💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
رفتن به کانال در Telegram
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
نمایش بیشتر8 855
مشترکین
+224 ساعت
+357 روز
-330 روز
آرشیو پست ها
~አንዲት ሴት ልጅ የሸቀጡን
ዋጋ ለማስቀነስ ብላ ሻጩ ጋር
ልትቀላለድ ፣ ወሬ ልታስረዝምና
ልትሳሳቅ አይገባትም።
የሷ ሐያእ ከሸቀጡ ዋጋ ውድ
ነውና።
"جاهد نفسك وتذكّر:
من سبقَ في الدنيا بالخيرات
فهو السابق في الآخرة إلى الجنات!"
ስለ እውቀትና ተግባር፦
➖➖➖➖➖➖...✍️
"እውቀት ማለት መሸምደድ ሳይሆን አላህን መፍራት ነው። አላህን የማይፈራ ሰው የፈለገውን ያህል ቢቀራ 'አሊም' ሊባል አይችልም።"
የሁሉም ጓደኞች የሚያውቁት ግን የማይተገብሩት ሀዲስ!
~ትዋደዱ ዘንድ ስጦታ ተሠጣጡ ረሱል ﷺ
👉 በሉ ፍጠኑ ስጡኝ¡
🔖ኢብኑ ቀይም አላህ ይዘንላችዉና እንዲህ ብለዋል፦
አንድ ባሪያ የቂያማ ቀን እንደ ተራራ የሆኑ መልካም ስራዎችን ይዞ ይመጣል ነገር ግን ምላሱ ሁሉንም እንዳፈረሰበት ያገኛል።
الداء والدواءአምስቱ ደረጃዎች፡-
ኢማም ኢብኑልቀይም እንዲህ ይላሉ፥ “ሰዎች በሶላታቸው መሠረት በአምስት ደረጃ ይከፈላሉ፡-
አንደኛው፡- ራሱን በእጅጉ የበደለና ድንበር ያለፈ ሰው ነው:: የዚህ ዓይነቱ ግለሰብ የሶላቷን ቅድመ ሁኔታ -ዉዱእ ያጓደለ፣ ወቅቶቿን ያልጠበቀና ግዴታዎቿን በትክክል ያላሟላ ሰው ነው::
ሁለተኛው፡- የሶላትን ወቅቶቿን፣ ሕግጋቷንና ግልጽ የሆኑ ማእዘናቶቿን የሚያከብር ሲሆን ነገር ግን ነፍሱ ከሸይጧን የሚደርስባትን ጉትጎታ ከመታገል ይልቅ ከጉትጎታውና ዓለማዊ ሀሳቡ ጋር የሚነጉደው ነው::
ሦስተኛው፡- የሶላትን ህግጋቶች በትክክል የጠበቀ ሲሆን ነፍሱ የሚደርስባትን የሸይጧን ውትወታና ምድራዊ ሃሳብ ለመቋቋም ትግል ላይ ነው:: ይህ ሰው ሶላቱ እንዳይሰረቅበት ለመከላከል ትግል ላይ በመሆን፧ በሶላትና በትግል መካከል ሶላቱን ይፈጽማል።
አራተኛው፡- ሶላት ውስጥ በሚገባበት ጊዜ የሶላቷን ግዴታዎችና ህግጋቶች በትክክል ያሟላል:: ልቡ የሶላቷን ሐቆች ላለማጉደል በከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠመዳል:: አንዳች ጉድለት እንዳይኖር የተቻለውን ያደርጋል:: ዋነኛ ሀሳቡ ሶላቱ እጅግ የተሟላችና የተዋበች እንድትሆን ማድረግ ነው:: ልቡ የተጠመደው በሶላቱ ጉዳይና በጌታው አምልኮ ላይ ብቻ ነው፡፡
አምስተኛው- ሶላት ውስጥ ሲገባ በተሟላ ሁኔታ ይሆናል:: ለየት የሚያደርገው ልቡን ሙሉ ለሙሉ ከጌታው ፊት ማስቀመጡ ነው:: በልቡ ወደ እርሱ ይመለከታል:: እንደሚከታተለው ይሰማዋል:: በጌታው ፍቅርና ልዕልና ሙሉ ልቦናው ተሞልቷል:: አላህን (ሱ.ወ.) የሚያየው ያህል ይሰማዋል:: የሸይጧን ውትወታዎችና ውልብታዎች በዚህ ልዩ የአምልኮት ስሜት ውስጥ ይጠፋሉ። በጌታውና በእርሱ መካከል ያለው ግርዶሽ ይነሳል:: የዚህ ዓይነቱ ሰው ሶላትና ፍፁም መዘናጋት ውስጥ ሆኖ የሚሰግድ ሰው ሶላት የሚበላለጡት የሰማይና የምድር ያህል ነው:: ምክንያቱም ይህ ሰው ሙሉ ሀሳቡ ጌታው ዘንድ የሆነና በሶላቱም ዐይኑ ያረፈ ሰው ነውና!
በዚሁ መነሻነት ስለ አምስቱ ሰዎች ሶላት እንዲህ ማለት ይቻላል)-
የመጀመሪያው ዓይነት ሰው ይቀጣል ሁለተኛው ይመረመራል ፤ ሶስተኛው ይቅር ይባላል፤ አራተኛው ይመነዳል፣ አምስተኛው ወደ ጌታው የተቃረበ ይሆናል::''
🔖ከእለታት አንድ ቀን ለኢማሙ ማሊክ፦
~እንዴት አደርክ ያ ኢማም?
ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም እንዲህ ብለው መለሱ፦ እድሜዬ እየቀነሰ ወንጀሌ እየጨመረ አደርኩ አሉ።
~
t.me/https_Asselfya🔖ኢማም ኢብኑ ኡሰይሚን "አላህ ይዘንላቸውና" እንዲህ ብለዋል።
~ የዶሮ ጩኸት የሰማ ሰው (اللهم إنا نسألك من فضلك) (አላህ ሆይ ከፈትሩፋትህ እንጠይቅሀለን) ይበል።
t.me/https_Asselfya
🔖
የሰዎችን ስራ የወደደ የውመልቂያማ ከነሱ ጋር ይቀሰቀሳል። የሉጥ ሚስት ሊዋጥን "ግብረ ሰዶማዊነት" ባትፈፅመውም ከሚፈፅሙት ሰዎች ጋር ስለነበረችና ስራቸውን ስለወደደች ከነሱ ጋር ትቀሰቀሳለች።
~ከኢብኑ ተይምያ ንግግር የተወሰደ*ንግስቶች* _እንጅ_ ማንም _የማይለብሰው_
እንቁዎች እንጅ ማንም የማይለብሰው
የምድር _ከዋክብቶች_ እንጅ ማንም የማይለብሰው
_የተመረጡ_ አላሁ ሱብሀነ ወተአላ ያደላቸው የወፈቃቸውጅ ማንም _የማይለብሰው_
ለጌታዋ ትእዛዝ እጅ እግር የሰጠች እንጅ ማንም የማይለብሰው
ብቻ አጠቃላይ እንቁዎች _ዳይመዶች_ እንጅ ማንም የማይለብሰው
*ኒቃብ* *ጅልባባችን* *በዱኒያ* *ከሀራም* *የመርከስ* *የምንጠበቅበት* *በጌታችን* *ፈቃድ*
*ስንሞትም* *ከፈናችን* *ኢንሻ* *አላህ*
*ከሰለፍያ ሴቶች መገናኛ የተወሰደች🎀*
በዚህ ዘመን እንደ ሐያእ ጥቃት የደረሰበት ነገር የለም። ሰዎች : ድርቅናቸውን : እፍረተ ቢስነታቸውን እንደ ንቃት የሚቆጥሩበት ዘመን ላይ ነው ያለነው።”
አርበዒን ሐዲሥ (14:9)
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
-
إِصبِر قَليلاً فبعد العُسرِ تَيسيرُ
وكُلُّ أَمرٍ لَهُ وَقتٌ وَتَدبيرُ..
