Abu Uwais Nafyad Kasim
رفتن به کانال در Telegram
ይህ የተለያዩ የዲን ትምህርቶች፣ ዳዐዋዎች እንዲሁም ኢስላማዊ ፅሑፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው። ይከታተሉ! በተቻለኝ ያክል ማበጀትን እንጂ አልሻም።
نمایش بیشتر1 709
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-27 روز
-1230 روز
آرشیو پست ها
አይመጣውም።
ምንም በሉ ምንም !
የአንድ ኡስታዝ ወይም ሸይኽ፤ ሚዲያ ላይ በመልካም ስራው ምናውቀው፤ ለሺዎች መቃናት ምክንያት የሆነ ሰው፤ አሁንም ድረስ መልካም ነገር እያሰራጨ ያለ እና ሰው እሱን እንደ አርዓያ ሚያየው የዚህ ትልቅ ሰው ሚስት/ባለቤት ተገላልጣ ሚዲያ ላይ መውጣቷ አይመጣውም። በምንም ተዓምር ፌር አይደለም። ስህተት ነው። ግን ግዙፍ እና ብዙ መልካም ስራዎቹ ይህን ስህተት ይሸፍናሉ። ለዚህሽ ስህተት ተብሎ ግን እሱን ማጣጣል፣ ማዋረድ፣ መናቅ፣ ዝቅ ማድረግ እና ምንም እንዳለስራ ማድረግ ሌላ ትክክል ያልሆነ ተግባር ነው። ነገሩን ትንሽ ያገዘፈው ሚዲያ ላይ መውጣቱ ነው። ወሏሂ ብዙ ሰው ደካማ ነው፤ ልክ ይህን ሲያይ በጣም የሂጃብን ጉዳይ ያቀላል። ኡስታዙ ካለው ተፅዕኖ አንፃር።
ፕሬዝዳንታችን ሸይኽ ሀጂ ኢብራሒም ቱፋም ባሌ ላይ ባደረጉት ንግግር "ወሊይ" ምናምን ምትለዋ ቃል ላይ "ተሳስተዋል" እንዳልን ሁሉ ይህም ኡስታዝ ባለቤቱ ተገላልጣ እራሷን ሚዲያ ላይ ስታነጥፍ ዝም ማለቱ ተሳስቷል። ይህን በምንም ተዓምር ማስተባበል አይቻልም። ምንም ውልግድ ውልግድ የለም። ስህተት ነው። አሏህ ሁላችንም ይቅር ይበለን። አበቃ!
https://t.me/AbuUweis
