Kaffa Zone Education Department Exam administration
رفتن به کانال در Telegram
For purpose of exam administration & current information exchange.
نمایش بیشتر2 167
مشترکین
+624 ساعت
+317 روز
+12130 روز
آرشیو پست ها
Repost from Ministry of Education Ethiopia
ማስታወቂያ
በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7/ 2019 ዓ.ም. እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም እራሳችሁ እንድትሞሉ እንገልጻለን።
የማስፈንጠሪያ ሊንክ (Link): https://student.ethernet.edu.et/preferences
ውድ የወረዳ ፈተና አስተዳደር ቡድን መሪዎች/ባለሙያዎች ሰላማችሁ ይብዛ እያልኩ 🤝🤝🤝
#የሪሚዲያል #ውጤት በተጠየቀው መሠረት በት/ቤትና በስትሪም ለይተው የላኩልን #ደካ፣ #ቢጣ፣ #ቦንጋ፣ #ጨና፣ ሺሺንዳና #ዋቻ ናቸው። እናመሠግናለን 🙏
👉ነገር ግን በወረዳ ጥቅል አድርጎ መላክ #አዲዮ፣ #ሳይለም፣ #ጌሻና #ገዋታ መረጃውን እንደገና በተገለጸው መሠረት ተደራጅተው እንዲመጣ እንጠይቃለን !
👉በስትሪም ለይቶ ያለመላክ #ጊምቦ እንደገና ተደራጅተው እንዲመጣ እንጨይቃለን!
👉ጭራሽ ምንም መረጃ ያልላኩ ወረዳዎች #ጨታ፣ #ዴቻ፣ #ጎባ፣ #ጠሎ፣ #አውራዳ፣ ሺሾእንዴ ናቸው።
ስለሆነም ማስተካከያ የተባላችሁና ምንም መረጃ ያልላካችሁ ነገ ቀን 7/01/2019 ዓ.ም እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ አድርሱን!
ካፋ ዞን ትም/መምሪያ ፈተናዎች አስተዳደር
ማስታወቂያ
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይመለከታል
በትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ሂደትን አጠናቋል።
ምደባው ፍትሐዊነትን፣ ግልጽነትን፣ እኩል ዕድልን እና ሚዛናዊ ስርጭትን በሚያረጋግጥ መልኩ፣ የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም እንዲሁም ሌሎች የምደባ መስፈርቶችን ታሳቢ በማድረግ ተከናውኗል።
1. የምደባው ዋና መስፈርቶች
1.1. የተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ
የተማሪዎች አጠቃላይ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የምደባው ዋና የቅደም ተከተል መስፈርት ሆኖ ተወስዷል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በምርጫቸው መሠረት የመመደብ ቅድሚያ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በተቻለ መጠን ከመረጧቸው የመጀመሪያ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።
1.2. የዩኒቨርስቲዎች የተማሪ ቅበላ አቅም
የእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ የተማሪ ቅበላ አቅም በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። በመሆኑም የተማሪው ውጤትና ምርጫ ከዩኒቨርስቲዎች የቅበላ አቅም ጋር በማጣጣም ምደባው ተከናውኗል።
1.3. የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት
በዩኒቨርሲቲዎቻችን ህብረ ብሄራዊነትን የሚያጸና እና የተማሪዎችን ሚዛናዊ ስርጭት ለማረጋገጥ፦
• 70 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ፤
• 30 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ በተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል። በተጨማሪም የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል።
1.4. የፆታ ሚዛን
በዩኒቨርሲቲዎች የሴትና የወንድ ተማሪዎች ስብጥር ሚዛናዊ እንዲሆን በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል።
2. ልዩ ምደባ
2.1. ማየት እና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች
ማየት እና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርትና የድጋፍ አገልግሎት ሊያገኙ በሚችሉባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።
2.2. 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች
በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ አጠቃላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ላስመዘገቡት የላቀ የአካዳሚክ ውጤት ልዩ ታሳቢነት በመስጠት፣ በመጀመሪያ ምርጫቸው ተመድበዋል።
ይህ ልዩ የምደባ አሠራር ተማሪዎቹ በብሔራዊ ፈተናው ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት ዕውቅና ለመስጠት እና ከፍተኛ አፈጻጸምን ለማበረታታት የተደረገ ነው።
3. የምደባ ውጤትን ስለመመልከት
ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት በመጠቀም ማየት ይችላሉ።
የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/view-placement
4. ቅሬታ ስለማቅረብ
በምደባው ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት ብቻ ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማያያዝ እንዲያቀርቡ እናሳስባለን።
የቅሬታ ማቅረቢያ ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints
• በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በመምጣት የሚቀርብ የምደባ ቅሬታ የማይስተናገድ መሆኑን ተማሪዎችና ወላጆች እንዲገነዘቡ እናሳውቃለን።
5. ማሳሰቢያ
ቅሬታ በሚቀርብበት ወቅት የሐሰት መረጃ፣ የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ ነው። በቅሬታ ሂደት የሚቀርቡ መረጃዎችና ሰነዶች ትክክለኛነት የሚረጋገጥ ሲሆን፣ የሐሰት መረጃ ወይም ሰነድ አቅርበው የተገኙ ተማሪዎች ምደባቸው ሊሰረዝ ይችላል።
በመሆኑም ሁሉም ተማሪዎች ቅሬታቸውን በእውነተኛና በተረጋገጠ መረጃ ላይ ብቻ በመመሥረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲያቀርቡ እናሳስባለን።
የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ፣ በቀጣዩ የከፍተኛ ትምህርት ጉዟችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
የትምህርት ሚኒስቴር
ውድ የወረዳ ፈተና አስተዳደር ቡድን መሪዎች/ባለሙያዎች ሰላማችሁ ይብዛ እያልኩ 🤝🤝🤝
#የሪሚዲያል #ውጤት በተጠየቀው መሠረት በት/ቤትና በስትሪም ለይተው የላኩልን #ደካ፣ #ቢጣ፣ #ቦንጋ፣ #ጨና፣ ሺሺንዳና #ዋቻ ናቸው። እናመሠግናለን 🙏
👉ነገር ግን በወረዳ ጥቅል አድርጎ መላክ #አዲዮ፣ ሳይለም፣ #ጌሻና #ገዋታ መረጃውን እንደገና በተገለጸው መሠረት ተደራጅተው እንዲመጣ እንጠይቃለን !
👉በስትሪም ለይቶ ያለመላክ #ጊምቦ እንደገና ተደራጅተው እንዲመጣ እንጨይቃለን!
👉ጭራሽ ምንም መረጃ ያልላኩ ወረዳዎች #ጨታ፣ #ዴቻ፣ #ጎባ፣ #ጠሎ፣ #አውራዳ፣ ሺሾእንዴ ናቸው።
ስለሆነም ማስተካከያ የተባላችሁና ምንም መረጃ ያልላካችሁ ነገ ቀን 7/01/2019 ዓ.ም እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ አድርሱን!
ካፋ ዞን ትም/መምሪያ ፈተናዎች አስተዳደር
ሠላም እንዴት ናችሁ ? እንኳን ለ2019 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ማስጀመሪያ ቀን አደረሳችሁ 😍🥰
የወረዳ/ከተማ አስ/ር ጽ/ቤት የፈተና አስተዳደር ቡድን/ባለሙያዎች የ12ኛ ክፍል የሪሚዲያል መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በት/ቤት፣ በስትሪምና በፆታ በመለየት ዛሬ እስከ 11 ሰዓት በአቶ #ጌታሁን ወይም #አባተ በግል ቴሌግራም አካውንታችን እንዲትልኩልን እንጠይቃለን !
መልካም የሥራ ውሎ!
ካፋ ዞን ትም/መምሪያ ፈተናዎች አስተዳደር
መላው የዚህ ቴሌግራም ገጽ የትምህርት ቤተሰብ አባላት በሙሉ እንኳን ለ2019 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ ! ዓመቱ የሠላም፣ የጤናና የስኬት እንዲሆንልን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ !
ሰላም እንዴት አደራችሁ 🤝?
የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ማሳያ ሮስቴር ሶፊት ኮፒ የወረዳ ፈተና አስተዳደር ባለሙያዎች ጋር ስለተላከ ት/ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ ሮስቴሩን በመውሰድ ምዝገባ ማካሄድ ትችላላችሁ ! የተማሪዎች ውጤትላይ ቅሬታ ካለ እስከ ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም እስከ 11 ሰዓት ድረስ በወረዳ ትም/ጽ/ቤት በህጋዊ ደብዳቤ መላክ ትችላላችሁ !
ካፋ ዞን ትም/መምሪያ ፈተናዎች አስተዳደር
Repost from Ministry of Education Ethiopia
ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ።
ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት በሚሰጥባቸው ነባርና አዲስ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን አወዳድሮ ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ተመዝግባችሁ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁና ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች በተመዘገባችሁበት ሊንክ መለያ ኮዳችሁን ( Reference Number) በማስገባት ማየት የምትችሉ መሆኑ እንገልጻለን።
በተጨማሪም ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች ፈተና የሚሰጠው በበየነ መረብ (online) ስለሆነ የሚቀርባችሁን የፈተና መስጫ ማዕከል በዛው ሊንክ በመግባት መምረጥ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የሙከራ ፈተና እሮብ ነሃሴ 27/2018 የሚሰጥ ሲሆን ዋና ፈተናው ነሃሴ 28 የሚሰጥ መሆኑ አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን።
#የ12ኛ ክፍል ውጤት እንደ ዞናችን #9.11% ተማሪዎች የዩንቨርስቲ መግቢያ ውጤት አስመዝግቧል ።
ሠላም እንዴት አደራችሁ እያልኩ ትናንት በተቀጣጠርነው መሠረት ለዚህ ቴሌግራም ግሩፕ የ12ኛ ክፍል አጠቃላይ ትነተና እንገልፃለን ባልነው መሠረት እንደ ካፋ ዞን #በተፈጥሮ ሳይንስ የተፈተነ ተማሪ ወ=123 ሴ=79 ድምር 202 (10.07%)
#ማህበራዊ ሳይንስ ወ=55 ሴ=38 ድምር 93 (7.5%)
#በጠቅላላ ወ=178 ሴ=117 ድምር 295 (9.11%) የዩንቨርስቲ መግቢያ ውጤት አስመዝግቧል ። ከ2017 ዓ.ም ከተመዘገበው ውጤት አንፃር የ4% ጭማሪ አሳይቷል።
በት/ቤት ደረጃ በማስገባት ምጣኔ
#በተፈጥሮ ሳይንስ ትም/ዘርፍ
👉ጊምቦ 88.57%
👉ግ/ጳውሎስ 59.38%
👉ውሽውሽ 47.83
👉ቢሻው ወ/ዮሀንስ 44.97% አስመዝግቧል
#በማህበራዊ ሳይንስ ትም/ዘርፍ
👉ውሽውሽ 68.4%
👉ጊምቦ 33.8% ተመዝግቧል
#ምንም ያላስገቡ ት/ቤቶች ብዛት
እንደዞናችን 34 ሲሆኑ ምንም ያላስገቡ ወረዳዎች #ጨና፣ #ጨታ፣ #ዴቻና #ሺሾእንዴ ናቸው።
ካፋ ዞን ትም/መምሪያ ፈተናዎች አስተዳደር
እንዴት አመሻችሁ ?
የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መልቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና ከምንም በላይ ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ የትምህርት ቆይታ ዓመታት ሲቆጠር ወደ 15 ነው። ስለዚህ የ15 የልጆቻችሁ ውጤት ማየት በላይ ምን የሚያኮራ ነገር አለ? ደግሞም ምንም ውጤት ባይመዘግ እንኳን ለቀጣይ ዓመት ብዙ መሥራት እንዳለብን የቤት ሥራ መሆኑን እያሳየ ስለሆነ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ የትም/ባለሙያዎችና የወረዳ መንግስታት ልትበረቱ ይገባል! አጠቃላ ዞናዊ ውጤት ነገ የሚገለፅ ይሆናል!
መልካም አዳር!
ካፋ ዞን ትም/መምሪያ ፈተናዎች አስተዳደር
ሰላም እንዴት ዋላችሁ🤝?
የ12ኛ ውጤት ከ50%ና በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎችን መረጃ የላኩ ወረዳዎች ቦንጋ፣ ገዋታ፣ ጌሻና ቢጣ ናቸው። ለእነዚህ ወረዳዎች ምስጋናዬ ላቅ ያለ መሆኑን እየገለፅኩ ቀሪዎቹ መረጃው በሰዓቱ ባለማድረሳች ለሚመለከተው ሪፖርት ለማድረግ ተቸግረናል ። እባካችሁ የዞን ደጋፊ ባለሙያዎችና የወረዳ ፈተና አስተዳደር ባለሙያዎች ለጉዳዩ ትኩረት ስጡትና ዛሬ እስከ 11:30 ድረስ ይደረሰን። እንደ ወረዳ ያስመዘገ ተማሪ ከሌለ የለም ብላችሁ መረጃ ስጡን!
ካፋ ዞን ትም/መምሪያ ፈተናዎች አስተዳደር
ሰላም እንዴት አደራችሁ 🤝?
የ12ኛ ክፍል ውጤት እላይ በተለጠፈው ሊንክ ማየት የሚቻል መሆኑን እየገለፅን ከ50%ና በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎችን መረጃ በት/ቤት፣ በስትሪምና በፆታ በማደራጀት በቴሌግራም ግል አካውንታችን 0966103308፣ 0910942473 ላይ ዛሬ በስራ ሰዓት እስከ 11:30 ድረስ እንዲትልኩልን እንጠይቃለን ።
ካፋ ዞን ትም/መምሪያ ፈተናዎች አስተዳደር
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።
የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። ተፈታኞችም ውጤታቸው ማየት ጀምረዋል።
ውጤት ለማየት ፦
👉 በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
👉 ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
👉 አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
በአንድ ጊዜ በርካታ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ስለሚሞክሩ የኔትዎርክ መጨናነቅ ሊያጋጥም ስለሚችል ደጋግሞ መሞከር ይገባል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ምላሹንም በዛው ማስፈንጠሪያ መከታተል እንደሚችሉ ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
ሰላም እንዴት ቆያችሁ🤝?
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት ስለተለቀቀ በበይነመረብ ማየት የሚቻል መሆኑን እየገለፅኩ result.eaes.et ገብቶ ማየት ይቻላል።
የወረዳ ፈተና አስተዳደር ባለሙያዎች መረጃው በየት/ቤት፣ በስትሪምና በፆታ በማደራጀት እስከ ነገ 19/12/2018 ዓ.ም ጥዋት 4 ሰዓት ለዞን ፈተና አስተዳደር እንዲታደርሱ እንጠይቃለን!
ካፋ ዞን ትም/መምሪያ ፈተናዎች አስተዳደር
ሰላም እንዴት ዋላችሁ ?🤝
👉የ2ኛ መንፈቀ ዓመት የተማሪዎች ውጤት ትንተና ያልላኩ ወረዳዎች #አውራዳ ፣ #ቦንጋ ፣ #ጨና ፣ #ዴቻ ፣ #ሳይለም ፣ #ሺሺንዳ ፣ #ሺሾእንዴና ዋቻ ናቸው።
👉የ6ኛ ክፍል ሮስቴር ያልላኩ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች #አውራዳ #ቦንጋ #ጊምቦ #ጎባ #ሳይለም #ሺሾእንዴና #ጠሎ ናቸው። እባካችሁ የወረዳ ፈተና አስተዳደሮችና ትም/ጽ/ቤት ኃላፊዎች ውጤት ትንተናውን ለሚመለከተው ክፍል ለማድረስና ሮስቴርን በጊዜ አጠናቀን ውጤት በእናንተ ምክንያት ስለታሰርን ጊዜ የማይባል ጉዳይ ስለሆነ ዛሬ ማታ አጠናቃለችሁ እንዲትልኩን እንጠይቃለን !
ካፋ ዞን ትም/መምሪያ ፈተናዎች አስተዳደር
ሰላም እንዴት ቆያችሁ?🤝
የ6ኛ ሮስቴርና የ2ኛ ሴሚስቴር ውጤት ትንተና ያልላካችሁ ወረዳዎች ዛሬ እስከ 8 ሰዓት ድረስ አድርሱን!
መልካም የመኝታ ሰዓት!
ሰላም እንዴት ቆያችሁ?🤝
እነሆ የ12ኛ ክፍል 1 ብለን ጀምረን የ5ኛ ዙር ፈተና አጠናቀን የ6ኛና የመጨረሻው ዙር ለማስጀመር የሰዓታት ዕድሜ ብቻ ቀርቷል። ስለዚህ ለዚህ ሁሉ ስኬት ከላይ እስከ ለተሳተፋችሁ ሁላችሁንም በዞኑ ፈተና አስተዳደር ስም ከልብ እያመሰገንን ከዚህ ፈተና ጉዳይ ጋር የተያያዘ ቀሪ ስራዎች
#1ኛ በየወረዳችሁ በየት/ቤቱና በምዝገባ ሞዳሊቲዎች የተመዘገቡና የተፈተኑ ተማሪዎችን ማደራጀት፥
#2ኛ የትንስፖርት መረጃን በነጠላ የጫኑትንና ደርሶ-መልስ የጫኑት መለየትና ዞን የተዛባ መረጃ ካለ ለትራንስፖርት ወጭ ክፍያ ለመፈጸም ስለሚያስቸግር ከወዲሁ በእጃሁ ያለው ቀሪ መረጃ አደራጅታችሁ ስትጠየቁ መስጠትና
#3ኛ ዞን ላይ ለዶክመንት ማጣራት የመጡትን የተመዝጋቢዎች የትምህርት መረጃቸውን መውሰድና ማረካከብ ትላልቅ ስራዎች ስለሚጠበቅባችሁ ሁሉም ከነገ ጀምሮ አደራጅታችሁ ለዞን ሪፖርት አድርጉ!
#ሌላውን በውስጥ መስመር እናወራለን!
መልካም አዳር!
ካፋ ዞን ትም/መምሪያ ፈተናዎች አስተዳደር
