy efficiency is often the cheapest "generation" we can create. 🔔 መረሳት የሌለበት ነገር…   ኃይልን መቆጠብ ሰዎች ለአንድ ሳምንት ብቻ የሚያስታውሱት የዘመቻ ተግባር መሆን የለበትም… የሁልጊዜ ልማድ እንጂ…     💡 የኃይል እይታ (Power Insight) ዛሬ የምንቆጥበው ኤሌክትሪክ፣ የነገውን ኤሌክትሪክ በሚያመነጨው ውኃ ላይ የሚፈጠረውን ጫና ይቀንሳል…   📌 የእርስዎ ሚና ለኃይል ዋስትና (Energy security) አስተዋፅኦ ለማድረግ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ መምራት አይጠበቅብዎትም… ከአቅራቢያዎ ተነስተው ልዩነት መፍጠር ይችላሉ… ከቢሮ፣ ከወርክሾፕ፣ ከክፍል፣ ከቤትዎ…     አንድ ማብሪያ/ማጥፊያ (Switch)፣ አንድ ኮምፒውተር፣ አንድ አምፑል፣ አንድ ኃላፊነት የተሞላበት ውሳኔ - ልዩነት ያመጣል… በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች የሚያደርጓቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ኃላፊነት የተሞሉ ውሳኔዎች ተደምረው፣ ትልቅ ብሔራዊ አስተዋፅኦ ሊሆኑ ይችላሉ… 🫥 ትልቁ ምስል አንዲት የውኃ ጠብታ ኢምንት ትመስላለች… አንዲት የኪሎዋት ሰዓት (kWh) ኤሌክትሪክም እንዲሁ… ነገር ግን ወንዝ ማለት አብረው የሚንቀሳቀሱ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጠብታዎች ስብስብ እንጂ ሌላ አይደለም…   የኤሌክትሪክ ሥርዓትም እርስ በእርሳቸው የተሳሰሩ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የግለሰብ እርምጃዎች ውጤት ነው…   ቀጣዩ ክፍል “ከግድብ ባሻገር”   “ምን ያህል ውኃ አለን?” ብለን መጠየቅ አቁመን፣ “ምን ያህል የተለያዩ የኃይል ምንጮችን መገንባት እንችላለን?” ብለን መጠየቅ ስንጀምር ምን ይፈጠራል?...     ከዝናብ እስከ ብርሃን ያለው ጉዞ ይቀጥላል...     ----   We Strive to Create a Learning Organization!!
1 576
15
🗓️ ክፍል 4 ባትሪው እየደከመ ሲመጣ... (ዝናብ ከሚያስፈልገን በታች ቢሰጠን ምን ይፈጠራል?...) (ሰሞናዊው የኤልኒኖ ስጋት የቀሰቀሰው፣ ሳይንስን በጨዋታ ያለዘብንበት የቤታችን ወግ እንደቀጠለ
🗓️ ክፍል 4 ባትሪው እየደከመ ሲመጣ...   (ዝናብ ከሚያስፈልገን በታች ቢሰጠን ምን ይፈጠራል?...)     (ሰሞናዊው የኤልኒኖ ስጋት የቀሰቀሰው፣ ሳይንስን በጨዋታ ያለዘብንበት የቤታችን ወግ እንደቀጠለ ነው…)     ደህና…     አንድ ግድብ ግዙፍ የሆነ የኃይል መጠንን ማከማቸት ይችላል… ነገር ግን ውኃን መፍጠር አይችልም… የዝናብ መጠን ለረጅም ጊዜ ከመደበኛው በታች ሲቀንስ፣ በተፈጥሮው የግድቡን የውኃ ክምችት መልሶ መሙላት (Natural recharge) ይቀንሳል…     ያኔ ሰንሰለቱ ይጀመራል፦ ዝናብ ማጠር ⬇️ ወደ ወንዞች የሚገባ ውኃ መቀነስ ⬇️ የግድብ ውኃ መጠን መውረድ ⬇️ የውኃ ግፊት (Hydraulic head) ማነስ ⬇️ ኃይል የማመንጨት አቅም መዳከም ⬇️ በኃይል ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ጫና መፈጠር     የአየር ንብረት መለዋወጥ (Climate variability) የኤሌክትሪክ አቅርቦት ደህንነት ጉዳይ የሚሆነው እዚህ ላይ ነው… ስሱ ሚዛን ውኃ ሲያንስ፣ የተቋማችን (EEP) አንገብጋቢ እና ስሱ ጥያቄ ይገጥመዋል፦   💠 የነገውን የማመንጨት አቅም ሳይጎዳ የዛሬውን የኤሌክትሪክ ፍላጎት እንዴት እናሟላ?... 💠   በከፍተኛ ደረጃ (Aggressively) ካመነጨን፣ የተከማቸው ውኃ በፍጥነት ሊያልቅ ይችላል… በጣም ከቆጠብን ደግሞ፣ ሥርዓቱ የዛሬን ፍላጎት ለማሟላት ይቸገራል… ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚገኘው የግድብ መጠንን፣ የወንዝ ፍሰትን፣ የፍላጎት ትንበያን፣ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ሁኔታ፣ የጥገና ፕሮግራሞችን እና አጠቃላይ የኃይል ማመንጫ ድብልቅን በጥንቃቄ በማቀናጀት ነው…   ለዚህ ነው እያንዳንዱ ሜጋዋት እና እያንዳንዱ ኩቢክ ሜትር ውኃ ትልቅ ዋጋ ያለው። ❕ አሁን ምን ማድረግ እንችላለን? የአየር ንብረት ክስተትን የኤሌክትሪክ ተቋም በማቋቋም ማስቆም አይቻልም… ነገር ግን የሚፈጥረውን ተጽዕኖ መቀነስ ይቻላል… ⭐️ ስትራቴጂካዊ የውኃ አጠቃቀም፦ የግድብ የውኃ መልቀቅን እንደ ወንዝ ፍሰት ትንበያ፣ እንደ ክምችት ሁኔታ እና እንደ ሥርዓቱ ፍላጎት መሠረት በማድረግ ማመቻቸት፤   ⭐️ የኃይል ብክነትን መቀነስ፦ እያንዳንዱ አላስፈላጊ የኪሎዋት ሰዓት (kWh) ማለት፣ አላስፈላጊ የኃይል ማመንጨት ማለት ነው… በውኃ ኃይል ላይ በተመሠረተ ሥርዓት ውስጥ፣ ይህ ማለት አላስፈላጊ የውኃ ፍጆታ ማለት ነው… ለምሳሌ፦ በቢሮዎች፣ በኢንዱስትሪዎች እና በመኖሪያ ቤቶች ጥቅም ላይ የማይውሉ መብራቶችን እና ማሽኖችን ማጥፋት የውኃ ብክነትን ለመቀነስ የሚደረግ ቀጥተኛ አስተዋፅኦ ነው…   ⭐️ ያለውን የኃይል ምንጭ መጠቀም፦ ሁኔታዎች ሲፈቅዱ በነፋስ፣ በፀሐይ፣ በጂኦተርማል እና በሌሎች አማራጭ የኃይል ምንጮች መገልገል፣ በውኃ ኃይል ጣቢያዎች ላይ ያለውን ጫና ይቀንሳል…   ⭐️ ትንበያን ማጠናከር፦ የአየር ሁኔታ፣ የሃይድሮሎጂ እና የኤሌክትሪክ ፍላጎት ትንበያዎች የሥራ አፈጻጸም ውሳኔዎችን መምራት አለባቸው…   ⭐️ ለከፋው መዘጋጀት፣ ለተሻለው ተስፋ ማድረግ፦ ግድቦች በአደገኛ ሁኔታ እስኪቀንሱ ከመጠበቅ ይልቅ፣ አስቀድሞ በተቀረጹ የዕቅድ አማራጮች (Scenario planning) ለዝናብ እጥረት መዘጋጀት…   የእኛ ሚና   ⚠️ ይህ ምላሽ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ኦፕሬተሮች ብቻ አይደለም… ✅ አላስፈላጊ መሣሪያዎችን የሚያጠፋ ሠራተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤   ✅ ቅልጥፍናን የሚጨምር መሐንዲስ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤   ✅ ጥንቃቄ የተሞላበት ውሳኔ የሚያደርግ ኦፕሬተር አስተዋጽኦ ያደርጋል፤   ✅ የተሻለ ትንበያ የሚጠቀም እቅድ አውጪ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤   ✅ ኃላፊነት የተሞላበት የኃይል አጠቃቀምን የሚያበረታታ አስተዳዳሪ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤   ✅ በሺዎች የሚቆጠሩ ትናንሽ ውሳኔዎች ተደምረው አንድ ትልቅ ብሔራዊ ምላሽ ይሆናሉ… የኃይል እይታ (Power Insight) ውኃ ሲያንስ፣ ኤሌክትሪክ የሁላችንም ኃላፊነት ይሆናል…   ትልቁ ምስል ሙሉ ግድብ ስለ መትረፍረፍ ያስተምረናል… እየቀነሰ ያለ ግድብ ደግሞ ስለ ኃላፊነት ያስተምረናል… ተፈጥሮ ነገን እንደ ዛሬ ለማድረግ ቃል ኪዳን አልገባችልንም… የመቋቋም አቅም (Resilience) ማለት ዛሬ ያለንን ሀብት በጥበብ እየተጠቀምን፣ ነገ ለሚፈጠረው እርግጠኛ አለመሆን (Uncertainty) መዘጋጀት ነው…   ምናልባት የአንድ ተቋም እውነተኛ መለኪያ፣ ሀብት ሲትረፈረፍ እንዴት እንደሚጠቀመው ማወቅ ብቻ ሳይሆን፣ ሀብት ሲጎድልበት በምን ዓይነት ጥበብ ምላሽ ይሰጣል የሚለው ጭምር ነው… ቀጣዩ ክፍል “እያንዳንዱ ኪሎዋት ልዩነት ያመጣል”   ውኃ የኃይል ምንጭ ከሆነ፣ ኤሌክትሪክን መቆጠብ በእውነት ውኃን መቆጠብ ያስችላል?... እንዴት?...   ከዝናብ እስከ ብርሃን ያለው ጉዞ ይቀጥላል... ____ We Strive to Create a Learning Organization!!
2 330
16
🔔 ክፍል 3 የማይታየው ባትሪ በሀገራችን ውስጥ ያሉት ትልልቅ ባትሪዎች ከሊቲየም (Lithium) ሳይሆን ከውኃ የተሠሩ ቢሆንስ?... አንድ ትልቅ ግድብ/የውኃ ማጠራቀሚያ (Reservoir) አጠገብ
🔔 ክፍል 3 የማይታየው ባትሪ በሀገራችን ውስጥ ያሉት ትልልቅ ባትሪዎች ከሊቲየም (Lithium) ሳይሆን ከውኃ የተሠሩ ቢሆንስ?...   አንድ ትልቅ ግድብ/የውኃ ማጠራቀሚያ (Reservoir) አጠገብ እንደቆሙ ያስቡ… ከዳርቻው ሆነው ሲመለከቱት ሰፊ፣ ሰላማዊ እና የተረጋጋ የውኃ አካል ብቻ ሊመስል ይችላል… ጸጥ ያለ… ረጭ ያለ… እንቅስቃሴ አልባ…   ነገር ግን ከዚያ ጸጥተኛ ገጽታ በታች አንድ አስደናቂ ነገር ተደብቋል… እሱም ክምቹ አቅም (Potential energy) ነው… ውኃው ጊዜውን እየጠበቀ ነው… ግድብ - ተፈጥሮ፣ ጊዜ እና ምህንድስና የሚገናኙበት ስፍራ ነው… ዝናቡ የዘነበው ከወራት በፊት ሊሆን ይችላል… ምናልባትም ከብዙ መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቆ በሚገኝ ቦታ… ሆኖም በምንጮችና በወንዞች በኩል ሲጓዝ መሐንዲሶች ጠልፈው አከማቹት… አሁን ደግሞ እየጠበቀ ነው - ብርሃን ለመሆን…   ለዚህ ነው አንድን ግድብ የኢትዮጵያ “የማይታይ ባትሪ” አድርገን ልናስበው የምንችለው… በተፈጥሮ የተሠራ ባትሪ   ስለ ባትሪ ስናስብ፣ አብዛኛውን ጊዜ ወደፊት ለመጠቀም ኃይልን የሚያከማች ነገር ወደ አእምሯችን ይመጣል… ግድብም የሚያደርገው በሚያስደንቅ ሁኔታ ተመሳሳይ የሆነ ነገር ነው… በከፍታ ላይ የተከተረ ውኃ ክምቹ አቅም (Gravitational potential energy) ይይዛል… በሃይድሮ ፓወር ተርባይን (Hydropower turbine) ውስጥ አልፎ ሲለቀቅ፣ ያ አቅም ወደ ሜካኒካዊ ኃይል (Mechanical energy)፣ ከዚያም ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል (Electrical energy) ይለወጣል…   ባትሪ ሊያልቅ (Discharged) ይሆናል… ግድብም እንዲሁ ነው… የወደፊቱን የውኃ ፍሰት ከግምት ሳናስገባ ኤሌክትሪክ የምናመነጭ ከሆነ፣ ዛሬ የተከማቸውን ውኃ በጣም በፍጥነት ልንጨርሰው እንችላለን… ዝናብ በበቂ መጠን ከሌለ ግድቡ ወዲያውኑ ራሱን መተካት አይችልም… ለዚህ ነው የግድብ አሰራር ዛሬ ብዙ ኤሌክትሪክ ስለማመንጨት ብቻ የማይሆነው… ይልቁንም በዛሬው ፍላጎት (Demand) እና በነገው ዋስትና (Security) መካከል ትክክለኛውን ሚዛን ማግኘትን ይጠይቃል… ይህ በተለይ በድርቅ እና በአየር ሁኔታ መለዋወጥ ወቅት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው…     ጥያቄው፦   “ምን ያህል ኤሌክትሪክ ማመንጨት እንችላለን?” የሚለው አይደለም…    “ነገ የማመንጨት አቅማችንን ጠብቀን፣ ዛሬ ምን ያህል ኤሌክትሪክ ማመንጨት እንችላለን?” የሚለው እንጂ… ግድቡ ሲሞላ፣ እያንዳንዱ ሜጋዋት (Megawatt) ቀላል ሊመስል ይችላል… ውኃው ማብቂያ የሌለው ሊመስል ይችላል… ነገር ግን እጥረት እይታችንን ይለውጠዋል… በድንገት፣ እያንዳንዱ ኩዩቢክ ሜትር ውኃ ዋጋ ይኖረዋል… እያንዳንዱ ውኃ መልቀቅ ቁልፍ ውሳኔ ይሆናል… እያንዳንዱ አላስፈላጊ አጠቃቀም የባከነ ዕድል ይሆናል..     የሰው ልጅ ብዙ ጊዜ የሚረሳውን ነገር ተፈጥሮ ታስተምረናለች፦ አንድ ነገር ስላለን ብቻ ዛሬውኑ ሁሉንም መፍጀት አለብን ማለት አይደለም… አንዳንድ ጊዜ ጥበብ ማለት መቼ መጠቀም እንዳለብን ማወቅ ነው… አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ጥበብ ማለት መቼ መጠበቅ እንዳለብን ማወቅ ነው… ለዚህ ነው ዘመናዊ የኃይል ሥርዓት አሠራር ከጊዜ ጥበቃ ወደ ጊዜ ትንበያ፣ ወደ ሞዴሊንግ (Modelling)፣ የመረጃ ትንተና፣ ሁኔታዎችን አስቀድሞ የማቀድ (Scenario planning) እና የተቀናጀ ውሳኔ አሰጣጥ ማደግ ያለበት… Plant Operator ዝም ብሎ ውኃን ብቻ የሚመለከት አይደለም… ጊዜን፣ ኃይልን፣ እርግጠኛ አለመሆንን (Uncertainties) እና ስጋትን (Risk) እያስተዳደረ ነው እንጂ… ባትሪው እየደከመ (Running down) ሲመጣ…   አሁን ደግሞ ከቅድሙ በተቃራኒው ያስቡ… የዝናብ መጠን ከመደበኛው በታች ነው፣ ወደ ወንዞች የሚገባው ውኃ ቀንሷል፣ የግድቡ ውኃ መቀነስ ጀምሯል፣ የኤሌክትሪክ ፍላጎት ግን ማደጉን ቀጥሏል… ይሄኔ የሥርዓቱ ኦፕሬተር አስቸጋሪ ምርጫ ይጋፈጣል፦ ዛሬ ብዙ አምርቶ ክምችቱን በፍጥነት መቀነስ?ወይስ ውኃውን ቆጥቦ የወደፊቱን የማመንጨት ሂደት ማስጠበቅ?...   ቀላል መልስ የለውም… ትክክለኛው ውሳኔ በአጠቃላይ ሥርዓቱ ላይ የተመሰረተ ነው… ለዚህ ነው የኃይል ዋስትና በመጨረሻ የሥርዓታዊ አስተሳሰብ (Systems thinking) ጉዳይ ሆኖ የሚከሰተው…   ግድቡ ከግሪዱ (Grid) ተነጥሎ ሊታይ አይችልም… ግሪዱ ከፍላጎት (Demand) ተነጥሎ ሊታይ አይችልም… ፍላጎት ከኢኮኖሚው ተነጥሎ ሊታይ አይችልም… እናም አንዳቸውም ቢሆኑ ከአየር ሁኔታ እና ከውኃ መጠን ተነጥለው ሊታዩ አይችሉም… ትልቁ ምስል   በግድብ ውስጥ እጅግ ጥልቅ የሆነ ውበት አለ… ስለ ጊዜ ያስተምረናል…     ዝናብ በአንድ ቅጽበት ይዘንባል… ግድብ ግን ያ ቅጽበት ሌላኛውን ቅጽበት እንዲያገለግል ይፈቅዳል… የትናንት ዝናብ የዛሬን ሆስፒታል ተግባር ይወስናል… የባለፈው ወር ዝናብ የዛሬን ፋብሪካ ሊያንቀሳቅስ ይችላል… በተራራ ላይ የወረደ ውኃ በመጨረሻ በብዙ መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኝ ከተማ ውስጥ ብርሃን ሊሆን ይችላል…   በዚህ መንገድ - ግድብ ያለፈውን፣ የአሁኑን እና የወደፊቱን ያገናኛል… ተፈጥሮ ዛሬ የሰጠችን የነገ ኃላፊነታችንንም ጭምር ነው… ሙሉ ግድብ የመትረፍረፍ ምልክት ብቻ አይደለም - ኃላፊነትም እንጂ… የጎደለ ግድብ ችግር ብቻ አይደለም - የጥበብ መፈተኛም እንጂ…   የኃይል እይታ (Power Insight)   ግድብ ከውኃ በላይ የሆነን ነገር ያከማቻል… ኃይልን፣ ጊዜን፣ ምርጫዎችን እና ኃላፊነትን…   ተቋማችን ሊማረው የሚገባው ጉዳይ…   በተለመደው የውኃ ፍሰት ቁጥጥር ዘይቤ ብቻ መጓዝ አሁን ላይ በቂ አይደለም… ይበልጥ የሚያስፈልጉን፦ ✅የተሻለ የሃይድሮሎጂ ትንበያ (Hydrological forecasting) ✅የአየር ሁኔታ መረጃን ያገናዘበ የማመንጨት እቅድ ግድቦችን በተሻለ ሁኔታ የመጠቀም (Reservoir optimization) ልምምድ ✅የቀጥታ ሰዓት መረጃ እና ክትትል (Real-time data and monitoring) ✅ሁኔታዎችን መሠረት ያደረገ እቅድ (Scenario-based planning) ✅በውኃ እና አየር ሁኔታ ጉዳይ ላይ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ጠንካራ ቅንጅት መፍጠር ✅በዲጂታል (በተለይ AI) የታገዙ የውሳኔ ድጋፍ ሥርዓቶችን መከተል ✅ቴክኒካዊውንና የክላይሜት ስጋቶችን የሚረዱ የተማሩ ባለሙያዎች ማፍራት   የውኃ ጥበብ   ውኃ ከተፈጥሮ መልክዓ ምድር ጋር መቼም አይከራከርም… መንገዱን ፈልጎ ያልፋል፣ በአንድ ቦታ ይሰበሰባል፣ ወደ ሌላ ቦታ ይንቀሳቀሳል፣ ቅርጹን ይለውጣል፣ ይጠብቃል፣ ይፈሳል፣ ኃይል ይሰጣል፣ እናም በመጨረሻ ወደ ሰማይ ይመለሳል…   ውኃ - ጥንካሬ ሁልጊዜ ጉልበት ማለት እንዳልሆነ ያስታውሰናል… አንዳንድ ጊዜ ጥንካሬ ትዕግሥት ነው፣ አንዳንድ ጊዜ ዕድገት መንቀሳቀስ ነው… አንዳንድ ጊዜ ጥበብ መቼ መፍሰስ እና መቼ መረጋጋት እንዳለብን ማወቅ ነው… እናም አንዳንድ ጊዜ መረጋጋት መስሎ የሚታየው ትክክለኛውን ቅጽበት የሚጠብቅ የተከማቸ እምቅ አቅም ነው…     ቀጣዩ ክፍል - “ውኃ ብርሃን ሲሆን”   ጸጥተኛው ግድብ እንዴት ሀገርን ወደሚያበራ ኤሌክትሪክ ይለወጣል?...   --- We Strive to Create a Learning Organization!!
1 828
17
💧🏪🫥 ሰላም ለእናንተ ይሁን!! -- ሰሞኑን በስልክ፣ በኢንቦክስና በአካል በተደጋጋሚ ከቀረቡልን ጥያቄዎች ውስጥ ‘ደራሽ ምን ላይ ደረሰ?’ የሚለው ጉዳይ ሚዛን የሚደፋ ሆኖ አግኝተነዋል… ☀️ እ
💧🏪🫥 ሰላም ለእናንተ ይሁን!! -- ሰሞኑን በስልክ፣ በኢንቦክስና በአካል በተደጋጋሚ ከቀረቡልን ጥያቄዎች ውስጥ ‘ደራሽ ምን ላይ ደረሰ?’ የሚለው ጉዳይ ሚዛን የሚደፋ ሆኖ አግኝተነዋል… ☀️ እውነት ለመናገር - ✅ይህ ክትትል ተስፋ ይሰጣል! ✅ይህ ጥያቄ ያበረታል! ✅ይህ ጉትጎታ የስንፍና እንቅልፍ ይነሳል! ✅ይህ ጥያቄ ደራሽ የሁሉም ሰው ሃሳብነቱን ያጎላል! እንደምታውቁት ጉዳዩ አዲስ ተቋማዊ ስርዓት የመፍጠር ሂደት እንደመሆኑና ገንዘብ ነክ እንቅስቃሴዎችም ስላሉበት ቀጣይነቱ፣ ተዓማኒነቱና ፍትሐዊነቱ ላይ ከጅምሩ መሰራት አለበት… በዚህም ምክንያት ጊዜ ወስዶብናል… ✅ የምናስበው ደራሽ - የኮሚቴ ስራ አይደለም! ✅ የምንገነባው ደራሽ - የአንድ ወቅት ተግባር አይደለም! ✅ የምናልመው ደራሽ - ከዕድሜያችን የሚበልጥ ነው! ይህ በእንዲህ እንዳለ ደራሽ ተቋማዊ ስርዓት ሆኖ ሙሉ ለሙሉ በአሰራር እስኪደገፍ ድረስ ብቻ የሚያደራጀው ጊዜያዊ ስብስብ በእስካሁን ቆይታው፡- ⭐ EEP Social Support Service (Derash) Directive - (መመሪያ)፤ ⭐ Membership registration template - (የአባልነት መመዝገቢያ)፤ ⭐ Financial management procedure - (የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ)፤ ⭐ Derash Governance Charter – (የደራሽ ማሕበራዊ ድጋፍ አገልግሎት ውል) ⭐ Emergency Support SOP – (የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ የአሰራር ስርዓት) ⭐ Digital system design – (ወደ ዲጂታል ስርዓት ማስገቢያ ሰነድ) ⭐ Vision, Mission & Guiding principles - አዘጋጅቶ ጨርሷል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቅርቡ ለሚደረገው መስራች ጉባኤ (ለዋ/መ/ቤት፣ ሦስቱ ሴንትራሎች፣ ረጲና ኤልዲሲ ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች) የሚቀርብ Preliminary Financial Analysis and Sustainability Model (የቅድመ ትግበራ የፋይናንስ ፍላጎት ትንተናና የማዝለቂያ ስልት - /የአባላት መዋጮ፣ የድጋፍ መጠን፣ ከተቋም የሚፈለግ እገዛ/… ወዘተ የያዘ) ንድፍ ሰነድ አዘጋጅቶ የስብሰባውን ቀን ይጠብቃል፡፡ 🙏 አብራችሁን ለተጓዛችሁና እንደመደበኛ ስራችሁ ሂደቱን ላገዛችሁ የስራ ኃላፊዎችና ጊዜያዊ አደራጆች እጅግ አድርገን እናመሰግናለን!! 👉 ደራሽ ቻናልን ተቀላቀሉ - https://t.me/eepderash በቅርቡ እንገናኝ!! 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
5 211
18
🔺🔺🔺 ክፍል 2 ያልተስተዋለው ነዳጅ የሃገራችን ኤሌክትሪክ ምንጭ - የመጀመሪያው ነዳጅ ከማዕድን ማውጫ የሚቆፈር አይደለም... ከሰማይ የሚወርድ እንጂ… ✅ የኤሌክትሪክ ነዳጃችን ምንድን ነው?..
🔺🔺🔺 ክፍል 2 ያልተስተዋለው ነዳጅ የሃገራችን ኤሌክትሪክ ምንጭ - የመጀመሪያው ነዳጅ ከማዕድን ማውጫ የሚቆፈር አይደለም... ከሰማይ የሚወርድ እንጂ… ✅ የኤሌክትሪክ ነዳጃችን ምንድን ነው?... ይህንን ጥያቄ ለማንኛውም ሰው ቢያነሱ፣ መልሱ ምናልባት፦ “ውኃ” የሚል ይሆናል… ይህ ግልጽ ይመስላል… ደግሞም ግድቦቻችን ውኃን ተጠቅመው ተርባይኖችን (Turbines) በማሽከርከር ኤሌክትሪክ እንደሚያመነጩ የታወቀ ነው…   ነገር ግን፣ ውኃ - የኃይል ሥርዓታችን የመጀመሪያው ነዳጅ አይደለም ብልዎትስ?...   Water is only the carrier… እውነተኛው ነዳጅ ወንዞች መፍሰስ ከመጀመራቸው ከብዙ ጊዜ በፊት በጸጥታ የቆየ፣ በዝምታ ያደፈጠ ነው... በደመናዎች ውስጥ!... ⛈ እያንዳንዱ ብርሃን የሚጀምረው ከዝናብ ጠብታ ነው ተርባይን መሽከርከር ከመጀመሩ በፊት... የማስተላለፊያ መስመሮች (Transmission lines) ኤሌክትሪክን በመላ ሀገሪቱ ከማድረሳቸው በፊት... በአንድ ክፍል ውስጥ አምፑል በርቶ ብርሃን ከመፈንጠቁ በፊት... [በቅድሚያ ሌላ ነገር መከሰት አለበት…]   ፀሐይ ውቅያኖሶችን ታሞቃለች… ውኃው ተንኖ ወደ ከባቢ አየር (Atmosphere) ይወጣል… ደመናት ይፈጠራሉ… ነፋሳት እነዚያን ደመናዎች አህጉራትን አቋርጠው ያጓጉዟቸዋል… በኢትዮጵያ ተራራማ ቦታዎች ላይ ዝናብ ይዘንባል… ያ ዝናብ ወንዞችን ይመግባል… እነዚያ ወንዞች ማጠራቀሚያዎችን (Reservoirs) ይሞላሉ… ግድቦቹ ውኃውን በተርባይኖች ውስጥ ይለቁታል… ኤሌክትሪክ ሊመረት የሚችለው ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው…   እኛ የምናበራው እያንዳንዱ መብራት ከምድር በላይ ከፍ ካለ ቦታ የጀመረ የራሱ ታሪክ አለው…   ✅ ተፈጥሮ የመጀመሪያዋ መሐንዲስ ናት አንድን የሃይድሮ ፓወር ጣቢያ ስናደንቅ፣ አብዛኛውን ጊዜ የምናደንቀው የኮንክሪት ግንቦቹን፣ ተርባይኖቹን፣ ጀነሬተሮቹን፣ ትራንስፎርመሮቹን እና የማስተላለፊያ ማማዎቹን ነው…   ነገር ግን የመጀመሪያዋ መሐንዲስ (ተፈጥሮ) አብዛኛውን ሥራ ቀድማ አከናውናዋለች… የሰው ልጅ ግድቦችን ከመገንባቱ ከረጅም ጊዜ በፊት ተፈጥሮ የውኃን ዑደት (Water cycle) ቀርጻለች…   ፀሐይ በየቀኑ በቢሊዮን የሚቆጠር ቶን ውኃ ከውቅያኖሶች ላይ ታነሳለች… ከባቢ አየር በመላው ዓለም ያጓጉዘዋል… ተራሮች የዝናብ ውኃውን ወደ ወንዞች ይመሩታል። መሐንዲሶች የዚያን ተፈጥሯዊ ጉዞ ጥቂት ክፍል ብቻ ጠልፈው ወደ ኤሌክትሪክ ይለውጡታል…   አዎን - ቴክኖሎጂ ተፈጥሮን አይተካም፤ ከተፈጥሮ ጋር አብሮ ይሠራል እንጂ… 🟢 ይህ ለተቋማችን (EEP) ለምን ያስፈለገዋል? ይህ መረዳት ለሥራችን ያለንን አመለካከት ይለውጠዋል። አንድ የሃይድሮ ፓወር ማመንጫ ጣቢያ ለብቻው ተለይቶ የቆመ ፋሲሊቲ አይደለም… እጅግ ሰፊ በሆነ ሰንሰለት ውስጥ የመጨረሻው ማያያዣ እንጂ… 👉 ዝናብ ሲቀንስ ➡️ ወደ ወንዞች የሚገባው ውኃ ይቀንሳል፤ 👉 ወደ ወንዞች የሚገባው ውኃ ሲቀንስ ➡️ በግድቦች የሚከማቸው ውኃ ያንሳል፤ 👉 በግድቦች የሚከማቸው ውኃ ሲያንሥ ➡️ ኃይል ማመንጨት ፈታኝ ይሆናል፤   ለዚህ ነው የአየር ሁኔታ ትንበያ፣ የወንዞች ተፋሰስ አስተዳደር (Watershed management)፣ የግድብ አሰራር እና የክላይሜት ሳይንስ (Climate science) ለተቋማችን ስትራቴጂካዊና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች የሚሆኑት…   ለዚህ ነው የኤሌክትሪክ ኃይላችንን የመጠበቅ ስራ የሚጀምረው ውኃው ግድብ ላይ ከመድረሱ ከብዙ ጊዜ በፊት ነው የምንለው… 🌧 ዝናብን በሌላ እይታ መመልከት ብዙ ሰዎች ዝናብን ዝም ብለው እንደ አየር ሁኔታ ያዩታል… የኃይል ዘርፍ ባለሙያዎች ግን ከዚያ በላይ የሆነ ነገር ያያሉ… እያንዳንዷ የዝናብ ጠብታ የወደፊቱን ኃይል የተሸከመች አነስተኛ እሽግ ናት… ሚሊዮን የዝናብ ጠብታዎች ምንጭ ይሆናሉ፤ ምንጮች ወንዝ ይሆናሉ፤ ወንዞች ግድብ ይሆናሉ፤ ግድቦች ደግሞ ኤሌክትሪክ ይሆናሉ… እያንዳንዱ የዝናብ ወቅት የሃገራችንን ግዙፍ ተፈጥሯዊ ባትሪዎች በጸጥታ መልሶ እየሞላ (Recharging) ነው… ⚡️ የኃይል እይታ (Power Insight) ተርባይኑን የሚያሽከረክረው ውኃ ቢሆንም፣ ውኃው እንዲኖር የሚያደርገው ግን ዝናብ ነው… በሃይድሮ ፓወር የሚመነጨው እያንዳንዱ ዩኒት ኤሌክትሪክ ጉዞውን የሚጀምረው ከዝናብ ጠብታ ነው… ➡️ የእርስዎ ሚና ኤሌክትሪክ እንዳይባክን ስንጠነቀቅ፣ በግድቦቻችን ውስጥ አላስፈላጊ ውኃ እንዳይፈስም እየጠበቅን ነው… ኤሌክትሪክ መቆጠብ ወጪን ስለመቀነስ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያን እጅግ ውድ የኃይል ሀብት — ውኃን — ስለመጠበቅም ጭምር እንጂ…   በሺዎች በሚቆጠሩ ሰራተኞች የሚታዩ ትናንሽ ተግባራት ተደምረው ለሀገራችን የኃይል ዋስትና (Energy security) ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ… ✅ ትልቁ ምስል አንድ የዝናብ ጠብታ በራሷ ኢምንት ልትመስል ትችላለች… ነገር ግን ስፍር ቁጥር የሌላቸው የዝናብ ጠብታዎች ሀገርን ማብራት ይችላሉ… ታላቅነት አብዛኛውን ጊዜ የሚገነባው እርስ በእርሳቸው ከተሳሰሩ ትናንሽ አስተዋፅኦዎች መሆኑን ተፈጥሮ ያስታውሰናል… በሰዎችም ዘንድ እውነታው ይሄው ነው… እያንዳንዱ ግለሰባዊ ጥረት፣ ምንም ያህል ትንሽ ቢመስል፣ ከሌሎች ጥረቶች ጋር ሲቀላቀል እጅግ ታላቅ የሆነ ነገር አካል ይሆናል… [ቀጣዩ ክፍል] “ግድቦች፦ የኢትዮጵያ የማይታዩ ባትሪዎች”   በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ትልልቅ ባትሪዎች ከሊቲየም (Lithium) ሳይሆን ከውኃ የተሠሩ ቢሆኑስ?...   --   We Strive to Create a Learning Organization!!
2 077
19
🌧 🔸💡 ከዝናብ እስከ ብርሃን የኤሌክትሪክ ሕቡዕ ጉዞ [ክፍል 1] --- መብራታችንን ማጥፋት የሚችለው ውቅያኖስ በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የተከሰተ ችግር… ከኢትዮጵያ ከ15,000 ኪሎ
🌧 🔸💡 ከዝናብ እስከ ብርሃን የኤሌክትሪክ ሕቡዕ ጉዞ [ክፍል 1] --- መብራታችንን ማጥፋት የሚችለው ውቅያኖስ በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የተከሰተ ችግር…   ከኢትዮጵያ ከ15,000 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ የሚገኝ ውቅያኖስ የሙቀት መጠን... መኖሪያ ቤቶቻችንን፣ ሆስፒታሎቻችንን፣ ኢንዱስትሪዎቻችንን እና የሥራ ቦታዎቻችንን የሚያበራውን ኤሌክትሪክ ሊነካው እንደሚችል አስበው ያውቃሉ?...   በመጀመሪያ ሲሰሙት የማይቻል ይመስላል…   በሌላኛው የዓለም ክፍል የሚገኝ ውቅያኖስ በኢትዮጵያ የሚገኝን የሃይድሮ ፓወር (Hydropower) ጣቢያ እንዴት ሊጎዳ ይችላል?...   ነገር ግን ኤል ኒኖ (El Niño) በሳይንቲስቶች፣ በመንግሥታት እና በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የኤሌክትሪክ ተቋማት — (EEP)ን ጨምሮ — በትኩረት ከሚከታተሏቸው የአየር ሁኔታ (Climate) ሁነቶች አንዱ የሆነበት ምክንያት አለ…   ነገርየውን ለመረዳት፣ በመጀመሪያ አንድን ትልቅ እውነት መረዳት አለብን፦   🔺 ተፈጥሮ እርስ በእርሱ የተሳሰረ አንድ ሥርዓት ነው።   ምንም ነገር ተነጥሎ አይኖርም። ውቅያኖሶች የአየር ሙቀትንና ግፊትን (Atmosphere) ይወስናሉ፤   አየር ንብረቱ ደግሞ የአየር ሁኔታን (Weather) ይቀርጻል፤   የአየር ሁኔታው የዝናብ መጠንን ይወስናል፤   ዝናብ ወንዞችን ይመግባል፤   ወንዞች ግድቦችን/ማጠራቀሚያዎችን (Reservoirs) ይሞላሉ፤   ግድቦች ኤሌክትሪክ ያመነጫሉ፤   ኤሌክትሪክ ደግሞ የእለት ተእለት ሕይወታችንን ያንቀሳቅሳል፤   በዚህ ሰንሰለት ውስጥ ባለው በአንዱ ክፍል ላይ የሚከሰት ለውጥ፣ በመጨረሻም እያንዳንዱን ክፍል ይነካዋል… ❓ 🧊ኤል ኒኖ (El Niño) ምንድን ነው? ኤል ኒኖ በማዕከላዊ እና በምስራቃዊ ፓሲፊክ ውቅያኖስ የላይኛው የውኃ አካል ላይ በሚከሰት ያልተለመደ የሙቀት መጨመር ምክንያት የሚፈጠር ተፈጥሯዊ የአየር ሁኔታ ለውጥ ሁነት ነው…   ከኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቆ ቢጀመርም፣ ያ የሙቀት መጨመር ግን የዓለም አቀፉን የከባቢ አየር ዝውውር ይለውጠዋል… የነፋስ አቅጣጫዎችና ዘይቤዎች ሲቀየሩ፣ በብዙ የዓለም ክፍሎች ያለው የዝናብ ሥርጭትም አብሮ ይለወጣል…   ✅ ሀገራት ከመጠን በላይ የሆነ ዝናብና የጎርፍ አደጋ ያጋጥማቸዋል… ✅ ሌሎች ደግሞ ከመደበኛው ያነሰ ዝናብ በማግኘት ለድርቅ ይጋለጣሉ…   ኤሌክትሪኳ በዋናነት በውኃ ላይ ለተመሰረተ ለእንደኛ ዓይነት ሃገር፣ ይህ ጉዳይ እጅግ በጣም ትልቅ ትርጉም አለው… ⭐️ ተቋማችን (EEP) ለምን ሊጨነቅ ይገባል? በዋናነት በከሰል፣ በነዳጅ ወይም በተፈጥሮ ጋዝ ከሚጠቀሙ ሀገራት በተለየ፣ ኢትዮጵያ አብዛኛውን የኤሌክትሪክ ኃይል የምታመነጨው ከ Hydro power (ከውኃ ኃይል) ነው…   ይህ ማለት የእኛ እጅግ ውድ የሆነው የኃይል ሀብታችን ከመሬት በታች የሚገኝ አይደለም… ከደመናት የሚወርድ እንጂ…   እያንዳንዱ የዝናብ ወቅት ግድቦቻችንን የሚመግቡትን ወንዞች ያድሳል… እነዚያ ግድቦች ውኃውን አከማችተው በመያዝ፣ በተርባይኖች (Turbines) ውስጥ አልፎ ኤሌክትሪክ እንዲያመነጭ ይለቁታል…   ዝናብ ለረጅም ጊዜ ሲቀንስ፣ ወንዞች የሚያመጡት የውኃ መጠን ያንሳል፤ በግድቦች ውስጥ ያለው የውኃ መጠን በሂደት ይቀንሳል፤ በዚህም ምክንያት ሊመነጭ የሚችለው የኤሌክትሪክ መጠን ሊቀንስ ይችላል…   ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ዝናብ ዝም ብሎ የአየር ሁኔታ ብቻ አይደለም…     ዝናብ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ሰንሰለታችን መነሻ ነው… ሁላችንንም የሚያያይዝ ሰንሰለት!!     ጉዞው እጅግ በጣም ቀላል እና ግልጽ ነው፦ የሞቀ የፓሲፊክ ውቅያኖስ ⬇️ የከባቢ አየር ዝውውር መለወጥ ⬇️ በኢትዮጵያ ላይ ያለው የዝናብ መጠን መለወጥ ⬇️ ወደ ወንዞች የሚገባው ውኃ መቀነስ ⬇️ በግድቦች የሚከማቸው ውኃ መቀነስ ⬇️ የሃይድሮ ፓወር ኤሌክትሪክ ምርት መቀነስ ⬇️ በብሔራዊ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ጫና መፈጠሩ     በውቅያኖስ ሙቀት ለውጥ የሚጀምረው ክስተት፣ በመጨረሻም ወደ እኛ የኃይል ሥርዓት ይደርሳል…   📌 ይህ ከ EEP በላይ ለሁላችንም ለምን ያሳስበናል? ኤሌክትሪክ ከብርሃን በላይ ነው…   ሕይወትን የሚያድኑ ሆስፒታሎችን ያንቀሳቅሳል፤ ኢንዱስትሪዎች ምርታማ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ ትምህርት ቤቶችን፣ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ የመገናኛ መረቦችን እና አስፈላጊ የሕዝብ አገልግሎቶችን ይደግፋል…   የኤሌክትሪክ አቅርቦት አስተማማኝነት ሲጎዳ፣ ጉዳቱ እያንዳንዱን ዜጋ እና እያንዳንዱን የኢኮኖሚ sector ይነካል… ለዚህ ነው የአየር ንብረት ለውጥ ሁኔታን መረዳት የኃይል አቅርቦትን የመረዳት አካል የሆነው… ✅ የኃይል እይታ (Power Insight)   የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ጉዞ የሚጀምረው ከግድብ ወይም ከተርባይን አይደለም… የሚጀምረው ከደመና፣ ከዝናብ፣ ከወንዞች እና ከፕላኔታችን እያንዳንዱን ክፍል ከሚያያይዘው የ Climate ሥርዓት ነው… ✅ የእርስዎ ሚና እያንዳንዱ ሰራተኛ መፃኢ የኃይል ምንጫችንን በመጠበቅ ረገድ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት ይችላል…   ስለ አየር ሁኔታ እና ክላይሜት በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ይጀምሩ… እነዚህ ጉዳዮች የአየር ሁኔታ ተንባዮች ብቻ የሚያነሷቸው አጀንዳዎች መሆናቸው አክትሟል… የዘመናዊ የኃይል ሥርዓቶች ቋንቋ አካል ሆነዋል…   በ Climate እና በኤሌክትሪክ መካከል ያለውን ግንኙነት በተረዳን ቁጥር፣ ለሀገራችን አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥ የተሻለ ዝግጅት ይኖረናል… ✅ ትልቁ ምስል ብዙ ጊዜ ዓለምን የተለያዩና የተነጣጣሉ ቦታዎች ስብስብ አድርገን እናስባለን፤ ተፈጥሮ ግን ሌላ ታሪክ ትነግረናለች…   ውቅያኖሶች፣ ከባቢ አየር፣ ተራሮች፣ ወንዞች እና የሰው ልጅ በአንድ ሕያው ሥርዓት ውስጥ ተሸምነዋል… ኤል ኒኖ በምድር በአንዱ በኩል የሚከሰት ክስተት በሌላኛው ወገን ያለውን ሕይወት ሊነካው እንደሚችል ያስታውሰናል… ይህንን እርስ በእርስ የመተሳሰር ሁኔታ መረዳት፣ በአደራ የተሰጡንን ሀብቶች በጥበብ ለማስተዳደር የመጀመሪያው እርምጃ ነው…     ---     በቀጣይ ክፍል፦   ውኃ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነዳጅ ካልሆነ፣ ታዲያ ምንድን ነው?...     ---   We Strive to Create a Learning Organization!!
2 547
20
🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤 ማስታወሻ ለጉግል ክሮም Browser ተጠቃሚዎች . . . "የጉግል ክሮም የደህንነት ቡድን በማሰሻው (Browser) ላይ ለተገኙ 370 የደህንነት ክፍተቶች የሶፍትዌር ማስተካከ
🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤 ማስታወሻ ለጉግል ክሮም Browser ተጠቃሚዎች . . .   "የጉግል ክሮም የደህንነት ቡድን በማሰሻው (Browser) ላይ ለተገኙ 370 የደህንነት ክፍተቶች የሶፍትዌር ማስተካከያ (Security Patches) አውጥቷል፤ ከእነዚህም ውስጥ 7ቱ እጅግ አሳሳቢ (Critical) የሚባሉ ናቸው።   ይህ የደህንነት ማስተካከያ እ.ኤ.አ ሐምሌ 29 የተለቀቀ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች የክሮም ቨርዥን 151 (Version 151) ለዊንዶውስ እና ማክ (151.0.7922.71/.72) እንዲሁም ለሊነክስ (151.0.7922.71) በአፋጣኝ ማዘመን (Update) ይኖርባቸዋል" ሲል INSA አሳስቧል... የኢንተርኔት ማፈላለጊያዎ ምንድነው? Chrome ከሆነ አሁኑኑ Update ያድርጉት... Settings - About chrome - Update [Automatic] ___ "Our digital future depends not only on the systems we build, but on the security habits we practice every day."
2 390