fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

رفتن به کانال در Telegram

💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

نمایش بیشتر
8 816
مشترکین
-724 ساعت
-227 روز
-830 روز
آرشیو پست ها
ማን ደስተኛ ያደርገኛል ሳይሆን እንዴት ነው ለራሴ ደስታን መፍጠር የምችለው? ብለሽ አስቢ ..... ከሰው ምንም ነገር አትጠብቂ አትደገፊበትም.... የጎደለሽን ሳይሆን የተሰጠሽን እያሰብሽ አሏህን አመስግኚ ፤ ደስተኛም ሁኚ። t.me/https_Asselfya

የጧት ቁርስ ይዛችሁ ¡ ኑ ቡና እንጠጣ.... =

5 ወሳኝ ምክሮች በስደት ላሉ ለእህቶች 1--የዋህነት አታብዙ ~እህቶች የዋህነታችሁ ጥሩ ሆኖ ሳለ ከልኩ በላይ ሲሆን ግን ይጎዳል። ሁሉም ነገር ላይ የዋህ አትሁኑ ።ለምን? እንዴት? ማለት ያለባችሁ ነገር ላይም ለምን በሉ። ብልሆች፣ብልጦች፣አስተዋዮች ሁኑ። 2--ሁሉንም አትመኑ ~ሁሉንም በማመናችሁ ያጣችሁት ነገር የለም? የተጎዳችሁት ነገር የለም?   በእርግጠኝነት ይኖራል ።ጥርጣሬም አታብዙ ግን ሁሉንም አትመኑ። ልቅ በሆነ እምነት ስንት ነገሮቻቸውን ያጡ አሉ መሰላችሁ። በተለያዩ ሽፋን በተለያዩ ካፓ የሚንቀሳቀሱ እንዳሉም እወቁ። ተጠንቀቁ።ንቁ። እራሳችሁን፣ገንዘባችሁን ጠብቁ። 3---ስትሰጡ በልክ ስጡ። መስጠት ያሰጣል።አላህም ይተካል። ጀነትን ያስገኛል።ደስታን ይሰጣል።መካራን  ያስወግዳል። ግን በልክ ይሁን ። 4- ለችግር ግዜ የሚሆናችሁን ገንዘብ አስቀምጡ። ~ሰው ነን መታመም ሊመጣ ይችላል።ስራ መፍታት ሊኖር ይችላል። የተለያዩ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ለዛ ችግር እዳም እንዳትገቡና እንዳትቸገሩ ለዚህ ቀን የሚሆን ከደሞዛችሁ፣ከጉዳዮቻችሁ ሸረፍ እያደረጋችሁ አስቀምጡ። 5--ደርስ ላይ ፣ቂረአት ላይ በርቱ ~በቻላችሁት አቅም  ግዜያችሁን ለመጠቀም ሞክሩ ።በስደት ቆይታችሁ ባለቻችሁ ሽራፊ ግዜ ለመጠቀም ሞክሩ። ወደ ሀገር ቤት ከተመለሳችሁ በሗላ ሁሉ ነገሩ እንደጠበቃችሁት ላይሆን ይችላል። የመቅራቱም ሞራል እንደዛ ላይሆን ይችላልና  በርቱ።ሸምቱ። በሶሻል ሚድያው ተጠቀሙ።           ✍አቡ ሀፍሷ ~››@AbuHafsaYimam ~››@AbuHafsaYimam

የመኗኗር ጥበብ ~ "ብልህና አስተዋይ ማለት ከቤተሰቡ፣ ከወዳጆቹ፣ ከጓደኞቹና ከጎረቤቶቹ ትንሽ ትልቁን አጥብቆ የማይዝ ነው።" ኢብኑል ጀውዚይ [ተህዝቡል ከማል፡ 19/370] = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

ዋ  የኛ ነገር በዘመድ ፣በጉቦ፣በብልጠት የማይታለፍበትና ሁሉም የስራውን ውጤት የሚሰጥበት ከባድ የመከራ ቀን ቂያማ‼️

በጊዜ ተንፍስ ~ አንዳንድ ወንድሞች በሆነ የዒልም ዘርፍ ከእኩዮቻቸው ሲበልጡ ወይም የበለጡ ሲመስላቸው ትእቢት ሲፈትናቸው ይታያሉ። አንዱን መናቅ፣ ያኛውን ማጣጣል፣ ሌሎችን በመገምገም ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ ላይ ይጠመዳሉ። የሸሪዐ እውቀት አላህን መፍሪያ መሳሪያ መሆኑ ሁሌም ሊዘነጋ አይገባም። ማወቅህ ትእቢት ካወረሰህ፣ በማወቅህ ለሌሎች ንቀትን ካዳበርክ ወላሂ ማወቅህ ጎድቶሃል። ጅህልና ላንተ የተሻለ ነበር። ሰው ቴኳንዶ ሰልጥኖ ቀድሞ ያልነበረውን አደብ ሲላበስ በምናይበት ጊዜ የሆነን ዒልም ሲማር እብሪትና ንቀትን የሚያዳብር ማየት አሳፋሪ ነው። ወንድሜ ሆይ! መከበር ከፈለግክ ሰዎችን አክብር። ሌሎችን መናቅ ምናልባት ጥቂት ጊዜ ቢያስከብር ነው። ወይ ሰዎች እስከሚነቁ፣ ወይ ደግሞ ማንነትህ እስከሚገለጥ ድረስ ቢዘልቅ ነው። ከዚያስ? ከዚያማ መናቅህ መንናቅን ነው የሚያስከትልብህ። መተንፈስህ ላይቀር አፀፋ ሳያስተነፍስህ በፊት አላህን ፈርተህ ተንፍስ። በጊዜ ተንፍስ። አዎ መተንፈስ ይሻልሃል። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

ለሆነ ነገር ጉጉ መሆናችሁን ሰዎች ሁሉ እስኪያወቅባችሁ ድረስ ስለዚያ ነገር አብዝታችሁ አታንሱ፡፡ ገንዘብ፣ ትዳር፣ ዝና … ጥቂቶች ናቸው፡፡ ምኞታችሁን ለአላህ ብቻ ንገሩ፡፡ ሰው ፊት አንድን ነገር አብዝቶ ማውሳት ልመና ይመስላል፡፡ ~         t.me/https_Asselfya

📌«إنَّ الصِّدِّيْقِينَ إذَا قُرِئَ عَليْهُمْ القُرآنُ، طَربَتْ قُلُوبُهُمْ إلىْٰ الآخرة» مالك بن دينار #تلاوة

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته መርከዝ-ረያን መርከዛችን በኦ-ላይን ከአሊፍ ጀምሮ እስከ ቁርአን ሂፍዝ ድረስ ከህፃን እስከ አዋቂዎች ከሁሉም የእድሜ ክልል የሚሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ በአላህ ፍቃድ ቁርአንን በቀላል ዘዴ ያቀርባል። እናም ወንድም እህቶች ፈጥነው እንዲመዘገቡ እናሳውቃለን። 👉 በመርከዛችን የሚሰጡ የት/ት                        አይነቶች፦ ➡️ቃኢደቱ ኑራኒያ ለጀማሪዎች ➡️ቁርአንን በእይታ(በነዞር) ከመሰረታዊ ተጅዊድ ጋር ➡️የቁርአን ሽምደዳ (ሂፍዝ) ከተሟላ ተጅዊድ ጋር በአላህ ፍቃድ እንሰጣለን። ⏰የቂርአት ክፍለ ጊዜ ↪️ጠዋት ከአንድ ሰዐት አስከ ሶስት ሰዐት ↪️ማታ ከሁለት ሰዐት እሰከ አራት ሰዐት ት/ቱ የሚሰጠው  በቴሌ ግራም መሆኑን እናሳውቃለን። 🌟መመዝገብ ለምትፈልጉ👇👇 @abu_munib1 @Umu_Khaled1

«እንዳታገቢ» በሰለፍያ ስም ዋሽቶ የሚነግድ፡ ሴት የማያከብር አስተሳሰብ ውልግድ፡ ብርሀን አልባ ፅልመት በቀን የሚለግድ፡ ሰነፍና ዋልጌ ማይሰራ ማይነግድ፡ ሴትን ለማሳመን በሱና እሚያማልል፡ ነገ የማይገባው ጂል ቡለሀ ቅውልል፡ ስሙን በመቀየር ሚስቱን የሚሰልል፡ በሌለው ማንነት አቅሙን የሚቆልል፡        «እንዳታገቢ» ለቅሶና ጭቅጭቅ ከሚሆን ህይወትሽ፡ ይህን ሰው አባሪው ነስከሽ ከፊትሽ፡ ተይው አይጠቅምሽም ለሱ ሚስትነትሽ፡ ባህሪው የሆነበት ማግባትና መፍታት፡ ምላሱ ቀጣፊ ባህሪው የራስ ምታት፡ ህልሙ ብር የሆነ ሰከንድም ሰዓታት፡        «አታግቢው» ትዳርን ሲፈልግ የማይገነዘብ፡ ትኩረቱ የሆነ ጥቅምና ገንዘብ፡ ባለው ንብረት ብቻ ሴትን የሚታዘብ፡ ሰለፍይ ነኝ ብሎ ምንም ቃል ቢገባ፡ በተግባር ካለዬ ምርቱ ከገለባ፡ ፊትና እሚናፍቀው የሚወድ ወከባ፡ ምንም ፎቶው ቢያምር ቢመስል አበባ፡ በጨለማ ገደል ይዞሽ እንዳይገባ፡     «እንዳታገቢ» ጌታን የሚያስቆጣ ሽርክን የሚሰራ፡ ቀብር የሚለምን ተሸክሞ እንስራ፡ ጀበናና ስኒ በጫት የሚመጀን፡ ነገ በአኸይራ እሳት የሚያስፈጀን፡ በየሚዲያው ላይ ሴት የሚጀናጀን፡     «እንዳታገቢ» ስሜት ያሰከረው መንፈሱ ታማሚ፡ መታዘዝ የማይወድ ለአባየም ለማሚ፡ የሀቅን ንግግር በጥመት ተርጓሚ፡ አንገት የሚደፋ እምነቱ ሲደፈር፡ የእምነቱ ፍቅር የማያልፍ ከከንፈር፡ ሰውነት የሌለው የሚል አፈር አፈር፡ ልማድ የሆነበት ዳንስና መጨፈር፡     «እንዳታገቢ» የተውሒድ አርበኛ ካልሆነልሽ ቀንድል፡ ሰለፍይ ነኝ ብሎ ሴትን የሚበድል፡ ሁሌ እሚለፈልፍ ያልሰራውን ገድል፡        «እንዳታገቢ» ሶላት የማይሰግድ ተጠቅልሎ ጋቢ፡ ፊትና የሚያሯሩጥ ችግር አራጋቢ፡ ውጭ የሚጠይቅ ሳያቀርብ ገቢ፡ ይህ አይነቱ አልጫ አወ እንዳታገቢ፡  👇👇[ተቀላቀሉ] ▣ تابعونا👇👇 https://t.me/Abuharisabdurahman

~የጭንቅ ግዜ ዱዓእ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿دعَواتُ المكروبِ: اللَّهمَّ رحمتَكَ أرجو فلا تكِلْني إلى نفسي طرفةَ عينٍ وأصلِحْ لي شأني كلَّه لا إلهَ إلّا أنتَ﴾ “የጭንቅ ግዜ ዱዓእ፦ ‘አላህ ሆይ! እዝነትህን አሻለሁ፡፡ ለቅፅበት ያክል እንኳ ለራሴ አትተወኝ፡፡ ሁለ ነገሬን ያማረ አድርግልኝ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡’” t.me/https_Asselfya

አላህ ሆይ !ኢማናችንን በቀልባችን አድስልን።

متى يكــــــــون العبد من الذاكرين الله كثيرا... 🎙استمع للشيخ عبد الرزاق البدر حفظه الله .

🔖አዲስ ተከታታይ  ደርስ 📚የተከበረው ቁርኣን ትርጉም 📄ክፍል:- 001 (የሱረቱል ፋቲሓ ቃል በቃል ትርጉም) (تفسير سورة الفاتحة ) 🎙አቅራቢ:-ሸይኽ ሙሐመድዘይን ኣደም  bdf ለመጋኘት https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/9840