fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚

📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚

رفتن به کانال در Telegram

↘️በዚህ ቻናል የሚተላለፉት ↘️በሱና ኡስታዞች የተቀሩ ደርሶች ↘️የሱና ኡስታዞች ሙሀደራዎች ↘️በመቀጠል አስተማሪ ፁሁፎች ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/htt_asselfya

نمایش بیشتر
3 819
مشترکین
-524 ساعت
+1617 روز
+15530 روز
آرشیو پست ها
ماشاء الله تبارك الرحمن إيذاء تعرفين وتعرفون بعد ماتسبون ويخلصون الشتم واللعن والشتم ماشاء الله تبارك الرحمن بدأتم تعرفون أن إيذاء المسلم تستغلين وتستدلون بكلام العلماء الربانيين الكبار السلفيين مثل ابن باز رحمه الله تعالى وابن عثيمين بعد ماضربتم منهاجهم لأجل التقارب مع الإخونجي والحزبيين ولأجل حكومة الكافر المرتد حتى يدمركم تدميرا لأنه هو قال ( مدمر +) يدمركم تدميرا

ሚቅዳድ ኢብኑ አስወድ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት ሰሃቦች አንዱ ነው። ๏ እስልምናቸውን መጀመሪያ ግልፅ ካወጡትም አንዱ ነው። ๏ ወደ ሐበሻ ከተሰደዱት ሰሃቦች አንዱ ነው። ๏ ረሱል (ﷺ) ዘንድ በጣም ተወዳጅ ነበር። ⇨እንዲህም ብለው ነበር ስለሱ‥ ከአብደላህ ኢብኑ ቡረይዳህና እና ከአባቱ (ረ.ዐ) እንደተላለፈው ረሱል (ﷺ) እንዲህ አሉ‥ " አላህ (ሱ.ወ) 4 ሰዎችን በመውደድ አዞኛል እንደሚወዳቸውም ነግሮኛል ዐሊይ ፣ ሚቅዳድ ፣ አቡ ዘር እና ሰልማን " [ቲርሚዚይ እና ኢብኑ ማጃህ] ‥ ከእለታት አንድ ቀን ሚቅዳድ እና አብዱረህማን ኢብኑ ዐውፍ (ረ.ዐ) አንድ ላይ ቁጭ ብለው ነበርና አብዱረህማን እንዲህ አለው " ምንድነው አታገባም እንዴ?" ሚቅዳድም መልሶ " ልጅህን ዳረኛ " አለው አብዱረህማን በጣም ተናደደና ተቆጣው ሚቅዳድም ወደ ረሱል (ﷺ) በመሄድ ስሞታ አቀረበ ረሱልም (ﷺ) እኔ እድርሃለሁ አለውና የአጎቱን ልጅ ዱባዐህ ቢንት ዙበይር ኢብኑ አብዱልሙጠሊብን ዳረው‥ ๏ በአላህ መንገድ የመጀመሪያው ፈረሰኛ ነው። ๏ ጎበዝ ቀስት ወርዋሪና ጀግና ፈረሰኛ ነበር። እንዲህም ይል ነበር… " ኢስላም አሸናፊ ሆኖ እሞታለሁ " ๏ 70 አመት ሲሆነው ጀረፍ በሚባል ቦታ ህይወቱ አለፈች ወደ መዲናም ይዞት ተመጣ ዑስማን ኢብኑ ዐፋን (ረ.ዐ) ሰገዱበት በቂዕም ተቀበረ። ⇨አንድ ሩማዊ ልጅ ሆዱን ቀዶት ገደለውና አመለጠ ይባላል ልጁም በርሱ ስር ነበር የሚኖረው። . ⇨ትክክለኛው ስሙ ሚቅዳድ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ ሰዕለባህ ይባላል ነገር ግን ሚቅዳድ ኢብኑ አስወድ በሚለው መጠሪያ ነበር። በጣም የሚታወቀው አስወድ ኢብኑ አብዱየጉስ እንደልጁ አድርጎት ስለነበር ሚቅዳድ ኢብኑ አስወድ ተባለ። በዘር ሀረጉ ላይ ውዝግብ ነበር ቁዳአህ ከሚባል ጎሳ ነው ፣ ሀድረሚይ ነው ፣ ባህራኒም ነው ይባል ነበር። ከዛም እንዲህ የምትል አንቀፅ ወረደች‥ " ለአባቶቻቸው (በማስጠጋት) ጥሯቸው ፣ እርሱ አላህ ዘንድ ትክክለኛ ነው ፡፡ አባቶቻቸውንም ባታውቁ በሃይማኖት ወንድሞቻችሁና ዘመዶቻችሁ ናቸው ፣ በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ኀጢአት የለባችሁም ፣ ግን ልቦቻችሁ ዐውቀው በሠሩት (ኀጢአት አለባችሁ) አላህም መሓሪ አዛኝ ነው ፡፡" [አህዛብ 5] ከዚህም በኋላ ሚቅዳድ ኢብኑ ዐምር ተባለ። https://t.me/umufwzan/8411 https://t.me/umufwzan/8411

» ኸዲጃህ ቢንት. ኹወይሊዲ ๏ የረሱል (ﷺ) የመጀመሪያ ሚስት ናት በህይወት እያለች በሷ ላይ አላገቡም ነበር ለእርሱም 6 ልጆች ወለደችላቸው። ① ቃሲም ኢብኑ ሙሐመድ ② አብደላህ ኢብኑ ሙሐመድ ③ ዘይነብ ቢንት ሙሐመድ ④ ሩቀያህ ቢንት ሙሐመድ ⑤ ኡሙ ኩልሱም ቢንት ሙሐመድ እና ⑥ ፋጢማህ ቢንት ሙሐመድ ናቸው (ረ.ዐ) ⇨ከረሱል (ﷺ) በፊት 2ቴ አግብታ ነበር ይባላል። የመጀሪያ ባለቤቷ አቡ ሃለህ ኢብኑ ዙራረህ ይባላል።2 ልጆች ወልዳለት ነበር ሂንድ እና ሃለህ ይባላሉ። ሁለተኛው ባለቤቷ ዐቲቅ ኢብኑ ዓኢዝ ይባላል ብዙም አብረው ሳይቆዩ ሞተባት ከዛ በኋላ ነበር ረሱልን (ﷺ) ያገባቸው። እርሳቸው 25 አመታቸው ነበር እሷ ደግሞ 40 አመቷ ነበር። ๏ ከሴትም ከወንድም መጀመሪያ በአላህ እና በረሱል (ﷺ) ያመነችዋ ናት። ๏ መጀመሪያ ውዱእ ያደረገችዋ ናት ๏ መጀመሪያ ሰላት የሰገደችዋ እናም ረሱል (ﷺ) መጀመሪያ ያሰገዷት ናት። ๏ አላህ (ሱ.ወ) ሰላምታውን የላከላት ናት እና ጂብሪልም (ዐ.ሰ) ሰላምታውን የላከላት ናት ๏ በጀነት ከተበሰሩት ሰሃቦች አንዷ ናት ๏ የረሱል (ﷺ) ጋሻና መከታ የነበረችዋ ናት።ሲታመሙ ህመማቸውን የምታበርድላቸው ሲያዝኑና ሲከፉ ሀዘናቸውን አባርራ የምታስደስታቸው ማንም ሳያምናቸው ሲቀር ያመነቻቸው ሁሉም ሲያርቋቸው ያስጠጋቻቸውና ታፀናቸው የነበረችዋ ናት። ๏ እስልምናን በንብረቷና በሀይሏ ከፍ ያደረገችዋ ናት። ๏ የዚህ ዓለምም ሆነ የጀነት በላጯ ሴት ናት። ⇨ኢማሙ አህመድ ኢብኑ ሀንበል በሙስነዱ እንደዘገበው ∶ ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ እንዲህ አለ " ረሱል (ﷺ) መሬት ላይ 4 መስመሮች አሰመሩና ይህን ታውቃላችሁ? አሉ እነሱም አላህ እና መልእክተኛው ያወቁ ናቸው አሉ። " ከጀነት ሴቶች በላጮቹ ኸዲጃህ ቢንት ኹወይሊድ ፣ ፋጢማህ ቢንት ሙሐመድ ፣ አሲያህ የፊርዐውን ልጅ እና መርየም ቢንት ዒምራን ናቸው አሉ ።" ๏ ከረሱል (ﷺ) ጋር 25 አመት ኖራለች ๏ ዓኢሻህ በርሷ በጣሙን ትቀናባት ነበር ረሱል (ሰ.ዐ ወ) ከሞተች በኋላ በጣም የወሷት ነበር ዓኢሻህ ምንድነው ያ ረሱለላህ ሁሌም የምታወሷት አላህ ከሷ በበለጠች ተክቶልሃልኮ አለቻቸው።እርሳቸውም " አላህ ከሷ በበለጠ አልተካልኝም እሷኮ ሰው በኔ ሲከዳ በኔ ያመነችዋ ናት ፣ ሰው ሲዋሸኝ እሷ ያመነችኟ ናት ፣ ሰው ንብረታቸውን ሲከለክሉኝ የሰጠችኟ ናት ፣ ከሷም አላህ ልጅን ረዝቆኛል " አሉ ‥ ๏ ከሞተች በኋላም ፍቅሯን ይጠብቁላት ነበር ፊየል እንኳን ካረዱ አከፋፍለው ለኸዲጃህ ጓደኞች ይልኩ ነበር። ๏ አንድ ነገር ሲሰጣቸው የእከሌ ቤት ወሰዱት የኸዲጃህ ጓደኛ ነበረች የእከሌ ቤት ውሰዱት ኸዲጃህን ትወዳት ነበር ይሉ ነበር ‥ ⇨ሙሉ ስሟ ኸዲጃህ ቢንት ኹወይሊድ ኢብኑ አሰድ ኢብኑ አብዱል ዑዝ ትባላለች ๏ አሲዲቃህ (እውነተኛዋ) የሚል ስያሜ አላት ከሁሉም በፊት በአላህና በረሱልም (ﷺ) እናም ይዘው በመጡትም ስላመነች አሲዲቃህ ተባለች። ๏ በጃህሊያ ጊዜ አጣሂራህ (ንፁኋ) ትባል ነበር ይህን ስያሜ ያገኘችው በተከበረ ቤት እና በውብ ስነምግባር ስላደገች ነው‥ ⇨የእናቷ ስም ፋጢማህ ቢንት ዛኢዳህ ኢብኑል አሰም ኢብኑ ረዋሃ ትባላለች‥ https://t.me/umufwzan/8424 https://t.me/umufwzan/8424

ዘይነብ ቢንት ጃህሽ ๏ የረሱል (ﷺ) አክስት/አሚማህ ልጅ ናት። ๏ መጀመሪ አካባቢ ከሰለሙት ውስጥ ነ ๏ ከረሱል (ﷺ) ባለቤቶች አንዷ ናት። ⇨ማታ እንዳየነው ዘይነብ መጀመሪያ የዘይድ ኢብኑ ሀሪሳህ (ረ.ዐ) ባለቤት ነበረች ብለን ነበር ሂደቱን አብረን እንመልከተው… ወደ መዲና በስደት ከመጣች በኋላ ረሱል (ﷺ) ለዘይድ አጭቷት ነበር ፣ እሷም አይ እኔ የቁረይሽ ልጅ ሆኜ ለራሴ አልፈልገውም አለችና እንቢ አለች ። ረሱልም (ﷺ) እኔ ወደጄልሻለሁ አሏት ፣ አይ አለች ከዛም አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ የሚልን ወህይ አወረደ " አላህና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልፅ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ ፡፡"   [አህዛብ 36] ከዚህ በኋላ ዘይነብ እሺ ብላ አገባችው ። ወደ አመት አከባቢ አብረው ከኖሩ በኋላ በመካከላቸው ውዝግብ ተፈጠረ ፣ ከዛ ዘይድወደ ረሱል (ﷺ) በመምጣት ስሞታ አቀረበ ፣ ሊፈታትም እያስፈቀደ ነበር ፣ ረሱልም (ﷺ) አላህን ፍራ ባለቤትህን ያዝና ታገስ ብለው መከሩት ። ከዛም እንዲህ የሚል ወህይ ወረደ " ለእዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና (አንተም ነፃ በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው (ለዘይድ) አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህ ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ «ሚስትህን ባንተ ዘንድ ያዝ ፤ (ከመፍታት) አላህንም ፍራ» በምትል ጊዜ (አስታውስ) ። ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈፀመ ጊዜ በምእምናኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጉዋቸው (ሰዎች) ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈፀሙ ጊዜ (በማግባት) ችግር እንዳይኖርባቸው እርሷን አጋባንህ ፡፡ የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው ፡፡" [አህዛብ 37] ⇨ዘይድም ዘይነብን ከፈታት እና ዒዳዋን ከጨረሰች በኋላ አላህም ከ7 ሰማያት በላይ ዘይነብን ዳራት ። ሙናፊቆች " የልጆችን ሚስት ማግባት ሐራም አድርጎ እራሱ የልጁን ሚስት አገባ " በማለት ወሬ ሲያናፍሱ ነበር ። ማታ እና ስለ ሚቅዳድ ኢብኑ አስወድ (ረ.ዐ) ስንመለከት በሱረቱል አህዛብ አንቀፅ 5 ላይ ወህይ ወርዶ ሁሉም በአባቱ እንዲጠራ ተደርጎ ነበር አላህም በዛም መልስ ሰጣቸው ። ዘይድም በረሱል (ﷺ) ሳይሆን በአባቱ መጠራት ተጀምሮ ነበር አሁንም እንዲህ የሚል ወይህ ወረደ " ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም ፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው ፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው ፡፡" [አህዛብ 40] ⇨ዘይነብም ከረሱል (ﷺ) ጋር ሙሉ ህይወቷን በፍቅርና በኢማን አበሯቸው ኖረች ። በሌሎች ሚስቶቻቸውም ላይ እንዲህ እያለች ትኮራባቸው ነበር " እናንተን ቤተሰቦቻችሁ ናቸው የዳሯችሁ ፣ እኔን ግን አላህ ከ7 ሰማያት በላይ ነው የዳረኝ " ትል ነበር ๏ ዘይነብ ከሩሰል (ﷺ) ጋር 2 ዘመቻዎችን ኸይበር እና ጣኢፍ ወጥታ ነበር ፣ እንዲሁም ሀጀተል ወዳዕ ላይም አብራው ነበረች ። ๏ ረሱል (ﷺ) ከሞቱ በኃላ እሷም እስከ ዑመር ኺላፋ ጊዜ ቆይታ እድሜዋ 53 ሲሆን ከዚህ አለም ወጣች ። ኸሊፋው ዑመር (ረ.ዐ) ሰግደውባት በቂዕም ተቀበረች ። ๏ ከረሱል (ﷺ) በኋላ ከባለቤቶቻቸው መጀመሪያ የሞተችው እሷ ነበረች‥
⇨ሙሉ ስሟ
ዘይነብ ቢንት ጃህሽ ኢብኑ ሪያብ ኢብኑ ያዕመር ትባላለች ๏ መጀመሪያ ስሟ በራህ ይባል ነበር ረሱል (ﷺ) ነው ዘይነብ ብለው ያወጡላት። ๏ ኡሙል ሀከም የሚል ስያሜም አላት።
⇨የእናቷ ስም
አሚማህ ቢንት አብዱልሙጠሊብ ትባላለች የረሱል (ﷺ) አክስት ናት ። https://t.me/umufwzan/8434 https://t.me/umufwzan/8434

عشرة أسئلة للدكتور محمد عبدالغفار الشريف افتنا وافدنا | لفضيلة الشيخ #سالم_الطويل 🔸تحميل المقطع 🔸 https://t.me/Saltaweel/5617 🔻5:42⏱️🔻 https://youtu.be/HK1-OBWyDcU?feature=shared

ለሚመለከተው ሁሉ! ~ የአሕ'ባሽ ቡድን ሙስሊሙን ወደ ሙታን አምልኮ የሚወስድ፣ "ቁርኣን የአላህ ንግግር አይደለም" የሚል፣ የአላህን መገለጫዎች (ሲፋት) የሚክድ፣ ከጠላት ጋር በመተባበር ሙስሊሞችን የሚያስመታ፣ በጥመቱ የማይጋሩትን ሙስሊሞች ነፍስ ለማጥፋት፣ መስጂድ ለማቃጠል የማያመነታ፣ "አላህ በ0ርሹ ላይ ነው" ብለው የሚያምኑ ከሰለፎች ጀምሮ ዛሬ ድረስ ያሉ ሙስሊሞችን ከተራ እስከ ታላላቅ ዓሊሞች ድረስ በጅምላ ከኢስላም የወጡ ከሃዲዎች ናቸው ብሎ ለማወጅ አይኑን የማያሽ፣ ከሙስሊሞች ይልቅ አይሁድና ነሷራ ይሻለናል የሚል፣ ... የጥፋት ጎተራ፣ የሙስሊሞች የህልውና ስጋት ነው። ቡድኑ ለዚህ ብልሹ እምነቱ ብዙ ርቀት መሄድ ይችላል። በወቅታዊ የመጅሊስ ሁኔታ ካኮረፉ አካላት ውስጥ ከፊሎቹ ጠመንጃ አንስተው ከሚፋለሙ ቡድኖች ጋር እስከሚቀላቀሉ መድረሳቸው ለዚህ አንድ ማሳያ መሆን ይችላል። ከትክክለኛው የኢስላም ጎዳና ያፈነገጠ መሆኑን የሚያውቁ የኢስላም ጠላቶችም "ነባሩ እስልምና" የሚል ሃሰተኛ ውዳሴ እየሰፈሩ ከጎኑ ሲቆሙ ማየት የተለመደ ነው። በሌላ በኩል ግን ይህንን መርዝ ነቅሎ ለመጣል ይሄ ነው የሚባል በቂ እና ትርጉም ያለው ስራ እየተሰራ አይደለም። በየተዋረዱ ያሉ የመጅሊስ አመራርም፣ በያካባቢው ያሉ ዱዓቶችም፣ የመስጂድ ኮሚቴዎችም፣ ባለ ሃብቶችም፣ "ያገባኛል" የሚሉ ሙስሊሞች ባጠቃላይ አካባቢያቸውን ብሎም ሃገሪቱን ከዚህ መርዝ ለማፅዳት ያላሰለሰ ጥረት ሊያደርጉ ይገባል። እውነት ለመናገር ከዚህ በላይ ለኢትዮጵያ ሙስሊም የሚዋል ውለታ የለም። የመጅሊስ አመራር ትላንትም ዛሬም የፖለቲካውን ንፋስ የመከተል አዝማሚያ አለው። የንፋሱ አቅጣጫ የተቀየረ እለት ነገም እንደ ትላንቱ አሕባሽን ማንገስ ሊመጣ ይችላል፣ አላህ አያድርገውና። ሁነኛው መድሃኒት ያለውን አንፃራዊ በጎ ሁኔታ በመጠቀም የጀርባ ደጀን የሚሆናቸው ህዝብ እንዳይኖር በያቅጣጫው አጥብቆ የማንቃት ስራ መስራት ነው፣ ማስተማር። ሙስሊሞች ዐቂዳቸውን በውል እንዲለዩ ጠንካራ ስራ መስራት ያስፈልጋል። እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ሙስሊሞችን በማክ^ፈር፣ የሺርክ መርዝ በመርጨት ላይ የተጠመዱ የሚታወቁ ቦታዎች እንዳሉ ግልፅ ነው። በመጅሊስ በኩል በዚህ ጉዳይ ላይ ቀላል የማይባሉ የተሰሩ ስራዎች አሉ። ሆኖም ግን ዋናዎቹ ዛሬም ድረስ አልተነኩም። ዛሬም ልጆችን እየመለመሉ ለአመታት እያሰለጠኑ ወደ ክፍለ ሀገር በመላክ ክፋታቸውን ማሰራጨቱን ተያይዘውታል። በሌላ በኩል ያለው ማንቀላፋት ግን እስከ ማንኮራፋት ደርሷል። ስለዚህ እነዚህን መርዞች በመንቀል ላይ ሰፊ ርብርብ ያስፈልጋልና ለወገን የሚቆረቆር ሁሉ በጊዚ የድርሻውን ቢወጣ መልካም ነው። Ibnu Munewor = * የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor * የዋትሳፕ ቻናል፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M * ፌስቡክ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL

ጥንቃቄ ~ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ብዙ ወጣት ሴቶች በሚዝናኑባቸው ቦታዎች ትላልቅ ከተማዎች ላይ GHB የሚባል ኬሚካል ተበራክቷል። "ጋባዦች" አንድ መጠጥ ውስጥ የGHB ጠብታ ሲጨምሩበት ተጠቂዎች (አብዛኛውን ጊዜ ሴቶች) በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ያሉበት፣ አብረዋቸው የነበሩበትን እና የተወሰዱበትን ቦታ አያስታውሱም። ገንዘብ ተከፍሏቸው የደነዘዙ ሴቶችን ለማስደፈር የሚያቀርቡ ውጣት ወንዶችም ሴቶችም ይሄንን እየሰሩ የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው። በተለይ "የቤት ልጅ" አይነት የሚባሉ (ተማሪዎች) እና ሌሎች ወጣት ሴቶች የዚህ ወንጀል ተጠቂ እየሆኑ ነው። GHB ከሰውነታቸው ወጥቶ ሲነቁ በማይታወቅ ቦታ ብዙ ጉዳት ደርሶባቸው ራሳቸውን ያገኛሉ። ምን እንደተፈጠረ አያውቁም። GHB የሰው ሕይወት ሊያጠፋ ይችላል። በከተሞች መዝናናት እና መገባበዝ ደግሞ የተለመደ ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። እንዲህ አይነት ወንጀሎች በቅርብ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ውጪ ከኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው። ኮፒ "ሼር" ቢደረግ ለወገን ይጠቅማል። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

ኢብኑ ዑሠይሚን - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ:- "ሚስትህ ጥፋት ብትፈፅምብህ የዛሬውን ጥፋት ብቻ አትመልከት። ወደኋላም ተመልከት። ወደፊትም ተመልከት። ከዚያም በፍትህ ፍረድ።" [ሸርሑ ሪያዲ ሷሊሒን፡ 2/73] ሚስትም የባሏን ጥፋት እንዲሁ ትመልከት። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

Repost from .
✏️ሱናን ያውቁ የነበሩ ሠዎች ነገር አለሙ ጠፍቶባቸው ሲዋልሉና ሲቧጭሩ ከተመለከትክ!! 〰〰 قال شيخُ الإسلام ابن تيمية -رحمهُ الله- : مَن أعرض عن اتِّباع الحقّ الذي يعلمه تبعاً لِهواهُ فإنَّ ذلِك يورثهُ الجهل والضَّلال حتى يعمى قلبهُ عن الحقّ الواضِح". مجموع الفتاوى (١٠/١٠). አላህ ይዘንላቸውና ሸይኸል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ብለዋል፦ ፍላጎቱን (ሥሜቱን) ተከትሎ የሚያውቀውን ሀቅ ከመከተል የሸሸ (ያፈነገጠ) ሰው ግልፅ ከሆነው እውነት ልቡ እስኪታወር ድረስ (መሀይምነትን) ድንቁርናን እና ጥመትን ያወርሰዋል። መጅሙዑል ፈታዋ: 10/10 وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا «ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች!» [ ሱረቱ አል-ኒሳእ - 115 t.me/Abdurhman_oumer t.me/Abdurhman_oumer

የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች! ክፍል - 1 ~ ወንድማችን ሳዳት ከማል የነዚህን ከራሳቸው ጋር እንኳ የማይግባቡ ጉዶች የተሳከረ አካሄድ ሲነቅፍ ጊዜ "በጀርሕ እና ተዕዲል ዒልም ላይ ተሳለቀ" ብለው ላንቃቸው እስኪበጠስ ሲጮሁ ነበር። የተቸው የነሱን ቅጣንባሩ የጠፋው አካሄድ እንደሆነ ጠፍቷቸው አይደለም። ሆነ ብለው ጩኸታቸው እንዲደምቅላቸው እና ቂላቂሎችን ለመጥለፍ አላማ ነው በዚያ መልኩ ያቀረቡት። ይሄው የራሳቸው ሰው በነብዩ ﷺ ሐዲሥ ላይ ሲሳለቅ ስሙት። (ሂሳቡ የራሳችሁ ነው።) ደግሞ አያፍሩም ይስቁለታል! = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

+1
ኢስቲቅባሉ ሸህሪ ረመዷን ክፍል 7 🌸በኡስታዝ ኸድር አህመድ ሀፊዘሁሏህ🌸 https://t.me/menhagsalef

+2
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ከሺርክ ለመዳን ሁነኛ ነጥቦች t.me/NABAWITUBE

ይህ አድሱ ቻናላችን ነው ግቡ ቻናል ቢፈርስ ቻናል ይከፈታል አትታለል ኢሊያስ ሀቅ አይደበቅም ቢመርህም ዋጠው ባንተ ምክናየት ቻናል ሲፈርስ ግን ሊያምህ ይገባል https://t.me/+ZKXkcQYiRdcyMDFk

https://t.me/+ZKXkcQYiRdcyMDFk ይህ አድሱ ቻናላችን ነው ግቡ ቻናል ቢፈርስ ቻናል ይከፈታል አትታለል ኢሊያስ ሀቅ አይደበቅም ቢመርህም ዋጠው ባንተ ምክናየት ቻናል ሲፈርስ ግን ሊያምህ ይገባል

https://t.me/+ZKXkcQYiRdcyMDFk ይህ አድሱ ቻናላችን ነው ግቡ ቻናል ቢፈርስ ቻናል ይከፈታል አትታለል ኢሊያስ ሀቅ አይደበቅም ቢመርህም ዋጠው