cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹

@Tewahdo27 ✞ በየጊዜው አዳዲስ መንፈሳዊ † ➢ ፅሁፎች ➢ መዝሙሮች ➢ ኦርቶዶክሳዊ መልእክቶች ➢ መንፈሳዊ ነገሮችን ሁሉንም ለማግኘት ከፈለጉ ተቀላቀሉን ✞ ለአስተያየቶ @Tewahdo27 ይጠቀሙ ➢ ሁሉም እንዲያነበው SHARE ያርጉ ! እናመሰግናለን !

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
3 157
مشترکین
-424 ساعت
-157 روز
-1030 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯 ⛪️✍ብርሃንሽ ከፀሐይ #ብረሃን_ይበልጣል ቅድሳን #በፍጹም_ደስታ ያዩሽ ኮከብ ካአንቺ የወጣ ተወለደ ነው (ተዓምረ #ማርያም )🙇‍♀🕯🦋 #እንኳን_አደረሳቹሁ_የእምየ_ተዋሕዶ_ልጆች ልደታ ማርያም ሐምሌ (፩🕯) ✳️ከሀና ማህጸን #የአዳም_ተስፋ_ታየች በኀጢአት የደረቀው የሰው ህይወት በድንግል መወለድ በተስፋ ለመለመ #ጨለማው_ዓለም በድንግል መወለድ ብርሃን ሆነ የሊባኖስ ተራራ በብርሃን ተከበበ #ሊባኖስ_የብርሃን መቀነት ታጠቀች ሊባኖስ #በብርሃን_አጥር ታጠረች #ኢያቄም የደስታ ካባ ደረበ #ሀና_የደስታ አክሊል ደፋች የብርሃን እናት ድንግል ተወልዳለታለችናችና የዓለም ሞት በህይወት ተቀየረ ሰማይ ከሀና ማኅፀን ተወለደች #የሐና_ማሕጸን የሰማዯ መውጫ ሆነ የውርስ ኀጢአት ከድንግል ራቀ ሰወች ሁሉ በውርስ ኀጢአት በሚወለዱበትን ያለውርስ ኀጢአት ንጹህ ሁና ወላዲተ አምላክ ተወለደች #ከኢያቄም_አብራክ ነጭ እንቁ አበራች ከሀና ማኅጸን ጸአዳ ርግብ ወጣች የሀና ታሪክ ተቀየረ ሀና የእግዚአብሔር ወልድ አያቱ ተባለች ሰማያት ሰለሰማዯ መወለድ ዝማሬ ዘመሩ ምድር ሰማይን በመሸከሟ እልል አለች ሰማዯ በምድር ታየች የአበው ተስፋ መሰረት ተጣለ አይሁድ አፈሩ ቤተ ክረርስቲያን #የድንግልን_መወለድ አበሰረች በ5485 ዓመተ ዓለም ድንግል ተወለደች ፀሐይ ሊወጣ ሰማይ ተገኘች ሰማዯ ከሰው #ተወልዳ_ፀሐይን ወለደች #እመቤቴ_በመወለድሽ የአበው ተስፋ እውን ሆነ። ⛪️🍂 #ተወለደች_ማርያም 🕯🦋 #ይጠብቃል_ተስፋ አዳም ተጨናንቆ የሕይወት መገናኛ #መሆንሽን_አውቆ ብረሃኑ ተገልጦ ሞት በሰው እንዲያቆም ድንግል ትመጣለች ትንቢቱ እንዲፈፀም #ለሀና_ለኢያቄም ብቻ አይደለም ደስታው ለዓለሙ ሀሴት ነው የመገኛሽ ቦታው ዮም ፍሥሐ ኮነ ተወልዳ ማርያም አምላክን እንድናይ #ከላይ_ከአርያም በህግ በትዕዛዝ ተገለጠች በዓለም ልደቷ ግሩም ነው ለዓለም የሚያበራ ሕይወቷም ስብከት ነው ጽድቅን የሚመራ አንደበቴ #አያውቅ_ክብርን ለሰው ማውጋት ልቤም ቅኔ አይችል ያንቺን ገድል ማውራት ፍስሐ ወሀሴት ተወለደች ማርያም ጌታ የተናገረው #ድህነት_እንዲፈፀም ✳️ ልደታ #ማርያም_እናቴ ልደትሽ ልደታችን ነው ሀገራችንን ሰላም አድርጊልን ከኃጢዓት በቀር የልባችንን መሻት ፈፅሚልን በያለንበት አንቺ ጠብቂን ወስብሐት #ለእግዚአብሔር @ortodox_27 🤲 🤲 🤲 #አሜን......... 🧡 ......... #አሜን ⊹ #አሜን🙏³ 🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂
نمایش همه...
ሰኔ 30 በዚህች ዕለት ነብይ፤ ካህን፤ መጥምቅ፤ መምህር፤ ፃድቅ፤ ሰማዕት፤ ሐዋርያ የሆነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ። ነብዩ ዳዊት በመዝሙሩ ፃድቅ ሰው እንደ ዘንባባ ያፈራል እንደዝግባም ይበዛል እንዳለ ዛሬም የቅዱስ ዩሐንስ መጥምቅ ጸሎቱ በረከቱ በሁላችን ላይ ፀንቶ ይደርብን አማላጅነቱ ይደረግልን ዛሬም ዘወትርም ለዘለአለሙ አሜን፡፡ እንኳን አደረሳችሁ #OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ #profile #timline #post #story On Telegram👇          • t.me/ortodox_27          • t.me/ortodox_27 Share 🙏 https://t.me/ortodox_27
نمایش همه...
ሰኔ  ፴   ልደቱ  ለመጥምቀ  መለኮት  ቅዱስ  ዮሐንስ @ortodox_27
نمایش همه...
ሰኔ 29/2016 #ቅዱስ_በዐለ_ወልድ #ፅንሰት_ልደት_ትንሣኤ #ፃድቁ_እጨጌ_ዮሐንስ 👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህ ቀን እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም የከበረ መልአክ የቅዱስ ገብርኤልን የምሥራች የሠማችበት አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የተወለደበት የከበረዉን #ትንሣኤውን የገለጠበት ወርሐዊ መታሰቢያ ነዉ እንኳን አደረሰን 👉እንዲሁም በዚህች ቀን #አለም_የተፈጠረበት የጌታችንን ዳግመኛ #ምፅአቱን የምንጠባበቅበት እለትም ጭምር ነዉ 👉በዚህች ቀን ለእመቤታችን ለቅድስት #ድንግል_ማርያም የከበረ #መልአክ_ገብርኤል_የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል እንዲህ ሲል 👉ኤልሳቤጥ በፀነሰች በስድተኛው ወር #መልአኩ_ገብርኤል የገሊላ ክፍል የሆነች ናዝሬት ወደምትባል አገር ከዳዊት ወገን ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች ወደ አንዲት ድንግል #ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ 👉የድንግሊቱም ስም #ማርያም ነው መልአኩም ወደርሷ ገብቶ ደስተኛ የሆንሽ ደስ ይበልሽ ፀጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት እርስዋም አይታ ከንግግሩ የተነሣ ደንግጣ እንዴት እንዲህ ያለ ሰላምታ ይቀበሏል ብላ አሰበች 👉መልአኩም እንዲህ አላት ማርያም ሆይ #በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና አትፍሪ እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም #ኢየሱስ ትይዋለሽ እርሱ ታላቅ ነው የልዑል #እግዚአብሔር ልጅም ይባላል 👉 #እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ለያዕቆብ ወገንም ለዘላለም ነግሦ ይኖራል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም አላት 👉ማርያምም መልአኩን ወንድ ሳላውቅ ይህ እንደምን ይሆናል አለችው መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ያድርብሻል የልዑል ኃይልም ያጸናሻል ከአንቺ የሚወለደው ከሶስቱ አካል አንዱ የልዑል #እግዚአብሔር ልጅ ይባላል 👉እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ፀንሳለች ወንድ ልጅም አገኘች ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና #ማርያምም እነሆኝ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለችው። 👉ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል #ወልድ_ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው 👉ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ የነበረ በማይመረመር ድንቅ በሆነ ተዋሕዶ እንዴትም እንደሆነ በማይታወቅ በቅድስት #ድንግል_ማርያም ማሕፀን አደረ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ተፀንሶ በህቱም ድንግልና #ታህሣሥ_ሀያ_ዘጠኝ ቀን ተወለደ 👉በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍጹም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኩር ናት በእርሷም #የዓለም_ድኅነት ተጀምሮዋልና 👉ዳግመኛ በዚህችም ዕለት ደግሞ በመድኃኒታችን በከበረችና ልዩ በሆነች #ትንሣኤው የዓለም ድኅነት ሆነ በረቀቀ ጥበቡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ያህል በምድር ላይ ሥራውን ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ በፈቃዱ ሕማማተ መስቀልን ተቀብሎ ሙቶ ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው በዚች ቀን በሃያ ዘጠኝ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና 👉በዚች ቀን አስቀድሞ ደጅ ለሚጠኑት በዓለም ላሉ ሰዎች ሰው በመሆኑ ድኅነታቸውን አበሠራቸው እንዲሁም ደግሞ በዚች ዕለት ከሲኦል በመዳን #ሙታንና_ሕያዋን ደስ አላቸው 👉በዚህም በጌታችንና በመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ መነሣት መነሣታቸውን አረጋገጡ የከበረ ጳውሎስ በመነሣቱ ክርስቶስ የሙታን በኵር ሆነ እንዳለ እርሱ ለሙታን በኵራቸዉ ነዉና 👉አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከበአሉ በረከት ሁላችንንም ያሣትፈን ዳግም ሲመጣም ከቅዱሳኑ ጋር ይደምረን የምንሰማዉን የምናየዉን ክፉ ነገር ሁሉ ወደ በጎ ነገር ይቀይርልን የቅዱሳን #አበዉ_ሐዋርያት ፀሎታቸው ይጠብቀን የተባረከ የተቀደሰ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" 👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ ፃድቁ አባታችን #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ በምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቁን "አሜን" ✝️💒✝️ @ortodox_27
نمایش همه...
. ♥[ #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ ]♥ [ #ዘፀግሮ ] የኖሩበት ዘመን "500" ዓመት ነው! የትውልድ ሀገራቸው በኢየሩሳሌም አውራጃ ሳሬራ የሚባል ስፍራ ሲሆን፤ በየካቲት "28" ተፀንሰው በህዳር "29" ተወለዱ! የአባታቸው ስም ዲላሶር፤ የእናታቸው እምነ ፅዮን ይባላል! ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በቅዱስ ገብርኤል መሪነት በአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመን ሲሆን ምንኩስናንም ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ተቀብለዋል! እረፍታቸው በሐምሌ "29" ሲሆን በመጋቢት "18" እለት ፍልሰተ አጽማቸው ነው!! መልካም ቀን። #ይቆይ// @ortodox_27
نمایش همه...
. ♥[ #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ ]♥ [ #ዘፀግሮ ] የኖሩበት ዘመን "500" ዓመት ነው! የትውልድ ሀገራቸው በኢየሩሳሌም አውራጃ ሳሬራ የሚባል ስፍራ ሲሆን፤ በየካቲት "28" ተፀንሰው በህዳር "29" ተወለዱ! የአባታቸው ስም ዲላሶር፤ የእናታቸው እምነ ፅዮን ይባላል! ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በቅዱስ ገብርኤል መሪነት በአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመን ሲሆን ምንኩስናንም ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ተቀብለዋል! እረፍታቸው በሐምሌ "29" ሲሆን በመጋቢት "18" እለት ፍልሰተ አጽማቸው ነው!! መልካም ቀን። #ይቆይ// @ortodox_27
نمایش همه...
🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂 ⛪️✍ ነፍሱን ሰለ #ዘደጆቹ_ከመስጠት_ይልቅ ከዚህ #የሚበልጥ_ፍቅር ለማንም የለውም። ( ዮሐ ፲፭÷፲፫)🥺❤🙏 እለተ #አርብ_የፍቅር ቀን😢💔 #አባት_አለኝ አዎ እኔስ አባት አለኝ በመስቀል የዋለ ምህረቱን አብዝቶ #ደሙን_የከፈለ መሞቴን ሰርዞ ነፍሴን የቀጠለ ከሰማየ ሰማይ ከዙፋኑ ወርዶ ፅድቁን አበዛልኝ ሀጥያቴን ጋርዶ መልካም ነገር የለኝ ከቶ ማይነገር ነገሬን አስዋበው አድሮ በመቃብር መልካም #መልካም_ቅዱስ ሊባል የተገባው በቀራንዮ ላይ እርቃኑን የዋለው እርሱ ነው አባቴ እኔን የወረሰው ክህነቱ ዘላለም እንደ መልከጼዴቅ ሞቴን የሞተው ነው #የዘላለሜ_ፅድቅ ፍፁም ሳይገባው መስቀል ተሸከመ እኔን ሊያበረታ ድክመቴን ደከመ እዳዬን ሒሳቤ በነፍሱ ተካልኝ ለነፍሴ አርነት ነፃነት ሆነልኝ #መንገዴ_የቀናው የተከናወነው ሰማይ በገባሁት በእግዚአብሔር አብ ልጅ ነው ይህ ነው አባቴ አዳኝ መድሀኒቴ በደከመኝ ዘመን የያዘኝ ጉልበቴ እርሱ #ባይኖርማ_ታሪክ ባልነበረኝ ታሪኬን ሸፍኖት ታሪኩን ሸለመኝ ማረፍ ሆነ ዛሬ ለሁላችሁ ሁሉ በማንም አይደለ በእርሱ በሀያሉ ተዉኝ አትንቀፉኝ ዝናውን ልመስክር አባቴን ሰብኬ ከመጣ መቃብር ለእኔስ መታደል ነው ከእርሱ መቆጠር አያልቅም ብናገር ስለ #አባቴ_ዝና ከቶ የማይደፈር ገናና ነውና በእኔ በበርባኑ በሆንኩኝ ግፈኛ ሲገፉ ዝም ያለ ታጋሽ ብርቱ እረኛ እርሱ ነው #አምላኬ_እውነተኛ ዳኛ መፍረድ ፍትህን መስጠት አቤት ሲችልበት እኔን አትመኑኝ ዮሴፍን ጠይቁት #በባህድ_ሀገር ላይ አብሮት የተሸጠው ሊተወው ያልቻለው ዮሴፍ የነገሰው በማንም አይደለ #በእርሱ_በአባቴ ነው አባ አባትማ ወዳጅ ከተባለ እንደ ጌታ ኢየሱስ እረ ወዴት አለ ምህረቱ ብዙ ነው ቸርነቱ ጥልቅ ለበደልኩት ልጁ ከቶ የማያልቅ በጎ ንጉስ አለኝ #በክብር_የነገሰ በልቤ መቅረዝ ላይ በፅድቅ የፈሰሰ ዝም #ብዬ_አይደለም አባቴ የምለው በተለምዶ አይደለም ኢየሱስ የምለው የሆነው ሆኖልኝ ስለ መዳኔ ነው #አሁን_አሁንማ ቅሬታዬም በዛ ክብሩን ሲያቀሉብኝ እንዲሁ እንደዋዛ መናፍቆች ተውኝ አባቴ ጌታ ነው አማላጅ አይደለም ኢየሱስ ፈራጅ ነው ለእኔና ለእናንተ መዳን ሲል ቢመጣ ክብሩን አትንኩብኝ #አታምጡብኝ_ጣጣ ቅር ይለኛል እኔን እርሱ እንዲህ ሲገፋ የፈሰሰው ደሙ በከንቱ ሲክፋፋ ፍቅር ነው ወዳጄ ፍቅርን የሚዘራ መንግስቱን ይወርሳል በእርሱ የተጠራ እና #ወገኖቼ_ከሀዲያን ሁሉ ለአባቴ ያላቹን አስተምሮ ጣሉ ዝምታው ፍቅር ነው መታገስ ይወዳል እኔ አውቀዋለሁ ማለፍን ይችላል እኔ ብዙ አልልም ብዙም አለወራም ስለ አባቴ አውርቼ #በፍፁም_አልጠግብም ያኔ ሲገባቹ የውዴ ጌትነት ትመለሳላቹ በፍቅሩ በጎነት ይህ ነው የኔ ወዳጅ ተራማጅ በባህር በሁሉ #የነገሰ_በሰማይ በምድር ስሙ መድሀኒት ነው ለታመነበት ሰው ባህሩን እንደ ግንብ ለሁለት የከፈለው የማንም አይደለም የአባቴ ስሙ ነው ማረፍ ሆኗል ዛሬ #በስሙ_በደሙ አያሳስበኝም መምሸት መጨለሙ ብርሀን ነው ልብሴ በሁሉ የሚያበራ ፈታዩ አባ ነው በደሙ የሰራ ደረቴን ነፍቼ አባቴ የምለው የናዝሬቱ ህፃን የእመቤቴ ልጅ ነው አዎ #እርሱ_አባቴ ነው ዛሬም አስቀድሞ ያኔ በእጁ ሰርቶኝ ዛሬ ደግሞ ታሞ ያኔም ሆነ ዛሬ ነገም በሚመጣው ኢየሱስ የሞተው ሁሌም አባቴ ነው አዎ ከሞት የተነሳው #ሁሌም_አባቴ ነው 🥀ዕለተ አርብ የፍቅር ቀን❤ ጌታ ሆይ ስለ ሰው #ልጆች_ፍቅር ስትል በዕለተ አርብ #በቆረስከው ስጋህ ባፈሰሰከው ደምህ ብለህ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን፡፡ ወስብሐት #ለእግዚአብሔር አሜን፫🤲🤲 @ortodox_27
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.