EB Media
Kanalga Telegram’da o‘tish
👉መዝናኛ 👉ዜና 🗣 Our YouTube Channel https://youtube.com/@ebmedia123?si=3Zgov2sCJcx1Qla4
Ko'proq ko'rsatish2 519
Obunachilar
+624 soatlar
+2757 kun
+24930 kun
Postlar arxiv
2 519
🇪🇹 “ለአፍሪካ ዋንጫ ካላለፍን ስራውን እለቃለሁ” — ዮሐንስ ሳህሌ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ ካላለፈ ከዋና አሰልጣኝነታቸው እንደሚለቁ ዮሐንስ ሳህሌ ተናገሩ።
“ሌላ አሰልጣኝ ይመጣል፤ ስምምነት አለን” ሲሉም ገልጸዋል።
2 519
በትግራይ ክልል የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት ዛሬ አርብ መቛረጡን ተጠቃሚዎች አስታወቁ።
ሳፋሪኮም ተቋርጧል።
አገልግሎቱ የታጎለው ከሕጋዊ ፓርቲነት የታገደዉ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፣የግል የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎት ሰጭ ሳፋሪኮምና መንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮም የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያቋርጡ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ነው ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ያላቸውን አራት ሰዎችና ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
አንድ የሮይተር ምንጭ ህወሓት የሞባይል እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ያዘዘው የመንግሥት ወታደሮች በውጊያ ድሮኖችን ሲጠቀሙ የሞባይል ኔትዎርኮችን እንዳያገኙ የተጠቀመበት ስልት አካል ሳይሆን እንዳልቀረ ተናግረዋል።
አዩዘሀበሻ
2 519
🚨 “ከፌዴራል ትዕዛዝ ካልመጣ አንቋርጥም” ያሉ የቴሌኮም ሰራተኞች ታሰሩ ተባለ!
በትግራይ የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክና ኢንተርኔት መቋረጡን ተከትሎ፣ አገልግሎቱን ለማቋረጥ ፈቃደኛ ያልሆኑ የቴሌኮም ሰራተኞች መታሰራቸው ተዘግቧል።
በተጨማሪም ዋናው የቴሌኮም መስመር መቆረጡና ሳፋሪኮም በአንዳንድ አካባቢዎች ተደራሽ መሆኑ ተገልጿል።
⚠️ ማስታወሻ፦ የሰራተኞች እስርና የመስመሩ መቆረጥ የሚሉት መረጃዎች ከአካባቢ ምንጮች የተገኙ መሆናቸው ተገልጿል፤ እስካሁን በተጨማሪ ኦፊሴላዊ ማረጋገጫ አልተጠቀሰም።
💬 ስለጉዳዩ ምን ይመስላችኋል? አስተያየታችሁን ያጋሩ።
2 519
⚠️ የጉዞ ማስጠንቀቂያ
በሸዋ ሮቢትና ደብረ ሲና መካከል የተኩስ ድምፅ መኖሩን የገለጸ መልእክት ደርሶናል።
ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ ወይም ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የምትጓዙ አሽከርካሪዎችና መንገደኞች፣ የመንገዱን ሁኔታ አረጋግጣችሁ በጥንቃቄ እንድትጓዙ መልእክት ተላልፏል።
📌 ማስታወሻ፦ ይህ መረጃ በውስጥ ከደረሰን መልእክት የተገኘ ሲሆን፣ እስካሁን በእኛ በኩል በግልፅ ምንጭ ያልተረጋገጠ ነው። ተጨማሪ መረጃ ሲገኝ እናሳውቃለን።
📲 ለተጨማሪ መረጃዎች፦
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
2 519
🚨 በትግራይ ውጥረት መባባሱን ተከትሎ ነዋሪዎች ሸቀጦችን በብዛት እየገዙ መሆኑ ተዘገበ
በትግራይ ክልል በቅርቡ የተፈጠረውን ውጥረትና ግጭት ተከትሎ፣ በመቀለና በአዲግራት ከተሞች ነዋሪዎች ግጭቱ ሊባባስ ይችላል በሚል ስጋት ምግብና ሌሎች መሠረታዊ የእለት ተጠቃሚ ዕቃዎችን በብዛት እየገዙ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
የመቀለ ነዋሪዎች ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ በመጠየቅ፣ አስፈላጊ የሆኑ ሸቀጦችን በተቻለ መጠን እየሸመቱ መሆናቸውን ገልጸዋል። አንድ ነዋሪ መሠረታዊ ፍላጎቶችን ማግኘትና መግዛት እየከበደ መምጣቱን ተናግረዋል።
በአዲግራትም ሰዎች በፍርሃት ምግብና ሌሎች ሸቀጦችን በብዛት በመግዛታቸው አንዳንድ የሱቅ መደርደሪያዎች ባዶ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለሮይተርስ መናገራቸው ተገልጿል። የአስፈላጊ መድኃኒቶች እጥረትና የዋጋ መጨመርም እንዳለ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በመቀለ የጸጥታ ኃይሎች መንቀሳቀስና የድሮን ድምጽ መሰማት ለሕዝቡ ስጋት መፍጠሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በተከሰተው ጦርነት ወቅት የታየው የምግብና የመድኃኒት እጥረት እንዳይደገም ስጋት መኖሩም ተገልጿል።
በሌላ በኩል፣ ተባብሶ የመጣው ውጥረት ወደ ግጭት መሸጋገሩን ተከትሎ በአማራና አፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ውጊያዎች መካሄዳቸው ተዘግቧል።
የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ህብረት ተፋላሚ ወገኖች ከግጭት እንዲታቀቡና በፕሪቶሪያ ስምምነት ወደተመሰረተው የሰላም ሂደት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።
📌 ምንጭ፦ Reuters / BBC
📲 ለተጨማሪ መረጃዎች፦
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
#EBMedia #Ethiopia #Tigray #News
2 519
🚨 መቀሌና አካባቢዋ የኔትወርክ መቋረጥ ተመዘገበ
በመቀሌ ከተማና አካባቢዋ የኢትዮ ቴሌኮም የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በተለያዩ አካባቢዎች መቋረጡ ተሰምቷል።
እንደ አካባቢው መረጃ፣ ችግሩ በከተማዋ ሁሉም አካባቢ ሳይሆን በተለያዩ ስፍራዎች የታየ ሲሆን፣ የሳፋሪኮም አገልግሎት ግን እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
እስካሁን ችግሩን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ይፋዊ ማብራሪያ አልተሰጠም።
2 519
ጀነራል ታደሰ ወረደ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። የቤተሰብ ምንጮች ጀነራሉ ለሻብያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ በሚል ስጋት ውስጥ ወድቀዋል።
📲 ለተጨማሪ መረጃዎች፦
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
2 519
+7
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ በጅቡቲ ተገኝተው፣ ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ እና ከዳንጎቴ ግሩፕ መስራች አሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን ጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ አዲስ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ፕሮጀክትን ይፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ በሁለቱም ጫፎች የሚገነቡ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናሎችን ያካተተ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ ትብብር እንደሚተገበር አመልክተዋል።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ፕሮጀክቱ የነዳጅ ማጓጓዣ ወጪንና መዘግየትን በመቀነስ የኢትዮጵያን የኃይል ዋስትና ለማጠናከር እንዲሁም በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለውን የንግድ መስመር የበለጠ ፈጣንና ዘላቂ ለማድረግ ያግዛል።
ፕሮጀክቱ ከነዳጅ ማጓጓዣ መሠረተ ልማት ባለፈ፣ የአፍሪካውያንን ኢንቨስትመንትና የጋራ ልማት ለማሳደግ የታለመ ሰፊ ኢንቨስትመንት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ/ም
2 519
latest update
የላሊበላ ኤርፖርት በረራዎችን ዛሬ ሰረዘ፤ በኤርፖርቱ ቅርብ ርቀት የፋኖ ሃይሎችና የመከላከያ ሰራዊት ውጊያ ላይ ናቸው። more to follow
2 519
በወልቃይት አቅጣጫ አዲስ ውጊያ‼️
በተከዜ ወንዝ አቅጣጫ በምዕራብ ግንባር አዲስ ከባድ ውጊያ መቀስቀሱ ተገለጸ።
በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ (ራያ ዋግኽምራ አፋር ሰሜን ወሎ)እየተደረገ ካለው ውጊያ ባሻገር፣ ዛሬ በምዕራብ ግንባር በተከዜ ወንዝ አቅጣጫ አዲስና ከባድ ውጊያ መቀስቀሱን ከግንባር የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።
ከሌሊት ጀምሮ በአየር እና በድሮን የታገዘ ድብደባ ሲደረግበት በነበረው በዚህ ግንባር፣ በአሁኑ ሰዓት ከወልቃይት ወደ ትግራይ በሚወስደው መስመር በተከዜ ወንዝ በኩል በሁለት አቅጣጫዎች ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል።
የመረጃ ምንጮች እንደጠቆሙት ውጊያው እየተካሄደባቸው ያሉት ሁለቱ ግንባሮች፦
* የጸሊሞይ ግንባር፦ በዋናው ድልድይ በኩል በወልቃይት እና በትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች፣ እና
* የጓል ተከዜ ግንባር፦ በተከዜ ወንዝ ዳርቻዎች ናቸው።
በእነዚህ ግንባሮች እየተካሄደ ባለው ከባድ ውጊያ እስካሁን ድረስ የደረሰው የሰው እና የንብረት ጉዳት አልታወቀም።
2 519
🥺 “በልጅነቴ ወላጆቼ ሞተዋል” — ቢኒያም ሽብሬ
“እኔም የአርባምንጭ ልጅ ነኝ። በልጅነቴ ወላጆቼን አጥቻለሁ። አርባምንጭን በተደጋጋሚ ጎብኝቻለሁ። አሁንም በድጋሚ እንድመጣ ስለጋበዘኝ ማስተር አገረሰላምን አመሰግናለሁ። የአርባምንጭ ነዋሪዎችም ላደረጉልን ደማቅ አቀባበል ከልብ አመሰግናለሁ።” ❤️
#EthioFightNight #BinyamShibre #Arbaminch #VisitGamo
2 519
🏠❤️ ኦብሴና እናቷ የመኖሪያ ቤት ተሰጣቸው!
የኦብሴን አሳዛኝ ጉዳይ ተከትሎ በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ የነበሩት ኦብሴና እናቷ ወይዘሮ ማሜ ባርሴሳ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የመኖሪያ ቤት ስጦታ አበረከቱላቸው።
ይህ ለእናትና ልጅ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ፣ የተስፋና የመረጋጋት መጀመሪያ ሆኗል። ❤️
🙏 እንኳን ደስ አላችሁ! አዲሱ ቤታችሁ የሰላም፣ የደስታና የተስፋ ቤት ይሁንላችሁ።
2 519
"ጦርነት የሞቀ ቤት ቁጭ ብሎ ሰበር
ዜና እንደማንጋጋት ቀላል አይደለም"
ጦርነት አስቀያሚ ነው። እግዚአብሔር ሰላሙን ያውርድልን።
ጦርነትን አልደግፍም። ጦርነትን አላውቀውም። ጥሩ የሚባል ጦርነት ግን የለም። መጥፎ የሚባል ሰላምም አላውቅም። በተለይ የርስበርስ ጦርነት የወጣቱን ነፍስ ይበላል። አገር ይበላል። ተስፋን ይበላል። በቀላሉ ስልክህን እየጠነቆልክ ቀነደሸው፣ ለበለበው፣ ሸኘው....እንደምትለው ቀላል አይደለም። ጦርነትን እንደ እግር ኳስ ለመመልከት የምትቋምጡ ፈጣሪ ልባችሁን ያብራላችሁ።
ጦርነት የሞቀ ቤት ቁጭ ብሎ ሰበር ዜና እንደማንጋጋት ቀላል አይደለም። በዚህም በዚያም ከሚወድቁ ዜጎቻችን ጀርባ ህልም አለ፤ ቤተሰብ አለ፤ ደረሰልኝ የሚል እናትና አባት አለ። በጦርነቱ ከሚወድቀው ሰው ጀርባ አሳዛኝ ታሪክ አለ።
እና እባካችሁ ለሰላም ዕድል ስጡ!! ብዙ ሰው አልቆ ወደ ጠረጴዛ ከምትሄዱ፤ ክቡሩ ሰው ሳይወድቅ ለንግግር ተዘጋጁ። አባቶች ጩሁ። የሃይማኖት አባቶች በዚያም በዚህም ለመገዳደል የቆሙ ኃይሎችን መሃል ገብታችሁ መጀመሪያ እኛን ግደሉ በሉ።
እንደ ግለሰብ ያለኝ አቅም ይኼ ብቻ ነው።
ጌታ ያስበን
Daniel Tefera
2 519
🕊️🇪🇹 የሰላም ጥሪ — ኢትዮጵያ ለሁላችንም!
“የጦርነት ጉሰማ ይብቃ! ሰላም ለኢትዮጵያ እና ለህዝቦቿ!”
የተለያዩ አመለካከትና ጥያቄዎች ሊኖሩን ይችላሉ፤ ነገር ግን ልዩነታችንን በጦርነት ሳይሆን በውይይት፣ በመቻቻልና በሰላማዊ መንገድ እንፍታ።
ኢትዮጵያዊ የሆንን ሁላችን የሰላም ድምፃችንን እናንሳ። የትኛውም ክልል፣ የትኛውም ማህበረሰብ፣ የትኛውም ወገን በጦርነት እንዳይጎዳ በጋራ እንስራ።
የድሃ ልጅ ደም አይፍሰስ፤ እናቶች አይልቀሱ፤ ሀገር አትውደም።
🤝 ልዩነታችንን በውይይት
🤝 ችግሮቻችንን በመግባባት
🤝 ወደፊትን በሰላም እንገንባ።
አንድ ሀገር፣ የተለያዩ ህዝቦች፣ አንድ የሰላም ጥሪ። 🇪🇹🕊️
ሰላም ለኢትዮጵያ!
ሰላም ለህዝባችን!
ሼር ሼር ሼር
📲 ለተጨማሪ መረጃዎች፦
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
2 519
😳 “16 ዓመታት ምግብና ውኃ አልወሰድኩም” — ሙሉወርቅ አምባው
በ10 ዓመቷ የምግብ ፍላጎቷ ከተዘጋ በኋላ፣ ላለፉት 16 ዓመታት ምንም ምግብና ውኃ ሳትወስድ እንደኖረች የምትናገረው ሙሉወርቅ አምባው ታሪኳ ብዙዎችን አስደንቋል።
እርሷ የመጨረሻ የተመገበችው ምስር ወጥ በእንጀራ እንደነበር ትናገራለች። በኢትዮጵያና በውጭ ሀገራት ሕክምናዊ ምርመራዎችንም እንዳደረገች ታስረዳለች።
የታሪኳ በስፋት የታወቀው የጉዞ ቪዲዮ አዘጋጁ ድሩ ቢንስኪ ወዳለችበት ሄዶ የዕለት ተዕለት ሕይወቷን ካሳየ በኋላ ነው።
⚠️ ሆኖም 16 ዓመታት ያለ ምግብና ውኃ መኖሯን የሚያረጋግጥ በሳይንሳዊ ቁጥጥር የተደረገ የሕክምና ማስረጃ እስካሁን አልቀረበም።
#Ethiopia #MuluworqAmbaw #EBMedia
