es
Feedback
Ethio Power Insight

Ethio Power Insight

Ir al canal en Telegram

Learn | Reflect | Share | Improve Sharing knowledge - Inspiring ideas - Building a Stronger Ethio Power. We strive to create a learning organization!!

Mostrar más
2 338
Suscriptores
-124 horas
-47 días
-4530 días
Archivo de publicaciones
Ethiopian Public Service - Masters Program Application Form.xlsx0.10 KB

🏪 . . . በተቋማችን የሴቶችን የውሳኔ ሰጭነት አቅም ለማሳደግ በዲፕሎማ የትምህርት መስክ ለ 25፣ በመጀመሪያ ዲግሪ ለ 20 እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ ለ 10 በድምሩ ለ 55 ሴቶች በየዓመቱ በጀት
+4
🏪 . . . በተቋማችን የሴቶችን የውሳኔ ሰጭነት አቅም ለማሳደግ በዲፕሎማ የትምህርት መስክ ለ 25፣ በመጀመሪያ ዲግሪ ለ 20 እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ ለ 10 በድምሩ ለ 55 ሴቶች በየዓመቱ በጀት ተይዞ የትምህርት ወጪ ምላሽ (Refund) ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ ፐፕሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ለ 2019 ያወጣውን የ Scholarship ዕድል በመጠቀም ለሴቶች ከሚሰጠው የትምህርት ዕድል ውስጥ የማስተርስ ፕሮግራሙን በሚከተሉት የትምህርት ዕድሎች ላይ ለማድረግ እንዲቻል ምዝገባ ጀምሯል። 1️⃣ Accounting and Finance - (2 ሴቶች) 2️⃣ Project Leadership and Management - (4 ሴቶች) 3️⃣ International Law - (1 ሴት) 4️⃣ Financial Regulation and Law - (2 ሴቶች) 5️⃣ Tax Policy and Administration - (1 ሴት)
ስለሆነም:-
✅ ከተመራጩ የትምህርት አይነት ጋር ተያያዥ እና እውቅና ከተሰጠው የትምህርት ተቋም የመጀመሪያ ዲግሪ ያገኛችሁ ✅ የትምህርት ሚኒስቴር የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ያለፋችሁ ✅ ከተመረጣችሁ በኋላ በምዝገባ ወቅት ኦሪጅናል ትራንክሪፕት ማቅረብ የምትችሉ ✅ የመጀመሪያ ዲግሪያችሁንን ከውጭ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ያገኛችሁ ከሆነ ከፌዴራል ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የትምህርት ማረጋገጫ ማያያዝ የምትችሉ ሴቶች፣  ➡️ [ከዚህ በታች በተያያዘው ቅጽ መረጃችሁን በመሙላትና የ NGAT ውጤታችሁን Original Scan Copy በማያያዝ በተከታዩ email አድራሻ እንድትልኩልን እናስታውቃለን።] ethiopoweracademy@gmail.com
ማሳሰቢያ
: ___ 📝 የዩኒቨርሲቲውን ማስታወቂያ በጥንቃቄ አንብቡ፤ መስፈርቱን የማታሟሉ ከሆነ አታመልክቱ፤ 🖱 ከላይ ከተዘረዘሩትና ተቋማችን ከምመደበኛ ስራው ጋር ያላቸውን ቀጥተኛ ግንኙነት መዝኖ ከመረጣቸው የትምህርት መስኮች ውጪ ማመልከት አይቻልም፤ ⏰ ለምዝገባ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ እጅግ አጭር ስለሆነና በድጋሚ ስለማይራዘም ከማክሰኞ (19/01/2019) 6:00 በኋላ የሚመጡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት የላቸውም!! ___ We Strive to Create a Learning Organization!!

🎓 ለተቋማችን ሴት ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች __ ዘንድሮ በትምህርታችሁ ከፍ ለማለት ምን ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው?... ሌቭል ወደ ዲፕሎማ፣ ዲፕሎማ ወደ ዲግሪ፣ ዲግሪ ወደ ማስተርስ ያድጋል ወይስ
🎓 ለተቋማችን ሴት ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች __ ዘንድሮ በትምህርታችሁ ከፍ ለማለት ምን ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው?... ሌቭል ወደ ዲፕሎማ፣ ዲፕሎማ ወደ ዲግሪ፣ ዲግሪ ወደ ማስተርስ ያድጋል ወይስ 'ያለኝ ዕውቀት ይበቃኛል' እያላችሁ ነው?...  ዘመኑ እየሮጠ ነው፣ ሁኔታዎችም በፍጥነት እየተለዋወጡ ነው... ከለውጡ ጋር ተሰናስሎ ለመጓዝ የሩቅ ታዛቢነት አያዋጣም... የዕውቀት መንገድ 'ይበቃል' አይባልም... በኑረት መንገድ ላይ በየዕለቱ ይጎድላል... እንደ ባትሪ ነው - ስለዚህም በየዕለቱ መሞላት አለበት... ይህ ግን በብላሽ አይሆንም... ትንሽ ትንሽ ዋጋ መክፈል ይሻል... ከዛሬ ላይ ቆርሰን ለነገ የምንሸርፋት ነገር ከሌለች መጪው ጊዜ በብዙ ነገር ፈታኝ ነው... ➡️ ሁሌም - መማር፣ ማወቅ፣ መጠየቅ፣ ማንበብ፣ አካባቢን መገንዘብ፣ ማስተዋል፣ ጉድለትን መፈተሽ፣ አስተሳሰብን መሞረድ - ወደ ነገ የምንሻገርበት ጽኑ ድልድይ ነው... ____
በነገራችን ላይ...
🟢 ተቋማችን በየዓመቱ ለ 55 ሴቶች የትምህርት ወጪ እንደሚሸፍን ታውቃላችሁ - ግን ስንቶቻችሁ በዚህ ዕድል ለመጠቀም ዝግጁ ናችሁ?... ⚫️ 25 ዲፕሎማ 🟣 20 ዲግሪ 🔘 10 ማስተርስ ኧረ የዘንድሮ ዕድለኛ ሴቶች እነማን ናችሁ?.... ____ 📣 እዚህ ላይ ሁለት ነጥቦች ብቻ... 📌 የዲግሪ ዕድል ለማግኘት ዘንድሮ በአንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመማር ተመዝግቦ ሰነድ መያዝ ያስፈልጋል። 📌 ለማስተርስ ደግሞ NGAT Certificate ወሳኝ ነው። ____ ⭐️ Surprise!! ⭐️ 🛒 ዘንድሮ ማስተርስ መማር ለሚፈልጉ ሴት ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች መልካም ዜና አለን... ____ 🍀 ለጊዜው ምስጢር ነው - መስፈርቱን ለሚያሟሉ ባልደረቦቻችሁ ሹክ በሏቸው... _ በቅርብ ቀን...

Three_group_trainees_excluding_TB & ECB_Project_office.xlsx0.73 KB

☀️☀️ የስልጠና መርሃግብር ማስታወቂያ ☀️☀️ የሰራተኞችን የስራ ተነሳሽነትና ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማጎልበት ታስቦ በ Employee Engagement ርዕሰ ጉዳይ ሁሉንም የዋና መ/ቤት ሰራተኞች ለማ
☀️☀️ የስልጠና መርሃግብር ማስታወቂያ ☀️☀️ የሰራተኞችን የስራ ተነሳሽነትና ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማጎልበት ታስቦ በ Employee Engagement ርዕሰ ጉዳይ ሁሉንም የዋና መ/ቤት ሰራተኞች ለማሰልጠን በታቀደው መሰረት በመጀመሪያው ዙር በኢንጂነሪንግ እና ትራንስሚሽን ቢዝነስ ውስጥ ለሚገኙ የፕሮጀክት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቶ መጠናቀቁ ይታወቃል፡፡ ይህ ስልጠና በሁሉም ሪጅኖችና የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በኦፕሬሽን ዘርፎች አማካይነት በሚወጣ መርሃግብር መሰረት ለሁሉም ሰራተኞች የሚሰጥ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረና ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ስልጠናውን በሦስት ዙር፣ ማለትም፡ 🍀 ቡድን 2 - ከመስከረም 11 - 12 🍀 ቡድን 3 - ከመስከረም 13 – 14 🍀 ቡድን 4 - ከመስከረም 18 – 19 የምትሳተፉ የዋናው መ/ቤት ሰራተኞች ከወዲሁ ለመርሃግብሩ ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን በስልጠናው ላይ ተሳትፎ አለማድረግ በሕብረት ስምምነቱ አባሪ ቁጥር አራት ገጽ 112 አንቀጽ 15.9 መሰረት እርምጃ የሚያስወስድ መሆኑን በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ➡️ በአራት ተከታታይ ዙሮች ውስጥ ጥሪ ያልተደረገላችሁና የስራ ቦታችሁ ዋ/መ/ቤት የሆነ ሰራተኞች በቅርቡ በማስታወቂያ በሚገለጸው የስም ዝርዝር መሰረት በአምስተኛ ዙር ከመስከረም 20 – 21 ድረስ ስልጠናውን የምትወስዱ መሆኑን እንገልፃለን፤ ➡️ ስማችሁ ከተገለጸበት ምድብ ውጭ ተሳትፎ ማድረግ የተከለከለ ነው፤ ➡️ አቴንዳንስ በተቀመጠው ቀንና ጊዜ ላይ ብቻ መፈረም ይኖርበታል፤ ➡️ በስልጠናው ለመሳተፍ የማያስችል ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ሲያጋጥም በስራ ክፍል ኃላፊዎች አማካይነት ሪፖርት መደረግ ይኖርበታል፤ ______ የዋና ሥ/አስፈፃሚ ጽ/ቤት

🎆 A New Year, A New Way of Seeing 🎆   As we welcome the New Year, Ethio Power Insight continues its journey as a space for ideas, experiences, reflection and shared learning.   May the year ahead bring us new approaches to familiar challenges, deeper insights into our work, greater curiosity to learn from one another, and the courage to turn knowledge into action.   Let us continue to learn from experience, reflect on what we do, share what we discover, and improve what we can.   Happy New Year to the entire Ethio Power family! 🎉 Learn • Reflect • Share • Improve

⚡️ . . . The Grand Ethiopian Renaissance Dam has become a major symbol of Ethiopia's development ambitions and its push for greater self reliance.  Former Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn reflects on what GERD represents for Ethiopia and the wider question of what Africa can build for itself. ____ Video credit: Susan Mwongeli

Repost from Derash | ደራሽ
📣 ለስራ ኃላፊዎችና ለሰራተኞች የቀረበ ጥሪ!! 🐲🐲🐲🐲 በዋናው መ/ቤት ከሚገኙ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር በደራሽ ጉዳይ ላይ ውይይት ማድረጋችን ይታወሳል… ስብሰባው ስለ ኢ.ኤ.ኃ. የማሕ
📣 ለስራ ኃላፊዎችና ለሰራተኞች የቀረበ ጥሪ!! 🐲🐲🐲🐲 በዋናው መ/ቤት ከሚገኙ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር በደራሽ ጉዳይ ላይ ውይይት ማድረጋችን ይታወሳል… ስብሰባው ስለ ኢ.ኤ.ኃ. የማሕበራዊ ድጋፍ አገልግሎት በይፋ የተነገረበት የመጀመሪያ መድረክ እንደመሆኑ እንደ ትልቅ milestone እንቆጥረዋለን… ስብሰባው እጅግ ወሳኝ ነበር… በርካታ ለውሳኔ ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦችም ተገኝተውበታል… በዕለቱ የተገኙ ተሰብሳቢዎች፦ ✅ ደራሽ ምን ምን ጉዳዮችን መደገፍ አለበት? ማንንሰ ማገልገል አለበት? ✅ የትኛው የሠራተኛ ወርሃዊ መዋጮ ፍትሐዊና ዘላቂ ነው? ✅ ከኢ.ኤ.ኃ (EEP) የሚጠበቀው የተቋማዊ ድጋፍ መጠን ስንት ቢሆን ተገቢ ነው? ✅ የትኛው የጥቅማጥቅም መጠን ትርጉም ያለውና ፍትሐዊ ነው? ✅ የአባልነት ብቁነትና አገልግሎት የማግኘት ሂደት እንዴት መመራት አለበት? ✅ ወደፊት አቅጣጫችን ምን መሆን አለበት? ምን ዓይነት «ደራሽ»ን መገንባት አለብን?   የሚሉ ሃሳቦች አንስተው ውይይት አድርገዋል…   ⏰ አሁን ደግሞ የእርስዎ ተራ ነው!     እነዚህን ጥያቄዎች በዋናው መሥሪያ ቤት ከሚገኙ ሠራተኞች ጋር ተወያይተንባቸዋል። አሁን ደግሞ በኃይል ማመንጫዎቻችን፣ በሪጅን ቢሮዎቻችን፣ በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎቻችን (Substations) እና በፕሮጀክት ሳይቶቻችን ላይ ከሚሰሩ ባልደረቦቻችን አስተያየት መስማት እንፈልጋለን።   🔗 እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን የመጠይቅ ማስፈንጠሪያ (Link) ተጠቅመው ጥያቄዎችን ለመሙላት ጥቂት ደቂቃዎችን ይውሰዱ።   https://forms.gle/4qvZTJFSZ6s5xAdcA     እርስዎና ባልደረቦችዎ የሚሰጡዋቸው ምላሾች ተሰብስበው ለመጨረሻው የደራሽ የውሳኔ ሃሳብ ሰነድ በግብዓትነት ያገለግላሉ።   🎁 ድምፅዎ ዋጋ አለው!   https://t.me/eepderash

🔔🔔🔔 በአዲስ አበባ ለምትገኙ የተቋማችን የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በሙሉ 📌 የደራሽ ምስረታ እውን ማድረጊያ ጉባኤ ጥሪ!! -- 🖥 ቀን ፡ ሐሙስ - 28/12/2018 ⏰ ሰዓት ፡ ከሰዓት 8፡
🔔🔔🔔 በአዲስ አበባ ለምትገኙ የተቋማችን የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በሙሉ 📌 የደራሽ ምስረታ እውን ማድረጊያ ጉባኤ ጥሪ!! -- 🖥 ቀን ፡ ሐሙስ - 28/12/2018 ⏰ ሰዓት ፡ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት 📍 ቦታ ፡ በተቋሙ ትልቁ አዳራሽ -- 💬 በዕለቱ በአገልግሎቱ ምስረታና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን ለምስረታ በተዘጋጀው ምክረ-ሃሳብ (Proposal) ላይ የተሳታፊዎችን ግብዓት የምንወስድበት የውይይት መርሃግብርም ተዘጋጅቷል፡፡ -- 🙏 በመሆኑም በዚሁ ዕለት በተቋማችን ትልቁ አዳራሽ ተገኝተው በደራሽ ምስረታ ጅማሬ ላይ የበኩልዎን አስተዋጽዎ እንዲያበረክቱ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡ -- የደራሽ ጊዜያዊ አደራጅ ኮሚቴ

. . . Quote of the day 💡 _____
. . . Quote of the day 💡 _____

🔖 . . . She doesn't climb to prove a point. She climbs because the job demands competence, and she has it in abundance. 💡 Every cable she pulls, every connection she secures, every fault she diagnoses—it's not about gender. 💡 It's about skill, precision, and the quiet confidence that comes from knowing exactly what she's doing. 💡 The grid doesn't care who fixes it. It just works when she's done. And that's all the statement she needs. _
"Current doesn't ask for permission — it asks for capability. And she delivers both."
_ 🔥 Yes - she can!! _

💡 ____ እግረመንገድ... ⚡️ ____ እነዚህን ሁለት Electrical terminologies በስራ ቦታችን ላይ እንደተመቸን ቀያይረን እንጠቀምባቸዋለን - Earthing እና Grounding... ለመሆኑ ልዩነታቸው ምንድነው?... የቃል ብቻ ወይስ የአተገባበርም?... ልዩነቱን አስባችሁበት ለማታውቁ ይህች አጭር ቪዲዮ በቂ ግንዛቤ እንደምትፈጥር ተስፋ እናደርጋለን... ____

EPI_Newsletter_001.pdf1.18 MB

🔔 ማስታወሻ ------- ትናንት ያጋራነውን የ Iberdrola ታሪክ ያነበቡ የገጹ ተከታታዮች አቀራረቡን በተመለከተ ጥሩ ጥሩ ሃሳቦች አጋርተውናል… ገጹ ላይ የማይፈለጉ ማስታወቂያዎችን ያስተዋሉም
🔔 ማስታወሻ ------- ትናንት ያጋራነውን የ Iberdrola ታሪክ ያነበቡ የገጹ ተከታታዮች አቀራረቡን በተመለከተ ጥሩ ጥሩ ሃሳቦች አጋርተውናል… ገጹ ላይ የማይፈለጉ ማስታወቂያዎችን ያስተዋሉም እንድናስተካክል ነግረውናል... (በነገራችን ላይ ገጹ ከእኛ ፍላጎት ውጪ የሚያመጣውን ማስታወቂያ ለማስቀረት ያለው አማራጭ ሁለት ነው - ተፈላጊው Boost level ላይ መድረስ አልያም Private ማድረግ፤ Boost level ላይ ለመድረስ የአንባቢያኑን ተሳትፎ ይፈልጋል፣ Private ማድረግ ደግሞ Search ሲደረግ የመገኘት ዕድሉን ያጠባል - ለማንኛውም መፍትሔ እንፈልጋለን)   ሌሎች ወዳጆች ደግሞ EPI_Newsletter የት አለ ብለውናል… -------- ሁላችሁንም እናመሰግናለን!! 🙏 --------- እነሆ - EPI_Newsletter 001 ⬇️   --------- We Strive to Create a Learning Organization!!

⭐️ INSIDE THE WORLD'S POWERHOUSES 🗓️ EPISODE 01 __________ ⚡️⚡️ IBERDROLA ⚡️⚡️ __________ Iberdrola ዋና መሥሪያ ቤቱ በ Bilbao, Spa
+2
⭐️ INSIDE THE WORLD'S POWERHOUSES 🗓️ EPISODE 01 __________   ⚡️⚡️ IBERDROLA ⚡️⚡️   __________   Iberdrola ዋና መሥሪያ ቤቱ በ Bilbao, Spain የሚገኝ ግዙፍ የኃይል አቅርቦት ድርጅት ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኤሌክትሪክ ኃይል በተለይም በ Renewable Energy ዘርፍ ከሚመሩ ታዋቂ ኩባንያዎች አንዱ ነው…     ኩባንያው የ125 ዓመታት ታሪክ ያለው ሲሆን፣ ከ25 ዓመታት በፊት Electrification፣ Renewable Energy እና Electricity Networks ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሚሄደውን አስፈላጊነት በማስላት የወሰደው ስትራቴጂያዊ እርምጃ ለገናናነቱ ትልቅ መሰረት እንደጣለ ይነገርለታል…     ዛሬ Iberdrola የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት፣ Networks፣ Renewable Energy፣ Storage እና የደንበኞች አገልግሎት ቢዝነሶችን በማቀናጀት በ14 አገራት ውስጥ ይንቀሳቀሳል…     ዋና ዋና ገበያዎቹ Spain፣ በ Scottish Power በኩል United Kingdom፣ በ Avangrid በኩል United States፣ በ Neoenergia በኩል Brazil፣ Mexico እና ሌሎች የ European ገበያዎች ናቸው።     🟢 Key Company Facts ✅ Headquarters: Bilbao, Spain   ✅ Ownership: Publicly listed private company   ✅ Core Focus: Electricity generation, Electricity networks, Renewable energy እና Electrification   ✅ Major Technologies: Wind, Solar, Hydro, Nuclear, Battery storage እና Pumped storage   ✅ Global Reach: በ14 አገራት ውስጥ ኤልክትሪክ አቅርቦት ስራ ይሰራል   ✅ Workforce: ከ 45,400 በላይ ሠራተኞች አሉት      🍀 Iberdrola in Numbers (ተቋሙን በውስን የቁጥሮች መስኮት እንመልከተው) ✅ 58,343 MW በ2025 ማጠቃለያ የኃይል ማመንጨት አቅሙ (Installed generation capacity) ደርሷል፤   ✅ 46,000+ MW የ Renewable አቅም አለው፤   ✅ 1.4 million km የ Electricity networks አለው፤   ✅ 45,400 ሠራተኞች ያስተዳድራል፤   ✅ €14.46 billion በ2025 ብቻ 14.46 ቢሊየን ዩሮ ለስራው ማስፋፊያ ኢንቨስት አድርጓል…   ሌላው አስደናቂ ቁጥር ደግሞ 85% ነው፤ ይህም በ2025 ማጠቃለያ ላይ ከካርቦን ልቀት ነፃ (Emission free) የነበረው የ Iberdrola የኢነርጂ አቅም ድርሻን ያሳያል…   ስለ ካምፓኒው ከዚህ በላይ በዝርዝር የማወቅ ፍላጎት ካላችሁ ከስር ያስቀመጥነውን EPI Newsletter - 001 እንድታነቡ እንጋብዛለን…   ❕ ከዝግጅቱ ጋር በተያያዘ ያላችሁን ማንኛውንም አስተያየት በገጹ DM (Direct message) በኩል ላኩልን… በሚቀጥለው Episode 2 የሌላ ግዙፍ ካምፓኒ ፕሮፋይል በ EPI Newsletter – 002 አማካይነት እናቀርብላችኋለን!!   ----   We Strive to Create a Learning Organization!!

🔵 "An organization's ability to learn, and translate that learning into action rapidly, is the ultimate competitive advantag
🔵
"An organization's ability to learn, and translate that learning into action rapidly, is the ultimate competitive advantage." — Jack Welch, Former Chairman & CEO of General Electric
  የገፃችንን ትኩረት ሰፋ ለማድረግ ባለን ፍላጎት የስያሜ፣ ዓርማና ዓላማ ማሻሻያ አድርገናል…   በዚህም መሰረት ስለ ዓለማችን የኃይል ተቋማት በተከታታይ የምናወራበትን ማስታወሻ ዛሬ እንጀምራለን… በምድሪቱ የኢነርጂ አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ጉልህ ሚና ያላቸውን ታላላቅ ተቋማትንም እንተዋወቃለን… በዚህ ሂደት መነሻ የሚሆኑ አጫጭር ታሪኮችን በ Fact file መልክ በጥቅል እናጋራችሁና ዝርዝር መረጃ ስትፈልጉ የምታነቡትን ማስታወሻ ደግሞ በ PDF ፎርማት እናስቀምጥላችኋለን…   ያለነው በኢነርጂ ተቋም ውስጥ እንደመሆኑ የሌሎች ዓለም አቀፍ ታላላቅ ተቋማትን ታሪክ ማወቅ ለስራችን መዘመንና ለተቋማችን ለውጥ ወሳኝ ነው ብለን እናምናለን…   የአሜሪካውን Walmart የመሰረተው Sam Walton አንድ ወቅት፡  
"Most everything I’ve done, I’ve copied from somebody else."
    ሲል ተናግሮ ነበር… አባባሉ የግለሰቡን ትህትና ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ለመማር ያለውንም ትጋት የሚያመለክት እንደመሆኑ ከተቋማዊ መማማር ጋር ተያይዞ በየጊዜው ይነሳል…  
"Foolish is the man who learns from his own mistakes. Wise is the man who learns from the mistakes of others." — Otto von Bismarck, Former Chancellor of Germany
  ይህም ሆኖ መማር ብቻውን ትርጉም አይኖረውም፤ የተማሩትን ለመተግበር መሞከር የበለጠ ጠቃሚ ነው… በዚህ ፈጣንና ውድድሩ ከባድ በሆነበት ዓለም አዳዲስ ነገሮችን ፈጥኖ መማርና ያወቁትንም እንደየ አውዱ መተግበር ጠንካራ ተቋም ለመፍጠር መሰረት ነው…  
"The only sustainable competitive advantage is an organization's ability to learn faster than the competition." — Peter Senge, Author of “The Fifth Discipline”
    🎓 አንብቡ፣ ሃሳብ ስጡ፣ ጠቃሚ ማስታወሻዎችን ተለዋወጡ!!     📌 We look outward to understand how others operate, inward to understand ourselves, and forward to identify capabilities that may matter tomorrow.   ----   We Strive to Create a Learning Organization!!

+1
. . . መስታወት የኃይል ምንጭ እንደሚሆን አስበው ያውቁ ኖሯል?... በዚህ ቪዲዮ - ሃገረ-ቻይና የመስታወቶችን ስብስብ ተጠቅማ እንዴት Energy እንደምታመርት ያያሉ... ነገርየው እንኳን የልጅነት ጨዋታችን አካል ነበር... ዛሬ የ Energy source መሆኑን ስንረዳ ቢገርመንም... _ This is a concentrated solar power (CSP) station in northwest China's Gansu Province, and it works completely differently from the panels on your roof. Instead of turning sunlight straight into electricity, it turns sunlight into heat — over 560°C, concentrated onto a receiver tower 260 meters tall. That heat melts salt, and the molten salt stores it like a giant thermal battery. Why does that matter?... Because solar's biggest weakness has always been timing. The sun goes down right when electricity demand goes up.  CSP solves that and keeps generating power long after sunset.

⚡️⚡️⚡️ CNN Africa's largest hydroelectric project is reshaping Ethiopia's energy future. CNN's Victoria Rubadiri visits the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) to see how the megaproject is generating power and transforming the region's energy landscape.

. . . Most organizations don’t lose their best people because of salary. They lose them because of decisions. When the wrong
. . . Most organizations don’t lose their best people because of salary. They lose them because of decisions. When the wrong people get promoted, three things happen: ☀️ Trust erodes ☀️ Motivation drops ☀️ High performers disengage And eventually… they leave. Promotion should never be a reward for loyalty, tenure, or politics. It should be based on competence, behavior, and leadership potential. One of the biggest leadership mistakes I see in organizations is promoting the best technical performer into a management role without asking a simple question: ❓ Can this person lead people — or only tasks?... Because management is not about being the best individual contributor. It’s about: ⭐️ Developing others ⭐️ Creating clarity ⭐️ Making decisions ⭐️ Taking responsibility ⭐️ Building trust ⭐️ Setting standards Poor promotion decisions don’t just create weak managers. They create organizational damage. People don’t leave companies. They leave leadership. Great leaders understand something critical: ✅ Promotion is culture. ✅ Promotion is strategy. ✅ Promotion is retention. 🗓️🗓️🗓️ Choose wisely. ✅✅✅ _ _ _ Robertson Hunter Stewart

🍀 ክፍል 7 (የመጨረሻ ክፍል) የነገው የኃይል ሥርዓት… . . ለረጅም ጊዜ የኃይል ሥርዓቶች ሲቀረጹ የነበረው በዋናነት በታሪካዊ ተሞክሮዎች ዙሪያ ነበር… ያለፈው ዓመት የዝናብ መጠን፣ ያለፉት ጊዜ
🍀 ክፍል 7 (የመጨረሻ ክፍል) የነገው የኃይል ሥርዓት… . . ለረጅም ጊዜ የኃይል ሥርዓቶች ሲቀረጹ የነበረው በዋናነት በታሪካዊ ተሞክሮዎች ዙሪያ ነበር… ያለፈው ዓመት የዝናብ መጠን፣ ያለፉት ጊዜያት የኤሌክትሪክ ፍላጎት፣ ያለፉት አምስት ዓመታት የማመንጨት መጠን ወዘተ…   ነገር ግን ታሪክ ሁልጊዜ ራሱን አይደግምም… የአየር ንብረት መለዋወጥ (Climate variability)፣ ተቀያያሪ ፍላጎት፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና በፍጥነት የሚለዋወጠው የኃይል ገጽታ ተጨማሪ ነገር ይፈልጋሉ… እሱም አስቀድሞ የመተንበይና የመረዳት አቅም ነው… 🍎 ከግሪድ (Grid) ወደ አስተዋይ (Intelligent) ሥርዓት የተለመደው የኃይል ሥርዓት በዋናነት ኤሌክትሪክን ከማመንጫዎች ወደ ማስተላለፊያዎች ያጓጉዛል… እየመጣ ያለው አዲሱ የኃይል ሥርዓት ግን ከዚያ ይበልጥ ብዙ ነገር ያደርጋል… It senses - It communicates - It analyzes - It predicts - It responds.   የስማርት ግሪድ (Smart grid) ፍልስፍና መሠረት ይህ ነው!!...   ሴንሰሮች (Sensors) መረጃ ይሰጣሉ፣ የመገናኛ መረቦች ሥርዓቱን ያገናኛሉ፣ ዲጂታል መሰረተ ልማቶች መረጃዎችን በአንድ ላይ ይሰበስባሉ፣ ትንተናዎች (Analytics) ሁነቶችን እንድናውቅ ይረዱናል፣ አውቶሜሽን (Automation) ፈጣን ውሳኔዎችን ይደግፋል፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence / AI) ሰዎች ሊስቷቸው የሚችሏቸውን ትስስሮች እና ስጋቶች ለመለየት ይረዳል… The result is not simply a more digital grid. It is a more aware grid.   💡 የኃይል እይታ (Power Insight) የነገው የኃይል ሥርዓት የሚገለጸው በሚኖረን የማመንጨት መጠን ብቻ ሳይሆን፣ በተፈጥሮ፣ በቴክኖሎጂ እና በሰዎች መካከል ያለውን ትስስር ምን ያህል በአስተዋይነት፣ በዘላቂነት እና በህብረት ማስተዳደር እንችላለን በሚለው ነው…   🟢 ትልቁ ምስል የወደፊቱ ጊዜ ዝም ብሎ የሚከሰት አድርገን እናስባለን… ነገሩ ግን እንደዚያ አይደለም… ዛሬ በምናደርጋቸው ነገሮችና በምናሳልፋቸው ውሳኔዎች የወደፊቱን እንፈጥረዋለን…   💸 ጉዞው ይቀጥላል... የወደፊቱ ጊዜ ድርቅንም፣ የዝናብ ወቅትንም ይዞ ይመጣል… አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና አዳዲስ ፈተናዎችንም ያመጣል… ያልተጠበቁ ሁከቶችን እና አዳዲስ ዕድሎችንም ይፈጥራል… የሚመጣውን ሁሉ መቆጣጠር አንችልም… ነገር ግን የተሻለ ዝግጅት ማድረግ እንችላለን… መማር እንችላለን፣ መላመድ እንችላለን፣ የኃይል ምንጮቻችንን ማበዛት እንችላለን፣ በህብረት መስራት እንችላለን፣ ከግል ኃላፊነታችን ባሻገር በማሰብ ጠቅላላውን ሥርዓት ማየት እንችላለን… ምናልባትም የመቋቋም አቅም (Resilience) ማለት ይሄው ነው - ነገ ምን እንደሚያመጣ በጥቅሉ ባናውቅም፣ የሚመጣውን ለመጋፈጥ ብቁ ሆነን መገኘት!... ☎️ መውጫ ሃሳብ…   የኃይል ዘርፍ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በምናመርተው የኤሌክትሪክ መጠን ብቻ ሳይሆን፣ ያንን ኤሌክትሪክ በምን ያህል ብልህነት እናመርታለን፣ እናከማቻለን፣ እናጓጉዛለን እንዲሁም ጥቅም ላይ እናውላለን በሚለው ጭምር ነው…     🎯 ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence)፡ በሰለጠነው ዓለም ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የኃይል ሥርዓቶች አስቀድመው እንዲተነብዩ፣ አሠራራቸውን እንዲያሻሽሉ እና ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል… የታዳሽ ኃይል ምርትንና የኤሌክትሪክ ፍላጎትን አስቀድሞ ከመተንበይ ጀምሮ፣ የመሳሪያዎችን ብልሽት እስከመለየትና የኃይል ማሰራጫ መረብ (Grid) ሥራዎችን እስከመደገፍ ድረስ ያግዛሉ…     🎯 የኃይል ማከማቻ (Next-Gen Battery Energy Storage Systems)፡ የወደፊቱ የኃይል ማሰራጫ መረብ ኃይል ማጓጓዝ ብቻ ሳይሆን ማከማቸትም ያስፈልገዋል… ዘመናዊ ባትሪዎችና አዳዲስ የኃይል ማከማቻ ቴክኖሎጂዎች ኤሌክትሪክን በጊዜ ሂደት በማሸጋገር፣ ተለዋዋጭ የታዳሽ ኃይል ምንጮችን ለማመጣጠን እንዲሁም ሥርዓቱን የበለጠ ተለዋዋጭና ጽኑ ለማድረግ ያስችላሉ…     🎯 የኃይል መረብ አቅም ማሳደጊያ ቴክኖሎጂዎች (Grid-Enhancing Technologies)፡ የወደፊቱ ጊዜ ተጨማሪ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን በመገንባት ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም… የላቀ የኃይል ፍሰት ቁጥጥር፣ የኃይል መረብ ክትትል እና ሌሎች ዲጂታል መፍትሔዎች ያሉዋቸው ቴክኖሎጂዎች መጠቀምም እንጂ… እነዚህን ከተጠቀምን ከኃይል ማሰራጫ መረባችን የበለጠ አቅም እንድናወጣ፣ አስተማማኝነትን እንድናሻሽል እንዲሁም ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች በበለጠ ብልህነት ምላሽ እንድንሰጥ ይረዱናል…     🎯 የሚማማር ተቋም (The Learning Organization)፡ ቴክኖሎጂ ብቻውን የኃይል ዘርፉን ሊለውጠው አይችልም… ለውጡን የሚያመጡት ሰዎች ናቸው… የወደፊቱ ጊዜ ሁልጊዜ የሚማሩ፣ እውቀትን የሚያካፍሉ፣ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች ጋር አብረው የሚሰሩ፣ መረጃዎችን በሚገባ የሚያቀናብሩ፣ ፈጠራን የሚቀበሉ እና ከለውጥ ጋር የሚላመዱ ባለሙያዎችን ይፈልጋል… ተማሪ ተቋም ሰዎችን ለዛሬው ቴክኖሎጂ ብቻ አያዘጋጅም - ይልቁንም የነገውን ቴክኖሎጂ ለመማር ዝግጁ ያደርጋቸዋል…   ------
The energy transition is therefore not simply a transition from hydro to solar or from conventional grids to smart grids. It is a transition: from reactive to predictive, from isolated to interconnected, from fixed to flexible, from consuming knowledge to continuously creating it. The power system of tomorrow will be intelligent because of technology, resilient because of diversity, and sustainable because of people who never stop learning.
  -----   በያለንበት እንበርታ!!   ------   We Strive to Create a Learning Organization!!