A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
📈 تحلیل کانال تلگرام A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
کانال A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU (@aahdabofficial) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 33 817 مشترک است و جایگاه 315 را در دسته املاک و مستغلات و رتبه 1 080 را در منطقه أثيوبيا دارد.
📊 شاخصهای مخاطب و پویایی
از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 33 817 مشترک جذب کرده است.
بر اساس آخرین دادهها در تاریخ 24 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 758 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -16 بوده و همچنان دسترسی گستردهای حفظ شده است.
- وضعیت تأیید: تأیید نشده
- نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 20.45% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 14.36% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب میکند.
- دسترسی پستها: هر پست به طور میانگین 6 914 بازدید دریافت میکند. در اولین روز معمولاً 4 857 بازدید جمعآوری میشود.
- واکنشها و تعامل: مخاطبان بهطور فعال حمایت میکنند؛ میانگین واکنش به هر پست 0 است.
📝 توضیح و سیاست محتوایی
توضیحی برای کانال ارائه نشده است.
به لطف بهروزرسانیهای پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 25 اکتبر, 2026)، کانال همواره بهروز و دارای دسترسی بالاست. تحلیلها نشان میدهد مخاطبان بهطور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته املاک و مستغلات تبدیل کردهاند.
در حال بارگذاری دادهها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 25 اکتبر | 0 | |||
| 24 اکتبر | 0 | |||
| 23 اکتبر | +7 | |||
| 22 اکتبر | +6 | |||
| 21 اکتبر | +6 | |||
| 20 اکتبر | +29 | |||
| 19 اکتبر | +29 | |||
| 18 اکتبر | +22 | |||
| 17 اکتبر | +7 | |||
| 16 اکتبر | +8 | |||
| 15 اکتبر | +10 | |||
| 14 اکتبر | +17 | |||
| 13 اکتبر | +20 | |||
| 12 اکتبر | +15 | |||
| 11 اکتبر | +11 | |||
| 10 اکتبر | +50 | |||
| 09 اکتبر | +29 | |||
| 08 اکتبر | +21 | |||
| 07 اکتبر | +78 | |||
| 06 اکتبر | +31 | |||
| 05 اکتبر | +69 | |||
| 04 اکتبر | +26 | |||
| 03 اکتبر | +61 | |||
| 02 اکتبر | +117 | |||
| 01 اکتبر | +23 |
| 2 | በተመጣጣኝ ዋጋ የፍጆታ ዕቃዎች የት ማግኘት ይችላሉ?
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ነዋሪው ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት መጠነ ሰፊ ተግባራትን እያከናውን ይገኛል ።
በተለይም የዕለት ተዕለት ፍጆታዎች በመዲናዋ በሚገኙ የተለያዪ ቦታዎችና አማራጮች በቀላሉና በተመጣጠነ ዋጋ ማግኝት እንዲቻል ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎች በመስራት ላይ ይገኛል።
በዚህም ነዋሪው የፍጆታ ምርቶችን የሚያገኙባቸው አማራጭ ቦታዎች የተቀመጡ ሲሆን ከ292 በላይ የሚሆኑ በከተማዋ ሁሉም አካባቢ የሚገኙ የሸማች ማህበራት የስጋ አቅርቦት ማዕከላት፣ የላፍቶ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 የገበያ ማዕከል ፣ የቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርት ማቅረብያ ማዕከል፣ የኮልፌ የግብርና ምርቶች መሸጫ የገበያ ማዕከል እንዲሁም የለሚ ሁለገብ የገበያ ማዕከል፣ የለሚ ኩራ የግብርና ምርቶች ገበያ ማዕከል፣ የአቃቂ የሰብል ምርት የገበያ ማዕከል፣ የአቃቂ የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ጨምሮ የካ ጉራራ የገቢያ ማዕከል እና በ119ኙም ወረዳዎች የሚገኙ 282 የሰንበት ገበያዎች ግብይት መፈፀም ይቻላል ።
የተለያዩ ምርቶችን መሸመት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ወደሚገኝ ገበያ ጎራ ብሎ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት ይችላል ። | 5 547 |
| 3 | የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትከከተማዋ አስፈጻሚ አካላት ጋር የግብ ስምምነት ተፈራረመ።
ምክር ቤት ጽ/ቤት — የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት፥ ክትትልና ቁጥጥር ከሚያደርግባቸው አስፈጻሚ አካላት ጋር የበጀት ዓመቱ ዕቅድ ዋና ዋና ግቦች ስምምነት ተፈራረመ።
"የጋራ ግብ፤ የተቀናጀ ተግባር፤ የላቀ ውጤት" ለማምጣት ባለመው በዚህ የየግብ ስምምነት መፈራረሚያ መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሪት ፋዒዛ መሐመድ እንደገለጹት፤ የስምምነቱ ዋና ዓላማ ለከተማችንና ለህዝባችን የተደመረ አቅም በመፍጠር፣ ተቀናጅቶና በአንድነት ለመሥራት የሚያስችል የጋራ ግብና አቋም ለመያዝ እንደሆነ ተናግረዋል።
ምክትል አፈ-ጉባኤዋ አክለውም፥ "በ4ኛው ዙር ምክር ቤታችን የሥራ ዘመን ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር ለመፈጸምና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት ካለፈው የሥራ ዘመን የወሰድናቸውን መልካም ልምዶች በማጎልበትና በማሣደግ ከሕዝባችንና ከአስፈጻሚ አካላት ጋር የጋራ ግብ ይዘን መሥራት ይኖርብናል ብለዋል። ይህም የከተማችንን ራዕይ እውን ለማድረግና የሕዝቡን እርካታ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ወሳኝ መሆኑን አስምረውበታል።
በሥነ-ሥርዓቱ ማጠቃለያም የምክር ቤቱ ሁሉም ቋሚ ኮሚቴዎች ክትትልና ቁጥጥር ከሚያደርጉባቸው አስፈጻሚ ተቋማት ጋር በበጀት ዓመቱ ዋና ዋና ግቦች ዙሪያ የስምምነት ሰነዱን ተፈራርመዋል። | 7 032 |
| 4 | بدون متن... | 6 705 |
| 5 | بدون متن... | 6 697 |
| 6 | ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪን ለመቆጣጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተናል!
በከተማችን በመሠረታዊ የዕለት ተዕለት ፍጆታዎችና በቤት ኪራይ ላይ እየታዩ ያሉ ምክንያታዊ ያልሆኑ የዋጋ ጭማሪዎችን ለመቆጣጠርና የዜጎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል እየተወሰዱ ባሉ የአጭርና የረጅም ጊዜ መፍትሔዎች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል።
በውይይቱ የሥጋ፣ የምግብ ዘይት፣ የዳቦ፣ የታሸገ ውኃና የቤት ኪራይ ዋጋዎች ላይ የሚታዩ ያልተገቡ ጭማሪዎች ተገምግመዋል። ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታትና ፍትሐዊ የገበያ ሥርዓትን ለማረጋገጥም የሚከተሉት ዋና ዋና እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ።
1. የምርት አቅርቦትን ማሳደግ
የመሠረታዊ ፍጆታ ምርቶችን አቅርቦት በመጨመር የዋጋ መረጋጋትን ለማምጣትና ሸማቹ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ሁኔታዎችን እናመቻቻለን።
2. የገበያ ማዕከላትን ማስፋፋትና የደላላ ሰንሰለትን ማሳጠር
አምራቾችንና ሸማቾችን በቀጥታ የሚያገናኙ የገበያ ማዕከላትን በከተማዋ መግቢያ በሮች ላይ በማቋቋም ምርቶች በቀጥታ ለሸማቾች እንዲቀርቡ እየሠራን ነው። ሕብረተሰቡም ከእነዚህ የገበያ ማዕከላት በመገበያየት የተመጣጣኝ ዋጋ አማራጮችን እንዲጠቀም እናበረታታለን።
3. የሸማቾች ማኅበራትን ማጠናከር
የሸማቾች ማኅበራት የምርት አቅርቦትና ጥራት እንዲያድግ ተጨማሪ 500 ሚሊዮን ብር የሚያዝ ተዘዋዋሪ ፈንድ (Revolving Fund) መድበናል።
4. የእሑድ ገበያዎችን ማስፋፋት
ሸማቾች መሠረታዊ የዕለት ተዕለት ፍጆታዎቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ የእሑድ ገበያዎችን እናስፋፋለን፤ አቅርቦታቸውንም እናጠናክራለን።
5. ቁጥጥርንና የሕግ ማስከበርን ማጠናከር
የገበያ ሥርዓትን በሚጥሱና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ ቁጥጥርና የሕግ ማስከበር ሥራችንን እናጠናክራለን።
6. የቤት ኪራይን በተመለከተ የአከራይና የተከራይ ግንኙነት በሕግ፣ በውል ስምምነትና በጋራ ኃላፊነት መመራት አለበት። ዜጎች መብታቸውን በሕጋዊ መንገድ እንዲያስከብሩና የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በማስረጃ እንዲያቀርቡ እናበረታታለን። በተመሳሳይም ተደራሽና ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ማሳደግ ዘላቂ መፍትሔ እየተሰራ ነዉ።
በውይይታችንም የአቅርቦት ችግሮችን ከመሠረቱ በመፍታት፣ ፍትሐዊ የገበያ ሥርዓትን በማረጋገጥና ሕገወጥ የዋጋ ጭማሪዎችን በመቆጣጠር የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል።
ሕብረተሰቡ አስተዳደሩ ባመቻቻቸው የሸማቾች ማኅበራትና የእሑድ ገበያዎች በመገበያየት የኑሮ ወጪውን እንዲቀንስ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን።
በተጨማሪም ዜጎች ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ወይም የገበያ ሕግ ጥሰት ሲያጋጥማቸው በቂ ማስረጃ በማቅረብ ለሚመለከተው የከተማ አስተዳደር አካል ሪፖርት እንዲያደርጉ፣ ከተረጋገጠ መረጃ ውጭ ወሬዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡና ፍትሐዊ የገበያ ሥርዓትን በጋራ እንዲደግፉ አሳስባለሁ።
የዜጎችን የኑሮ ጫና ማቃለልና ፍትሐዊ የገበያ ሥርዓትን ማረጋገጥ የጋራ ኃላፊነታችን ነው!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ | 7 412 |
| 7 | بدون متن... | 6 702 |
| 8 | ከደሳሳ ጎጆ ወደ ዘመናዊ መኖሪያ የተሸጋገረው የአቃቂ ቃሊቲ ነዋሪዎች ሕይወት
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በበጎነት መንደር አዲስ ቤት የተረከቡ ነዋሪዎች ከዓመታት እንግልት በኋላ ያገኙትን እፎይታ እና ደስታ ለኤ ኤም ኤን አጋርተዋል።
በአቃቂ ቃሊቲ አዲስ በተገነባው የበጎነት መንደር ቤት ከተረከቡት መካከል እናት አልማዝ አበራ አንዷ ናቸው፡፡ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት የኖሩበት የቀበሌ ቤት በዕድሜ ርዝማኔ እጅግ አርጅታ ዘማለች፡፡
"ቤቷ አረጀች፤ ምስጥ ወጥቶባት እስከ ግድግዳው ድረስ በላው። በምን አቅማችን እንሥራው? የምናገኛት ገቢ ከእጃችን ወደ አፋችን ናት..." ይላሉ እናት አልማዝ ያለፉትን ችግር ሲያስታውሱ። በክረምት ደግሞ የጎርፍ ስጋቱ በእጥፍ ይጨምራል።
ይህ የእናት አልማዝ ብቻ ሳይሆን የጎረቤታቸው የወይዘሮ ሙሉ ታደሰም መከራ ነበር። በጠበቧ ቤት ውስጥ በርካታ ልጆችና የልጅ ልጆች ተሰብስበው ነበር የሚኖሩት፡፡ በዘመመችው ጎጆ የሚበረታው ቅዝቃዜ ለህመም ተጋላጭ ያደረጋቸው ነበር፡፡፣ የሕፃናት የሥነ-ልቦና ጉዳት ፈተና ሆኖባቸው እንደነበር ይናገራሉ።
የሁለት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ካሳሁን አለሙም በወቅቱ የነበረው ችግር መልከ ብዙ እንደነበር ይገልጻሉ፡፡ በአንድ አካባቢ ላሉ 15 ቤቶች አንድ ሽንት ቤት ብቻ ይጠቀሙ እንደነበር ነው የሚጠቅሱት።ይህም ከጤና እና ከንጽህና አንጻር በተለይም ለሕፃናት እጅግ አስቸጋሪ እንደነበር ነው የሚያስታውሱት።
ለእናት አልማዝ፣ ለወይዘሮ ሙሉ እና ለአቶ ካሳሁን ቤተሰብ ያ ሁሉ ሀሳብ፣ ጭንቀት እና ስቃይ ዛሬ ታሪክ ሆኗል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ ተግባር በበጎነት መንደር ፕሮጀክት አማካኝነት፣ እነዚህ አባወራዎች እና እመወራዎች ዛሬ የዘመናዊ መኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን በቅተዋል።
አዲሱን ቤታቸውን ሲረከቡ የተሰማቸውን ደስታ ሲገልጹም በፊት በምኖርበት ቤት በማፈር አዲስ ልብስ ለብሼ ለመውጣት እንኳ እፈራ ነበር የሚሉት እናት አልማዝ ዛሬ ግን በደስታ እወጣለሁ ይላሉ፡፡ ለዚህም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያላቸውን ምስጋና በደስታ ታጅበው አቅርበዋል፡፡
አቶ ካሳሁንም የልጆቻቸውን ፈገግታ በማየታቸው የተሰማቸውን እፎይታ "ትልቅ ለውጥ ነው! በተለይ ከመታጠቢያ እና ከንጽህና መጠበቂያ አንጻር ሙሉ በሙሉ ተለውጠናል። አሁን ልጆቼ የራሳቸው መታጠቢያ እና መጸዳጃ ቤት አላቸው። በነሱ ደስታ እኔ እጅግ ደስተኛ ነኝ"ሲሉ ያብራራሉ።
ኢትዮጵያውያን ስንተባበር የማንወጣው ተራራ እና የማንሻገረው ችግር እንደሌለ ይህ አጋጣሚ ማሳያ ነው።
አዲስ አበባ ከተማን ደረጃዋን የጠበቀችና ውብ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የነዋሪዎችን ሕይወት መለወጥ እና ሰብዓዊ ክብርን ማስጠበቅ ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተሰራ ለመሆኑ የእነዚህ እናቶችና አባቶች ደስታ ምስክር ነው። | 7 157 |
| 9 | بدون متن... | 7 384 |
| 10 | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ሌ/ጄኔራል በላይ ሥዩም አከለን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል - ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ አድርገው ሾመዋል።
Prime Minister Abiy Ahmed (PhD) today appointed Lt. General Belay Seyoum Akele as the Ethiopian Federal Police Deputy Commissioner General - Crime Prevention Main Department Commander. | 6 779 |
| 11 | አገልግሎትን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በስታንዳርዱ መሰረት መስጠት ይገባል ተባለ
የቤቶች ልማት እና አስተደደር ቢሮ ከፐብሊክ ስርቪስ እና ከሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ዛሬ በአገልግሎት አሰጣጥ ንጽጽር እና ምዝገባ ዙሪያ ከማእከል እስከ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ዳይሬክተሮች ፤ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ ፡፡
በስልጠናው መክፈቻ አቶ መብራቱ ደሴ የቢሮው ጽህፈት ቤት ኃላፊ ባደረጉት ንግግር የቢሮው አገልግሎት አሰጣጥ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በስታንዳርዱ መሰረት እየተሰጠ መሆኑን በማረጋገጥ ከስታንዳርድ በታች እገልግሎት የሚሰጡትን ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና ነው ብለዋል፡፡
ስልጠናው ወቅቱን የጠበቀ እና ሰራተኛው ከዚህ ቀደም የነበረውን ግንዛቤ ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ እንዳልካቸው እንዳይላሉ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ እና ክትትል ቡድን መሪ ስልጠናውን ሰጥተዋል ፡፡
ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aahdab | 7 940 |
| 12 | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኬንያ ነፃነት፣ ሉዓላዊነትና ልማት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ጀግኖች ክብር በሚሰጥበት የማሹጃ ቀን (የጀግኖች ቀን) ብሔራዊ በዓል አከባበር ላይ በክብር እንግድነት ለመታደም ኤልዶሬት፣ ኬንያ ገብተዋል። | 7 271 |
| 13 | ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በመጣስ የትግራይን ሕዝብ ከልማት እና ከሰላም አርቋል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አሸናፊ እና ተሸናፊ በእኩልነት የተስተናገዱበት ታሪካዊ አጋጣሚ እና በሀገራችን አዲስ የሰላም ምዕራፍ የከፈተ ቢሆንም ህወሓት የገባውን ቃል በማጠፉ ስምምነቱ እንዲደናቀፍ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የፌዴራል መንግሥት በስምምነቱ መሠረት ተኩስ ከማቆም ጀምሮ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት የመመለስ ኃላፊነቱን በአግባቡ ቢወጣም፣ ድርጅቱ ግን ትጥቅ ከመፍታት ይልቅ ወደ መሣሪያ ግዢ እና ወጣቶችን በግዳጅ ወደ መመልመል መግባቱን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢቢሲ ጋር በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ እንዳብራሩት፣ ድርጅቱ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እንዳይመለሱ በመያዣነት ከመጠቀሙም በላይ የፌዴራል መንግሥት የጀመራቸውን የአየር ትራንስፖርት፣ የባንክ እና የቴሌኮም አገልግሎቶችን በማስተጓጎል ሕዝቡ ላይ ዳግም ስቃይ አድርሷል ብለዋል።
መንግሥት ‘ጦርነት አያዋጣም፣ ሰላም ይሻለናል’ በሚል ተደጋጋሚ ምክር ቢለግስም፣ ቡድኑ ግን ምክሩን ወደ ጎን በመተው እና ከተለያዩ ኃይሎች ጋር በማበር ወደማያዋጣ ጦርነት መግባቱን ጠቁመዋል።
ባለፉት ስድስት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ የኮሪደር ልማት በስፋት እየተተገበረ ባለበት ወቅት፣ በትግራይ ግን አንድ ኪሎ ሜትር እንኳ የኮሪደር ልማት አለመከናወኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንጽጽር አቅርበዋል።
ድርጅቱ ለሕዝብ ልማት ከመሥራት ይልቅ፣ ለዕርዳታ የመጣን እህል ከተፈናቃዮች ጎሮሮ እየነጠቀ እና ማዕድናትን እየዘረፈ ድሮኖችን እና የጦር መሣሪያዎችን በመግዛት ላይ ተጠምዶ መቆየቱን አጋልጠዋል።
ከሁሉም በላይ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከባድ ድርቅ ተከስቶ እያለ፣ ቡድኑ ጦርነት በማወጅ እና የአየር ትራንስፖርት እንዲዘጋ በማድረግ ሕዝቡን ለከፋ ችግር መዳረጉ እጅግ አሳዛኝ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
ህወሓት ‘እኔ ከሞትኩ ትግራይ የለችም’ በሚል ከንቱ አስተሳሰብ ተተኪ ትውልድ እንዳይኖር ቢጥርም፣ የትግራይ ሕዝብ ግን ይህንን መራራ ምዕራፍ አልፎ ወደ ልማት እና ሰላም እንደሚሸጋገር ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል።
#የመደመርመንግሥት | 8 459 |
| 14 | بدون متن... | 8 126 |
| 15 | በቢሮው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በየወሩ እየተዘጋጀ ለንባብ የሚበቃው ዜና መፅሔት የወርሀ መስከረም 2019 ዕትም እነሆ
ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aahdab | 9 192 |
| 16 | ለእኛ የቤት ልማት ማለት ሕንፃ መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ የዜጎችን ክብር ማስጠበቅ፣ የኑሮ ጥራትን ማሻሻልና የተሻለ ነገን መገንባት ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ | 9 852 |
| 17 | ማስታወቂያ
ለ70/30 ማህበር ቤት ተጠባባቂ ተመዝጋቢዎች | 9 747 |
| 18 | ዛሬ የቄራ አልማዝዬ ስፖርት ሜዳ እና ሥልጠና ማዕከልን በዘመናዊ መልኩ መልሰን ገንብተን ለስፖርት ቤተሰቡና ለወጣቶቻችን ማበርከታችን ትልቅ ደስታ ነው።
ይህ ሜዳ በታሪኩ ለኢትዮጵያ ኩራት የሆኑ ታዋቂ ስፖርተኞችን አፍርቷል። ዛሬም ከዚህ ሜዳ አዳዲስ የስፖርት ጀግኖች፣ የሀገር ኩራቶችና የድል ባለቤቶች እንዲፈልቁ እድሉን እየፈጠርን ነው።
ሜዳው ከዚህ ቀደም በአቧራና በጥሻ ተውጦ፣ ለስፖርት እንቅስቃሴ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ቆይቶ ነበር። ዛሬ ግን በድጋሚ ለወጣቶቻችን፣ ለታዳጊዎችም አካታች ሆኖ ስለተገነባ የችሎታቸው መድረክና የሕልማቸው ተስፋ ሆኖ ተመልሷል።
በከተማችን የስፖርት መሠረተ ልማትን ማስፋታችን ለወጣቶችና ለታዳጊ ልጆች ጤናማ፣ ተስፋ የሞላበትና የስኬት መንገድ እየከፈትን መሆናችን ነው። ከዚህ ሜዳ በሀገርና በዓለም መድረክ የሚያበሩ ታላላቅ ስፖርተኞች ይፈልቃሉ የሚል እምነት አለን!
ይህ የጋራ ሀብታችን ነው። እንጠብቀው፣ እናልማበት፣ በጋራም እናሳድገው!
ለወጣቶቻችን ዕድል እንፍጠር፤ ለሕልማቸው መንገድ እንክፈት፤ ለኢትዮጵያም አዲስ የድል ታሪክ እንጻፍ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ | 9 168 |
| 19 | የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤው ለሚከናወኑ የቤት ልማትና አስተዳደር ስራዎች ትልቅ እገዛ እደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሚያከናውናቸውን የቤት ልማት ስራዎችንና አገልግሎቶችን ለማሳለጥ በቢሮውና በህዝብ መካከል እንደድልድይ ሆኖ ለማገልገል የተቋቋመው የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ አጋዥ ኃይል እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ፡፡
መማክርት ጉባኤው በ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና በ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ከአባላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የቢሮው ኃላፊ ኢንጂነር ሄለን ታምሩ፤ የመማክርት ጉባኤው ቢሮው እየሰጠ ያለው አገልግሎት እንዲሻሻልና እንዲቀላጠፍ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ገልጸው ወደፊት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ተዋቡ ቀስቅስ በበኩላቸው የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥና ለማዘመን ሁሉም የጉባኤው አባላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በ2018 በጀት ዓመት የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ለማሻሻልና ለማዘመን፣ መመሪያዎችንና ደንቦችን መሰረት ያደረገ ግልጽነት ያለው እና የተደራጀ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለመዘርጋት የተከናወኑ ስራዎች በጉባኤው ላይ ቀርበዋል፡፡
የመማክርት ጉባኤው የመንግስትን የአሰራር ጉድለቶች በመለየትና በመሙላት የተገልጋዮችን ጥያቄዎች በአስተማማኝ ሁኔታ ለመመለስ ትልቅ ሚና እንዳለው በውይይቱ ላይ ተመላክቷል።
በቀጣይም የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ የተቀላጠፈ፣ አካታች እና ዘመናዊ በማድረግ የህብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተጠቁሟል።
በመጨረሻም የተጓደሉ የመማክርት ጉባኤ አመራሮችን በማሟላት ጉባኤው ተጠናቋል።
ጥቅምት 6/2019 ዓ.ም
የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ
የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aahdab | 9 261 |
| 20 | بدون متن... | 9 108 |
